quranm◉

Surah Al-Anfal transliteration

◉ ሱራ · ∞

8:1

يَسۡـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلۡأَنفَالِۖ قُلِ ٱلۡأَنفَالُ لِلَّهِ وَٱلرَّسُولِۖ فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَصۡلِحُواْ ذَاتَ بَيۡنِكُمۡۖ وَأَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥٓ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ ﴿1﴾

Transliteration: Yasaloonaka AAani alanfali quli alanfalu lillahi waalrrasooli faittaqoo Allaha waaslihoo thata baynikum waateeAAoo Allaha warasoolahu in kuntum mumineena

Translation: 1.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጦርነት ከተማረኩ ገንዘቦች ይጠይቁሃል። «በጦርነት የተዘረፉ ገንዘቦች የአላህና የመልዕክተኛው ናቸው:: ስለዚህ አላህን ፍሩ:: በመካከላችሁ ያለውንም ሁኔታ አሳምሩ:: ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ።» በላቸው።

8:2

إِنَّمَا ٱلۡمُؤۡمِنُونَ ٱلَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ ٱللَّهُ وَجِلَتۡ قُلُوبُهُمۡ وَإِذَا تُلِيَتۡ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتُهُۥ زَادَتۡهُمۡ إِيمَٰنٗا وَعَلَىٰ رَبِّهِمۡ يَتَوَكَّلُونَ ﴿2﴾

Transliteration: Innama almuminoona allatheena itha thukira Allahu wajilat quloobuhum waitha tuliyat AAalayhim ayatuhu zadathum eemanan waAAala rabbihim yatawakkaloona

Translation: 2. ፍጹም ትክክለኛ አማኞች ማለት እነዚያ አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚፈሩ፤ በእነርሱም ላይ የቁርኣን አናቅጽ በተነበቡ ጊዜ እምነትን የሚጨምሩላቸውና በጌታቸው ላይ ብቻም የሚመኩት ብቻ ናቸው::

8:3

ٱلَّذِينَ يُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَمِمَّا رَزَقۡنَٰهُمۡ يُنفِقُونَ ﴿3﴾

Transliteration: Allatheena yuqeemoona alssalata wamimma razaqnahum yunfiqoona

Translation: 3. እነዚያ ሰላትንም (ወቅቱን ጠብቀውና ደንቡን አሟልተው) የሚሰግዱና ከሰጠናቸዉም ሲሳይ የሚለግሱ ናቸው::

8:4

أُوْلَـٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ حَقّٗاۚ لَّهُمۡ دَرَجَٰتٌ عِندَ رَبِّهِمۡ وَمَغۡفِرَةٞ وَرِزۡقٞ كَرِيمٞ ﴿4﴾

Transliteration: Olaika humu almuminoona haqqan lahum darajatun AAinda rabbihim wamaghfiratun warizqun kareemun

Translation: 4. እነዚያ ትክክለኛ አማኞች ማለት እነርሱው ናቸው:: ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ብዙ ደረጃዎች፤ የአላህ ምሕረትና የከበረ ሲሳይ አለላቸው::

8:5

كَمَآ أَخۡرَجَكَ رَبُّكَ مِنۢ بَيۡتِكَ بِٱلۡحَقِّ وَإِنَّ فَرِيقٗا مِّنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ لَكَٰرِهُونَ ﴿5﴾

Transliteration: Kama akhrajaka rabbuka min baytika bialhaqqi wainna fareeqan mina almumineena lakarihoona

Translation: 5. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ይህ በምርኮ ክፍያ ሂደት ላይ የታየው የከፊሉ ሰው መጥላት ምሳሌው) ከአማኞች ከፊሉ እየጠሉ ጌታህ ከቤትህ በእውነት ላይ ሆነህ እንዳወጣህ ምሳሌ ነው::

8:6

يُجَٰدِلُونَكَ فِي ٱلۡحَقِّ بَعۡدَ مَا تَبَيَّنَ كَأَنَّمَا يُسَاقُونَ إِلَى ٱلۡمَوۡتِ وَهُمۡ يَنظُرُونَ ﴿6﴾

Transliteration: Yujadiloonaka fee alhaqqi baAAdama tabayyana kaannama yusaqoona ila almawti wahum yanthuroona

Translation: 6.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱ እያዩ ወደ ሞት እንደሚነዱ ሆነው በእውነቱ ነገር ላይ በመጋደል ግዴታነት ከተገለጸላቸው በኋላ ይከራከሩሃል::

8:7

وَإِذۡ يَعِدُكُمُ ٱللَّهُ إِحۡدَى ٱلطَّآئِفَتَيۡنِ أَنَّهَا لَكُمۡ وَتَوَدُّونَ أَنَّ غَيۡرَ ذَاتِ ٱلشَّوۡكَةِ تَكُونُ لَكُمۡ وَيُرِيدُ ٱللَّهُ أَن يُحِقَّ ٱلۡحَقَّ بِكَلِمَٰتِهِۦ وَيَقۡطَعَ دَابِرَ ٱلۡكَٰفِرِينَ ﴿7﴾

Transliteration: Waith yaAAidukumu Allahu ihda alttaifatayni annaha lakum watawaddoona anna ghayra thati alshshawkati takoonu lakum wayureedu Allahu an yuhiqqa alhaqqa bikalimatihi wayaqtaAAa dabira alkafireena

Translation: 7. (እናንተ ተከራካሪዎች ሆይ!)፤ አላህ ከሁለቱ ቡድኖች አንደኛዋን ለእናንተ ናት ሲል ተስፋ በሰጣችሁና የኃይል ባለቤት ያልሆነችውን የነጋዴይቱን ቡድን ለእናንተ ልትሆን በወደዳችሁ ጊዜ አላህም በተስፋ ቃላቱ እውነቱን ማረጋገጡን ሊገልጽና የካሓዲያንንም መጨረሻ ሊቆርጥ በፈለገ ጊዜ (የሆነውን አስታውስ)::

8:8

لِيُحِقَّ ٱلۡحَقَّ وَيُبۡطِلَ ٱلۡبَٰطِلَ وَلَوۡ كَرِهَ ٱلۡمُجۡرِمُونَ ﴿8﴾

Transliteration: Liyuhiqqa alhaqqa wayubtila albatila walaw kariha almujrimoona

Translation: 8. ይህንንም ያደረገው አጋሪዎቹ ቢጠሉም እውነቱን ሊያረጋግጥና ክህደትን ሊያጠፋ ነው::

8:9

إِذۡ تَسۡتَغِيثُونَ رَبَّكُمۡ فَٱسۡتَجَابَ لَكُمۡ أَنِّي مُمِدُّكُم بِأَلۡفٖ مِّنَ ٱلۡمَلَـٰٓئِكَةِ مُرۡدِفِينَ ﴿9﴾

Transliteration: Ith tastagheethoona rabbakum faistajaba lakum annee mumiddukum bialfin mina almalaikati murdifeena

Translation: 9. (ሙስሊሞች ሆይ!) ከጌታችሁ እርዳታን በፈለጋችሁ ጊዜ «እኔ በሺህ መላዕክት ተከታታዮች ሲሆኑ እረዳችኋለሁ።» ሲል ለእናንተ የተቀበላችሁን አስታውሱ።

8:10

وَمَا جَعَلَهُ ٱللَّهُ إِلَّا بُشۡرَىٰ وَلِتَطۡمَئِنَّ بِهِۦ قُلُوبُكُمۡۚ وَمَا ٱلنَّصۡرُ إِلَّا مِنۡ عِندِ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ ﴿10﴾

Transliteration: Wama jaAAalahu Allahu illa bushra walitatmainna bihi quloobukum wama alnnasru illa min AAindi Allahi inna Allaha AAazeezun hakeemun

Translation: 10. አላህ ይህንን እርዳታ ለብስራትና ልቦቻችሁ በእርሱ ሊረኩበት እንጂ ለሌላ አላደረገዉም:: ድልም የሚገኘው ከአላህ ዘንድ ብቻ ነው:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::

8:11

إِذۡ يُغَشِّيكُمُ ٱلنُّعَاسَ أَمَنَةٗ مِّنۡهُ وَيُنَزِّلُ عَلَيۡكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ لِّيُطَهِّرَكُم بِهِۦ وَيُذۡهِبَ عَنكُمۡ رِجۡزَ ٱلشَّيۡطَٰنِ وَلِيَرۡبِطَ عَلَىٰ قُلُوبِكُمۡ وَيُثَبِّتَ بِهِ ٱلۡأَقۡدَامَ ﴿11﴾

