quranm◉

Surah Ash-Shuraa transliteration

◉ ሱራ · ∞

42:1

حمٓ ﴿1﴾

Transliteration: Hameem

Translation: 1. ሓ፤ሚይም፤

42:2

عٓسٓقٓ ﴿2﴾

Transliteration: AAaynseenqaf

Translation: 2. ዐይን፤ ሲን፤ ቃፍ::

42:3

كَذَٰلِكَ يُوحِيٓ إِلَيۡكَ وَإِلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكَ ٱللَّهُ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ ﴿3﴾

Transliteration: Kathalika yoohee ilayka waila allatheena min qablika Allahu alAAazeezu alhakeemu

Translation: 3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ እንዳለው አሸናፊውና ጥበበኛው አላህ ወደ አንተ ያወርዳል:: ወደ እነዚያም ካንተ በፊት ወደ ነበሩት ህዝቦችም አውርዷል::

42:4

لَهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۖ وَهُوَ ٱلۡعَلِيُّ ٱلۡعَظِيمُ ﴿4﴾

Transliteration: Lahu ma fee alssamawati wama fee alardi wahuwa alAAaliyyu alAAatheemu

Translation: 4. በሰማያትና በምድር ዉስጥ ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: እርሱም የበላዩ ታላቁ ነው::

42:5

تَكَادُ ٱلسَّمَٰوَٰتُ يَتَفَطَّرۡنَ مِن فَوۡقِهِنَّۚ وَٱلۡمَلَـٰٓئِكَةُ يُسَبِّحُونَ بِحَمۡدِ رَبِّهِمۡ وَيَسۡتَغۡفِرُونَ لِمَن فِي ٱلۡأَرۡضِۗ أَلَآ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ ﴿5﴾

Transliteration: Takadu alssamawatu yatafattarna min fawqihinna waalmalaikatu yusabbihoona bihamdi rabbihim wayastaghfiroona liman fee alardi ala inna Allaha huwa alghafooru alrraheemu

Translation: 5. ከአላህ ፍራቻ የተነሳ ሰማያት ከበላያቸው ሊቀደዱ ይቀርባሉ፤ መላእክትም ጌታቸውን እያመሰገኑ ያጠራሉ:: በምድር ላለው ፍጡርም ምህረትን ይለምናሉ:: (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተዉሉ:: መሀሪውና አዛኙ አላህ ነው::

42:6

وَٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِهِۦٓ أَوۡلِيَآءَ ٱللَّهُ حَفِيظٌ عَلَيۡهِمۡ وَمَآ أَنتَ عَلَيۡهِم بِوَكِيلٖ ﴿6﴾

Transliteration: Waallatheena ittakhathoo min doonihi awliyaa Allahu hafeethun AAalayhim wama anta AAalayhim biwakeelin

Translation: 6. እነዚያም ከእርሱ ሌላ ጣዖታትን ረዳቶች አድርገው የያዙ ሁሉ አላህ በእነርሱ ላይ ተጠባባቂ ነው:: አንተም በእነርሱ ላይ ሀላፊ አይደለህም::

42:7

وَكَذَٰلِكَ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ قُرۡءَانًا عَرَبِيّٗا لِّتُنذِرَ أُمَّ ٱلۡقُرَىٰ وَمَنۡ حَوۡلَهَا وَتُنذِرَ يَوۡمَ ٱلۡجَمۡعِ لَا رَيۡبَ فِيهِۚ فَرِيقٞ فِي ٱلۡجَنَّةِ وَفَرِيقٞ فِي ٱلسَّعِيرِ ﴿7﴾

Transliteration: Wakathalika awhayna ilayka quranan AAarabiyyan litunthira omma alqura waman hawlaha watunthira yawma aljamAAi la rayba feehi fareequn fee aljannati wafareequn fee alssaAAeeri

Translation: 7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁም የከተሞች እናት የሆነችውን የመካን ሰዎችና በአካባቢዋ ያሉትን ህዝቦች ልታስፈራራ የመሰብሰቢያውንም ቀን በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ልታስጠነቅቅ በዐረበኛ ቋንቋ የሆነን ቁርኣንን ወደ አንተ አወረድን:: ከእነርሱም ከፊሉ በገነት ውስጥ ከፊሉም ደግሞ በእሳት ውስጥ ነው::

42:8

وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ لَجَعَلَهُمۡ أُمَّةٗ وَٰحِدَةٗ وَلَٰكِن يُدۡخِلُ مَن يَشَآءُ فِي رَحۡمَتِهِۦۚ وَٱلظَّـٰلِمُونَ مَا لَهُم مِّن وَلِيّٖ وَلَا نَصِيرٍ ﴿8﴾

Transliteration: Walaw shaa Allahu lajaAAalahum ommatan wahidatan walakin yudkhilu man yashao fee rahmatihi waalththalimoona ma lahum min waliyyin wala naseerin

Translation: 8. አላህ በፈለገ ኖሮ ሰዎችን በአንድ ሃይማኖት ላይ የሆኑ አንድ ህዝብ ባደረጋቸው ነበር:: ግን የሚፈልገውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባዋል:: በዳዮች ሁሉ ምንም ወዳጅና ረዳት የላቸዉም::

42:9

أَمِ ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِهِۦٓ أَوۡلِيَآءَۖ فَٱللَّهُ هُوَ ٱلۡوَلِيُّ وَهُوَ يُحۡيِ ٱلۡمَوۡتَىٰ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ ﴿9﴾

Transliteration: Ami ittakhathoo min doonihi awliyaa faAllahu huwa alwaliyyu wahuwa yuhyee almawta wahuwa AAala kulli shayin qadeerun

Translation: 9. ከእርሱ ሌላ ረዳቶች ያዙን? (እነርሱ ረዳቶች አይደሉም) ትክክለኛ ረዳት አላህ ብቻ ነው:: እርሱ ሙታንን ህያው ያደርጋል:: እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነውና::

