quranm◉

Surah Luqman transliteration

◉ ሱራ · ∞

31:1

الٓمٓ ﴿1﴾

Transliteration: Aliflammeem

Translation: 1. አሊፍ፤ ላም፤ ሚይም፤

31:2

تِلۡكَ ءَايَٰتُ ٱلۡكِتَٰبِ ٱلۡحَكِيمِ ﴿2﴾

Transliteration: Tilka ayatu alkitabi alhakeemi

Translation: 2. እነዚህ አናቅጽ ጥበብ ከተሞላው መጽሐፍ ናቸው።

31:3

هُدٗى وَرَحۡمَةٗ لِّلۡمُحۡسِنِينَ ﴿3﴾

Transliteration: Hudan warahmatan lilmuhsineena

Translation: 3. ለበጎ አድራጊዎች ሁሉ መሪ፣ እዝነት ሲሆን፤

31:4

ٱلَّذِينَ يُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَيُؤۡتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَهُم بِٱلۡأٓخِرَةِ هُمۡ يُوقِنُونَ ﴿4﴾

Transliteration: Allatheena yuqeemoona alssalata wayutoona alzzakata wahum bialakhirati hum yooqinoona

Translation: 4. ለእነዚያ ሶላትን አስተካክለው ለሚሰግዱ፤ ዘካንም ለሚሰጡት፤ በመጨረሻይቱም ዓለም የሚያረጋግጡ ለሆኑት፤

31:5

أُوْلَـٰٓئِكَ عَلَىٰ هُدٗى مِّن رَّبِّهِمۡۖ وَأُوْلَـٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ ﴿5﴾

Transliteration: Olaika AAala hudan min rabbihim waolaika humu almuflihoona

Translation: 5. እነዚያ (የተጠቀሱትን ባህሪያት የሚላበሱ ሰዎች ሁሉ) በጌታቸው መመሪያ ላይ የሚጓዙ ናቸው። እነዚያ ፍላጎታቸውንም ያገኙትም እነርሱ ብቻ ናቸው::

31:6

وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَشۡتَرِي لَهۡوَ ٱلۡحَدِيثِ لِيُضِلَّ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ بِغَيۡرِ عِلۡمٖ وَيَتَّخِذَهَا هُزُوًاۚ أُوْلَـٰٓئِكَ لَهُمۡ عَذَابٞ مُّهِينٞ ﴿6﴾

Transliteration: Wamina alnnasi man yashtaree lahwa alhadeethi liyudilla AAan sabeeli Allahi bighayri AAilmin wayattakhithaha huzuwan olaika lahum AAathabun muheenun

Translation: 6. ከሰዎች መካከል ያለ ምንም እውቀት ሰዎችን ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና የአላህን መንገድ ማላገጫ ሊያደርግ አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ:: እነዚያ ይህን የሚያደርጉ ሁሉ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አለባቸው::

31:7

وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِ ءَايَٰتُنَا وَلَّىٰ مُسۡتَكۡبِرٗا كَأَن لَّمۡ يَسۡمَعۡهَا كَأَنَّ فِيٓ أُذُنَيۡهِ وَقۡرٗاۖ فَبَشِّرۡهُ بِعَذَابٍ أَلِيمٍ ﴿7﴾

Transliteration: Waitha tutla AAalayhi ayatuna walla mustakbiran kaan lam yasmaAAha kaanna fee othunayhi waqran fabashshirhu biAAathabin aleemin

Translation: 7. አናቅጻችን በእርሱ ላይ በሚነበቡ ጊዜ እንዳልሰማትና በጆሮቹ ድንቁርና እንዳለበት የኮራ ሆኖ ይዞራል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህን ሰው በአሳማሚ ቅጣት አብስረው::

31:8

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّـٰلِحَٰتِ لَهُمۡ جَنَّـٰتُ ٱلنَّعِيمِ ﴿8﴾

Transliteration: Inna allatheena amanoo waAAamiloo alssalihati lahum jannatu alnnaAAeemi