Transliteration: Ith yughashsheekumu alnnuAAasa amanatan minhu wayunazzilu AAalaykum mina alssamai maan liyutahhirakum bihi wayuthhiba AAankum rijza alshshaytani waliyarbita AAala quloobikum wayuthabbita bihi alaqdama

Translation: 11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) ከእርሱ በሆነው ጸጥታ በጦር ግንባር በእንቅልፍ በሸፈናችሁና ውሃውንም በእርሱ ሊያጠራችሁ፤ የሰይጣንንም ጉትጎታ ከናንተ ላይ ሊያስወግድላችሁ፤ ልቦቻችሁንም በትዕግሥት ሊያጠነክርላችሁ፤ በእርሱም ጫማዎችን በአሸዋው ላይ ሊያደላድልላችሁ በእናንተ ላይ ከሰማይ ዝናብን ባወረደ ጊዜ የሆነውን አስታውስ::

8:12

إِذۡ يُوحِي رَبُّكَ إِلَى ٱلۡمَلَـٰٓئِكَةِ أَنِّي مَعَكُمۡ فَثَبِّتُواْ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْۚ سَأُلۡقِي فِي قُلُوبِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ ٱلرُّعۡبَ فَٱضۡرِبُواْ فَوۡقَ ٱلۡأَعۡنَاقِ وَٱضۡرِبُواْ مِنۡهُمۡ كُلَّ بَنَانٖ ﴿12﴾

Transliteration: Ith yoohee rabbuka ila almalaikati annee maAAakum fathabbitoo allatheena amanoo saolqee fee quloobi allatheena kafaroo alrruAAba faidriboo fawqa alaAAnaqi waidriboo minhum kulla bananin

Translation: 12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ወደ መላዕክቱ «እኔ በእርዳታዬ ከናንተ ጋር ነኝና እነዚያን በእኔ ያመኑትን ሰዎች አጽናኑ:: በእነዚያ በአላህ በካዱት ልቦች ውስጥ ደግሞ ፍርሀትን እጥላለሁ:: ከአንገቶችም በላይ እራሶችን ምቱ:: ከእነርሱም የቅርንጫፎችን መለያ ( አትቆች) ሁሉ ምቱ።» ሲል ያወረደውን አስታውስ።

8:13

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ شَآقُّواْ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥۚ وَمَن يُشَاقِقِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ فَإِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ ﴿13﴾

Transliteration: Thalika biannahum shaqqoo Allaha warasoolahu waman yushaqiqi Allaha warasoolahu fainna Allaha shadeedu alAAiqabi

Translation: 13. ይህ የሆነው በአላህና በመልዕክተኛው ስለካዱ ነው:: አላህንና መልዕክተኛውን ለሚቃወም ሁሉ አላህም ቅጣቱ ብርቱ ነው::

8:14

ذَٰلِكُمۡ فَذُوقُوهُ وَأَنَّ لِلۡكَٰفِرِينَ عَذَابَ ٱلنَّارِ ﴿14﴾

Transliteration: Thalikum fathooqoohu waanna lilkafireena AAathaba alnnari

Translation: 14. (ከሓዲያን ሆይ!) ይህ ቅጣታችሁ ነው:: እናም ቅመሱት:: ለከሓዲያን የገሀነም እሳት ቅጣት በእርግጥ አለባቸው::

8:15

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِذَا لَقِيتُمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ زَحۡفٗا فَلَا تُوَلُّوهُمُ ٱلۡأَدۡبَارَ ﴿15﴾

Transliteration: Ya ayyuha allatheena amanoo itha laqeetumu allatheena kafaroo zahfan fala tuwalloohumu aladbara

Translation: 15. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያን በአላህ የካዱትን ለጦር ሲጓዙ ባገኛቹኋቸው ጊዜ ጀርባዎችን አታዙሩላቸው::

8:16

وَمَن يُوَلِّهِمۡ يَوۡمَئِذٖ دُبُرَهُۥٓ إِلَّا مُتَحَرِّفٗا لِّقِتَالٍ أَوۡ مُتَحَيِّزًا إِلَىٰ فِئَةٖ فَقَدۡ بَآءَ بِغَضَبٖ مِّنَ ٱللَّهِ وَمَأۡوَىٰهُ جَهَنَّمُۖ وَبِئۡسَ ٱلۡمَصِيرُ ﴿16﴾

Transliteration: Waman yuwallihim yawmaithin duburahu illa mutaharrifan liqitalin aw mutahayyizan ila fiatin faqad baa bighadabin mina Allahi wamawahu jahannamu wabisa almaseeru

Translation: 16. ያን ጊዜ ለግድያ ለመዘዋወር ወይም ወደ ሰራዊት ለመቀላቀል ሳይሆን ጀርባውን የሚያዞርላቸው ሰው ሁሉ ከአላህ የሆነን ቁጣ አትርፏል። መኖሪያዉም ገሀነም ናት:: የገሀነም መመለሻነትም ከፋ!

8:17

فَلَمۡ تَقۡتُلُوهُمۡ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ قَتَلَهُمۡۚ وَمَا رَمَيۡتَ إِذۡ رَمَيۡتَ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ رَمَىٰ وَلِيُبۡلِيَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ مِنۡهُ بَلَآءً حَسَنًاۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٞ ﴿17﴾

Transliteration: Falam taqtuloohum walakinna Allaha qatalahum wama ramayta ith ramayta walakinna Allaha rama waliyubliya almumineena minhu balaan hasanan inna Allaha sameeAAun AAaleemun

Translation: 17. እናንተ አልገደላችኋቸዉም:: ግን አላህ ገደላቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጭብጥን አፈር በወረወርክም ጊዜ አንተ አልወረወርክም:: ግን አላህ ወረወረ። አማኞችን ሁሉ ከእርሱ የሆነን መልካም ፈተናን ለመፈተን ይህንን አደረገ። አላህም ሁሉን ሰሚ፤ ሁሉንም አዋቂ ነውና::

8:18

ذَٰلِكُمۡ وَأَنَّ ٱللَّهَ مُوهِنُ كَيۡدِ ٱلۡكَٰفِرِينَ ﴿18﴾

Transliteration: Thalikum waanna Allaha moohinu kaydi alkafireena

Translation: 18. ይህ ከአላህ የተቸረ ዕውነት ነው:: አላህ የከሓዲያንን ሁሉ ተንኮል አድካሚ ነውና::

8:19

إِن تَسۡتَفۡتِحُواْ فَقَدۡ جَآءَكُمُ ٱلۡفَتۡحُۖ وَإِن تَنتَهُواْ فَهُوَ خَيۡرٞ لَّكُمۡۖ وَإِن تَعُودُواْ نَعُدۡ وَلَن تُغۡنِيَ عَنكُمۡ فِئَتُكُمۡ شَيۡـٔٗا وَلَوۡ كَثُرَتۡ وَأَنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ﴿19﴾

Transliteration: In tastaftihoo faqad jaakumu alfathu wain tantahoo fahuwa khayrun lakum wain taAAoodoo naAAud walan tughniya AAankum fiatukum shayan walaw kathurat waanna Allaha maAAa almumineena

Translation: 19. (ከሓዲያን ሆይ!) ፍትሕን ብትጠይቁ ፍትሁ በእርግጥ መጥቶላችኋል:: ክሕደትና መዋጋታችሁን ብትከለከሉም እርሱ ለእናንተ የተሻለ ነው:: ወደ መጋደል ብትመለሱም እንመለሳለን:: ሰራዊታችሁ ብትበዛም እንኳ ለእናንተ ምንም አትጠቅማችሁም:: አላህ ሁልጊዜም ከትክክለኛ አማኞች ጋር ነውና::

8:20

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَلَا تَوَلَّوۡاْ عَنۡهُ وَأَنتُمۡ تَسۡمَعُونَ ﴿20﴾

Transliteration: Ya ayyuha allatheena amanoo ateeAAoo Allaha warasoolahu wala tawallaw AAanhu waantum tasmaAAoona

Translation: 20. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ:: እናንተም እየሰማችሁ ከእርሱ አትሽሹ::

