quranm◉

Surah At-Tawbah transliteration

◉ ሱራ · ∞

9:1

بَرَآءَةٞ مِّنَ ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦٓ إِلَى ٱلَّذِينَ عَٰهَدتُّم مِّنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ ﴿1﴾

Transliteration: Baraatun mina Allahi warasoolihi ila allatheena AAahadtum mina almushrikeena

Translation: 1.(ሙስሊሞች ሆይ! ይህ) ከአላህና ከመልዕክተኛው ወደ እነዚያ ቃል ኪዳን ወደ ተጋባችኋቸው አጋሪዎች የሚደርስ የውል መሻሪያ መልዕክት ነው::

9:2

فَسِيحُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ أَرۡبَعَةَ أَشۡهُرٖ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّكُمۡ غَيۡرُ مُعۡجِزِي ٱللَّهِ وَأَنَّ ٱللَّهَ مُخۡزِي ٱلۡكَٰفِرِينَ ﴿2﴾

Transliteration: Faseehoo fee alardi arbaAAata ashhurin waiAAlamoo annakum ghayru muAAjizee Allahi waanna Allaha mukhzee alkafireena

Translation: 2. (ከሓዲያን ሆይ!) በምድር ላይ አራት ወሮችን ጸጥተኛ ስትሆኑ ተንቀሳቀሱ:: እናንተ ከአላህ ቅጣት የማታመልጡ መሆናችሁንና አላህ ከሓዲያንን አዋራጅ መሆኑንም እወቁ፡፡

9:3

وَأَذَٰنٞ مِّنَ ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦٓ إِلَى ٱلنَّاسِ يَوۡمَ ٱلۡحَجِّ ٱلۡأَكۡبَرِ أَنَّ ٱللَّهَ بَرِيٓءٞ مِّنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ وَرَسُولُهُۥۚ فَإِن تُبۡتُمۡ فَهُوَ خَيۡرٞ لَّكُمۡۖ وَإِن تَوَلَّيۡتُمۡ فَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّكُمۡ غَيۡرُ مُعۡجِزِي ٱللَّهِۗ وَبَشِّرِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِعَذَابٍ أَلِيمٍ ﴿3﴾

Transliteration: Waathanun mina Allahi warasoolihi ila alnnasi yawma alhajji alakbari anna Allaha bareeon mina almushrikeena warasooluhu fain tubtum fahuwa khayrun lakum wain tawallaytum faiAAlamoo annakum ghayru muAAjizee Allahi wabashshiri allatheena kafaroo biAAathabin aleemin

Translation: 3. (ይህ) ከአላህና ከመልዕክተኛው በታላቁ ሐጅ ቀን የወጣ አላህ እና መልዕክተኛው ከአጋሪዎቹ ንጹህ መሆናቸውን የሚገልፅ አዋጅ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከክህደት ብትጸጸቱ እርሱ ለእናንተ በላጭ ነው:: ከእምነት ብትሸሹ ግን እናንተ አላህን የማታቅቱት መሆናችሁን እወቁ በማለት ወደ ሰዎች የሚደርስ ማስታወቂያ ነው:: እነዚያን በአላህ የካዱትን ሰዎች በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው::

9:4

إِلَّا ٱلَّذِينَ عَٰهَدتُّم مِّنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ ثُمَّ لَمۡ يَنقُصُوكُمۡ شَيۡـٔٗا وَلَمۡ يُظَٰهِرُواْ عَلَيۡكُمۡ أَحَدٗا فَأَتِمُّوٓاْ إِلَيۡهِمۡ عَهۡدَهُمۡ إِلَىٰ مُدَّتِهِمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلۡمُتَّقِينَ ﴿4﴾

Transliteration: Illa allatheena AAahadtum mina almushrikeena thumma lam yanqusookum shayan walam yuthahiroo AAalaykum ahadan faatimmoo ilayhim AAahdahum ila muddatihim inna Allaha yuhibbu almuttaqeena

Translation: 4. እነዚያ ከአጋሪዎቹ መካከል እነዚያ ቃል ኪዳን የተጋባችሁላቸውና ከዚያ ምንም ያላጎደሉባችሁ፤ በእናንተ ላይ ለማጥቃት አንድንም ያልተባበሩባችሁ ቃል ኪዳናቸውን እስከ ጊዜያቸው መጨረሻ ድረስ ሙሉላቸው:: አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና::

9:5

فَإِذَا ٱنسَلَخَ ٱلۡأَشۡهُرُ ٱلۡحُرُمُ فَٱقۡتُلُواْ ٱلۡمُشۡرِكِينَ حَيۡثُ وَجَدتُّمُوهُمۡ وَخُذُوهُمۡ وَٱحۡصُرُوهُمۡ وَٱقۡعُدُواْ لَهُمۡ كُلَّ مَرۡصَدٖۚ فَإِن تَابُواْ وَأَقَامُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتَوُاْ ٱلزَّكَوٰةَ فَخَلُّواْ سَبِيلَهُمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٞ ﴿5﴾

Transliteration: Faitha insalakha alashhuru alhurumu faoqtuloo almushrikeena haythu wajadtumoohum wakhuthoohum waohsuroohum waoqAAudoo lahum kulla marsadin fain taboo waaqamoo alssalata waatawoo alzzakata fakhalloo sabeelahum inna Allaha ghafoorun raheemun

Translation: 5. የተከበሩት ወሮች ባለቁ ጊዜ አጋሪዎቹን ባገኛችሁባቸው ስፍራ ሁሉ ግደሏቸው:: ያዟቸዉም:: ክበቧቸዉም:: እነርሱንም ለመጠባበቅ ስትሉ በየኬላው ላይ ተቀመጡ:: ሆኖም ቢጸጸቱ፤ ሶላትን በደንቡ ቢሰግዱና ግዴታ የሆነባቸውን የዘካ ምጽዋትን በትክክል ከሰጡ መንገዳቸውን ልቀቁላቸው:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::

9:6

وَإِنۡ أَحَدٞ مِّنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ ٱسۡتَجَارَكَ فَأَجِرۡهُ حَتَّىٰ يَسۡمَعَ كَلَٰمَ ٱللَّهِ ثُمَّ أَبۡلِغۡهُ مَأۡمَنَهُۥۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ قَوۡمٞ لَّا يَعۡلَمُونَ ﴿6﴾

Transliteration: Wain ahadun mina almushrikeena istajaraka faajirhu hatta yasmaAAa kalama Allahi thumma ablighhu mamanahu thalika biannahum qawmun la yaAAlamoona

Translation: 6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከአጋሪዎች መካከል አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅህ የአላህን ቃል ይሰማ ዘንድ አስጠጋው:: ከዚያ ወደ ሰላም ማግኛው ስፍራ አድርሰው:: ይህም የሆነው እነርሱ የማያውቁ ህዝቦች በመሆናቸው ነው ::

9:7

كَيۡفَ يَكُونُ لِلۡمُشۡرِكِينَ عَهۡدٌ عِندَ ٱللَّهِ وَعِندَ رَسُولِهِۦٓ إِلَّا ٱلَّذِينَ عَٰهَدتُّمۡ عِندَ ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِۖ فَمَا ٱسۡتَقَٰمُواْ لَكُمۡ فَٱسۡتَقِيمُواْ لَهُمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلۡمُتَّقِينَ ﴿7﴾

Transliteration: Kayfa yakoonu lilmushrikeena AAahdun AAinda Allahi waAAinda rasoolihi illa allatheena AAahadtum AAinda almasjidi alharami fama istaqamoo lakum faistaqeemoo lahum inna Allaha yuhibbu almuttaqeena

Translation: 7. ለአጋሪዎች ከአላህና ከመልዕክተኛው ዘንድ የሰላም ቃል ኪዳን እንዴት ይኖራቸዋል? እነዚያ በተከበረው መስጊድ ዘንድ ቃል ኪዳን የገባችሁላቸው ሰዎች ብቻ ሲቀሩ:: እነዚያማ በቃል ኪዳናቸው ለእናንተ ቀጥ እስካሉላችሁ ድረስ ለእርሱም በቃላችሁ ቀጥ በሉላቸው:: አላህ ጥንቁቆችን ሁሉ ይወዳልና::

9:8

كَيۡفَ وَإِن يَظۡهَرُواْ عَلَيۡكُمۡ لَا يَرۡقُبُواْ فِيكُمۡ إِلّٗا وَلَا ذِمَّةٗۚ يُرۡضُونَكُم بِأَفۡوَٰهِهِمۡ وَتَأۡبَىٰ قُلُوبُهُمۡ وَأَكۡثَرُهُمۡ فَٰسِقُونَ ﴿8﴾

Transliteration: Kayfa wain yathharoo AAalaykum la yarquboo feekum illan wala thimmatan yurdoonakum biafwahihim wataba quloobuhum waaktharuhum fasiqoona

Translation: 8. በእናንተ ላይ ቢያይሉ ዝምድናንና ቃልኪዳንን የማይጠብቁ ሰዎች ሲሆኑ እንዴት ከአላህና ከመልዕክተኛው ዘንድ ቃልኪዳን ይኖራቸዋል? በአፎቻቸው ይሸነግሏችኋል:: ልቦቻቸው ግን እምቢ ይላሉ:: አብዛኞቻቸዉም አመጸኞች ናቸው::

9:9

ٱشۡتَرَوۡاْ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ ثَمَنٗا قَلِيلٗا فَصَدُّواْ عَن سَبِيلِهِۦٓۚ إِنَّهُمۡ سَآءَ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ ﴿9﴾

Transliteration: Ishtaraw biayati Allahi thamanan qaleelan fasaddoo AAan sabeelihi innahum saa ma kanoo yaAAmaloona

Translation: 9. በአላህ አናቅጽ ጥቂትን ዋጋ ገዙ:: እናም ከመንገዱም ሰዎችን አገዱ:: እነርሱ ይሰሩት የነበሩት ሥራም እጅግ በጣም ከፋ::

9:10

لَا يَرۡقُبُونَ فِي مُؤۡمِنٍ إِلّٗا وَلَا ذِمَّةٗۚ وَأُوْلَـٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُعۡتَدُونَ ﴿10﴾

Transliteration: La yarquboona fee muminin illan wala thimmatan waolaika humu almuAAtadoona

Translation: 10. በትክክለኛ አማኞች ላይ ዝምድናንም ሆነ ቃል ኪዳንን አይጠብቁም:: ወሰን አላፊዎች ማለት እነርሱው ናቸው::

9:11

فَإِن تَابُواْ وَأَقَامُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتَوُاْ ٱلزَّكَوٰةَ فَإِخۡوَٰنُكُمۡ فِي ٱلدِّينِۗ وَنُفَصِّلُ ٱلۡأٓيَٰتِ لِقَوۡمٖ يَعۡلَمُونَ ﴿11﴾

Transliteration: Fain taboo waaqamoo alssalata waatawoo alzzakata faikhwanukum fee alddeeni wanufassilu alayati liqawmin yaAAlamoona

Translation: 11. (ሙስሊሞች ሆይ!) ቢጸጸቱ፤ ሶላትንም ደንቡን አሟልተው ቢሰገዱና ግድ የሆነባቸውንም ዘካን በትክክል ቢሰጡ የእምነት ወንድሞቻችሁ ናቸው:: ለሚያውቁ ህዝቦች ሁሉ አናቅጽን እናብራራለን::

9:12

وَإِن نَّكَثُوٓاْ أَيۡمَٰنَهُم مِّنۢ بَعۡدِ عَهۡدِهِمۡ وَطَعَنُواْ فِي دِينِكُمۡ فَقَٰتِلُوٓاْ أَئِمَّةَ ٱلۡكُفۡرِ إِنَّهُمۡ لَآ أَيۡمَٰنَ لَهُمۡ لَعَلَّهُمۡ يَنتَهُونَ ﴿12﴾

Transliteration: Wain nakathoo aymanahum min baAAdi AAahdihim wataAAanoo fee deenikum faqatiloo aimmata alkufri innahum la aymana lahum laAAallahum yantahoona

Translation: 12. ከቃልኪዳናቸው በኋላ መሀላዎቻቸውን ካፈረሱና ሃይማኖታችሁን ካንቋሸሹ የክህደት መሪዎች ከክህደት ተግባራቸው ይከለከሉ ዘንድ ተዋጓቸው:: እነርሱ ምንም ቃልኪዳን የላቸዉምና::

9:13

أَلَا تُقَٰتِلُونَ قَوۡمٗا نَّكَثُوٓاْ أَيۡمَٰنَهُمۡ وَهَمُّواْ بِإِخۡرَاجِ ٱلرَّسُولِ وَهُم بَدَءُوكُمۡ أَوَّلَ مَرَّةٍۚ أَتَخۡشَوۡنَهُمۡۚ فَٱللَّهُ أَحَقُّ أَن تَخۡشَوۡهُ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ ﴿13﴾

Transliteration: Ala tuqatiloona qawman nakathoo aymanahum wahammoo biikhraji alrrasooli wahum badaookum awwala marratin atakhshawnahum faAllahu ahaqqu an takhshawhu in kuntum mumineena

Translation: 13. እነዚያ መሀላዎቻቸውን ያፈረሱትን፤ መልዕክተኛውንም ከሀገር ለማውጣት ያሰቡትን ህዝቦች እነርሱ ለመጀመሪያ ጊዜ ጦርነት የጀመሯችሁን ህዝቦች ሲሆኑ ለምን አትወጓቸዉም? ትፈሯቸዋላችሁን? ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ አላህን ይበልጥ ልትፈሩት የተገባው ነው::

9:14

قَٰتِلُوهُمۡ يُعَذِّبۡهُمُ ٱللَّهُ بِأَيۡدِيكُمۡ وَيُخۡزِهِمۡ وَيَنصُرۡكُمۡ عَلَيۡهِمۡ وَيَشۡفِ صُدُورَ قَوۡمٖ مُّؤۡمِنِينَ ﴿14﴾

Transliteration: Qatiloohum yuAAaththibhumu Allahu biaydeekum wayukhzihim wayansurkum AAalayhim wayashfi sudoora qawmin mumineena

Translation: 14. (ሙስሊሞች ሆይ!) ተጋደሏቸው:: አላህ በእጆቻችሁ ያሰቃያቸዋል:: ያዋርዳቸዋልም:: በእነርሱም ላይ ይረዳችኋል:: የአማኝ ህዝቦችን ልቦችንም ያሽራል::

9:15

وَيُذۡهِبۡ غَيۡظَ قُلُوبِهِمۡۗ وَيَتُوبُ ٱللَّهُ عَلَىٰ مَن يَشَآءُۗ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ ﴿15﴾

Transliteration: Wayuthhib ghaytha quloobihim wayatoobu Allahu AAala man yashao waAllahu AAaleemun hakeemun

Translation: 15. የልቦቻቸውንም ቁጭት ያስወግዳል:: አላህ ከሚፈልገው ሰው ላይ ጸጸትን ይቀበላል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና::

9:16

أَمۡ حَسِبۡتُمۡ أَن تُتۡرَكُواْ وَلَمَّا يَعۡلَمِ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ جَٰهَدُواْ مِنكُمۡ وَلَمۡ يَتَّخِذُواْ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَا رَسُولِهِۦ وَلَا ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَلِيجَةٗۚ وَٱللَّهُ خَبِيرُۢ بِمَا تَعۡمَلُونَ ﴿16﴾

Transliteration: Am hasibtum an tutrakoo walamma yaAAlami Allahu allatheena jahadoo minkum walam yattakhithoo min dooni Allahi wala rasoolihi wala almumineena waleejatan waAllahu khabeerun bima taAAmaloona

Translation: 16. አላህ ከመካከላችሁ በትክክል ለአላህ መስዋዕት የሚከፍሉትንና (የታገሉትንና) ከአላህ፣ ከመልዕክተኛውና ከትክክለኛ አማኞች በስተቀር አማካሪ ያልያዙትን ክፍሎች ለይቶ ሳያውቅ (ሳይገልጽ) የምትተዉ መሰላችሁን? አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ዉስጠ አዋቂ ነው::

9:17

مَا كَانَ لِلۡمُشۡرِكِينَ أَن يَعۡمُرُواْ مَسَٰجِدَ ٱللَّهِ شَٰهِدِينَ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِم بِٱلۡكُفۡرِۚ أُوْلَـٰٓئِكَ حَبِطَتۡ أَعۡمَٰلُهُمۡ وَفِي ٱلنَّارِ هُمۡ خَٰلِدُونَ ﴿17﴾

Transliteration: Ma kana lilmushrikeena an yaAAmuroo masajida Allahi shahideena AAala anfusihim bialkufri olaika habitat aAAmaluhum wafee alnnari hum khalidoona

