quranm◉

Surah Al-Isra transliteration

◉ ሱራ · ∞

17:1

سُبۡحَٰنَ ٱلَّذِيٓ أَسۡرَىٰ بِعَبۡدِهِۦ لَيۡلٗا مِّنَ ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِ إِلَى ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡأَقۡصَا ٱلَّذِي بَٰرَكۡنَا حَوۡلَهُۥ لِنُرِيَهُۥ مِنۡ ءَايَٰتِنَآۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡبَصِيرُ ﴿1﴾

Transliteration: Subhana allathee asra biAAabdihi laylan mina almasjidi alharami ila almasjidi alaqsa allathee barakna hawlahu linuriyahu min ayatina innahu huwa alssameeAAu albaseeru

Translation: 1. ጥራት ለዚያ ባሪያውን (ሙሐመድን) ከተከበረው የሐረም መስጊድ ወደ እዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ሩቁ (አል አቅሷ) መስጊድ በሌሊት ለወሰደው አምላክ ለአላህ ይሁን:: ይህን ያደረግን ተዓምራታችንን ልናሳየው ነው:: እነሆ እርሱ (አላህ) ሰሚዉና ተመልካቹ ነው::

17:2

وَءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ وَجَعَلۡنَٰهُ هُدٗى لِّبَنِيٓ إِسۡرَـٰٓءِيلَ أَلَّا تَتَّخِذُواْ مِن دُونِي وَكِيلٗا ﴿2﴾

Transliteration: Waatayna moosa alkitaba wajaAAalnahu hudan libanee israeela alla tattakhithoo min doonee wakeelan

Translation: 2. ለሙሳም (ተውራት የተባለውን) መጽሐፍ ሰጠነውና ለኢስራኢል ልጆች መሪ አደረግነው:: ከእኔ ሌላ ወኪል (መጠጊያ) አድርጋችሁ ማንንም አታድርጉ“ስንልም አዘዝናቸው::

17:3

ذُرِّيَّةَ مَنۡ حَمَلۡنَا مَعَ نُوحٍۚ إِنَّهُۥ كَانَ عَبۡدٗا شَكُورٗا ﴿3﴾

Transliteration: Thurriyyata man hamalna maAAa noohin innahu kana AAabdan shakooran

Translation: 3. «ከኑህ ጋር (በመርከቧ ላይ) የጫንናቸው (አማኝ )ዝርዮች ሆይ! (አላህን ተገዙ)፤ ኑህ በእርግጥ አምላኩን በብዛት አመስጋኝ ባሪያ ነበርና» አልናቸው።

17:4

وَقَضَيۡنَآ إِلَىٰ بَنِيٓ إِسۡرَـٰٓءِيلَ فِي ٱلۡكِتَٰبِ لَتُفۡسِدُنَّ فِي ٱلۡأَرۡضِ مَرَّتَيۡنِ وَلَتَعۡلُنَّ عُلُوّٗا كَبِيرٗا ﴿4﴾

Transliteration: Waqadayna ila banee israeela fee alkitabi latufsidunna fee alardi marratayni walataAAlunna AAuluwwan kabeeran

Translation: 4. ለኢስራኢል ልጆችም፡ “በምድር ላይ ሁለት ጊዜ ጥፋት ትፈጽማላችሁ:: አለቅጥም አምባገነን ትሆናላችሁ::” ስንል በመጽሐፉ ውስጥ ገለጽን::

17:5

فَإِذَا جَآءَ وَعۡدُ أُولَىٰهُمَا بَعَثۡنَا عَلَيۡكُمۡ عِبَادٗا لَّنَآ أُوْلِي بَأۡسٖ شَدِيدٖ فَجَاسُواْ خِلَٰلَ ٱلدِّيَارِۚ وَكَانَ وَعۡدٗا مَّفۡعُولٗا ﴿5﴾

Transliteration: Faitha jaa waAAdu oolahuma baAAathna AAalaykum AAibadan lana olee basin shadeedin fajasoo khilala alddiyari wakana waAAdan mafAAoolan

Translation: 5. ከሁለቱ የመጀመሪያው ጥፋት መፈጸሚያ ወቅቱ በደረሰ ጊዜ የበረታ ኃይል ያላቸውን ባሮቻችንን በእናነተ ላይ ላክንባችሁ:: እነርሱም ቤቶችን ሁሉ በረበሩ:: ይህ መፈጸሙ የማይቀር ውሳኔ ነበር::

17:6

ثُمَّ رَدَدۡنَا لَكُمُ ٱلۡكَرَّةَ عَلَيۡهِمۡ وَأَمۡدَدۡنَٰكُم بِأَمۡوَٰلٖ وَبَنِينَ وَجَعَلۡنَٰكُمۡ أَكۡثَرَ نَفِيرًا ﴿6﴾

Transliteration: Thumma radadna lakumu alkarrata AAalayhim waamdadnakum biamwalin wabaneena wajaAAalnakum akthara nafeeran

Translation: 6. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ከዚያም በኋላ በእነርሱ ላይ የድል አድራጊነትን እድል ሰጠናችሁ:: ገንዘብንና ወንዶች ልጆችንም ለገስናችሁ:: በሰው ኃይልም ብዙ አደረግናችሁ::

17:7

إِنۡ أَحۡسَنتُمۡ أَحۡسَنتُمۡ لِأَنفُسِكُمۡۖ وَإِنۡ أَسَأۡتُمۡ فَلَهَاۚ فَإِذَا جَآءَ وَعۡدُ ٱلۡأٓخِرَةِ لِيَسُـُٔواْ وُجُوهَكُمۡ وَلِيَدۡخُلُواْ ٱلۡمَسۡجِدَ كَمَا دَخَلُوهُ أَوَّلَ مَرَّةٖ وَلِيُتَبِّرُواْ مَا عَلَوۡاْ تَتۡبِيرًا ﴿7﴾

Transliteration: In ahsantum ahsantum lianfusikum wain asatum falaha faitha jaa waAAdu alakhirati liyasoooo wujoohakum waliyadkhuloo almasjida kama dakhaloohu awwala marratin waliyutabbiroo ma AAalaw tatbeeran

Translation: 7. መልካምን ብትሠሩ ለነፍሶቻችሁ መልካምን ሠራችሁ:: መጥፎንም ብትሠሩ በነፍሶቻችሁ ላይ ነው:: የኋለኛይቱ ጥፋት ቀጠሮ በደረሰ ጊዜ ፊቶቻችሁን ሊያስከፉ፤ መስጊዱንም በመጀመሪያ ጊዜ እንደገቡቡት ሊገቡ፤ ያሸነፉትንም ሁሉ ፈጽመው ማጥፋትን እንዲያጠፉ እንልካቸዋለን::

17:8

عَسَىٰ رَبُّكُمۡ أَن يَرۡحَمَكُمۡۚ وَإِنۡ عُدتُّمۡ عُدۡنَاۚ وَجَعَلۡنَا جَهَنَّمَ لِلۡكَٰفِرِينَ حَصِيرًا ﴿8﴾

Transliteration: AAasa rabbukum an yarhamakum wain AAudtum AAudna wajaAAalna jahannama lilkafireena haseeran

Translation: 8. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ! በመጽሐፉም አልን ብትጸጸቱ) «ጌታችሁ ሊያዝንላችሁ ይከጀላል:: ወደ ማጥፋት እንደገና ብትመለሱም እኛም ወደ ቅጣቱ እንመለሳለን:: ገሀነምንም ለከሓዲያን ሁሉ ማሰሪያ አድርገናል።»

17:9

إِنَّ هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانَ يَهۡدِي لِلَّتِي هِيَ أَقۡوَمُ وَيُبَشِّرُ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ٱلَّذِينَ يَعۡمَلُونَ ٱلصَّـٰلِحَٰتِ أَنَّ لَهُمۡ أَجۡرٗا كَبِيرٗا ﴿9﴾

Transliteration: Inna hatha alqurana yahdee lillatee hiya aqwamu wayubashshiru almumineena allatheena yaAAmaloona alssalihati anna lahum ajran kabeeran

Translation: 9. ይህ ቁርኣን ወደዚያች በሁሉ ነገር ቀጥተኛ ወደ ሆነችው መንገድ ይመራል:: እነዚያንም በጎ የሚሠሩትንም አማኞች ለእነርሱ ታላቅ ምንዳ ያላቸው መሆኑን ያበስራል::