8:21

وَلَا تَكُونُواْ كَٱلَّذِينَ قَالُواْ سَمِعۡنَا وَهُمۡ لَا يَسۡمَعُونَ ﴿21﴾

Transliteration: Wala takoonoo kaallatheena qaloo samiAAna wahum la yasmaAAoona

Translation: 21. እንደነዚያም የማይሰሙ ሲሆኑ ሰማን እንዳሉትም አትሁኑ::

8:22

إِنَّ شَرَّ ٱلدَّوَآبِّ عِندَ ٱللَّهِ ٱلصُّمُّ ٱلۡبُكۡمُ ٱلَّذِينَ لَا يَعۡقِلُونَ ﴿22﴾

Transliteration: Inna sharra alddawabbi AAinda Allahi alssummu albukmu allatheena la yaAAqiloona

Translation: 22. ከተንቀሳቃሾች ፍጡራን ሁሉ አላህ ዘንድ መጥፎዎች ማለት እነዚያ ሐቅን የማይሰሙ ደንቆሮዎቹ፣ እውነትን የማይናገሩና እውነታን የማያስተውሉት ናቸው::

8:23

وَلَوۡ عَلِمَ ٱللَّهُ فِيهِمۡ خَيۡرٗا لَّأَسۡمَعَهُمۡۖ وَلَوۡ أَسۡمَعَهُمۡ لَتَوَلَّواْ وَّهُم مُّعۡرِضُونَ ﴿23﴾

Transliteration: Walaw AAalima Allahu feehim khayran laasmaAAahum walaw asmaAAahum latawallaw wahum muAAridoona

Translation: 23. በውስጣቸው ደግ መኖሩን አላህ ባወቀ ኖሮ የመረዳትን መስማት ያሰማቸው ነበር:: ደግ የሌለባቸው መሆኑን እያወቀ ባሰማቸዉም ኖሮ እነርሱ እውነትን የተዉ ሆነው በሸሹ ነበር።

8:24

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱسۡتَجِيبُواْ لِلَّهِ وَلِلرَّسُولِ إِذَا دَعَاكُمۡ لِمَا يُحۡيِيكُمۡۖ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ يَحُولُ بَيۡنَ ٱلۡمَرۡءِ وَقَلۡبِهِۦ وَأَنَّهُۥٓ إِلَيۡهِ تُحۡشَرُونَ ﴿24﴾

Transliteration: Ya ayyuha allatheena amanoo istajeeboo lillahi walilrrasooli itha daAAakum lima yuhyeekum waiAAlamoo anna Allaha yahoolu bayna almari waqalbihi waannahu ilayhi tuhsharoona

Translation: 24. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! (መልዕክተኛው) ህያው ወደ የሚያደርጋችሁ (እምነት) በጠራችሁ ጊዜ ለአላህና ለመልዕክተኛው ታዘዙ:: አላህ በሰውየውና በልቡ መካከል የሚጋርድ መሆኑንና ወደ እርሱም የምትሰበሰቡ መሆናችሁንም እወቁ::

8:25

وَٱتَّقُواْ فِتۡنَةٗ لَّا تُصِيبَنَّ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ مِنكُمۡ خَآصَّةٗۖ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ ﴿25﴾

Transliteration: Waittaqoo fitnatan la tuseebanna allatheena thalamoo minkum khassatan waiAAlamoo anna Allaha shadeedu alAAiqabi

Translation: 25. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከናንተ መካከል እነዚያን የበደሉትን ብቻ ለይታ የማትጎዳን ፈተና ተጠንቀቁ:: አላህ ቅጣቱ ብርቱ መሆኑንም እወቁ::

8:26

وَٱذۡكُرُوٓاْ إِذۡ أَنتُمۡ قَلِيلٞ مُّسۡتَضۡعَفُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ تَخَافُونَ أَن يَتَخَطَّفَكُمُ ٱلنَّاسُ فَـَٔاوَىٰكُمۡ وَأَيَّدَكُم بِنَصۡرِهِۦ وَرَزَقَكُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَٰتِ لَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ ﴿26﴾

Transliteration: Waothkuroo ith antum qaleelun mustadAAafoona fee alardi takhafoona an yatakhattafakumu alnnasu faawakum waayyadakum binasrihi warazaqakum mina alttayyibati laAAallakum tashkuroona

Translation: 26. (ሙስሊሞች ሆይ!) እናንተ በምድር ላይ የተናቃችሁ ጥቂቶች ሆናችሁ ሳላችሁ ሰዎች ሊነጥቋችሁ የምትፈሩ ስትሆኑ ያስጠጋችሁን፤ በእርዳታዉም ያበረታችሁን፤ ከመልካሞች ሲሳዮችም ታመሰግኑ ዘንድ የሰጣችሁን አላህን አስታውሱ::

8:27

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَخُونُواْ ٱللَّهَ وَٱلرَّسُولَ وَتَخُونُوٓاْ أَمَٰنَٰتِكُمۡ وَأَنتُمۡ تَعۡلَمُونَ ﴿27﴾

Transliteration: Ya ayyuha allatheena amanoo la takhoonoo Allaha waalrrasoola watakhoonoo amanatikum waantum taAAlamoona

Translation: 27. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህንና መልዕክተኛውን አትካዱ:: አደራዎቻችሁንም እያወቃችሁ አትካዱ::

8:28

وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّمَآ أَمۡوَٰلُكُمۡ وَأَوۡلَٰدُكُمۡ فِتۡنَةٞ وَأَنَّ ٱللَّهَ عِندَهُۥٓ أَجۡرٌ عَظِيمٞ ﴿28﴾

Transliteration: WaiAAlamoo annama amwalukum waawladukum fitnatun waanna Allaha AAindahu ajrun AAatheemun

Translation: 28. ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ ለፈተና ብቻ መሆናቸውንና አላህ ዘንድ ታላቅ ምንዳ ያለ መሆኑን ዕወቁ።

8:29

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِن تَتَّقُواْ ٱللَّهَ يَجۡعَل لَّكُمۡ فُرۡقَانٗا وَيُكَفِّرۡ عَنكُمۡ سَيِّـَٔاتِكُمۡ وَيَغۡفِرۡ لَكُمۡۗ وَٱللَّهُ ذُو ٱلۡفَضۡلِ ٱلۡعَظِيمِ ﴿29﴾

Transliteration: Ya ayyuha allatheena amanoo in tattaqoo Allaha yajAAal lakum furqanan wayukaffir AAankum sayyiatikum wayaghfir lakum waAllahu thoo alfadli alAAatheemi

Translation: 29. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ብትፈሩ የእውነት መለያ ብርሃንን ያደርግላችኋል:: ክፉ ሥራዎቻችሁንም ከናንተ ላይ ያብስላችኋል:: እናንተንም ይምርላችኃል:: አላህ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነውና::

8:30

وَإِذۡ يَمۡكُرُ بِكَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لِيُثۡبِتُوكَ أَوۡ يَقۡتُلُوكَ أَوۡ يُخۡرِجُوكَۚ وَيَمۡكُرُونَ وَيَمۡكُرُ ٱللَّهُۖ وَٱللَّهُ خَيۡرُ ٱلۡمَٰكِرِينَ ﴿30﴾

Transliteration: Waith yamkuru bika allatheena kafaroo liyuthbitooka aw yaqtulooka aw yukhrijooka wayamkuroona wayamkuru Allahu waAllahu khayru almakireena

Translation: 30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በአላህ የካዱ ሰዎች ሊያስሩህ ወይም ሊገድሉህ ወይም ከመካ ሊያስወጡህ ባንተ ላይ ባሴሩብህ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: ያሴራሉም:: አላህም ተንኮላቸውን ይመልስባቸዋል:: አላህ ግን ከሴረኞቹ ሁሉ በላይ ነውና::

8:31

وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتُنَا قَالُواْ قَدۡ سَمِعۡنَا لَوۡ نَشَآءُ لَقُلۡنَا مِثۡلَ هَٰذَآ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّآ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ ﴿31﴾

Transliteration: Waitha tutla AAalayhim ayatuna qaloo qad samiAAna law nashao laqulna mithla hatha in hatha illa asateeru alawwaleena

Translation: 31. አናቅጻችን በነርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜም: «በእርግጥ ሰምተናል። በሻን ኖሮ የዚህን አባባል ተመሳሳይ ባልን ነበር:: ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም።» ይላሉ።