42:10

وَمَا ٱخۡتَلَفۡتُمۡ فِيهِ مِن شَيۡءٖ فَحُكۡمُهُۥٓ إِلَى ٱللَّهِۚ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبِّي عَلَيۡهِ تَوَكَّلۡتُ وَإِلَيۡهِ أُنِيبُ ﴿10﴾

Transliteration: Wama ikhtalaftum feehi min shayin fahukmuhu ila Allahi thalikumu Allahu rabbee AAalayhi tawakkaltu wailayhi oneebu

Translation: 10. (ሰዎች ሆይ!) «ያ የተለያያችሁበት ነገር ሁሉ ፍርዱ ወደ አላህ ብቻ ነው:: እርሱ (አላህ) ጌታዬ ነው:: በእርሱ ላይ ተመካሁ:: ወደ እርሱም ብቻ እመለሳለሁ» በላቸው::

42:11

فَاطِرُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ جَعَلَ لَكُم مِّنۡ أَنفُسِكُمۡ أَزۡوَٰجٗا وَمِنَ ٱلۡأَنۡعَٰمِ أَزۡوَٰجٗا يَذۡرَؤُكُمۡ فِيهِۚ لَيۡسَ كَمِثۡلِهِۦ شَيۡءٞۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡبَصِيرُ ﴿11﴾

Transliteration: Fatiru alssamawati waalardi jaAAala lakum min anfusikum azwajan wamina alanAAami azwajan yathraokum feehi laysa kamithlihi shayon wahuwa alssameeAAu albaseeru

Translation: 11. ሰማያትንና ምድርን የፈጠረው አላህ ከነፍሶቻችሁ ሴቶችን ከቤት እንሰሳዎችም አይነቶችን (ወንዶችና ሴቶችን) ለእናንተ ፈጠረላችሁ:: በዚህ ድርጊቱም ያባዛችኋል:: የሚመስለው ምንም ነገር የለም:: እርሱ ሁሉን ነገር ሰሚና ሁሉን ተመልካች ነው::

42:12

لَهُۥ مَقَالِيدُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ يَبۡسُطُ ٱلرِّزۡقَ لِمَن يَشَآءُ وَيَقۡدِرُۚ إِنَّهُۥ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٞ ﴿12﴾

Transliteration: Lahu maqaleedu alssamawati waalardi yabsutu alrrizqa liman yashao wayaqdiru innahu bikulli shayin AAaleemun

Translation: 12. የሰማያትና የምድር (ድልቦች) መክፈቻዎች የእርሱ ብቻ ናቸው:: ሲሳይን ለሚፈልገው ሰው ያሰፋል:: ለሚፈልገዉም ያጠባል:: እርሱ ሁሉን ነገር አዋቂ ነውና::

42:13

شَرَعَ لَكُم مِّنَ ٱلدِّينِ مَا وَصَّىٰ بِهِۦ نُوحٗا وَٱلَّذِيٓ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ وَمَا وَصَّيۡنَا بِهِۦٓ إِبۡرَٰهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَىٰٓۖ أَنۡ أَقِيمُواْ ٱلدِّينَ وَلَا تَتَفَرَّقُواْ فِيهِۚ كَبُرَ عَلَى ٱلۡمُشۡرِكِينَ مَا تَدۡعُوهُمۡ إِلَيۡهِۚ ٱللَّهُ يَجۡتَبِيٓ إِلَيۡهِ مَن يَشَآءُ وَيَهۡدِيٓ إِلَيۡهِ مَن يُنِيبُ ﴿13﴾

Transliteration: SharaAAa lakum mina alddeeni ma wassa bihi noohan waallathee awhayna ilayka wama wassayna bihi ibraheema wamoosa waAAeesa an aqeemoo alddeena wala tatafarraqoo feehi kabura AAala almushrikeena ma tadAAoohum ilayhi Allahu yajtabee ilayhi man yashao wayahdee ilayhi man yuneebu

Translation: 13. (ሰዎች ሆይ!) ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑህን ያዘዘበትን ያንንም ወደ አንተ ያወረድነውን ያንንም ኢብራሂምን፤ ሙሳንና ዒሳንም በእርሱ ያዘዝንበት የሆነውን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም ላይ አትለያዩ በማለት ደነገገላችሁ::(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ አጋሪዎች ያ ወደ እርሱ የምትጠራቸው ነገር (ኢስላም) ከበዳቸው:: አላህ የሚፈልገውን ሰው ወደ እርሱ እምነት ይመርጣል:: የሚመለስንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል::

42:14

وَمَا تَفَرَّقُوٓاْ إِلَّا مِنۢ بَعۡدِ مَا جَآءَهُمُ ٱلۡعِلۡمُ بَغۡيَۢا بَيۡنَهُمۡۚ وَلَوۡلَا كَلِمَةٞ سَبَقَتۡ مِن رَّبِّكَ إِلَىٰٓ أَجَلٖ مُّسَمّٗى لَّقُضِيَ بَيۡنَهُمۡۚ وَإِنَّ ٱلَّذِينَ أُورِثُواْ ٱلۡكِتَٰبَ مِنۢ بَعۡدِهِمۡ لَفِي شَكّٖ مِّنۡهُ مُرِيبٖ ﴿14﴾

Transliteration: Wama tafarraqoo illa min baAAdi ma jaahumu alAAilmu baghyan baynahum walawla kalimatun sabaqat min rabbika ila ajalin musamman laqudiya baynahum wainna allatheena oorithoo alkitaba min baAAdihim lafee shakkin minhu mureebin