17:10

وَأَنَّ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ أَعۡتَدۡنَا لَهُمۡ عَذَابًا أَلِيمٗا ﴿10﴾

Transliteration: Waanna allatheena la yuminoona bialakhirati aAAtadna lahum AAathaban aleeman

Translation: 10. እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣትን አዘጋጅተንላቸዋል::

17:11

وَيَدۡعُ ٱلۡإِنسَٰنُ بِٱلشَّرِّ دُعَآءَهُۥ بِٱلۡخَيۡرِۖ وَكَانَ ٱلۡإِنسَٰنُ عَجُولٗا ﴿11﴾

Transliteration: WayadAAu alinsanu bialshsharri duAAaahu bialkhayri wakana alinsanu AAajoolan

Translation: 11. ሰው መልካምን ነገር እንደሚለምን ሁሉ መጥፎንም ነገር ይለምናል:: ሰዉም ቸኳይ ነውና::

17:12

وَجَعَلۡنَا ٱلَّيۡلَ وَٱلنَّهَارَ ءَايَتَيۡنِۖ فَمَحَوۡنَآ ءَايَةَ ٱلَّيۡلِ وَجَعَلۡنَآ ءَايَةَ ٱلنَّهَارِ مُبۡصِرَةٗ لِّتَبۡتَغُواْ فَضۡلٗا مِّن رَّبِّكُمۡ وَلِتَعۡلَمُواْ عَدَدَ ٱلسِّنِينَ وَٱلۡحِسَابَۚ وَكُلَّ شَيۡءٖ فَصَّلۡنَٰهُ تَفۡصِيلٗا ﴿12﴾

Transliteration: WajaAAalna allayla waalnnahara ayatayni famahawna ayata allayli wajaAAalna ayata alnnahari mubsiratan litabtaghoo fadlan min rabbikum walitaAAlamoo AAadada alssineena waalhisaba wakulla shayin fassalnahu tafseelan

Translation: 12. ሌሊትንና ቀንን ለችሎታችን ምልክቶች አደረግን:: የሌሊትን ምልክትም አበስን:: የቀንን ምልክትም የምታሳይ አደረግን:: ይህም የሆነበት ከአላህ ትርፍን ልትፈልጉበትና የዓመታትንም ቁጥርና ሒሳብን ታውቁበት ዘንድ ነው:: ነገሩንም ሁሉ ለያይተን ዘረዘርነው::

17:13

وَكُلَّ إِنسَٰنٍ أَلۡزَمۡنَٰهُ طَـٰٓئِرَهُۥ فِي عُنُقِهِۦۖ وَنُخۡرِجُ لَهُۥ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ كِتَٰبٗا يَلۡقَىٰهُ مَنشُورًا ﴿13﴾

Transliteration: Wakulla insanin alzamnahu tairahu fee AAunuqihi wanukhriju lahu yawma alqiyamati kitaban yalqahu manshooran

Translation: 13. ሰውን ሁሉ በራሪውን (ሥራውን) በአንገቱ ላይ አስያዝነው:: ለእርሱም በትንሣኤ ቀን የተዘረጋ ሆኖ የሚያገኘው የሆነን መጽሐፍ እናወጣለታለን::

17:14

ٱقۡرَأۡ كِتَٰبَكَ كَفَىٰ بِنَفۡسِكَ ٱلۡيَوۡمَ عَلَيۡكَ حَسِيبٗا ﴿14﴾

Transliteration: Iqra kitabaka kafa binafsika alyawma AAalayka haseeban

Translation: 14. (ከዚያም) «መጽሐፍህን አንብብ:: ዛሬ ባንተ ላይ ተቆጣጣሪነት በነፍስህ ብቻ በቃ።» ይባላል።

17:15

مَّنِ ٱهۡتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهۡتَدِي لِنَفۡسِهِۦۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيۡهَاۚ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٞ وِزۡرَ أُخۡرَىٰۗ وَمَا كُنَّا مُعَذِّبِينَ حَتَّىٰ نَبۡعَثَ رَسُولٗا ﴿15﴾

Transliteration: Mani ihtada fainnama yahtadee linafsihi waman dalla fainnama yadillu AAalayha wala taziru waziratun wizra okhra wama kunna muAAaththibeena hatta nabAAatha rasoolan

Translation: 15. በቀናው መንገድ የተመራ ሁሉ የሚመራው ለእራሱ ብቻ ነው:: ከቀናው መንገድ የተሳሳተም የመሳሳቱ ጉዳት በእርሱ ላይ ብቻ ነው:: ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ኃጢአት አትሸከምም:: መልዕክተኛንም እስከምንልክ ድረስ ማንንም የምንቀጣ አይደለንም።

17:16

وَإِذَآ أَرَدۡنَآ أَن نُّهۡلِكَ قَرۡيَةً أَمَرۡنَا مُتۡرَفِيهَا فَفَسَقُواْ فِيهَا فَحَقَّ عَلَيۡهَا ٱلۡقَوۡلُ فَدَمَّرۡنَٰهَا تَدۡمِيرٗا ﴿16﴾

Transliteration: Waitha aradna an nuhlika qaryatan amarna mutrafeeha fafasaqoo feeha fahaqqa AAalayha alqawlu fadammarnaha tadmeeran

Translation: 16. ማንኛዋንም ከተማ ለማጥፋት በፈለግን ጊዜ ባለ ጸጋዎችዋን እናዛቸዋለን:: በውስጧም ያምፃሉ:: በእርሷም ላይ የቅጣት ቃሉ ይፈጸምባታል:: ከዚያም ማውደምን እናወድማታለን::

17:17

وَكَمۡ أَهۡلَكۡنَا مِنَ ٱلۡقُرُونِ مِنۢ بَعۡدِ نُوحٖۗ وَكَفَىٰ بِرَبِّكَ بِذُنُوبِ عِبَادِهِۦ خَبِيرَۢا بَصِيرٗا ﴿17﴾

Transliteration: Wakam ahlakna mina alqurooni min baAAdi noohin wakafa birabbika bithunoobi AAibadihi khabeeran baseeran

Translation: 17. ከኑሕም በኋላ ከየክፍለ ዘመናት ሰዎች ያጠፋናቸው ብዙዎች ናቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የባሮቹንም ኃጢአቶች ውስጠ አዋቂ ተመልካች መሆን በጌታህ ብቻ በቃ::

17:18

مَّن كَانَ يُرِيدُ ٱلۡعَاجِلَةَ عَجَّلۡنَا لَهُۥ فِيهَا مَا نَشَآءُ لِمَن نُّرِيدُ ثُمَّ جَعَلۡنَا لَهُۥ جَهَنَّمَ يَصۡلَىٰهَا مَذۡمُومٗا مَّدۡحُورٗا ﴿18﴾

Transliteration: Man kana yureedu alAAajilata AAajjalna lahu feeha ma nashao liman nureedu thumma jaAAalna lahu jahannama yaslaha mathmooman madhooran

Translation: 18. ጊዜያዊቱን ዓለም (በሥራው) የሚፈልግ ሁሉ ለእርሱ ከእርሷ ውስጥ የፈለግነውን ጸጋ ብቻ ለምንፈልገውም ብቻ እናስቸኩልለታለን:: ከዚያም ለእርሱ ገሀነምን መኖሪያ አድርገንለታል:: ተወቃሽና ከአላህ እዝነት የተባረረ ሆኖ ይገባባታል።

17:19

وَمَنۡ أَرَادَ ٱلۡأٓخِرَةَ وَسَعَىٰ لَهَا سَعۡيَهَا وَهُوَ مُؤۡمِنٞ فَأُوْلَـٰٓئِكَ كَانَ سَعۡيُهُم مَّشۡكُورٗا ﴿19﴾

Transliteration: Waman arada alakhirata wasaAAa laha saAAyaha wahuwa muminun faolaika kana saAAyuhum mashkooran

Translation: 19. የመጨረሻይቱን ዓለም የፈለገ እና እርሱ አማኝ ሆኖ ለእርሷ ተገቢ የሆነን ሥራ የሠራ ደግሞ እነዚህ ሥራቸው የተመሰገነ ይሆናል::