Translation: 17. አጋሪዎች በራሳቸው ላይ በክህደት የሚመሰክሩ ሲሆኑ የአላህን መስጊዶች ሊንከባከቡ አይገባቸዉም:: እነዚያ ሥራዎቻቸው የተበላሹና በአኼራም በእሳት ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::

9:18

إِنَّمَا يَعۡمُرُ مَسَٰجِدَ ٱللَّهِ مَنۡ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِ وَأَقَامَ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتَى ٱلزَّكَوٰةَ وَلَمۡ يَخۡشَ إِلَّا ٱللَّهَۖ فَعَسَىٰٓ أُوْلَـٰٓئِكَ أَن يَكُونُواْ مِنَ ٱلۡمُهۡتَدِينَ ﴿18﴾

Transliteration: Innama yaAAmuru masajida Allahi man amana biAllahi waalyawmi alakhiri waaqama alssalata waata alzzakata walam yakhsha illa Allaha faAAasa olaika an yakoonoo mina almuhtadeena

Translation: 18. የአላህን መስጊዶች የሚንከባከቡ ሰዎች በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመኑ፤ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀው የሚሰግዱ፤ ግዴታ ምጽዋትን በትክክል የሚሰጡ፤ ከአላህ ሌላ ምንንም ያልፈሩ ሰዎች ብቻ ናቸው:: እንዲህ ያሉት ሰዎች ቀናዉን መስመር ከያዙት መሆናቸው ይከጀላልና::

9:19

أَجَعَلۡتُمۡ سِقَايَةَ ٱلۡحَآجِّ وَعِمَارَةَ ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِ كَمَنۡ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِ وَجَٰهَدَ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِۚ لَا يَسۡتَوُۥنَ عِندَ ٱللَّهِۗ وَٱللَّهُ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلظَّـٰلِمِينَ ﴿19﴾

Transliteration: AjaAAaltum siqayata alhajji waAAimarata almasjidi alharami kaman amana biAllahi waalyawmi alakhiri wajahada fee sabeeli Allahi la yastawoona AAinda Allahi waAllahu la yahdee alqawma alththalimeena

Translation: 19. ሰዎችን ማጠጣትንና የተከበረውን መስጊድ መንከባከብን፤ በአላህና በመጨረሻው ቀን እንዳመነና በአላህ መንገድም እንደታገለ ሰው እምነትና ትግል አደረጋችሁትን? በአላህ ዘንድ ፈጽሞ ሁለቱ ተግባሮች አይስተካከሉም:: አላህ በዳይ ህዝቦችን ሁሉ ወደ ቀጥተኛው መንገድ አይመራምና::

9:20

ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَهَاجَرُواْ وَجَٰهَدُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ بِأَمۡوَٰلِهِمۡ وَأَنفُسِهِمۡ أَعۡظَمُ دَرَجَةً عِندَ ٱللَّهِۚ وَأُوْلَـٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡفَآئِزُونَ ﴿20﴾

Transliteration: Allatheena amanoo wahajaroo wajahadoo fee sabeeli Allahi biamwalihim waanfusihim aAAthamu darajatan AAinda Allahi waolaika humu alfaizoona

Translation: 20. እነዚያ በአላህ ያመኑት ከየአገሮቻቸዉም የተሰደዱት በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸዉም በአላህ መንገድ ላይ የታገሉት አላህ ዘንድ በደረጃ በጣም የላቁ ናቸው:: ፍላጎታቸውን ያገኙ ማለትም እነርሱው ናቸው::

9:21

يُبَشِّرُهُمۡ رَبُّهُم بِرَحۡمَةٖ مِّنۡهُ وَرِضۡوَٰنٖ وَجَنَّـٰتٖ لَّهُمۡ فِيهَا نَعِيمٞ مُّقِيمٌ ﴿21﴾

Transliteration: Yubashshiruhum rabbuhum birahmatin minhu waridwanin wajannatin lahum feeha naAAeemun muqeemun

Translation: 21. ጌታቸው ከእርሱ በሆነው እዝነትና ውዴታ፤ በውስጧ የማያቋርጥ መጠቀሚያ ባለባት ገነትም ያበስራቸዋል::

9:22

خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدًاۚ إِنَّ ٱللَّهَ عِندَهُۥٓ أَجۡرٌ عَظِيمٞ ﴿22﴾

Transliteration: Khalideena feeha abadan inna Allaha AAindahu ajrun AAatheemun

Translation: 22. በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ሲሆኑ ያበስራቸዋል:: አላህ እርሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ አለና::

9:23

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَتَّخِذُوٓاْ ءَابَآءَكُمۡ وَإِخۡوَٰنَكُمۡ أَوۡلِيَآءَ إِنِ ٱسۡتَحَبُّواْ ٱلۡكُفۡرَ عَلَى ٱلۡإِيمَٰنِۚ وَمَن يَتَوَلَّهُم مِّنكُمۡ فَأُوْلَـٰٓئِكَ هُمُ ٱلظَّـٰلِمُونَ ﴿23﴾

Transliteration: Ya ayyuha allatheena amanoo la tattakhithoo abaakum waikhwanakum awliyaa ini istahabboo alkufra AAala aleemani waman yatawallahum minkum faolaika humu alththalimoona

Translation: 23. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አባቶቻችሁንና ወንድሞቻችሁን ክህደትን ከእምነት አብልጠው ከወደዱ ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዟቸው:: ከናንተ መካከል እነርሱን ወዳጅ የሚያደርጓቸው ሁሉ በዳዮች ማለት እነርሱው ናቸው::

9:24

قُلۡ إِن كَانَ ءَابَآؤُكُمۡ وَأَبۡنَآؤُكُمۡ وَإِخۡوَٰنُكُمۡ وَأَزۡوَٰجُكُمۡ وَعَشِيرَتُكُمۡ وَأَمۡوَٰلٌ ٱقۡتَرَفۡتُمُوهَا وَتِجَٰرَةٞ تَخۡشَوۡنَ كَسَادَهَا وَمَسَٰكِنُ تَرۡضَوۡنَهَآ أَحَبَّ إِلَيۡكُم مِّنَ ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَجِهَادٖ فِي سَبِيلِهِۦ فَتَرَبَّصُواْ حَتَّىٰ يَأۡتِيَ ٱللَّهُ بِأَمۡرِهِۦۗ وَٱللَّهُ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلۡفَٰسِقِينَ ﴿24﴾

Transliteration: Qul in kana abaokum waabnaokum waikhwanukum waazwajukum waAAasheeratukum waamwalun iqtaraftumooha watijaratun takhshawna kasadaha wamasakinu tardawnaha ahabba ilaykum mina Allahi warasoolihi wajihadin fee sabeelihi fatarabbasoo hatta yatiya Allahu biamrihi waAllahu la yahdee alqawma alfasiqeena

Translation: 24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አባቶቻችሁ፤ ወንዶች ልጆቻችሁ፤ ወንድሞቻችሁ፤ ሚስቶቻችሁ ዘመዶቻችሁ፤ የሰበሰባችኋቸው ሀብቶች፤ መክሰሯን የምትፈሯት ንግድና የምትወዷቸው መኖሪያዎች በእናንተ ዘንድ ከአላህ፤ ከመልዕክተኛውና በእርሱ መንገድ ከመታገል ይበልጥ የተወደዱ ከሆኑ አላህ ጉዳዩን እስከሚያመጣ ድረስ ተጠባበቁ በላቸው:: አላህ አመጸኞች ህዝቦችን ሁሉ አይመራም::

9:25

لَقَدۡ نَصَرَكُمُ ٱللَّهُ فِي مَوَاطِنَ كَثِيرَةٖ وَيَوۡمَ حُنَيۡنٍ إِذۡ أَعۡجَبَتۡكُمۡ كَثۡرَتُكُمۡ فَلَمۡ تُغۡنِ عَنكُمۡ شَيۡـٔٗا وَضَاقَتۡ عَلَيۡكُمُ ٱلۡأَرۡضُ بِمَا رَحُبَتۡ ثُمَّ وَلَّيۡتُم مُّدۡبِرِينَ ﴿25﴾

Transliteration: Laqad nasarakumu Allahu fee mawatina katheeratin wayawma hunaynin ith aAAjabatkum kathratukum falam tughni AAankum shayan wadaqat AAalaykumu alardu bima rahubat thumma wallaytum mudbireena

Translation: 25. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህ በብዙ የጦር ሜዳዎች ላይ እገዛውን ለግሶላችኋል:: የሁነይንም ቀን ብዛታችሁ ባስደነቀቻችሁና ለእናንተም ብዛት ምንም ባልጠቀመቻችሁ ጊዜ ምድርም ከስፋቷ ጋር በጠበበቻችሁና ከዚያ ተሸናፊዎች ሆናችሁም በዞራችሁ ጊዜ ረዳችሁ::

9:26

ثُمَّ أَنزَلَ ٱللَّهُ سَكِينَتَهُۥ عَلَىٰ رَسُولِهِۦ وَعَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَأَنزَلَ جُنُودٗا لَّمۡ تَرَوۡهَا وَعَذَّبَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْۚ وَذَٰلِكَ جَزَآءُ ٱلۡكَٰفِرِينَ ﴿26﴾

Transliteration: Thumma anzala Allahu sakeenatahu AAala rasoolihi waAAala almumineena waanzala junoodan lam tarawha waAAaththaba allatheena kafaroo wathalika jazao alkafireena

Translation: 26. ከዚያም አላህ እርጋታውን በመልዕክተኛውና በምዕመናኖች ላይ አወረደ:: ያላያችኋቸውንም ሰራዊት አወረደ:: እነዚያን የካዱትንም ሰዎች በመግደልና በመማረክ አሰቃየ:: ይህም የከሓዲያን ፍዳ ነው::

9:27

ثُمَّ يَتُوبُ ٱللَّهُ مِنۢ بَعۡدِ ذَٰلِكَ عَلَىٰ مَن يَشَآءُۗ وَٱللَّهُ غَفُورٞ رَّحِيمٞ ﴿27﴾

Transliteration: Thumma yatoobu Allahu min baAAdi thalika AAala man yashao waAllahu ghafoorun raheemun

Translation: 27. ከዚያም ከዚህ በኋላ አላህ ከሚፈልገው ሰው ላይ ጸጸትን ይቀበላል:: አላህ እጅግ መሀሪና አዛኝ ነውና::

9:28

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِنَّمَا ٱلۡمُشۡرِكُونَ نَجَسٞ فَلَا يَقۡرَبُواْ ٱلۡمَسۡجِدَ ٱلۡحَرَامَ بَعۡدَ عَامِهِمۡ هَٰذَاۚ وَإِنۡ خِفۡتُمۡ عَيۡلَةٗ فَسَوۡفَ يُغۡنِيكُمُ ٱللَّهُ مِن فَضۡلِهِۦٓ إِن شَآءَۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌ حَكِيمٞ ﴿28﴾

Transliteration: Ya ayyuha allatheena amanoo innama almushrikoona najasun fala yaqraboo almasjida alharama baAAda AAamihim hatha wain khiftum AAaylatan fasawfa yughneekumu Allahu min fadlihi in shaa inna Allaha AAaleemun hakeemun

Translation: 28. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ አጋሪዎች እርኩሶች ብቻ ናቸው:: እናም ከዚህ ዓመታቸው በኋላ ወደ ተከበረው መስጊድ እንዳይቀርቡ። ድህነትንም ብትፈሩ አላህ ቢፈልግ ከችሮታው በእርግጥ ያከብራችኋል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።

9:29

قَٰتِلُواْ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَلَا بِٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِ وَلَا يُحَرِّمُونَ مَا حَرَّمَ ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥ وَلَا يَدِينُونَ دِينَ ٱلۡحَقِّ مِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ حَتَّىٰ يُعۡطُواْ ٱلۡجِزۡيَةَ عَن يَدٖ وَهُمۡ صَٰغِرُونَ ﴿29﴾

Transliteration: Qatiloo allatheena la yuminoona biAllahi wala bialyawmi alakhiri wala yuharrimoona ma harrama Allahu warasooluhu wala yadeenoona deena alhaqqi mina allatheena ootoo alkitaba hatta yuAAtoo aljizyata AAan yadin wahum saghiroona

Translation: 29. (ሙስሊሞች ሆይ!) ከእነዚያ መጽሐፍን ከተሰጡ ሰዎች መካከል እነዚያን በአላህና በመጨረሻው ቀን የማያምኑትን ክፍሎች አላህና መልዕክተኛው እርም ያደረጉትንም እርም የማያደርጉትን፤ እውነተኛውንም ሃይማኖት የማይቀበሉትን የተዋረዱ ሆነው ግብርን በእጆቻቸው እስከሚሰጡ ድረስ ተዋጓቸው::

9:30

وَقَالَتِ ٱلۡيَهُودُ عُزَيۡرٌ ٱبۡنُ ٱللَّهِ وَقَالَتِ ٱلنَّصَٰرَى ٱلۡمَسِيحُ ٱبۡنُ ٱللَّهِۖ ذَٰلِكَ قَوۡلُهُم بِأَفۡوَٰهِهِمۡۖ يُضَٰهِـُٔونَ قَوۡلَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِن قَبۡلُۚ قَٰتَلَهُمُ ٱللَّهُۖ أَنَّىٰ يُؤۡفَكُونَ ﴿30﴾

Transliteration: Waqalati alyahoodu AAuzayrun ibnu Allahi waqalati alnnasara almaseehu ibnu Allahi thalika qawluhum biafwahihim yudahioona qawla allatheena kafaroo min qablu qatalahumu Allahu anna yufakoona

Translation: 30. አይሁድ «ኡዘይር የአላህ ልጅ ነው።» አሉ:: ክርስቲያኖችም «አል-መሲህ የአላህ ልጅ ነው።» አሉ:: ይህ በአፎቻቸው የሚናገሩት ጸያፍ ቃላቸው ነው:: የእነዚያን ከእነርሱ በፊት የካዱትን (ሰዎች) ቃል ያመሳስላሉ:: አላህ ያጥፋቸው:: ከእውነት እንዴት ያፈነግጣሉ?

9:31

ٱتَّخَذُوٓاْ أَحۡبَارَهُمۡ وَرُهۡبَٰنَهُمۡ أَرۡبَابٗا مِّن دُونِ ٱللَّهِ وَٱلۡمَسِيحَ ٱبۡنَ مَرۡيَمَ وَمَآ أُمِرُوٓاْ إِلَّا لِيَعۡبُدُوٓاْ إِلَٰهٗا وَٰحِدٗاۖ لَّآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۚ سُبۡحَٰنَهُۥ عَمَّا يُشۡرِكُونَ ﴿31﴾

Transliteration: Ittakhathoo ahbarahum waruhbanahum arbaban min dooni Allahi waalmaseeha ibna maryama wama omiroo illa liyaAAbudoo ilahan wahidan la ilaha illa huwa subhanahu AAamma yushrikoona

Translation: 31. አይሁድና ክርስቲያኖች ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንዱን አምላክ አላህን ብቻ ሊገዙ እንጂ ያልታዘዙ ሲሆኑ ሊቃውንቶቻቸውን፤ መነኮሳቶቻቸውንና የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ:: ከእርሱ በስተቀር ትክክለኛ አምላክ የለም:: አላህ ግን ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው::

9:32

يُرِيدُونَ أَن يُطۡفِـُٔواْ نُورَ ٱللَّهِ بِأَفۡوَٰهِهِمۡ وَيَأۡبَى ٱللَّهُ إِلَّآ أَن يُتِمَّ نُورَهُۥ وَلَوۡ كَرِهَ ٱلۡكَٰفِرُونَ ﴿32﴾

Transliteration: Yureedoona an yutfioo noora Allahi biafwahihim wayaba Allahu illa an yutimma noorahu walaw kariha alkafiroona

Translation: 32. ከሓዲያን የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋት ይፈልጋሉ:: እርሱ (አላህ) ከሓዲያን ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን መሙላትን እንጂ ሌላን አይሻም::

9:33

هُوَ ٱلَّذِيٓ أَرۡسَلَ رَسُولَهُۥ بِٱلۡهُدَىٰ وَدِينِ ٱلۡحَقِّ لِيُظۡهِرَهُۥ عَلَى ٱلدِّينِ كُلِّهِۦ وَلَوۡ كَرِهَ ٱلۡمُشۡرِكُونَ ﴿33﴾

Transliteration: Huwa allathee arsala rasoolahu bialhuda wadeeni alhaqqi liyuthhirahu AAala alddeeni kullihi walaw kariha almushrikoona

Translation: 33. አላህ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርገው ዘንድ መልዕክተኛው ሙሓመድን በቅን መንገድና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ አድርጎ የላከው ብቸኛ አምላክ ነው።

