quranm◉

Surah Yusuf transliteration

◉ ሱራ · ∞

12:1

الٓرۚ تِلۡكَ ءَايَٰتُ ٱلۡكِتَٰبِ ٱلۡمُبِينِ ﴿1﴾

Transliteration: Aliflamra tilka ayatu alkitabi almubeenu

Translation: 1.አሊፍ፤ ላም፤ ራ፤ እነዚህ አናቅጽ ግልጽና የተብራራ ከሆነው መጽሐፍ አናቅጽ ናቸው።

12:2

إِنَّآ أَنزَلۡنَٰهُ قُرۡءَٰنًا عَرَبِيّٗا لَّعَلَّكُمۡ تَعۡقِلُونَ ﴿2﴾

Transliteration: Inna anzalnahu quranan AAarabiyyan laAAallakum taAAqiloona

Translation: 2. እኛ ይህንን ቁርኣንን ትረዱት ዘንድ በዐረበኛ ቋንቋ አወረድነው።

12:3

نَحۡنُ نَقُصُّ عَلَيۡكَ أَحۡسَنَ ٱلۡقَصَصِ بِمَآ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانَ وَإِن كُنتَ مِن قَبۡلِهِۦ لَمِنَ ٱلۡغَٰفِلِينَ ﴿3﴾

Transliteration: Nahnu naqussu AAalayka ahsana alqasasi bima awhayna ilayka hatha alqurana wain kunta min qablihi lamina alghafileena

Translation: 3.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህንን የቁርኣን ወደ አንተ በማውረዳችን እጅግ ውብና ማራኪ የሆነ ታሪክ እንተርክልሃለን:: ከዚህ በፊት አንተም ይህንን ታሪክ ከማያውቁት ነበርክ::

12:4

إِذۡ قَالَ يُوسُفُ لِأَبِيهِ يَـٰٓأَبَتِ إِنِّي رَأَيۡتُ أَحَدَ عَشَرَ كَوۡكَبٗا وَٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَ رَأَيۡتُهُمۡ لِي سَٰجِدِينَ ﴿4﴾

Transliteration: Ith qala yoosufu liabeehi ya abati innee raaytu ahada AAashara kawkaban waalshshamsa waalqamara raaytuhum lee sajideena

Translation: 4. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነብዩ ዩሱፍ በልጅነቱ ለአባቱ «አባቴ ሆይ! እኔ አስራ አንድ ኮከቦችን፤ ጨረቃንና ጸሐይን ሲሰግዱልኝ በሕልሜ አየሁኝ።» ባለ ጊዜ የሆነውን ታሪክ ለህዝቦችህ አስታውስ።

12:5

قَالَ يَٰبُنَيَّ لَا تَقۡصُصۡ رُءۡيَاكَ عَلَىٰٓ إِخۡوَتِكَ فَيَكِيدُواْ لَكَ كَيۡدًاۖ إِنَّ ٱلشَّيۡطَٰنَ لِلۡإِنسَٰنِ عَدُوّٞ مُّبِينٞ ﴿5﴾

Transliteration: Qala ya bunayya la taqsus ruyaka AAala ikhwatika fayakeedoo laka kaydan inna alshshaytana lilinsani AAaduwwun mubeenun

Translation: 5. አባቱም አለ: «ልጄ ሆይ! ይህን ህልምህን ለወንድሞችህ አትንገር። ባንተ ላይ ተንኮል እንዳያሴሩ። ምክንያቱም ሰይጣን ለሰው ልጅ ሁልጊዜም ግልጽ ጠላት ነውና።

12:6

وَكَذَٰلِكَ يَجۡتَبِيكَ رَبُّكَ وَيُعَلِّمُكَ مِن تَأۡوِيلِ ٱلۡأَحَادِيثِ وَيُتِمُّ نِعۡمَتَهُۥ عَلَيۡكَ وَعَلَىٰٓ ءَالِ يَعۡقُوبَ كَمَآ أَتَمَّهَا عَلَىٰٓ أَبَوَيۡكَ مِن قَبۡلُ إِبۡرَٰهِيمَ وَإِسۡحَٰقَۚ إِنَّ رَبَّكَ عَلِيمٌ حَكِيمٞ ﴿6﴾

Transliteration: Wakathalika yajtabeeka rabbuka wayuAAallimuka min taweeli alahadeethi wayutimmu niAAmatahu AAalayka waAAala ali yaAAqooba kama atammaha AAala abawayka min qablu ibraheema waishaqa inna rabbaka AAaleemun hakeemun

Translation: 6. «ጌታህ ልክ ይህን ህልም እንዳሳየህ ሁሉ ለነብይነትም ይመርጥሃል:: የንንግግሮችን ፍፃሜ ያስተምርሃል:: ጸጋውንም ቀደም ሲል ለአባቶችህ ለኢብራሂምና ለኢስሃቅ እንደሞላ ሁሉ ላንተና ለያዕቁብ ቤተሰቦችም ይሞላል:: ጌታህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።»

12:7

لَّقَدۡ كَانَ فِي يُوسُفَ وَإِخۡوَتِهِۦٓ ءَايَٰتٞ لِّلسَّآئِلِينَ ﴿7﴾

Transliteration: Laqad kana fee yoosufa waikhwatihi ayatun lilssaileena

Translation: 7. በዩሱፍና በወንድሞቹ ታሪክ ዉስጥ እውቀትን በመሻት ለሚጠይቁ ሁሉ እያሌ ተዓምራት አሉ::

12:8

إِذۡ قَالُواْ لَيُوسُفُ وَأَخُوهُ أَحَبُّ إِلَىٰٓ أَبِينَا مِنَّا وَنَحۡنُ عُصۡبَةٌ إِنَّ أَبَانَا لَفِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٍ ﴿8﴾

Transliteration: Ith qaloo layoosufu waakhoohu ahabbu ila abeena minna wanahnu AAusbatun inna abana lafee dalalin mubeenin

Translation: 8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) ባሉ ጊዜ: «እኛ በቁጥር ብዙዎች ሁነን እያለ ዩሱፍና ወንድሙ (ብንያም) ከአባታችን ዘንድ ከእኛ ይበልጥ ተወዳጆች ናቸው:: በእውነቱ አባታችን ግልጽ ስህተት ውስጥ ነው።

12:9

ٱقۡتُلُواْ يُوسُفَ أَوِ ٱطۡرَحُوهُ أَرۡضٗا يَخۡلُ لَكُمۡ وَجۡهُ أَبِيكُمۡ وَتَكُونُواْ مِنۢ بَعۡدِهِۦ قَوۡمٗا صَٰلِحِينَ ﴿9﴾

Transliteration: Oqtuloo yoosufa awi itrahoohu ardan yakhlu lakum wajhu abeekum watakoonoo min baAAdihi qawman saliheena

Translation: 9. «ዩሱፍን ግደሉት ወይም እሩቅ ቦታ ጣሉት:: ይህን ካረጋችሁ የአባታችሁን ፊት ትኩረትና ውዴታ የራሳችሁ ብቻ ታደርጋላችሁ:: ከዚህ በኋላ ከኃጥያታችሁ በመመለስ መልካም ሰዎች ትሆናለችሁ።

12:10

قَالَ قَآئِلٞ مِّنۡهُمۡ لَا تَقۡتُلُواْ يُوسُفَ وَأَلۡقُوهُ فِي غَيَٰبَتِ ٱلۡجُبِّ يَلۡتَقِطۡهُ بَعۡضُ ٱلسَّيَّارَةِ إِن كُنتُمۡ فَٰعِلِينَ ﴿10﴾

Transliteration: Qala qailun minhum la taqtuloo yoosufa waalqoohu fee ghayabati aljubbi yaltaqithu baAAdu alssayyarati in kuntum faAAileena

Translation: 10. ከእነሱ አንድ ተናጋሪ «ዩሱፍን አትግደሉ ግን በጉድጓድ አዘቅት ጨለማ ውስጥ ጣሉት፤ ከተጓዢዎች አንዱ ያነሳዋልና፡፡ ሠሪዎች ብትኾኑ (በዚሁ ተብቃቁ) አላቸው፡፡

12:11

قَالُواْ يَـٰٓأَبَانَا مَا لَكَ لَا تَأۡمَ۬نَّا عَلَىٰ يُوسُفَ وَإِنَّا لَهُۥ لَنَٰصِحُونَ ﴿11﴾

Transliteration: Qaloo ya abana ma laka la tamanna AAala yoosufa wainna lahu lanasihoona

Translation: 11. አሉም: «አባታችን ሆይ! በዩሱፍ ጉዳይ እኛ ለእርሱ ቅን አሳቢዎች ሁነን ሳለ ለምን አታምነንም?

12:12

أَرۡسِلۡهُ مَعَنَا غَدٗا يَرۡتَعۡ وَيَلۡعَبۡ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ ﴿12﴾

Transliteration: Arsilhu maAAana ghadan yartaAA wayalAAab wainna lahu lahafithoona

Translation: 12. «እስቲ ይዝናና ይጫወት ዘንድ ነገ ከእኛ ጋር አብረህ ላከው::እኛም ለእርሱ ጠባቂዎች ነን።»

12:13

قَالَ إِنِّي لَيَحۡزُنُنِيٓ أَن تَذۡهَبُواْ بِهِۦ وَأَخَافُ أَن يَأۡكُلَهُ ٱلذِّئۡبُ وَأَنتُمۡ عَنۡهُ غَٰفِلُونَ ﴿13﴾

Transliteration: Qala innee layahzununee an thathhaboo bihi waakhafu an yakulahu alththibu waantum AAanhu ghafiloona

Translation: 13. አባቱም «እርሱን መውሰዳችሁ ያሳዝነኛል። ዘንግታችሁት ተኩላ እንዳይበላዉም እፈራለሁ።» አለ።

12:14

قَالُواْ لَئِنۡ أَكَلَهُ ٱلذِّئۡبُ وَنَحۡنُ عُصۡبَةٌ إِنَّآ إِذٗا لَّخَٰسِرُونَ ﴿14﴾

Transliteration: Qaloo lain akalahu alththibu wanahnu AAusbatun inna ithan lakhasiroona

Translation: 14. እነርሱም «እኛ እንዲህ ጭፍሮች ሆነን ተኩላ ከበላውማ ከሳሪዎቹ እኛ ነን።» አሉ።

12:15

فَلَمَّا ذَهَبُواْ بِهِۦ وَأَجۡمَعُوٓاْ أَن يَجۡعَلُوهُ فِي غَيَٰبَتِ ٱلۡجُبِّۚ وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡهِ لَتُنَبِّئَنَّهُم بِأَمۡرِهِمۡ هَٰذَا وَهُمۡ لَا يَشۡعُرُونَ ﴿15﴾

Transliteration: Falamma thahaboo bihi waajmaAAoo an yajAAaloohu fee ghayabati aljubbi waawhayna ilayhi latunabiannahum biamrihim hatha wahum la yashAAuroona

Translation: 15. እርሱንም ወስደውት በጉድጓድ ወለል ላይ ሊጥሉት በወሰኑ ጊዜ «እነርሱ ሳያውቁ ይህን ጸያፍ ተግባራቸውን ወደ ፊት ትነግራቸዋለህ» የሚል መልዕክት ላክንለት።

12:16

وَجَآءُوٓ أَبَاهُمۡ عِشَآءٗ يَبۡكُونَ ﴿16﴾

Transliteration: Wajaoo abahum AAishaan yabkoona

Translation: 16. አባታቸውንም በምሽት እያለቀሱ መጡት።

12:17

قَالُواْ يَـٰٓأَبَانَآ إِنَّا ذَهَبۡنَا نَسۡتَبِقُ وَتَرَكۡنَا يُوسُفَ عِندَ مَتَٰعِنَا فَأَكَلَهُ ٱلذِّئۡبُۖ وَمَآ أَنتَ بِمُؤۡمِنٖ لَّنَا وَلَوۡ كُنَّا صَٰدِقِينَ ﴿17﴾

Transliteration: Qaloo ya abana inna thahabna nastabiqu watarakna yoosufa AAinda mataAAina faakalahu alththibu wama anta bimuminin lana walaw kunna sadiqeena