8:32

وَإِذۡ قَالُواْ ٱللَّهُمَّ إِن كَانَ هَٰذَا هُوَ ٱلۡحَقَّ مِنۡ عِندِكَ فَأَمۡطِرۡ عَلَيۡنَا حِجَارَةٗ مِّنَ ٱلسَّمَآءِ أَوِ ٱئۡتِنَا بِعَذَابٍ أَلِيمٖ ﴿32﴾

Transliteration: Waith qaloo allahumma in kana hatha huwa alhaqqa min AAindika faamtir AAalayna hijaratan mina alssamai awi itina biAAathabin aleemin

Translation: 32. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታችን ሆይ! ይህ እርሱ ካንተ ዘንድ የተወረደ እውነት እንደሆነ በእኛ ላይ ከሰማይ ድንጋዮችን አዝንብብን ወይም አሳማሚ ቅጣትን አምጣብን።» ባሉጊዜ (የሆነውን አስታውስ)።

8:33

وَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيُعَذِّبَهُمۡ وَأَنتَ فِيهِمۡۚ وَمَا كَانَ ٱللَّهُ مُعَذِّبَهُمۡ وَهُمۡ يَسۡتَغۡفِرُونَ ﴿33﴾

Transliteration: Wama kana Allahu liyuAAaththibahum waanta feehim wama kana Allahu muAAaththibahum wahum yastaghfiroona

Translation: 33. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ በመካከላቸው እያለህ አላህ የሚቀጣቸው አይደለም። እነርሱም ምሕረትን የሚለምኑት ሲሆኑ አላህ የሚቀጣቸው አይደለም።

8:34

وَمَا لَهُمۡ أَلَّا يُعَذِّبَهُمُ ٱللَّهُ وَهُمۡ يَصُدُّونَ عَنِ ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِ وَمَا كَانُوٓاْ أَوۡلِيَآءَهُۥٓۚ إِنۡ أَوۡلِيَآؤُهُۥٓ إِلَّا ٱلۡمُتَّقُونَ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ ﴿34﴾

Transliteration: Wama lahum alla yuAAaththibahumu Allahu wahum yasuddoona AAani almasjidi alharami wama kanoo awliyaahu in awliyaohu illa almuttaqoona walakinna aktharahum la yaAAlamoona

Translation: 34. እነርሱ ከተከበረው መስጊድ የሚከለክሉ ሲሆኑ አላህ የማይቀጣቸው ለመሆኑ ለእነርሱ ምን ዋስትና አላቸው? የቤቱ ጠባቂዎቹ አልነበሩም:: ጠባቂዎቹም ክሕደትን ተጠንቃቂዎቹ እንጂ ሌሎቹ አይደሉም:: ግን አብዛኛዎቹ አያውቁም::

8:35

وَمَا كَانَ صَلَاتُهُمۡ عِندَ ٱلۡبَيۡتِ إِلَّا مُكَآءٗ وَتَصۡدِيَةٗۚ فَذُوقُواْ ٱلۡعَذَابَ بِمَا كُنتُمۡ تَكۡفُرُونَ ﴿35﴾

Transliteration: Wama kana salatuhum AAinda albayti illa mukaan watasdiyatan fathooqoo alAAathaba bima kuntum takfuroona

Translation: 35. በከዕባ ውስጥ ስግደታቸውም ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም። «ትክዱት በነበራችሁትም ነገር ቅጣትን ቅመሱ» (ይባላሉ)::

8:36

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ يُنفِقُونَ أَمۡوَٰلَهُمۡ لِيَصُدُّواْ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِۚ فَسَيُنفِقُونَهَا ثُمَّ تَكُونُ عَلَيۡهِمۡ حَسۡرَةٗ ثُمَّ يُغۡلَبُونَۗ وَٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِلَىٰ جَهَنَّمَ يُحۡشَرُونَ ﴿36﴾

Transliteration: Inna allatheena kafaroo yunfiqoona amwalahum liyasuddoo AAan sabeeli Allahi fasayunfiqoonaha thumma takoonu AAalayhim hasratan thumma yughlaboona waallatheena kafaroo ila jahannama yuhsharoona

Translation: 36. እነዚያ የካዱት ከአላህ መንገድ ሊከለክሉ ገንዘቦቻቸውን ያወጣሉ:: በእርግጥም ያወጡታል:: ከዚያ ግን በእነርሱ ላይ ጸጸት ይሆንባቸዋል:: ከዚያም ይሸነፋሉ:: እነዚያም የካዱት ሁሉ ወደ ገሀነም ይሰበሰባሉ::

8:37

لِيَمِيزَ ٱللَّهُ ٱلۡخَبِيثَ مِنَ ٱلطَّيِّبِ وَيَجۡعَلَ ٱلۡخَبِيثَ بَعۡضَهُۥ عَلَىٰ بَعۡضٖ فَيَرۡكُمَهُۥ جَمِيعٗا فَيَجۡعَلَهُۥ فِي جَهَنَّمَۚ أُوْلَـٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡخَٰسِرُونَ ﴿37﴾

Transliteration: Liyameeza Allahu alkhabeetha mina alttayyibi wayajAAala alkhabeetha baAAdahu AAala baAAdin fayarkumahu jameeAAan fayajAAalahu fee jahannama olaika humu alkhasiroona

Translation: 37. አላህ መጥፎውን ነገር ከመልካሙ ሊለይ መጥፎውንም ከፊሉን በከፊሉ ላይ ሊያደርግና በአንድ ላይ ሊያነባብረው በገሀነም ውስጥም ሊያደርገው (ይሰበሰባሉ):: እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎቹ ናቸው::

8:38

قُل لِّلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِن يَنتَهُواْ يُغۡفَرۡ لَهُم مَّا قَدۡ سَلَفَ وَإِن يَعُودُواْ فَقَدۡ مَضَتۡ سُنَّتُ ٱلۡأَوَّلِينَ ﴿38﴾

Transliteration: Qul lillatheena kafaroo in yantahoo yughfar lahum ma qad salafa wain yaAAoodoo faqad madat sunnatu alawwaleena

Translation: 38. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነዚያ በአላህ ለካዱት ቢከለከሉ ለእነርሱ በእርግጥ ያለፈውን ሥራ ምሕረት እንደሚደረግላቸው፤ ወደ መጋደል ቢመለሱም (እንደምናጠፋቸው ንገራቸው)። የቀድሞዎቹ ሕዝቦች ልማድ በእርግጥ አልፏልና።

8:39

وَقَٰتِلُوهُمۡ حَتَّىٰ لَا تَكُونَ فِتۡنَةٞ وَيَكُونَ ٱلدِّينُ كُلُّهُۥ لِلَّهِۚ فَإِنِ ٱنتَهَوۡاْ فَإِنَّ ٱللَّهَ بِمَا يَعۡمَلُونَ بَصِيرٞ ﴿39﴾

Transliteration: Waqatiloohum hatta la takoona fitnatun wayakoona alddeenu kulluhu lillahi faini intahaw fainna Allaha bima yaAAmaloona baseerun

Translation: 39. ሁከት እስከሚጠፋና ሃይማኖት ሁሉ ለአላህ ብቻ እስከሚሆንም ድረስ ተጋደሏቸው:: ቢከለከሉም አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው::

8:40

وَإِن تَوَلَّوۡاْ فَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ مَوۡلَىٰكُمۡۚ نِعۡمَ ٱلۡمَوۡلَىٰ وَنِعۡمَ ٱلنَّصِيرُ ﴿40﴾

Transliteration: Wain tawallaw faiAAlamoo anna Allaha mawlakum niAAma almawla waniAAma alnnaseeru

Translation: 40. (ሙስሊሞች ሆይ!) ከእምነት ቢዞሩም አላህ ረዳታችሁ መሆኑን እወቁ:: እርሱ ምን ያምር ጠባቂ! ምን ያምርም ረዳት ነው!