9:34

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِنَّ كَثِيرٗا مِّنَ ٱلۡأَحۡبَارِ وَٱلرُّهۡبَانِ لَيَأۡكُلُونَ أَمۡوَٰلَ ٱلنَّاسِ بِٱلۡبَٰطِلِ وَيَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِۗ وَٱلَّذِينَ يَكۡنِزُونَ ٱلذَّهَبَ وَٱلۡفِضَّةَ وَلَا يُنفِقُونَهَا فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ فَبَشِّرۡهُم بِعَذَابٍ أَلِيمٖ ﴿34﴾

Transliteration: Ya ayyuha allatheena amanoo inna katheeran mina alahbari waalrruhbani layakuloona amwala alnnasi bialbatili wayasuddoona AAan sabeeli Allahi waallatheena yaknizoona alththahaba waalfiddata wala yunfiqoonaha fee sabeeli Allahi fabashshirhum biAAathabin aleemin

Translation: 34. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከሊቃውንትና ከመነኮሳት ብዙዎቹ የሰዎችን ገንዘቦች በውሸትም ይበላሉ:: ከአላህም መንገድም ሰዎችን ያግዳሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያንም ወርቅንና ብርን የሚያደልቡትን በአላህም መንገድ ላይ የማያወጧቸውን ሰዎች በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው::

9:35

يَوۡمَ يُحۡمَىٰ عَلَيۡهَا فِي نَارِ جَهَنَّمَ فَتُكۡوَىٰ بِهَا جِبَاهُهُمۡ وَجُنُوبُهُمۡ وَظُهُورُهُمۡۖ هَٰذَا مَا كَنَزۡتُمۡ لِأَنفُسِكُمۡ فَذُوقُواْ مَا كُنتُمۡ تَكۡنِزُونَ ﴿35﴾

Transliteration: Yawma yuhma AAalayha fee nari jahannama fatukwa biha jibahuhum wajunoobuhum wathuhooruhum hatha ma kanaztum lianfusikum fathooqoo ma kuntum taknizoona

Translation: 35. (በብሩና በወርቁ) ላይ በገሀነም እሳት ውስጥ በሚግሉበትና ግንባሮቻቸውም፣ ጎኖቻቸውም፣ ጀርቦቻቸውም በእርሱ በሚተኮሱበት ቀን አሳማሚ በሆነ ቅጣት አብስራቸው:: «ይህ ለነፍሶቻችሁ ያደለባችሁት ነው:: ታደልቡት የነበራችሁትንም ቅመሱ።» ይባላሉ::

9:36

إِنَّ عِدَّةَ ٱلشُّهُورِ عِندَ ٱللَّهِ ٱثۡنَا عَشَرَ شَهۡرٗا فِي كِتَٰبِ ٱللَّهِ يَوۡمَ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ مِنۡهَآ أَرۡبَعَةٌ حُرُمٞۚ ذَٰلِكَ ٱلدِّينُ ٱلۡقَيِّمُۚ فَلَا تَظۡلِمُواْ فِيهِنَّ أَنفُسَكُمۡۚ وَقَٰتِلُواْ ٱلۡمُشۡرِكِينَ كَآفَّةٗ كَمَا يُقَٰتِلُونَكُمۡ كَآفَّةٗۚ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلۡمُتَّقِينَ ﴿36﴾

Transliteration: Inna AAiddata alshshuhoori AAinda Allahi ithna AAashara shahran fee kitabi Allahi yawma khalaqa alssamawati waalarda minha arbaAAatun hurumun thalika alddeenu alqayyimu fala tathlimoo feehinna anfusakum waqatiloo almushrikeena kaffatan kama yuqatiloonakum kaffatan waiAAlamoo anna Allaha maAAa almuttaqeena

Translation: 36. የወራት ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን አስራ ሁለት ወር ብቻ ነው:: ከእነርሱም መካከል አራቱ የተከበሩ ወሮች ናቸው:: ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው:: በእነርሱ ውስጥም (ክብሮቻቸውን በመጣስ) ነፍሶቻችሁን አትበድሉ:: አጋሪዎችንም በአንድ ላይ ሆነው እንደሚጋደሏችሁ በአንድ ላይ ሆናችሁ ተጋደሏቸው:: አላህ በእርዳታው እርሱኑ ከሚፈሩት ጋር መሆኑን እወቁ::

9:37

إِنَّمَا ٱلنَّسِيٓءُ زِيَادَةٞ فِي ٱلۡكُفۡرِۖ يُضَلُّ بِهِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ يُحِلُّونَهُۥ عَامٗا وَيُحَرِّمُونَهُۥ عَامٗا لِّيُوَاطِـُٔواْ عِدَّةَ مَا حَرَّمَ ٱللَّهُ فَيُحِلُّواْ مَا حَرَّمَ ٱللَّهُۚ زُيِّنَ لَهُمۡ سُوٓءُ أَعۡمَٰلِهِمۡۗ وَٱللَّهُ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلۡكَٰفِرِينَ ﴿37﴾

Transliteration: Innama alnnaseeo ziyadatun fee alkufri yudallu bihi allatheena kafaroo yuhilloonahu AAaman wayuharrimoonahu AAaman liyuwatioo AAiddata ma harrama Allahu fayuhilloo ma harrama Allahu zuyyina lahum sooo aAAmalihim waAllahu la yahdee alqawma alkafireena

Translation: 37. የአንዱን ወር ክብር ወደ ሌላው ማዘግየት በክህደት ላይ ክህደትን መጨመር ነው:: በዚህ ተግባር ላይ እነዚያ በአላህ የካዱት (ሰዎች) ይሳሳቱበታል:: በአንደኛው ዓመት የተፈቀደ ያደርጉታል:: በሌላው ዓመት ደግሞ ያወግዙታል:: ይህም አላህ ያከበራቸውን ወሮች ቁጥር ሊሞሉበትና አላህ እርም ያደረገውን ደግሞ የተፈቀደ ሊያደርጉበት ነው:: መጥፎ ሥራዎቻቸው ለእነርሱ ተዋበላቸው:: አላህ ከሓዲያን ህዝቦችን ወደ ቀናው መንገድ አይመራም::

9:38

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَا لَكُمۡ إِذَا قِيلَ لَكُمُ ٱنفِرُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ ٱثَّاقَلۡتُمۡ إِلَى ٱلۡأَرۡضِۚ أَرَضِيتُم بِٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا مِنَ ٱلۡأٓخِرَةِۚ فَمَا مَتَٰعُ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا فِي ٱلۡأٓخِرَةِ إِلَّا قَلِيلٌ ﴿38﴾

Transliteration: Ya ayyuha allatheena amanoo ma lakum itha qeela lakumu infiroo fee sabeeli Allahi iththaqaltum ila alardi aradeetum bialhayati alddunya mina alakhirati fama mataAAu alhayati alddunya fee alakhirati illa qaleelun

Translation: 38. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! «በአላህ መንገድ ለመታገል ዝመቱ።» በተባላችሁ ጊዜ ወደ ምድር የምትወዘፉት ለምንድን ነው? የቅርቢቱን ህይወት ከመጨረሻይቱ ህይወት ይበልጥ ወደዳችሁን? የቅርቢቱ ህይወት ጥቅም ከመጨረሻይቱ ህይወት አንፃር ጥቂት እንጂ ምንም አይደለም::

9:39

إِلَّا تَنفِرُواْ يُعَذِّبۡكُمۡ عَذَابًا أَلِيمٗا وَيَسۡتَبۡدِلۡ قَوۡمًا غَيۡرَكُمۡ وَلَا تَضُرُّوهُ شَيۡـٔٗاۗ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ ﴿39﴾

Transliteration: Illa tanfiroo yuAAaththibkum AAathaban aleeman wayastabdil qawman ghayrakum wala tadurroohu shayan waAllahu AAala kulli shayin qadeerun

Translation: 39. ( አማኞች ሆይ!) ለዘመቻ ባትወጡ አላህ አሳማሚ ቅጣት ይቀጣችኋል:: ከናንተ ሌላ የሆኑን ህዝቦችም ይለውጣል:: አላህን በምንም አትጎዱትምም:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::

9:40

إِلَّا تَنصُرُوهُ فَقَدۡ نَصَرَهُ ٱللَّهُ إِذۡ أَخۡرَجَهُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ ثَانِيَ ٱثۡنَيۡنِ إِذۡ هُمَا فِي ٱلۡغَارِ إِذۡ يَقُولُ لِصَٰحِبِهِۦ لَا تَحۡزَنۡ إِنَّ ٱللَّهَ مَعَنَاۖ فَأَنزَلَ ٱللَّهُ سَكِينَتَهُۥ عَلَيۡهِ وَأَيَّدَهُۥ بِجُنُودٖ لَّمۡ تَرَوۡهَا وَجَعَلَ كَلِمَةَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ ٱلسُّفۡلَىٰۗ وَكَلِمَةُ ٱللَّهِ هِيَ ٱلۡعُلۡيَاۗ وَٱللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٌ ﴿40﴾

Transliteration: Illa tansuroohu faqad nasarahu Allahu ith akhrajahu allatheena kafaroo thaniya ithnayni ith huma fee alghari ith yaqoolu lisahibihi la tahzan inna Allaha maAAana faanzala Allahu sakeenatahu AAalayhi waayyadahu bijunoodin lam tarawha wajaAAala kalimata allatheena kafaroo alssufla wakalimatu Allahi hiya alAAulya waAllahu AAazeezun hakeemun

Translation: 40. (ሙስሊሞች ሆይ!) ነብዩ ሙሐመድን ባትረዱት እነዚያ በአላህ የካዱት ህዝቦች የሁለት ሰዎች ሁለተኛ ሆኖ ከመካ ባስወጡት ጊዜ አላህ ረድቶታል:: ሁለቱም በዋሻው ሳሉ ለጓደኛው «አትዘን አላህ ከእኛ ጋር ነውና» ባለ ጊዜ አላህ እርጋታውን በእርሱ ላይ አወረደ:: ባላያችኋቸዉም ሰራዊት አበረታው:: የእነዚያን በአላህ የካዱትን ሰዎች ቃል የበታች አደረገ:: የአላህ ቃል ግን የበላይ ነው:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::

9:41

ٱنفِرُواْ خِفَافٗا وَثِقَالٗا وَجَٰهِدُواْ بِأَمۡوَٰلِكُمۡ وَأَنفُسِكُمۡ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِۚ ذَٰلِكُمۡ خَيۡرٞ لَّكُمۡ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ ﴿41﴾

Transliteration: Infiroo khifafan wathiqalan wajahidoo biamwalikum waanfusikum fee sabeeli Allahi thalikum khayrun lakum in kuntum taAAlamoona

Translation: 41.(አማኞች ሆይ!) ቀላሎችም ከባዶችም ኾናችሁ ዝመቱ:: በአላህ መንገድ በገንዘቦቻችሁና በነፍሶቻችሁ ታገሉ :: ይህ ተግባር የምታውቁ ከሆናችሁ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነው::

9:42

لَوۡ كَانَ عَرَضٗا قَرِيبٗا وَسَفَرٗا قَاصِدٗا لَّٱتَّبَعُوكَ وَلَٰكِنۢ بَعُدَتۡ عَلَيۡهِمُ ٱلشُّقَّةُۚ وَسَيَحۡلِفُونَ بِٱللَّهِ لَوِ ٱسۡتَطَعۡنَا لَخَرَجۡنَا مَعَكُمۡ يُهۡلِكُونَ أَنفُسَهُمۡ وَٱللَّهُ يَعۡلَمُ إِنَّهُمۡ لَكَٰذِبُونَ ﴿42﴾

Transliteration: Law kana AAaradan qareeban wasafaran qasidan laittabaAAooka walakin baAAudat AAalayhimu alshshuqqatu wasayahlifoona biAllahi lawi istataAAna lakharajna maAAakum yuhlikoona anfusahum waAllahu yaAAlamu innahum lakathiboona

Translation: 42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጠራህባቸው ነገር ቅርብ ጥቅምና መካከለኛ ጉዞ በሆነ ኖሮ በተከተሉህ ነበር:: ግን በእነርሱ ላይ መንገዲቱ ራቀችባቸው:: «በቻልንም ኖሮ ከናንተ ጋር በወጣን ነበር» ሲሉ በአላህ ይምላሉ:: እራሳቸውን ለጥፋት (በውሸት) ይዳርጋሉ :: አላህ እነርሱ ውሸታሞች መሆናቸውን ያውቃል::

9:43

عَفَا ٱللَّهُ عَنكَ لِمَ أَذِنتَ لَهُمۡ حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَكَ ٱلَّذِينَ صَدَقُواْ وَتَعۡلَمَ ٱلۡكَٰذِبِينَ ﴿43﴾

Transliteration: AAafa Allahu AAanka lima athinta lahum hatta yatabayyana laka allatheena sadaqoo wataAAlama alkathibeena

Translation: 43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) አላህ ይቅር ብሎሀል:: እነዚያ እውነተኞቹ እስከሚገለጹልህና ውሸታሞቹን ለይተህ እስከምታውቅ ድረስ ለእነርሱ ከዘመቻ እንዲቀሩ ለምን ፈቀድክላቸው?

9:44

لَا يَسۡتَـٔۡذِنُكَ ٱلَّذِينَ يُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِ أَن يُجَٰهِدُواْ بِأَمۡوَٰلِهِمۡ وَأَنفُسِهِمۡۗ وَٱللَّهُ عَلِيمُۢ بِٱلۡمُتَّقِينَ ﴿44﴾

Transliteration: La yastathinuka allatheena yuminoona biAllahi waalyawmi alakhiri an yujahidoo biamwalihim waanfusihim waAllahu AAaleemun bialmuttaqeena

Translation: 44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑት በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው ከመታገላቸው ለመቅረት ፈቃድን አይጠይቁህም:: አላህም በትክክል የሚፈሩትን ሰዎች ሁሉ አዋቂ ነው::

9:45

إِنَّمَا يَسۡتَـٔۡذِنُكَ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِ وَٱرۡتَابَتۡ قُلُوبُهُمۡ فَهُمۡ فِي رَيۡبِهِمۡ يَتَرَدَّدُونَ ﴿45﴾

Transliteration: Innama yastathinuka allatheena la yuminoona biAllahi waalyawmi alakhiri wairtabat quloobuhum fahum fee raybihim yataraddadoona

Translation: 45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ፈቃድ የሚጠይቁህ እነዚያ በአላህና በመጨረሻው ቀን የማያምኑት፤ ልቦቻቸው የተጠራጠሩት ሰዎች ብቻ ናቸው:: እነርሱም በጥርጣሬያቸው ውስጥ ይዋልላሉ::

9:46

وَلَوۡ أَرَادُواْ ٱلۡخُرُوجَ لَأَعَدُّواْ لَهُۥ عُدَّةٗ وَلَٰكِن كَرِهَ ٱللَّهُ ٱنۢبِعَاثَهُمۡ فَثَبَّطَهُمۡ وَقِيلَ ٱقۡعُدُواْ مَعَ ٱلۡقَٰعِدِينَ ﴿46﴾

Transliteration: Walaw aradoo alkhurooja laaAAaddoo lahu AAuddatan walakin kariha Allahu inbiAAathahum fathabbatahum waqeela oqAAudoo maAAa alqaAAideena

Translation: 46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ ዘመቻ መውጣት ባሰቡ ኖሮ ለእርሱ ዝግጅትን ባሰናዱ ነበር:: ግን አላህ ለመውጣት እንቅስቃሴያቸውን ጠላውና አሰነፋቸው:: «ከተቀማጮቹ ጋር ተቀመጡ።» ተባሉም::

9:47

لَوۡ خَرَجُواْ فِيكُم مَّا زَادُوكُمۡ إِلَّا خَبَالٗا وَلَأَوۡضَعُواْ خِلَٰلَكُمۡ يَبۡغُونَكُمُ ٱلۡفِتۡنَةَ وَفِيكُمۡ سَمَّـٰعُونَ لَهُمۡۗ وَٱللَّهُ عَلِيمُۢ بِٱلظَّـٰلِمِينَ ﴿47﴾

Transliteration: Law kharajoo feekum ma zadookum illa khabalan walaawdaAAoo khilalakum yabghoonakumu alfitnata wafeekum sammaAAoona lahum waAllahu AAaleemun bialththalimeena

Translation: 47. (አማኞች ሆይ!) ከናንተ ጋር በወጡ ኖሮ ጥፋትን እንጂ አይጨምሩላችሁም ነበር:: ሁከትንም የሚፈልጉላችሁ ሲሆኑ በመካከላችሁ ነገርን በማሳበቅ ይቻኮሉ ነበር:: በእናንተ ውስጥ ለእነርሱ አዳማጮች አሏቸው:: አላህም በዳዮችን አዋቂ ነው::

9:48

لَقَدِ ٱبۡتَغَوُاْ ٱلۡفِتۡنَةَ مِن قَبۡلُ وَقَلَّبُواْ لَكَ ٱلۡأُمُورَ حَتَّىٰ جَآءَ ٱلۡحَقُّ وَظَهَرَ أَمۡرُ ٱللَّهِ وَهُمۡ كَٰرِهُونَ ﴿48﴾

