quranm◉

Surah Al-Mujadila transliteration

◉ ሱራ · ∞

58:1

قَدۡ سَمِعَ ٱللَّهُ قَوۡلَ ٱلَّتِي تُجَٰدِلُكَ فِي زَوۡجِهَا وَتَشۡتَكِيٓ إِلَى ٱللَّهِ وَٱللَّهُ يَسۡمَعُ تَحَاوُرَكُمَآۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعُۢ بَصِيرٌ ﴿1﴾

Transliteration: Qad samiAAa Allahu qawla allatee tujadiluka fee zawjiha watashtakee ila Allahi waAllahu yasmaAAu tahawurakuma inna Allaha sameeAAun baseerun

Translation: 1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የዚያችን በባሏ ጉዳይ ላይ የምትከራከርህንና ወደ አላህ ስሞታን የምታሰማውን ሴትዮ ቃል ሰማ:: አላህ በንግግር መመላለሳችሁን (መወያየታችሁን) ይሰማል:: አላህ (ለሚባለው) ሁሉ ሰሚ (ለሚፈጸመው ሁሉ ነገር) አዋቂ ነውና።

58:2

ٱلَّذِينَ يُظَٰهِرُونَ مِنكُم مِّن نِّسَآئِهِم مَّا هُنَّ أُمَّهَٰتِهِمۡۖ إِنۡ أُمَّهَٰتُهُمۡ إِلَّا ٱلَّـٰٓـِٔي وَلَدۡنَهُمۡۚ وَإِنَّهُمۡ لَيَقُولُونَ مُنكَرٗا مِّنَ ٱلۡقَوۡلِ وَزُورٗاۚ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَعَفُوٌّ غَفُورٞ ﴿2﴾

Transliteration: Allatheena yuthahiroona minkum min nisaihim ma hunna ommahatihim in ommahatuhum illa allaee waladnahum wainnahum layaqooloona munkaran mina alqawli wazooran wainna Allaha laAAafuwwun ghafoorun

Translation: 2. እነዚያ ከናንተ መካከል ሚስቶቻቸውን እንደእናቶቻቸው ጀርባዎች ይሁኑብን በማለት የሚምሉ ሰዎች እነርሱ እናቶቻቸው አይደሉም:: ትክክለኛ እናቶቻቸው እነዚያ የወለዷቸው ሴቶች ብቻ ናቸው:: እነርሱ በዚህ ቃል የተጠላ ንግግርንና ውሸትን በእርግጥ ይናገራሉ:: አላህ ለሚጸጸት ሰው ሁሉ ይቅር ባይና መሀሪ ነው::

58:3

وَٱلَّذِينَ يُظَٰهِرُونَ مِن نِّسَآئِهِمۡ ثُمَّ يَعُودُونَ لِمَا قَالُواْ فَتَحۡرِيرُ رَقَبَةٖ مِّن قَبۡلِ أَن يَتَمَآسَّاۚ ذَٰلِكُمۡ تُوعَظُونَ بِهِۦۚ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ خَبِيرٞ ﴿3﴾

Transliteration: Waallatheena yuthahiroona min nisaihim thumma yaAAoodoona lima qaloo fatahreeru raqabatin min qabli an yatamassa thalikum tooAAathoona bihi waAllahu bima taAAmaloona khabeerun

Translation: 3. እነዚያ ሚስቶቻቸውን እንደእናቶቻቸው ጀርባዎች ይሁኑብን በማለት የሚምሉና ከዚያ ወደ ተናገሩት የሚመለሱ ሳይነካኩ በፊት በባርነት የተያዘችዋን ጫንቃ ነፃ ማውጣት ግዴታ አለባቸው:: ይህ ህግ (የተጠቀሰው ህግ) በእርሱ ትገሰጹበታላችሁ:: አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው።

58:4

فَمَن لَّمۡ يَجِدۡ فَصِيَامُ شَهۡرَيۡنِ مُتَتَابِعَيۡنِ مِن قَبۡلِ أَن يَتَمَآسَّاۖ فَمَن لَّمۡ يَسۡتَطِعۡ فَإِطۡعَامُ سِتِّينَ مِسۡكِينٗاۚ ذَٰلِكَ لِتُؤۡمِنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦۚ وَتِلۡكَ حُدُودُ ٱللَّهِۗ وَلِلۡكَٰفِرِينَ عَذَابٌ أَلِيمٌ ﴿4﴾

