فَجَعَلَهُمۡ جُذَٰذًا إِلَّا كَبِيرٗا لَّهُمۡ لَعَلَّهُمۡ إِلَيۡهِ يَرۡجِعُونَ ﴿58﴾فَجَعَلَهُمۡ جُذَٰذًا إِلَّا كَبِيرٗا لَّهُمۡ لَعَلَّهُمۡ إِلَيۡهِ يَرۡجِعُونَ
58. ዘወር ሲሉም ስብርብሮች አደረጋቸው:: ለእነርሱ የሆነ አንድ ትልቅ ጣዖት ብቻ ሲቀር :: ወደ እርሱ ይመለሱ ዘንድ እርሱን ብቻ ተወው።
قَالُواْ مَن فَعَلَ هَٰذَا بِـَٔالِهَتِنَآ إِنَّهُۥ لَمِنَ ٱلظَّـٰلِمِينَ ﴿59﴾قَالُواْ مَن فَعَلَ هَٰذَا بِـَٔالِهَتِنَآ إِنَّهُۥ لَمِنَ ٱلظَّـٰلِمِينَ
59. «በአማልክቶቻችን ይህንን የሰራ ማነው? እርሱ በእርግጥ ከበደለኞች ነው።» አሉ።
قَالُواْ سَمِعۡنَا فَتٗى يَذۡكُرُهُمۡ يُقَالُ لَهُۥٓ إِبۡرَٰهِيمُ ﴿60﴾قَالُواْ سَمِعۡنَا فَتٗى يَذۡكُرُهُمۡ يُقَالُ لَهُۥٓ إِبۡرَٰهِيمُ
60. «ኢብራሂም የሚባል ጎበዝ (ወጣት) በመጥፎ ሲያነሳቸው ሰምተናል።» ተባባሉ።
قَالُواْ فَأۡتُواْ بِهِۦ عَلَىٰٓ أَعۡيُنِ ٱلنَّاسِ لَعَلَّهُمۡ يَشۡهَدُونَ ﴿61﴾قَالُواْ فَأۡتُواْ بِهِۦ عَلَىٰٓ أَعۡيُنِ ٱلنَّاسِ لَعَلَّهُمۡ يَشۡهَدُونَ
61. «ይመሰክሩበት ዘንድ በሰዎች ዓይን ፊት ላይ አምጡት።» አሉ።
قَالُوٓاْ ءَأَنتَ فَعَلۡتَ هَٰذَا بِـَٔالِهَتِنَا يَـٰٓإِبۡرَٰهِيمُ ﴿62﴾قَالُوٓاْ ءَأَنتَ فَعَلۡتَ هَٰذَا بِـَٔالِهَتِنَا يَـٰٓإِبۡرَٰهِيمُ
62. «ኢብራሂም ሆይ! በአማልክቶቻችን ይህንን የሰራህ አንተ ነህን?» አሉት።
قَالَ بَلۡ فَعَلَهُۥ كَبِيرُهُمۡ هَٰذَا فَسۡـَٔلُوهُمۡ إِن كَانُواْ يَنطِقُونَ ﴿63﴾قَالَ بَلۡ فَعَلَهُۥ كَبِيرُهُمۡ هَٰذَا فَسۡـَٔلُوهُمۡ إِن كَانُواْ يَنطِقُونَ
63. «አይደለም:: ይህ ትልቃቸው ሰራው፤ ይናገሩም እንደ ሆነ ጠይቋቸው።» አለ።
فَرَجَعُوٓاْ إِلَىٰٓ أَنفُسِهِمۡ فَقَالُوٓاْ إِنَّكُمۡ أَنتُمُ ٱلظَّـٰلِمُونَ ﴿64﴾فَرَجَعُوٓاْ إِلَىٰٓ أَنفُسِهِمۡ فَقَالُوٓاْ إِنَّكُمۡ أَنتُمُ ٱلظَّـٰلِمُونَ
64. ወደ ነፍሶቻቸዉም ተመለሱ: «እናንተ በመጠየቃችሁ በዳዮቹ እናንተው ናችሁ።» ተባባሉም።
ثُمَّ نُكِسُواْ عَلَىٰ رُءُوسِهِمۡ لَقَدۡ عَلِمۡتَ مَا هَـٰٓؤُلَآءِ يَنطِقُونَ ﴿65﴾ثُمَّ نُكِسُواْ عَلَىٰ رُءُوسِهِمۡ لَقَدۡ عَلِمۡتَ مَا هَـٰٓؤُلَآءِ يَنطِقُونَ
65. ከዚያም በራሶቻቸው ላይ ተገለበጡና «እነዚህ የሚናገሩ አለመሆናቸውን በእርግጥ አውቀሃል።» አሉ።
قَالَ أَفَتَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَنفَعُكُمۡ شَيۡـٔٗا وَلَا يَضُرُّكُمۡ ﴿66﴾قَالَ أَفَتَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَنفَعُكُمۡ شَيۡـٔٗا وَلَا يَضُرُّكُمۡ
66.ኢብራሂምም አላቸው: «ታዲያ ለእናንተ ብታመልኳቸው ምንም የማይጠቅማችሁንና ባታመልኳቸዉም በምንም ነገር የማይጎዳችሁን ጣዖታትን ከአላህ ሌላ ትገዛላችሁን?