Transliteration: Laqadi ibtaghawoo alfitnata min qablu waqallaboo laka alomoora hatta jaa alhaqqu wathahara amru Allahi wahum karihoona

Translation: 48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱ ጠይዎች ሲኾኑ እውነቱ እስከመጣና የአላህም ትዕዛዝ እስከተገለጸ ድረስ ከዚህ በፊት ሁከትን በእርግጥ ፈለጉ፡፡ ነገሮችንም ሁሉ አገላበጡልህ፡፡

9:49

وَمِنۡهُم مَّن يَقُولُ ٱئۡذَن لِّي وَلَا تَفۡتِنِّيٓۚ أَلَا فِي ٱلۡفِتۡنَةِ سَقَطُواْۗ وَإِنَّ جَهَنَّمَ لَمُحِيطَةُۢ بِٱلۡكَٰفِرِينَ ﴿49﴾

Transliteration: Waminhum man yaqoolu ithan lee wala taftinnee ala fee alfitnati saqatoo wainna jahannama lamuheetatun bialkafireena

Translation: 49. ከእነርሱም ውስጥ «ፍቀድልኝ አትሞክረኝ» የሚል ሰው አለ። (ሙስሊሞች) አስተውሉ! እነኝህ ሰዎች በመከራ ውስጥ ወደቁ:: ገሀነም ከሓዲያንን ከባቢ ናት::

9:50

إِن تُصِبۡكَ حَسَنَةٞ تَسُؤۡهُمۡۖ وَإِن تُصِبۡكَ مُصِيبَةٞ يَقُولُواْ قَدۡ أَخَذۡنَآ أَمۡرَنَا مِن قَبۡلُ وَيَتَوَلَّواْ وَّهُمۡ فَرِحُونَ ﴿50﴾

Transliteration: In tusibka hasanatun tasuhum wain tusibka museebatun yaqooloo qad akhathna amrana min qablu wayatawallaw wahum farihoona

Translation: 50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መልካም ነገር ቢያገኝህ ያስከፋቸዋል:: መከራ ቢያገኝህ ግን «ፊቱንም ይህን ፈርተን የግል ጥንቃቄያችንን ይዘናል።» ይላሉ። ተደሳቾች ሆነዉም ይሸሻሉ::

9:51

قُل لَّن يُصِيبَنَآ إِلَّا مَا كَتَبَ ٱللَّهُ لَنَا هُوَ مَوۡلَىٰنَاۚ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلۡيَتَوَكَّلِ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ ﴿51﴾

Transliteration: Qul lan yuseebana illa ma kataba Allahu lana huwa mawlana waAAala Allahi falyatawakkali almuminoona

Translation: 51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ለእኛ የጻፈልን እንጂ ሌላ አይነካንም:: እርሱ ረዳታችን ነው:: ምዕምናን በአላህ ላይ ብቻ ይመኩ።» በላቸው::

9:52

قُلۡ هَلۡ تَرَبَّصُونَ بِنَآ إِلَّآ إِحۡدَى ٱلۡحُسۡنَيَيۡنِۖ وَنَحۡنُ نَتَرَبَّصُ بِكُمۡ أَن يُصِيبَكُمُ ٱللَّهُ بِعَذَابٖ مِّنۡ عِندِهِۦٓ أَوۡ بِأَيۡدِينَاۖ فَتَرَبَّصُوٓاْ إِنَّا مَعَكُم مُّتَرَبِّصُونَ ﴿52﴾

Transliteration: Qul hal tarabbasoona bina illa ihda alhusnayayni wanahnu natarabbasu bikum an yuseebakumu Allahu biAAathabin min AAindihi aw biaydeena fatarabbasoo inna maAAakum mutarabbisoona

Translation: 52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእኛ ላይ ከሁለቱ መልካሞች አንደኛዋን እንጂ ሌላን ትጠባበቃላችሁን? እኛም አላህ ከእርሱ በሆነው ቅጣት ወይም በእጆቻችን የሚያጠፋችሁ መሆኑን በእናንተ ላይ እንጠባበቃለን:: ተጠባበቁ:: እኛም ከናንተው ጋር ተጠባባቂዎች ነንና።» በላቸው::

9:53

قُلۡ أَنفِقُواْ طَوۡعًا أَوۡ كَرۡهٗا لَّن يُتَقَبَّلَ مِنكُمۡ إِنَّكُمۡ كُنتُمۡ قَوۡمٗا فَٰسِقِينَ ﴿53﴾

Transliteration: Qul anfiqoo tawAAan aw karhan lan yutaqabbala minkum innakum kuntum qawman fasiqeena

Translation: 53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ወዳችሁም ሆነ ጠልታችሁ ለግሱ ከናንተ ተቀባይ የላችሁም:: እናንተ አመጸኞች ህዝቦች ናችሁና።» በላቸው::

9:54

وَمَا مَنَعَهُمۡ أَن تُقۡبَلَ مِنۡهُمۡ نَفَقَٰتُهُمۡ إِلَّآ أَنَّهُمۡ كَفَرُواْ بِٱللَّهِ وَبِرَسُولِهِۦ وَلَا يَأۡتُونَ ٱلصَّلَوٰةَ إِلَّا وَهُمۡ كُسَالَىٰ وَلَا يُنفِقُونَ إِلَّا وَهُمۡ كَٰرِهُونَ ﴿54﴾

Transliteration: Wama manaAAahum an tuqbala minhum nafaqatuhum illa annahum kafaroo biAllahi wabirasoolihi wala yatoona alssalata illa wahum kusala wala yunfiqoona illa wahum karihoona

Translation: 54. ልግስናዎቻቸውን ከእነርሱ ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ያደረገው በአላህና በመልዕክተኛው የካዱ፤ ሶላትንም ስልቹዎች ሆነው እንጂ የማይሰግዱ፤ እነርሱም ጠይዎች ሆነው እንጂ የማይሰጡ ከመሆናቸው በስተቀር ሌላ ነገር አልከለከላቸዉም::

9:55

فَلَا تُعۡجِبۡكَ أَمۡوَٰلُهُمۡ وَلَآ أَوۡلَٰدُهُمۡۚ إِنَّمَا يُرِيدُ ٱللَّهُ لِيُعَذِّبَهُم بِهَا فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَتَزۡهَقَ أَنفُسُهُمۡ وَهُمۡ كَٰفِرُونَ ﴿55﴾

Transliteration: Fala tuAAjibka amwaluhum wala awladuhum innama yureedu Allahu liyuAAaththibahum biha fee alhayati alddunya watazhaqa anfusuhum wahum kafiroona

Translation: 55. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸው አይድነቁህ:: አላህ የሚሻው በቅርቢቱ ህይወት በእነርሱ (በገንዘቦቻቸውና በልጆቻቸው) ሊቀጣቸው ነፍሶቻቸዉም ከሓዲያን ሆነው ሊሞቱ ብቻ ነውና::

9:56

وَيَحۡلِفُونَ بِٱللَّهِ إِنَّهُمۡ لَمِنكُمۡ وَمَا هُم مِّنكُمۡ وَلَٰكِنَّهُمۡ قَوۡمٞ يَفۡرَقُونَ ﴿56﴾

Transliteration: Wayahlifoona biAllahi innahum laminkum wama hum minkum walakinnahum qawmun yafraqoona

Translation: 56. እነርሱም ከናንተ ጋር ለመሆናቸው በአላህ ይምላሉ:: እነርሱ ግን ከናንተ ጋር አይደሉም:: ይልቁንም እነርሱ አጋሪዎችን ያገኘው ነገር እንዳያገኛቸው የሚፈሩ ህዝቦች ናቸው::

9:57

لَوۡ يَجِدُونَ مَلۡجَـًٔا أَوۡ مَغَٰرَٰتٍ أَوۡ مُدَّخَلٗا لَّوَلَّوۡاْ إِلَيۡهِ وَهُمۡ يَجۡمَحُونَ ﴿57﴾

Transliteration: Law yajidoona maljaan aw magharatin aw muddakhalan lawallaw ilayhi wahum yajmahoona

Translation: 57. (ሙስሊሞች ሆይ!) መጠጊያ ወይም መሸሸጊያ ዋሻዎችን ወይም መግቢያ ቀዳዳዎችን ባገኙ ኖሮ በፍጥነት ወደ እርሱ በሸሹ ነበር::

9:58

وَمِنۡهُم مَّن يَلۡمِزُكَ فِي ٱلصَّدَقَٰتِ فَإِنۡ أُعۡطُواْ مِنۡهَا رَضُواْ وَإِن لَّمۡ يُعۡطَوۡاْ مِنۡهَآ إِذَا هُمۡ يَسۡخَطُونَ ﴿58﴾

Transliteration: Waminhum man yalmizuka fee alssadaqati fain oAAtoo minha radoo wain lam yuAAtaw minha itha hum yaskhatoona

Translation: 58. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ መካከል በምጽዋቶች ክፍፍል ዙሪያ የሚዘልፉህ ሰዎች አሉ:: ከእርሷም የሚሹትን ያህል ቢሰጡ ይደሰታሉ:: ከእርሷ ምንም ካልተሰጣቸው ግን ይጠላሉ::

9:59

وَلَوۡ أَنَّهُمۡ رَضُواْ مَآ ءَاتَىٰهُمُ ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥ وَقَالُواْ حَسۡبُنَا ٱللَّهُ سَيُؤۡتِينَا ٱللَّهُ مِن فَضۡلِهِۦ وَرَسُولُهُۥٓ إِنَّآ إِلَى ٱللَّهِ رَٰغِبُونَ ﴿59﴾

Transliteration: Walaw annahum radoo ma atahumu Allahu warasooluhu waqaloo hasbuna Allahu sayuteena Allahu min fadlihi warasooluhu inna ila Allahi raghiboona

Translation: 59. እነርሱም አላህና መልእክተኛው የሰጣቸውን በወደዱ፤ «አላህ በቂያችን ነው አላህ ከችሮታው በእርግጥ ይሰጠናል፣ መልክተኛውም (ይሰጠናል) እኛ ወደ አላህ ከጃዮች ነን።» ባሉ ኖሮ ለነርሱ በተሸላቸው ነበር::

9:60

إِنَّمَا ٱلصَّدَقَٰتُ لِلۡفُقَرَآءِ وَٱلۡمَسَٰكِينِ وَٱلۡعَٰمِلِينَ عَلَيۡهَا وَٱلۡمُؤَلَّفَةِ قُلُوبُهُمۡ وَفِي ٱلرِّقَابِ وَٱلۡغَٰرِمِينَ وَفِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَٱبۡنِ ٱلسَّبِيلِۖ فَرِيضَةٗ مِّنَ ٱللَّهِۗ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٞ ﴿60﴾

Transliteration: Innama alssadaqatu lilfuqarai waalmasakeeni waalAAamileena AAalayha waalmuallafati quloobuhum wafee alrriqabi waalgharimeena wafee sabeeli Allahi waibni alssabeeli fareedatan mina Allahi waAllahu AAaleemun hakeemun

Translation: 60. ግዴታ ዘካን የሚከፈሉት ለድሆች፤ ለችግረኞች፤ በእርሷም ላይ ለሚሰሩ ሠራተኞች፤ ልቦቻቸው በኢስላም ለሚለማመዱት ወገኖች፤ ጫንቃዎችን (ባሪያዎች) ነጻ ለማውጣት፤ ባለ እዳ ለሆኑት፤ በአላህ መንገድም ለሚሰሩና (ስንቅ ላለቀበት) መንገደኛ ብቻ ነው:: ይህ ስርአት ከአላህ የተደነገገ ግዴታ ነው:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።

9:61

وَمِنۡهُمُ ٱلَّذِينَ يُؤۡذُونَ ٱلنَّبِيَّ وَيَقُولُونَ هُوَ أُذُنٞۚ قُلۡ أُذُنُ خَيۡرٖ لَّكُمۡ يُؤۡمِنُ بِٱللَّهِ وَيُؤۡمِنُ لِلۡمُؤۡمِنِينَ وَرَحۡمَةٞ لِّلَّذِينَ ءَامَنُواْ مِنكُمۡۚ وَٱلَّذِينَ يُؤۡذُونَ رَسُولَ ٱللَّهِ لَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ ﴿61﴾

Transliteration: Waminhumu allatheena yuthoona alnnabiyya wayaqooloona huwa othunun qul othunu khayrin lakum yuminu biAllahi wayuminu lilmumineena warahmatun lillatheena amanoo minkum waallatheena yuthoona rasoola Allahi lahum AAathabun aleemun

Translation: 61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) ከአስመሳዮች መካከል ነብዩ ሙሐመድን የሚያስቸግሩና «እርሱ እኮ ወሬ ሰሚ ነው።» የሚሉ አሉ። «ለእናንተ የበጎ ወሬ ሰሚ ነው:: በአላህ ያምናል:: አማኞችንም ያምናቸዋል:: ከናንተ መካከል ለእነዚያ በአላህ ላመኑት ሰዎችም እዝነት ነው።» በላቸው:: እነዚያ የአላህን መልዕክተኛ የሚያስቸግሩ ሰዎች ሁሉ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው።

9:62

يَحۡلِفُونَ بِٱللَّهِ لَكُمۡ لِيُرۡضُوكُمۡ وَٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥٓ أَحَقُّ أَن يُرۡضُوهُ إِن كَانُواْ مُؤۡمِنِينَ ﴿62﴾

Transliteration: Yahlifoona biAllahi lakum liyurdookum waAllahu warasooluhu ahaqqu an yurdoohu in kanoo mumineena

Translation: 62. አላህንና መልዕክተኛውን ሊያስወድዱ ሲገባቸው እናንተን ሊያስወድዷችሁ ዘንድ በአላህ ይምሉላችኋል። ትክክለኛ አማኞች ከሆኑ (ግን አላህንና መልዕክተኛው ሊያስወድዱ ይገባቸዋል)::

9:63

أَلَمۡ يَعۡلَمُوٓاْ أَنَّهُۥ مَن يُحَادِدِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ فَأَنَّ لَهُۥ نَارَ جَهَنَّمَ خَٰلِدٗا فِيهَاۚ ذَٰلِكَ ٱلۡخِزۡيُ ٱلۡعَظِيمُ ﴿63﴾

Transliteration: Alam yaAAlamoo annahu man yuhadidi Allaha warasoolahu faanna lahu nara jahannama khalidan feeha thalika alkhizyu alAAatheemu

Translation: 63. አላህንና መልዕክተኛውን የሚከራከር ሰው ሁሉ በውስጡ ዘውታሪ ሲሆን የተዘጋጀችለት የገሀነም እሳት መሆኑን አያውቁምን? ይህ ደግሞ ታላቅ ውርደት ነው::

9:64

يَحۡذَرُ ٱلۡمُنَٰفِقُونَ أَن تُنَزَّلَ عَلَيۡهِمۡ سُورَةٞ تُنَبِّئُهُم بِمَا فِي قُلُوبِهِمۡۚ قُلِ ٱسۡتَهۡزِءُوٓاْ إِنَّ ٱللَّهَ مُخۡرِجٞ مَّا تَحۡذَرُونَ ﴿64﴾

Transliteration: Yahtharu almunafiqoona an tunazzala AAalayhim sooratun tunabbiohum bima fee quloobihim quli istahzioo inna Allaha mukhrijun ma tahtharoona

Translation: 64. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አስመሳዮች በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ የሚነግራቸው ምዕራፍ በእነርሱ ላይ መወረዱን ዘወትር ይፈራሉ:: «ተሳለቁ:: አላህ የምትፈሩትን ነገር ሁሉ ገላጭ ነው።» በላቸው::

9:65

وَلَئِن سَأَلۡتَهُمۡ لَيَقُولُنَّ إِنَّمَا كُنَّا نَخُوضُ وَنَلۡعَبُۚ قُلۡ أَبِٱللَّهِ وَءَايَٰتِهِۦ وَرَسُولِهِۦ كُنتُمۡ تَسۡتَهۡزِءُونَ ﴿65﴾

Transliteration: Walain saaltahum layaqoolunna innama kunna nakhoodu wanalAAabu qul abiAllahi waayatihi warasoolihi kuntum tastahzioona

Translation: 65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ብትጠይቃቸው «እኛ የምንዘባርቅና የምንጫወት ሰዎች ብቻ ነበርን።» ይላሉ:: «በአላህ፤ በአናቅጹና በመልዕክተኛው ላይ ትቀልዱ ነበራችሁን?» በላቸው::

9:66

لَا تَعۡتَذِرُواْ قَدۡ كَفَرۡتُم بَعۡدَ إِيمَٰنِكُمۡۚ إِن نَّعۡفُ عَن طَآئِفَةٖ مِّنكُمۡ نُعَذِّبۡ طَآئِفَةَۢ بِأَنَّهُمۡ كَانُواْ مُجۡرِمِينَ ﴿66﴾