Translation: 8. እነዚያ ያመኑና መልካሞችን ተግባራት የሰሩ ሁሉ ለእነርሱ የጸጋ ገነቶች አሏቸው::

31:9

خَٰلِدِينَ فِيهَاۖ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقّٗاۚ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ ﴿9﴾

Transliteration: Khalideena feeha waAAda Allahi haqqan wahuwa alAAazeezu alhakeemu

Translation: 9. በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ሲሆኑ አላህ እውነተኛን የተስፋ ቃል ገባላቸው:: እርሱም ሁሉንም አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::

31:10

خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ بِغَيۡرِ عَمَدٖ تَرَوۡنَهَاۖ وَأَلۡقَىٰ فِي ٱلۡأَرۡضِ رَوَٰسِيَ أَن تَمِيدَ بِكُمۡ وَبَثَّ فِيهَا مِن كُلِّ دَآبَّةٖۚ وَأَنزَلۡنَا مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَأَنۢبَتۡنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوۡجٖ كَرِيمٍ ﴿10﴾

Transliteration: Khalaqa alssamawati bighayri AAamadin tarawnaha waalqa fee alardi rawasiya an tameeda bikum wabaththa feeha min kulli dabbatin waanzalna mina alssamai maan faanbatna feeha min kulli zawjin kareemin

Translation: 10. ሰማያትን የምታዮዋት ምሰሶ ሳያደርግላት ፈጠረ:: በምድርም ውስጥ በእናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለ:: በእርሷም ላይ ከተንቀሳቃሽ ነገሮች ሁሉ በተነ:: ከሰማይም ውሃን አወረድን:: በእርሷ ውስጥ ከመልካም ዓይነት ሁሉ አበቀልን::

31:11

هَٰذَا خَلۡقُ ٱللَّهِ فَأَرُونِي مَاذَا خَلَقَ ٱلَّذِينَ مِن دُونِهِۦۚ بَلِ ٱلظَّـٰلِمُونَ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ ﴿11﴾

Transliteration: Hatha khalqu Allahi faaroonee matha khalaqa allatheena min doonihi bali alththalimoona fee dalalin mubeenin

Translation: 11. ይህ ሁሉ የአላህ ፍጡር ነው:: እነዚያ ከእርሱ ሌላ ያሉት ምንን እንደ ፈጠሩ እስኪ አሳዩኝ:: በዳዮች በእውነት በግልጽ ጥመት ውስጥ ናቸው::

31:12

وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا لُقۡمَٰنَ ٱلۡحِكۡمَةَ أَنِ ٱشۡكُرۡ لِلَّهِۚ وَمَن يَشۡكُرۡ فَإِنَّمَا يَشۡكُرُ لِنَفۡسِهِۦۖ وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَنِيٌّ حَمِيدٞ ﴿12﴾

Transliteration: Walaqad atayna luqmana alhikmata ani oshkur lillahi waman yashkur fainnama yashkuru linafsihi waman kafara fainna Allaha ghaniyyun hameedun

Translation: 12. ለሉቅማንም ጥበብን በእርግጥ ሰጠነው:: አላህን አመስግን አልነዉም:: ያመሰገነም ሁሉ የሚያመሰግነው ለራሱ ብቻ ነው:: የካደም ሰውም (በራሱ ላይ ነው::) አላህ ተብቃቂና ምስጉን ነውና::

31:13

وَإِذۡ قَالَ لُقۡمَٰنُ لِٱبۡنِهِۦ وَهُوَ يَعِظُهُۥ يَٰبُنَيَّ لَا تُشۡرِكۡ بِٱللَّهِۖ إِنَّ ٱلشِّرۡكَ لَظُلۡمٌ عَظِيمٞ ﴿13﴾

Transliteration: Waith qala luqmanu liibnihi wahuwa yaAAithuhu ya bunayya la tushrik biAllahi inna alshshirka lathulmun AAatheemun

