quranm◉

Surah Fussilat transliteration

◉ ሱራ · ∞

41:1

حمٓ ﴿1﴾

Transliteration: Hameem

Translation: 1. ሓ፤ ሚይም፤

41:2

تَنزِيلٞ مِّنَ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ ﴿2﴾

Transliteration: Tanzeelun mina alrrahmani alrraheemi

Translation: 2. ይህ ቁርኣን እጅግ በጣም ሩህሩህና በጣም አዛኝ ከሆነው ጌታ ከአላህ የተወረደ ነው::

41:3

كِتَٰبٞ فُصِّلَتۡ ءَايَٰتُهُۥ قُرۡءَانًا عَرَبِيّٗا لِّقَوۡمٖ يَعۡلَمُونَ ﴿3﴾

Transliteration: Kitabun fussilat ayatuhu quranan AAarabiyyan liqawmin yaAAlamoona

Translation: 3. አናቅጾቹ የተብራሩ የሆነ መጽሐፍ ነው:: ዐረበኛ ቁርኣን ሲሆን ለሚያውቁ ሕዝቦች የተብራራ ነው::

41:4

بَشِيرٗا وَنَذِيرٗا فَأَعۡرَضَ أَكۡثَرُهُمۡ فَهُمۡ لَا يَسۡمَعُونَ ﴿4﴾

Transliteration: Basheeran wanatheeran faaAArada aktharuhum fahum la yasmaAAoona

Translation: 4. አብሳሪና አስፈራሪ ሲሆን ተወረደ። አብዛኞቻቸዉም ተውት:: እነርሱም አይሰሙም::

41:5

وَقَالُواْ قُلُوبُنَا فِيٓ أَكِنَّةٖ مِّمَّا تَدۡعُونَآ إِلَيۡهِ وَفِيٓ ءَاذَانِنَا وَقۡرٞ وَمِنۢ بَيۡنِنَا وَبَيۡنِكَ حِجَابٞ فَٱعۡمَلۡ إِنَّنَا عَٰمِلُونَ ﴿5﴾

Transliteration: Waqaloo quloobuna fee akinnatin mimma tadAAoona ilayhi wafee athanina waqrun wamin baynina wabaynika hijabun faiAAmal innana AAamiloona

Translation: 5. አሉም፡- «ልቦቻችን ከዚያ ወደርሱ ከምትጠራን እምነት በመሸፈኛዎች ውስጥ ናቸው:: በጆሮቻችንም ላይ ድንቁርና አለ:: በእኛና በአንተ መካከል ግርዶሽ አለ:: በሃይማኖትህ ስራ እኛም ሰሪዎች ነንና::»

41:6

قُلۡ إِنَّمَآ أَنَا۠ بَشَرٞ مِّثۡلُكُمۡ يُوحَىٰٓ إِلَيَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمۡ إِلَٰهٞ وَٰحِدٞ فَٱسۡتَقِيمُوٓاْ إِلَيۡهِ وَٱسۡتَغۡفِرُوهُۗ وَوَيۡلٞ لِّلۡمُشۡرِكِينَ ﴿6﴾

Transliteration: Qul innama ana basharun mithlukum yooha ilayya annama ilahukum ilahun wahidun faistaqeemoo ilayhi waistaghfiroohu wawaylun lilmushrikeena

Translation: 6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንዲህ በላቸው «እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: ወደ እርሱም ቀጥ በሉ:: ምህረትንም ለምኑት በማለት ወደ እኔ ይወርድልኛል እንጂ መሰላችሁ ሰው ብቻ ነኝ።» ለአጋሪዎችም ወዮላቸው።

41:7

ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَهُم بِٱلۡأٓخِرَةِ هُمۡ كَٰفِرُونَ ﴿7﴾

Transliteration: Allatheena la yutoona alzzakata wahum bialakhirati hum kafiroona

Translation: 7. ለእነዚያ ዘካን ለማይሰጡ እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ ከሓዲያን ለሆኑት (ወዮላቸው)::

41:8

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّـٰلِحَٰتِ لَهُمۡ أَجۡرٌ غَيۡرُ مَمۡنُونٖ ﴿8﴾

Transliteration: Inna allatheena amanoo waAAamiloo alssalihati lahum ajrun ghayru mamnoonin

Translation: 8. እነዚያ ያመኑትና በጎ ስራዎችንም የሰሩት ሁሉ ለእነርሱ የማይቋረጥ ምንዳ አላቸው::

41:9

قُلۡ أَئِنَّكُمۡ لَتَكۡفُرُونَ بِٱلَّذِي خَلَقَ ٱلۡأَرۡضَ فِي يَوۡمَيۡنِ وَتَجۡعَلُونَ لَهُۥٓ أَندَادٗاۚ ذَٰلِكَ رَبُّ ٱلۡعَٰلَمِينَ ﴿9﴾

Transliteration: Qul ainnakum latakfuroona biallathee khalaqa alarda fee yawmayni watajAAaloona lahu andadan thalika rabbu alAAalameena

Translation: 9. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ !) «እናንተ በዚያ ምድርን በሁለት ቀናት ውስጥ በፈጠረው አምላክ በእርግጥ ትክዳላችሁን? ለእርሱም ባላንጣዎች ታደርጋላችሁን? ያ (ይህንን የሰራው) የዓለማቱ ጌታ ነው።» በላቸው::