Translation: 14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሃይማኖት ሰዎች እውቀት ከመጣላቸው በኋላ በመካከላቸው ባለ ወሰን አላፊነት እንጂ በሌላ አልተለያዩም:: እስከተወሰነ ጊዜ በማቆየት ከጌታህ ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በእነርሱ መካከል አሁኑኑ በተፈረደ ነበር:: እነዚያም ከኋላቸው መጽሐፍን እንዲወርሱ የተደረጉት ከእርሱ በእርግጥ ባወላዋይ ጥርጣሬ ውስጥ ናቸው::

42:15

فَلِذَٰلِكَ فَٱدۡعُۖ وَٱسۡتَقِمۡ كَمَآ أُمِرۡتَۖ وَلَا تَتَّبِعۡ أَهۡوَآءَهُمۡۖ وَقُلۡ ءَامَنتُ بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ مِن كِتَٰبٖۖ وَأُمِرۡتُ لِأَعۡدِلَ بَيۡنَكُمُۖ ٱللَّهُ رَبُّنَا وَرَبُّكُمۡۖ لَنَآ أَعۡمَٰلُنَا وَلَكُمۡ أَعۡمَٰلُكُمۡۖ لَا حُجَّةَ بَيۡنَنَا وَبَيۡنَكُمُۖ ٱللَّهُ يَجۡمَعُ بَيۡنَنَاۖ وَإِلَيۡهِ ٱلۡمَصِيرُ ﴿15﴾

Transliteration: Falithalika faodAAu waistaqim kama omirta wala tattabiAA ahwaahum waqul amantu bima anzala Allahu min kitabin waomirtu liaAAdila baynakum Allahu rabbuna warabbukum lana aAAmaluna walakum aAAmalukum la hujjata baynana wabaynakumu Allahu yajmaAAu baynana wailayhi almaseeru

Translation: 15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እዚህ መንገድም ጋኔንንና ሰዎችን ጥራ:: ልክ እንደታዘዝከዉም ቀጥ በል:: ዝንባሌያቸውን አትከተል:: «ከመጽሐፍም አላህ ባወረደው ሁሉ አመንኩ:: በመካከላችሁ በፍርድ ላስተካክልም ታዘዝኩ:: አላህ ጌታችን ጌታችሁም ነው:: ለእኛ ስራዎቻችን አሉን:: ለእናንተም እንዲሁ ስራዎቻችሁ አሏችሁ:: በእኛና በእናንተ መካከል ክርክር የለም:: አላህ በመካከላችን ይሰበስባል:: መመለሻው ወደ እርሱ ብቻ ነው።» በላቸው::

42:16

وَٱلَّذِينَ يُحَآجُّونَ فِي ٱللَّهِ مِنۢ بَعۡدِ مَا ٱسۡتُجِيبَ لَهُۥ حُجَّتُهُمۡ دَاحِضَةٌ عِندَ رَبِّهِمۡ وَعَلَيۡهِمۡ غَضَبٞ وَلَهُمۡ عَذَابٞ شَدِيدٌ ﴿16﴾

Transliteration: Waallatheena yuhajjoona fee Allahi min baAAdi ma istujeeba lahu hujjatuhum dahidatun AAinda rabbihim waAAalayhim ghadabun walahum AAathabun shadeedun

Translation: 16. እነዚያም በአላህ ሃይማኖት ተቀባይነት ካገኘ በኋላ የሚከራከሩት ሰዎች ማስረጃዎቻቸው በጌታቸው ዘንድ ብልሹ (ዉድቅ) ናቸው:: በእነርሱም ላይ የአላህ ቁጣ አለባቸው (ወደቀባቸው):: ለእነርሱም ብርቱ ቅጣት አለባቸው::

42:17

ٱللَّهُ ٱلَّذِيٓ أَنزَلَ ٱلۡكِتَٰبَ بِٱلۡحَقِّ وَٱلۡمِيزَانَۗ وَمَا يُدۡرِيكَ لَعَلَّ ٱلسَّاعَةَ قَرِيبٞ ﴿17﴾

Transliteration: Allahu allathee anzala alkitaba bialhaqqi waalmeezani wama yudreeka laAAalla alssaAAata qareebun

Translation: 17. አላህ ያ መጽሐፉን በእውነት ያወረደ ነው:: ሚዛንንም ልክ እንደዚሁ ያወረደ ነው:: ሰዓቲቱ ምን አልባት ቅርብ ብትሆንስ ምን አሳወቀህ?

42:18

يَسۡتَعۡجِلُ بِهَا ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِهَاۖ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مُشۡفِقُونَ مِنۡهَا وَيَعۡلَمُونَ أَنَّهَا ٱلۡحَقُّۗ أَلَآ إِنَّ ٱلَّذِينَ يُمَارُونَ فِي ٱلسَّاعَةِ لَفِي ضَلَٰلِۭ بَعِيدٍ ﴿18﴾

Transliteration: YastaAAjilu biha allatheena la yuminoona biha waallatheena amanoo mushfiqoona minha wayaAAlamoona annaha alhaqqu ala inna allatheena yumaroona fee alssaAAati lafee dalalin baAAeedin

Translation: 18. እነዚያ በእርሷ የማያምኑት በእርሷ ያቻኩላሉ:: እነዚያ በአላህ ያመኑት ግን ከእርሷ ፈሪዎች ናቸው:: እርሷ እውነት መሆኗንም በትክክል ያውቃሉ:: (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ:: እነዚያ በሰዓቲቱ የሚከራከሩ ሰዎች ሁሉ በእርግጥ ከእውነት በራቀ ስህተት ውስጥ ናቸው::

42:19

ٱللَّهُ لَطِيفُۢ بِعِبَادِهِۦ يَرۡزُقُ مَن يَشَآءُۖ وَهُوَ ٱلۡقَوِيُّ ٱلۡعَزِيزُ ﴿19﴾