Transliteration: Faman lam yajid fasiyamu shahrayni mutatabiAAayni min qabli an yatamassa faman lam yastatiAA faitAAamu sitteena miskeenan thalika lituminoo biAllahi warasoolihi watilka hudoodu Allahi walilkafireena AAathabun aleemun

Translation: 4. ይህን ላላገኘም ሰው ከመነካካታቸው በፊት ሁለት ተከታታይ ወሮችን መፆም አለበት:: ይህን ላልቻለም ሰው ስልሳ ድሆችን ማብላት አለበት:: ይህ በአላህና በመልዕክተኛው እንድታምኑ ነው:: እነኚህ ህግጋት የአላህ ህግጋት ናቸው:: (እናም አትተላለፏቸው::) ለከሓዲያንም ሁሉ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::

58:5

إِنَّ ٱلَّذِينَ يُحَآدُّونَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ كُبِتُواْ كَمَا كُبِتَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ وَقَدۡ أَنزَلۡنَآ ءَايَٰتِۭ بَيِّنَٰتٖۚ وَلِلۡكَٰفِرِينَ عَذَابٞ مُّهِينٞ ﴿5﴾

Transliteration: Inna allatheena yuhaddoona Allaha warasoolahu kubitoo kama kubita allatheena min qablihim waqad anzalna ayatin bayyinatin walilkafireena AAathabun muheenun

Translation: 5. ግልጽ ማስረጃዎችን ያወረድን ስንሆን እነዚያ አላህንና መልዕክተኛውን የሚከራከሩ ሰዎች እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩ ሰዎች እንደተዋረዱት ሁሉ ተዋርደዋል:: ለከሓዲያን አዋራጅ ቅጣት አለባቸው::

58:6

يَوۡمَ يَبۡعَثُهُمُ ٱللَّهُ جَمِيعٗا فَيُنَبِّئُهُم بِمَا عَمِلُوٓاْۚ أَحۡصَىٰهُ ٱللَّهُ وَنَسُوهُۚ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ شَهِيدٌ ﴿6﴾

Transliteration: Yawma yabAAathuhumu Allahu jameeAAan fayunabbiohum bima AAamiloo ahsahu Allahu wanasoohu waAllahu AAala kulli shayin shaheedun

Translation: 6. አላህ ሁላቸውንም በአንድ አድርጎ (አንድም ሳይቀር በአንድ ዓይነት) በሚቀሰቅሳቸው ቀን (ይቀጣቸዋል):: ከዚያም በዚህ ዓለም የሰሩትን ነገር ሁሉ ይነግራቸዋል:: እነርሱ የረሱት ሲሆን (መዝገባቸው ተመዝግቦ ያገኙታል) አላህ ግን አንድም ሳይቀር አውቆታል:: አላህ ሁሉንም ነገር ተመልካች ነውና::

58:7

أَلَمۡ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۖ مَا يَكُونُ مِن نَّجۡوَىٰ ثَلَٰثَةٍ إِلَّا هُوَ رَابِعُهُمۡ وَلَا خَمۡسَةٍ إِلَّا هُوَ سَادِسُهُمۡ وَلَآ أَدۡنَىٰ مِن ذَٰلِكَ وَلَآ أَكۡثَرَ إِلَّا هُوَ مَعَهُمۡ أَيۡنَ مَا كَانُواْۖ ثُمَّ يُنَبِّئُهُم بِمَا عَمِلُواْ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۚ إِنَّ ٱللَّهَ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٌ ﴿7﴾

Transliteration: Alam tara anna Allaha yaAAlamu ma fee alssamawati wama fee alardi ma yakoonu min najwa thalathatin illa huwa rabiAAuhum wala khamsatin illa huwa sadisuhum wala adna min thalika wala akthara illa huwa maAAahum ayna ma kanoo thumma yunabbiohum bima AAamiloo yawma alqiyamati inna Allaha bikulli shayin AAaleemun

Translation: 7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅ መሆኑን አታውቅምን? (በእውነቱ ሁሉንም አካቧል::) የሶስት ሰዎች መንሾካሾክ አይከሰትም፤ አላህ አራተኛው ቢሆን እንጂ፤ የአምስትም ሰዎች መንሾካሾክ አይከሰትም እርሱ ስድስተኛ ቢሆን እንጂ፤ ከዚያ ያነሰም ይሁን የበዛ ሰው መሾካሾክ አይከሰትም እርሱ ባሉበት ቦታ አብሯቸው ቢሆን እንጂ:: ከዚያ በትንሳኤ ቀን የሰሩትን ሁሉ ይነግራቸዋል:: አላህ ሁሉን ነገር አዋቂ ነው።