41:10

وَجَعَلَ فِيهَا رَوَٰسِيَ مِن فَوۡقِهَا وَبَٰرَكَ فِيهَا وَقَدَّرَ فِيهَآ أَقۡوَٰتَهَا فِيٓ أَرۡبَعَةِ أَيَّامٖ سَوَآءٗ لِّلسَّآئِلِينَ ﴿10﴾

Transliteration: WajaAAala feeha rawasiya min fawqiha wabaraka feeha waqaddara feeha aqwataha fee arbaAAati ayyamin sawaan lilssaileena

Translation: 10. በእርሷም ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ:: በእርሷም በረከትን አደረገ:: በውስጧም ምግቦችዋን (ካለፉት ሁለት ቀኖች ጋር) በአራት ቀናት ውስጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲሆን ወሰነ::

41:11

ثُمَّ ٱسۡتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ وَهِيَ دُخَانٞ فَقَالَ لَهَا وَلِلۡأَرۡضِ ٱئۡتِيَا طَوۡعًا أَوۡ كَرۡهٗا قَالَتَآ أَتَيۡنَا طَآئِعِينَ ﴿11﴾

Transliteration: Thumma istawa ila alssamai wahiya dukhanun faqala laha walilardi itiya tawAAan aw karhan qalata atayna taiAAeena

Translation: 11. ከዚያም እርሷ ጭስ ሆና ሳለች ወደ ሰማይ አሰበ:: ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ሆነ ጠልታችሁ ኑ» አላቸው:: «ታዛዦች ሆነን መጣን» አሉ::

41:12

فَقَضَىٰهُنَّ سَبۡعَ سَمَٰوَاتٖ فِي يَوۡمَيۡنِ وَأَوۡحَىٰ فِي كُلِّ سَمَآءٍ أَمۡرَهَاۚ وَزَيَّنَّا ٱلسَّمَآءَ ٱلدُّنۡيَا بِمَصَٰبِيحَ وَحِفۡظٗاۚ ذَٰلِكَ تَقۡدِيرُ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡعَلِيمِ ﴿12﴾

Transliteration: Faqadahunna sabAAa samawatin fee yawmayni waawha fee kulli samain amraha wazayyanna alssamaa alddunya bimasabeeha wahifthan thalika taqdeeru alAAazeezi alAAaleemi

Translation: 12. በሁለት ቀናትም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው:: በሰማያትም ሁሉ ነገሯን አዘጋጀ:: ቅርቢቱንም ሰማይ በመብራቶች አጌጥን:: ከሰይጣናት መጠበቅንም ጠበቅናት:: ይህ የአሸናፊውና የአዋቂው ጌታ ውሳኔ ነው::

41:13

فَإِنۡ أَعۡرَضُواْ فَقُلۡ أَنذَرۡتُكُمۡ صَٰعِقَةٗ مِّثۡلَ صَٰعِقَةِ عَادٖ وَثَمُودَ ﴿13﴾

Transliteration: Fain aAAradoo fuqul anthartukum saAAiqatan mithla saAAiqati AAadin wathamooda

Translation: 13. ከእምነት እምቢ ቢሉም (እንዲህ) በላቸው: «እንደ ዓድና ሰሙድ መቅሰፍት ብጤ የሆነን መቅሰፍት አስጠነቅቄያችኋለሁ።»

41:14

إِذۡ جَآءَتۡهُمُ ٱلرُّسُلُ مِنۢ بَيۡنِ أَيۡدِيهِمۡ وَمِنۡ خَلۡفِهِمۡ أَلَّا تَعۡبُدُوٓاْ إِلَّا ٱللَّهَۖ قَالُواْ لَوۡ شَآءَ رَبُّنَا لَأَنزَلَ مَلَـٰٓئِكَةٗ فَإِنَّا بِمَآ أُرۡسِلۡتُم بِهِۦ كَٰفِرُونَ ﴿14﴾

Transliteration: Ith jaathumu alrrusulu min bayni aydeehim wamin khalfihim alla taAAbudoo illa Allaha qaloo law shaa rabbuna laanzala malaikatan fainna bima orsiltum bihi kafiroona

Translation: 14. መልዕክተኞቹ «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ» በማለት ከስተፊታቸዉም ከበስተኋላቸዉም በመጡባቸው ጊዜ «ጌታችን በሻ ኖሮ መላዕክትን ባወረደ ነበር:: ስለዚህ እኛ በዚህ በእርሱ በተላካችሁት ከሓዲያን ነን።» አሉ።

41:15

فَأَمَّا عَادٞ فَٱسۡتَكۡبَرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ بِغَيۡرِ ٱلۡحَقِّ وَقَالُواْ مَنۡ أَشَدُّ مِنَّا قُوَّةًۖ أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ أَنَّ ٱللَّهَ ٱلَّذِي خَلَقَهُمۡ هُوَ أَشَدُّ مِنۡهُمۡ قُوَّةٗۖ وَكَانُواْ بِـَٔايَٰتِنَا يَجۡحَدُونَ ﴿15﴾

Transliteration: Faamma AAadun faistakbaroo fee alardi bighayri alhaqqi waqaloo man ashaddu minna quwwatan awalam yaraw anna Allaha allathee khalaqahum huwa ashaddu minhum quwwatan wakanoo biayatina yajhadoona

Translation: 15. የዓድም ነገዶችም በምድር ላይ ያለ አግባብ ኮሩ፤ ከእኛ ይበልጥ በኃይል ብርቱ ማን ነው ? አሉም ያ የፈጠራቸው አላህ እርሱ በኃይል ከእነርሱ ይበልጥ የበረታ መሆኑን አያምኑምን? በታዐምራታችንም ይክዱ ነበሩ::