8:41

وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّمَا غَنِمۡتُم مِّن شَيۡءٖ فَأَنَّ لِلَّهِ خُمُسَهُۥ وَلِلرَّسُولِ وَلِذِي ٱلۡقُرۡبَىٰ وَٱلۡيَتَٰمَىٰ وَٱلۡمَسَٰكِينِ وَٱبۡنِ ٱلسَّبِيلِ إِن كُنتُمۡ ءَامَنتُم بِٱللَّهِ وَمَآ أَنزَلۡنَا عَلَىٰ عَبۡدِنَا يَوۡمَ ٱلۡفُرۡقَانِ يَوۡمَ ٱلۡتَقَى ٱلۡجَمۡعَانِۗ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ ﴿41﴾

Transliteration: WaiAAlamoo annama ghanimtum min shayin faanna lillahi khumusahu walilrrasooli walithee alqurba waalyatama waalmasakeeni waibni alssabeeli in kuntum amantum biAllahi wama anzalna AAala AAabdina yawma alfurqani yawma iltaqa aljamAAani waAllahu AAala kulli shayin qadeerun

Translation: 41.(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከማንኛዉም ነገር በጦርነት ከካሓዲያን የማረካችሁትም ሁሉ አንድ አምስተኛው ለአላህና ለመልዕክተኛው፤ ለነብዩ የዝምድና ባለቤቶች፤ ለየቲሞች፤ ለሚስኪኖች፤ ለመንገደኞችም የተገባ መሆኑን እወቁ:: በአላህና በዚያም እውነትና ውሸት በተለየበት ቀን ሁለቱ ቡድኖች በተገናኙበት (በበድር) ቀን ባገልጋያችን ላይ ባወረድነውም የምታምኑ እንደ ሆናችሁ ይህንን እወቁ:: አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።

8:42

إِذۡ أَنتُم بِٱلۡعُدۡوَةِ ٱلدُّنۡيَا وَهُم بِٱلۡعُدۡوَةِ ٱلۡقُصۡوَىٰ وَٱلرَّكۡبُ أَسۡفَلَ مِنكُمۡۚ وَلَوۡ تَوَاعَدتُّمۡ لَٱخۡتَلَفۡتُمۡ فِي ٱلۡمِيعَٰدِ وَلَٰكِن لِّيَقۡضِيَ ٱللَّهُ أَمۡرٗا كَانَ مَفۡعُولٗا لِّيَهۡلِكَ مَنۡ هَلَكَ عَنۢ بَيِّنَةٖ وَيَحۡيَىٰ مَنۡ حَيَّ عَنۢ بَيِّنَةٖۗ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَسَمِيعٌ عَلِيمٌ ﴿42﴾

Transliteration: Ith antum bialAAudwati alddunya wahum bialAAudwati alquswa waalrrakbu asfala minkum walaw tawaAAadtum laikhtalaftum fee almeeAAadi walakin liyaqdiya Allahu amran kana mafAAoolan liyahlika man halaka AAan bayyinatin wayahya man hayya AAan bayyinatin wainna Allaha lasameeAAun AAaleemun

Translation: 42. (ሙስሊሞች ሆይ!) እናንተ በቅርቢቱ ዳርቻ ሁናችሁ እነርሱ ደግሞ በሩቂቱ ዳርቻ ሆነው የነጋዴዎቹም ቡድን ከናንተ በታች ሲሆኑ በሰፈራችሁ ጊዜ ያደረግንላችሁን አስታውሱ:: በተቃጠራችሁም ኖሮ ግን በቀጠሮው በተለያያችሁ ነበር:: ግን አላህ ሊሠራው የሚገባውን ነገር ሊፈጽምና የሚጠፋም ከአስረጅ መድረስ በኋላ እንዲጠፋ፤ ሕያው የሚሆንም ከአስረጅ መድረስ በኋላ ሕያው እንዲሆን ያለቀጠሮ አጋጠማችሁ:: አላህ በእርግጥ ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነውና::

8:43

إِذۡ يُرِيكَهُمُ ٱللَّهُ فِي مَنَامِكَ قَلِيلٗاۖ وَلَوۡ أَرَىٰكَهُمۡ كَثِيرٗا لَّفَشِلۡتُمۡ وَلَتَنَٰزَعۡتُمۡ فِي ٱلۡأَمۡرِ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ سَلَّمَۚ إِنَّهُۥ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ ﴿43﴾

Transliteration: Ith yureekahumu Allahu fee manamika qaleelan walaw arakahum katheeran lafashiltum walatanazaAAtum fee alamri walakinna Allaha sallama innahu AAaleemun bithati alssudoori

Translation: 43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በሕልምህ እነርሱን ጥቂት አድርጎ ባሳየህ ጊዜ አስታውስ:: እነርሱን ብዙ አድርጎ ባሳየህም ኖሮ በፈራችሁና በነገሩ በተጨቃጨቃችሁ ነበር ግን አላህ አዳናችሁ:: እርሱ በደረቶች ውስጥ ያለን ሁሉ አዋቂ ነውና::

8:44

وَإِذۡ يُرِيكُمُوهُمۡ إِذِ ٱلۡتَقَيۡتُمۡ فِيٓ أَعۡيُنِكُمۡ قَلِيلٗا وَيُقَلِّلُكُمۡ فِيٓ أَعۡيُنِهِمۡ لِيَقۡضِيَ ٱللَّهُ أَمۡرٗا كَانَ مَفۡعُولٗاۗ وَإِلَى ٱللَّهِ تُرۡجَعُ ٱلۡأُمُورُ ﴿44﴾

Transliteration: Waith yureekumoohum ithi iltaqaytum fee aAAyunikum qaleelan wayuqallilukum fee aAAyunihim liyaqdiya Allahu amran kana mafAAoolan waila Allahi turjaAAu alomooru

Translation: 44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህም ሊሠራው የሚገባን ነገር ይፈጽም ዘንድ በተጋጠማችሁ ጊዜ እነርሱን በዓይኖቻችሁ ጥቂት አድርጎ ያሳያችሁንና በዓይኖቻቸውም ላይ ያሳነሳችሁን (አስታውሱ)፡፡ ነገሮቹም ሁሉ ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ፡፡

8:45

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِذَا لَقِيتُمۡ فِئَةٗ فَٱثۡبُتُواْ وَٱذۡكُرُواْ ٱللَّهَ كَثِيرٗا لَّعَلَّكُمۡ تُفۡلِحُونَ ﴿45﴾

Transliteration: Ya ayyuha allatheena amanoo itha laqeetum fiatan faothbutoo waothkuroo Allaha katheeran laAAallakum tuflihoona

Translation: 45. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሰራዊትን በገጠማችሁ ጊዜ እርጉ (መክቱ):: አላህንም በብዙው አውሱ:: በእርግጥ ትድናላችሁና::

8:46

وَأَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَلَا تَنَٰزَعُواْ فَتَفۡشَلُواْ وَتَذۡهَبَ رِيحُكُمۡۖ وَٱصۡبِرُوٓاْۚ إِنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلصَّـٰبِرِينَ ﴿46﴾

Transliteration: WaateeAAoo Allaha warasoolahu wala tanazaAAoo fatafshaloo watathhaba reehukum waisbiroo inna Allaha maAAa alssabireena

Translation: 46. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ :: አትጨቃጨቁም ትፈራላችሁና ኃይላችሁም ትሄዳለችና:: ታገሡም አላህ በእርዳታው ከትዕግሥተኞች ጋር ነውና::

8:47

وَلَا تَكُونُواْ كَٱلَّذِينَ خَرَجُواْ مِن دِيَٰرِهِم بَطَرٗا وَرِئَآءَ ٱلنَّاسِ وَيَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِۚ وَٱللَّهُ بِمَا يَعۡمَلُونَ مُحِيطٞ ﴿47﴾

Transliteration: Wala takoonoo kaallatheena kharajoo min diyarihim bataran wariaa alnnasi wayasuddoona AAan sabeeli Allahi waAllahu bima yaAAmaloona muheetun

Translation: 47. እንደ እነዚያ ለትዕቢትና ለሰዎች ይዩልኝ ሲሉ ከአላህም መንገድ ለማገድ ከሀገራቸው እንደወጡት ሰዎች አትሁኑ:: አላህ በሚሠሩት ሁሉ በእውቀቱ ከባቢ ነውና::

8:48

وَإِذۡ زَيَّنَ لَهُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ أَعۡمَٰلَهُمۡ وَقَالَ لَا غَالِبَ لَكُمُ ٱلۡيَوۡمَ مِنَ ٱلنَّاسِ وَإِنِّي جَارٞ لَّكُمۡۖ فَلَمَّا تَرَآءَتِ ٱلۡفِئَتَانِ نَكَصَ عَلَىٰ عَقِبَيۡهِ وَقَالَ إِنِّي بَرِيٓءٞ مِّنكُمۡ إِنِّيٓ أَرَىٰ مَا لَا تَرَوۡنَ إِنِّيٓ أَخَافُ ٱللَّهَۚ وَٱللَّهُ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ ﴿48﴾