Transliteration: La taAAtathiroo qad kafartum baAAda eemanikum in naAAfu AAan taifatin minkum nuAAaththib taifatan biannahum kanoo mujrimeena

Translation: 66. (አስመሳዮች ሆይ!) አታመካኙ ከእምነታችሁ በኋላ በእርግጥ ክዳችኋልና:: ከናንተ አንዷን ቡድን ብንምር የሌላዋን ቡድን አባላት ግን ኃጢአተኞች በመሆናቸው እንቀጣለን::

9:67

ٱلۡمُنَٰفِقُونَ وَٱلۡمُنَٰفِقَٰتُ بَعۡضُهُم مِّنۢ بَعۡضٖۚ يَأۡمُرُونَ بِٱلۡمُنكَرِ وَيَنۡهَوۡنَ عَنِ ٱلۡمَعۡرُوفِ وَيَقۡبِضُونَ أَيۡدِيَهُمۡۚ نَسُواْ ٱللَّهَ فَنَسِيَهُمۡۚ إِنَّ ٱلۡمُنَٰفِقِينَ هُمُ ٱلۡفَٰسِقُونَ ﴿67﴾

Transliteration: Almunafiqoona waalmunafiqatu baAAduhum min baAAdin yamuroona bialmunkari wayanhawna AAani almaAAroofi wayaqbidoona aydiyahum nasoo Allaha fanasiyahum inna almunafiqeena humu alfasiqoona

Translation: 67. የወንድ አስመሳዮችና የሴት አስመሳዮች ከፊሎቻቸው ከከፊሉ ናቸው:: በመጥፎ ነገር ያዛሉ:: ከደግ ነገርም ይከለክላሉ:: እጆቻቸውን ከልግስና ይሰበስባሉ:: ለአላህ መታዘዝን ረሱ (ተዉ):: ስለዚህ እርሱም ተዋቸው:: አስመሳዮቹ አመጸኞች ማለት እነርሱው ናቸው::

9:68

وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلۡمُنَٰفِقِينَ وَٱلۡمُنَٰفِقَٰتِ وَٱلۡكُفَّارَ نَارَ جَهَنَّمَ خَٰلِدِينَ فِيهَاۚ هِيَ حَسۡبُهُمۡۚ وَلَعَنَهُمُ ٱللَّهُۖ وَلَهُمۡ عَذَابٞ مُّقِيمٞ ﴿68﴾

Transliteration: WaAAada Allahu almunafiqeena waalmunafiqati waalkuffara nara jahannama khalideena feeha hiya hasbuhum walaAAanahumu Allahu walahum AAathabun muqeemun

Translation: 68. የወንድ አስመሳዮችንና የሴት አስመሳዮችን እንዲሁም ከሓዲያንን የገሀነምን እሳት በውስጧ ዘውታሪዎች ሲሆኑ አላህ ቃል ገብቶላቸዋል:: እርሷ በቂያቸው ናት:: አላህ ረግሟቸዋል:: ለእነርሱም ዘውታሪ ቅጣት አለባቸው::

9:69

كَٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكُمۡ كَانُوٓاْ أَشَدَّ مِنكُمۡ قُوَّةٗ وَأَكۡثَرَ أَمۡوَٰلٗا وَأَوۡلَٰدٗا فَٱسۡتَمۡتَعُواْ بِخَلَٰقِهِمۡ فَٱسۡتَمۡتَعۡتُم بِخَلَٰقِكُمۡ كَمَا ٱسۡتَمۡتَعَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكُم بِخَلَٰقِهِمۡ وَخُضۡتُمۡ كَٱلَّذِي خَاضُوٓاْۚ أُوْلَـٰٓئِكَ حَبِطَتۡ أَعۡمَٰلُهُمۡ فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِۖ وَأُوْلَـٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡخَٰسِرُونَ ﴿69﴾

Transliteration: Kaallatheena min qablikum kanoo ashadda minkum quwwatan waakthara amwalan waawladan faistamtaAAoo bikhalaqihim faistamtaAAtum bikhalaqikum kama istamtaAAa allatheena min qablikum bikhalaqihim wakhudtum kaallathee khadoo olaika habitat aAAmaluhum fee alddunya waalakhirati waolaika humu alkhasiroona

Translation: 69. (አስመሳዮች ሆይ!) ተግባራችሁ ልክ እንደእነዚያ ከናንተ በፊት እንደነበሩት ህዝቦች ነው:: ከናንተ ይበልጥ በሃይል የበረቱ በገንዘብና በልጆችም ከናንተ ይበልጥ የበዙ ነበሩ:: በእድላቸው ተጠቀሙ:: እነዚያም ከእናንተ በፊት የነበሩት በዕድላቸው እንደተጠቀሙ በዕድላችሁ ተጠቀማችሁ፡፡ እንደዘባረቁትም ዘባረቃችሁ:: እነዚያ ስራዎቻቸው በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ተበላሸ:: ከሳሪዎቹም ማለት እነርሱው ናቸው::

9:70

أَلَمۡ يَأۡتِهِمۡ نَبَأُ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ قَوۡمِ نُوحٖ وَعَادٖ وَثَمُودَ وَقَوۡمِ إِبۡرَٰهِيمَ وَأَصۡحَٰبِ مَدۡيَنَ وَٱلۡمُؤۡتَفِكَٰتِۚ أَتَتۡهُمۡ رُسُلُهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِۖ فَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيَظۡلِمَهُمۡ وَلَٰكِن كَانُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ ﴿70﴾

Transliteration: Alam yatihim nabao allatheena min qablihim qawmi noohin waAAadin wathamooda waqawmi ibraheema waashabi madyana waalmutafikati atathum rusuluhum bialbayyinati fama kana Allahu liyathlimahum walakin kanoo anfusahum yathlimoona

Translation: 70. የእነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት የኑህ፤ የዓድ፤ የሰሙድ፤ የኢብራሂም ህዝቦች፤ የመድየን ባለቤቶችና የተገልባጮቹም ከተሞች ታሪክ አልመጣላቸዉምን? መልዕክተኞቻቸው ግልጽ ተዓምራትን አመጡላቸው:: አላህ የሚበድላቸው አልነበረም:: ግን በራሳቸው ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ::

9:71

وَٱلۡمُؤۡمِنُونَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتُ بَعۡضُهُمۡ أَوۡلِيَآءُ بَعۡضٖۚ يَأۡمُرُونَ بِٱلۡمَعۡرُوفِ وَيَنۡهَوۡنَ عَنِ ٱلۡمُنكَرِ وَيُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَيُؤۡتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَيُطِيعُونَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥٓۚ أُوْلَـٰٓئِكَ سَيَرۡحَمُهُمُ ٱللَّهُۗ إِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٞ ﴿71﴾

Transliteration: Waalmuminoona waalmuminatu baAAduhum awliyao baAAdin yamuroona bialmaAAroofi wayanhawna AAani almunkari wayuqeemoona alssalata wayutoona alzzakata wayuteeAAoona Allaha warasoolahu olaika sayarhamuhumu Allahu inna Allaha AAazeezun hakeemun

Translation: 71. ወንድ አማኞችና ሴት አማኞች ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው:: በደግ ነገር ያዝዛሉ:: ከክፉም ነገር ይከለክላሉ:: ሶላትን ይሰግዳሉ:: ዘካን ይሰጣሉ:: አላህንና መልዕክተኛውን ይታዘዛሉ:: እነዚያን አላህ በእርግጥ ያዝንላቸዋል:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::

9:72

وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ جَنَّـٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا وَمَسَٰكِنَ طَيِّبَةٗ فِي جَنَّـٰتِ عَدۡنٖۚ وَرِضۡوَٰنٞ مِّنَ ٱللَّهِ أَكۡبَرُۚ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ ﴿72﴾

Transliteration: WaAAada Allahu almumineena waalmuminati jannatin tajree min tahtiha alanharu khalideena feeha wamasakina tayyibatan fee jannati AAadnin waridwanun mina Allahi akbaru thalika huwa alfawzu alAAatheemu

Translation: 72. አላህ የወንድ ትክክለኛ አማኞችንና የሴት ትክክለኛ አማኞችን ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ በመኖሪያ ገነቶችም ውስጥ መልካም መኖሪያ ቤቶችን ቃል ገብቶላቸዋል:: ከአላህ የሆነው ውዴታ ደግሞ ከሁሉ የበለጠ ነው:: ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው::

9:73

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ جَٰهِدِ ٱلۡكُفَّارَ وَٱلۡمُنَٰفِقِينَ وَٱغۡلُظۡ عَلَيۡهِمۡۚ وَمَأۡوَىٰهُمۡ جَهَنَّمُۖ وَبِئۡسَ ٱلۡمَصِيرُ ﴿73﴾

Transliteration: Ya ayyuha alnnabiyyu jahidi alkuffara waalmunafiqeena waoghluth AAalayhim wamawahum jahannamu wabisa almaseeru

Translation: 73. አንተ ነብዩ ሆይ! ከሓዲያንንና አስመሳዮችን ታገል:: በእነርሱ ላይም ጨክን:: መኖሪያቸዉም ገሀነም ናት:: መመለሻይቱም በጣም ከፋች::

9:74

يَحۡلِفُونَ بِٱللَّهِ مَا قَالُواْ وَلَقَدۡ قَالُواْ كَلِمَةَ ٱلۡكُفۡرِ وَكَفَرُواْ بَعۡدَ إِسۡلَٰمِهِمۡ وَهَمُّواْ بِمَا لَمۡ يَنَالُواْۚ وَمَا نَقَمُوٓاْ إِلَّآ أَنۡ أَغۡنَىٰهُمُ ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥ مِن فَضۡلِهِۦۚ فَإِن يَتُوبُواْ يَكُ خَيۡرٗا لَّهُمۡۖ وَإِن يَتَوَلَّوۡاْ يُعَذِّبۡهُمُ ٱللَّهُ عَذَابًا أَلِيمٗا فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِۚ وَمَا لَهُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ مِن وَلِيّٖ وَلَا نَصِيرٖ ﴿74﴾

Transliteration: Yahlifoona biAllahi ma qaloo walaqad qaloo kalimata alkufri wakafaroo baAAda islamihim wahammoo bima lam yanaloo wama naqamoo illa an aghnahumu Allahu warasooluhu min fadlihi fain yatooboo yaku khayran lahum wain yatawallaw yuAAaththibhumu Allahu AAathaban aleeman fee alddunya waalakhirati wama lahum fee alardi min waliyyin wala naseerin

Translation: 74. ምንም ያላሉ ለመሆናቸው በአላህ ይምላሉ:: ግን የክህደትን ቃል በእርግጥ አሉ:: ከእስልምናቸዉም በኋላ ካዱ:: ያላገኙትንም ነገር አሰቡ:: አላህና መልዕክተኛው ከችሮታው ያከበራቸው መሆኑን እንጂ ሌላን አልጠሉም:: ቢጸጸቱም ለእነርሱ የተሻለ ይሆናል:: ቢሸሹም አላህ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም አሳማሚን ቅጣት ይቀጣቸዋል:: ለእነርሱም በምድር ውስጥ ምንም ወዳጅና ረዳት የላቸዉም::

9:75

وَمِنۡهُم مَّنۡ عَٰهَدَ ٱللَّهَ لَئِنۡ ءَاتَىٰنَا مِن فَضۡلِهِۦ لَنَصَّدَّقَنَّ وَلَنَكُونَنَّ مِنَ ٱلصَّـٰلِحِينَ ﴿75﴾

Transliteration: Waminhum man AAahada Allaha lain atana min fadlihi lanassaddaqanna walanakoonanna mina alssaliheena

Translation: 75. ከእነርሱም መካከል አላህን «ከችሮታው ቢሰጠን በእርግጥ እንመጸውታለን::በእርግጥ ከመልካሞችም እንሆናለን።» ሲል ቃል የገባ አለ::

9:76

فَلَمَّآ ءَاتَىٰهُم مِّن فَضۡلِهِۦ بَخِلُواْ بِهِۦ وَتَوَلَّواْ وَّهُم مُّعۡرِضُونَ ﴿76﴾

Transliteration: Falamma atahum min fadlihi bakhiloo bihi watawallaw wahum muAAridoona

Translation: 76. ከዚያም ከችሮታዉም በሰጣቸው ጊዜ ሰሰቱ:: እነርሱ ቃል ኪዳናቸውን የተው ሆነዉም ዞሩ::

9:77

فَأَعۡقَبَهُمۡ نِفَاقٗا فِي قُلُوبِهِمۡ إِلَىٰ يَوۡمِ يَلۡقَوۡنَهُۥ بِمَآ أَخۡلَفُواْ ٱللَّهَ مَا وَعَدُوهُ وَبِمَا كَانُواْ يَكۡذِبُونَ ﴿77﴾

Transliteration: FaaAAqabahum nifaqan fee quloobihim ila yawmi yalqawnahu bima akhlafoo Allaha ma waAAadoohu wabima kanoo yakthiboona

Translation: 77. ለአላህ ቃል የገቡትን በማፍረሳቸውና ይዋሹትም በነበሩት ውሸት ምክንያት እስከሚገናኙት ቀን ድረስ ንፍቅናን በልቦቻቻው አስከተላቸው::

9:78

أَلَمۡ يَعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ سِرَّهُمۡ وَنَجۡوَىٰهُمۡ وَأَنَّ ٱللَّهَ عَلَّـٰمُ ٱلۡغُيُوبِ ﴿78﴾

Transliteration: Alam yaAAlamoo anna Allaha yaAAlamu sirrahum wanajwahum waanna Allaha AAallamu alghuyoobi

Translation: 78. (አስመሳዮችን) አላህ ምስጢራቸውንና ውይይታቸውን የሚያውቅ መሆኑንና አላህም ሩቅ ነገሮችን ሁሉ በጣም አዋቂ መሆኑን አያውቁምን?

9:79

ٱلَّذِينَ يَلۡمِزُونَ ٱلۡمُطَّوِّعِينَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ فِي ٱلصَّدَقَٰتِ وَٱلَّذِينَ لَا يَجِدُونَ إِلَّا جُهۡدَهُمۡ فَيَسۡخَرُونَ مِنۡهُمۡ سَخِرَ ٱللَّهُ مِنۡهُمۡ وَلَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٌ ﴿79﴾

Transliteration: Allatheena yalmizoona almuttawwiAAeena mina almumineena fee alssadaqati waallatheena la yajidoona illa juhdahum fayaskharoona minhum sakhira Allahu minhum walahum AAathabun aleemun

Translation: 79. እነዚያ ከምዕምናን በምጽዋቶች ፈቃደኛ የሆኑትን የችሎታቸውን ያክል እንጂ የማያገኙትን ሰዎች የሚያነውሩና በእነርሱ የሚሳለቁ ሰዎች ሁሉ አላህ ከእነርሱ ይሳለቅባቸዋል:: ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::

9:80

ٱسۡتَغۡفِرۡ لَهُمۡ أَوۡ لَا تَسۡتَغۡفِرۡ لَهُمۡ إِن تَسۡتَغۡفِرۡ لَهُمۡ سَبۡعِينَ مَرَّةٗ فَلَن يَغۡفِرَ ٱللَّهُ لَهُمۡۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ كَفَرُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦۗ وَٱللَّهُ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلۡفَٰسِقِينَ ﴿80﴾

Transliteration: Istaghfir lahum aw la tastaghfir lahum in tastaghfir lahum sabAAeena marratan falan yaghfira Allahu lahum thalika biannahum kafaroo biAllahi warasoolihi waAllahu la yahdee alqawma alfasiqeena

Translation: 80. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነርሱ ምሕረትን ብትለምንላቸዉም ወይም ባትለምንላቸው ሁሉም እኩል ነው:: ለእነርሱ ሰባ ጊዜ ምህረትን ብትለምንላቸው እንኳን አላህ በፍጹም አይምራቸዉምና:: ምክንያቱም እነርሱ በአላህና በመልዕክተኛው ክደዋልና:: አላህ አመጸኞች ህዝቦችን አያቀናም::

9:81

فَرِحَ ٱلۡمُخَلَّفُونَ بِمَقۡعَدِهِمۡ خِلَٰفَ رَسُولِ ٱللَّهِ وَكَرِهُوٓاْ أَن يُجَٰهِدُواْ بِأَمۡوَٰلِهِمۡ وَأَنفُسِهِمۡ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَقَالُواْ لَا تَنفِرُواْ فِي ٱلۡحَرِّۗ قُلۡ نَارُ جَهَنَّمَ أَشَدُّ حَرّٗاۚ لَّوۡ كَانُواْ يَفۡقَهُونَ ﴿81﴾