Transliteration: Allahu lateefun biAAibadihi yarzuqu man yashao wahuwa alqawiyyu alAAazeezu

Translation: 19. አላህ ለባሮቹ በጣም ሩህሩህ ነው:: ለሚፈልገው ሰውም ሁሉ በሰፊው ሲሳይን ይሰጣል:: እርሱም ብርቱዉ እና አሸናፊው ነው::

42:20

مَن كَانَ يُرِيدُ حَرۡثَ ٱلۡأٓخِرَةِ نَزِدۡ لَهُۥ فِي حَرۡثِهِۦۖ وَمَن كَانَ يُرِيدُ حَرۡثَ ٱلدُّنۡيَا نُؤۡتِهِۦ مِنۡهَا وَمَا لَهُۥ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ مِن نَّصِيبٍ ﴿20﴾

Transliteration: Man kana yureedu hartha alakhirati nazid lahu fee harthihi waman kana yureedu hartha alddunya nutihi minha wama lahu fee alakhirati min naseebin

Translation: 20. በስራው የኋለኛይቱን ዓለም አዝመራ የሚፈልግ ሰው ሁሉ ለእርሱ በአዝመራው ላይ ሌላን እንጨምርለታለን:: የቅርቢቱን ዓለም አዝመራ የሚፈልግ ሰው ግን በእርሷ የተወሰነለትን ብቻ እንሰጠዋለን:: ለእርሱም በኋለኛይቱ ዓለም ምንም ድርሻ የለዉም::

42:21

أَمۡ لَهُمۡ شُرَكَـٰٓؤُاْ شَرَعُواْ لَهُم مِّنَ ٱلدِّينِ مَا لَمۡ يَأۡذَنۢ بِهِ ٱللَّهُۚ وَلَوۡلَا كَلِمَةُ ٱلۡفَصۡلِ لَقُضِيَ بَيۡنَهُمۡۗ وَإِنَّ ٱلظَّـٰلِمِينَ لَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ ﴿21﴾

Transliteration: Am lahum shurakao sharaAAoo lahum mina alddeeni ma lam yathan bihi Allahu walawla kalimatu alfasli laqudiya baynahum wainna alththalimeena lahum AAathabun aleemun

Translation: 21. ከሓዲያን ከአላህ ያልተፈቀደውን ሃይማኖት የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አሏቸውን? የፍርዱ ቃል ባልነበረ ኖሮ በመካከላቸው ወዲያውኑ በተፈረደ ነበር:: በደለኞችም አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ አለባቸው::

42:22

تَرَى ٱلظَّـٰلِمِينَ مُشۡفِقِينَ مِمَّا كَسَبُواْ وَهُوَ وَاقِعُۢ بِهِمۡۗ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّـٰلِحَٰتِ فِي رَوۡضَاتِ ٱلۡجَنَّاتِۖ لَهُم مَّا يَشَآءُونَ عِندَ رَبِّهِمۡۚ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلۡفَضۡلُ ٱلۡكَبِيرُ ﴿22﴾

Transliteration: Tara alththalimeena mushfiqeena mimma kasaboo wahuwa waqiAAun bihim waallatheena amanoo waAAamiloo alssalihati fee rawdati aljannati lahum ma yashaoona AAinda rabbihim thalika huwa alfadlu alkabeeru

Translation: 22. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በደለኞችን በሰሩት ስራ ዋጋ በትንሳኤ ቀን ፈሪዎች ሆነው ታያቸዋለህ:: እርሱም በእነርሱ ላይ የማይቀር ወዳቂ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በአላህ ያመኑና መልካም ስራን የሰሩ ሁሉ በገነት ጨፌዎች ዉስጥ ናቸው:: ለእነርሱም በጌታቸው ዘንድ የሚፈልጉት ሁሉ አለላቸው:: ይህ ታላቅ ችሮታ ነው::

42:23

ذَٰلِكَ ٱلَّذِي يُبَشِّرُ ٱللَّهُ عِبَادَهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّـٰلِحَٰتِۗ قُل لَّآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ أَجۡرًا إِلَّا ٱلۡمَوَدَّةَ فِي ٱلۡقُرۡبَىٰۗ وَمَن يَقۡتَرِفۡ حَسَنَةٗ نَّزِدۡ لَهُۥ فِيهَا حُسۡنًاۚ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ شَكُورٌ ﴿23﴾

Transliteration: Thalika allathee yubashshiru Allahu AAibadahu allatheena amanoo waAAamiloo alssalihati qul la asalukum AAalayhi ajran illa almawaddata fee alqurba waman yaqtarif hasanatan nazid lahu feeha husnan inna Allaha ghafoorun shakoorun

Translation: 23. (ይህ ታላቅ ችሮታ) ያ አላህ እነዚያን በትክክል ያመኑትንና መልካሞችን የሰሩት ባሮቹን የሚያበስርበት ነው::(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መልዕክቴን በማድረሴ ላይ የዝምድና ውዴታየን እንጂ ሌላ ዋጋ አልጠይቃችሁም በላቸው:: መልካም ስራ የሚሰራ ሰው ሁሉ ለእርሱ በእርሷ ላይ መልካምን ነገርን እንጨምርለታለን:: አላህ መሀሪ እና አመስጋኝ ነውና::

42:24

أَمۡ يَقُولُونَ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبٗاۖ فَإِن يَشَإِ ٱللَّهُ يَخۡتِمۡ عَلَىٰ قَلۡبِكَۗ وَيَمۡحُ ٱللَّهُ ٱلۡبَٰطِلَ وَيُحِقُّ ٱلۡحَقَّ بِكَلِمَٰتِهِۦٓۚ إِنَّهُۥ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ ﴿24﴾

Transliteration: Am yaqooloona iftara AAala Allahi kathiban fain yashai Allahu yakhtim AAala qalbika wayamhu Allahu albatila wayuhiqqu alhaqqa bikalimatihi innahu AAaleemun bithati alssudoori