أُفّٖ لَّكُمۡ وَلِمَا تَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ ﴿67﴾أُفّٖ لَّكُمۡ وَلِمَا تَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ
67. «ኡፍ! ለእናንተም ሆነ ከአላህ ሌላ ለምትገዙት ጣዖታት። አታስተውሉምን?» አለ።
قَالُواْ حَرِّقُوهُ وَٱنصُرُوٓاْ ءَالِهَتَكُمۡ إِن كُنتُمۡ فَٰعِلِينَ ﴿68﴾قَالُواْ حَرِّقُوهُ وَٱنصُرُوٓاْ ءَالِهَتَكُمۡ إِن كُنتُمۡ فَٰعِلِينَ
68. «ሰሪዎች (ተቆርቋሪዎች) እንደ ሆናችሁ ኢብራሂምን በእሳት አቃጥሉት አማልክቶቻችሁንም እርዱ።» አሉ:: (በእሳት ላይ ጣሉትም።)
قُلۡنَا يَٰنَارُ كُونِي بَرۡدٗا وَسَلَٰمًا عَلَىٰٓ إِبۡرَٰهِيمَ ﴿69﴾قُلۡنَا يَٰنَارُ كُونِي بَرۡدٗا وَسَلَٰمًا عَلَىٰٓ إِبۡرَٰهِيمَ
69. «እሳት ሆይ! በኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛና ሰላም ሁኚ።» አልን።
وَأَرَادُواْ بِهِۦ كَيۡدٗا فَجَعَلۡنَٰهُمُ ٱلۡأَخۡسَرِينَ ﴿70﴾وَأَرَادُواْ بِهِۦ كَيۡدٗا فَجَعَلۡنَٰهُمُ ٱلۡأَخۡسَرِينَ
70. በእርሱም ተንኮልን አሰቡ። በጣም ከሳሪዎች አደረግናቸው።
وَنَجَّيۡنَٰهُ وَلُوطًا إِلَى ٱلۡأَرۡضِ ٱلَّتِي بَٰرَكۡنَا فِيهَا لِلۡعَٰلَمِينَ ﴿71﴾وَنَجَّيۡنَٰهُ وَلُوطًا إِلَى ٱلۡأَرۡضِ ٱلَّتِي بَٰرَكۡنَا فِيهَا لِلۡعَٰلَمِينَ
71. እርሱንና ሉጥንም ወደዚያች በውስጡ ለዓለማት በረከትን ወደ አደረግንባት ምድር በመውሰድ አዳንናቸው::
وَوَهَبۡنَا لَهُۥٓ إِسۡحَٰقَ وَيَعۡقُوبَ نَافِلَةٗۖ وَكُلّٗا جَعَلۡنَا صَٰلِحِينَ ﴿72﴾وَوَهَبۡنَا لَهُۥٓ إِسۡحَٰقَ وَيَعۡقُوبَ نَافِلَةٗۖ وَكُلّٗا جَعَلۡنَا صَٰلِحِينَ
72.ለእርሱም ኢስሐቅን ያዕቆብንም ተጨማሪ አድርገን ሰጠነው:: ሁሉንም መልካሞች አደረግን::