Transliteration: Fariha almukhallafoona bimaqAAadihim khilafa rasooli Allahi wakarihoo an yujahidoo biamwalihim waanfusihim fee sabeeli Allahi waqaloo la tanfiroo fee alharri qul naru jahannama ashaddu harran law kanoo yafqahoona

Translation: 81. እነዚያ ከዘመቻ የቀሩት ሰዎች ከአላህ መልዕክተኛ በኋላ ተገንጥለው በመቀመጣቸው ተደሰቱ:: በአላህ መንገድ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው መታገልን ጠሉ:: ለሌሎችም «በሐሩር አትሂዱ» አሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የገሀነም እሳት ትኩሳት በጣም ከዚህ የበረታ ነው።» በላቸው:: እናም የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ ከዘመቻው አይቀሩም ነበር::

9:82

فَلۡيَضۡحَكُواْ قَلِيلٗا وَلۡيَبۡكُواْ كَثِيرٗا جَزَآءَۢ بِمَا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ ﴿82﴾

Transliteration: Falyadhakoo qaleelan walyabkoo katheeran jazaan bima kanoo yaksiboona

Translation: 82. አስመሳዮች ጥቂት ጊዜን ብቻ ይሳቁ:: ይሠሩት በነበሩት እኩይ ተግባር ምክንያት ዋጋ ብዙ ጊዜ ያለቅሳሉና::

9:83

فَإِن رَّجَعَكَ ٱللَّهُ إِلَىٰ طَآئِفَةٖ مِّنۡهُمۡ فَٱسۡتَـٔۡذَنُوكَ لِلۡخُرُوجِ فَقُل لَّن تَخۡرُجُواْ مَعِيَ أَبَدٗا وَلَن تُقَٰتِلُواْ مَعِيَ عَدُوًّاۖ إِنَّكُمۡ رَضِيتُم بِٱلۡقُعُودِ أَوَّلَ مَرَّةٖ فَٱقۡعُدُواْ مَعَ ٱلۡخَٰلِفِينَ ﴿83﴾

Transliteration: Fain rajaAAaka Allahu ila taifatin minhum faistathanooka lilkhurooji faqul lan takhrujoo maAAiya abadan walan tuqatiloo maAAiya AAaduwwan innakum radeetum bialquAAoodi awwala marratin faoqAAudoo maAAa alkhalifeena

Translation: 83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ መካከል ወደ ሆነችው ቡድን አላህ በሰላም ቢመልስህና ካንተ ጋር ዘመቻ ለመውጣት ቢያስፈቅዱህ «ከእኔ ጋር በፍጹም አትወጡም:: ከእኔም ጋር ጠላትን አትዋጉም:: እናንተ በመጀመሪያ ጊዜ መቀመጥን ወዳችኋልና:: ይልቁንም ከተቀማጮች ጋር ተቀመጡ።» በላቸው::

9:84

وَلَا تُصَلِّ عَلَىٰٓ أَحَدٖ مِّنۡهُم مَّاتَ أَبَدٗا وَلَا تَقُمۡ عَلَىٰ قَبۡرِهِۦٓۖ إِنَّهُمۡ كَفَرُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَمَاتُواْ وَهُمۡ فَٰسِقُونَ ﴿84﴾

Transliteration: Wala tusalli AAala ahadin minhum mata abadan wala taqum AAala qabrihi innahum kafaroo biAllahi warasoolihi wamatoo wahum fasiqoona

Translation: 84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ መካከል በሞተ በአንዱም ሰው ላይ ቢሆን ፈጽሞ አትስገድ:: በመቃብሩም ላይ አትቁም:: እነርሱ በአላህና በመልዕክተኛው ክደዋል:: እነርሱ አመጸኞችም ሆነው ሞተዋልና::

9:85

وَلَا تُعۡجِبۡكَ أَمۡوَٰلُهُمۡ وَأَوۡلَٰدُهُمۡۚ إِنَّمَا يُرِيدُ ٱللَّهُ أَن يُعَذِّبَهُم بِهَا فِي ٱلدُّنۡيَا وَتَزۡهَقَ أَنفُسُهُمۡ وَهُمۡ كَٰفِرُونَ ﴿85﴾

Transliteration: Wala tuAAjibka amwaluhum waawladuhum innama yureedu Allahu an yuAAaththibahum biha fee alddunya watazhaqa anfusuhum wahum kafiroona

Translation: 85. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸው አይድነቁህ:: አላህ የሚፈልገው በቅርቢቱ ዓለም በገንዘቦቻቸውና በልጆቻቸው ሊቀጣቸውና ከሓዲያንም ሆነው ነፍሶቻቸው እንዲወጡ ሊያደርግ ብቻ ነውና::

9:86

وَإِذَآ أُنزِلَتۡ سُورَةٌ أَنۡ ءَامِنُواْ بِٱللَّهِ وَجَٰهِدُواْ مَعَ رَسُولِهِ ٱسۡتَـٔۡذَنَكَ أُوْلُواْ ٱلطَّوۡلِ مِنۡهُمۡ وَقَالُواْ ذَرۡنَا نَكُن مَّعَ ٱلۡقَٰعِدِينَ ﴿86﴾

Transliteration: Waitha onzilat sooratun an aminoo biAllahi wajahidoo maAAa rasoolihi istathanaka oloo alttawli minhum waqaloo tharna nakun maAAa alqaAAideena

Translation: 86. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ እመኑ:: ከመልዕክተኛው ጋር ሆናችሁ ታገሉ በማለት የቁርኣን ምዕራፍ በተወረደ ጊዜ ከእነርሱ የሰፊ ሀብት ባለቤቶች የሆኑት ሰዎች ለመቅረት ፈቃድ ይጠይቁሃል:: «ከተቀማጮቹ ጋር እንሁን ተወን» ይሉሃል::

9:87

رَضُواْ بِأَن يَكُونُواْ مَعَ ٱلۡخَوَالِفِ وَطُبِعَ عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ فَهُمۡ لَا يَفۡقَهُونَ ﴿87﴾

Transliteration: Radoo bian yakoonoo maAAa alkhawalifi watubiAAa AAala quloobihim fahum la yafqahoona

Translation: 87. በቤት ከሚቀሩት ወገኖች ጋር መሆናቸውን ወደዱ:: በልቦቻቸዉም ላይ (ዝገት) ታተመባቸው:: ስለዚህ እነርሱ አያውቁም::

9:88

لَٰكِنِ ٱلرَّسُولُ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَعَهُۥ جَٰهَدُواْ بِأَمۡوَٰلِهِمۡ وَأَنفُسِهِمۡۚ وَأُوْلَـٰٓئِكَ لَهُمُ ٱلۡخَيۡرَٰتُۖ وَأُوْلَـٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ ﴿88﴾

Transliteration: Lakini alrrasoolu waallatheena amanoo maAAahu jahadoo biamwalihim waanfusihim waolaika lahumu alkhayratu waolaika humu almuflihoona

Translation: 88. ግን መልዕክተኛውና ከእርሱ ጋር ያመኑት ሰዎች በገንዘቦቻቸዉም በነፍሶቻቸዉም ታገሉ:: እነዚያም መልካሞች ሁሉ ለእነርሱ ብቻ የተዘጋጁ ናቸው:: እነዚያም እነርሱ ምኞታቸውን ያገኙ ናቸው::

9:89

أَعَدَّ ٱللَّهُ لَهُمۡ جَنَّـٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَاۚ ذَٰلِكَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ ﴿89﴾

Transliteration: aAAadda Allahu lahum jannatin tajree min tahtiha alanharu khalideena feeha thalika alfawzu alAAatheemu

Translation: 89. አላህ ለእነርሱ በሥራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶችን በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ አዘጋጅቶላቸዋል:: ይህ ታላቅ ማግኜት (እድል) ነው::

9:90

وَجَآءَ ٱلۡمُعَذِّرُونَ مِنَ ٱلۡأَعۡرَابِ لِيُؤۡذَنَ لَهُمۡ وَقَعَدَ ٱلَّذِينَ كَذَبُواْ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥۚ سَيُصِيبُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِنۡهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ ﴿90﴾

Transliteration: Wajaa almuAAaththiroona mina alaAArabi liyuthana lahum waqaAAada allatheena kathaboo Allaha warasoolahu sayuseebu allatheena kafaroo minhum AAathabun aleemun

Translation: 90. ከአረብ ዘላኖች መካከል ይቅርታ ፈላጊዎቹ እንዲፈቀድላቸው መጡ:: እነዚያ አላህንና መልዕክተኛውን ያስተባበሉት ግን ተቀመጡ:: እነዚያን በአላህ የካዱት ሰዎች አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ይነካቸዋል (ያገኛቸዋል)::

9:91

لَّيۡسَ عَلَى ٱلضُّعَفَآءِ وَلَا عَلَى ٱلۡمَرۡضَىٰ وَلَا عَلَى ٱلَّذِينَ لَا يَجِدُونَ مَا يُنفِقُونَ حَرَجٌ إِذَا نَصَحُواْ لِلَّهِ وَرَسُولِهِۦۚ مَا عَلَى ٱلۡمُحۡسِنِينَ مِن سَبِيلٖۚ وَٱللَّهُ غَفُورٞ رَّحِيمٞ ﴿91﴾

Transliteration: Laysa AAala aldduAAafai wala AAala almarda wala AAala allatheena la yajidoona ma yunfiqoona harajun itha nasahoo lillahi warasoolihi ma AAala almuhsineena min sabeelin waAllahu ghafoorun raheemun

Translation: 91. በደካሞች ላይ፤ በበሽተኞች ላይ፤ በእነዚያም ለስንቅና ለትጥቅ የሚያወጡት ገንዘብ በማያገኙት ላይ ለአላህና ለመልዕክተኛው ፍጹም ታዛዦች ከሆኑ ወደ ዘመቻ ባይወጡም ኃጢአት የለባቸዉም:: በበጎ አድራጊዎች ላይ ምንም የመወቀሻ መንገድ የለባቸዉም:: አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና::

9:92

وَلَا عَلَى ٱلَّذِينَ إِذَا مَآ أَتَوۡكَ لِتَحۡمِلَهُمۡ قُلۡتَ لَآ أَجِدُ مَآ أَحۡمِلُكُمۡ عَلَيۡهِ تَوَلَّواْ وَّأَعۡيُنُهُمۡ تَفِيضُ مِنَ ٱلدَّمۡعِ حَزَنًا أَلَّا يَجِدُواْ مَا يُنفِقُونَ ﴿92﴾

Transliteration: Wala AAala allatheena itha ma atawka litahmilahum qulta la ajidu ma ahmilukum AAalayhi tawallaw waaAAyunuhum tafeedu mina alddamAAi hazanan alla yajidoo ma yunfiqoona

Translation: 92. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በነዚያም መጓጓዣያ እንድትሰጣቸው ፈልገው ወደ አንተ በመጡ ጊዜ «እናንተን የምጭንበት (አጋሰስ) አላገኝም።» ያልካቸው ስትሆን የሚያወጡት ገንዘብ ባለማግኘታቸው ለማዘናቸው ዓይኖቻቸው እንባን እያፈሰሱ በዞሩት ላይ ምንም ወቀሳ የለባቸዉም::

9:93

إِنَّمَا ٱلسَّبِيلُ عَلَى ٱلَّذِينَ يَسۡتَـٔۡذِنُونَكَ وَهُمۡ أَغۡنِيَآءُۚ رَضُواْ بِأَن يَكُونُواْ مَعَ ٱلۡخَوَالِفِ وَطَبَعَ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ فَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ ﴿93﴾

Transliteration: Innama alssabeelu AAala allatheena yastathinoonaka wahum aghniyao radoo bian yakoonoo maAAa alkhawalifi watabaAAa Allahu AAala quloobihim fahum la yaAAlamoona

Translation: 93. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሚወቀሱት እነዚያ ባለጸጋዎች ሆነው ሳሉ ለመቅረት ፈቃድ በሚጠይቁህ ሰዎች ላይ ብቻ ናቸው:: ከቀሪዎቹ ጋር መሆናቸውን ወደዱ:: አላህ በልቦቻቸው ላይ አተመባቸው:: ስለዚህ እነርሱ አያውቁም::

9:94

يَعۡتَذِرُونَ إِلَيۡكُمۡ إِذَا رَجَعۡتُمۡ إِلَيۡهِمۡۚ قُل لَّا تَعۡتَذِرُواْ لَن نُّؤۡمِنَ لَكُمۡ قَدۡ نَبَّأَنَا ٱللَّهُ مِنۡ أَخۡبَارِكُمۡۚ وَسَيَرَى ٱللَّهُ عَمَلَكُمۡ وَرَسُولُهُۥ ثُمَّ تُرَدُّونَ إِلَىٰ عَٰلِمِ ٱلۡغَيۡبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ ﴿94﴾

Transliteration: YaAAtathiroona ilaykum itha rajaAAtum ilayhim qul la taAAtathiroo lan numina lakum qad nabbaana Allahu min akhbarikum wasayara Allahu AAamalakum warasooluhu thumma turaddoona ila AAalimi alghaybi waalshshahadati fayunabbiokum bima kuntum taAAmaloona

Translation: 94. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነርሱ በተመለሳችሁ ጊዜ ምክንያቶቻቸውን ያቀርቡላችኋል:: «አታመካኙ እናንተን ፈጽሞ አናምንም:: አላህ ከወሬዎቻችሁ አስቀድሞ ነግሮናልና:: አላህና መልዕክተኛው ሥራችሁን ያያሉ:: ከዚያ ሩቅንና ቅርብን ሁሉ አዋቂ ወደ ሆነው አላህ ትመለሳላችሁ:: ወዲያዉም ትሠሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል።» በላቸው::

9:95

سَيَحۡلِفُونَ بِٱللَّهِ لَكُمۡ إِذَا ٱنقَلَبۡتُمۡ إِلَيۡهِمۡ لِتُعۡرِضُواْ عَنۡهُمۡۖ فَأَعۡرِضُواْ عَنۡهُمۡۖ إِنَّهُمۡ رِجۡسٞۖ وَمَأۡوَىٰهُمۡ جَهَنَّمُ جَزَآءَۢ بِمَا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ ﴿95﴾

Transliteration: Sayahlifoona biAllahi lakum itha inqalabtum ilayhim lituAAridoo AAanhum faaAAridoo AAanhum innahum rijsun wamawahum jahannamu jazaan bima kanoo yaksiboona

Translation: 95. (አማኞች ሆይ!) ከዘመቻ ወደ እነርሱ በተመለሳችሁ ጊዜ ጥፋታቸውን ይቅር እንድትሉሏቸው ለእናንተ በአላህ ይምላሉ:: እነርሱን ተዏቸው:: እነርሱ እርኩሶች ናቸውና:: ይሠሩትም በነበረው ኃጢአት መኖሪያቸው ገሀነም ነው::

9:96

يَحۡلِفُونَ لَكُمۡ لِتَرۡضَوۡاْ عَنۡهُمۡۖ فَإِن تَرۡضَوۡاْ عَنۡهُمۡ فَإِنَّ ٱللَّهَ لَا يَرۡضَىٰ عَنِ ٱلۡقَوۡمِ ٱلۡفَٰسِقِينَ ﴿96﴾

Transliteration: Yahlifoona lakum litardaw AAanhum fain tardaw AAanhum fainna Allaha la yarda AAani alqawmi alfasiqeena

Translation: 96. እነርሱ ትወዱላቸው ዘንድ ለእናንተ ይምሉላችኋል:: እናንተ ብትወዱላቸውም አላህ ከአመጸኛ ህዝቦች አይወድም::

9:97

ٱلۡأَعۡرَابُ أَشَدُّ كُفۡرٗا وَنِفَاقٗا وَأَجۡدَرُ أَلَّا يَعۡلَمُواْ حُدُودَ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ عَلَىٰ رَسُولِهِۦۗ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٞ ﴿97﴾

Transliteration: AlaAArabu ashaddu kufran wanifaqan waajdaru alla yaAAlamoo hudooda ma anzala Allahu AAala rasoolihi waAllahu AAaleemun hakeemun

Translation: 97. ዘላን አረቦች በክሕደትና በንፍቅና በጣም የበረቱ፤ አላህ በመልዕክተኛው ላይ ያወረደውን ህግጋት ባለማወቅም የተገቡ ናቸው:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::

9:98

وَمِنَ ٱلۡأَعۡرَابِ مَن يَتَّخِذُ مَا يُنفِقُ مَغۡرَمٗا وَيَتَرَبَّصُ بِكُمُ ٱلدَّوَآئِرَۚ عَلَيۡهِمۡ دَآئِرَةُ ٱلسَّوۡءِۗ وَٱللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٞ ﴿98﴾