Translation: 24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁንም «በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፈ» ይላሉን? አላህም ቢፈልግ በልብህ ላይ ያትማል:: አላህ ውሸትን ያብሳል:: እውነትንም በቃላቱ ያረጋግጣል:: እርሱ በይፋ የተነገሩት ቀርቶ በልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ አዋቂ ነውና::

42:25

وَهُوَ ٱلَّذِي يَقۡبَلُ ٱلتَّوۡبَةَ عَنۡ عِبَادِهِۦ وَيَعۡفُواْ عَنِ ٱلسَّيِّـَٔاتِ وَيَعۡلَمُ مَا تَفۡعَلُونَ ﴿25﴾

Transliteration: Wahuwa allathee yaqbalu alttawbata AAan AAibadihi wayaAAfoo AAani alssayyiati wayaAAlamu ma tafAAaloona

Translation: 25. እርሱም አላህ ያ ሁልጊዜም ከባሮቹ ንስሀን የሚቀበል ኃጢአቶችንም ይቅር የሚል የምትሰሩትንም ሁሉ የሚያውቅ ጌታ ነው::

42:26

وَيَسۡتَجِيبُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّـٰلِحَٰتِ وَيَزِيدُهُم مِّن فَضۡلِهِۦۚ وَٱلۡكَٰفِرُونَ لَهُمۡ عَذَابٞ شَدِيدٞ ﴿26﴾

Transliteration: Wayastajeebu allatheena amanoo waAAamiloo alssalihati wayazeeduhum min fadlihi waalkafiroona lahum AAathabun shadeedun

Translation: 26. እነዚያም በአላህ ያመኑትና መልካም ተግባሮችን የሰሩትን ልመናቸውን ይቀበላል:: ከችሮታዉም ይጨምርላቸዋል:: ከሓዲያንም ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አለባቸው::

42:27

وَلَوۡ بَسَطَ ٱللَّهُ ٱلرِّزۡقَ لِعِبَادِهِۦ لَبَغَوۡاْ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَٰكِن يُنَزِّلُ بِقَدَرٖ مَّا يَشَآءُۚ إِنَّهُۥ بِعِبَادِهِۦ خَبِيرُۢ بَصِيرٞ ﴿27﴾

Transliteration: Walaw basata Allahu alrrizqa liAAibadihi labaghaw fee alardi walakin yunazzilu biqadarin ma yashao innahu biAAibadihi khabeerun baseerun

Translation: 27. አላህም ለባሮቹ ሁሉ ሲሳይን በዘረጋ ኖሮ በምድር ውስጥ ሁሉም ወሰን ባለፉ ነበር:: ግን የሚፈልገውን በልክ ያወርዳል:: እርሱ በባሮቹ ውስጠ አዋቂ፤ ተመልካች ነውና::

42:28

وَهُوَ ٱلَّذِي يُنَزِّلُ ٱلۡغَيۡثَ مِنۢ بَعۡدِ مَا قَنَطُواْ وَيَنشُرُ رَحۡمَتَهُۥۚ وَهُوَ ٱلۡوَلِيُّ ٱلۡحَمِيدُ ﴿28﴾

Transliteration: Wahuwa allathee yunazzilu alghaytha min baAAdi ma qanatoo wayanshuru rahmatahu wahuwa alwaliyyu alhameedu

Translation: 28. አላህ ያ ተስፋ ከቆረጡ በኋላ ዝናብን የሚያወርድ ችሮታውንም የሚዘረጋ ነው:: እርሱም ረዳቱና ምስጉኑ ነውና::

42:29

وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦ خَلۡقُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَثَّ فِيهِمَا مِن دَآبَّةٖۚ وَهُوَ عَلَىٰ جَمۡعِهِمۡ إِذَا يَشَآءُ قَدِيرٞ ﴿29﴾

Transliteration: Wamin ayatihi khalqu alssamawati waalardi wama baththa feehima min dabbatin wahuwa AAala jamAAihim itha yashao qadeerun

Translation: 29. ሰማያትንና ምድርን መፍጠሩ ከተንቀሳቃሽም በሁለቱ ውስጥ የበተነውን ፍጡር መፍጠሩ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ከፊሎቹ ናቸው:: እርሱም በሚፈልግ ጊዜ እነርሱን በመሰብሰብ ላይ ቻይ ነው::

42:30

وَمَآ أَصَٰبَكُم مِّن مُّصِيبَةٖ فَبِمَا كَسَبَتۡ أَيۡدِيكُمۡ وَيَعۡفُواْ عَن كَثِيرٖ ﴿30﴾

Transliteration: Wama asabakum min museebatin fabima kasabat aydeekum wayaAAfoo AAan katheerin

Translation: 30. (ሰዎች ሆይ!) ማንኛዉም መከራ (ያገኛችሁ ነገር) እጆቻችሁ በሰሩት ኃጢአት ምክንያት ብቻ ነው:: ብዙውንም ይቅር ይላል::

42:31

وَمَآ أَنتُم بِمُعۡجِزِينَ فِي ٱلۡأَرۡضِۖ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ مِن وَلِيّٖ وَلَا نَصِيرٖ ﴿31﴾

Transliteration: Wama antum bimuAAjizeena fee alardi wama lakum min dooni Allahi min waliyyin wala naseerin

Translation: 31. (ሰዎች ሆይ!) እናንተ በምድር ውስጥ የምትሳኑን (አምላጮች) አይደላችሁም:: ለእናንተም ከአላህ ሌላ ወዳጅም ሆነ ረዳት ምንም የላችሁም::