Translation: 17. «አባታችን ሆይ! እኛ ለሩጫና ለውርወራ ልንሽቀዳደም ሄድን። ዩሱፍንም እቃችን ዘንድ ተውነው:: ወዲያዉም ተኩላ በላው:: አንተም እውነተኞች ብንሆንም የምታምነን አይደለህም።» አሉ።

12:18

وَجَآءُو عَلَىٰ قَمِيصِهِۦ بِدَمٖ كَذِبٖۚ قَالَ بَلۡ سَوَّلَتۡ لَكُمۡ أَنفُسُكُمۡ أَمۡرٗاۖ فَصَبۡرٞ جَمِيلٞۖ وَٱللَّهُ ٱلۡمُسۡتَعَانُ عَلَىٰ مَا تَصِفُونَ ﴿18﴾

Transliteration: Wajaoo AAala qameesihi bidamin kathibin qala bal sawwalat lakum anfusukum amran fasabrun jameelun waAllahu almustaAAanu AAala ma tasifoona

Translation: 18. በቀሚሱም ላይ የውሸትን ደም አመጡ:: አባታቸውም: «ይህ ትክክል አይደለም። ይልቁን ነፍሶቻችሁ ውሸት ነገርን ለናንተ ሸለሙላችሁ:: ስለዚህ መልካም ትዕግስት ማድረግ አለብኝ:: በምትሉትም ነገር ላይ መታገዣው አላህ ብቻ ነው።» አለ።

12:19

وَجَآءَتۡ سَيَّارَةٞ فَأَرۡسَلُواْ وَارِدَهُمۡ فَأَدۡلَىٰ دَلۡوَهُۥۖ قَالَ يَٰبُشۡرَىٰ هَٰذَا غُلَٰمٞۚ وَأَسَرُّوهُ بِضَٰعَةٗۚ وَٱللَّهُ عَلِيمُۢ بِمَا يَعۡمَلُونَ ﴿19﴾

Transliteration: Wajaat sayyaratun faarsaloo waridahum faadla dalwahu qala ya bushra hatha ghulamun waasarroohu bidaAAatan waAllahu AAaleemun bima yaAAmaloona

Translation: 19. መንገደኞችም መጡ:: ውሃ ቀጂያቸውንም ላኩ:: አኮሌውንም ወደ ጉድጎዱ ሰደደ:: የምስራች:: «ይህ ልጅ ነው።» አለ:: ሸቀጥ አድርገዉም ደበቁት:: አላህ የሚሠሩትን ሁሉ አዋቂ ነው::

12:20

وَشَرَوۡهُ بِثَمَنِۭ بَخۡسٖ دَرَٰهِمَ مَعۡدُودَةٖ وَكَانُواْ فِيهِ مِنَ ٱلزَّـٰهِدِينَ ﴿20﴾

Transliteration: Washarawhu bithamanin bakhsin darahima maAAdoodatin wakanoo feehi mina alzzahideena

Translation: 20. በርካሽ ዋጋና በሚቆጠሩ ዲርሃሞች ሸጡት:: በእርሱም ላይ ከቸልተኞቹ ነበሩ::

12:21

وَقَالَ ٱلَّذِي ٱشۡتَرَىٰهُ مِن مِّصۡرَ لِٱمۡرَأَتِهِۦٓ أَكۡرِمِي مَثۡوَىٰهُ عَسَىٰٓ أَن يَنفَعَنَآ أَوۡ نَتَّخِذَهُۥ وَلَدٗاۚ وَكَذَٰلِكَ مَكَّنَّا لِيُوسُفَ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلِنُعَلِّمَهُۥ مِن تَأۡوِيلِ ٱلۡأَحَادِيثِۚ وَٱللَّهُ غَالِبٌ عَلَىٰٓ أَمۡرِهِۦ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ ﴿21﴾

Transliteration: Waqala allathee ishtarahu min misra liimraatihi akrimee mathwahu AAasa an yanfaAAana aw nattakhithahu waladan wakathalika makkanna liyoosufa fee alardi walinuAAallimahu min taweeli alahadeethi waAllahu ghalibun AAala amrihi walakinna akthara alnnasi la yaAAlamoona

Translation: 21. ያም ከምስር የገዛው ሰው ለሚስቱ «ይህ ልጅ መኖሪያውን አክብሪ ሊጠቅመን ወይም ልጅ አድርገን ልንይዘው ይከጅላልና።» አላት:: ልክ እንደዚሁ ለዩሱፍ ገዥ ልናደርገውና የሕልሞችንም ፍች ልናስተምረው በምድር ላይ አስመቸነው:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ አሸናፊ ነው። ግን አብዛኞቹ ሰዎች ይህን አያውቁም::

12:22

وَلَمَّا بَلَغَ أَشُدَّهُۥٓ ءَاتَيۡنَٰهُ حُكۡمٗا وَعِلۡمٗاۚ وَكَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ ﴿22﴾

Transliteration: Walamma balagha ashuddahu ataynahu hukman waAAilman wakathalika najzee almuhsineena

Translation: 22. ጥንካሬውንም በደረሰ ጊዜ ጥበብንና ዕውቀትን ሰጠነው:: ልክ እንደዚህም መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን::

12:23

وَرَٰوَدَتۡهُ ٱلَّتِي هُوَ فِي بَيۡتِهَا عَن نَّفۡسِهِۦ وَغَلَّقَتِ ٱلۡأَبۡوَٰبَ وَقَالَتۡ هَيۡتَ لَكَۚ قَالَ مَعَاذَ ٱللَّهِۖ إِنَّهُۥ رَبِّيٓ أَحۡسَنَ مَثۡوَايَۖ إِنَّهُۥ لَا يُفۡلِحُ ٱلظَّـٰلِمُونَ ﴿23﴾

Transliteration: Warawadathu allatee huwa fee baytiha AAan nafsihi waghallaqati alabwaba waqalat hayta laka qala maAAatha Allahi innahu rabbee ahsana mathwaya innahu la yuflihu alththalimoona

Translation: 23. ያችም እርሱ በቤትዋ የነበረባት ሴት ከነፍሱ አባበለችው:: ደጃፎቹንም ዘጋችና «ይኸው ላንተ ተዘጋጂቼልሃለሁና ቶሎ በል» አለችው:: እሱም «ከዚህ ጸያፍ ተግባር በአላህ እጠበቃለሁ:: እርሱ የገዘኝ ጌታዬ ኑሮዬን ያሳመረልኝ ነውና አልከዳዉም:: እነሆ በደለኞች ሁሉ አይድኑምና» አላት።

12:24

وَلَقَدۡ هَمَّتۡ بِهِۦۖ وَهَمَّ بِهَا لَوۡلَآ أَن رَّءَا بُرۡهَٰنَ رَبِّهِۦۚ كَذَٰلِكَ لِنَصۡرِفَ عَنۡهُ ٱلسُّوٓءَ وَٱلۡفَحۡشَآءَۚ إِنَّهُۥ مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُخۡلَصِينَ ﴿24﴾

Transliteration: Walaqad hammat bihi wahamma biha lawla an raa burhana rabbihi kathalika linasrifa AAanhu alssooa waalfahshaa innahu min AAibadina almukhlaseena

Translation: 24. በእርሱም በእርግጥ አሰበች፡፡ በእርሷም አሰበ ፡፡የጌታውን ማስረጃ ባላዬ ኖሮ (በእርሷም ባሰበ ነበር) ፡፡ልክ እንደዚሁ መጥፎ ነገርንና ኃጢአትን ከእርሱ ላይ ልንመልስለት አስረጃችንን አሳየነው ፡፡እርሱ ከተጠበቁት ባሮቻችን አንዱ ነዉና ፡፡

12:25

وَٱسۡتَبَقَا ٱلۡبَابَ وَقَدَّتۡ قَمِيصَهُۥ مِن دُبُرٖ وَأَلۡفَيَا سَيِّدَهَا لَدَا ٱلۡبَابِۚ قَالَتۡ مَا جَزَآءُ مَنۡ أَرَادَ بِأَهۡلِكَ سُوٓءًا إِلَّآ أَن يُسۡجَنَ أَوۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ ﴿25﴾

Transliteration: Waistabaqa albaba waqaddat qameesahu min duburin waalfaya sayyidaha lada albabi qalat ma jazao man arada biahlika sooan illa an yusjana aw AAathabun aleemun

Translation: 25. እርሱና እርሷ በሩን ተሸቀዳደሙና ቀሚሱን ከኋላው ቀደደችው። ባለቤትዋን እበሩ አጠገብ አገኙት:: እርሷም ቀደም ብላ «በባለቤትህ መጥፎን ያሰበ ሰው ቅጣቱ መታሰር ወይም አሳማሚ ስቃይ እንጂ ሌላ አይደለም።» አለችው።

12:26

قَالَ هِيَ رَٰوَدَتۡنِي عَن نَّفۡسِيۚ وَشَهِدَ شَاهِدٞ مِّنۡ أَهۡلِهَآ إِن كَانَ قَمِيصُهُۥ قُدَّ مِن قُبُلٖ فَصَدَقَتۡ وَهُوَ مِنَ ٱلۡكَٰذِبِينَ ﴿26﴾

Transliteration: Qala hiya rawadatnee AAan nafsee washahida shahidun min ahliha in kana qameesuhu qudda min qubulin fasadaqat wahuwa mina alkathibeena

Translation: 26. ዩሱፍም «እርሷ ናት ከነፍሴ ያባበለችኝ።» አለ:: ከቤተሰቦቿም አንድ መስካሪ (እንዲህ) መሰከረ: «ቀሚሱ ከበስተፊት ተቀዶ ከሆነ እርሷ እውነት ተናገረች:: እርሱ ከውሸታሞቹ አንዱ ነው።

12:27

وَإِن كَانَ قَمِيصُهُۥ قُدَّ مِن دُبُرٖ فَكَذَبَتۡ وَهُوَ مِنَ ٱلصَّـٰدِقِينَ ﴿27﴾

Transliteration: Wain kana qameesuhu qudda min duburin fakathabat wahuwa mina alssadiqeena

Translation: 27. «ቀሚሱም ከበስተኋላው ተቀዶ እንደሆነ ዋሸች:: እርሱም ከእውነተኞቹ ነው።»

12:28

فَلَمَّا رَءَا قَمِيصَهُۥ قُدَّ مِن دُبُرٖ قَالَ إِنَّهُۥ مِن كَيۡدِكُنَّۖ إِنَّ كَيۡدَكُنَّ عَظِيمٞ ﴿28﴾

Transliteration: Falamma raa qameesahu qudda min duburin qala innahu min kaydikunna inna kaydakunna AAatheemun

Translation: 28. ቀሚሱንም ከበስተኋላ ተቀዶ ባየ ጊዜ አለ: «እርሱ የተናገርሽው ከተንኮላችሁ ነው። የእንናንተ የሴቶች ተንኮል በእርግጥ ብርቱ ነው።

12:29

يُوسُفُ أَعۡرِضۡ عَنۡ هَٰذَاۚ وَٱسۡتَغۡفِرِي لِذَنۢبِكِۖ إِنَّكِ كُنتِ مِنَ ٱلۡخَاطِـِٔينَ ﴿29﴾

Transliteration: Yoosufu aAArid AAan hatha waistaghfiree lithanbiki innaki kunti mina alkhatieena

Translation: 29. «ዩሱፍ ሆይ! አንተም ከዚህ ወሬ ተከልከል:: አንቺም ለኃጢአትሽ ማርታን ለምኝ። አንቺ ከስሕተተኞቹ ሆነሻልና።» አለ::

12:30

وَقَالَ نِسۡوَةٞ فِي ٱلۡمَدِينَةِ ٱمۡرَأَتُ ٱلۡعَزِيزِ تُرَٰوِدُ فَتَىٰهَا عَن نَّفۡسِهِۦۖ قَدۡ شَغَفَهَا حُبًّاۖ إِنَّا لَنَرَىٰهَا فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ ﴿30﴾

Transliteration: Waqala niswatun fee almadeenati imraatu alAAazeezi turawidu fataha AAan nafsihi qad shaghafaha hubban inna lanaraha fee dalalin mubeenin