58:8

أَلَمۡ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ نُهُواْ عَنِ ٱلنَّجۡوَىٰ ثُمَّ يَعُودُونَ لِمَا نُهُواْ عَنۡهُ وَيَتَنَٰجَوۡنَ بِٱلۡإِثۡمِ وَٱلۡعُدۡوَٰنِ وَمَعۡصِيَتِ ٱلرَّسُولِۖ وَإِذَا جَآءُوكَ حَيَّوۡكَ بِمَا لَمۡ يُحَيِّكَ بِهِ ٱللَّهُ وَيَقُولُونَ فِيٓ أَنفُسِهِمۡ لَوۡلَا يُعَذِّبُنَا ٱللَّهُ بِمَا نَقُولُۚ حَسۡبُهُمۡ جَهَنَّمُ يَصۡلَوۡنَهَاۖ فَبِئۡسَ ٱلۡمَصِيرُ ﴿8﴾

Transliteration: Alam tara ila allatheena nuhoo AAani alnnajwa thumma yaAAoodoona lima nuhoo AAanhu wayatanajawna bialithmi waalAAudwani wamaAAsiyati alrrasooli waitha jaooka hayyawka bima lam yuhayyika bihi Allahu wayaqooloona fee anfusihim lawla yuAAaththibuna Allahu bima naqoolu hasbuhum jahannamu yaslawnaha fabisa almaseeru

Translation: 8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ በመጥፎ ነገር ከመመሳጠር ወደ ተከለከሉት፤ ከዚያ ከእርሱ ወደ ተከለከሉት ነገር የሚመለሱትንና በኃጢአት፣ በጠላትነትና መልዕክተኛውን በመቃወም ወደ ሚመሳጠሩ አላየህምን? (ሰላም ሊሉ) ወደ አንተ በመጡ ጊዜ አላህ ባላናገረህ ቃል ያናግሩሃል:: ውስጣቸው ይህ ሰው ነብይ ከሆነ በምንለው ነገር አላህ አይቀጣንም ኖሯልን? (ነብይ ከሆነስ) የለመነውን ነገር አላህ ተቀብሎት በሞትን ነበር ይላሉ:: ገሀነም የሚገቡባት ሲሆኑ ከአሁኑ ሞት ይልቅ በቂያቸው ናት:: ገሀነምም መመለሻነቷ ከፋች!

58:9

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِذَا تَنَٰجَيۡتُمۡ فَلَا تَتَنَٰجَوۡاْ بِٱلۡإِثۡمِ وَٱلۡعُدۡوَٰنِ وَمَعۡصِيَتِ ٱلرَّسُولِ وَتَنَٰجَوۡاْ بِٱلۡبِرِّ وَٱلتَّقۡوَىٰۖ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ ٱلَّذِيٓ إِلَيۡهِ تُحۡشَرُونَ ﴿9﴾

Transliteration: Ya ayyuha allatheena amanoo itha tanajaytum fala tatanajaw bialithmi waalAAudwani wamaAAsiyati alrrasooli watanajaw bialbirri waalttaqwa waittaqoo Allaha allathee ilayhi tuhsharoona

Translation: 9. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በተመሳጠራችሁ ጊዜ በኃጢአት ወሰንን በማለፍና መልዕክተኛውንም በመቃወም አትሾካሾኩ ግን በበጎ ስራና አላህን በመፍራት ተወያዩ:: ያንንም ወደ እርሱ የምትሰበሰቡበትን አላህን ፍሩ::

58:10

إِنَّمَا ٱلنَّجۡوَىٰ مِنَ ٱلشَّيۡطَٰنِ لِيَحۡزُنَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَلَيۡسَ بِضَآرِّهِمۡ شَيۡـًٔا إِلَّا بِإِذۡنِ ٱللَّهِۚ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلۡيَتَوَكَّلِ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ ﴿10﴾

Transliteration: Innama alnnajwa mina alshshaytani liyahzuna allatheena amanoo walaysa bidarrihim shayan illa biithni Allahi waAAala Allahi falyatawakkali almuminoona