42:32

وَمِنۡ ءَايَٰتِهِ ٱلۡجَوَارِ فِي ٱلۡبَحۡرِ كَٱلۡأَعۡلَٰمِ ﴿32﴾

Transliteration: Wamin ayatihi aljawari fee albahri kaalaAAlami

Translation: 32. በባህር ላይ እንደ ጋራዎች ሆነው ተንሻላዮቹ መርከቦችም ከአስደናቂ ምልክቶቹ ናቸው::

42:33

إِن يَشَأۡ يُسۡكِنِ ٱلرِّيحَ فَيَظۡلَلۡنَ رَوَاكِدَ عَلَىٰ ظَهۡرِهِۦٓۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّكُلِّ صَبَّارٖ شَكُورٍ ﴿33﴾

Transliteration: In yasha yuskini alrreeha fayathlalna rawakida AAala thahrihi inna fee thalika laayatin likulli sabbarin shakoorin

Translation: 33. ቢፈልግ ንፋሱን የረጋ ያደርገዋል:: ከዚያም መርከቦች በባህሩ ጀርባ ላይ የረጉ ይሆናሉ:: በዚህ ውስጥ በጣም ታጋሽ፤ አመስጋኝ ለሆኑ ሁሉ በእርግጥም ብዙ ተዓምራት አሉ::

42:34

أَوۡ يُوبِقۡهُنَّ بِمَا كَسَبُواْ وَيَعۡفُ عَن كَثِيرٖ ﴿34﴾

Transliteration: Aw yoobiqhunna bima kasaboo wayaAAfu AAan katheerin

Translation: 34. ወይም ተሳፋሪዎች በሰሩት ኃጢአት ምክንያት እነርሱን በባህሩ በማስመጥ ያጠፋቸዋል:: ከብዙ ጥፋቶችም ይቅርታ ያደርጋል።

42:35

وَيَعۡلَمَ ٱلَّذِينَ يُجَٰدِلُونَ فِيٓ ءَايَٰتِنَا مَا لَهُم مِّن مَّحِيصٖ ﴿35﴾

Transliteration: WayaAAlama allatheena yujadiloona fee ayatina ma lahum min maheesin

Translation: 35. ከእነርሱ መካከል እነዚያን በአናቅጻችን የሚከራከሩትን ሰዎች ለማወቅ (ያጠፋቸዋል):: ለእነርሱም ከእርሱ ሌላ ምንም መሸሻ የላቸዉም::

42:36

فَمَآ أُوتِيتُم مِّن شَيۡءٖ فَمَتَٰعُ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۚ وَمَا عِندَ ٱللَّهِ خَيۡرٞ وَأَبۡقَىٰ لِلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَلَىٰ رَبِّهِمۡ يَتَوَكَّلُونَ ﴿36﴾

Transliteration: Fama ooteetum min shayin famataAAu alhayati alddunya wama AAinda Allahi khayrun waabqa lillatheena amanoo waAAala rabbihim yatawakkaloona

Translation: 36. (ሰዎች ሆይ!) የተሰጣችሁት ነገር ሁሉ የቅርቢቱ ሕይወት መጠቃቀሚያ ብቻ ነው:: በአላህ ዘንድ ያለው ምንዳ ግን ለእነዚያ በትክክል በእሱ ላመኑትና በጌታቸው ላይ ብቻ ለሚመኩት ሁሉ በላጭና ሁልጊዜ ነዋሪ ነው::

42:37

وَٱلَّذِينَ يَجۡتَنِبُونَ كَبَـٰٓئِرَ ٱلۡإِثۡمِ وَٱلۡفَوَٰحِشَ وَإِذَا مَا غَضِبُواْ هُمۡ يَغۡفِرُونَ ﴿37﴾

Transliteration: Waallatheena yajtaniboona kabaira alithmi waalfawahisha waitha ma ghadiboo hum yaghfiroona

Translation: 37. ለእነዚያም ታላላቅ ሃጢያቶችንና ዝሙትን የሚርቁ፤ በተቆጡም ጊዜ የሚምሩ ለሆኑት፤

42:38

وَٱلَّذِينَ ٱسۡتَجَابُواْ لِرَبِّهِمۡ وَأَقَامُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَأَمۡرُهُمۡ شُورَىٰ بَيۡنَهُمۡ وَمِمَّا رَزَقۡنَٰهُمۡ يُنفِقُونَ ﴿38﴾

Transliteration: Waallatheena istajaboo lirabbihim waaqamoo alssalata waamruhum shoora baynahum wamimma razaqnahum yunfiqoona

Translation: 38. ለእነዚያም የጌታቸውን ጥሪ ለተቀበሉት፤ ሶላትንም ላዘወተሩት፤ በነገራቸው ላይም በመካከላቸው መመካከር ልምዳቸው ለሆነው፤ ከሰጠናቸዉም ሲሳይ ለሚለግሱት፤

42:39

وَٱلَّذِينَ إِذَآ أَصَابَهُمُ ٱلۡبَغۡيُ هُمۡ يَنتَصِرُونَ ﴿39﴾

Transliteration: Waallatheena itha asabahumu albaghyu hum yantasiroona

Translation: 39. ለእነዚያም በደል በደረሰባቸው ጊዜ በመሰሉ የሚመልሱ ለሆኑት (በላጭና ነዋሪ ነው)::

42:40

وَجَزَـٰٓؤُاْ سَيِّئَةٖ سَيِّئَةٞ مِّثۡلُهَاۖ فَمَنۡ عَفَا وَأَصۡلَحَ فَأَجۡرُهُۥ عَلَى ٱللَّهِۚ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلظَّـٰلِمِينَ ﴿40﴾

Transliteration: Wajazao sayyiatin sayyiatun mithluha faman AAafa waaslaha faajruhu AAala Allahi innahu la yuhibbu alththalimeena