Translation: 30. በከተማው ያሉ ሴቶችም «የዐዚዝ ሚስት ሰራተኛዋን ከነፍሱ ታባብለዋለች:: በእውነቱ ፍቅሩ ልቧን መቷታል:: እኛ በግልጽ ስሕተት ውስጥ ሆና በእርግጥ እናያታለን።» አሉ።

12:31

فَلَمَّا سَمِعَتۡ بِمَكۡرِهِنَّ أَرۡسَلَتۡ إِلَيۡهِنَّ وَأَعۡتَدَتۡ لَهُنَّ مُتَّكَـٔٗا وَءَاتَتۡ كُلَّ وَٰحِدَةٖ مِّنۡهُنَّ سِكِّينٗا وَقَالَتِ ٱخۡرُجۡ عَلَيۡهِنَّۖ فَلَمَّا رَأَيۡنَهُۥٓ أَكۡبَرۡنَهُۥ وَقَطَّعۡنَ أَيۡدِيَهُنَّ وَقُلۡنَ حَٰشَ لِلَّهِ مَا هَٰذَا بَشَرًا إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا مَلَكٞ كَرِيمٞ ﴿31﴾

Transliteration: Falamma samiAAat bimakrihinna arsalat ilayhinna waaAAtadat lahunna muttakaan waatat kulla wahidatin minhunna sikkeenan waqalati okhruj AAalayhinna falamma raaynahu akbarnahu waqattaAAna aydiyahunna waqulna hasha lillahi ma hatha basharan in hatha illa malakun kareemun

Translation: 31. እርሷም ሐሜታቸውን በሰማች ጊዜ ወደነሱ ላከችባቸው:: ግብዣንም ለእነርሱ አዘጋጀችላቸው:: ለያንዳንዳቸዉም ቢላዋን ሰጠችና «በእነርሱም ላይ ውጣ።» አለችው:: እነርሱም በተመለከቱት ጊዜ በጣም አደነቁት:: እጆቻቸዉንም ቆረጡ። «ለአላህ ጥራት ይገባው:: ይህ ሰው አይደለም:: ይህ የተከበረ መልአክ እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ።

12:32

قَالَتۡ فَذَٰلِكُنَّ ٱلَّذِي لُمۡتُنَّنِي فِيهِۖ وَلَقَدۡ رَٰوَدتُّهُۥ عَن نَّفۡسِهِۦ فَٱسۡتَعۡصَمَۖ وَلَئِن لَّمۡ يَفۡعَلۡ مَآ ءَامُرُهُۥ لَيُسۡجَنَنَّ وَلَيَكُونٗا مِّنَ ٱلصَّـٰغِرِينَ ﴿32﴾

Transliteration: Qalat fathalikunna allathee lumtunnanee feehi walaqad rawadtuhu AAan nafsihi faistAAsama walain lam yafAAal ma amuruhu layusjananna walayakoonan mina alssaghireena

Translation: 32. በዚህ ጊዜ «ይህ እኮ ነው ያ በእርሱ ፍቅር ያማችሁኝ ሰው:: በእርግጥም ከነፍሱ አባባልኩት ግና እርሱ እንቢ አለ:: ወደፊትም የማዘውን ነገር ባይሠራ በእርግጥ ይታሰራል ከወራዶቹም ይሆናል።» አለች።

12:33

قَالَ رَبِّ ٱلسِّجۡنُ أَحَبُّ إِلَيَّ مِمَّا يَدۡعُونَنِيٓ إِلَيۡهِۖ وَإِلَّا تَصۡرِفۡ عَنِّي كَيۡدَهُنَّ أَصۡبُ إِلَيۡهِنَّ وَأَكُن مِّنَ ٱلۡجَٰهِلِينَ ﴿33﴾

Transliteration: Qala rabbi alssijnu ahabbu ilayya mimma yadAAoonanee ilayhi wailla tasrif AAannee kaydahunna asbu ilayhinna waakun mina aljahileena

Translation: 33. «ጌታዬ ሆይ! ወደ እርሱ ከሚጠሩኝ ነገር (ከዝሙት) ይልቅ መታሰር ለእኔ የተወደደ ነው:: ተንኮላቸውንም ከእኔ ላይ ባትመልስልኝ ወደ እነርሱ እዘነበላለሁ:: ከስሕተተኞቹም እሆናለሁ።» አለ።

12:34

فَٱسۡتَجَابَ لَهُۥ رَبُّهُۥ فَصَرَفَ عَنۡهُ كَيۡدَهُنَّۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ ﴿34﴾

Transliteration: Faistajaba lahu rabbuhu fasarafa AAanhu kaydahunna innahu huwa alssameeAAu alAAaleemu

Translation: 34. ጌታዉም ጸሎቱን ተቀበለው፤ ተንኮላቸውንም ከእርሱ መለሰለት:: እነሆ እርሱ ሁሉን ሰሚና ሁሉን አዋቂ ነውና።

12:35

ثُمَّ بَدَا لَهُم مِّنۢ بَعۡدِ مَا رَأَوُاْ ٱلۡأٓيَٰتِ لَيَسۡجُنُنَّهُۥ حَتَّىٰ حِينٖ ﴿35﴾

Transliteration: Thumma bada lahum min baAAdi ma raawoo alayati layasjununnahu hatta heenin

Translation: 35. ከዚያም ማስረጃዎችን ካዩ በኋላ እስከ ጊዜ ድረስ እንዲያስሩት ለእነርሱ ታያቸው::

12:36

وَدَخَلَ مَعَهُ ٱلسِّجۡنَ فَتَيَانِۖ قَالَ أَحَدُهُمَآ إِنِّيٓ أَرَىٰنِيٓ أَعۡصِرُ خَمۡرٗاۖ وَقَالَ ٱلۡأٓخَرُ إِنِّيٓ أَرَىٰنِيٓ أَحۡمِلُ فَوۡقَ رَأۡسِي خُبۡزٗا تَأۡكُلُ ٱلطَّيۡرُ مِنۡهُۖ نَبِّئۡنَا بِتَأۡوِيلِهِۦٓۖ إِنَّا نَرَىٰكَ مِنَ ٱلۡمُحۡسِنِينَ ﴿36﴾

Transliteration: Wadakhala maAAahu alssijna fatayani qala ahaduhuma innee aranee aAAsiru khamran waqala alakharu innee aranee ahmilu fawqa rasee khubzan takulu alttayru minhu nabbina bitaweelihi inna naraka mina almuhsineena

Translation: 36. ከእሱም ጋር ሁለት ወጣቶች እስር ቤቱ ገቡ:: አንደኛቸው «እኔ በሕልሜ የወይን ጠጅን ስጠምቅ አየሁ።» አለ:: ሌላው ደግሞ «እኔ በራሴ ላይ ቂጣን ተሸክሜ ከእሱ በራሪ አሞራ ስትበላ አየሁ ፍችውን ንገረን እኛ ከአሳማሪዎች ሁነህ እናይሃለንና።» አሉት።

12:37

قَالَ لَا يَأۡتِيكُمَا طَعَامٞ تُرۡزَقَانِهِۦٓ إِلَّا نَبَّأۡتُكُمَا بِتَأۡوِيلِهِۦ قَبۡلَ أَن يَأۡتِيَكُمَاۚ ذَٰلِكُمَا مِمَّا عَلَّمَنِي رَبِّيٓۚ إِنِّي تَرَكۡتُ مِلَّةَ قَوۡمٖ لَّا يُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَهُم بِٱلۡأٓخِرَةِ هُمۡ كَٰفِرُونَ ﴿37﴾

Transliteration: Qala la yateekuma taAAamun turzaqanihi illa nabbatukuma bitaweelihi qabla an yatiyakuma thalikuma mimma AAallamanee rabbee innee taraktu millata qawmin la yuminoona biAllahi wahum bialakhirati hum kafiroona

Translation: 37. ዩሱፍም አለ: «ማንኛዉም የምትሰጡት ምግብ ለእናንተ ከመምጣቱ በፊት ፍችውን የምነግራችሁ ቢሆን እንጂ አይመጣላችሁም:: ይህ ጉዳይ ጌታዬ ካሳወቀኝ ነገር ነው:: እኔም በአላህ የማያምኑትንና በመጨረሻይቱ ዓለም ከሓዲያን የሆኑ ሕዝቦችን ሃይማኖት ትቻለሁ::

12:38

وَٱتَّبَعۡتُ مِلَّةَ ءَابَآءِيٓ إِبۡرَٰهِيمَ وَإِسۡحَٰقَ وَيَعۡقُوبَۚ مَا كَانَ لَنَآ أَن نُّشۡرِكَ بِٱللَّهِ مِن شَيۡءٖۚ ذَٰلِكَ مِن فَضۡلِ ٱللَّهِ عَلَيۡنَا وَعَلَى ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَشۡكُرُونَ ﴿38﴾

Transliteration: WaittabaAAtu millata abaee ibraheema waishaqa wayaAAqooba ma kana lana an nushrika biAllahi min shayin thalika min fadli Allahi AAalayna waAAala alnnasi walakinna akthara alnnasi la yashkuroona

Translation: 38. «የአባቶቼንም የኢብራሂምን፤ የኢስሐቅንና የያዕቁብን ሃይማኖት ተከትያለሁ:: ለእኛ በአላህ ምንንም ማጋራት አይገባንም:: ያ አለማጋራት በእኛ ላይና በሰዎች ላይ የአላህ ችሮታ ነው:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያመሰግኑም::

12:39

يَٰصَٰحِبَيِ ٱلسِّجۡنِ ءَأَرۡبَابٞ مُّتَفَرِّقُونَ خَيۡرٌ أَمِ ٱللَّهُ ٱلۡوَٰحِدُ ٱلۡقَهَّارُ ﴿39﴾

Transliteration: Ya sahibayi alssijni aarbabun mutafarriqoona khayrun ami Allahu alwahidu alqahharu

Translation: 39. «የእስር ቤት ጓደኞቼ ሆይ! የተለያዩ አምላኮች ይሻላሉን ወይስ አሸናፊውና አንዱ አላህ?

12:40

مَا تَعۡبُدُونَ مِن دُونِهِۦٓ إِلَّآ أَسۡمَآءٗ سَمَّيۡتُمُوهَآ أَنتُمۡ وَءَابَآؤُكُم مَّآ أَنزَلَ ٱللَّهُ بِهَا مِن سُلۡطَٰنٍۚ إِنِ ٱلۡحُكۡمُ إِلَّا لِلَّهِ أَمَرَ أَلَّا تَعۡبُدُوٓاْ إِلَّآ إِيَّاهُۚ ذَٰلِكَ ٱلدِّينُ ٱلۡقَيِّمُ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ ﴿40﴾

Transliteration: Ma taAAbudoona min doonihi illa asmaan sammaytumooha antum waabaokum ma anzala Allahu biha min sultanin ini alhukmu illa lillahi amara alla taAAbudoo illa iyyahu thalika alddeenu alqayyimu walakinna akthara alnnasi la yaAAlamoona

Translation: 40. «ከእርሱ ሌላ እናንተና አባቶቻችሁ አማልክት ብላችሁ የጠራችኋቸውን ስሞች እንጂ አትገዙም። አላህ በእርሷ ምንም አስረጂ አላወረደም። ፍርዱ የአላህ እንጂ ሌላ አይደለም:: እርሱን እንጂ ሌላን እንዳትገዙም አዟል:: ይህ ትክክለኛው ሃይማኖት ነው:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም::

12:41

يَٰصَٰحِبَيِ ٱلسِّجۡنِ أَمَّآ أَحَدُكُمَا فَيَسۡقِي رَبَّهُۥ خَمۡرٗاۖ وَأَمَّا ٱلۡأٓخَرُ فَيُصۡلَبُ فَتَأۡكُلُ ٱلطَّيۡرُ مِن رَّأۡسِهِۦۚ قُضِيَ ٱلۡأَمۡرُ ٱلَّذِي فِيهِ تَسۡتَفۡتِيَانِ ﴿41﴾

Transliteration: Ya sahibayi alssijni amma ahadukuma fayasqee rabbahu khamran waamma alakharu fayuslabu fatakulu alttayru min rasihi qudiya alamru allathee feehi tastaftiyani

Translation: 41. «የአስር ቤት ጓደኞቼ ሆይ! አንደኛችሁማ ንጉሡን ጠጅ ያጠጣል። ሌላውም ይሰቀላል:: ከራሱም በራሪ አሞራ ትበላለች:: ያ ፍቹን የምትጠይቁት ነገር ተፈጸመ።» አላቸው።

