quranm◉

ገጽ 365

Range
from 25:56 to 25:67
Surahs covered
ትርጉም
12 ትርጉም

◉

25:56

وَمَآ أَرۡسَلۡنَٰكَ إِلَّا مُبَشِّرٗا وَنَذِيرٗا ﴿56﴾

56. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን እንጂ አላክንህም::

25:57

قُلۡ مَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٍ إِلَّا مَن شَآءَ أَن يَتَّخِذَ إِلَىٰ رَبِّهِۦ سَبِيلٗا ﴿57﴾

57. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርሱ ላይ ዋጋን በፍጹም አልጠይቃችሁም። ወደ ጌታው መልካም መንገድን ለመያዝ የሻ ሰው ይስራ።» በላቸው።

25:58

وَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱلۡحَيِّ ٱلَّذِي لَا يَمُوتُ وَسَبِّحۡ بِحَمۡدِهِۦۚ وَكَفَىٰ بِهِۦ بِذُنُوبِ عِبَادِهِۦ خَبِيرًا ﴿58﴾

58. በዚያም በማይሞተው ህያው አምላክ ላይ ተመካ፤ ከማመስገንም ጋር አጥራው:: የባሮቹን ኃጢአቶች ውስጥ በማወቅ በእርሱ በቃ::

25:59

ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ وَمَا بَيۡنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٖ ثُمَّ ٱسۡتَوَىٰ عَلَى ٱلۡعَرۡشِۖ ٱلرَّحۡمَٰنُ فَسۡـَٔلۡ بِهِۦ خَبِيرٗا ﴿59﴾

59. ያ ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ ብቻ የፈጠረ ነው። ከዚያም በዐርሹ ላይ ከፍ አለ:: አር-ረህማን ነው:: ከእርሱም አዋቂን ጠይቅ።

25:60

وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ٱسۡجُدُواْۤ لِلرَّحۡمَٰنِ قَالُواْ وَمَا ٱلرَّحۡمَٰنُ أَنَسۡجُدُ لِمَا تَأۡمُرُنَا وَزَادَهُمۡ نُفُورٗا۩ ﴿60﴾

60. ለእነርሱም «ለአር-ረህማን ስገዱ።» በተባሉ ጊዜ «አር-ረህማን ማን ነው? ለምታዘንና ለማናውቀው እንሰግዳለን እንዴ?» ይላሉ። ይህም መራቅን ጨመራቸው። {1}

25:61

تَبَارَكَ ٱلَّذِي جَعَلَ فِي ٱلسَّمَآءِ بُرُوجٗا وَجَعَلَ فِيهَا سِرَٰجٗا وَقَمَرٗا مُّنِيرٗا ﴿61﴾

61. ያ በሰማይ ቡሩጆችን ያደረገና በእርሷም አንጸባራቂን ጸሐይ አብሪ ጨረቃንም የፈጠረ ጌታ ክብሩ በጣም ላቀ።

25:62

وَهُوَ ٱلَّذِي جَعَلَ ٱلَّيۡلَ وَٱلنَّهَارَ خِلۡفَةٗ لِّمَنۡ أَرَادَ أَن يَذَّكَّرَ أَوۡ أَرَادَ شُكُورٗا ﴿62﴾

62. እርሱም ያ ያመለጠውን ስራ ማስታወስን ለሚፈልግ ወይም ማመስገንን ለሚፈልግ ሌሊትንና ቀንን ተተካኪ ያደረገ ነው::

25:63

وَعِبَادُ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلَّذِينَ يَمۡشُونَ عَلَى ٱلۡأَرۡضِ هَوۡنٗا وَإِذَا خَاطَبَهُمُ ٱلۡجَٰهِلُونَ قَالُواْ سَلَٰمٗا ﴿63﴾

63. የአር-ረህማን ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚሄዱት፤ ባለጌዎችም (በክፉ) ባነጋገሯቸው ጊዜ ሰላም የሚሉት ናቸው::

25:64

وَٱلَّذِينَ يَبِيتُونَ لِرَبِّهِمۡ سُجَّدٗا وَقِيَٰمٗا ﴿64﴾

64. እነዚያም ለጌታቸው በግንባራቸው ተደፊዎችና ቋሚዎች (ሰጋጆች) ሆነው የሚያድሩት ናቸው።

25:65

وَٱلَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَا ٱصۡرِفۡ عَنَّا عَذَابَ جَهَنَّمَۖ إِنَّ عَذَابَهَا كَانَ غَرَامًا ﴿65﴾

65. እነዚያም (እንዲህ) የሚሉት ናቸው: «ጌታችን ሆይ! የገሀነምን ቅጣት ከእኛ ላይ መልስልን ቅጣቷ የማይለይለቅ ነውና።

25:66

إِنَّهَا سَآءَتۡ مُسۡتَقَرّٗا وَمُقَامٗا ﴿66﴾

66. «እርሷ መርጊያና መቀመጫ ለመሆን ከፋች!» የሚሉት ናቸው።

25:67

وَٱلَّذِينَ إِذَآ أَنفَقُواْ لَمۡ يُسۡرِفُواْ وَلَمۡ يَقۡتُرُواْ وَكَانَ بَيۡنَ ذَٰلِكَ قَوَامٗا ﴿67﴾

67. እነዚያም በለገሱ ጊዜ የማያባክኑት የማይቆጥቡትም ናቸው:: በዚህም መካከል ልግስናቸው ትክክለኛ የሆነ ነው::