Translation: 13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገስጸው ሲሆን «ልጄ ሆይ! በአላህ አታጋራ። ማጋራት ታላቅ በደል ነውና።» ያለውን አስታውስ።

31:14

وَوَصَّيۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ بِوَٰلِدَيۡهِ حَمَلَتۡهُ أُمُّهُۥ وَهۡنًا عَلَىٰ وَهۡنٖ وَفِصَٰلُهُۥ فِي عَامَيۡنِ أَنِ ٱشۡكُرۡ لِي وَلِوَٰلِدَيۡكَ إِلَيَّ ٱلۡمَصِيرُ ﴿14﴾

Transliteration: Wawassayna alinsana biwalidayhi hamalathu ommuhu wahnan AAala wahnin wafisaluhu fee AAamayni ani oshkur lee waliwalidayka ilayya almaseeru

Translation: 14. ሰውንም በወላጆቹ በጎ እንዲያደርግ በጥብቅ አዘዝነው:: እናቱ ከድካም በላይ በሆነ ድካም አረገዘችው:: ጡት መጣያዉም በሁለት ዓመት ውስጥ ነው:: «ለእኔም ለወላጆችህም አመስግን" በማለትም አዘዝነው። መመለሻው ወደ እኔ ብቻ ነው።

31:15

وَإِن جَٰهَدَاكَ عَلَىٰٓ أَن تُشۡرِكَ بِي مَا لَيۡسَ لَكَ بِهِۦ عِلۡمٞ فَلَا تُطِعۡهُمَاۖ وَصَاحِبۡهُمَا فِي ٱلدُّنۡيَا مَعۡرُوفٗاۖ وَٱتَّبِعۡ سَبِيلَ مَنۡ أَنَابَ إِلَيَّۚ ثُمَّ إِلَيَّ مَرۡجِعُكُمۡ فَأُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ ﴿15﴾

Transliteration: Wain jahadaka AAala an tushrika bee ma laysa laka bihi AAilmun fala tutiAAhuma wasahibhuma fee alddunya maAAroofan waittabiAA sabeela man anaba ilayya thumma ilayya marjiAAukum faonabbiokum bima kuntum taAAmaloona

Translation: 15. ላንተ በእርሱ እውቀት የሌለህን ነገር በእኔ እንድታጋራ ቢያስገድዱህ አትታዘዛቸው:: በቅርቢቱም ዓለም በመልካም ስራ ተወዳጃቸው:: ወደ እኔም የተመለሰን ሰው መንገድ ተከተል:: ከዚያ መመለሻችሁ ወደ እኔ ነው:: ትሰሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ (አልነው)።

31:16

يَٰبُنَيَّ إِنَّهَآ إِن تَكُ مِثۡقَالَ حَبَّةٖ مِّنۡ خَرۡدَلٖ فَتَكُن فِي صَخۡرَةٍ أَوۡ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ أَوۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ يَأۡتِ بِهَا ٱللَّهُۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَطِيفٌ خَبِيرٞ ﴿16﴾

Transliteration: Ya bunayya innaha in taku mithqala habbatin min khardalin fatakun fee sakhratin aw fee alssamawati aw fee alardi yati biha Allahu inna Allaha lateefun khabeerun

Translation: 16. (ሉቅማንም አለ:) «ልጄ ሆይ! የእርሷ (መጥፎም ይሁን በጎ) የሰናፍጭ ቅንጣት ክብደት ያህል እንኳን ብትሆንና በቋጥኝ ውስጥ ወይም በሰማያት ውስጥ ወይም በምድር ውስጥ ብትሆን አላህ ያመጣታል:: አላህ ሩህሩህና ውስጠ አዋቂ ነውና።

31:17

يَٰبُنَيَّ أَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ وَأۡمُرۡ بِٱلۡمَعۡرُوفِ وَٱنۡهَ عَنِ ٱلۡمُنكَرِ وَٱصۡبِرۡ عَلَىٰ مَآ أَصَابَكَۖ إِنَّ ذَٰلِكَ مِنۡ عَزۡمِ ٱلۡأُمُورِ ﴿17﴾

