quranm◉

ገጽ 334

Range
from 22:16 to 22:23
Surahs covered
ትርጉም
8 ትርጉም

◉

22:16

وَكَذَٰلِكَ أَنزَلۡنَٰهُ ءَايَٰتِۭ بَيِّنَٰتٖ وَأَنَّ ٱللَّهَ يَهۡدِي مَن يُرِيدُ ﴿16﴾

16. ልክ እንደዚሁ (ቁርኣንን) የተብራሩ አናቅጽ አድርገን አወረድነው:: አላህ የሚሻውን ሁሉ ይመራልና።

22:17

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَٱلَّذِينَ هَادُواْ وَٱلصَّـٰبِـِٔينَ وَٱلنَّصَٰرَىٰ وَٱلۡمَجُوسَ وَٱلَّذِينَ أَشۡرَكُوٓاْ إِنَّ ٱللَّهَ يَفۡصِلُ بَيۡنَهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ شَهِيدٌ ﴿17﴾

17. እነዚያ በአላህ ያመኑ እነዚያ አይሁዳውያን፤ እነዚያ ምንም እምነት የሌላቸው ሳቢያኖች፤ ክርስቲያኖችም፤ መጁሶችም እነዚያም (ጣዖታትን በአላህ) ያጋሩ ሁሉ አላህ በትንሳኤ ቀን በመካከላቸው በፍርድ ይለያል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ በእርግጥ አዋቂ ነውና::

22:18

أَلَمۡ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ يَسۡجُدُۤ لَهُۥۤ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَن فِي ٱلۡأَرۡضِ وَٱلشَّمۡسُ وَٱلۡقَمَرُ وَٱلنُّجُومُ وَٱلۡجِبَالُ وَٱلشَّجَرُ وَٱلدَّوَآبُّ وَكَثِيرٞ مِّنَ ٱلنَّاسِۖ وَكَثِيرٌ حَقَّ عَلَيۡهِ ٱلۡعَذَابُۗ وَمَن يُهِنِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِن مُّكۡرِمٍۚ إِنَّ ٱللَّهَ يَفۡعَلُ مَا يَشَآءُ۩ ﴿18﴾

18. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ጸሐይና፤ ጨረቃም፤ ከዋክብትም፤ ተራሮችም፤ ዛፎችም፤ ተንቀሳቃሾችም ፍጡራንና ከሰዎች ብዙዎችም ለእርሱ የሚሰግዱለት መሆኑን አታውቅምን? ብዙዉም በእርሱ ላይ የአላህ ቅጣት ተረጋገጠበት:: አላህ የሚያዋርደው ሰው ለእርሱ ምንም አክባሪ የለዉም:: አላህ የሻውን ይሰራልና:: {1}

22:19

هَٰذَانِ خَصۡمَانِ ٱخۡتَصَمُواْ فِي رَبِّهِمۡۖ فَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ قُطِّعَتۡ لَهُمۡ ثِيَابٞ مِّن نَّارٖ يُصَبُّ مِن فَوۡقِ رُءُوسِهِمُ ٱلۡحَمِيمُ ﴿19﴾

19. እነዚህ በጌታቸው ጉዳይ የተከራከሩ ሁለት ባላጋራዎች ናቸው:: እነዚያ በአላህ የካዱት የእሳት ልብሶች ተለክተውላቸዋል፤ እንዲቀልጥ ከራሶቻቸው ላይ የፈላ ውሃ ይምቧቧባቸዋል።

22:20

يُصۡهَرُ بِهِۦ مَا فِي بُطُونِهِمۡ وَٱلۡجُلُودُ ﴿20﴾

20. በሆዶቻቸው ውስጥ ያለውና ቆዳዎቻቸው በእርሱ ይቀለጣል::

22:21

وَلَهُم مَّقَٰمِعُ مِنۡ حَدِيدٖ ﴿21﴾

21. ለእነርሱም (መቅጫ) ከብረት የሆኑ መዶሻዎች አሉ::

22:22

كُلَّمَآ أَرَادُوٓاْ أَن يَخۡرُجُواْ مِنۡهَا مِنۡ غَمٍّ أُعِيدُواْ فِيهَا وَذُوقُواْ عَذَابَ ٱلۡحَرِيقِ ﴿22﴾

22. ከጭንቀት ብርታት የተነሳ ከእርሷ ለመውጣት በፈለጉ ቁጥር በእርሷ ውስጥ እንዲመለሱ ይደረጋሉ። «ያን በጣም የሚያቃጥለውን ቅጣት ቅመሱ።» (ይባላሉ።)

22:23

إِنَّ ٱللَّهَ يُدۡخِلُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّـٰلِحَٰتِ جَنَّـٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ يُحَلَّوۡنَ فِيهَا مِنۡ أَسَاوِرَ مِن ذَهَبٖ وَلُؤۡلُؤٗاۖ وَلِبَاسُهُمۡ فِيهَا حَرِيرٞ ﴿23﴾

23. አላህ እነዚያን በትክክል ያመኑትንና መልካም ስራዎችን የሰሩትን ሰዎች በስሮቻቸው ጅረት ወንዞች በሚፈሱባቸው ገነቶች ያስገባቸዋል:: በእርሷ ውስጥ የወርቅ አንባሮችና ሉልን ይሸለማሉ:: በእርሷ ውስጥ ልብሶቻቸዉም ከሐር የተሰሩ ናቸው::