quranm◉

ገጽ 74

Range
from 3:181 to 3:186
Surahs covered
ትርጉም
6 ትርጉም

◉

3:181

لَّقَدۡ سَمِعَ ٱللَّهُ قَوۡلَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓاْ إِنَّ ٱللَّهَ فَقِيرٞ وَنَحۡنُ أَغۡنِيَآءُۘ سَنَكۡتُبُ مَا قَالُواْ وَقَتۡلَهُمُ ٱلۡأَنۢبِيَآءَ بِغَيۡرِ حَقّٖ وَنَقُولُ ذُوقُواْ عَذَابَ ٱلۡحَرِيقِ ﴿181﴾

181. አላህ የእነዚያን «አላህ ድሃ ነው እኛ ግን ከበርቴዎች ነን።» ያሉትን ሰዎች ቃል በእርግጥ ሰማ:: ያንን ያሉትንና ነብያትን ያለ ህግ መግደላቸውንም በእርግጥ እንጽፋለን:: «የማቃጠልንም ስቃይ ቅመሱ።» እንላቸዋለን።

3:182

ذَٰلِكَ بِمَا قَدَّمَتۡ أَيۡدِيكُمۡ وَأَنَّ ٱللَّهَ لَيۡسَ بِظَلَّامٖ لِّلۡعَبِيدِ ﴿182﴾

182. ያ ስቃይ እጃችሁ ባሳለፉት ስራና አላህም ለባሮቹ በዳይ ባለመሆኑ ነው::

3:183

ٱلَّذِينَ قَالُوٓاْ إِنَّ ٱللَّهَ عَهِدَ إِلَيۡنَآ أَلَّا نُؤۡمِنَ لِرَسُولٍ حَتَّىٰ يَأۡتِيَنَا بِقُرۡبَانٖ تَأۡكُلُهُ ٱلنَّارُۗ قُلۡ قَدۡ جَآءَكُمۡ رُسُلٞ مِّن قَبۡلِي بِٱلۡبَيِّنَٰتِ وَبِٱلَّذِي قُلۡتُمۡ فَلِمَ قَتَلۡتُمُوهُمۡ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ ﴿183﴾

183. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ይህን ቃል የተናገሩት: «ለማንኛዉም መልዕክተኛ እሳት የምትበላው ቁርባን እስከሚያመጣልን ድረስ በሱ እንዳናምን አላህ ወደ እኛ አዝዟል።» ያሉ ናቸው:: «ብዙ መልዕክተኞች ከእኔ በፊት በግልጽ ተዓምራትና በዚያ ባላችሁት ቁርባን በእርግጥ መጥተውላችኋል:: እውነተኞች ከሆናችሁ ታዲያ ለምን ገደላቸኃቸው?» በላቸው::

3:184

فَإِن كَذَّبُوكَ فَقَدۡ كُذِّبَ رُسُلٞ مِّن قَبۡلِكَ جَآءُو بِٱلۡبَيِّنَٰتِ وَٱلزُّبُرِ وَٱلۡكِتَٰبِ ٱلۡمُنِيرِ ﴿184﴾

184. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉህም ካንተ በፊትም በግልጽ ተዐምራት፣ በጽሁፎች፣ በብሩህ መጽሐፍም የመጡ መልዕክተኞችም በእርግጥ (በእነርሱ መሰሎች) ተስተባብለዋል::

3:185

كُلُّ نَفۡسٖ ذَآئِقَةُ ٱلۡمَوۡتِۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوۡنَ أُجُورَكُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۖ فَمَن زُحۡزِحَ عَنِ ٱلنَّارِ وَأُدۡخِلَ ٱلۡجَنَّةَ فَقَدۡ فَازَۗ وَمَا ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَآ إِلَّا مَتَٰعُ ٱلۡغُرُورِ ﴿185﴾

185. ነፍስ ሁሉ ሞትን በእርግጥ ቀማሽ ናት:: ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በትንሳኤ ቀን ብቻ ነው:: ከእሳት እንዲርቅ ተደርጎ ገነት እንዲገባ የተደረገም በእርግጥ ምኞቱን አገኘ:: የቅርቢቱ ሕይወት ማታለያ እንጂ ሌላ አይደለችም::

3:186

لَتُبۡلَوُنَّ فِيٓ أَمۡوَٰلِكُمۡ وَأَنفُسِكُمۡ وَلَتَسۡمَعُنَّ مِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ مِن قَبۡلِكُمۡ وَمِنَ ٱلَّذِينَ أَشۡرَكُوٓاْ أَذٗى كَثِيرٗاۚ وَإِن تَصۡبِرُواْ وَتَتَّقُواْ فَإِنَّ ذَٰلِكَ مِنۡ عَزۡمِ ٱلۡأُمُورِ ﴿186﴾

186. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በገንዘቦቻችሁና በነፍሶቻችሁ ትፈተናላችሁ:: ከእነዚያ ከናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡትም ከእነዚያ በአላህ ካጋሩትም ቡድኖች ብዙ መጥፎ ነገሮችን ትሰማላችሁ:: ብትታገሱና ብትጠነቀቁ (በጣም ጥሩ ነው።) ይህ ተግባር ከታላላቅ ነገሮች አንዱ ነው።