Transliteration: Ya bunayya aqimi alssalata wamur bialmaAAroofi wainha AAani almunkari waisbir AAala ma asabaka inna thalika min AAazmi alomoori

Translation: 17. «ልጄ ሆይ! ሶላትን አስተካክለህ ስገድ፤ በበጎ ነገርም እዘዝ ከሚጠላም ሁሉ ከልክል፤ በሚያገኝህም መከራ ላይ ታገስ ይህ በምር ከሚያዙ ወሳኝ ነገሮች ነው።

31:18

وَلَا تُصَعِّرۡ خَدَّكَ لِلنَّاسِ وَلَا تَمۡشِ فِي ٱلۡأَرۡضِ مَرَحًاۖ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ كُلَّ مُخۡتَالٖ فَخُورٖ ﴿18﴾

Transliteration: Wala tusaAAAAir khaddaka lilnnasi wala tamshi fee alardi marahan inna Allaha la yuhibbu kulla mukhtalin fakhoorin

Translation: 18. «ጉንጭህንም በኩራት ከሰዎች አታዙር:: በምድርም ላይ ተንበጥርረህ አትሂድ:: አላህ ተንበጥራሪን (ኮራተኛ) ጉረኛን ሁሉ አይወድምና::

31:19

وَٱقۡصِدۡ فِي مَشۡيِكَ وَٱغۡضُضۡ مِن صَوۡتِكَۚ إِنَّ أَنكَرَ ٱلۡأَصۡوَٰتِ لَصَوۡتُ ٱلۡحَمِيرِ ﴿19﴾

Transliteration: Waiqsid fee mashyika waoghdud min sawtika inna ankara alaswati lasawtu alhameeri

Translation: 19. «በአካሄድህም መካከለኛ ሁን:: ከድምጽህም ዝቅ አድርግ:: ከድምፆች ሁሉ አስከፊው የአህዮች ድምጽ ነውና።»

31:20

أَلَمۡ تَرَوۡاْ أَنَّ ٱللَّهَ سَخَّرَ لَكُم مَّا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ وَأَسۡبَغَ عَلَيۡكُمۡ نِعَمَهُۥ ظَٰهِرَةٗ وَبَاطِنَةٗۗ وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يُجَٰدِلُ فِي ٱللَّهِ بِغَيۡرِ عِلۡمٖ وَلَا هُدٗى وَلَا كِتَٰبٖ مُّنِيرٖ ﴿20﴾

Transliteration: Alam taraw anna Allaha sakhkhara lakum ma fee alssamawati wama fee alardi waasbagha AAalaykum niAAamahu thahiratan wabatinatan wamina alnnasi man yujadilu fee Allahi bighayri AAilmin wala hudan wala kitabin muneerin

Translation: 20. (ሰዎች ሆይ!) አላህ በሰማያት እና በምድር ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ ለእናንተ ያገራላችሁ፤ ጸጋዎችንም ግልጽም ይሁኑ ድብቅ የሞላላችሁ መሆኑን አታዩምን? ከስሞች መካከል ያለ በቂ እውቀትና ያለ መሪ፤ ያለ ግልጽ መጽሀፍም፤ ስለ አላህ የሚከራከር አለ::

31:21

وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ٱتَّبِعُواْ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ قَالُواْ بَلۡ نَتَّبِعُ مَا وَجَدۡنَا عَلَيۡهِ ءَابَآءَنَآۚ أَوَلَوۡ كَانَ ٱلشَّيۡطَٰنُ يَدۡعُوهُمۡ إِلَىٰ عَذَابِ ٱلسَّعِيرِ ﴿21﴾

Transliteration: Waitha qeela lahumu ittabiAAoo ma anzala Allahu qaloo bal nattabiAAu ma wajadna AAalayhi abaana awalaw kana alshshaytanu yadAAoohum ila AAathabi alssaAAeeri

Translation: 21. ለእነርሱም «አላህ ያወረደውን ተከተሉ።» በተባሉ ጊዜ «አይደለም በእርሱ ላይ አባቶቻችንን ያገኘንበትን እንከተላለን።» ይላሉ:: ሰይጣን (ይህን ተግባር በማስዋብ) ወደ እሳት ቅጣት የሚጠራቸው ቢሆንም ይከተሏቸዋልን?