Transliteration: Waith zayyana lahumu alshshaytanu aAAmalahum waqala la ghaliba lakumu alyawma mina alnnasi wainnee jarun lakum falamma taraati alfiatani nakasa AAala AAaqibayhi waqala innee bareeon minkum innee ara ma la tarawna innee akhafu Allaha waAllahu shadeedu alAAiqabi

Translation: 48. ሰይጣንም ሥራዎቻቸውን ለእነርሱ ባሳመረላቸውና «ዛሬ ለእናንተ ከሰዎች አሸናፊ የላችሁም:: እኔም ለእናንተ ረዳት ነኝ።» ባለ ጊዜም (የሆነውን አስታውስ):: ሁለቱ ቡድኖችም በተያዩ ጊዜ ወደኋላው አፈገፈገ:: «እኔ ከናንተ ንጹህ ነኝ:: እኔ እናንተ የማታዩትን አያለሁ:: እኔ አላህን እፈራለሁ:: አላህም ቅጣተ ብርቱ ነው።» አላቸው::

8:49

إِذۡ يَقُولُ ٱلۡمُنَٰفِقُونَ وَٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٌ غَرَّ هَـٰٓؤُلَآءِ دِينُهُمۡۗ وَمَن يَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱللَّهِ فَإِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٞ ﴿49﴾

Transliteration: Ith yaqoolu almunafiqoona waallatheena fee quloobihim maradun gharra haolai deenuhum waman yatawakkal AAala Allahi fainna Allaha AAazeezun hakeemun

Translation: 49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አስመሳዮችና እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው ሰዎች «እነዚህን ሙስሊሞች ሃይማኖታቸው አታለላቸው።» ባሉ ጊዜ (የነበረውን አስታውስ):: በአላህ ላይ የሚጠጋ (ሁልጊዜም ያሸንፋል):: አላህ ሁሉንም አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::

8:50

وَلَوۡ تَرَىٰٓ إِذۡ يَتَوَفَّى ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ ٱلۡمَلَـٰٓئِكَةُ يَضۡرِبُونَ وُجُوهَهُمۡ وَأَدۡبَٰرَهُمۡ وَذُوقُواْ عَذَابَ ٱلۡحَرِيقِ ﴿50﴾

Transliteration: Walaw tara ith yatawaffa allatheena kafaroo almalaikatu yadriboona wujoohahum waadbarahum wathooqoo AAathaba alhareeqi

Translation: 50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያንም በአላህ የካዱትን ሰዎች መላዕክት ፊቶቻቸውንና ጀርቦቻቸውን እየመቱ «የቃጠሎን ስቃይ ቅመሱ።» እያሉ በሚገድሏቸው ጊዜ ብታይ ኖሮ (አስደንጋጭን ነገር ታይ ነበር)::

8:51

ذَٰلِكَ بِمَا قَدَّمَتۡ أَيۡدِيكُمۡ وَأَنَّ ٱللَّهَ لَيۡسَ بِظَلَّـٰمٖ لِّلۡعَبِيدِ ﴿51﴾

Transliteration: Thalika bima qaddamat aydeekum waanna Allaha laysa bithallamin lilAAabeedi

Translation: 51. «ይህ እጆቻችሁ ባስቀደሙት ምክንያት አላህ ለባሮቹ በዳይ ባለመሆኑ ነው።» ይባላሉ።

8:52

كَدَأۡبِ ءَالِ فِرۡعَوۡنَ وَٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ فَأَخَذَهُمُ ٱللَّهُ بِذُنُوبِهِمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ قَوِيّٞ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ ﴿52﴾

Transliteration: Kadabi ali firAAawna waallatheena min qablihim kafaroo biayati Allahi faakhathahumu Allahu bithunoobihim inna Allaha qawiyyun shadeedu alAAiqabi

Translation: 52. የእነዚያ ሰዎች ልማድ እንደ ፈርዖን ቤተሰብና እንደነዚያም ከእነርሱ በፊት እንደ ነበሩት ህዝቦች ልማድ ነው:: በአላህ አናቅጽ ካዱ:: አላህም በኃጢአቶቻቸው ያዛቸው:: አላህ ሀይለኛና ቅጣተ ብርቱ ነውና::

8:53

ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ لَمۡ يَكُ مُغَيِّرٗا نِّعۡمَةً أَنۡعَمَهَا عَلَىٰ قَوۡمٍ حَتَّىٰ يُغَيِّرُواْ مَا بِأَنفُسِهِمۡ وَأَنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٞ ﴿53﴾

Transliteration: Thalika bianna Allaha lam yaku mughayyiran niAAmatan anAAamaha AAala qawmin hatta yughayyiroo ma bianfusihim waanna Allaha sameeAAun AAaleemun

Translation: 53. ይህ ቅጣት አላህ በሕዝቦች ላይ የለገሰውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን ነገር እስከሚለውጡ ድረስ የማይለውጥ በመሆኑ ምክንያት ነው:: አላህም ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነውና::

8:54

كَدَأۡبِ ءَالِ فِرۡعَوۡنَ وَٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمۡ فَأَهۡلَكۡنَٰهُم بِذُنُوبِهِمۡ وَأَغۡرَقۡنَآ ءَالَ فِرۡعَوۡنَۚ وَكُلّٞ كَانُواْ ظَٰلِمِينَ ﴿54﴾

Transliteration: Kadabi ali firAAawna waallatheena min qablihim kaththaboo biayati rabbihim faahlaknahum bithunoobihim waaghraqna ala firAAawna wakullun kanoo thalimeena

Translation: 54. እንደ ፈርዖን ቤተሰቦችና እንደእነዚያ ከእነርሱ በፊት እንደ ነበሩት ልማድ (እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥባቸዉም)። በጌታቸው ታዓምራት አስተባበሉና በኃጢአቶቻቸው አጠፋናቸው:: የፈርዖንን ቤተሰቦች አስመጥናቸው:: ሁሉም በዳዮች ነበሩና::

8:55

إِنَّ شَرَّ ٱلدَّوَآبِّ عِندَ ٱللَّهِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فَهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ ﴿55﴾

Transliteration: Inna sharra alddawabbi AAinda Allahi allatheena kafaroo fahum la yuminoona

Translation: 55. ከሚንቀሳቀሱ እንስሳዎች ሁሉ አላህ ዘንድ ይበልጥ ክፉዎቹ እነዚያ የካዱት ሰዎች ናቸው:: ስለዚህ እነርሱ አያምኑም።

8:56

ٱلَّذِينَ عَٰهَدتَّ مِنۡهُمۡ ثُمَّ يَنقُضُونَ عَهۡدَهُمۡ فِي كُلِّ مَرَّةٖ وَهُمۡ لَا يَتَّقُونَ ﴿56﴾

Transliteration: Allatheena AAahadta minhum thumma yanqudoona AAahdahum fee kulli marratin wahum la yattaqoona

Translation: 56. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ከእነርሱ ቃል ኪዳን የያዝክባቸውና ከዚያም በየጊዜው ቃል ኪዳናቸውን የሚያፈርሱ ናቸው:: እነርሱም አይጠነቀቁም::

8:57

فَإِمَّا تَثۡقَفَنَّهُمۡ فِي ٱلۡحَرۡبِ فَشَرِّدۡ بِهِم مَّنۡ خَلۡفَهُمۡ لَعَلَّهُمۡ يَذَّكَّرُونَ ﴿57﴾

Transliteration: Faimma tathqafannahum fee alharbi fasharrid bihim man khalfahum laAAallahum yaththakkaroona

Translation: 57. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጦር ላይ ብታገኛቸው በእነርሱ ቅጣት ምክንያት ሌሎቹ ከሓዲያን ይገሠጡ ዘንድ ከኋላቸው ያሉትን በትንባቸው::

8:58

وَإِمَّا تَخَافَنَّ مِن قَوۡمٍ خِيَانَةٗ فَٱنۢبِذۡ إِلَيۡهِمۡ عَلَىٰ سَوَآءٍۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ ٱلۡخَآئِنِينَ ﴿58﴾

Transliteration: Waimma takhafanna min qawmin khiyanatan fainbith ilayhim AAala sawain inna Allaha la yuhibbu alkhaineena

Translation: 58. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሕዝቦችም በኩል ክህደትን ብትፈራ የቃል ኪዳኑን መፍረስ በማወቅ በኩል ተመሳሳይ ሆናችሁ ቃል ኪዳናቸውን ወደ እነርሱ ጣልላቸው:: አላህ ከዳተኞችን ሁሉ አይወድምና::

