ሱራ Ali 'Imran 3:183
ٱلَّذِينَ قَالُوٓاْ إِنَّ ٱللَّهَ عَهِدَ إِلَيۡنَآ أَلَّا نُؤۡمِنَ لِرَسُولٍ حَتَّىٰ يَأۡتِيَنَا بِقُرۡبَانٖ تَأۡكُلُهُ ٱلنَّارُۗ قُلۡ قَدۡ جَآءَكُمۡ رُسُلٞ مِّن قَبۡلِي بِٱلۡبَيِّنَٰتِ وَبِٱلَّذِي قُلۡتُمۡ فَلِمَ قَتَلۡتُمُوهُمۡ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ ﴿١٨٣﴾
◉
ትርጉም
183. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ይህን ቃል የተናገሩት: «ለማንኛዉም መልዕክተኛ እሳት የምትበላው ቁርባን እስከሚያመጣልን ድረስ በሱ እንዳናምን አላህ ወደ እኛ አዝዟል።» ያሉ ናቸው:: «ብዙ መልዕክተኞች ከእኔ በፊት በግልጽ ተዓምራትና በዚያ ባላችሁት ቁርባን በእርግጥ መጥተውላችኋል:: እውነተኞች ከሆናችሁ ታዲያ ለምን ገደላቸኃቸው?» በላቸው::
እነዚያ ለማንኛውም መልክተኛ «እሳት የምትበላው የኾነን ቁርባን እስከሚያመጣልን ድረስ ላናምን አላህ ወደኛ አዟል» ያሉ ናቸው፡፡«መልክተኞች ከእኔ በፊት በተዓምራትና በዚያም ባላችሁት (ቁርባን) በእርግጥ መጥተውላችኋል፡፡ እውነተኞች ከኾናችሁ ታዲያ ለምን ገደላችኋቸው» በላቸው፡፡