quranm◉

ሱራ An-Nur 24:35 – Ayat an-Nur

۞ٱللَّهُ نُورُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ مَثَلُ نُورِهِۦ كَمِشۡكَوٰةٖ فِيهَا مِصۡبَاحٌۖ ٱلۡمِصۡبَاحُ فِي زُجَاجَةٍۖ ٱلزُّجَاجَةُ كَأَنَّهَا كَوۡكَبٞ دُرِّيّٞ يُوقَدُ مِن شَجَرَةٖ مُّبَٰرَكَةٖ زَيۡتُونَةٖ لَّا شَرۡقِيَّةٖ وَلَا غَرۡبِيَّةٖ يَكَادُ زَيۡتُهَا يُضِيٓءُ وَلَوۡ لَمۡ تَمۡسَسۡهُ نَارٞۚ نُّورٌ عَلَىٰ نُورٖۚ يَهۡدِي ٱللَّهُ لِنُورِهِۦ مَن يَشَآءُۚ وَيَضۡرِبُ ٱللَّهُ ٱلۡأَمۡثَٰلَ لِلنَّاسِۗ وَٱللَّهُ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٞ ﴿٣٥﴾

◉

ትርጉም

35. አላህ የሰማያትና የምድር ብርሃን (አብሪ) ነው፤ የብርሃኑ ምሳሌ በውስጡ መብራት እንዳለባት ዝግ መስኮት፤ መብራቱ በብርጭቆ ውስጥ የሆነ፤ ብርጭቆው ደግሞ ፍጹም ሉላዊ ክብ የምትመስል ምስራቃዊም ምዕራባዊም ካልሆነች፤ ከተባረከች የወይራ ዛፍ ዘይቷ እሳት ባይነካዉም እንኳ ሊያበራ የሚቀርብ ከሆነች ዘይት የሚቃጠል እንደሆነ መብራት ነው:: ይህ በብርሃን ላይ የሆነ ብርሃን ነው:: አላህ ወደ ብርሃኑ የሚሻውን ሰው ይመራል:: አላህም ለሰዎች ምሳሌዎችን ያቀርባል። አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ ነውና።
— Africa Academy
አላህ የሰማያትና የምድር አብሪ ነው፡፡ የብርሃኑ ምሳሌ በውስጧ መብራት እንዳለባት (ዝግ) መስኮት፣ መብራቱ በብርጭቆ ውስጥ የኾነ፣ ብርጭቆይቱ ፍፁም ሉላዊ ኮከብ የምትመሰል፣ ምሥራቃዊው ምዕራባዊም ካልኾነች ከተባረከች የወይራ ዛፍ ዘይቷ እሳት ባይነካውም እንኳ ሊያበራ የሚቀርብ ከኾነች (ዘይት) የሚቃጠል እንደ ሆነ (መብራት) ነው፡፡ (ይህ) በብርሃን ላይ የኾነ ብርሃን ነው፡፡ አላህ ወደ ብርሃኑ የሚሻውን ሰው ይመራል፡፡ አላህም ለሰዎች ምሳሌዎችን ያቀርባል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
— Sadiq and Sani

ርዕሶች · አያት

◉ ሱራ · ∞