8:59

وَلَا يَحۡسَبَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ سَبَقُوٓاْۚ إِنَّهُمۡ لَا يُعۡجِزُونَ ﴿59﴾

Transliteration: Wala yahsabanna allatheena kafaroo sabaqoo innahum la yuAAjizoona

Translation: 59. እነዚያም የካዱት ከአላህ ቅጣት ያመለጡ መሆናቸውን አያስቡ:: እነርሱ አያቅቱምና (አያሸንፉምና)::

8:60

وَأَعِدُّواْ لَهُم مَّا ٱسۡتَطَعۡتُم مِّن قُوَّةٖ وَمِن رِّبَاطِ ٱلۡخَيۡلِ تُرۡهِبُونَ بِهِۦ عَدُوَّ ٱللَّهِ وَعَدُوَّكُمۡ وَءَاخَرِينَ مِن دُونِهِمۡ لَا تَعۡلَمُونَهُمُ ٱللَّهُ يَعۡلَمُهُمۡۚ وَمَا تُنفِقُواْ مِن شَيۡءٖ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ يُوَفَّ إِلَيۡكُمۡ وَأَنتُمۡ لَا تُظۡلَمُونَ ﴿60﴾

Transliteration: WaaAAiddoo lahum ma istataAAtum min quwwatin wamin ribati alkhayli turhiboona bihi AAaduwwa Allahi waAAaduwwakum waakhareena min doonihim la taAAlamoonahumu Allahu yaAAlamuhum wama tunfiqoo min shayin fee sabeeli Allahi yuwaffa ilaykum waantum la tuthlamoona

Translation: 60. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ለእነርሱ ከማንኛውም ኃይልና ከታጀቡ ፈረሶች የቻላችሁትን ሁሉ በእርሱ የአላህን ጠላትና ጠላታችሁን ሌሎችንም ከእነርሱ በስተቀር ያሉትን የማታውቋቸውን አላህ ብቻ የሚያውቃቸውን አስመሳዮች የምታሸብሩበት ስትሆኑ አዘጋጁላቸው:: ከማንኛዉም ነገር በአላህ መንገድ የምትለግሱት ምንዳው ወደ እናንተ በሙሉ ይሰጣል:: እናንተ ቅንጣት አትበደሉም::

8:61

وَإِن جَنَحُواْ لِلسَّلۡمِ فَٱجۡنَحۡ لَهَا وَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱللَّهِۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ ﴿61﴾

Transliteration: Wain janahoo lilssalmi faijnah laha watawakkal AAala Allahi innahu huwa alssameeAAu alAAaleemu

Translation: 61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ ዕርቅ ቢያዘነብሉ አንተም ወደ እርቁ ተዘንበልና በአላህ ላይ ብቻ ተመካ:: እነሆ እርሱ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን አዋቂው ነውና።

8:62

وَإِن يُرِيدُوٓاْ أَن يَخۡدَعُوكَ فَإِنَّ حَسۡبَكَ ٱللَّهُۚ هُوَ ٱلَّذِيٓ أَيَّدَكَ بِنَصۡرِهِۦ وَبِٱلۡمُؤۡمِنِينَ ﴿62﴾

Transliteration: Wain yureedoo an yakhdaAAooka fainna hasbaka Allahu huwa allathee ayyadaka binasrihi wabialmumineena

Translation: 62. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሊያታልሉህ ቢፈልጉ አላህ በቂህ ነው:: እርሱ ያ በእርዳታውና በምዕምናን ያበረታህ ነውና::

8:63

وَأَلَّفَ بَيۡنَ قُلُوبِهِمۡۚ لَوۡ أَنفَقۡتَ مَا فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗا مَّآ أَلَّفۡتَ بَيۡنَ قُلُوبِهِمۡ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ أَلَّفَ بَيۡنَهُمۡۚ إِنَّهُۥ عَزِيزٌ حَكِيمٞ ﴿63﴾

Transliteration: Waallafa bayna quloobihim law anfaqta ma fee alardi jameeAAan ma allafta bayna quloobihim walakinna Allaha allafa baynahum innahu AAazeezun hakeemun

Translation: 63. በልቦቻቸውም መካከል ያስማማ ነው፡፡ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በምድር ያለውን ሁሉ ሀብት ብትለገስ ኖሮ እንኳን በልቦቻቸው መካከል ባላስማማህ ነበር:: ግን አላህ በመካከላቸው አስማማ:: እርሱ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::

8:64

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ حَسۡبُكَ ٱللَّهُ وَمَنِ ٱتَّبَعَكَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ﴿64﴾

Transliteration: Ya ayyuha alnnabiyyu hasbuka Allahu wamani ittabaAAaka mina almumineena

Translation: 64. አንተ ነብይ ሆይ! ለሁሉ ነገር በቂህ አላህ ነው:: ለተከተሉህም ምዕምናን በቂያቸው አላህ ነው::

8:65

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ حَرِّضِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ عَلَى ٱلۡقِتَالِۚ إِن يَكُن مِّنكُمۡ عِشۡرُونَ صَٰبِرُونَ يَغۡلِبُواْ مِاْئَتَيۡنِۚ وَإِن يَكُن مِّنكُم مِّاْئَةٞ يَغۡلِبُوٓاْ أَلۡفٗا مِّنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِأَنَّهُمۡ قَوۡمٞ لَّا يَفۡقَهُونَ ﴿65﴾

Transliteration: Ya ayyuha alnnabiyyu harridi almumineena AAala alqitali in yakun minkum AAishroona sabiroona yaghliboo miatayni wain yakun minkum miatun yaghliboo alfan mina allatheena kafaroo biannahum qawmun la yafqahoona

Translation: 65. አንተ ነብይ ሆይ! አማኞችን ጠላቶቻቸውን በመዋጋት ላይ አደፋፍራቸው:: ከናንተ ውስጥ ሃያ ታጋሾች ቢኖሩ ሁለት መቶን ያሸንፋሉ:: ከናንተም መካከል መቶ ሰዎች ቢኖሩ ከእነዚያ ከካዱት ሕዝቦች መካከል አንድ ሺሕን ያሸንፋሉ:: ምክንያቱም እነርሱ የማይገነዘቡ ህዝቦች ናቸዉና::

8:66

ٱلۡـَٰٔنَ خَفَّفَ ٱللَّهُ عَنكُمۡ وَعَلِمَ أَنَّ فِيكُمۡ ضَعۡفٗاۚ فَإِن يَكُن مِّنكُم مِّاْئَةٞ صَابِرَةٞ يَغۡلِبُواْ مِاْئَتَيۡنِۚ وَإِن يَكُن مِّنكُمۡ أَلۡفٞ يَغۡلِبُوٓاْ أَلۡفَيۡنِ بِإِذۡنِ ٱللَّهِۗ وَٱللَّهُ مَعَ ٱلصَّـٰبِرِينَ ﴿66﴾

Transliteration: Alana khaffafa Allahu AAankum waAAalima anna feekum daAAfan fain yakun minkum miatun sabiratun yaghliboo miatayni wain yakun minkum alfun yaghliboo alfayni biithni Allahi waAllahu maAAa alssabireena

Translation: 66. አሁን አላህ ከናንተ ላይ አቀለለላችሁ:: በእናንተ ውስጥም ድክመት መኖሩን አወቀ:: ስለዚህ ከናንተ መካካል መቶ ታጋሾች ቢኖሩ ሁለት መቶን ያሸንፋሉ:: ከናንተም አንድ ሺህ ቢኖሩ በአላህ ፍቃድ ሁለት ሺዎችን ያሸንፋሉ:: አላህ ከታጋሾቹ ጋር ነዉና::

8:67

مَا كَانَ لِنَبِيٍّ أَن يَكُونَ لَهُۥٓ أَسۡرَىٰ حَتَّىٰ يُثۡخِنَ فِي ٱلۡأَرۡضِۚ تُرِيدُونَ عَرَضَ ٱلدُّنۡيَا وَٱللَّهُ يُرِيدُ ٱلۡأٓخِرَةَۗ وَٱللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٞ ﴿67﴾

Transliteration: Ma kana linabiyyin an yakoona lahu asra hatta yuthkhina fee alardi tureedoona AAarada alddunya waAllahu yureedu alakhirata waAllahu AAazeezun hakeemun