41:16

فَأَرۡسَلۡنَا عَلَيۡهِمۡ رِيحٗا صَرۡصَرٗا فِيٓ أَيَّامٖ نَّحِسَاتٖ لِّنُذِيقَهُمۡ عَذَابَ ٱلۡخِزۡيِ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۖ وَلَعَذَابُ ٱلۡأٓخِرَةِ أَخۡزَىٰۖ وَهُمۡ لَا يُنصَرُونَ ﴿16﴾

Transliteration: Faarsalna AAalayhim reehan sarsaran fee ayyamin nahisatin linutheeqahum AAathaba alkhizyi fee alhayati alddunya walaAAathabu alakhirati akhza wahum la yunsaroona

Translation: 16. በቅርቢቱ ሕይወት የውርደትን ቅጣት ልናቀምሳቸዉም በእነርሱ ላይ የሚንሻሻ ብርቱ ነፋስ መናጢዎች በሆኑ ቀናት ውስጥ ላክንባቸው:: የመጨረሻይቱም ዓለም ስቃይ በጣም አዋራጅ ነው:: እነርሱም አይረዱም::

41:17

وَأَمَّا ثَمُودُ فَهَدَيۡنَٰهُمۡ فَٱسۡتَحَبُّواْ ٱلۡعَمَىٰ عَلَى ٱلۡهُدَىٰ فَأَخَذَتۡهُمۡ صَٰعِقَةُ ٱلۡعَذَابِ ٱلۡهُونِ بِمَا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ ﴿17﴾

Transliteration: Waamma thamoodu fahadaynahum faistahabboo alAAama AAala alhuda faakhathathum saAAiqatu alAAathabi alhooni bima kanoo yaksiboona

Translation: 17. ሰሙዶችማ ወደ ቀናው መንገድ መራናቸው:: እነርሱ ግን እውርነትን ከቅንነት ይልቅ መረጡ:: ይሰሩትም በነበሩት ኃጢአት አዋራጅ የሆነችው የመብረቅ ቅጣት ያዘቻቸው::

41:18

وَنَجَّيۡنَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَكَانُواْ يَتَّقُونَ ﴿18﴾

Transliteration: Wanajjayna allatheena amanoo wakanoo yattaqoona

Translation: 18. እነዚያንም ያመኑትንና ይጠነቀቁ የነበሩትንም አዳንናቸው::

41:19

وَيَوۡمَ يُحۡشَرُ أَعۡدَآءُ ٱللَّهِ إِلَى ٱلنَّارِ فَهُمۡ يُوزَعُونَ ﴿19﴾

Transliteration: Wayawma yuhsharu aAAdao Allahi ila alnnari fahum yoozaAAoona

Translation: 19. የአላህም ጠላቶች ወደ እሳት የሚሰበሰቡበትን ቀን አስታውሱ:: የሚከመከሙ ሆነውም ይነዳሉ።

41:20

حَتَّىٰٓ إِذَا مَا جَآءُوهَا شَهِدَ عَلَيۡهِمۡ سَمۡعُهُمۡ وَأَبۡصَٰرُهُمۡ وَجُلُودُهُم بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ ﴿20﴾

Transliteration: Hatta itha ma jaooha shahida AAalayhim samAAuhum waabsaruhum wajulooduhum bima kanoo yaAAmaloona

Translation: 20. በመጧትም ጊዜ ጀሮዎቻቸው፤ ዓይኖቻቸውና ቆዳዎቻቸዉም ይሰሩት በነበረ ነገር በእነርሱ ላይ ይመሰክሩባቸዋል::

41:21

وَقَالُواْ لِجُلُودِهِمۡ لِمَ شَهِدتُّمۡ عَلَيۡنَاۖ قَالُوٓاْ أَنطَقَنَا ٱللَّهُ ٱلَّذِيٓ أَنطَقَ كُلَّ شَيۡءٖۚ وَهُوَ خَلَقَكُمۡ أَوَّلَ مَرَّةٖ وَإِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ ﴿21﴾

Transliteration: Waqaloo lijuloodihim lima shahidtum AAalayna qaloo antaqana Allahu allathee antaqa kulla shayin wahuwa khalaqakum awwala marratin wailayhi turjaAAoona

Translation: 21. ለቆዳዎቻቸዉም «በእኛ ላይ ለምን መሰከራችሁብን?» ይላሉ። «ያ ሁሉን ነገር ያናገረው አላህ አናገረን:: እርሱም (ነው) በመጀመሪያ ጊዜ የፈጠራችሁ። ወደ እርሱም ብቻ ትመለሳላችሁ» ይሏቸዋል::

41:22

وَمَا كُنتُمۡ تَسۡتَتِرُونَ أَن يَشۡهَدَ عَلَيۡكُمۡ سَمۡعُكُمۡ وَلَآ أَبۡصَٰرُكُمۡ وَلَا جُلُودُكُمۡ وَلَٰكِن ظَنَنتُمۡ أَنَّ ٱللَّهَ لَا يَعۡلَمُ كَثِيرٗا مِّمَّا تَعۡمَلُونَ ﴿22﴾

Transliteration: Wama kuntum tastatiroona an yashhada AAalaykum samAAukum wala absarukum wala juloodukum walakin thanantum anna Allaha la yaAAlamu katheeran mimma taAAmaloona