Translation: 10. በመጥፎ መመሳጠር ከሰይጣን ማስዋብና ማሳመር የሚመጣ ብቻ ነው:: እነዚያ ያመኑ ሙስሊሞች ያዝኑ ዘንድ ይቀሰቅሰዋል:: ከአላህ ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር የሰይጣንም መመሳጠር በምንም ነገር አይጎዳቸዉም:: እናም ትክክለኛ አማኞች በአላህ ብቻ ይመኩ::

58:11

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِذَا قِيلَ لَكُمۡ تَفَسَّحُواْ فِي ٱلۡمَجَٰلِسِ فَٱفۡسَحُواْ يَفۡسَحِ ٱللَّهُ لَكُمۡۖ وَإِذَا قِيلَ ٱنشُزُواْ فَٱنشُزُواْ يَرۡفَعِ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مِنكُمۡ وَٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡعِلۡمَ دَرَجَٰتٖۚ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ خَبِيرٞ ﴿11﴾

Transliteration: Ya ayyuha allatheena amanoo itha qeela lakum tafassahoo fee almajalisi faifsahoo yafsahi Allahu lakum waitha qeela onshuzoo faonshuzoo yarfaAAi Allahu allatheena amanoo minkum waallatheena ootoo alAAilma darajatin waAllahu bima taAAmaloona khabeerun

Translation: 11. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለእናንተ በመቀመጫዎች ስፍራ ተስፋፉ በተባላችሁ ጊዜ ስፍራን አስፉ:: አላህ በገነት ያሰፋላችኃልና:: ተነሱ በተባለም ጊዜ ተነሱ:: አላህ ከናንተ መካከል እነዚያን በትክክል ያመኑትንና እነዚያንም እውቀትን የተሰጡትን በደረጃዎች (በዚች ዓለምም ሆነ በአኼራ) ከፍ ያደርጋል:: አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አወቂ ነውና::

58:12

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِذَا نَٰجَيۡتُمُ ٱلرَّسُولَ فَقَدِّمُواْ بَيۡنَ يَدَيۡ نَجۡوَىٰكُمۡ صَدَقَةٗۚ ذَٰلِكَ خَيۡرٞ لَّكُمۡ وَأَطۡهَرُۚ فَإِن لَّمۡ تَجِدُواْ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٌ ﴿12﴾

Transliteration: Ya ayyuha allatheena amanoo itha najaytumu alrrasoola faqaddimoo bayna yaday najwakum sadaqatan thalika khayrun lakum waatharu fain lam tajidoo fainna Allaha ghafoorun raheemun

Translation: 12. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከመልዕክተኛው ጋር በተወያያችሁ ጊዜ ከመወያየታችሁ በፊት ምጽዋትን አስቀድሙ:: (ሰደቃ ስጡ):: ይህ (ምጸዋትን አስቀድሞ መስጠት) ለእናንተ መልካምና አጥሪ ነው:: ባታገኙም ምንንም (ሳትከፈሉ) ሳትሰጡ ብትወያዩ ችግር የለባችሁም:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::

58:13

ءَأَشۡفَقۡتُمۡ أَن تُقَدِّمُواْ بَيۡنَ يَدَيۡ نَجۡوَىٰكُمۡ صَدَقَٰتٖۚ فَإِذۡ لَمۡ تَفۡعَلُواْ وَتَابَ ٱللَّهُ عَلَيۡكُمۡ فَأَقِيمُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتُواْ ٱلزَّكَوٰةَ وَأَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥۚ وَٱللَّهُ خَبِيرُۢ بِمَا تَعۡمَلُونَ ﴿13﴾

Transliteration: Aashfaqtum an tuqaddimoo bayna yaday najwakum sadaqatin faith lam tafAAaloo wataba Allahu AAalaykum faaqeemoo alssalata waatoo alzzakata waateeAAoo Allaha warasoolahu waAllahu khabeerun bima taAAmaloona

Translation: 13. ከውይይታችሁ በፊት ምጽዋቶችን በማስቀደም ድህነትን ፈራችሁን? የታዘዛችሁትን ባልሰራችሁ ጊዜ አላህ ከናንተ ጸጸትን የተቀበለ ሲሆን ሶላትን ስገዱ፤ ዘካንም ስጡ፤ አላህንና መልዕክተኛውንም ታዘዙ:: አላህ በምትሰሩት ነገር ውስጠ አዋቂ ነውና::