Translation: 67. ለነብይ በምድር ላይ ጠላቶቹን እስኪያደክም ድረስ ለእርሱ ምረኮኞች ሊኖሩት አይገባም:: (አማኞች ሆይ!) የቅርቢቱን ዓለም ጠፊ ጥቅም ትፈልጋላችሁ:: አላህ መጨረሻይቱን ይሻል:: አላህም ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው::

8:68

لَّوۡلَا كِتَٰبٞ مِّنَ ٱللَّهِ سَبَقَ لَمَسَّكُمۡ فِيمَآ أَخَذۡتُمۡ عَذَابٌ عَظِيمٞ ﴿68﴾

Transliteration: Lawla kitabun mina Allahi sabaqa lamassakum feema akhathtum AAathabun AAatheemun

Translation: 68. ከአላህ ያለፈ ውሳኔ ባልነበረ ኖሮ በወሰዳችሁት ቤዛ ከባድ ቅጣት በነካችሁ ነበር::

8:69

فَكُلُواْ مِمَّا غَنِمۡتُمۡ حَلَٰلٗا طَيِّبٗاۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٞ ﴿69﴾

Transliteration: Fakuloo mimma ghanimtum halalan tayyiban waittaqoo Allaha inna Allaha ghafoorun raheemun

Translation: 69. (አማኞች ሆይ!) ያ! ከጠላት የማረካችሁትን ሀብት የተፈቀደና መልካም ሲሆን ብሉ:: አላህንም ፍሩ:: አላህም መሓሪና አዛኝ ነውና::

8:70

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ قُل لِّمَن فِيٓ أَيۡدِيكُم مِّنَ ٱلۡأَسۡرَىٰٓ إِن يَعۡلَمِ ٱللَّهُ فِي قُلُوبِكُمۡ خَيۡرٗا يُؤۡتِكُمۡ خَيۡرٗا مِّمَّآ أُخِذَ مِنكُمۡ وَيَغۡفِرۡ لَكُمۡۚ وَٱللَّهُ غَفُورٞ رَّحِيمٞ ﴿70﴾

Transliteration: Ya ayyuha alnnabiyyu qul liman fee aydeekum mina alasra in yaAAlami Allahu fee quloobikum khayran yutikum khayran mimma okhitha minkum wayaghfir lakum waAllahu ghafoorun raheemun

Translation: 70. አንተ ነብይ ሆይ! ከምርኮኞች መካከል በእጆቻችሁ ላሉት «አላህ በልቦቻቸው ውስጥ በጎን ነገር (እምነትን) ቢያውቅ ከተወሰደባችሁ የተሻለን ይሰጣችኋል:: ለእናንተም ይምራችኋል:: አላህም መሓሪና አዛኝ ነውና።» በላቸው።

8:71

وَإِن يُرِيدُواْ خِيَانَتَكَ فَقَدۡ خَانُواْ ٱللَّهَ مِن قَبۡلُ فَأَمۡكَنَ مِنۡهُمۡۗ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ ﴿71﴾

Transliteration: Wain yureedoo khiyanataka faqad khanoo Allaha min qablu faamkana minhum waAllahu AAaleemun hakeemun

Translation: 71. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሊክዱህ ቢፈልጉ ከዚህ በፊት አላህን በእርግጥ ከድተዋል:: እናም ከእነርሱ አስመችቶሃል:: አላህም ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::

8:72

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَهَاجَرُواْ وَجَٰهَدُواْ بِأَمۡوَٰلِهِمۡ وَأَنفُسِهِمۡ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَٱلَّذِينَ ءَاوَواْ وَّنَصَرُوٓاْ أُوْلَـٰٓئِكَ بَعۡضُهُمۡ أَوۡلِيَآءُ بَعۡضٖۚ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَلَمۡ يُهَاجِرُواْ مَا لَكُم مِّن وَلَٰيَتِهِم مِّن شَيۡءٍ حَتَّىٰ يُهَاجِرُواْۚ وَإِنِ ٱسۡتَنصَرُوكُمۡ فِي ٱلدِّينِ فَعَلَيۡكُمُ ٱلنَّصۡرُ إِلَّا عَلَىٰ قَوۡمِۭ بَيۡنَكُمۡ وَبَيۡنَهُم مِّيثَٰقٞۗ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٞ ﴿72﴾

Transliteration: Inna allatheena amanoo wahajaroo wajahadoo biamwalihim waanfusihim fee sabeeli Allahi waallatheena awaw wanasaroo olaika baAAduhum awliyao baAAdin waallatheena amanoo walam yuhajiroo ma lakum min walayatihim min shayin hatta yuhajiroo waini istansarookum fee alddeeni faAAalaykumu alnnasru illa AAala qawmin baynakum wabaynahum meethaqun waAllahu bima taAAmaloona baseerun

Translation: 72. እነዚያ በአላህ አምነው ለእርሱም ሲሉ ከሀገራቸው የተሰደዱ በአላህ መንገድ ላይም በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው የታገሉ እና እነዚያም ስደተኞቹን ያስጠጉና የረዱ ሰዎች እነዚያ ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው:: እነዚያ አምነውም ያልተሰደዱ ሰዎች ደግሞ ለአላህ ብለው እስከሚሰደዱ ድረስ ከእነርሱ ምንም ዝምድና የላችሁም:: በሃይማኖት እርዳታን ቢፈልጉባችሁ በእናንተና በእነርሱ መካከል ቃል ኪዳን ባላችሁ ሕዝቦች ላይ ካልሆነ በስተቀር በእናንተ ላይ እነርሱን መርዳት አለባችሁ:: አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::

8:73

وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بَعۡضُهُمۡ أَوۡلِيَآءُ بَعۡضٍۚ إِلَّا تَفۡعَلُوهُ تَكُن فِتۡنَةٞ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَفَسَادٞ كَبِيرٞ ﴿73﴾

Transliteration: Waallatheena kafaroo baAAduhum awliyao baAAdin illa tafAAaloohu takun fitnatun fee alardi wafasadun kabeerun

Translation: 73. እነዚያም በአላህ የካዱ ሰዎች ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው:: (ከምዕምናን ጋር መረዳዳትን ከከሓዲያን መቆራረጥን) ባትሠሩት በምድር ላይ ሁከትና ታላቅ ጥፋት ይሆናል::

8:74

وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَهَاجَرُواْ وَجَٰهَدُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَٱلَّذِينَ ءَاوَواْ وَّنَصَرُوٓاْ أُوْلَـٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ حَقّٗاۚ لَّهُم مَّغۡفِرَةٞ وَرِزۡقٞ كَرِيمٞ ﴿74﴾

Transliteration: Waallatheena amanoo wahajaroo wajahadoo fee sabeeli Allahi waallatheena awaw wanasaroo olaika humu almuminoona haqqan lahum maghfiratun warizqun kareemun

Translation: 74. እነዚያ አምነው ለእርሱም ሲሉ የተሰደዱት፤ በአላህ መንገድ ላይም የታገሉ እና እነዚያም ያስጠጉና የረዱ እነዚያ ትክክለኛ አማኞች እነርሱው ናቸው:: ለእነርሱም ምሕረትና የከበረ ሲሳይ አለላቸው::

8:75

وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مِنۢ بَعۡدُ وَهَاجَرُواْ وَجَٰهَدُواْ مَعَكُمۡ فَأُوْلَـٰٓئِكَ مِنكُمۡۚ وَأُوْلُواْ ٱلۡأَرۡحَامِ بَعۡضُهُمۡ أَوۡلَىٰ بِبَعۡضٖ فِي كِتَٰبِ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمُۢ ﴿75﴾

Transliteration: Waallatheena amanoo min baAAdu wahajaroo wajahadoo maAAakum faolaika minkum waoloo alarhami baAAduhum awla bibaAAdin fee kitabi Allahi inna Allaha bikulli shayin AAaleemun

Translation: 75. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እነዚያ በኋላ ያመኑና ከሀገራቸው የተሰደዱ ከናንተም ጋር ሆነው የታገሉ እነዚያ ከናንተው ናቸው:: የዝምድናዎች ባለቤቶች በአላህ መጽሐፍ ከፊሎቻቸው ከከፊሉ ለመውረስ የተገቡ ናቸው። አላህ ሁሉን ነገር አዋቂ ነውና::

Transliteration source: English Transliteration by Tanzil. Used under Tanzil's non-commercial terms; see the source and latest updates at Tanzil. Tanzil translation download