Transliteration: Wamina alaAArabi man yattakhithu ma yunfiqu maghraman wayatarabbasu bikumu alddawaira AAalayhim dairatu alssawi waAllahu sameeAAun AAaleemun

Translation: 98. ከዘለኖች መካከል በአላህ መንገድ የሚያወጣውን ገንዘብ እዳ አድርጎ የሚይዝና በእናንተ ላይ የጊዜን መገለባበጥ የሚጠባበቅ ሰው አለ:: በእነርሱ ላይ ጥፋቱ ይዙርባቸው:: አላህ ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነው::

9:99

وَمِنَ ٱلۡأَعۡرَابِ مَن يُؤۡمِنُ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِ وَيَتَّخِذُ مَا يُنفِقُ قُرُبَٰتٍ عِندَ ٱللَّهِ وَصَلَوَٰتِ ٱلرَّسُولِۚ أَلَآ إِنَّهَا قُرۡبَةٞ لَّهُمۡۚ سَيُدۡخِلُهُمُ ٱللَّهُ فِي رَحۡمَتِهِۦٓۚ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٞ ﴿99﴾

Transliteration: Wamina alaAArabi man yuminu biAllahi waalyawmi alakhiri wayattakhithu ma yunfiqu qurubatin AAinda Allahi wasalawati alrrasooli ala innaha qurbatun lahum sayudkhiluhumu Allahu fee rahmatihi inna Allaha ghafoorun raheemun

Translation: 99. ከአረብ ዘላኖች መካከል በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሚሰጣቸውንም ምጽዋቶች አላህ ዘንድ መቃረቢያዎችና ወደ መልዕክተኛው ጸሎቶች መዳረሻ አድርጎ የሚይዝ ክፍል አለ:: አስተዉሉ! እርሷ ለእነርሱ በእርግጥ አቃራቢ ናት:: አላህ በችሮታው ውስጥ በገነቱ በእርግጥ ያስገባቸዋል:: አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና ::

9:100

وَٱلسَّـٰبِقُونَ ٱلۡأَوَّلُونَ مِنَ ٱلۡمُهَٰجِرِينَ وَٱلۡأَنصَارِ وَٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوهُم بِإِحۡسَٰنٖ رَّضِيَ ٱللَّهُ عَنۡهُمۡ وَرَضُواْ عَنۡهُ وَأَعَدَّ لَهُمۡ جَنَّـٰتٖ تَجۡرِي تَحۡتَهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدٗاۚ ذَٰلِكَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ ﴿100﴾

Transliteration: Waalssabiqoona alawwaloona mina almuhajireena waalansari waallatheena ittabaAAoohum biihsanin radiya Allahu AAanhum waradoo AAanhu waaAAadda lahum jannatin tajree tahtaha alanharu khalideena feeha abadan thalika alfawzu alAAatheemu

Translation: 100. ከስደተኞቹም ሆነ ከረዳቶቹ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎችና እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው ሰዎች አላህ የእነርሱን ተግባር ወዶላቸዋል:: እነርሱም ወደውለታል:: በሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸዉም ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲሆኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል:: ይህ ታላቅ እድለኛነት ነው::

9:101

وَمِمَّنۡ حَوۡلَكُم مِّنَ ٱلۡأَعۡرَابِ مُنَٰفِقُونَۖ وَمِنۡ أَهۡلِ ٱلۡمَدِينَةِ مَرَدُواْ عَلَى ٱلنِّفَاقِ لَا تَعۡلَمُهُمۡۖ نَحۡنُ نَعۡلَمُهُمۡۚ سَنُعَذِّبُهُم مَّرَّتَيۡنِ ثُمَّ يُرَدُّونَ إِلَىٰ عَذَابٍ عَظِيمٖ ﴿101﴾

Transliteration: Wamimman hawlakum mina alaAArabi munafiqoona wamin ahli almadeenati maradoo AAala alnnifaqi la taAAlamuhum nahnu naAAlamuhum sanuAAaththibuhum marratayni thumma yuraddoona ila AAathabin AAatheemin

Translation: 101. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዙሪያችሁም ካሉት የዐረብ ዘላኖች አስመሳዮች አሉ:: ከመዲና ሰዎችም በንፍቅና ላይ በማመጽ የዘወተሩ አሉ:: አታውቃቸዉም:: እኛ እናውቃቸዋለን:: ሁለት ጊዜ እንቀጣቸዋለን:: ከዚያ ወደ ታላቅ ቅጣት ይመለሳሉ::

9:102

وَءَاخَرُونَ ٱعۡتَرَفُواْ بِذُنُوبِهِمۡ خَلَطُواْ عَمَلٗا صَٰلِحٗا وَءَاخَرَ سَيِّئًا عَسَى ٱللَّهُ أَن يَتُوبَ عَلَيۡهِمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٌ ﴿102﴾

Transliteration: Waakharoona iAAtarafoo bithunoobihim khalatoo AAamalan salihan waakhara sayyian AAasa Allahu an yatooba AAalayhim inna Allaha ghafoorun raheemun

Translation: 102. ሌሎችም ኃጢአቶቻቸውን የተናዘዙ መልካም ሥራንና ሌላን መጥፎ ሥራ የቀላቀሉ አሉ:: አላህ ጸጸታቸውን ሊቀበል ይከጀላል:: አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና::

9:103

خُذۡ مِنۡ أَمۡوَٰلِهِمۡ صَدَقَةٗ تُطَهِّرُهُمۡ وَتُزَكِّيهِم بِهَا وَصَلِّ عَلَيۡهِمۡۖ إِنَّ صَلَوٰتَكَ سَكَنٞ لَّهُمۡۗ وَٱللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ ﴿103﴾

Transliteration: Khuth min amwalihim sadaqatan tutahhiruhum watuzakkeehim biha wasalli AAalayhim inna salataka sakanun lahum waAllahu sameeAAun AAaleemun

Translation: 103. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከገንዘቦቻቸው የምታጠራቸውና የምታፋፋቸውን ምጽዋት ያዝ:: ለነሱም ዱኣ አድርግላቸው፡፡ ዱኣእህ ለእነሱ እርጋታ ነውና አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡

9:104

أَلَمۡ يَعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ هُوَ يَقۡبَلُ ٱلتَّوۡبَةَ عَنۡ عِبَادِهِۦ وَيَأۡخُذُ ٱلصَّدَقَٰتِ وَأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلتَّوَّابُ ٱلرَّحِيمُ ﴿104﴾

Transliteration: Alam yaAAlamoo anna Allaha huwa yaqbalu alttawbata AAan AAibadihi wayakhuthu alssadaqati waanna Allaha huwa alttawwabu alrraheemu

Translation: 104. አላህም እርሱ ከባሮቹ ንሰሃን የሚቀበልና ምጽዋቶችንም የሚወስድ፤ አላህ ብቸኛ ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ መሆኑን አያውቁምን?

9:105

وَقُلِ ٱعۡمَلُواْ فَسَيَرَى ٱللَّهُ عَمَلَكُمۡ وَرَسُولُهُۥ وَٱلۡمُؤۡمِنُونَۖ وَسَتُرَدُّونَ إِلَىٰ عَٰلِمِ ٱلۡغَيۡبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ ﴿105﴾

Transliteration: Waquli iAAmaloo fasayara Allahu AAamalakum warasooluhu waalmuminoona wasaturaddoona ila AAalimi alghaybi waalshshahadati fayunabbiokum bima kuntum taAAmaloona

Translation: 105. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሥሩ:: አላህ መልዕክተኛውና አማኞችም ሥራችሁን በእርግጥ ያያሉና:: ሩቁንና ቅርቡን ሁሉ አዋቂ ወደ ሆነው አላህ በእርግጥ ትመለሳላችሁ:: ትሰሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል።» በላቸው::

9:106

وَءَاخَرُونَ مُرۡجَوۡنَ لِأَمۡرِ ٱللَّهِ إِمَّا يُعَذِّبُهُمۡ وَإِمَّا يَتُوبُ عَلَيۡهِمۡۗ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٞ ﴿106﴾

Transliteration: Waakharoona murjawna liamri Allahi imma yuAAaththibuhum waimma yatoobu AAalayhim waAllahu AAaleemun hakeemun

Translation: 106. ሌሎችም የአላህን ውሳኔ ትዕዛዝ እንዲጠብቁ የተቆዩ ህዝቦች አሉ:: ይቀጣቸዋል ወይም ጸጸታቸውን ይቀበላቸዋል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነዉና፡፡

9:107

وَٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ مَسۡجِدٗا ضِرَارٗا وَكُفۡرٗا وَتَفۡرِيقَۢا بَيۡنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَإِرۡصَادٗا لِّمَنۡ حَارَبَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ مِن قَبۡلُۚ وَلَيَحۡلِفُنَّ إِنۡ أَرَدۡنَآ إِلَّا ٱلۡحُسۡنَىٰۖ وَٱللَّهُ يَشۡهَدُ إِنَّهُمۡ لَكَٰذِبُونَ ﴿107﴾

Transliteration: Waallatheena ittakhathoo masjidan diraran wakufran watafreeqan bayna almumineena wairsadan liman haraba Allaha warasoolahu min qablu walayahlifunna in aradna illa alhusna waAllahu yashhadu innahum lakathiboona

Translation: 107. እነዚያም አማኞችን ለመጉዳት ክህደትንም ለማበረታታት በአማኞችም መካከል ለመለያየት ከአሁን በፊት አላህንና መልዕክተኛውን የተዋጋውን ሰው ለመጠባበቅ መስጊዱን የሠሩት ሰዎች ከእነርሱ ናቸው:: «መልካምን እንጂ ሌላ አልሻንም።» ሲሉ በእርግጥ ይምላሉ:: አላህ ደግሞ ውሸታሞች መሆናቸውን በእርግጥ ይመሰክራል::

9:108

لَا تَقُمۡ فِيهِ أَبَدٗاۚ لَّمَسۡجِدٌ أُسِّسَ عَلَى ٱلتَّقۡوَىٰ مِنۡ أَوَّلِ يَوۡمٍ أَحَقُّ أَن تَقُومَ فِيهِۚ فِيهِ رِجَالٞ يُحِبُّونَ أَن يَتَطَهَّرُواْۚ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلۡمُطَّهِّرِينَ ﴿108﴾

Transliteration: La taqum feehi abadan lamasjidun ossisa AAala alttaqwa min awwali yawmin ahaqqu an taqooma feehi feehi rijalun yuhibboona an yatatahharoo waAllahu yuhibbu almuttahhireena

Translation: 108. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእርሱ ውስጥ በፍጹም አትስገድ:: ይልቁንም ከመጀመሪያ ቀን ይዞ በአላህ ፍራቻ ላይ የተመሠረተው (የቁባ ) መስጊድ በውስጡ ልትሰግዱበት የተገባው ነው:: በውስጡ መጥራራትን የሚወዱ ወንዶች አሉ:: አላህ ተጥራሪዎችን ይወዳል::

9:109

أَفَمَنۡ أَسَّسَ بُنۡيَٰنَهُۥ عَلَىٰ تَقۡوَىٰ مِنَ ٱللَّهِ وَرِضۡوَٰنٍ خَيۡرٌ أَم مَّنۡ أَسَّسَ بُنۡيَٰنَهُۥ عَلَىٰ شَفَا جُرُفٍ هَارٖ فَٱنۡهَارَ بِهِۦ فِي نَارِ جَهَنَّمَۗ وَٱللَّهُ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلظَّـٰلِمِينَ ﴿109﴾

Transliteration: Afaman assasa bunyanahu AAala taqwa mina Allahi waridwanin khayrun am man assasa bunyanahu AAala shafa jurufin harin fainhara bihi fee nari jahannama waAllahu la yahdee alqawma alththalimeena

Translation: 109. አላህን በመፍራትና ውዴታውን በመፈለግ ላይ ግንቡን የመሠረተ ሰው ወይስ ጎርፍ በሸረሸረው ለመናድ በተቃረበ ገደል አፋፍ ላይ ግንቡን የመሠረተውና እርሱንም ይዞት ወደ ገሀነም እሳት ውስጥ የወደቀው ይበልጣልን? አላህ በደለኛ ሕዝቦችን አይመራም::

9:110

لَا يَزَالُ بُنۡيَٰنُهُمُ ٱلَّذِي بَنَوۡاْ رِيبَةٗ فِي قُلُوبِهِمۡ إِلَّآ أَن تَقَطَّعَ قُلُوبُهُمۡۗ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ ﴿110﴾

Transliteration: La yazalu bunyanuhumu allathee banaw reebatan fee quloobihim illa an taqattaAAa quloobuhum waAllahu AAaleemun hakeemun

Translation: 110. ያ የካቡት ግንባቸው ልቦቻቸው በሞት ካልተቆራረጡ በስተቀር በልቦቻቸው ውስጥ የመጠራጠር ምክንያት ከመሆን አይወገድም:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::

9:111

إِنَّ ٱللَّهَ ٱشۡتَرَىٰ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ أَنفُسَهُمۡ وَأَمۡوَٰلَهُم بِأَنَّ لَهُمُ ٱلۡجَنَّةَۚ يُقَٰتِلُونَ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ فَيَقۡتُلُونَ وَيُقۡتَلُونَۖ وَعۡدًا عَلَيۡهِ حَقّٗا فِي ٱلتَّوۡرَىٰةِ وَٱلۡإِنجِيلِ وَٱلۡقُرۡءَانِۚ وَمَنۡ أَوۡفَىٰ بِعَهۡدِهِۦ مِنَ ٱللَّهِۚ فَٱسۡتَبۡشِرُواْ بِبَيۡعِكُمُ ٱلَّذِي بَايَعۡتُم بِهِۦۚ وَذَٰلِكَ هُوَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ ﴿111﴾

Transliteration: Inna Allaha ishtara mina almumineena anfusahum waamwalahum bianna lahumu aljannata yuqatiloona fee sabeeli Allahi fayaqtuloona wayuqtaloona waAAdan AAalayhi haqqan fee alttawrati waalinjeeli waalqurani waman awfa biAAahdihi mina Allahi faistabshiroo bibayAAikumu allathee bayaAAtum bihi wathalika huwa alfawzu alAAatheemu

Translation: 111. አላህ ከትክክለኛ አማኞች ነፍሶቻቸውንና ገንዘቦቻቸውን ገነትን ለእነርሱ በማድረግ ገዛቸው:: በአላህ መንገድ ላይ ይጋደላሉ:: ይገድላሉም:: ይገደላሉም:: በተውራት፤ በኢንጂልና በቁርኣንም የተነገረውን ተስፋ በእርሱ ላይ አረጋገጠ:: ከአላህ የበለጠ በቃል ኪዳኑ የሚሞላ ማን ነው? (ትክክለኛ አማኞች ሆይ!) በዚያም በእርሱ በተሻሻጣችሁበት ሽያጫችሁ ተደሰቱ:: ይህ ታላቅ ዕድል ነውና::

9:112

ٱلتَّـٰٓئِبُونَ ٱلۡعَٰبِدُونَ ٱلۡحَٰمِدُونَ ٱلسَّـٰٓئِحُونَ ٱلرَّـٰكِعُونَ ٱلسَّـٰجِدُونَ ٱلۡأٓمِرُونَ بِٱلۡمَعۡرُوفِ وَٱلنَّاهُونَ عَنِ ٱلۡمُنكَرِ وَٱلۡحَٰفِظُونَ لِحُدُودِ ٱللَّهِۗ وَبَشِّرِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ﴿112﴾

Transliteration: Alttaiboona alAAabidoona alhamidoona alssaihoona alrrakiAAoona alssajidoona alamiroona bialmaAAroofi waalnnahoona AAani almunkari waalhafithoona lihudoodi Allahi wabashshiri almumineena

Translation: 112. እነርሱ ተጸፃቾች፤ ተገዢዎች፤ አመስጋኞች፤ ፆመኞች፤ (በሶላት) አጎንባሾች፤ በግንባር ተደፊዎች፤ በበጎ ሥራ አዛዦች፤ ከክፉ ከልካዮች እና የአላህንም ሕግጋት ጠባቂዎች ናቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ትክክለኛ አማኞችንም አብስር::

9:113

مَا كَانَ لِلنَّبِيِّ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَن يَسۡتَغۡفِرُواْ لِلۡمُشۡرِكِينَ وَلَوۡ كَانُوٓاْ أُوْلِي قُرۡبَىٰ مِنۢ بَعۡدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُمۡ أَنَّهُمۡ أَصۡحَٰبُ ٱلۡجَحِيمِ ﴿113﴾

Transliteration: Ma kana lilnnabiyyi waallatheena amanoo an yastaghfiroo lilmushrikeena walaw kanoo olee qurba min baAAdi ma tabayyana lahum annahum ashabu aljaheemi