17:20

كُلّٗا نُّمِدُّ هَـٰٓؤُلَآءِ وَهَـٰٓؤُلَآءِ مِنۡ عَطَآءِ رَبِّكَۚ وَمَا كَانَ عَطَآءُ رَبِّكَ مَحۡظُورًا ﴿20﴾

Transliteration: Kullan numiddu haolai wahaolai min AAatai rabbika wama kana AAatao rabbika mahthooran

Translation: 20. ሁሉንም እነዚህንም እነዚያንም ከጌታህ ስጦታ በዚህ ዓለም እንጨምርላቸዋለን:: የጌታህም ስጦታ በዚች ዓለም ክልክል አይደለም::

17:21

ٱنظُرۡ كَيۡفَ فَضَّلۡنَا بَعۡضَهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖۚ وَلَلۡأٓخِرَةُ أَكۡبَرُ دَرَجَٰتٖ وَأَكۡبَرُ تَفۡضِيلٗا ﴿21﴾

Transliteration: Onthur kayfa faddalna baAAdahum AAala baAAdin walalakhiratu akbaru darajatin waakbaru tafdeelan

Translation: 21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ እንዴት እንዳስበለጥን ተመልከት:: የመጨረሻይቱም ሀገር በማዕረጎች በጣም የከበረችና በመብለጥም የላቀች ናት::

17:22

لَّا تَجۡعَلۡ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَتَقۡعُدَ مَذۡمُومٗا مَّخۡذُولٗا ﴿22﴾

Transliteration: La tajAAal maAAa Allahi ilahan akhara fataqAAuda mathmooman makhthoolan

Translation: 22. (የሰው ልጅ ሆይ!) ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ አታድርግ:: የተወቀስክ፤ ረዳት የሌለህ ትሆናለህና::

17:23

وَقَضَىٰ رَبُّكَ أَلَّا تَعۡبُدُوٓاْ إِلَّآ إِيَّاهُ وَبِٱلۡوَٰلِدَيۡنِ إِحۡسَٰنًاۚ إِمَّا يَبۡلُغَنَّ عِندَكَ ٱلۡكِبَرَ أَحَدُهُمَآ أَوۡ كِلَاهُمَا فَلَا تَقُل لَّهُمَآ أُفّٖ وَلَا تَنۡهَرۡهُمَا وَقُل لَّهُمَا قَوۡلٗا كَرِيمٗا ﴿23﴾

Transliteration: Waqada rabbuka alla taAAbudoo illa iyyahu wabialwalidayni ihsanan imma yablughanna AAindaka alkibara ahaduhuma aw kilahuma fala taqul lahuma offin wala tanharhuma waqul lahuma qawlan kareeman

Translation: 23. (የሰው ልጅ ሆይ!) ጌታህ እንዲህ ሲል አዘዘ:: እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፤ ለወላጆቻችሁም መልካምን ሥሩ፤ ባንተ ዘንድ ሆነው ከወላጆችህ አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ «ኡፍ!» እንኳን አትበላቸው:: አትገላምጣቸዉም:: ለእነርሱም መልካምን ቃል ብቻ ተናገራቸው::

17:24

وَٱخۡفِضۡ لَهُمَا جَنَاحَ ٱلذُّلِّ مِنَ ٱلرَّحۡمَةِ وَقُل رَّبِّ ٱرۡحَمۡهُمَا كَمَا رَبَّيَانِي صَغِيرٗا ﴿24﴾

Transliteration: Waikhfid lahuma janaha alththulli mina alrrahmati waqul rabbi irhamhuma kama rabbayanee sagheeran

Translation: 24. (ልጅ ሆይ!) ለሁለቱም የመተናነስ ክንፍን ዝቅ አድርግላቸው። «ጌታዬ ሆይ! በሕጻንነቴ በርህራሄ እንዳሳደጉኝ ሁሉ ለእነርሱም እዘንላቸው።» በልም።

17:25

رَّبُّكُمۡ أَعۡلَمُ بِمَا فِي نُفُوسِكُمۡۚ إِن تَكُونُواْ صَٰلِحِينَ فَإِنَّهُۥ كَانَ لِلۡأَوَّـٰبِينَ غَفُورٗا ﴿25﴾

Transliteration: Rabbukum aAAlamu bima fee nufoosikum in takoonoo saliheena fainnahu kana lilawwabeena ghafooran

Translation: 25. (ሰዎች ሆይ!) ጌታችሁ በነፍሶቻችሁ ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ ይበልጥ አዋቂ ነው:: ታዛዦችም ብትሆኑ ወይም ብታጠፉ እርሱ ለተመላሾች ሁሉ መሓሪ ነው::

17:26

وَءَاتِ ذَا ٱلۡقُرۡبَىٰ حَقَّهُۥ وَٱلۡمِسۡكِينَ وَٱبۡنَ ٱلسَّبِيلِ وَلَا تُبَذِّرۡ تَبۡذِيرًا ﴿26﴾

Transliteration: Waati tha alqurba haqqahu waalmiskeena waibna alssabeeli wala tubaththir tabtheeran

Translation: 26. (የሰው ልጅ ሆይ!) ለዝምድና ባለቤት ሁሉ ተገቢ መብቱን ስጥ:: ለምስኪንና ለመንገደኛም እንዲሁ መብቱን ስጥ:: (በሁሉም ነገር ላይ) ማባከንንም አታባክን::

17:27

إِنَّ ٱلۡمُبَذِّرِينَ كَانُوٓاْ إِخۡوَٰنَ ٱلشَّيَٰطِينِۖ وَكَانَ ٱلشَّيۡطَٰنُ لِرَبِّهِۦ كَفُورٗا ﴿27﴾

Transliteration: Inna almubaththireena kanoo ikhwana alshshayateeni wakana alshshaytanu lirabbihi kafooran

Translation: 27. አባካኞች የሰይጣናት ወንድሞች ናቸውና:: ሰይጣንም ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው::

17:28

وَإِمَّا تُعۡرِضَنَّ عَنۡهُمُ ٱبۡتِغَآءَ رَحۡمَةٖ مِّن رَّبِّكَ تَرۡجُوهَا فَقُل لَّهُمۡ قَوۡلٗا مَّيۡسُورٗا ﴿28﴾

Transliteration: Waimma tuAAridanna AAanhumu ibtighaa rahmatin min rabbika tarjooha faqul lahum qawlan maysooran

Translation: 28. ከጌታህም የምትከጅላትን ጸጋ ለማምጣት በማሰብ ከእነርሱ ብትዞር ለእነርሱ ልዝብን ቃል ተናገራቸው::

17:29

وَلَا تَجۡعَلۡ يَدَكَ مَغۡلُولَةً إِلَىٰ عُنُقِكَ وَلَا تَبۡسُطۡهَا كُلَّ ٱلۡبَسۡطِ فَتَقۡعُدَ مَلُومٗا مَّحۡسُورًا ﴿29﴾

Transliteration: Wala tajAAal yadaka maghloolatan ila AAunuqika wala tabsutha kulla albasti fataqAAuda malooman mahsooran

Translation: 29. እጅህን ወደ አንገትህ ታጥፋ የታሠረች አታድርግ:: መዘርጋትንም ሁሉ አትዘርጋት:: የተወቀስክና የተቆጨህ ትሆናለህና::

17:30

إِنَّ رَبَّكَ يَبۡسُطُ ٱلرِّزۡقَ لِمَن يَشَآءُ وَيَقۡدِرُۚ إِنَّهُۥ كَانَ بِعِبَادِهِۦ خَبِيرَۢا بَصِيرٗا ﴿30﴾

Transliteration: Inna rabbaka yabsutu alrrizqa liman yashao wayaqdiru innahu kana biAAibadihi khabeeran baseeran

Translation: 30. ጌታህ ሲሳይን ለሚፈልገው ሁሉ ያሰፋል። ለሚፈልገውም ያጠባል። እርሱ በባሮቹ ሁኔታ ውስጠ አዋቂና ተመልካች ነውና።

17:31

وَلَا تَقۡتُلُوٓاْ أَوۡلَٰدَكُمۡ خَشۡيَةَ إِمۡلَٰقٖۖ نَّحۡنُ نَرۡزُقُهُمۡ وَإِيَّاكُمۡۚ إِنَّ قَتۡلَهُمۡ كَانَ خِطۡـٔٗا كَبِيرٗا ﴿31﴾

Transliteration: Wala taqtuloo awladakum khashyata imlaqin nahnu narzuquhum waiyyakum inna qatlahum kana khitan kabeeran

Translation: 31. (ሰዎች ሆይ!) ልጆቻችሁንም ድህነትን በመፍራት አትግደሉ:: እኛ እንመግባቸዋለን:: እናንተንም እንመግባችኃለን:: እነርሱን መግደል ታላቅ ኃጢአት ነውና::

17:32

وَلَا تَقۡرَبُواْ ٱلزِّنَىٰٓۖ إِنَّهُۥ كَانَ فَٰحِشَةٗ وَسَآءَ سَبِيلٗا ﴿32﴾

Transliteration: Wala taqraboo alzzina innahu kana fahishatan wasaa sabeelan

Translation: 32. (ሰዎች ሆይ!) ዝሙትንም አትቅረቡ:: እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና:: መንገድነቱም ከፋ!