12:42

وَقَالَ لِلَّذِي ظَنَّ أَنَّهُۥ نَاجٖ مِّنۡهُمَا ٱذۡكُرۡنِي عِندَ رَبِّكَ فَأَنسَىٰهُ ٱلشَّيۡطَٰنُ ذِكۡرَ رَبِّهِۦ فَلَبِثَ فِي ٱلسِّجۡنِ بِضۡعَ سِنِينَ ﴿42﴾

Transliteration: Waqala lillathee thanna annahu najin minhuma othkurnee AAinda rabbika faansahu alshshaytanu thikra rabbihi falabitha fee alssijni bidAAa sineena

Translation: 42. ለዚያም ከሁለቱ እርሱ የሚድን መሆኑን ለተጠራጠረው እጌታህ ዘንድ አስታውሰኝ አለው፡፡ ጌታውንም ከማስታወስ ሰይጣን አስረሳው፡፡ ለጥቂት ዓመታትም በወህኒ ቤቱ ውስጥ ቆየ፡፡

12:43

وَقَالَ ٱلۡمَلِكُ إِنِّيٓ أَرَىٰ سَبۡعَ بَقَرَٰتٖ سِمَانٖ يَأۡكُلُهُنَّ سَبۡعٌ عِجَافٞ وَسَبۡعَ سُنۢبُلَٰتٍ خُضۡرٖ وَأُخَرَ يَابِسَٰتٖۖ يَـٰٓأَيُّهَا ٱلۡمَلَأُ أَفۡتُونِي فِي رُءۡيَٰيَ إِن كُنتُمۡ لِلرُّءۡيَا تَعۡبُرُونَ ﴿43﴾

Transliteration: Waqala almaliku innee ara sabAAa baqaratin simanin yakuluhunna sabAAun AAijafun wasabAAa sunbulatin khudrin waokhara yabisatin ya ayyuha almalao aftoonee fee ruyaya in kuntum lilrruya taAAburoona

Translation: 43. ንጉሡም «እኔ ሰባት የሰቡ ላሞችን ሰባት የከሱ ላሞች ሲበሉዋቸው፤ ሰባት ለምለም ዘለላዎችም ሌሎች ሰባት ደረቆችን ስብርብር ሲያደርጉ በሕልሜ አየሁ:: እናንተ ታላላቅ ሰዎች ሆይ! ሕልም መፍታት የምታውቁ ከሆናችሁ ሕልሜን ፍቱልኝ።» አላቸው።

12:44

قَالُوٓاْ أَضۡغَٰثُ أَحۡلَٰمٖۖ وَمَا نَحۡنُ بِتَأۡوِيلِ ٱلۡأَحۡلَٰمِ بِعَٰلِمِينَ ﴿44﴾

Transliteration: Qaloo adghathu ahlamin wama nahnu bitaweeli alahlami biAAalimeena

Translation: 44. «ሕልሞችህ ቅዠቶች ናቸው:: እኛም የሕልሞችን ፍች አዋቂዎች አይደለንም።» አሉት።

12:45

وَقَالَ ٱلَّذِي نَجَا مِنۡهُمَا وَٱدَّكَرَ بَعۡدَ أُمَّةٍ أَنَا۠ أُنَبِّئُكُم بِتَأۡوِيلِهِۦ فَأَرۡسِلُونِ ﴿45﴾

Transliteration: Waqala allathee naja minhuma waiddakara baAAda ommatin ana onabbiokum bitaweelihi faarsilooni

Translation: 45. ያም ከሁለቱ መካከል የዳነውና ከብዙ ጊዜ በኋላ ዩሱፍን ያስታወሰው ሰው «እኔ ፍቹን እነግራችኋለሁና ላኩኝ።» አለ።

12:46

يُوسُفُ أَيُّهَا ٱلصِّدِّيقُ أَفۡتِنَا فِي سَبۡعِ بَقَرَٰتٖ سِمَانٖ يَأۡكُلُهُنَّ سَبۡعٌ عِجَافٞ وَسَبۡعِ سُنۢبُلَٰتٍ خُضۡرٖ وَأُخَرَ يَابِسَٰتٖ لَّعَلِّيٓ أَرۡجِعُ إِلَى ٱلنَّاسِ لَعَلَّهُمۡ يَعۡلَمُونَ ﴿46﴾

Transliteration: Yoosufu ayyuha alssiddeequ aftina fee sabAAi baqaratin simanin yakuluhunna sabAAun AAijafun wasabAAi sunbulatin khudrin waokhara yabisatin laAAallee arjiAAu ila alnnasi laAAallahum yaAAlamoona

Translation: 46. «አንተ እውነተኛው ዩሱፍ ሆይ! ሰባትን የሰቡ ላሞች ሰባት ከሲታዎች ላሞች ሲበሏቸው፤ ሰባትን ለምለም ዘለላዎችም ሌሎች ሰባት ደረቆች በእነርሱ ላይ ስብርብር ሲያደርጉ ያየን ሰው ሕልም ፍች እስቲ ተችልን:: ያውቁ ዘንድ ወደ ሰዎቹ ልመለስ እከጅላለሁና።» አለው።

12:47

قَالَ تَزۡرَعُونَ سَبۡعَ سِنِينَ دَأَبٗا فَمَا حَصَدتُّمۡ فَذَرُوهُ فِي سُنۢبُلِهِۦٓ إِلَّا قَلِيلٗا مِّمَّا تَأۡكُلُونَ ﴿47﴾

Transliteration: Qala tazraAAoona sabAAa sineena daaban fama hasadtum fatharoohu fee sunbulihi illa qaleelan mimma takuloona

Translation: 47. እርሱም አለ: «ሰባትን የተከታተሉ ዓመታት ትዘራላችሁ ያጨዳችሁትንም ሁሉ ከምትበሉት ጥቂት በስተቀር በዘለላው ውስጥ ተውት።

12:48

ثُمَّ يَأۡتِي مِنۢ بَعۡدِ ذَٰلِكَ سَبۡعٞ شِدَادٞ يَأۡكُلۡنَ مَا قَدَّمۡتُمۡ لَهُنَّ إِلَّا قَلِيلٗا مِّمَّا تُحۡصِنُونَ ﴿48﴾

Transliteration: Thumma yatee min baAAdi thalika sabAAun shidadun yakulna ma qaddamtum lahunna illa qaleelan mimma tuhsinoona

Translation: 48. «ከዚያም ከነዚያ በኋላ ካደለባችሁት ጥቂት ሲቀር ለእነርሱ ያደለባችሁትን ሁሉ የሚበሉ ሰባት የችግር ዓመታት ይመጣሉ።

12:49

ثُمَّ يَأۡتِي مِنۢ بَعۡدِ ذَٰلِكَ عَامٞ فِيهِ يُغَاثُ ٱلنَّاسُ وَفِيهِ يَعۡصِرُونَ ﴿49﴾

Transliteration: Thumma yatee min baAAdi thalika AAamun feehi yughathu alnnasu wafeehi yaAAsiroona

Translation: 49. «ከዚያ ከእነዚያ በኋላ ሰዎቹ በእርሱ ዝናብ የሚያገኙበትና በእርሱም ወይንን የሚጨምቁበት ዓመት ይመጣል።»

12:50

وَقَالَ ٱلۡمَلِكُ ٱئۡتُونِي بِهِۦۖ فَلَمَّا جَآءَهُ ٱلرَّسُولُ قَالَ ٱرۡجِعۡ إِلَىٰ رَبِّكَ فَسۡـَٔلۡهُ مَا بَالُ ٱلنِّسۡوَةِ ٱلَّـٰتِي قَطَّعۡنَ أَيۡدِيَهُنَّۚ إِنَّ رَبِّي بِكَيۡدِهِنَّ عَلِيمٞ ﴿50﴾

Transliteration: Waqala almaliku itoonee bihi falamma jaahu alrrasoolu qala irjiAA ila rabbika faisalhu ma balu alnniswati allatee qattaAAna aydiyahunna inna rabbee bikaydihinna AAaleemun

Translation: 50. ንጉሡም «እርሱን አምጡልኝ።» አለ። መልእክተኛዉም ወደ ዩሱፍ በመጣ ጊዜ ዩሱፍ: «ወደ ጌታህ ተመለስና የእነዚያን እጆቻቸውን የቆረጡትን ሴቶች ሁኔታ ጠይቀው ጌታዬ ተንኮላቸውን አዋቂ ነውና።» አለው።

12:51

قَالَ مَا خَطۡبُكُنَّ إِذۡ رَٰوَدتُّنَّ يُوسُفَ عَن نَّفۡسِهِۦۚ قُلۡنَ حَٰشَ لِلَّهِ مَا عَلِمۡنَا عَلَيۡهِ مِن سُوٓءٖۚ قَالَتِ ٱمۡرَأَتُ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡـَٰٔنَ حَصۡحَصَ ٱلۡحَقُّ أَنَا۠ رَٰوَدتُّهُۥ عَن نَّفۡسِهِۦ وَإِنَّهُۥ لَمِنَ ٱلصَّـٰدِقِينَ ﴿51﴾

Transliteration: Qala ma khatbukunna ith rawadtunna yoosufa AAan nafsihi qulna hasha lillahi ma AAalimna AAalayhi min sooin qalati imraatu alAAazeezi alana hashasa alhaqqu ana rawadtuhu AAan nafsihi wainnahu lamina alssadiqeena

Translation: 51. ንጉሡም «ዩሱፍን ከነፍሱ ባባበላችሁት ጊዜ ነገራችሁ ምንድን ነው?» አላቸው። «ለአላህ ጥራት ይገባው በእርሱ ላይ ምንም መጥፎን ነገር አላወቅንም (አላየንም)።» አሉት። የዐዚዝ ሚስትም አለች: «አሁን እውነቱ ተገለጸ እኔ አባበልኩት እርሱም ከእውነተኞቹ ነው።

12:52

ذَٰلِكَ لِيَعۡلَمَ أَنِّي لَمۡ أَخُنۡهُ بِٱلۡغَيۡبِ وَأَنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي كَيۡدَ ٱلۡخَآئِنِينَ ﴿52﴾

Transliteration: Thalika liyaAAlama annee lam akhunhu bialghaybi waanna Allaha la yahdee kayda alkhaineena

Translation: 52. «ይህ ጌታዬ ሩቅ ሆኖ ሳለ ያልከዳሁት መሆኔንና አላህም የከዳተኞችን ተንኮል የማያቃና መሆኑን እንዲያውቅ ነው።»

12:53

وَمَآ أُبَرِّئُ نَفۡسِيٓۚ إِنَّ ٱلنَّفۡسَ لَأَمَّارَةُۢ بِٱلسُّوٓءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّيٓۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٞ رَّحِيمٞ ﴿53﴾

Transliteration: Wama obarrio nafsee inna alnnafsa laammaratun bialssooi illa ma rahima rabbee inna rabbee ghafoorun raheemun

Translation: 53. «ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም:: ነፍስ ሁሉ ጌታዬ ያዘነላት (የጠበቃት) ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና:: ጌታዬ በጣም መሐሪና አዛኝ ነው።»

12:54

وَقَالَ ٱلۡمَلِكُ ٱئۡتُونِي بِهِۦٓ أَسۡتَخۡلِصۡهُ لِنَفۡسِيۖ فَلَمَّا كَلَّمَهُۥ قَالَ إِنَّكَ ٱلۡيَوۡمَ لَدَيۡنَا مَكِينٌ أَمِينٞ ﴿54﴾

Transliteration: Waqala almaliku itoonee bihi astakhlishu linafsee falamma kallamahu qala innaka alyawma ladayna makeenun ameenun

Translation: 54. ንጉሡም «እርሱን አምጡልኝ ለራሴ የግሌ አደርገዋለሁና።» አለ። ባናገረዉም ጊዜ «አንተ ዛሬ እኛ ዘንድ ባለሟልና ታማኝ ነህ።» አለው።