Translation: 22. ጆሮዎቻችሁ ዓይኖቻችሁና ቆዳዎቻችሁ በእናንተ ላይ እንዳይመሰክሩባችሁ የምትደበቁባቸው አልነበራችሁም:: ግን አላህ ከምትሰሩት ብዙውን አያውቅም ብላችሁ ጠረጠራችሁ::

41:23

وَذَٰلِكُمۡ ظَنُّكُمُ ٱلَّذِي ظَنَنتُم بِرَبِّكُمۡ أَرۡدَىٰكُمۡ فَأَصۡبَحۡتُم مِّنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ ﴿23﴾

Transliteration: Wathalikum thannukumu allathee thanantum birabbikum ardakum faasbahtum mina alkhasireena

Translation: 23. ይህም ለጌታችሁ የጠረጣችሁት ጥርጣሬያችሁ አጠፋችሁ:: ከከሳሪዎችም ሆናችሁ ይባላሉ::

41:24

فَإِن يَصۡبِرُواْ فَٱلنَّارُ مَثۡوٗى لَّهُمۡۖ وَإِن يَسۡتَعۡتِبُواْ فَمَا هُم مِّنَ ٱلۡمُعۡتَبِينَ ﴿24﴾

Transliteration: Fain yasbiroo faalnnaru mathwan lahum wain yastaAAtiboo fama hum mina almuAAtabeena

Translation: 24. ቢታገሱም እሳት ለእነርሱ መኖሪያቸው ናት:: ወደ ሚወዱት መመለስንም ቢጠይቁ እነርሱ ተቀባይ የሚያገኙ አይደሉም::

41:25

وَقَيَّضۡنَا لَهُمۡ قُرَنَآءَ فَزَيَّنُواْ لَهُم مَّا بَيۡنَ أَيۡدِيهِمۡ وَمَا خَلۡفَهُمۡ وَحَقَّ عَلَيۡهِمُ ٱلۡقَوۡلُ فِيٓ أُمَمٖ قَدۡ خَلَتۡ مِن قَبۡلِهِم مِّنَ ٱلۡجِنِّ وَٱلۡإِنسِۖ إِنَّهُمۡ كَانُواْ خَٰسِرِينَ ﴿25﴾

Transliteration: Waqayyadna lahum quranaa fazayyanoo lahum ma bayna aydeehim wama khalfahum wahaqqa AAalayhimu alqawlu fee omamin qad khalat min qablihim mina aljinni waalinsi innahum kanoo khasireena

Translation: 25. ለእነርሱም ቁራኛዎችን አዘጋጀንላቸው:: በፊታቸውን ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ለእነርሱ ሸለሙላቸው:: ከአጋንንትና ከሰዉም ከእነርሱ በፊት በእርግጥ ካለፉት ህዝቦች ጋር ሆነው ቃሉ በእነርሱ ላይ ተረጋገጠባቸው:: እነርሱ በእርግጥ ከሳሪዎች ነበሩና::

41:26

وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَا تَسۡمَعُواْ لِهَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانِ وَٱلۡغَوۡاْ فِيهِ لَعَلَّكُمۡ تَغۡلِبُونَ ﴿26﴾

Transliteration: Waqala allatheena kafaroo la tasmaAAoo lihatha alqurani wailghaw feehi laAAallakum taghliboona

Translation: 26. እነዚያም «በአላህ የካዱት ሰዎች ይህንን ቁርኣን አታዳምጡ ታሸንፉም ዘንድ ሲነበብም ተንጫጩበት።» አሉ።

41:27

فَلَنُذِيقَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ عَذَابٗا شَدِيدٗا وَلَنَجۡزِيَنَّهُمۡ أَسۡوَأَ ٱلَّذِي كَانُواْ يَعۡمَلُونَ ﴿27﴾

Transliteration: Falanutheeqanna allatheena kafaroo AAathaban shadeedan walanajziyannahum aswaa allathee kanoo yaAAmaloona

Translation: 27. እነዚያንም በአላህ የካዱትን ብርቱ ቅጣት እናቀምሳቸዋለን:: የእነዚያንም ይሰሩት የነበሩትን መጥፎውን ፍዳ እንመነዳቸዋለን::

41:28

ذَٰلِكَ جَزَآءُ أَعۡدَآءِ ٱللَّهِ ٱلنَّارُۖ لَهُمۡ فِيهَا دَارُ ٱلۡخُلۡدِ جَزَآءَۢ بِمَا كَانُواْ بِـَٔايَٰتِنَا يَجۡحَدُونَ ﴿28﴾

Transliteration: Thalika jazao aAAdai Allahi alnnaru lahum feeha daru alkhuldi jazaan bima kanoo biayatina yajhadoona

Translation: 28. ይህ የአላህ ጠላቶች ፍዳ እሳት ነው:: በውስጧም ለእነርሱ የዘላለም መኖሪያ አገር አላቸው:: በአንቀፆቻቸን ይክዱ በነበሩት ምንዳ ይመነዳሉ::

41:29

وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ رَبَّنَآ أَرِنَا ٱلَّذَيۡنِ أَضَلَّانَا مِنَ ٱلۡجِنِّ وَٱلۡإِنسِ نَجۡعَلۡهُمَا تَحۡتَ أَقۡدَامِنَا لِيَكُونَا مِنَ ٱلۡأَسۡفَلِينَ ﴿29﴾

Transliteration: Waqala allatheena kafaroo rabbana arina allathayni adallana mina aljinni waalinsi najAAalhuma tahta aqdamina liyakoona mina alasfaleena