17:33

وَلَا تَقۡتُلُواْ ٱلنَّفۡسَ ٱلَّتِي حَرَّمَ ٱللَّهُ إِلَّا بِٱلۡحَقِّۗ وَمَن قُتِلَ مَظۡلُومٗا فَقَدۡ جَعَلۡنَا لِوَلِيِّهِۦ سُلۡطَٰنٗا فَلَا يُسۡرِف فِّي ٱلۡقَتۡلِۖ إِنَّهُۥ كَانَ مَنصُورٗا ﴿33﴾

Transliteration: Wala taqtuloo alnnafsa allatee harrama Allahu illa bialhaqqi waman qutila mathlooman faqad jaAAalna liwaliyyihi sultanan fala yusrif fee alqatli innahu kana mansooran

Translation: 33. (ሰዎች ሆይ!) ያቺንም አላህ ያከበራትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ:: የተበደለ ሆኖ ለተገደለም ሰው ዘመዱ በገዳዩ ላይ ስልጣንን አድርገንለታል:: በመግደል ወሰንን አይለፍ:: እርሱ እገዛ ያለው ነውና::

17:34

وَلَا تَقۡرَبُواْ مَالَ ٱلۡيَتِيمِ إِلَّا بِٱلَّتِي هِيَ أَحۡسَنُ حَتَّىٰ يَبۡلُغَ أَشُدَّهُۥۚ وَأَوۡفُواْ بِٱلۡعَهۡدِۖ إِنَّ ٱلۡعَهۡدَ كَانَ مَسۡـُٔولٗا ﴿34﴾

Transliteration: Wala taqraboo mala alyateemi illa biallatee hiya ahsanu hatta yablugha ashuddahu waawfoo bialAAahdi inna alAAahda kana masoolan

Translation: 34. (ሰዎች ሆይ!) የየቲምንም ገንዘብ የብርታቱን ጊዜ እስኪደርስ ድረስ በዚያች እርሷ መልካም በሆነች ሁኔታ እንጂ አትቅረቡ:: በቃል ኪዳናችሁም ሙሉ:: ቃል ኪዳን የሚጠየቁበት ጉዳይ ነውና::

17:35

وَأَوۡفُواْ ٱلۡكَيۡلَ إِذَا كِلۡتُمۡ وَزِنُواْ بِٱلۡقِسۡطَاسِ ٱلۡمُسۡتَقِيمِۚ ذَٰلِكَ خَيۡرٞ وَأَحۡسَنُ تَأۡوِيلٗا ﴿35﴾

Transliteration: Waawfoo alkayla itha kiltum wazinoo bialqistasi almustaqeemi thalika khayrun waahsanu taweelan

Translation: 35. (ሰዎች ሆይ!) በሰፈራችሁም ጊዜ ስፍርን ሙሉ:: በትክክለኛው ሚዛንም መዝኑ:: ይህ መልካም ነገር ነው:: መጨረሻዉም ያማረ ነው::

17:36

وَلَا تَقۡفُ مَا لَيۡسَ لَكَ بِهِۦ عِلۡمٌۚ إِنَّ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡبَصَرَ وَٱلۡفُؤَادَ كُلُّ أُوْلَـٰٓئِكَ كَانَ عَنۡهُ مَسۡـُٔولٗا ﴿36﴾

Transliteration: Wala taqfu ma laysa laka bihi AAilmun inna alssamAAa waalbasara waalfuada kullu olaika kana AAanhu masoolan

Translation: 36. (የሰው ልጅ ሆይ!) ላንተ በእርሱ እውቀት የሌለህንም ነገር አትከተል:: መስሚያ፤ ማያ፤ ማሰቢያም እነዚህ ሁሉ ባለቤታቸው ከእነርሱ ተጠያቂ ነውና::

17:37

وَلَا تَمۡشِ فِي ٱلۡأَرۡضِ مَرَحًاۖ إِنَّكَ لَن تَخۡرِقَ ٱلۡأَرۡضَ وَلَن تَبۡلُغَ ٱلۡجِبَالَ طُولٗا ﴿37﴾

Transliteration: Wala tamshi fee alardi marahan innaka lan takhriqa alarda walan tablugha aljibala toolan

Translation: 37. (የሰው ልጅ ሆይ!) በምድር ላይ የተንበጣረርክ ሆነህም አትሂድ:: አንተ ፈጽሞ ምድርን አትሰረጉድምና:: በርዝመትም ፈጽሞ ጋራዎችን አትደርስምና::

17:38

كُلُّ ذَٰلِكَ كَانَ سَيِّئُهُۥ عِندَ رَبِّكَ مَكۡرُوهٗا ﴿38﴾

Transliteration: Kullu thalika kana sayyiohu AAinda rabbika makroohan

Translation: 38. (የሰው ልጅ ሆይ!) ይህ ሁሉ ክፋቱ ከጌታህ ዘንድ የተጠላ ነው።

17:39

ذَٰلِكَ مِمَّآ أَوۡحَىٰٓ إِلَيۡكَ رَبُّكَ مِنَ ٱلۡحِكۡمَةِۗ وَلَا تَجۡعَلۡ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَتُلۡقَىٰ فِي جَهَنَّمَ مَلُومٗا مَّدۡحُورًا ﴿39﴾

Transliteration: Thalika mimma awha ilayka rabbuka mina alhikmati wala tajAAal maAAa Allahi ilahan akhara fatulqa fee jahannama malooman madhooran

Translation: 39. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ጌታህ ከጥበብ ወደ አንተ ካወረደው ነገር ነው:: ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ አታድርግ:: የተወቀስክ፤ የተባረርክ ሆነህ በገሀነም ውስጥ ትጣላለህና::

17:40

أَفَأَصۡفَىٰكُمۡ رَبُّكُم بِٱلۡبَنِينَ وَٱتَّخَذَ مِنَ ٱلۡمَلَـٰٓئِكَةِ إِنَٰثًاۚ إِنَّكُمۡ لَتَقُولُونَ قَوۡلًا عَظِيمٗا ﴿40﴾

Transliteration: Afaasfakum rabbukum bialbaneena waittakhatha mina almalaikati inathan innakum lataqooloona qawlan AAatheeman

Translation: 40. (ጣኦታዊያን ሆይ!) ጌታችሁ በወንዶች ልጆች መረጣችሁና ከመላዕክት ሴቶችን ልጆች ለራሱ ያዘን? እናንተ ከባድ ቃልን በእርግጥ ትናገራላችሁ::

17:41

وَلَقَدۡ صَرَّفۡنَا فِي هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانِ لِيَذَّكَّرُواْ وَمَا يَزِيدُهُمۡ إِلَّا نُفُورٗا ﴿41﴾

Transliteration: Walaqad sarrafna fee hatha alqurani liyaththakkaroo wama yazeeduhum illa nufooran

Translation: 41. ይገሰጹ ዘንድ በዚህ ቁርኣን ውስጥ ደጋግመን በእርግጥ ገለጽን:: ለእነርሱ ግን ከትክክለኛው መንገድ መበርገግን እንጂ ሌላን አይጨምርላቸዉም::

17:42

قُل لَّوۡ كَانَ مَعَهُۥٓ ءَالِهَةٞ كَمَا يَقُولُونَ إِذٗا لَّٱبۡتَغَوۡاْ إِلَىٰ ذِي ٱلۡعَرۡشِ سَبِيلٗا ﴿42﴾