Translation: 40. የመጥፎ ነገሮች ሁሉ ዋጋው ተመሳሳዩ መጥፎ ነው:: ይቅር ያለና ያሳመረ ሰው ደግሞ ምንዳው በአላህ ላይ ብቻ ነው:: እርሱ በደለኞችን አይወድምና::

42:41

وَلَمَنِ ٱنتَصَرَ بَعۡدَ ظُلۡمِهِۦ فَأُوْلَـٰٓئِكَ مَا عَلَيۡهِم مِّن سَبِيلٍ ﴿41﴾

Transliteration: Walamani intasara baAAda thulmihi faolaika ma AAalayhim min sabeelin

Translation: 41. እነዚያ ከተበደሉ በኋላ በመሰሉ የተበቀሉ በእነርሱ ላይ ምንም የወቀሳ መንገድ የለባቸዉም::

42:42

إِنَّمَا ٱلسَّبِيلُ عَلَى ٱلَّذِينَ يَظۡلِمُونَ ٱلنَّاسَ وَيَبۡغُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ بِغَيۡرِ ٱلۡحَقِّۚ أُوْلَـٰٓئِكَ لَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ ﴿42﴾

Transliteration: Innama alssabeelu AAala allatheena yathlimoona alnnasa wayabghoona fee alardi bighayri alhaqqi olaika lahum AAathabun aleemun

Translation: 42. የወቀሳ መንገዱ በእነዚያ ሰዎችን በሚበድሉት እና በምድር ውስጥም ያለ ህግ ወሰንን በሚያልፉት ሰዎች ላይ ብቻ ነው:: እነዚያ ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::

42:43

وَلَمَن صَبَرَ وَغَفَرَ إِنَّ ذَٰلِكَ لَمِنۡ عَزۡمِ ٱلۡأُمُورِ ﴿43﴾

Transliteration: Walaman sabara waghafara inna thalika lamin AAazmi alomoori

Translation: 43. የታገሰና ምህረት ያደረገ፤ ይህ ተግባር በእጅጉን ተፈላጊ ከሆኑ ነገሮች አንዱ ነው::

42:44

وَمَن يُضۡلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِن وَلِيّٖ مِّنۢ بَعۡدِهِۦۗ وَتَرَى ٱلظَّـٰلِمِينَ لَمَّا رَأَوُاْ ٱلۡعَذَابَ يَقُولُونَ هَلۡ إِلَىٰ مَرَدّٖ مِّن سَبِيلٖ ﴿44﴾

Transliteration: Waman yudlili Allahu fama lahu min waliyyin min baAAdihi watara alththalimeena lamma raawoo alAAathaba yaqooloona hal ila maraddin min sabeelin

Translation: 44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የሚያጠመውን ሰው ከእርሱ ማጥመም በኋላ ለእርሱ ምንም ወዳጅ የለዉም:: በደለኞችም ቅጣትን ባዩ ጊዜ «ለመመለስ መንገድ አለን?» የሚሉ ሲሆኑ ታያቸዋለህ::

42:45

وَتَرَىٰهُمۡ يُعۡرَضُونَ عَلَيۡهَا خَٰشِعِينَ مِنَ ٱلذُّلِّ يَنظُرُونَ مِن طَرۡفٍ خَفِيّٖۗ وَقَالَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِنَّ ٱلۡخَٰسِرِينَ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ وَأَهۡلِيهِمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۗ أَلَآ إِنَّ ٱلظَّـٰلِمِينَ فِي عَذَابٖ مُّقِيمٖ ﴿45﴾

Transliteration: Watarahum yuAAradoona AAalayha khashiAAeena mina alththulli yanthuroona min tarfin khafiyyin waqala allatheena amanoo inna alkhasireena allatheena khasiroo anfusahum waahleehim yawma alqiyamati ala inna alththalimeena fee AAathabin muqeemin

Translation: 45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከውርደት የተነሳ ፈሪዎች ሆነው በዓይን ስርቆት ወደ እሳት እያስተዋሉ በእርሷ ላይ የሚቀርቡ ሁነው ታያቸዋለህ:: እነዚያም በአላህ ያመኑት፡- «በእርግጥ ከሳሪዎች ማለት እነዚያ ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን በትንሳኤ ቀን የከሰሩት ናቸው» ይላሉ:: (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተዉሉ:: በደለኞች በእርግጥ ዘወታሪ ስቃይ ውስጥ ናቸው::

42:46

وَمَا كَانَ لَهُم مِّنۡ أَوۡلِيَآءَ يَنصُرُونَهُم مِّن دُونِ ٱللَّهِۗ وَمَن يُضۡلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِن سَبِيلٍ ﴿46﴾

Transliteration: Wama kana lahum min awliyaa yansuroonahum min dooni Allahi waman yudlili Allahu fama lahu min sabeelin

Translation: 46. ለእነርሱም ከአላህ ሌላ የሚረዷቸው ረዳቶች ምንም አልነበሯቸዉም:: አላህ የሚያጠመው ሰው ሁሉ ለእርሱ ወደ እውነት የሚመለስበት ምንም መንገድ የለዉም::

42:47

ٱسۡتَجِيبُواْ لِرَبِّكُم مِّن قَبۡلِ أَن يَأۡتِيَ يَوۡمٞ لَّا مَرَدَّ لَهُۥ مِنَ ٱللَّهِۚ مَا لَكُم مِّن مَّلۡجَإٖ يَوۡمَئِذٖ وَمَا لَكُم مِّن نَّكِيرٖ ﴿47﴾

Transliteration: Istajeeboo lirabbikum min qabli an yatiya yawmun la maradda lahu mina Allahi ma lakum min maljain yawmaithin wama lakum min nakeerin

Translation: 47. ያ ከአላህ ከመጣ መላሽ የሌለለው ቀን ከመምጣቱ በፊት ለጌታችሁ ታዘዙ:: በዚያ ቀን ለእናንተ ምንም መጠጊያም ሆነ መቃወም የላችሁም።