Translation: 29. እነዚያም በአላህ የካዱት በእሳት ውስጥ ሆነው «ጌታችን ሆይ! እነዚያ ከአጋንንትና ከሰው ያሳሳቱንን አሳየን። ከታችኞች ይሆኑ ዘንድ ከጫማዎቻችን ስር እናደርጋቸዋለንና» ይላሉ::

41:30

إِنَّ ٱلَّذِينَ قَالُواْ رَبُّنَا ٱللَّهُ ثُمَّ ٱسۡتَقَٰمُواْ تَتَنَزَّلُ عَلَيۡهِمُ ٱلۡمَلَـٰٓئِكَةُ أَلَّا تَخَافُواْ وَلَا تَحۡزَنُواْ وَأَبۡشِرُواْ بِٱلۡجَنَّةِ ٱلَّتِي كُنتُمۡ تُوعَدُونَ ﴿30﴾

Transliteration: Inna allatheena qaloo rabbuna Allahu thumma istaqamoo tatanazzalu AAalayhimu almalaikatu alla takhafoo wala tahzanoo waabshiroo bialjannati allatee kuntum tooAAadoona

Translation: 30. እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉና ከዚያም ቀጥ ያሉ። እንዲህ እያሉ መላዕክቱ በነርሱ ላይ ይወርዳሉ: «አትፍሩ አትዘኑ:: በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላቸሁ:: በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ።

41:31

نَحۡنُ أَوۡلِيَآؤُكُمۡ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَفِي ٱلۡأٓخِرَةِۖ وَلَكُمۡ فِيهَا مَا تَشۡتَهِيٓ أَنفُسُكُمۡ وَلَكُمۡ فِيهَا مَا تَدَّعُونَ ﴿31﴾

Transliteration: Nahnu awliyaokum fee alhayati alddunya wafee alakhirati walakum feeha ma tashtahee anfusukum walakum feeha ma taddaAAoona

Translation: 31. «እኛ በቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱም ረዳቶቻችሁ ነን! ለእናተም በእርሷ ውስጥ ነፍሶቻችሁ የሚሹት ሁሉ አላችሁ:: ለእናንተም በእርሷ ውስጥ የምታዙት ሁሉ አለላችሁ::

41:32

نُزُلٗا مِّنۡ غَفُورٖ رَّحِيمٖ ﴿32﴾

Transliteration: Nuzulan min ghafoorin raheemin

Translation: 32. «መሀሪና አዛኝ ከሆነው አላህ መስተንግዶ ሲሆን» ይባላሉ።

41:33

وَمَنۡ أَحۡسَنُ قَوۡلٗا مِّمَّن دَعَآ إِلَى ٱللَّهِ وَعَمِلَ صَٰلِحٗا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ ٱلۡمُسۡلِمِينَ ﴿33﴾

Transliteration: Waman ahsanu qawlan mimman daAAa ila Allahi waAAamila salihan waqala innanee mina almuslimeena

Translation: 33. ወደ አላህ ከጠራንና መልካምንም ከሰራ፤ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለው ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?

41:34

وَلَا تَسۡتَوِي ٱلۡحَسَنَةُ وَلَا ٱلسَّيِّئَةُۚ ٱدۡفَعۡ بِٱلَّتِي هِيَ أَحۡسَنُ فَإِذَا ٱلَّذِي بَيۡنَكَ وَبَيۡنَهُۥ عَدَٰوَةٞ كَأَنَّهُۥ وَلِيٌّ حَمِيمٞ ﴿34﴾

Transliteration: Wala tastawee alhasanatu wala alssayyiatu idfaAA biallatee hiya ahsanu faitha allathee baynaka wabaynahu AAadawatun kaannahu waliyyun hameemun

Translation: 34. መልካሚቱና ክፉይቱም ጸባይ አይስተካሉም በዚያች እርሷ መልካም በሆነችው ጸባይ መጥፎይቱን ገፍትር፤ ያን ጊዜ ባንተና በእርሱ መካከል ጠብ ያለው ሰው እርሱ ልክ እንደ ወዳጅ ዘመድ ይሆናል::

41:35

وَمَا يُلَقَّىٰهَآ إِلَّا ٱلَّذِينَ صَبَرُواْ وَمَا يُلَقَّىٰهَآ إِلَّا ذُو حَظٍّ عَظِيمٖ ﴿35﴾

Transliteration: Wama yulaqqaha illa allatheena sabaroo wama yulaqqaha illa thoo haththin AAatheemin

Translation: 35. ይህችንም ጸባይ እነዚያን የታገሱት እንጂ ሌላው አያገኛትም:: የትልቅም እድል ባለቤት እንጂ ማንም አያገኛትም::

41:36

وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ ٱلشَّيۡطَٰنِ نَزۡغٞ فَٱسۡتَعِذۡ بِٱللَّهِۖ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ ﴿36﴾

Transliteration: Waimma yanzaghannaka mina alshshaytani nazghun faistaAAith biAllahi innahu huwa alssameeAAu alAAaleemu

Translation: 36. ከሰይጣን ጉትጎታ ቢያገኝህ (ከመልካም ጸባይ ቢመልስህ) በአላህ ተጠበቅ እነሆ እርሱ ሁሉን ሰሚና ሁሉን አዋቂ ነውና::

41:37

وَمِنۡ ءَايَٰتِهِ ٱلَّيۡلُ وَٱلنَّهَارُ وَٱلشَّمۡسُ وَٱلۡقَمَرُۚ لَا تَسۡجُدُواْ لِلشَّمۡسِ وَلَا لِلۡقَمَرِ وَٱسۡجُدُواْۤ لِلَّهِۤ ٱلَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمۡ إِيَّاهُ تَعۡبُدُونَ ﴿37﴾