12:55

قَالَ ٱجۡعَلۡنِي عَلَىٰ خَزَآئِنِ ٱلۡأَرۡضِۖ إِنِّي حَفِيظٌ عَلِيمٞ ﴿55﴾

Transliteration: Qala ijAAalnee AAala khazaini alardi innee hafeethun AAaleemun

Translation: 55. «በምድር ግምጃ ቤቶች ላይ ሹም አድርገኝ እኔ ጠባቂ አዋቂ ነኝና።» አለ።

12:56

وَكَذَٰلِكَ مَكَّنَّا لِيُوسُفَ فِي ٱلۡأَرۡضِ يَتَبَوَّأُ مِنۡهَا حَيۡثُ يَشَآءُۚ نُصِيبُ بِرَحۡمَتِنَا مَن نَّشَآءُۖ وَلَا نُضِيعُ أَجۡرَ ٱلۡمُحۡسِنِينَ ﴿56﴾

Transliteration: Wakathalika makanna liyoosufa fee alardi yatabawwao minha haythu yashao nuseebu birahmatina man nashao wala nudeeAAu ajra almuhsineena

Translation: 56. እንደዚሁም ለዩሱፍ በምድር ላይ ከእርሷ በፈለገው ስፍራ የሚሰፍር ሲሆን አስመቸነው:: በችሮታችን የምንሻውን ሰው እንለያለን። የበጎ ሠሪዎችንም ዋጋ አናጠፋም።

12:57

وَلَأَجۡرُ ٱلۡأٓخِرَةِ خَيۡرٞ لِّلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَكَانُواْ يَتَّقُونَ ﴿57﴾

Transliteration: Walaajru alakhirati khayrun lillatheena amanoo wakanoo yattaqoona

Translation: 57. የመጨረሻይቱም ዓለም ምንዳ ለእነዚያ ላመኑትና ይጠነቀቁ ለነበሩት የበለጠ ነው::

12:58

وَجَآءَ إِخۡوَةُ يُوسُفَ فَدَخَلُواْ عَلَيۡهِ فَعَرَفَهُمۡ وَهُمۡ لَهُۥ مُنكِرُونَ ﴿58﴾

Transliteration: Wajaa ikhwatu yoosufa fadakhaloo AAalayhi faAAarafahum wahum lahu munkiroona

Translation: 58. የዩሱፍ ወንድሞችም መጡ በእርሱም ላይ ገቡ:: እነርሱም እርሱን የሳቱት ሲሆኑ አወቃቸው::

12:59

وَلَمَّا جَهَّزَهُم بِجَهَازِهِمۡ قَالَ ٱئۡتُونِي بِأَخٖ لَّكُم مِّنۡ أَبِيكُمۡۚ أَلَا تَرَوۡنَ أَنِّيٓ أُوفِي ٱلۡكَيۡلَ وَأَنَا۠ خَيۡرُ ٱلۡمُنزِلِينَ ﴿59﴾

Transliteration: Walamma jahhazahum bijahazihim qala itoonee biakhin lakum min abeekum ala tarawna annee oofee alkayla waana khayru almunzileena

Translation: 59. ጉዳያቸውን ፈጽሞ ስንቃቸውንም ባዘጋጀላቸው ጊዜ አለ: «ከአባታችሁ በኩል የሆነውን ወንድማችሁን አምጡልኝ እኔ ከአስተናጋጆች ሁሉ በላጭ ስሆን ስፍርን የምሞላ መሆኔን አታዩምን?

12:60

فَإِن لَّمۡ تَأۡتُونِي بِهِۦ فَلَا كَيۡلَ لَكُمۡ عِندِي وَلَا تَقۡرَبُونِ ﴿60﴾

Transliteration: Fain lam tatoonee bihi fala kayla lakum AAindee wala taqrabooni

Translation: 60. «እርሱንም ባታመጡልኝ። እኔ ዘንድ ለእናንተ ስፍር የላችሁም:: አትቀርቡኝምም።» አለ

12:61

قَالُواْ سَنُرَٰوِدُ عَنۡهُ أَبَاهُ وَإِنَّا لَفَٰعِلُونَ ﴿61﴾

Transliteration: Qaloo sanurawidu AAanhu abahu wainna lafaAAiloona

Translation: 61. «ስለ እርሱ አባቱን በጥብቅ እንጠይቃለን፤ እኛም ይህንን በእርግጥ ሰሪዎች ነን።» አሉት።

12:62

وَقَالَ لِفِتۡيَٰنِهِ ٱجۡعَلُواْ بِضَٰعَتَهُمۡ فِي رِحَالِهِمۡ لَعَلَّهُمۡ يَعۡرِفُونَهَآ إِذَا ٱنقَلَبُوٓاْ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِمۡ لَعَلَّهُمۡ يَرۡجِعُونَ ﴿62﴾

Transliteration: Waqala lifityanihi ijAAaloo bidaAAatahum fee rihalihim laAAallahum yaAArifoonaha itha inqalaboo ila ahlihim laAAallahum yarjiAAoona

Translation: 62. ለአሽከሮቹም፡- «ወደ ቤተሰቦቻቸው በተመለሱ ጊዜ ሸቀጣቸውን (ገንዘባቸውን) ያውቋት ዘንድ በየጓዞቻቸው ውስጥ አድርጉላቸው ሊመለሱ ይከጀላልና።» አላቸው።

12:63

فَلَمَّا رَجَعُوٓاْ إِلَىٰٓ أَبِيهِمۡ قَالُواْ يَـٰٓأَبَانَا مُنِعَ مِنَّا ٱلۡكَيۡلُ فَأَرۡسِلۡ مَعَنَآ أَخَانَا نَكۡتَلۡ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ ﴿63﴾

Transliteration: Falamma rajaAAoo ila abeehim qaloo ya abana muniAAa minna alkaylu faarsil maAAana akhana naktal wainna lahu lahafithoona

Translation: 63. ወደ አባታቸዉም በተመለሱ ጊዜ፡- «አባታችን ሆይ! (ወንድማችንን እስከምንወስድ) ስፍር ከኛ ተከልክሏል። ስለዚህ ወንድማችንን ከእኛ ጋር ላከው፤ ይሰፈርልናልና እኛም ለእርሱ ጠባቂዎች ነን።» አሉ::

12:64

قَالَ هَلۡ ءَامَنُكُمۡ عَلَيۡهِ إِلَّا كَمَآ أَمِنتُكُمۡ عَلَىٰٓ أَخِيهِ مِن قَبۡلُ فَٱللَّهُ خَيۡرٌ حَٰفِظٗاۖ وَهُوَ أَرۡحَمُ ٱلرَّـٰحِمِينَ ﴿64﴾

Transliteration: Qala hal amanukum AAalayhi illa kama amintukum AAala akheehi min qablu faAllahu khayrun hafithan wahuwa arhamu alrrahimeena

Translation: 64. «ከአሁን በፊት በወንድሙ ላይ እንዳመንኳችሁ እንጂ በእርሱ ላይ አምናችኋለሁን? አላህም በጠባቂነት ከሁሉ የበለጠ ነው:: እርሱም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነው።» አላቸው።

12:65

وَلَمَّا فَتَحُواْ مَتَٰعَهُمۡ وَجَدُواْ بِضَٰعَتَهُمۡ رُدَّتۡ إِلَيۡهِمۡۖ قَالُواْ يَـٰٓأَبَانَا مَا نَبۡغِيۖ هَٰذِهِۦ بِضَٰعَتُنَا رُدَّتۡ إِلَيۡنَاۖ وَنَمِيرُ أَهۡلَنَا وَنَحۡفَظُ أَخَانَا وَنَزۡدَادُ كَيۡلَ بَعِيرٖۖ ذَٰلِكَ كَيۡلٞ يَسِيرٞ ﴿65﴾

Transliteration: Walamma fatahoo mataAAahum wajadoo bidaAAatahum ruddat ilayhim qaloo ya abana ma nabghee hathihi bidaAAatuna ruddat ilayna wanameeru ahlana wanahfathu akhana wanazdadu kayla baAAeerin thalika kaylun yaseerun

Translation: 65. እቃቸውንም በከፈቱ ጊዜ ሸቀጣቸውን ወደ እነርሱ ተመልሶ አገኙት። «አባታችን ሆይ! ምን እንፈልጋለን? ይህች ሸቀጣችን ናት ወደ እኛ ተመልሳልናለች እንረዳባታለን:: ለቤተሰቦቻችንም እንሸምታለን። ወንድማችንንም እንጠብቃለን:: የአንድ ግመልን ጭነትም እንጨምራለን:: ይህ በንጉሱ ላይ ቀላል ስፍር ነው።» አሉ።

12:66

قَالَ لَنۡ أُرۡسِلَهُۥ مَعَكُمۡ حَتَّىٰ تُؤۡتُونِ مَوۡثِقٗا مِّنَ ٱللَّهِ لَتَأۡتُنَّنِي بِهِۦٓ إِلَّآ أَن يُحَاطَ بِكُمۡۖ فَلَمَّآ ءَاتَوۡهُ مَوۡثِقَهُمۡ قَالَ ٱللَّهُ عَلَىٰ مَا نَقُولُ وَكِيلٞ ﴿66﴾

Transliteration: Qala lan orsilahu maAAakum hatta tutooni mawthiqan mina Allahi latatunnanee bihi illa an yuhata bikum falamma atawhu mawthiqahum qala Allahu AAala ma naqoolu wakeelun

Translation: 66. «ካልተከበባችሁ በስተቀር እርሱን በእርግጥ የምታመጡልኝ ለመሆናችሁ ከአላህ የሆነን ቃልኪዳን (መተማመኛ) እስከምትሰጡኝ ድረስ ከናንተ ጋር ፈጽሞ አልከዉም።» አላቸው። መተማመኛቸውንም በሰጡ ጊዜ «አላህ በምንለው ሁሉ ላይ ዋስ ነው።» አላቸው።

12:67

وَقَالَ يَٰبَنِيَّ لَا تَدۡخُلُواْ مِنۢ بَابٖ وَٰحِدٖ وَٱدۡخُلُواْ مِنۡ أَبۡوَٰبٖ مُّتَفَرِّقَةٖۖ وَمَآ أُغۡنِي عَنكُم مِّنَ ٱللَّهِ مِن شَيۡءٍۖ إِنِ ٱلۡحُكۡمُ إِلَّا لِلَّهِۖ عَلَيۡهِ تَوَكَّلۡتُۖ وَعَلَيۡهِ فَلۡيَتَوَكَّلِ ٱلۡمُتَوَكِّلُونَ ﴿67﴾

Transliteration: Waqala ya baniyya la tadkhuloo min babin wahidin waodkhuloo min abwabin mutafarriqatin wama oghnee AAankum mina Allahi min shayin ini alhukmu illa lillahi AAalayhi tawakkaltu waAAalayhi falyatawakkali almutawakkiloona

Translation: 67. አለም፡- «ልጆቼ ሆይ! በአንድ በር አትግቡ:: ግን በተለያዩ በሮች ግቡ:: ከአላህም ፍርድ በምንም አልጠቅማችሁም (አልመልስላችሁም)። ፍርዱ የአላህ እንጂ የሌላ አይደለም:: በእርሱ ላይ ብቻ ተመካሁ:: ተመኪዎችም ሁሉ በእርሱ ላይ ብቻ ይመኩ።»

12:68

وَلَمَّا دَخَلُواْ مِنۡ حَيۡثُ أَمَرَهُمۡ أَبُوهُم مَّا كَانَ يُغۡنِي عَنۡهُم مِّنَ ٱللَّهِ مِن شَيۡءٍ إِلَّا حَاجَةٗ فِي نَفۡسِ يَعۡقُوبَ قَضَىٰهَاۚ وَإِنَّهُۥ لَذُو عِلۡمٖ لِّمَا عَلَّمۡنَٰهُ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ ﴿68﴾

Transliteration: Walamma dakhaloo min haythu amarahum aboohum ma kana yughnee AAanhum mina Allahi min shayin illa hajatan fee nafsi yaAAqooba qadaha wainnahu lathoo AAilmin lima AAallamnahu walakinna akthara alnnasi la yaAAlamoona

Translation: 68. አባታቸው ካዘዛቸው ስፍራ በገቡ ጊዜ ከአላህ ፍርድ ምንም ነገር ከእነርሱ የሚከለክልላቸው አልነበረም:: ግን በየዕቁብ ነፍስ ውስጥ የነበረች ጉዳይ ናት:: ፈጸማት። እርሱም ስላሳወቅነው የእውቀት ባለቤት ነው። ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም::