31:22

وَمَن يُسۡلِمۡ وَجۡهَهُۥٓ إِلَى ٱللَّهِ وَهُوَ مُحۡسِنٞ فَقَدِ ٱسۡتَمۡسَكَ بِٱلۡعُرۡوَةِ ٱلۡوُثۡقَىٰۗ وَإِلَى ٱللَّهِ عَٰقِبَةُ ٱلۡأُمُورِ ﴿22﴾

Transliteration: Waman yuslim wajhahu ila Allahi wahuwa muhsinun faqadi istamsaka bialAAurwati alwuthqa waila Allahi AAaqibatu alomoori

Translation: 22. መልካም ሰሪ ሆኖ ፊቱን ወደ አላህ የሚሰጥ ሁሉ ጠንካራ ገመድን በእርግጥ ጨበጠ:: የነገሩ ሁሉ ፍጻሜ ወደ አላህ ብቻ ነው::

31:23

وَمَن كَفَرَ فَلَا يَحۡزُنكَ كُفۡرُهُۥٓۚ إِلَيۡنَا مَرۡجِعُهُمۡ فَنُنَبِّئُهُم بِمَا عَمِلُوٓاْۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ ﴿23﴾

Transliteration: Waman kafara fala yahzunka kufruhu ilayna marjiAAuhum fanunabbiohum bima AAamiloo inna Allaha AAaleemun bithati alssudoori

Translation: 23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ የካደም ሁሉ ክህደቱ አያሳዝንህ። መመለሻቸው ወደ እኛ ብቻ ነውና:: ከዚያም የሰሩትንም ሁሉ እንነግራቸዋለን:: አላህ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ ያውቃልና፡፡

31:24

نُمَتِّعُهُمۡ قَلِيلٗا ثُمَّ نَضۡطَرُّهُمۡ إِلَىٰ عَذَابٍ غَلِيظٖ ﴿24﴾

Transliteration: NumattiAAuhum qaleelan thumma nadtarruhum ila AAathabin ghaleethin

Translation: 24. ጥቂትን ጊዜ እናጣቅማቸዋለን:: ከዚያም ወደ ብርቱ ቅጣት እናስገድዳቸዋለን::

31:25

وَلَئِن سَأَلۡتَهُم مَّنۡ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُۚ قُلِ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِۚ بَلۡ أَكۡثَرُهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ ﴿25﴾

Transliteration: Walain saaltahum man khalaqa alssamawati waalarda layaqoolunna Allahu quli alhamdu lillahi bal aktharuhum la yaAAlamoona

Translation: 25. ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው «በእርግጥ አላህ ነው።» ይላሉ። «ምስጋና ሁሉ ለአላህ ብቻ ይገባው።» በላቸው:: ይልቁንም አብዛኞቹ አያውቁም።

31:26

لِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡغَنِيُّ ٱلۡحَمِيدُ ﴿26﴾

Transliteration: Lillahi ma fee alssamawati waalardi inna Allaha huwa alghaniyyu alhameedu

Translation: 26. በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: አላህ በራሱ ተብቃቂዉና ምስጉኑ ነው::

31:27

وَلَوۡ أَنَّمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ مِن شَجَرَةٍ أَقۡلَٰمٞ وَٱلۡبَحۡرُ يَمُدُّهُۥ مِنۢ بَعۡدِهِۦ سَبۡعَةُ أَبۡحُرٖ مَّا نَفِدَتۡ كَلِمَٰتُ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٞ ﴿27﴾