Transliteration: Qul law kana maAAahu alihatun kama yaqooloona ithan laibtaghaw ila thee alAAarshi sabeelan

Translation: 42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነርሱ እንደሚሉት ከእርሱ ጋር ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ ያን ጊዜ ወደ ዐርሹ ባለቤት መንገድን በፈለጉ ነበር።» በላቸው።

17:43

سُبۡحَٰنَهُۥ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يَقُولُونَ عُلُوّٗا كَبِيرٗا ﴿43﴾

Transliteration: Subhanahu wataAAala AAamma yaqooloona AAuluwwan kabeeran

Translation: 43. ጥራት ይገባው:: አላህ እነርሱ ከሚሉት ነገር ሁሉ ከፍ ያለን ልቅና ላቀ::

17:44

تُسَبِّحُ لَهُ ٱلسَّمَٰوَٰتُ ٱلسَّبۡعُ وَٱلۡأَرۡضُ وَمَن فِيهِنَّۚ وَإِن مِّن شَيۡءٍ إِلَّا يُسَبِّحُ بِحَمۡدِهِۦ وَلَٰكِن لَّا تَفۡقَهُونَ تَسۡبِيحَهُمۡۚ إِنَّهُۥ كَانَ حَلِيمًا غَفُورٗا ﴿44﴾

Transliteration: Tusabbihu lahu alssamawatu alssabAAu waalardu waman feehinna wain min shayin illa yusabbihu bihamdihi walakin la tafqahoona tasbeehahum innahu kana haleeman ghafooran

Translation: 44. ሰባቱ ሰማያትና ምድር እንዲሁም በውስጣቸውም ያለው ሁሉ እርሱን ያጠራሉ:: ከነገሩ ሁሉ እሱን ከማመስገን ጋር የሚያጠራው እንጂ አንድም የለም:: ማጥራታቸውን ግን አታውቁትም:: እርሱ ታጋሽና መሓሪ ነው::

17:45

وَإِذَا قَرَأۡتَ ٱلۡقُرۡءَانَ جَعَلۡنَا بَيۡنَكَ وَبَيۡنَ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ حِجَابٗا مَّسۡتُورٗا ﴿45﴾

Transliteration: Waitha qarata alqurana jaAAalna baynaka wabayna allatheena la yuminoona bialakhirati hijaban mastooran

Translation: 45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቁርኣንን ባነበብክ ጊዜ ባንተና በእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም በማያምኑት ሰዎች መካከል የሚሸሸግን ግርዶሽ አድርገናል::

17:46

وَجَعَلۡنَا عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ أَكِنَّةً أَن يَفۡقَهُوهُ وَفِيٓ ءَاذَانِهِمۡ وَقۡرٗاۚ وَإِذَا ذَكَرۡتَ رَبَّكَ فِي ٱلۡقُرۡءَانِ وَحۡدَهُۥ وَلَّوۡاْ عَلَىٰٓ أَدۡبَٰرِهِمۡ نُفُورٗا ﴿46﴾

Transliteration: WajaAAalna AAala quloobihim akinnatan an yafqahoohu wafee athanihim waqran waitha thakarta rabbaka fee alqurani wahdahu wallaw AAala adbarihim nufooran

Translation: 46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንዳያውቁትም በልቦቻቸው ላይ ሽፋንን፤ በጆሮቻቸዉም ውስጥ ድንቁርናን አደረግን:: ጌታህንም ብቻውን ሆኖ በቁርኣን ባወሳሀው ጊዜ የሚሸሹ ሆነው በጀርባዎቻቸዉ ላይ ይዞራሉ::

17:47

نَّحۡنُ أَعۡلَمُ بِمَا يَسۡتَمِعُونَ بِهِۦٓ إِذۡ يَسۡتَمِعُونَ إِلَيۡكَ وَإِذۡ هُمۡ نَجۡوَىٰٓ إِذۡ يَقُولُ ٱلظَّـٰلِمُونَ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا رَجُلٗا مَّسۡحُورًا ﴿47﴾

Transliteration: Nahnu aAAlamu bima yastamiAAoona bihi ith yastamiAAoona ilayka waith hum najwa ith yaqoolu alththalimoona in tattabiAAoona illa rajulan mashooran

Translation: 47. እኛ ወደ አንተ በሚያዳምጡ፤ በሚንሾካሸኩ፤ በዳዮችም እርስ በእርሳቸው «የተደገመበትን ሰው እንጂ አትከተሉም።» በሚሉ ጊዜ የሚያዳምጡበትን ምክንያት አዋቂ ነን።

17:48

ٱنظُرۡ كَيۡفَ ضَرَبُواْ لَكَ ٱلۡأَمۡثَالَ فَضَلُّواْ فَلَا يَسۡتَطِيعُونَ سَبِيلٗا ﴿48﴾

Transliteration: Onthur kayfa daraboo laka alamthala fadalloo fala yastateeAAoona sabeelan

Translation: 48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ላንተ ምሳሌዎችን እንዴት እንዳደረጉልህና ከዚያም እንዴት እንደ ተሳሳቱ ተመልከት:: ወደ እውነቱ ለመድረስ ትክክለኛውን መንገድ መከተል አይችሉም።

17:49

وَقَالُوٓاْ أَءِذَا كُنَّا عِظَٰمٗا وَرُفَٰتًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ خَلۡقٗا جَدِيدٗا ﴿49﴾

Transliteration: Waqaloo aitha kunna AAithaman warufatan ainna lamabAAoothoona khalqan jadeedan

Translation: 49. አሉም፡- «አጥንቶችና ብስብሶች በሆን ጊዜ እኛ እንዴት እንደገና አዲስ ፍጥረት ሆነን በእርግጥ ተቀስቃሾች እንሆናለን?»

17:50

قُلۡ كُونُواْ حِجَارَةً أَوۡ حَدِيدًا ﴿50﴾

Transliteration: Qul koonoo hijaratan aw hadeedan

Translation: 50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (እንዲህ) በላቸው: «ድንጋዮች ወይም ብረትም ሁኑ፤

17:51

أَوۡ خَلۡقٗا مِّمَّا يَكۡبُرُ فِي صُدُورِكُمۡۚ فَسَيَقُولُونَ مَن يُعِيدُنَاۖ قُلِ ٱلَّذِي فَطَرَكُمۡ أَوَّلَ مَرَّةٖۚ فَسَيُنۡغِضُونَ إِلَيۡكَ رُءُوسَهُمۡ وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هُوَۖ قُلۡ عَسَىٰٓ أَن يَكُونَ قَرِيبٗا ﴿51﴾

Transliteration: Aw khalqan mimma yakburu fee sudoorikum fasayaqooloona man yuAAeeduna quli allathee fatarakum awwala marratin fasayunghidoona ilayka ruoosahum wayaqooloona mata huwa qul AAasa an yakoona qareeban

Translation: 51. ወይም በልቦቻቸሁ ውስጥ የሚተልቅን ፍጥረትም ሁኑ (መቀስቀሳችሁ አይቀርም።)» «የሚመልሰንም ማነው?» ይላሉም። «ያ በመጀመሪያ ጊዜ የፈጠራችሁ ነው።» በላቸው:: ወደ አንተም ራሶቻቸውን ይነቀንቃሉ። «እርሱም መቼ ነው?» ይላሉም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) በላቸው: «እርሱ በቅርብ ቀን ሊሆን ይችላል።

17:52

يَوۡمَ يَدۡعُوكُمۡ فَتَسۡتَجِيبُونَ بِحَمۡدِهِۦ وَتَظُنُّونَ إِن لَّبِثۡتُمۡ إِلَّا قَلِيلٗا ﴿52﴾

Transliteration: Yawma yadAAookum fatastajeeboona bihamdihi watathunnoona in labithtum illa qaleelan

Translation: 52. «እርሱም የሚጠራችሁንና አላህን አመስጋኞቹ ሆናችሁ ጥሪውን የምትቀበሉበት፤ ጥቂትን ቀናት እንጂ ያልቆያችሁ መሆናችሁን የምትጠራጠሩበት ቀን ነው።» በላቸው::

17:53

وَقُل لِّعِبَادِي يَقُولُواْ ٱلَّتِي هِيَ أَحۡسَنُۚ إِنَّ ٱلشَّيۡطَٰنَ يَنزَغُ بَيۡنَهُمۡۚ إِنَّ ٱلشَّيۡطَٰنَ كَانَ لِلۡإِنسَٰنِ عَدُوّٗا مُّبِينٗا ﴿53﴾