12:69

وَلَمَّا دَخَلُواْ عَلَىٰ يُوسُفَ ءَاوَىٰٓ إِلَيۡهِ أَخَاهُۖ قَالَ إِنِّيٓ أَنَا۠ أَخُوكَ فَلَا تَبۡتَئِسۡ بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ ﴿69﴾

Transliteration: Walamma dakhaloo AAala yoosufa awa ilayhi akhahu qala innee ana akhooka fala tabtais bima kanoo yaAAmaloona

Translation: 69. በዩሱፍ ላይ በገቡ ጊዜም ወንድሙን ወደ እርሱ አስጠጋውና «እነሆ እኔ ወንድምህ ነኝ:: ይሰሩት በነበሩትም ሁሉ አትበሳጭ።» አለው።

12:70

فَلَمَّا جَهَّزَهُم بِجَهَازِهِمۡ جَعَلَ ٱلسِّقَايَةَ فِي رَحۡلِ أَخِيهِ ثُمَّ أَذَّنَ مُؤَذِّنٌ أَيَّتُهَا ٱلۡعِيرُ إِنَّكُمۡ لَسَٰرِقُونَ ﴿70﴾

Transliteration: Falamma jahhazahum bijahazihim jaAAala alssiqayata fee rahli akheehi thumma aththana muaththinun ayyatuha alAAeeru innakum lasariqoona

Translation: 70. እቃቸውን ባዘጋጀላቸው ጊዜ ዋንጫይቱን በወንድሙ እቃ ውስጥ አደረገና ከዚያ «እናንተ ባለ ግመሎች ሆይ! እናንተ በእርግጥ ሌቦች ናችሁ።» ሲል ጠሪ ተጣራ።

12:71

قَالُواْ وَأَقۡبَلُواْ عَلَيۡهِم مَّاذَا تَفۡقِدُونَ ﴿71﴾

Transliteration: Qaloo waaqbaloo AAalayhim matha tafqidoona

Translation: 71. ወደ እነርሱ ዞረዉም: «ምንድን ጠፋችሁ?» አሉ።

12:72

قَالُواْ نَفۡقِدُ صُوَاعَ ٱلۡمَلِكِ وَلِمَن جَآءَ بِهِۦ حِمۡلُ بَعِيرٖ وَأَنَا۠ بِهِۦ زَعِيمٞ ﴿72﴾

Transliteration: Qaloo nafqidu suwaAAa almaliki waliman jaa bihi himlu baAAeerin waana bihi zaAAeemun

Translation: 72. «የንጉሱ መስፈሪያ ጠፍቶናል እርሱንም ላመጣ ሰው የአንድ ግመል ጭነት አለው። እኔም በእርሱ ተያዥ ነኝ።» አለ።

12:73

قَالُواْ تَٱللَّهِ لَقَدۡ عَلِمۡتُم مَّا جِئۡنَا لِنُفۡسِدَ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا كُنَّا سَٰرِقِينَ ﴿73﴾

Transliteration: Qaloo taAllahi laqad AAalimtum ma jina linufsida fee alardi wama kunna sariqeena

Translation: 73. «በአላህ እንምላለን! በምድር ላይ ለማጥፋት እንዳልመጣን በእርግጥ አውቃችኋል ሌቦችም አልነበርንም።» አሉ።

12:74

قَالُواْ فَمَا جَزَـٰٓؤُهُۥٓ إِن كُنتُمۡ كَٰذِبِينَ ﴿74﴾

Transliteration: Qaloo fama jazaohu in kuntum kathibeena

Translation: 74. «ውሸታሞች ብትሆኑስ ቅጣቱ ምንድን ነው?» አሏቸው።

12:75

قَالُواْ جَزَـٰٓؤُهُۥ مَن وُجِدَ فِي رَحۡلِهِۦ فَهُوَ جَزَـٰٓؤُهُۥۚ كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلظَّـٰلِمِينَ ﴿75﴾

Transliteration: Qaloo jazaohu man wujida fee rahlihi fahuwa jazaohu kathalika najzee alththalimeena

Translation: 75. «ቅጣቱ በየዕቁብ ሕግ እቃው በጓዙ ውስጥ የተገኘበት ሰው ራሱ ባሪያ ተደርጎ መውሰድ ነው። እርሱም ቅጣቱ ነው:: ልክ እንደዚሁ በደለኞችን እንቀጣለን።» አሉ።

12:76

فَبَدَأَ بِأَوۡعِيَتِهِمۡ قَبۡلَ وِعَآءِ أَخِيهِ ثُمَّ ٱسۡتَخۡرَجَهَا مِن وِعَآءِ أَخِيهِۚ كَذَٰلِكَ كِدۡنَا لِيُوسُفَۖ مَا كَانَ لِيَأۡخُذَ أَخَاهُ فِي دِينِ ٱلۡمَلِكِ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُۚ نَرۡفَعُ دَرَجَٰتٖ مَّن نَّشَآءُۗ وَفَوۡقَ كُلِّ ذِي عِلۡمٍ عَلِيمٞ ﴿76﴾

Transliteration: Fabadaa biawAAiyatihim qabla wiAAai akheehi thumma istakhrajaha min wiAAai akheehi kathalika kidna liyoosufa ma kana liyakhutha akhahu fee deeni almaliki illa an yashaa Allahu narfaAAu darajatin man nashao wafawqa kulli thee AAilmin AAaleemun

Translation: 76. ምርመራውን ከወንድሙ እቃ በፊትም በእቃዎቻቸው ጀመረ:: ከዚያ ዋንጫይቱን ከወንድሙ እቃ ውስጥ አወጣት። ልክ እንደዚሁ ለዩሱፍ ብልሃትን አስተማርነው:: አላህ ባልሻ ኖሮ በንጉሱ ሕግ ወንድሙን ሊይዝ አይገባዉም ነበር:: የምንሻውን ሰው በደረጃዎች ከፍ እናደርጋለን። ከእውቀት ባለቤቶች ሁሉ በላይም አዋቂ አለ::

12:77

قَالُوٓاْ إِن يَسۡرِقۡ فَقَدۡ سَرَقَ أَخٞ لَّهُۥ مِن قَبۡلُۚ فَأَسَرَّهَا يُوسُفُ فِي نَفۡسِهِۦ وَلَمۡ يُبۡدِهَا لَهُمۡۚ قَالَ أَنتُمۡ شَرّٞ مَّكَانٗاۖ وَٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِمَا تَصِفُونَ ﴿77﴾

Transliteration: Qaloo in yasriq faqad saraqa akhun lahu min qablu faasarraha yoosufu fee nafsihi walam yubdiha lahum qala antum sharrun makanan waAllahu aAAlamu bima tasifoona

Translation: 77. «እርሱ ቢሰርቅ ከአሁን በፊት የእርሱው ወንድም በእርግጥ ሰርቋል።» አሉ። ዩሱፍም ይህችን (አስቀያሚ ንግግር) በነፍሱ ውስጥ ደበቃት:: ለእነርሱም አልገለጣትም። በልቡ «እናንተ ሥራችሁ የከፋ ነው:: አላህ የምትሉትን ሁሉ ይበልጥ አዋቂ ነው።» አለ።

12:78

قَالُواْ يَـٰٓأَيُّهَا ٱلۡعَزِيزُ إِنَّ لَهُۥٓ أَبٗا شَيۡخٗا كَبِيرٗا فَخُذۡ أَحَدَنَا مَكَانَهُۥٓۖ إِنَّا نَرَىٰكَ مِنَ ٱلۡمُحۡسِنِينَ ﴿78﴾

Transliteration: Qaloo ya ayyuha alAAazeezu inna lahu aban shaykhan kabeeran fakhuth ahadana makanahu inna naraka mina almuhsineena

Translation: 78. «አንተ የተከበርከው ሆይ! ለእርሱ በእርግጥ ታላቅ ሽማግሌ አባት አለው:: ስለዚህ በእርሱ ስፍራ አንደኛችንን ያዝ:: እኛ ከመልካም ሠሪዎች ሆነህ እናይሃለንና።» አሉት።

12:79

قَالَ مَعَاذَ ٱللَّهِ أَن نَّأۡخُذَ إِلَّا مَن وَجَدۡنَا مَتَٰعَنَا عِندَهُۥٓ إِنَّآ إِذٗا لَّظَٰلِمُونَ ﴿79﴾

Transliteration: Qala maAAatha Allahi an nakhutha illa man wajadna mataAAana AAindahu inna ithan lathalimoona

Translation: 79. «ዕቃችንን እርሱ ዘንድ ያገኘንበትን ሰው እንጂ ሌላን ከመያዝ በአላህ እንጠበቃለን:: እኛ ያን ባደረግን ጊዜ በእርግጥ በዳዮች ነን።» አለ።

12:80

فَلَمَّا ٱسۡتَيۡـَٔسُواْ مِنۡهُ خَلَصُواْ نَجِيّٗاۖ قَالَ كَبِيرُهُمۡ أَلَمۡ تَعۡلَمُوٓاْ أَنَّ أَبَاكُمۡ قَدۡ أَخَذَ عَلَيۡكُم مَّوۡثِقٗا مِّنَ ٱللَّهِ وَمِن قَبۡلُ مَا فَرَّطتُمۡ فِي يُوسُفَۖ فَلَنۡ أَبۡرَحَ ٱلۡأَرۡضَ حَتَّىٰ يَأۡذَنَ لِيٓ أَبِيٓ أَوۡ يَحۡكُمَ ٱللَّهُ لِيۖ وَهُوَ خَيۡرُ ٱلۡحَٰكِمِينَ ﴿80﴾

Transliteration: Falamma istayasoo minhu khalasoo najiyyan qala kabeeruhum alam taAAlamoo anna abakum qad akhatha AAalaykum mawthiqan mina Allahi wamin qablu ma farrattum fee yoosufa falan abraha alarda hatta yathana lee abee aw yahkuma Allahu lee wahuwa khayru alhakimeena

Translation: 80. ከእርሱም ተስፋን በቆረጡ ጊዜ የሚመካከሩ ሆነው ገለል አሉ:: ታላቃቸውም አለ: «አባታችሁ በእናንተ ላይ ከአላህ የሆነን መተማመኛ ቃል ኪዳን በእርግጥ የያዘባችሁ መሆኑንና ከዚህም በፊት በዩሱፍ ላይ ግፍ የሠራችሁትን አታውቁምን? ስለዚህ አባቴ ለእኔ እስከሚፈቅድልኝ ወይም አላህ ለእኔ እስከሚፈርድልኝ ድረስ የምስርን (የግብጽን) ምድር አልለይም:: እርሱ ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው።

12:81

ٱرۡجِعُوٓاْ إِلَىٰٓ أَبِيكُمۡ فَقُولُواْ يَـٰٓأَبَانَآ إِنَّ ٱبۡنَكَ سَرَقَ وَمَا شَهِدۡنَآ إِلَّا بِمَا عَلِمۡنَا وَمَا كُنَّا لِلۡغَيۡبِ حَٰفِظِينَ ﴿81﴾

Transliteration: IrjiAAoo ila abeekum faqooloo ya abana inna ibnaka saraqa wama shahidna illa bima AAalimna wama kunna lilghaybi hafitheena

Translation: 81. «ወደ አባታችሁ ተመለሱ:: በሉትም: ‹አባታችን ሆይ ልጅህ ሰረቀ፤ ባወቅነዉም ነገር እንጂ አልመሰከርንም:: ሩቁንም ነገር ምስጢሩን አዋቂዎች አልነበርንም።

12:82

وَسۡـَٔلِ ٱلۡقَرۡيَةَ ٱلَّتِي كُنَّا فِيهَا وَٱلۡعِيرَ ٱلَّتِيٓ أَقۡبَلۡنَا فِيهَاۖ وَإِنَّا لَصَٰدِقُونَ ﴿82﴾

Transliteration: Waisali alqaryata allatee kunna feeha waalAAeera allatee aqbalna feeha wainna lasadiqoona