Transliteration: Wamin ayatihi allaylu waalnnaharu waalshshamsu waalqamaru la tasjudoo lilshshamsi wala lilqamari waosjudoo lillahi alathee khalaqahunna in kuntum iyyahu taAAbudoona

Translation: 37. ሌሊትና ቀንም ጸሀይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው። ለጸሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፤ ለዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ:: እርሱን ብቻ የምትገዙ እንደሆናችሁ (ለሌላ አትስገዱ)::

41:38

فَإِنِ ٱسۡتَكۡبَرُواْ فَٱلَّذِينَ عِندَ رَبِّكَ يُسَبِّحُونَ لَهُۥ بِٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِ وَهُمۡ لَا يَسۡـَٔمُونَ۩ ﴿38﴾

Transliteration: Faini istakbaroo faallatheena AAinda rabbika yusabbihoona lahu biallayli waalnnahari wahum la yasamoona

Translation: 38. ቢኮሩም እነዚያ በጌታህ ዘንድ ያሉት መላዕክት በቀንም በሌሊትም ለእርሱ ያወድሳሉ:: እነርሱም አይሰለቹም:: {1}

41:39

وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦٓ أَنَّكَ تَرَى ٱلۡأَرۡضَ خَٰشِعَةٗ فَإِذَآ أَنزَلۡنَا عَلَيۡهَا ٱلۡمَآءَ ٱهۡتَزَّتۡ وَرَبَتۡۚ إِنَّ ٱلَّذِيٓ أَحۡيَاهَا لَمُحۡيِ ٱلۡمَوۡتَىٰٓۚ إِنَّهُۥ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ ﴿39﴾

Transliteration: Wamin ayatihi annaka tara alarda khashiAAatan faitha anzalna AAalayha almaa ihtazzat warabat inna allathee ahyaha lamuhyee almawta innahu AAala kulli shayin qadeerun

Translation: 39. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ምድርን ደረቅ ሆና ማየትህም ከምልክቶቹ ነው:: በእርሷም ላይ ውሃን ባወረድን ጊዜ በቡቃያዎችዋ ትላወሳለች፤ ትነፋለችም። ያ ህያው ያደረጋት ጌታ በእርግጥ ሙታንንም ህያው አድራጊ ነው:: እርሱ በነገሩ ሁሉ ቻይ ነውና።

41:40

إِنَّ ٱلَّذِينَ يُلۡحِدُونَ فِيٓ ءَايَٰتِنَا لَا يَخۡفَوۡنَ عَلَيۡنَآۗ أَفَمَن يُلۡقَىٰ فِي ٱلنَّارِ خَيۡرٌ أَم مَّن يَأۡتِيٓ ءَامِنٗا يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۚ ٱعۡمَلُواْ مَا شِئۡتُمۡ إِنَّهُۥ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٌ ﴿40﴾

Transliteration: Inna allatheena yulhidoona fee ayatina la yakhfawna AAalayna afaman yulqa fee alnnari khayrun am man yatee aminan yawma alqiyamati iAAmaloo ma shitum innahu bima taAAmaloona baseerun

Translation: 40. እነዚያ አናቅጻችንን የሚያጣምሙ በእኛ ላይ አይደበቁም:: (የሚያጣምም) በእሳት ውስጥ የሚጣለው ይበልጣልን? ወይስ በትንሳኤ ቀን ደህነኛ ሆኖ የሚመጣው? የሻችሁትን ስሩ:: ዋጋችሁን ታገላችሁ:: እርሱም (አላህ) የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::

41:41

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِٱلذِّكۡرِ لَمَّا جَآءَهُمۡۖ وَإِنَّهُۥ لَكِتَٰبٌ عَزِيزٞ ﴿41﴾

Transliteration: Inna allatheena kafaroo bialththikri lamma jaahum wainnahu lakitabun AAazeezun

Translation: 41. እነዚያ በቁርኣን እርሱ አሸናፊው መጽሐፍ ሲሆን በመጣላቸው ጊዜ የካዱ ሁሉ ጠፊዎች ናቸው::

41:42

لَّا يَأۡتِيهِ ٱلۡبَٰطِلُ مِنۢ بَيۡنِ يَدَيۡهِ وَلَا مِنۡ خَلۡفِهِۦۖ تَنزِيلٞ مِّنۡ حَكِيمٍ حَمِيدٖ ﴿42﴾

Transliteration: La yateehi albatilu min bayni yadayhi wala min khalfihi tanzeelun min hakeemin hameedin

Translation: 42. ከኋላዉም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም:: ጥበበኛ ምስጉን ከሆነው ጌታ የተወረደ ነው::

41:43

مَّا يُقَالُ لَكَ إِلَّا مَا قَدۡ قِيلَ لِلرُّسُلِ مِن قَبۡلِكَۚ إِنَّ رَبَّكَ لَذُو مَغۡفِرَةٖ وَذُو عِقَابٍ أَلِيمٖ ﴿43﴾

Transliteration: Ma yuqalu laka illa ma qad qeela lilrrusuli min qablika inna rabbaka lathoo maghfiratin wathoo AAiqabin aleemin

Translation: 43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ለነበሩት መልዕክተኞች የተባለው ቢጤ እንጂ ላንተ ሌላ አይባልም:: ጌታህ የምህረት ባለቤትና የአሳማሚ ቅጣትም ባለቤት ነው::