Transliteration: Waqul liAAibadee yaqooloo allatee hiya ahsanu inna alshshaytana yanzaghu baynahum inna alshshaytana kana lilinsani AAaduwwan mubeenan

Translation: 53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለባሮቼም ንገራቸው:: መልካም የሆነችውን ቃል ብቻ ይናገሩ:: ሰይጣን በመካከላቸው ያበላሻልና:: ሰይጣን ለሰው ልጆች ግልጽ ጠላት ነውና::

17:54

رَّبُّكُمۡ أَعۡلَمُ بِكُمۡۖ إِن يَشَأۡ يَرۡحَمۡكُمۡ أَوۡ إِن يَشَأۡ يُعَذِّبۡكُمۡۚ وَمَآ أَرۡسَلۡنَٰكَ عَلَيۡهِمۡ وَكِيلٗا ﴿54﴾

Transliteration: Rabbukum aAAlamu bikum in yasha yarhamkum aw in yasha yuAAaththibkum wama arsalnaka AAalayhim wakeelan

Translation: 54. (ሰዎች ሆይ!) ጌታችሁ በእናንተ ሁኔታ አዋቂ ነው:: ቢፈልግ ያዝንላችኋል፤ ቢፈልግም ይቀጣችኃል። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነርሱ ላይ ሀላፊ ሆነህ አላክንህም:: አታስገድዳቸዉም::

17:55

وَرَبُّكَ أَعۡلَمُ بِمَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۗ وَلَقَدۡ فَضَّلۡنَا بَعۡضَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ عَلَىٰ بَعۡضٖۖ وَءَاتَيۡنَا دَاوُۥدَ زَبُورٗا ﴿55﴾

Transliteration: Warabbuka aAAlamu biman fee alssamawati waalardi walaqad faddalna baAAda alnnabiyyeena AAala baAAdin waatayna dawooda zabooran

Translation: 55. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በሰማያትና በምድር ያለውን ሁሉ አዋቂ ነው:: ከፊሉን ነብያት በከፊሉ ላይ አብልጠናል:: ዳውድንም ዘቡርን ሰጥተነዋል::

17:56

قُلِ ٱدۡعُواْ ٱلَّذِينَ زَعَمۡتُم مِّن دُونِهِۦ فَلَا يَمۡلِكُونَ كَشۡفَ ٱلضُّرِّ عَنكُمۡ وَلَا تَحۡوِيلًا ﴿56﴾

Transliteration: Quli odAAu allatheena zaAAamtum min doonihi fala yamlikoona kashfa alddurri AAankum wala tahweelan

Translation: 56. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በለቸው (ጣዖታዊያን ሆይ!) « እነዚያን ከእርሱ ሌላ አማልዕክት የምትሏቸውን እስቲ ጥሯቸው:: ከናንተም ላይ ጉዳትን ማስወገድን ወደ ሌላ ማዞርንም አይችሉም።»።

17:57

أُوْلَـٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ يَبۡتَغُونَ إِلَىٰ رَبِّهِمُ ٱلۡوَسِيلَةَ أَيُّهُمۡ أَقۡرَبُ وَيَرۡجُونَ رَحۡمَتَهُۥ وَيَخَافُونَ عَذَابَهُۥٓۚ إِنَّ عَذَابَ رَبِّكَ كَانَ مَحۡذُورٗا ﴿57﴾

Transliteration: Olaika allatheena yadAAoona yabtaghoona ila rabbihimu alwaseelata ayyuhum aqrabu wayarjoona rahmatahu wayakhafoona AAathabahu inna AAathaba rabbika kana mahthooran

Translation: 57. እነዚያ እነርሱ የሚገዟቸው ማንኛቸዉም (ወደ አላህ) በጣም ቀራቢያቸው እንኳን ለራሳቸው ወደ ጌታቸው መቃረቢያን ሥራ ይፈልጋሉ:: እዝነቱንም ይከጅላሉ:: ቅጣቱንም ይፈራሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህ ቅጣት የሚፈራ ነውና::

17:58

وَإِن مِّن قَرۡيَةٍ إِلَّا نَحۡنُ مُهۡلِكُوهَا قَبۡلَ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ أَوۡ مُعَذِّبُوهَا عَذَابٗا شَدِيدٗاۚ كَانَ ذَٰلِكَ فِي ٱلۡكِتَٰبِ مَسۡطُورٗا ﴿58﴾

Transliteration: Wain min qaryatin illa nahnu muhlikooha qabla yawmi alqiyamati aw muAAaththibooha AAathaban shadeedan kana thalika fee alkitabi mastooran

Translation: 58. አንዲትም ከተማ የለችም እኛ ከትንሳኤ ቀን በፊት አጥፊዎችዋ ወይም ብርቱን ቅጣት ቀጭዎችዋ ብንሆን እንጂ:: ይህም በመጽሐፍ የተጻፈ ነው::

17:59

وَمَا مَنَعَنَآ أَن نُّرۡسِلَ بِٱلۡأٓيَٰتِ إِلَّآ أَن كَذَّبَ بِهَا ٱلۡأَوَّلُونَۚ وَءَاتَيۡنَا ثَمُودَ ٱلنَّاقَةَ مُبۡصِرَةٗ فَظَلَمُواْ بِهَاۚ وَمَا نُرۡسِلُ بِٱلۡأٓيَٰتِ إِلَّا تَخۡوِيفٗا ﴿59﴾

Transliteration: Wama manaAAana an nursila bialayati illa an kaththaba biha alawwaloona waatayna thamooda alnnaqata mubsiratan fathalamoo biha wama nursilu bialayati illa takhweefan

Translation: 59. ተዓምራትን ከመላክ የቀድሞዎቹ ሰዎች በእርሷ ማስተባበልና መጥፋት እንጂ ሌላ አልከለከለንም። ለሠሙድም ግመልን ግልጽ ተዓምር ሆና ሰጠናቸው:: በእርሷም በደሉ፤ ተዓምራትንም ለማስፈራራት እንጂ አንልክም::

17:60

وَإِذۡ قُلۡنَا لَكَ إِنَّ رَبَّكَ أَحَاطَ بِٱلنَّاسِۚ وَمَا جَعَلۡنَا ٱلرُّءۡيَا ٱلَّتِيٓ أَرَيۡنَٰكَ إِلَّا فِتۡنَةٗ لِّلنَّاسِ وَٱلشَّجَرَةَ ٱلۡمَلۡعُونَةَ فِي ٱلۡقُرۡءَانِۚ وَنُخَوِّفُهُمۡ فَمَا يَزِيدُهُمۡ إِلَّا طُغۡيَٰنٗا كَبِيرٗا ﴿60﴾

Transliteration: Waith qulna laka inna rabbaka ahata bialnnasi wama jaAAalna alrruya allatee araynaka illa fitnatan lilnnasi waalshshajarata almalAAoonata fee alqurani wanukhawwifuhum fama yazeeduhum illa tughyanan kabeeran

Translation: 60. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ላንተም ጌታህ በእውቀቱ ሰዎችን ያካበበ መሆኑን በነገርንህ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: በሌሊቱ ጉዞ በዓይንህ ያሳየንህም ትርኢት ለሰዎች ፈተና እንጂ አላደረግነዉም:: በቁርኣንም የተረገመችውን ዛፍ እንደዚሁ ፈተና እንጂ አላደረግንም፤ እናስፈራራቸዋለንም፤ ትልቅንም ጥመት እንጂ አይጨምርላቸዉም::

17:61

وَإِذۡ قُلۡنَا لِلۡمَلَـٰٓئِكَةِ ٱسۡجُدُواْ لِأٓدَمَ فَسَجَدُوٓاْ إِلَّآ إِبۡلِيسَ قَالَ ءَأَسۡجُدُ لِمَنۡ خَلَقۡتَ طِينٗا ﴿61﴾

Transliteration: Waith qulna lilmalaikati osjudoo liadama fasajadoo illa ibleesa qala aasjudu liman khalaqta teenan

Translation: 61. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለመላዕክትም «ለአደም ስገዱ» ባልናቸው ጊዜ የነበረውን ሁኔታ አስታውስ:: ወዲያዉም ሰገዱ ዲያብሎስ ብቻ ሲቀር «ከጭቃ ለፈጠርከው ሰው እሰግዳለሁን?» አለ።