Transliteration: Walaw annama fee alardi min shajaratin aqlamun waalbahru yamudduhu min baAAdihi sabAAatu abhurin ma nafidat kalimatu Allahi inna Allaha AAazeezun hakeemun

Translation: 27. በምድር ያሉ ሁሉ ዛፎች ብዕሮች ቢሆኑ ኖሮ ባህሩም ከእርሱ ማለቅ በኋላ ሰባት ባህሮች የሚጨመሩለት ሆኖ ቀለም ቢሆንና ቢጻፍባቸው የአላህ ቃላት ባላለቀች ነበር:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::

31:28

مَّا خَلۡقُكُمۡ وَلَا بَعۡثُكُمۡ إِلَّا كَنَفۡسٖ وَٰحِدَةٍۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعُۢ بَصِيرٌ ﴿28﴾

Transliteration: Ma khalqukum wala baAAthukum illa kanafsin wahidatin inna Allaha sameeAAun baseerun

Translation: 28. (ሰዎች ሆይ!) እናንተን መፍጠርና እናንተን መቀስቀስ እንደ አንዲት ነፍስ እንጂ ሌላ አይደለም:: አላህ ሁሉን ሰሚና ሁሉን ተመልካች ነውና::

31:29

أَلَمۡ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ يُولِجُ ٱلَّيۡلَ فِي ٱلنَّهَارِ وَيُولِجُ ٱلنَّهَارَ فِي ٱلَّيۡلِ وَسَخَّرَ ٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَۖ كُلّٞ يَجۡرِيٓ إِلَىٰٓ أَجَلٖ مُّسَمّٗى وَأَنَّ ٱللَّهَ بِمَا تَعۡمَلُونَ خَبِيرٞ ﴿29﴾

Transliteration: Alam tara anna Allaha yooliju allayla fee alnnahari wayooliju alnnahara fee allayli wasakhkhara alshshamsa waalqamara kullun yajree ila ajalin musamman waanna Allaha bima taAAmaloona khabeerun

Translation: 29. (የሰው ልጅ ሆይ) አላህ ሌሊትን በቀን ውስጥ የሚያስገባ ቀንንም በሌሊት ውስጥ የሚያስገባ ጸሀይንና ጨረቃንም የገራ መሆኑን አታይምን? ሁሉም እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ይሮጣሉ:: አላህም በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው::

31:30

ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡحَقُّ وَأَنَّ مَا يَدۡعُونَ مِن دُونِهِ ٱلۡبَٰطِلُ وَأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡعَلِيُّ ٱلۡكَبِيرُ ﴿30﴾

Transliteration: Thalika bianna Allaha huwa alhaqqu waanna ma yadAAoona min doonihi albatilu waanna Allaha huwa alAAaliyyu alkabeeru

Translation: 30. ይህም የእርሱ (የአላህ) ብቸኛ አምላክነት እውነት በመሆኑ፤ ከእርሱ ሌላ የሚገዙት ጣዖት ሁሉ ውሸት በመሆኑና አላህ የበላይ ታላቅ በመሆኑ ነው።

31:31

أَلَمۡ تَرَ أَنَّ ٱلۡفُلۡكَ تَجۡرِي فِي ٱلۡبَحۡرِ بِنِعۡمَتِ ٱللَّهِ لِيُرِيَكُم مِّنۡ ءَايَٰتِهِۦٓۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّكُلِّ صَبَّارٖ شَكُورٖ ﴿31﴾

Transliteration: Alam tara anna alfulka tajree fee albahri biniAAmati Allahi liyuriyakum min ayatihi inna fee thalika laayatin likulli sabbarin shakoorin

Translation: 31. (የሰው ልጅ ሆይ!) ከአስደናቂ ምልክቶቹ ሊያሳያችሁ መርከቦች በአላህ ችሮታ በባህር ውስጥ የሚንሻለሉ መሆናቸውን አታይምን? በዚህ ውስጥ በጣም ታጋሽ አመስጋኝ ለሆኑ ሁሉ አያሌ ተዓምራት አሉበት::