41:44

وَلَوۡ جَعَلۡنَٰهُ قُرۡءَانًا أَعۡجَمِيّٗا لَّقَالُواْ لَوۡلَا فُصِّلَتۡ ءَايَٰتُهُۥٓۖ ءَا۬عۡجَمِيّٞ وَعَرَبِيّٞۗ قُلۡ هُوَ لِلَّذِينَ ءَامَنُواْ هُدٗى وَشِفَآءٞۚ وَٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ فِيٓ ءَاذَانِهِمۡ وَقۡرٞ وَهُوَ عَلَيۡهِمۡ عَمًىۚ أُوْلَـٰٓئِكَ يُنَادَوۡنَ مِن مَّكَانِۭ بَعِيدٖ ﴿44﴾

Transliteration: Walaw jaAAalnahu quranan aAAjamiyyan laqaloo lawla fussilat ayatuhu aaAAjamiyyun waAAarabiyyun qul huwa lillatheena amanoo hudan washifaon waallatheena la yuminoona fee athanihim waqrun wahuwa AAalayhim AAaman olaika yunadawna min makanin baAAeedin

Translation: 44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአዕጀምኛ የሆነ ቁርኣን ባረግነው ኖሮ «አናቅጹ በምናውቀው ቋንቋ አይብራሩም ኖሯልን? (ቁርኣኑ) አዕጀምኛና (መልዕክተኛው) አረባዊ ይሆናልን?» ባሉ ነበር:: እርሱ ለእነዚያ በአላህ ላመኑት ሰዎች መመሪያና መፈወሻ ነው:: እነዚያም የማያምኑት በጆሮዎቻቸው ውስጥ ድንቁርና ነው (አይሰሙትም):: እርሱ በእነርሱ ላይ እውርነት ነው:: እነዚያ ከሩቅ ስፍራ እንደሚጠሩ ናቸው::

41:45

وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ فَٱخۡتُلِفَ فِيهِۚ وَلَوۡلَا كَلِمَةٞ سَبَقَتۡ مِن رَّبِّكَ لَقُضِيَ بَيۡنَهُمۡۚ وَإِنَّهُمۡ لَفِي شَكّٖ مِّنۡهُ مُرِيبٖ ﴿45﴾

Transliteration: Walaqad atayna moosa alkitaba faikhtulifa feehi walawla kalimatun sabaqat min rabbika laqudiya baynahum wainnahum lafee shakkin minhu mureebin

Translation: 45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳንም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው። በእርሱም ተለያዩበት። ከጌታህም ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በመካከላቸው በተፈረደ ነበር፤ እነርሱም በእርሱ አወላዋይ በሆነ ጥርጣሬ ውስጥ ናቸው::

41:46

مَّنۡ عَمِلَ صَٰلِحٗا فَلِنَفۡسِهِۦۖ وَمَنۡ أَسَآءَ فَعَلَيۡهَاۗ وَمَا رَبُّكَ بِظَلَّـٰمٖ لِّلۡعَبِيدِ ﴿46﴾

Transliteration: Man AAamila salihan falinafsihi waman asaa faAAalayha wama rabbuka bithallamin lilAAabeedi

Translation: 46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መልካምን የሰራ ለነፍሱ ነው:: ያጠፋም በእርሷው ላይ ነው:: ጌታህም ለባሮቹ በዳይ አይደለም::

41:47

إِلَيۡهِ يُرَدُّ عِلۡمُ ٱلسَّاعَةِۚ وَمَا تَخۡرُجُ مِن ثَمَرَٰتٖ مِّنۡ أَكۡمَامِهَا وَمَا تَحۡمِلُ مِنۡ أُنثَىٰ وَلَا تَضَعُ إِلَّا بِعِلۡمِهِۦۚ وَيَوۡمَ يُنَادِيهِمۡ أَيۡنَ شُرَكَآءِي قَالُوٓاْ ءَاذَنَّـٰكَ مَامِنَّا مِن شَهِيدٖ ﴿47﴾

Transliteration: Ilayhi yuraddu AAilmu alssaAAati wama takhruju min thamaratin min akmamiha wama tahmilu min ontha wala tadaAAu illa biAAilmihi wayawma yunadeehim ayna shurakaee qaloo athannaka ma minna min shaheedin

Translation: 47. የትንሳኤ መከሰቻ ሰዐቱን ማወቅ ወደ እርሱ ብቻ ይመለሳል:: ከፍሬዎችም ከሽፋኖቻቸው አይወጡም ከሴትም አንዲትም አታረግዝም፤ አትወልድምም በእውቀቱ ቢሆን እንጂ:: «ተጋሪዎቼ የት ናቸው?» በማለት በሚጠራቸው ቀንም ከእኛ ውስጥ («ተጋሪ አለህ» ብሎ) ምንም መስካሪ አለመኖሩን አምነናል» ይላሉ::

41:48

وَضَلَّ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَدۡعُونَ مِن قَبۡلُۖ وَظَنُّواْ مَا لَهُم مِّن مَّحِيصٖ ﴿48﴾

Transliteration: Wadalla AAanhum ma kanoo yadAAoona min qablu wathannoo ma lahum min maheesin

Translation: 48. ያም በፊት ይገዙት የነበሩት ጣዖት ከእነርሱ ይጠፋቸዋል:: ለእነርሱም ምንም መሸሻ የሌላቸው መሆኑን ያረጋግጣሉ::