42:48

فَإِنۡ أَعۡرَضُواْ فَمَآ أَرۡسَلۡنَٰكَ عَلَيۡهِمۡ حَفِيظًاۖ إِنۡ عَلَيۡكَ إِلَّا ٱلۡبَلَٰغُۗ وَإِنَّآ إِذَآ أَذَقۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ مِنَّا رَحۡمَةٗ فَرِحَ بِهَاۖ وَإِن تُصِبۡهُمۡ سَيِّئَةُۢ بِمَا قَدَّمَتۡ أَيۡدِيهِمۡ فَإِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ كَفُورٞ ﴿48﴾

Transliteration: Fain aAAradoo fama arsalnaka AAalayhim hafeethan in AAalayka illa albalaghu wainna itha athaqna alinsana minna rahmatan fariha biha wain tusibhum sayyiatun bima qaddamat aydeehim fainna alinsana kafoorun

Translation: 48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢዞሩም (ወቀሳ የለብህም::) በእነርሱ ላይ ጠባቂ አድረገን አላክንህምና:: ባንተ ላይ ማድረስ እንጂ ሌላ የለብህም:: እኛም ሰውን ከእኛ የሆነን ጸጋ ባቀመስነው ጊዜ በእርሷ ይደሰታል:: እጆቻቸው ባስቀደሙት ኃጢአት ምክንያት መከራ ብትደርስባቸው ደግሞ ተስፋ ይቆርጣሉ:: ሰው በጣም ውለታን ከሓዲ ነውና::

42:49

لِّلَّهِ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ يَخۡلُقُ مَا يَشَآءُۚ يَهَبُ لِمَن يَشَآءُ إِنَٰثٗا وَيَهَبُ لِمَن يَشَآءُ ٱلذُّكُورَ ﴿49﴾

Transliteration: Lillahi mulku alssamawati waalardi yakhluqu ma yashao yahabu liman yashao inathan wayahabu liman yashao alththukoora

Translation: 49. የሰማያትና የምድር ንግስና የአላህ ብቻ ነው:: የሚፈልገውን ይፈጥራል:: ለሚፈልገው ሴቶችን ልጆች ይሰጣል:: ለሚፈልገዉም ወንዶችን ይሰጣል::

42:50

أَوۡ يُزَوِّجُهُمۡ ذُكۡرَانٗا وَإِنَٰثٗاۖ وَيَجۡعَلُ مَن يَشَآءُ عَقِيمًاۚ إِنَّهُۥ عَلِيمٞ قَدِيرٞ ﴿50﴾

Transliteration: Aw yuzawwijuhum thukranan wainathan wayajAAalu man yashao AAaqeeman innahu AAaleemun qadeerun

Translation: 50. ወይም ወንዶችንና ሴቶችን አድርጎ ያጠናዳቸዋል:: የሚፈልገውንም መካን ያደርገዋል:: እርሱ ሁሉን አዋቂና ሁሉን ቻይ ነውና::

42:51

وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ ٱللَّهُ إِلَّا وَحۡيًا أَوۡ مِن وَرَآيِٕ حِجَابٍ أَوۡ يُرۡسِلَ رَسُولٗا فَيُوحِيَ بِإِذۡنِهِۦ مَا يَشَآءُۚ إِنَّهُۥ عَلِيٌّ حَكِيمٞ ﴿51﴾

Transliteration: Wama kana libasharin an yukallimahu Allahu illa wahyan aw min warai hijabin aw yursila rasoolan fayoohiya biithnihi ma yashao innahu AAaliyyun hakeemun

Translation: 51. ሰውን አላህ በራዕይ ወይም ከግርዶሹ ወዲያ ወይም መልዕከተኛን በመላክና በፈቃዱ የሚፈልገውን ነገር የሚያወርድለት ቢሆን እንጂ በገሀድ ሊያናግረው ተገቢው አይደለም:: እርሱ የበላይና ጥበበኛ ነውና::

42:52

وَكَذَٰلِكَ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ رُوحٗا مِّنۡ أَمۡرِنَاۚ مَا كُنتَ تَدۡرِي مَا ٱلۡكِتَٰبُ وَلَا ٱلۡإِيمَٰنُ وَلَٰكِن جَعَلۡنَٰهُ نُورٗا نَّهۡدِي بِهِۦ مَن نَّشَآءُ مِنۡ عِبَادِنَاۚ وَإِنَّكَ لَتَهۡدِيٓ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ ﴿52﴾

Transliteration: Wakathalika awhayna ilayka roohan min amrina ma kunta tadree ma alkitabu wala aleemanu walakin jaAAalnahu nooran nahdee bihi man nashao min AAibadina wainnaka latahdee ila siratin mustaqeemin

Translation: 52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ ወደ አንተ ከትዕዛዛችን ሲሆን ሂወት የሆነውን (ቁርአን) አወረድነው:: መጽሐፉም ሆነ እምነቱ ምን እንደሆነ የምታውቅ አልነበርክም:: ግን ቁርኣንን ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው:: አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ::

42:53

صِرَٰطِ ٱللَّهِ ٱلَّذِي لَهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۗ أَلَآ إِلَى ٱللَّهِ تَصِيرُ ٱلۡأُمُورُ ﴿53﴾

Transliteration: Sirati Allahi allathee lahu ma fee alssamawati wama fee alardi ala ila Allahi taseeru alomooru

Translation: 53. ወደዚያ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ወደ ሆነው ወደ አላህ መንገድ (ትመራለህ):: ሙስሊሞች ሆይ! አስተውሉ:: ነገሮች ሁሉ ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ::

Transliteration source: English Transliteration by Tanzil. Used under Tanzil's non-commercial terms; see the source and latest updates at Tanzil. Tanzil translation download