17:62

قَالَ أَرَءَيۡتَكَ هَٰذَا ٱلَّذِي كَرَّمۡتَ عَلَيَّ لَئِنۡ أَخَّرۡتَنِ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ لَأَحۡتَنِكَنَّ ذُرِّيَّتَهُۥٓ إِلَّا قَلِيلٗا ﴿62﴾

Transliteration: Qala araaytaka hatha allathee karramta AAalayya lain akhkhartani ila yawmi alqiyamati laahtanikanna thurriyyatahu illa qaleelan

Translation: 62. «እስቲ ንገረኝ ይህ ያ በእኔ ላይ ያበለጥከው ነውን? እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ብታቆየኝ ዘሮቹን ጥቂቶች ሲቀሩ ወደ ስህተት በእርግጥ እስባቸዋለሁ።» አለ።

17:63

قَالَ ٱذۡهَبۡ فَمَن تَبِعَكَ مِنۡهُمۡ فَإِنَّ جَهَنَّمَ جَزَآؤُكُمۡ جَزَآءٗ مَّوۡفُورٗا ﴿63﴾

Transliteration: Qala ithhab faman tabiAAaka minhum fainna jahannama jazaokum jazaan mawfooran

Translation: 63. አላህም አለው: «ሂድ ከእነርሱም የተከተለህ ገሀነም የተሟላች ቅጣት ስትሆን ፍዳችሁ ናት።

17:64

وَٱسۡتَفۡزِزۡ مَنِ ٱسۡتَطَعۡتَ مِنۡهُم بِصَوۡتِكَ وَأَجۡلِبۡ عَلَيۡهِم بِخَيۡلِكَ وَرَجِلِكَ وَشَارِكۡهُمۡ فِي ٱلۡأَمۡوَٰلِ وَٱلۡأَوۡلَٰدِ وَعِدۡهُمۡۚ وَمَا يَعِدُهُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ إِلَّا غُرُورًا ﴿64﴾

Transliteration: Waistafziz mani istataAAta minhum bisawtika waajlib AAalayhim bikhaylika warajlika washarikhum fee alamwali waalawladi waAAidhum wama yaAAiduhumu alshshaytanu illa ghurooran

Translation: 64. «ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምጽህ ገፋፋ:: በእነርሱም ላይ በፈረሰኞችህ በእግረኞችህም ሆነህ ለልብ (አውጅ)። በገንዘቦቻቸዉም በልጆቻቸዉም ተጋራቸው:: የተስፋ ቃልም ግባላቸው።» ሰይጣንም ማታለልን እንጂ ተስፋ ቃልን አይገባላቸዉም::

17:65

إِنَّ عِبَادِي لَيۡسَ لَكَ عَلَيۡهِمۡ سُلۡطَٰنٞۚ وَكَفَىٰ بِرَبِّكَ وَكِيلٗا ﴿65﴾

Transliteration: Inna AAibadee laysa laka AAalayhim sultanun wakafa birabbika wakeelan

Translation: 65. ንጹህ ባሮቼ ግን በእነርሱ ላይ ፈጽሞ ላንተ ስልጣን የለህም:: ዋስም በጌታህ በቃ።

17:66

رَّبُّكُمُ ٱلَّذِي يُزۡجِي لَكُمُ ٱلۡفُلۡكَ فِي ٱلۡبَحۡرِ لِتَبۡتَغُواْ مِن فَضۡلِهِۦٓۚ إِنَّهُۥ كَانَ بِكُمۡ رَحِيمٗا ﴿66﴾

Transliteration: Rabbukumu allathee yuzjee lakumu alfulka fee albahri litabtaghoo min fadlihi innahu kana bikum raheeman

Translation: 66. (ሰዎች ሆይ!) ጌታችሁ ያ ከችሮታው ትፈልጉ ዘንድ መርከቦችን በባህር ላይ ለእናንተ የሚነዳላችሁ ነው:: እነሆ እርሱ ለእናንተ አዛኝ ነውና::

17:67

وَإِذَا مَسَّكُمُ ٱلضُّرُّ فِي ٱلۡبَحۡرِ ضَلَّ مَن تَدۡعُونَ إِلَّآ إِيَّاهُۖ فَلَمَّا نَجَّىٰكُمۡ إِلَى ٱلۡبَرِّ أَعۡرَضۡتُمۡۚ وَكَانَ ٱلۡإِنسَٰنُ كَفُورًا ﴿67﴾

Transliteration: Waitha massakumu alddurru fee albahri dalla man tadAAoona illa iyyahu falamma najjakum ila albarri aAAradtum wakana alinsanu kafooran

Translation: 67. በባህሩ ውስጥ ሆናችሁ ጉዳት በደረሰባችሁ ጊዜ የምትጠሯቸው አማልክት ሁሉ ይጠፉባችሁና እርሱ አላህ ብቻ ይቀራል። ወደ የብስም በማድረስ ባዳናችሁ ጊዜ እምነትን ትተዋላችሁ:: ሰው ሲባል በጣም ከሓዲ ነውና::

17:68

أَفَأَمِنتُمۡ أَن يَخۡسِفَ بِكُمۡ جَانِبَ ٱلۡبَرِّ أَوۡ يُرۡسِلَ عَلَيۡكُمۡ حَاصِبٗا ثُمَّ لَا تَجِدُواْ لَكُمۡ وَكِيلًا ﴿68﴾

Transliteration: Afaamintum an yakhsifa bikum janiba albarri aw yursila AAalaykum hasiban thumma la tajidoo lakum wakeelan

Translation: 68. (ሰዎች ሆይ!) የየብሱን በኩል ምድርን በናንተ መገልበጡን ወይም ጠጠርን የያዘ ንፋስን በእናንተ ላይ መላኩን ከዚያም ለእናንተ ጠባቂ አለማግኘታችሁን አትፈሩምን?

17:69

أَمۡ أَمِنتُمۡ أَن يُعِيدَكُمۡ فِيهِ تَارَةً أُخۡرَىٰ فَيُرۡسِلَ عَلَيۡكُمۡ قَاصِفٗا مِّنَ ٱلرِّيحِ فَيُغۡرِقَكُم بِمَا كَفَرۡتُمۡ ثُمَّ لَا تَجِدُواْ لَكُمۡ عَلَيۡنَا بِهِۦ تَبِيعٗا ﴿69﴾

Transliteration: Am amintum an yuAAeedakum feehi taratan okhra fayursila AAalaykum qasifan mina alrreehi fayughriqakum bima kafartum thumma la tajidoo lakum AAalayna bihi tabeeAAan

Translation: 69. ወይስ ሌላ ጊዜ ወደ እርሱ (ወደ ባህር) የሚመልሳችሁ ወዲያውኑም በእናንተ ላይ ብርቱን ነፋስ የሚልክ፤ በክህደታችሁም ምክንያት የሚያሰምጣችሁ መሆኑን ከዚያም በእኛ ላይ በእርሱ ተከታይነት (ረዳትን) ለእናንተ የማታገኙ መሆናቸሁን አትፈሩምን?