Translation: 82. «‹ያችንም በውስጧ የነበርንባትን ከተማ ያችንም በውስጧ የመጣነውን ባለ ግመል ጓድ ጠይቅ እኛም በእርግጥ እውነተኞች ነን።›»

12:83

قَالَ بَلۡ سَوَّلَتۡ لَكُمۡ أَنفُسُكُمۡ أَمۡرٗاۖ فَصَبۡرٞ جَمِيلٌۖ عَسَى ٱللَّهُ أَن يَأۡتِيَنِي بِهِمۡ جَمِيعًاۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡعَلِيمُ ٱلۡحَكِيمُ ﴿83﴾

Transliteration: Qala bal sawwalat lakum anfusukum amran fasabrun jameelun AAasa Allahu an yatiyanee bihim jameeAAan innahu huwa alAAaleemu alhakeemu

Translation: 83. ያዕቁብም፡- «አይደለም። ነፍሶቻችሁ አንዳች ነገርን ለእናንተ ሸለሙላቸሁና ሠራችሁት እንጂ:: እናም መልካም ትዕግስት ማድረግ አለብኝ:: እነርሱን ሁሉንም የተሰበሰቡ ሆነው አላህ ሊያመጣልኝ ይከጀላል:: እነሆ እርሱ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።» አላቸው።

12:84

وَتَوَلَّىٰ عَنۡهُمۡ وَقَالَ يَـٰٓأَسَفَىٰ عَلَىٰ يُوسُفَ وَٱبۡيَضَّتۡ عَيۡنَاهُ مِنَ ٱلۡحُزۡنِ فَهُوَ كَظِيمٞ ﴿84﴾

Transliteration: Watawalla AAanhum waqala ya asafa AAala yoosufa waibyaddat AAaynahu mina alhuzni fahuwa katheemun

Translation: 84. ከነርሱም ዞር አለና፡- «በዩሱፍ ላይ ዋ ሐዘኔ!» አለ:: ዓይኖቹም ከሐዘን የተነሳ ነጡ:: እርሱም በትካዜ የተሞላ ነው።

12:85

قَالُواْ تَٱللَّهِ تَفۡتَؤُاْ تَذۡكُرُ يُوسُفَ حَتَّىٰ تَكُونَ حَرَضًا أَوۡ تَكُونَ مِنَ ٱلۡهَٰلِكِينَ ﴿85﴾

Transliteration: Qaloo taAllahi taftao tathkuru yoosufa hatta takoona haradan aw takoona mina alhalikeena

Translation: 85. እነርሱም፡- «በአላህ እንምላለን! ለጥፋት የቀረብክ እስከምትሆን ወይም ከጠፊዎቹ እስከምትሆን ድረስ ዩሱፍን ከማውሳት አትወገድም።» አሉ።

12:86

قَالَ إِنَّمَآ أَشۡكُواْ بَثِّي وَحُزۡنِيٓ إِلَى ٱللَّهِ وَأَعۡلَمُ مِنَ ٱللَّهِ مَا لَا تَعۡلَمُونَ ﴿86﴾

Transliteration: Qala innama ashkoo baththee wahuznee ila Allahi waaAAlamu mina Allahi ma la taAAlamoona

Translation: 86. «ጭንቀቴንና ሐዘኔን የማሰሙተው ወደ አላህ ብቻ ነው። ከአላህ በኩል የማታውቁትን ነገር እኔ አውቃለሁና።» አላቸው።

12:87

يَٰبَنِيَّ ٱذۡهَبُواْ فَتَحَسَّسُواْ مِن يُوسُفَ وَأَخِيهِ وَلَا تَاْيۡـَٔسُواْ مِن رَّوۡحِ ٱللَّهِۖ إِنَّهُۥ لَا يَاْيۡـَٔسُ مِن رَّوۡحِ ٱللَّهِ إِلَّا ٱلۡقَوۡمُ ٱلۡكَٰفِرُونَ ﴿87﴾

Transliteration: Ya baniyya ithhaboo fatahassasoo min yoosufa waakheehi wala tayasoo min rawhi Allahi innahu la yayasu min rawhi Allahi illa alqawmu alkafiroona

Translation: 87. «ልጆቼ ሆይ! ሂዱ ከዩሱፍና ከወንድሙም ወሬ ተመራመሩ:: ከአላህም እዝነት ተስፋ አትቁረጡ:: እነሆ ከአላህ እዝነት ከሓዲያን ህዝቦች እንጂ ማንም ተስፋ አይቆርጥም።» አለ።

12:88

فَلَمَّا دَخَلُواْ عَلَيۡهِ قَالُواْ يَـٰٓأَيُّهَا ٱلۡعَزِيزُ مَسَّنَا وَأَهۡلَنَا ٱلضُّرُّ وَجِئۡنَا بِبِضَٰعَةٖ مُّزۡجَىٰةٖ فَأَوۡفِ لَنَا ٱلۡكَيۡلَ وَتَصَدَّقۡ عَلَيۡنَآۖ إِنَّ ٱللَّهَ يَجۡزِي ٱلۡمُتَصَدِّقِينَ ﴿88﴾

Transliteration: Falamma dakhaloo AAalayhi qaloo ya ayyuha alAAazeezu massana waahlana alddurru wajina bibidaAAatin muzjatin faawfi lana alkayla watasaddaq AAalayna inna Allaha yajzee almutasaddiqeena

Translation: 88. በእርሱም ላይ በገቡ ጊዜ: «አንተ የተከበርከው ሆይ! እኛንም ቤተሰቦቻችንንም ጉዳት ደረሰብን። እርካሽ ሸቀጥም ይዘን መጥተናል:: ስፍርንም ለእኛ ሙላልን:: በእኛም ላይ መጽውት:: አላህ መጽዋቾችን ይመነዳልና።» አሉት።

12:89

قَالَ هَلۡ عَلِمۡتُم مَّا فَعَلۡتُم بِيُوسُفَ وَأَخِيهِ إِذۡ أَنتُمۡ جَٰهِلُونَ ﴿89﴾

Transliteration: Qala hal AAalimtum ma faAAaltum biyoosufa waakheehi ith antum jahiloona

Translation: 89. «እናንተ የማታውቁ በነበራችሁ ጊዜ በዩሱፍና በወንድሙ ላይ የሠራችሁትን ግፍ አወቃችሁን?» አላቸው።

12:90

قَالُوٓاْ أَءِنَّكَ لَأَنتَ يُوسُفُۖ قَالَ أَنَا۠ يُوسُفُ وَهَٰذَآ أَخِيۖ قَدۡ مَنَّ ٱللَّهُ عَلَيۡنَآۖ إِنَّهُۥ مَن يَتَّقِ وَيَصۡبِرۡ فَإِنَّ ٱللَّهَ لَا يُضِيعُ أَجۡرَ ٱلۡمُحۡسِنِينَ ﴿90﴾

Transliteration: Qaloo ainnaka laanta yoosufa qala ana yoosufu wahatha akhee qad manna Allahu AAalayna innahu man yattaqi wayasbir fainna Allaha la yudeeAAu ajra almuhsineena

Translation: 90. «አንተ በእርግጥ አንተ ዩሱፍ ነህን?» አሉት። «አዎ እኔ በትክክል ዩሱፍ ነኝ:: ይህም ወንድሜ ነው:: አላህ በእኛ ላይ በእርግጥ ለገሰልን:: እነሆ የሚጠነቀቅና የሚታገስ ሰው አላህ ይክሰዋል:: አላህ የበጎ አድራጊዎችን ዋጋ አያጠፋምና።» አለ።

12:91

قَالُواْ تَٱللَّهِ لَقَدۡ ءَاثَرَكَ ٱللَّهُ عَلَيۡنَا وَإِن كُنَّا لَخَٰطِـِٔينَ ﴿91﴾

Transliteration: Qaloo taAllahi laqad atharaka Allahu AAalayna wain kunna lakhatieena

Translation: 91. «በአላህ እንምላለን! አላህ በእኛ ላይ በእርግጥ አበለጠህ፤ እኛም በእርግጥ አጥፊዎች ነበርን።» አሉ::

12:92

قَالَ لَا تَثۡرِيبَ عَلَيۡكُمُ ٱلۡيَوۡمَۖ يَغۡفِرُ ٱللَّهُ لَكُمۡۖ وَهُوَ أَرۡحَمُ ٱلرَّـٰحِمِينَ ﴿92﴾

Transliteration: Qala la tathreeba AAalaykumu alyawma yaghfiru Allahu lakum wahuwa arhamu alrrahimeena

Translation: 92. እርሱም አላቸው: «ዛሬ በእናንተ ላይ ምንም ወቀሳ የለባችሁም። አላህ ለእናንተ ይምራል። እርሱም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነውና።»

12:93

ٱذۡهَبُواْ بِقَمِيصِي هَٰذَا فَأَلۡقُوهُ عَلَىٰ وَجۡهِ أَبِي يَأۡتِ بَصِيرٗا وَأۡتُونِي بِأَهۡلِكُمۡ أَجۡمَعِينَ ﴿93﴾

Transliteration: Ithhaboo biqameesee hatha faalqoohu AAala wajhi abee yati baseeran watoonee biahlikum ajmaAAeena

Translation: 93. «ይህንን ቀሚሴን ይዛችሁ ሂዱ:: በአባቴ ፊትም ጣሉት:: የሚያይ ሆኖ ይመጣልና:: ቤተሰቦቻችሁንም በሙሉ ሰብስባችሁ አምጡልኝ።» አላቸው።

12:94

وَلَمَّا فَصَلَتِ ٱلۡعِيرُ قَالَ أَبُوهُمۡ إِنِّي لَأَجِدُ رِيحَ يُوسُفَۖ لَوۡلَآ أَن تُفَنِّدُونِ ﴿94﴾

Transliteration: Walamma fasalati alAAeeru qala aboohum innee laajidu reeha yoosufa lawla an tufannidooni

Translation: 94. ግመል ጫኞችም ከግብጽ በወጡ ጊዜ አባታቸው «እኔ የዩሱፍን ሽታ በእርግጥ አገኛለሁ:: ባታቄሉኝ ኖሮ ታምኑኝ ነበር።» አለ።

12:95

قَالُواْ تَٱللَّهِ إِنَّكَ لَفِي ضَلَٰلِكَ ٱلۡقَدِيمِ ﴿95﴾

Transliteration: Qaloo taAllahi innaka lafee dalalika alqadeemi

Translation: 95. «በአላህ እንምላለን! አንተ በእርግጥ እስካሁንም በዚያው በቀድሞው ስህተትህ ውስጥ ነህ።» አሉት።

12:96

فَلَمَّآ أَن جَآءَ ٱلۡبَشِيرُ أَلۡقَىٰهُ عَلَىٰ وَجۡهِهِۦ فَٱرۡتَدَّ بَصِيرٗاۖ قَالَ أَلَمۡ أَقُل لَّكُمۡ إِنِّيٓ أَعۡلَمُ مِنَ ٱللَّهِ مَا لَا تَعۡلَمُونَ ﴿96﴾

Transliteration: Falamma an jaa albasheeru alqahu AAala wajhihi fairtadda baseeran qala alam aqul lakum innee aAAlamu mina Allahi ma la taAAlamoona

Translation: 96. አብሳሪዉም በመጣ ጊዜ ቀሚሱን በፊቱ ላይ ጣለው፤ ወዲያዉም የሚያይ ሆነ:: «እኔ ለእናንተ ከአላህ በኩል የማታውቁትን አውቃለሁ አላልኳችሁም ነበርን?» አላቸው።

12:97

قَالُواْ يَـٰٓأَبَانَا ٱسۡتَغۡفِرۡ لَنَا ذُنُوبَنَآ إِنَّا كُنَّا خَٰطِـِٔينَ ﴿97﴾

Transliteration: Qaloo ya abana istaghfir lana thunoobana inna kunna khatieena

Translation: 97. «አባታችን ሆይ! ለኃጢያቶቻችን ምሕረትን ለምንልን:: እኛ ጥፋተኞች ነበርንና።» አሉ::

12:98

قَالَ سَوۡفَ أَسۡتَغۡفِرُ لَكُمۡ رَبِّيٓۖ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ ﴿98﴾

Transliteration: Qala sawfa astaghfiru lakum rabbee innahu huwa alghafooru alrraheemu