58:14

أَلَمۡ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ تَوَلَّوۡاْ قَوۡمًا غَضِبَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِم مَّا هُم مِّنكُمۡ وَلَا مِنۡهُمۡ وَيَحۡلِفُونَ عَلَى ٱلۡكَذِبِ وَهُمۡ يَعۡلَمُونَ ﴿14﴾

Transliteration: Alam tara ila allatheena tawallaw qawman ghadiba Allahu AAalayhim ma hum minkum wala minhum wayahlifoona AAala alkathibi wahum yaAAlamoona

Translation: 14. ወደ እነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ የተቆጣባቸውን ህዝቦች (አይሁዶች) ወደ ተወዳጁት አስመሳዮች አላየህምን? እነርሱ ከናንተ አይደሉም:: ከእነርሱም አይደሉም። እያወቁ በውሸት ይምላሉ።

58:15

أَعَدَّ ٱللَّهُ لَهُمۡ عَذَابٗا شَدِيدًاۖ إِنَّهُمۡ سَآءَ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ ﴿15﴾

Transliteration: aAAadda Allahu lahum AAathaban shadeedan innahum saa ma kanoo yaAAmaloona

Translation: 15. አላህ ለእነርሱ (በዚህ መወዳጃና የሀሰት መሀላ) ብርቱ ቅጣትን አዘጋጀ:: እነርሱ ይሰሩት የነበሩት መጥፎ ስራ ምንኛ ከፋ!

58:16

ٱتَّخَذُوٓاْ أَيۡمَٰنَهُمۡ جُنَّةٗ فَصَدُّواْ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ فَلَهُمۡ عَذَابٞ مُّهِينٞ ﴿16﴾

Transliteration: Ittakhathoo aymanahum junnatan fasaddoo AAan sabeeli Allahi falahum AAathabun muheenun

Translation: 16. መሓሎቻቸውን ጋሻ አድርገው ያዙ:: ሰዎችንም ከአላህ መንገድ አገዱ:: ስለዚህ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አለባቸው::

58:17

لَّن تُغۡنِيَ عَنۡهُمۡ أَمۡوَٰلُهُمۡ وَلَآ أَوۡلَٰدُهُم مِّنَ ٱللَّهِ شَيۡـًٔاۚ أُوْلَـٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ ﴿17﴾

Transliteration: Lan tughniya AAanhum amwaluhum wala awladuhum mina Allahi shayan olaika ashabu alnnari hum feeha khalidoona

Translation: 17. ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸውም ከአላህ (ቅጣት) ምንም አያድኗቸዉም:: እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው:: እነርሱ በእርሷ ውስጥ ዘወታሪዎች ናቸው::

58:18

يَوۡمَ يَبۡعَثُهُمُ ٱللَّهُ جَمِيعٗا فَيَحۡلِفُونَ لَهُۥ كَمَا يَحۡلِفُونَ لَكُمۡ وَيَحۡسَبُونَ أَنَّهُمۡ عَلَىٰ شَيۡءٍۚ أَلَآ إِنَّهُمۡ هُمُ ٱلۡكَٰذِبُونَ ﴿18﴾

Transliteration: Yawma yabAAathuhumu Allahu jameeAAan fayahlifoona lahu kama yahlifoona lakum wayahsaboona annahum AAala shayin ala innahum humu alkathiboona

Translation: 18. አላህ የተሰበሰቡ ሆነው በሚያስነሳቸውም ቂያማ ቀን ለእናንተ እንደ ሚምሉላችሁ በሚጠቅም ነገር ላይ መሆናቸውን የሚያስቡ ሆነው ለእርሱም (ለአላህም) ይምላሉ:: ሙስሊሞች አስተዉሉ:: ውሸታሞች እነርሱ ብቻ ናቸው::

58:19

ٱسۡتَحۡوَذَ عَلَيۡهِمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ فَأَنسَىٰهُمۡ ذِكۡرَ ٱللَّهِۚ أُوْلَـٰٓئِكَ حِزۡبُ ٱلشَّيۡطَٰنِۚ أَلَآ إِنَّ حِزۡبَ ٱلشَّيۡطَٰنِ هُمُ ٱلۡخَٰسِرُونَ ﴿19﴾