31:32

وَإِذَا غَشِيَهُم مَّوۡجٞ كَٱلظُّلَلِ دَعَوُاْ ٱللَّهَ مُخۡلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ فَلَمَّا نَجَّىٰهُمۡ إِلَى ٱلۡبَرِّ فَمِنۡهُم مُّقۡتَصِدٞۚ وَمَا يَجۡحَدُ بِـَٔايَٰتِنَآ إِلَّا كُلُّ خَتَّارٖ كَفُورٖ ﴿32﴾

Transliteration: Waitha ghashiyahum mawjun kaalththulali daAAawoo Allaha mukhliseena lahu alddeena falamma najjahum ila albarri faminhum muqtasidun wama yajhadu biayatina illa kullu khattarin kafoorin

Translation: 32. እንደ ጥላዎች የሆነ ማዕበል በሸፈናቸው ጊዜ ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው አላህን ይጠሩታል:: ወደ የብስ ባዳናቸው ጊዜ ግን ከእነርሱ መካከል ትክክለኛም አለ:: (ከእነርሱም መካከል የሚክድ አለ):: በአናቅጻችንም አታላይና ከዳተኛ የሆነ ሁሉ እንጂ ሌላው አይክድም::

31:33

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ٱتَّقُواْ رَبَّكُمۡ وَٱخۡشَوۡاْ يَوۡمٗا لَّا يَجۡزِي وَالِدٌ عَن وَلَدِهِۦ وَلَا مَوۡلُودٌ هُوَ جَازٍ عَن وَالِدِهِۦ شَيۡـًٔاۚ إِنَّ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقّٞۖ فَلَا تَغُرَّنَّكُمُ ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَا وَلَا يَغُرَّنَّكُم بِٱللَّهِ ٱلۡغَرُورُ ﴿33﴾

Transliteration: Ya ayyuha alnnasu ittaqoo rabbakum waikhshaw yawman la yajzee walidun AAan waladihi wala mawloodun huwa jazin AAan walidihi shayan inna waAAda Allahi haqqun fala taghurrannakumu alhayatu alddunya wala yaghurrannakum biAllahi algharooru

Translation: 33. እናንተ ሰዎች ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ:: ወላጅ ከልጁ በምንም የማይጠቅምበት ልጅም ወላጅን በምንም ጠቃሚ የማይሆንበትን ቀን ፍሩ:: የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና:: ቅርቢቱም ህይወት አትሸንግላችሁ:: በአላህ (መታገስም) አታላዩ (ሰይጣን) አያታልላችሁ።

31:34

إِنَّ ٱللَّهَ عِندَهُۥ عِلۡمُ ٱلسَّاعَةِ وَيُنَزِّلُ ٱلۡغَيۡثَ وَيَعۡلَمُ مَا فِي ٱلۡأَرۡحَامِۖ وَمَا تَدۡرِي نَفۡسٞ مَّاذَا تَكۡسِبُ غَدٗاۖ وَمَا تَدۡرِي نَفۡسُۢ بِأَيِّ أَرۡضٖ تَمُوتُۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرُۢ ﴿34﴾

Transliteration: Inna Allaha AAindahu AAilmu alssaAAati wayunazzilu alghaytha wayaAAlamu ma fee alarhami wama tadree nafsun matha taksibu ghadan wama tadree nafsun biayyi ardin tamootu inna Allaha AAaleemun khabeerun

Translation: 34. አላህ የሰዓቲቱ እውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው:: ዝናብንም ያወርዳል:: በማህጸኖችም ውስጥ ያለን ሁሉ ያውቃል። ማንኛይቱም ነፍስ ነገ የምትሰራውን አታውቅም:: ማንኛይቱም ነፍስ በየትኛው ምድር እንደምትሞትም አታውቅም:: አላህ አዋቂና ውስጠ አዋቂ ነው::

Transliteration source: English Transliteration by Tanzil. Used under Tanzil's non-commercial terms; see the source and latest updates at Tanzil. Tanzil translation download