Translation: 113. መልዕክተኛዉም ሆነ እነዚያ በእሱ ያመኑት ሰዎች ለአጋሪዎቹ የዝምድና ባለቤቶች ቢሆኑም እንኳ ከሓዲያን እነርሱ የእሳት ጓዶች መሆናቸው ከተገለጸላቸው በኋላ የአላህን ምሕረት ሊለምኑላቸው የሚገባ አልነበረም::

9:114

وَمَا كَانَ ٱسۡتِغۡفَارُ إِبۡرَٰهِيمَ لِأَبِيهِ إِلَّا عَن مَّوۡعِدَةٖ وَعَدَهَآ إِيَّاهُ فَلَمَّا تَبَيَّنَ لَهُۥٓ أَنَّهُۥ عَدُوّٞ لِّلَّهِ تَبَرَّأَ مِنۡهُۚ إِنَّ إِبۡرَٰهِيمَ لَأَوَّـٰهٌ حَلِيمٞ ﴿114﴾

Transliteration: Wama kana istighfaru ibraheema liabeehi illa AAan mawAAidatin waAAadaha iyyahu falamma tabayyana lahu annahu AAaduwwun lillahi tabarraa minhu inna ibraheema laawwahun haleemun

Translation: 114. ኢብራሂምም ለአባቱ ምህረትን መለመኑ ቀድሞ ገብቶለት የነበረውን ቃል ለመሙላት እንጂ ለሌላ አልነበረም:: እናም የአላህ ጠላት መሆኑ በተገለጸለት ጊዜ ከእርሱ ራቀ:: (ተወው):: ኢብራሂም በእርግጥ አልቃሻ እና ታጋሽ ነበርና።

9:115

وَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيُضِلَّ قَوۡمَۢا بَعۡدَ إِذۡ هَدَىٰهُمۡ حَتَّىٰ يُبَيِّنَ لَهُم مَّا يَتَّقُونَۚ إِنَّ ٱللَّهَ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٌ ﴿115﴾

Transliteration: Wama kana Allahu liyudilla qawman baAAda ith hadahum hatta yubayyina lahum ma yattaqoona inna Allaha bikulli shayin AAaleemun

Translation: 115. አላህ ህዝቦችን ካቀናቸው በኋላ የሚጠነቀቁትን ነገር እሥከሚገልጽላቸው ድረስ ሳያውቁ በሰሩት ጥፋት ጥፋተኛ የሚያደርግ ጌታ አይደለም:: አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነውና::

9:116

إِنَّ ٱللَّهَ لَهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ يُحۡيِۦ وَيُمِيتُۚ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ مِن وَلِيّٖ وَلَا نَصِيرٖ ﴿116﴾

Transliteration: Inna Allaha lahu mulku alssamawati waalardi yuhyee wayumeetu wama lakum min dooni Allahi min waliyyin wala naseerin

Translation: 116. አላህ የሰማያትና የምድር ንግስና የእርሱ ብቻ ነው:: ህያው ያደርጋል:: ይገድላልም:: ለእናንተም ከእርሱ በስተቀር ጠባቂም ሆነ ወዳጅ የላችሁም::

9:117

لَّقَد تَّابَ ٱللَّهُ عَلَى ٱلنَّبِيِّ وَٱلۡمُهَٰجِرِينَ وَٱلۡأَنصَارِ ٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوهُ فِي سَاعَةِ ٱلۡعُسۡرَةِ مِنۢ بَعۡدِ مَا كَادَ يَزِيغُ قُلُوبُ فَرِيقٖ مِّنۡهُمۡ ثُمَّ تَابَ عَلَيۡهِمۡۚ إِنَّهُۥ بِهِمۡ رَءُوفٞ رَّحِيمٞ ﴿117﴾

Transliteration: Laqad taba Allahu AAala alnnabiyyi waalmuhajireena waalansari allatheena ittabaAAoohu fee saAAati alAAusrati min baAAdi ma kada yazeeghu quloobu fareeqin minhum thumma taba AAalayhim innahu bihim raoofun raheemun

Translation: 117. በመልዕክተኛው በስደተኞችና በረዳቶች በእነዚህም በችግሩ ጊዜ (በተቡክ ዘመቻ) ከእነርሱ የከፊሎቹ ልቦች ለመቅረት ሊዘነበሉ ከተቃረቡ በኋላ በተከተሉት ላይ አላህ በእርግጥ ጸጸታቸውን ተቀበለ:: ከዚያ ከእነርሱ ንሰሃ መግባታቸውን ተቀበለ:: እርሱ(አላህ ) ለእነርሱ ሩህሩህና አዛኝ ነውና::

9:118

وَعَلَى ٱلثَّلَٰثَةِ ٱلَّذِينَ خُلِّفُواْ حَتَّىٰٓ إِذَا ضَاقَتۡ عَلَيۡهِمُ ٱلۡأَرۡضُ بِمَا رَحُبَتۡ وَضَاقَتۡ عَلَيۡهِمۡ أَنفُسُهُمۡ وَظَنُّوٓاْ أَن لَّا مَلۡجَأَ مِنَ ٱللَّهِ إِلَّآ إِلَيۡهِ ثُمَّ تَابَ عَلَيۡهِمۡ لِيَتُوبُوٓاْۚ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلتَّوَّابُ ٱلرَّحِيمُ ﴿118﴾

Transliteration: WaAAala alththalathati allatheena khullifoo hatta itha daqat AAalayhimu alardu bima rahubat wadaqat AAalayhim anfusuhum wathannoo an la maljaa mina Allahi illa ilayhi thumma taba AAalayhim liyatooboo inna Allaha huwa alttawwabu alrraheemu

Translation: 118. በእነዚያም ወደ ኋላ በቀሩት በሶስቱ ሰዎች ላይ ምድር ከስፋቷ ጋር በእነርሱ ላይ እስከምትጠብባቸው፤ ነፍሶቻቸዉም በእነርሱ ላይ እስከምትጠብባቸው፤ ከአላህም ወደ እርሱ ብቻ እንጂ ሌላ መጠጊያ አለመኖሩን እስከሚያረጋግጡ ድረስ በተቆዩት ላይ አላህ ጸጸትን ተቀበለ:: ከዚያም ይጸጸቱ ዘንድ ወደ ጸጸት መራቸው:: አላህ ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ ነውና::

9:119

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَكُونُواْ مَعَ ٱلصَّـٰدِقِينَ ﴿119﴾

Transliteration: Ya ayyuha allatheena amanoo ittaqoo Allaha wakoonoo maAAa alssadiqeena

Translation: 119. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን በትክክል ፍሩ:: ከእውነተኞቹም ጋር ሁኑ::

9:120

مَا كَانَ لِأَهۡلِ ٱلۡمَدِينَةِ وَمَنۡ حَوۡلَهُم مِّنَ ٱلۡأَعۡرَابِ أَن يَتَخَلَّفُواْ عَن رَّسُولِ ٱللَّهِ وَلَا يَرۡغَبُواْ بِأَنفُسِهِمۡ عَن نَّفۡسِهِۦۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ لَا يُصِيبُهُمۡ ظَمَأٞ وَلَا نَصَبٞ وَلَا مَخۡمَصَةٞ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَلَا يَطَـُٔونَ مَوۡطِئٗا يَغِيظُ ٱلۡكُفَّارَ وَلَا يَنَالُونَ مِنۡ عَدُوّٖ نَّيۡلًا إِلَّا كُتِبَ لَهُم بِهِۦ عَمَلٞ صَٰلِحٌۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُضِيعُ أَجۡرَ ٱلۡمُحۡسِنِينَ ﴿120﴾

Transliteration: Ma kana liahli almadeenati waman hawlahum mina alaAArabi an yatakhallafoo AAan rasooli Allahi wala yarghaboo bianfusihim AAan nafsihi thalika biannahum la yuseebuhum thamaon wala nasabun wala makhmasatun fee sabeeli Allahi wala yataoona mawtian yagheethu alkuffara wala yanaloona min AAaduwwin naylan illa kutiba lahum bihi AAamalun salihun inna Allaha la yudeeAAu ajra almuhsineena

Translation: 120. የመዲና ሰዎችና በዙሪያቸው ያሉት የዘላን ዓረብ ህዝቦች ከአላህ መልዕክተኛ ጥሪ ወደ ኋላ ሊቀሩና ነፍሶቻቸውንም ከነፍሱ አብልጠው ሊወዱ አይገባቸዉም ነበር:: ይህም የሆነው ለእነርሱ መልካም ሥራ የሚጻፍላቸው ቢሆን እንጂ በአላህ መንገድ ላይ ጥምም ድካምም ርሀብም የማይነካቸው ከሓዲያንንም የሚያስቆጭን ስፍራ የማይረግጡ ከጠላትም የሚጎዳን ነገር (መግደል) የማያገኙ በመሆናቸው ነው:: አላህ የመልካም ሠሪዎችን ምንዳ አያጠፋምና::

9:121

وَلَا يُنفِقُونَ نَفَقَةٗ صَغِيرَةٗ وَلَا كَبِيرَةٗ وَلَا يَقۡطَعُونَ وَادِيًا إِلَّا كُتِبَ لَهُمۡ لِيَجۡزِيَهُمُ ٱللَّهُ أَحۡسَنَ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ ﴿121﴾

Transliteration: Wala yunfiqoona nafaqatan sagheeratan wala kabeeratan wala yaqtaAAoona wadiyan illa kutiba lahum liyajziyahumu Allahu ahsana ma kanoo yaAAmaloona

Translation: 121. ትንሽንም ትልቅንም ልግስና አይለግሱም ወንዝንም አያቋርጡም አላህ ይሠሩት ከነበረው የበለጠን ምንዳ ይመነዳቸው ዘንድ ለእነርሱ የሚጽፍላቸው ቢሆን እንጂ::

9:122

وَمَا كَانَ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ لِيَنفِرُواْ كَآفَّةٗۚ فَلَوۡلَا نَفَرَ مِن كُلِّ فِرۡقَةٖ مِّنۡهُمۡ طَآئِفَةٞ لِّيَتَفَقَّهُواْ فِي ٱلدِّينِ وَلِيُنذِرُواْ قَوۡمَهُمۡ إِذَا رَجَعُوٓاْ إِلَيۡهِمۡ لَعَلَّهُمۡ يَحۡذَرُونَ ﴿122﴾

Transliteration: Wama kana almuminoona liyanfiroo kaffatan falawla nafara min kulli firqatin minhum taifatun liyatafaqqahoo fee alddeeni waliyunthiroo qawmahum itha rajaAAoo ilayhim laAAallahum yahtharoona

Translation: 122. ምእምናንም (ከነቢዩ ጋር ካልኾነ) በሙሉ ሊወጡ አይገባም፡፡ ከእነሱ ውስጥ ከየክፍሉ አንዲት ጭፍራ ለምን አትወጣም፡፡ (ሌሎቹ) ሃይማኖትን እንዲማሩና ወገኖቻቸው ወደነርሱ በተመለሱ ጊዜ እንዲጠነቀቁ ይገስጹዋቸው ዘንድ (ለምን አይቀሩም)፡፡

9:123

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ قَٰتِلُواْ ٱلَّذِينَ يَلُونَكُم مِّنَ ٱلۡكُفَّارِ وَلۡيَجِدُواْ فِيكُمۡ غِلۡظَةٗۚ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلۡمُتَّقِينَ ﴿123﴾

Transliteration: Ya ayyuha allatheena amanoo qatiloo allatheena yaloonakum mina alkuffari walyajidoo feekum ghilthatan waiAAlamoo anna Allaha maAAa almuttaqeena

Translation: 123. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያን በአቅራቢያችሁ ያሉትን ከሓዲያን ተዋጉ:: በናንተ ውስጥ ብርታትን ያግኙ:: አላህም ከሚጠነቀቁት ጋር መሆኑን እወቁ::

9:124

وَإِذَا مَآ أُنزِلَتۡ سُورَةٞ فَمِنۡهُم مَّن يَقُولُ أَيُّكُمۡ زَادَتۡهُ هَٰذِهِۦٓ إِيمَٰنٗاۚ فَأَمَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ فَزَادَتۡهُمۡ إِيمَٰنٗا وَهُمۡ يَسۡتَبۡشِرُونَ ﴿124﴾

Transliteration: Waitha ma onzilat sooratun faminhum man yaqoolu ayyukum zadathu hathihi eemanan faamma allatheena amanoo fazadathum eemanan wahum yastabshiroona

Translation: 124. ምዕራፍ በተወረደ ጊዜ ከአስመሳዮች ውስጥ «ማንኛችሁ ነው ይህ ምዕራፍ እምነትን የጨመረለት?» የሚል ሰው አለ:: እነዚያ ያመኑት ሰዎች የሚደሰቱ ሲሆኑ እምነትን ጨመረላቸው::

9:125

وَأَمَّا ٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٞ فَزَادَتۡهُمۡ رِجۡسًا إِلَىٰ رِجۡسِهِمۡ وَمَاتُواْ وَهُمۡ كَٰفِرُونَ ﴿125﴾

Transliteration: Waamma allatheena fee quloobihim maradun fazadathum rijsan ila rijsihim wamatoo wahum kafiroona

Translation: 125. እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው ክፍሎች ግን በርክሰታቸው ላይ እርክሰትን ጨመረላቸው:: እነርሱም ከሓዲያን ሆነው ሞቱ::

9:126

أَوَلَا يَرَوۡنَ أَنَّهُمۡ يُفۡتَنُونَ فِي كُلِّ عَامٖ مَّرَّةً أَوۡ مَرَّتَيۡنِ ثُمَّ لَا يَتُوبُونَ وَلَا هُمۡ يَذَّكَّرُونَ ﴿126﴾

Transliteration: Awala yarawna annahum yuftanoona fee kulli AAamin marratan aw marratayni thumma la yatooboona wala hum yaththakkaroona

Translation: 126. በየዓመቱ አንድ ወይም ሁለት ጊዜ እነርሱ የሚሞከሩ መሆናቸውን አያዩምን? ከዚያ አይጸጸቱምን?እነርሱም አይገሰጹምን?

9:127

وَإِذَا مَآ أُنزِلَتۡ سُورَةٞ نَّظَرَ بَعۡضُهُمۡ إِلَىٰ بَعۡضٍ هَلۡ يَرَىٰكُم مِّنۡ أَحَدٖ ثُمَّ ٱنصَرَفُواْۚ صَرَفَ ٱللَّهُ قُلُوبَهُم بِأَنَّهُمۡ قَوۡمٞ لَّا يَفۡقَهُونَ ﴿127﴾

Transliteration: Waitha ma onzilat sooratun nathara baAAduhum ila baAAdin hal yarakum min ahadin thumma insarafoo sarafa Allahu quloobahum biannahum qawmun la yafqahoona

Translation: 127. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን የሚያወሳ ምዕራፍም በተወረደ ጊዜ «የሚያያችሁ (ሰው) አለን?» እያሉ ከፊሎቻቸው ወደ ከፊሉ ይመለከታሉ:: ከዚያ ተደብቀው ይሄዳሉ:: እነርሱ የማያውቁ ህዝቦች በመሆናቸው አላህ ልቦቻቸውን አዞረ::

9:128

لَقَدۡ جَآءَكُمۡ رَسُولٞ مِّنۡ أَنفُسِكُمۡ عَزِيزٌ عَلَيۡهِ مَا عَنِتُّمۡ حَرِيصٌ عَلَيۡكُم بِٱلۡمُؤۡمِنِينَ رَءُوفٞ رَّحِيمٞ ﴿128﴾

Transliteration: Laqad jaakum rasoolun min anfusikum AAazeezun AAalayhi ma AAanittum hareesun AAalaykum bialmumineena raoofun raheemun

Translation: 128. (ሰዎች ሆይ!) ከጎሳችሁ ውስጥ የሆነ መቸገራችሁ በእርሱ ላይ ከባድ ጉዳይ የሆነበት፤ እናንተ እምነት እንዲኖራችሁ በጣም የሚጓጓና ለትክክለኛ አማኞችም ሩህሩህና አዛኝ የሆነ መልዕክተኛ (ሙሐመድ) መጣላችሁ::

9:129

فَإِن تَوَلَّوۡاْ فَقُلۡ حَسۡبِيَ ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ عَلَيۡهِ تَوَكَّلۡتُۖ وَهُوَ رَبُّ ٱلۡعَرۡشِ ٱلۡعَظِيمِ ﴿129﴾

Transliteration: Fain tawallaw faqul hasbiya Allahu la ilaha illa huwa AAalayhi tawakkaltu wahuwa rabbu alAAarshi alAAatheemi

Translation: 129. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ቢያፈገፍጉ አላህ በቂዬ ነው:: ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: በእርሱ ላይ ብቻ ተመካሁ:: እርሱም የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው።» በላቸው::

Transliteration source: English Transliteration by Tanzil. Used under Tanzil's non-commercial terms; see the source and latest updates at Tanzil. Tanzil translation download