Translation: 98. «ወደ ፊት ለእናንተ ጌታዬን ምሕረትን እለምንላችኋለሁ:: እነሆ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና።» አላቸው።

12:99

فَلَمَّا دَخَلُواْ عَلَىٰ يُوسُفَ ءَاوَىٰٓ إِلَيۡهِ أَبَوَيۡهِ وَقَالَ ٱدۡخُلُواْ مِصۡرَ إِن شَآءَ ٱللَّهُ ءَامِنِينَ ﴿99﴾

Transliteration: Falamma dakhaloo AAala yoosufa awa ilayhi abawayhi waqala odkhuloo misra in shaa Allahu amineena

Translation: 99. በዩሱፍ ላይም በገቡ ጊዜ ወላጆቹን ወደ እርሱ አስጠጋቸው፤ «በአላህም ፈቃድ ጥብቆች ስትሆኑ ሚስርን (ግብጽ) ግቡ።» አላቸው::

12:100

وَرَفَعَ أَبَوَيۡهِ عَلَى ٱلۡعَرۡشِ وَخَرُّواْ لَهُۥ سُجَّدٗاۖ وَقَالَ يَـٰٓأَبَتِ هَٰذَا تَأۡوِيلُ رُءۡيَٰيَ مِن قَبۡلُ قَدۡ جَعَلَهَا رَبِّي حَقّٗاۖ وَقَدۡ أَحۡسَنَ بِيٓ إِذۡ أَخۡرَجَنِي مِنَ ٱلسِّجۡنِ وَجَآءَ بِكُم مِّنَ ٱلۡبَدۡوِ مِنۢ بَعۡدِ أَن نَّزَغَ ٱلشَّيۡطَٰنُ بَيۡنِي وَبَيۡنَ إِخۡوَتِيٓۚ إِنَّ رَبِّي لَطِيفٞ لِّمَا يَشَآءُۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡعَلِيمُ ٱلۡحَكِيمُ ﴿100﴾

Transliteration: WarafaAAa abawayhi AAala alAAarshi wakharroo lahu sujjadan waqala ya abati hatha taweelu ruyaya min qablu qad jaAAalaha rabbee haqqan waqad ahsana bee ith akhrajanee mina alssijni wajaa bikum mina albadwi min baAAdi an nazagha alshshaytanu baynee wabayna ikhwatee inna rabbee lateefun lima yashao innahu huwa alAAaleemu alhakeemu

Translation: 100. ወላጆቹንም በዙፋኑ ላይ አወጣቸው ለርሱም ሰጋጆች ሆነው ወረዱለት። «አባቴም ሆይ! ይህ ፊት ያየኋት ሕልሜ ፍች ነው፡፡ ጌታዬ በእርግጥ እውነት አደረጋት፡፡ ከወህኒ ቤትም ባወጣኝና ሰይጣንም በእኔና በወንድሞቼ መካከል ካበላሸ በኋላ እናንተን ከገጠር ባመጣችሁ ጊዜ በእርግጥ ለእኔ መልካም ዋለልኝ:: ጌታዬ ለሚሻው ነገር እዝነቱ ረቂቅ ነው:: እነሆ እርሱ አዋቂውና ጥበበኛው ነው።» አለ።

12:101

رَبِّ قَدۡ ءَاتَيۡتَنِي مِنَ ٱلۡمُلۡكِ وَعَلَّمۡتَنِي مِن تَأۡوِيلِ ٱلۡأَحَادِيثِۚ فَاطِرَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ أَنتَ وَلِيِّۦ فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِۖ تَوَفَّنِي مُسۡلِمٗا وَأَلۡحِقۡنِي بِٱلصَّـٰلِحِينَ ﴿101﴾

Transliteration: Rabbi qad ataytanee mina almulki waAAallamtanee min taweeli alahadeethi fatira alssamawati waalardi anta waliyyee fee alddunya waalakhirati tawaffanee musliman waalhiqnee bialssaliheena

Translation: 101. «ጌታዬ ሆይ! ከንግስና በእርግጥ ሰጠኸኝ:: ከህልሞችም ፍች አስተማርከኝ:: የሰማያትና የምድር ፈጣሪ ሆይ! አንተ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም ረዳቴ ነህ:: ሙስሊም ሆኜ ግደለኝ:: ወደ መልካም ሰሪዎችም አስጠጋኝ።» አለ።

12:102

ذَٰلِكَ مِنۡ أَنۢبَآءِ ٱلۡغَيۡبِ نُوحِيهِ إِلَيۡكَۖ وَمَا كُنتَ لَدَيۡهِمۡ إِذۡ أَجۡمَعُوٓاْ أَمۡرَهُمۡ وَهُمۡ يَمۡكُرُونَ ﴿102﴾

Transliteration: Thalika min anbai alghaybi nooheehi ilayka wama kunta ladayhim ith ajmaAAoo amrahum wahum yamkuroona

Translation: 102. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ወደ አንተ የምናወርደው ሲሆን ከሩቅ ወሬዎች ነው:: አንተም እነርሱ በዩሱፍ ላይ የሚያሴሩ ሆነው ነገራቸውን በቆረጡ ጊዜ እነርሱ ዘንድ አብረህ አልነበርክም::

12:103

وَمَآ أَكۡثَرُ ٱلنَّاسِ وَلَوۡ حَرَصۡتَ بِمُؤۡمِنِينَ ﴿103﴾

Transliteration: Wama aktharu alnnasi walaw harasta bimumineena

Translation: 103. አብዛኛዎቹ ሰዎች ለማመናቸው ብትጓጓም የሚያምኑ አይደሉም::

12:104

وَمَا تَسۡـَٔلُهُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٍۚ إِنۡ هُوَ إِلَّا ذِكۡرٞ لِّلۡعَٰلَمِينَ ﴿104﴾

Transliteration: Wama tasaluhum AAalayhi min ajrin in huwa illa thikrun lilAAalameena

Translation: 104. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በቁርኣን ላይ ምንም ዋጋን አትጠይቃቸዉም:: እርሱ ለዓለማት ግሳጼ እንጂ ሌላ አይደለም::

12:105

وَكَأَيِّن مِّنۡ ءَايَةٖ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ يَمُرُّونَ عَلَيۡهَا وَهُمۡ عَنۡهَا مُعۡرِضُونَ ﴿105﴾

Transliteration: Wakaayyin min ayatin fee alssamawati waalardi yamurroona AAalayha wahum AAanha muAAridoona

Translation: 105. በሰማያትና በምድር ካለችው ምልክት ብዙይቱ እነርሱ ከእርሷ ዘንጊዎች ሆነው በእርሷ ላይ ያልፋሉ::

12:106

وَمَا يُؤۡمِنُ أَكۡثَرُهُم بِٱللَّهِ إِلَّا وَهُم مُّشۡرِكُونَ ﴿106﴾

Transliteration: Wama yuminu aktharuhum biAllahi illa wahum mushrikoona

Translation: 106. አብዛኞቻቸዉም እነርሱ አጋሪዎች ሆነው እንጂ በአላህ አያምኑም::

12:107

أَفَأَمِنُوٓاْ أَن تَأۡتِيَهُمۡ غَٰشِيَةٞ مِّنۡ عَذَابِ ٱللَّهِ أَوۡ تَأۡتِيَهُمُ ٱلسَّاعَةُ بَغۡتَةٗ وَهُمۡ لَا يَشۡعُرُونَ ﴿107﴾

Transliteration: Afaaminoo an tatiyahum ghashiyatun min AAathabi Allahi aw tatiyahumu alssaAAatu baghtatan wahum la yashAAuroona

Translation: 107. ከአላህ ቅጣት ሽፋኝ አደጋ የምትመጣባቸው ወይም ሰዓቲቱ እነርሱ የማያውቁ ሲሆኑ በድንገት የምትመጣባቸው መሆኑዋን አይፈሩምን?

12:108

قُلۡ هَٰذِهِۦ سَبِيلِيٓ أَدۡعُوٓاْ إِلَى ٱللَّهِۚ عَلَىٰ بَصِيرَةٍ أَنَا۠ وَمَنِ ٱتَّبَعَنِيۖ وَسُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ وَمَآ أَنَا۠ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ ﴿108﴾

Transliteration: Qul hathihi sabeelee adAAoo ila Allahi AAala baseeratin ana wamani ittabaAAanee wasubhana Allahi wama ana mina almushrikeena

Translation: 108. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ይህ መንገዴ ነው:: ወደ አላህ እጠራለሁ:: እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን:: ጥራትም ለአላህ ብቻ ይገባው:: እኔም ከአጋሪዎች አይደለሁም።» በል::

12:109

وَمَآ أَرۡسَلۡنَا مِن قَبۡلِكَ إِلَّا رِجَالٗا نُّوحِيٓ إِلَيۡهِم مِّنۡ أَهۡلِ ٱلۡقُرَىٰٓۗ أَفَلَمۡ يَسِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَيَنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۗ وَلَدَارُ ٱلۡأٓخِرَةِ خَيۡرٞ لِّلَّذِينَ ٱتَّقَوۡاْۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ ﴿109﴾

Transliteration: Wama arsalna min qablika illa rijalan noohee ilayhim min ahli alqura afalam yaseeroo fee alardi fayanthuroo kayfa kana AAaqibatu allatheena min qablihim waladaru alakhirati khayrun lillatheena ittaqaw afala taAAqiloona

Translation: 109. ካንተ በፊትም ከከተሞች ሰዎች ወደነርሱ ራዕይ የምናወርድላቸው የሆኑን ወንዶችን እንጂ አላክንም:: በምድር ላይ አይሄዱምና የእነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ሰዎች መጨረሻ እንዴት እንደሆነ አይመለከቱምን? የአኺራ ደስታ ለተጠነቀቁት ሰዎች ሁሉ በእርግጥ የተሻለች ናት:: አታውቁምን?

12:110

حَتَّىٰٓ إِذَا ٱسۡتَيۡـَٔسَ ٱلرُّسُلُ وَظَنُّوٓاْ أَنَّهُمۡ قَدۡ كُذِبُواْ جَآءَهُمۡ نَصۡرُنَا فَنُجِّيَ مَن نَّشَآءُۖ وَلَا يُرَدُّ بَأۡسُنَا عَنِ ٱلۡقَوۡمِ ٱلۡمُجۡرِمِينَ ﴿110﴾

Transliteration: Hatta itha istayasa alrrusulu wathannoo annahum qad kuthiboo jaahum nasruna fanujjiya man nashao wala yuraddu basuna AAani alqawmi almujrimeena

Translation: 110. መልዕክተኞች ተስፋ በቆረጡና እነርሱ በእርግጥ የተዋሹ መሆናቸውን በተጠራጠሩ ጊዜ እርዳታችን መጣላቸው:: ከዚያ እኛ የምንፈልገው ሰው እንዲድን ተደረገ:: ቅጣታችንም ከአመፀኞቹ ህዝቦች ላይ አይመለስም::

12:111

لَقَدۡ كَانَ فِي قَصَصِهِمۡ عِبۡرَةٞ لِّأُوْلِي ٱلۡأَلۡبَٰبِۗ مَا كَانَ حَدِيثٗا يُفۡتَرَىٰ وَلَٰكِن تَصۡدِيقَ ٱلَّذِي بَيۡنَ يَدَيۡهِ وَتَفۡصِيلَ كُلِّ شَيۡءٖ وَهُدٗى وَرَحۡمَةٗ لِّقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ ﴿111﴾

Transliteration: Laqad kana fee qasasihim AAibratun liolee alalbabi ma kana hadeethan yuftara walakin tasdeeqa allathee bayna yadayhi watafseela kulli shayin wahudan warahmatan liqawmin yuminoona

Translation: 111. በታሪካቸው ውስጥ ለአዕምሮ ባለቤቶች ሁሉ በእርግጥ መገሰጫ ነበረ:: ይህ ቁርኣን የሚቀጣጥፍ ወሬ አይደለም:: ይልቁንም ያንን በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ፤ ሁሉን ጉዳዮች ገላጭና ለሚያምኑ ህዝቦችም ሁሉ መሪ፤ ችሮታ ነው::

Transliteration source: English Transliteration by Tanzil. Used under Tanzil's non-commercial terms; see the source and latest updates at Tanzil. Tanzil translation download