41:49

لَّا يَسۡـَٔمُ ٱلۡإِنسَٰنُ مِن دُعَآءِ ٱلۡخَيۡرِ وَإِن مَّسَّهُ ٱلشَّرُّ فَيَـُٔوسٞ قَنُوطٞ ﴿49﴾

Transliteration: La yasamu alinsanu min duAAai alkhayri wain massahu alshsharru fayaoosun qanootun

Translation: 49. ሰው በጎ ነገርን ከመለመን አይሰለችም:: ክፋት ቢያገኘው (ግን) ወዲያውኑ በጣም ተስፋ ቆራጭ ተበሳጭ ይሆናል::

41:50

وَلَئِنۡ أَذَقۡنَٰهُ رَحۡمَةٗ مِّنَّا مِنۢ بَعۡدِ ضَرَّآءَ مَسَّتۡهُ لَيَقُولَنَّ هَٰذَا لِي وَمَآ أَظُنُّ ٱلسَّاعَةَ قَآئِمَةٗ وَلَئِن رُّجِعۡتُ إِلَىٰ رَبِّيٓ إِنَّ لِي عِندَهُۥ لَلۡحُسۡنَىٰۚ فَلَنُنَبِّئَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِمَا عَمِلُواْ وَلَنُذِيقَنَّهُم مِّنۡ عَذَابٍ غَلِيظٖ ﴿50﴾

Transliteration: Walain athaqnahu rahmatan minna min baAAdi darraa massathu layaqoolanna hatha lee wama athunnu alssaAAata qaimatan walain rujiAAtu ila rabbee inna lee AAindahu lalhusna falanunabbianna allatheena kafaroo bima AAamiloo walanutheeqannahum min AAathabin ghaleethin

Translation: 50. ካገኘችዉም መከራ በኋላ ከእኛ የሆነን እዝነት ብናቀምሰው «ይህ ለእኔ በስራየ የተገባኝ ነው፤ ሰዓቲቱም መጪ ናት ብየ አላስብም። ወደ ጌታየ ብመለስ (እንኳ) ለእኔ እርሱ ዘንድ መልካሚቱ ገነት በእርግጥ አለችኝ» ይላል:: እነዚህም የካዱትን ስራዎቻቸውን በእርግጥ እንነግራቸዋለን:: ከበረታዉም ስቃይም በእርግጥ እናቀምሳቸዋለን::

41:51

وَإِذَآ أَنۡعَمۡنَا عَلَى ٱلۡإِنسَٰنِ أَعۡرَضَ وَنَـَٔا بِجَانِبِهِۦ وَإِذَا مَسَّهُ ٱلشَّرُّ فَذُو دُعَآءٍ عَرِيضٖ ﴿51﴾

Transliteration: Waitha anAAamna AAala alinsani aAArada wanaa bijanibihi waitha massahu alshsharru fathoo duAAain AAareedin

Translation: 51. በሰዉም ላይ ጸጋችንን በለገስን ጊዜ ከማመስገን ይዞራል በጎኑም ይርቃል:: መከራም ባገኘው ጊዜ የብዙ ልመና ባለቤት ይሆናል::

41:52

قُلۡ أَرَءَيۡتُمۡ إِن كَانَ مِنۡ عِندِ ٱللَّهِ ثُمَّ كَفَرۡتُم بِهِۦ مَنۡ أَضَلُّ مِمَّنۡ هُوَ فِي شِقَاقِۭ بَعِيدٖ ﴿52﴾

Transliteration: Qul araaytum in kana min AAindi Allahi thumma kafartum bihi man adallu mimman huwa fee shiqaqin baAAeedin

Translation: 52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው: «እስቲ ንገሩኝ ቁርኣን ከአላህ ዘንድ ቢሆንና ከዚያም በእርሱ ብትክዱ፤ ከእውነት በራቀ ጭቅጭቅ ላይ ከሆነ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማን ነው?»

41:53

سَنُرِيهِمۡ ءَايَٰتِنَا فِي ٱلۡأٓفَاقِ وَفِيٓ أَنفُسِهِمۡ حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَهُمۡ أَنَّهُ ٱلۡحَقُّۗ أَوَلَمۡ يَكۡفِ بِرَبِّكَ أَنَّهُۥ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ شَهِيدٌ ﴿53﴾

Transliteration: Sanureehim ayatina fee alafaqi wafee anfusihim hatta yatabayyana lahum annahu alhaqqu awalam yakfi birabbika annahu AAala kulli shayin shaheedun

Translation: 53. እርሱም (ቁርኣን) እውነት መሆኑ ለእነርሱ እስከሚገለጽላቸው ድረስ በአጽናፎችና በነፍሶቻቸዉም ውስጥ ያሉትን ታዐምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን:: ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ አዋቂ መሆኑ አይበቃቸዉምን?

41:54

أَلَآ إِنَّهُمۡ فِي مِرۡيَةٖ مِّن لِّقَآءِ رَبِّهِمۡۗ أَلَآ إِنَّهُۥ بِكُلِّ شَيۡءٖ مُّحِيطُۢ ﴿54﴾

Transliteration: Ala innahum fee miryatin min liqai rabbihim ala innahu bikulli shayin muheetun

Translation: 54. (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ! እነርሱ ከጌታቸው ጋር መገናኘትን በመጠራጠር ውስጥ ናቸው:: (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ! እርሱ በነገሩ ሁሉ በእውቀቱ ከባቢ ነው::

Transliteration source: English Transliteration by Tanzil. Used under Tanzil's non-commercial terms; see the source and latest updates at Tanzil. Tanzil translation download