Transliteration: Istahwatha AAalayhimu alshshaytanu faansahum thikra Allahi olaika hizbu alshshaytani ala inna hizba alshshaytani humu alkhasiroona

Translation: 19. በእነርሱም ላይ ሰይጣን ተሾመባቸው (ተመቻቸባቸው) እናም አላህን ማስታወስን አስረሳቸው( ትዕዛዛቱን ተው):: እነዚያ የሰይጣን ቡድኖች ( ሰራዊቶች) ናቸው:: ሙስሊሞች አስተዉሉ:: የሰይጣን ቡድኖች ከሳሪዎች እነርሱ ብቻ ናቸው::

58:20

إِنَّ ٱلَّذِينَ يُحَآدُّونَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥٓ أُوْلَـٰٓئِكَ فِي ٱلۡأَذَلِّينَ ﴿20﴾

Transliteration: Inna allatheena yuhaddoona Allaha warasoolahu olaika fee alathalleena

Translation: 20. እነዚያ አላህንና መልዕክተኛውን የሚከራከሩ ሁሉ እነዚያ በዱንያም ሆነ በአኺራ በጣም ከተዋረዱ ወገኖች ውስጥ ናቸው::

58:21

كَتَبَ ٱللَّهُ لَأَغۡلِبَنَّ أَنَا۠ وَرُسُلِيٓۚ إِنَّ ٱللَّهَ قَوِيٌّ عَزِيزٞ ﴿21﴾

Transliteration: Kataba Allahu laaghlibanna ana warusulee inna Allaha qawiyyun AAazeezun

Translation: 21. አላህ እኔ አሸንፋለሁ መልዕክተኞቼም እንዲሁ ያሸንፋሉ ሲል ድሮውኑ ጽፏል:: አላህ ብርቱና አሸናፊ ነውና::

58:22

لَّا تَجِدُ قَوۡمٗا يُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِ يُوَآدُّونَ مَنۡ حَآدَّ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَلَوۡ كَانُوٓاْ ءَابَآءَهُمۡ أَوۡ أَبۡنَآءَهُمۡ أَوۡ إِخۡوَٰنَهُمۡ أَوۡ عَشِيرَتَهُمۡۚ أُوْلَـٰٓئِكَ كَتَبَ فِي قُلُوبِهِمُ ٱلۡإِيمَٰنَ وَأَيَّدَهُم بِرُوحٖ مِّنۡهُۖ وَيُدۡخِلُهُمۡ جَنَّـٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَاۚ رَضِيَ ٱللَّهُ عَنۡهُمۡ وَرَضُواْ عَنۡهُۚ أُوْلَـٰٓئِكَ حِزۡبُ ٱللَّهِۚ أَلَآ إِنَّ حِزۡبَ ٱللَّهِ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ ﴿22﴾

Transliteration: La tajidu qawman yuminoona biAllahi waalyawmi alakhiri yuwaddoona man hadda Allaha warasoolahu walaw kanoo abaahum aw abnaahum aw ikhwanahum aw AAasheeratahum olaika kataba fee quloobihimu aleemana waayyadahum biroohin minhu wayudkhiluhum jannatin tajree min tahtiha alanharu khalideena feeha radiya Allahu AAanhum waradoo AAanhu olaika hizbu Allahi ala inna hizba Allahi humu almuflihoona

Translation: 22. በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትን ህዝቦች አላህንና መልዕክተኛውን የሚከራከሩት ሰዎች አባቶቻቸው ወይም ልጆቻቸው ወይም ወንድሞቻቸው ወይም ዘመዶቻቸው ቢሆኑም እንኳ የሚወዳጁ ሆነው አታገኛቸዉም:: እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ እምነትን ጽፏል:: ከእርሱም በሆነ መንፈስ ደግፏቸዋል:: ከስሮቻቸዉም ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጣቸው ዘወታሪዎች ሲሆኑ ያስገባቸዋል:: አላህ ተግባራቸውን ወዷል:: እነርሱም የእርሱን ችሮታ ወደዋል:: እነዚያ የአላህ ህዝቦች ናቸው:: ንቁ! የአላህ ህዝቦች ምኞታቸውን የሚያገኙ እነርሱ ናቸው::

Transliteration source: English Transliteration by Tanzil. Used under Tanzil's non-commercial terms; see the source and latest updates at Tanzil. Tanzil translation download