17:70

وَلَقَدۡ كَرَّمۡنَا بَنِيٓ ءَادَمَ وَحَمَلۡنَٰهُمۡ فِي ٱلۡبَرِّ وَٱلۡبَحۡرِ وَرَزَقۡنَٰهُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَٰتِ وَفَضَّلۡنَٰهُمۡ عَلَىٰ كَثِيرٖ مِّمَّنۡ خَلَقۡنَا تَفۡضِيلٗا ﴿70﴾

Transliteration: Walaqad karramna banee adama wahamalnahum fee albarri waalbahri warazaqnahum mina alttayyibati wafaddalnahum AAala katheerin mimman khalaqna tafdeelan

Translation: 70. የአደምን ልጆች በእርግጥ ከሌላው ፍጡር አከበርናቸው:: በየብስና በባህርም አሳፈርናቸው:: ከመልካሞችም ሲሳዮችም ሰጠናቸው፤ ከፈጠርናቸው ፍጡራንም በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጥናቸው::

17:71

يَوۡمَ نَدۡعُواْ كُلَّ أُنَاسِۭ بِإِمَٰمِهِمۡۖ فَمَنۡ أُوتِيَ كِتَٰبَهُۥ بِيَمِينِهِۦ فَأُوْلَـٰٓئِكَ يَقۡرَءُونَ كِتَٰبَهُمۡ وَلَا يُظۡلَمُونَ فَتِيلٗا ﴿71﴾

Transliteration: Yawma nadAAoo kulla onasin biimamihim faman ootiya kitabahu biyameenihi faolaika yaqraoona kitabahum wala yuthlamoona fateelan

Translation: 71. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰዎችን ሁሉ በመሪያቸው የምንጠራበትን ቀን አስታውስ። ያ መጽሐፉንም በቀኙ የተሰጠ ሰው እነዚያ መጽሐፋቸውን ያነባሉ፤ በተምር ፍሬ ስንጥቅ ላይ ያለውን ክር ያክል እንኳን አይበደሉም::

17:72

وَمَن كَانَ فِي هَٰذِهِۦٓ أَعۡمَىٰ فَهُوَ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ أَعۡمَىٰ وَأَضَلُّ سَبِيلٗا ﴿72﴾

Transliteration: Waman kana fee hathihi aAAma fahuwa fee alakhirati aAAma waadallu sabeelan

Translation: 72. በዚህች ዓለም ልበ እውር የሆነ ሰው ሁሉ እርሱ በመጨረሻይቱም ዓለም እውር ነው:: መንገድንም በጣም የተሳሳተ ነው::

17:73

وَإِن كَادُواْ لَيَفۡتِنُونَكَ عَنِ ٱلَّذِيٓ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ لِتَفۡتَرِيَ عَلَيۡنَا غَيۡرَهُۥۖ وَإِذٗا لَّٱتَّخَذُوكَ خَلِيلٗا ﴿73﴾

Transliteration: Wain kadoo layaftinoonaka AAani allathee awhayna ilayka litaftariya AAalayna ghayrahu waithan laittakhathooka khaleelan

Translation: 73. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነሆ ከዚያም ወደ አንተ ካወረድነው ሌላን በእኛ ላይ ትዋሽ ዘንድ ሊፈትኑህ በእርግጥ ተቃረቡ፤ ያን ጊዜም ወዳጅ አድርገው በያዙህ ነበር::

17:74

وَلَوۡلَآ أَن ثَبَّتۡنَٰكَ لَقَدۡ كِدتَّ تَرۡكَنُ إِلَيۡهِمۡ شَيۡـٔٗا قَلِيلًا ﴿74﴾

Transliteration: Walawla an thabbatnaka laqad kidta tarkanu ilayhim shayan qaleelan

Translation: 74.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ባላረጋጋንህም ኖሮ ወደ እነርሱ ጥቂትን ዝንባሌ ልትዘነበል በእርግጥ በተቃረብክ ነበር::

17:75

إِذٗا لَّأَذَقۡنَٰكَ ضِعۡفَ ٱلۡحَيَوٰةِ وَضِعۡفَ ٱلۡمَمَاتِ ثُمَّ لَا تَجِدُ لَكَ عَلَيۡنَا نَصِيرٗا ﴿75﴾

Transliteration: Ithan laathaqnaka diAAfa alhayati wadiAAfa almamati thumma la tajidu laka AAalayna naseeran

Translation: 75. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያን ጊዜ የሕይወትን ሆነ የሞትን ድርብ ቅጣት እናቀምስህ ነበር:: ከዚያም ላንተ በእኛ ላይ ረዳትን አታገኝም ነበር::

17:76

وَإِن كَادُواْ لَيَسۡتَفِزُّونَكَ مِنَ ٱلۡأَرۡضِ لِيُخۡرِجُوكَ مِنۡهَاۖ وَإِذٗا لَّا يَلۡبَثُونَ خِلَٰفَكَ إِلَّا قَلِيلٗا ﴿76﴾

Transliteration: Wain kadoo layastafizzoonaka mina alardi liyukhrijooka minha waithan la yalbathoona khilafaka illa qaleelan

Translation: 76. ከምድሪቱ (ከዓረብ) ምድር ከእርሷ ያወጡህ ዘንድ ሊያሸብሩህ በእርግጥ ተቃረቡ:: ያን ጊዜም ካንተ በኋላ ጥቂትን ጊዜ እንጂ አይቆዩም ነበር::

17:77

سُنَّةَ مَن قَدۡ أَرۡسَلۡنَا قَبۡلَكَ مِن رُّسُلِنَاۖ وَلَا تَجِدُ لِسُنَّتِنَا تَحۡوِيلًا ﴿77﴾

Transliteration: Sunnata man qad arsalna qablaka min rusulina wala tajidu lisunnatina tahweelan

Translation: 77. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞቻችን ካንተ በፊት በእርግጥ እንደ ላክናቸው ሰዎች ልማድ ብጤ ይጠፋ ነበር፤ ለልማዳችንም መለወጥን አታገኝም (አይለወጥም)።

17:78

أَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ لِدُلُوكِ ٱلشَّمۡسِ إِلَىٰ غَسَقِ ٱلَّيۡلِ وَقُرۡءَانَ ٱلۡفَجۡرِۖ إِنَّ قُرۡءَانَ ٱلۡفَجۡرِ كَانَ مَشۡهُودٗا ﴿78﴾

Transliteration: Aqimi alssalata lidulooki alshshamsi ila ghasaqi allayli waqurana alfajri inna qurana alfajri kana mashhoodan

Translation: 78. ሶላትን ከጸሐይ መዘንበል እስከ ሌሊት ጨለማ ድረስ ስገድ:: የጎህንም ሶላት ስገድ:: የጎህ ሶላት መላዕክት የሚገኙበት ነውና::

17:79

وَمِنَ ٱلَّيۡلِ فَتَهَجَّدۡ بِهِۦ نَافِلَةٗ لَّكَ عَسَىٰٓ أَن يَبۡعَثَكَ رَبُّكَ مَقَامٗا مَّحۡمُودٗا ﴿79﴾

Transliteration: Wamina allayli fatahajjad bihi nafilatan laka AAasa an yabAAathaka rabbuka maqaman mahmoodan

Translation: 79. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሌሊት ላንተ ተጨማሪ የሆነችን ሶላት በቁርኣን ስገድ:: ጌታህ ምስጉን በሆነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃልና::

17:80

وَقُل رَّبِّ أَدۡخِلۡنِي مُدۡخَلَ صِدۡقٖ وَأَخۡرِجۡنِي مُخۡرَجَ صِدۡقٖ وَٱجۡعَل لِّي مِن لَّدُنكَ سُلۡطَٰنٗا نَّصِيرٗا ﴿80﴾

Transliteration: Waqul rabbi adkhilnee mudkhala sidqin waakhrijnee mukhraja sidqin waijAAal lee min ladunka sultanan naseeran

Translation: 80. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በልም: «ጌታዬ ሆይ! የተወደደን መግባት አስገባኝ፤ የተወደደንም መውጣት አስወጣኝ:: ለእኔም ካንተ ዘንድ የተረዳን ስልጣን አድርግልኝ።»

17:81

وَقُلۡ جَآءَ ٱلۡحَقُّ وَزَهَقَ ٱلۡبَٰطِلُۚ إِنَّ ٱلۡبَٰطِلَ كَانَ زَهُوقٗا ﴿81﴾

Transliteration: Waqul jaa alhaqqu wazahaqa albatilu inna albatila kana zahooqan

Translation: 81. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና።» በል።

17:82

وَنُنَزِّلُ مِنَ ٱلۡقُرۡءَانِ مَا هُوَ شِفَآءٞ وَرَحۡمَةٞ لِّلۡمُؤۡمِنِينَ وَلَا يَزِيدُ ٱلظَّـٰلِمِينَ إِلَّا خَسَارٗا ﴿82﴾

Transliteration: Wanunazzilu mina alqurani ma huwa shifaon warahmatun lilmumineena wala yazeedu alththalimeena illa khasaran

Translation: 82. ከቁርኣን ለአማኞች መድሓኒትና እዝነት የሆነን እናወርዳለን በዳዮችንም ኪሳራን እንጂ ሌላ አይጨምርላቸዉም::

17:83

وَإِذَآ أَنۡعَمۡنَا عَلَى ٱلۡإِنسَٰنِ أَعۡرَضَ وَنَـَٔا بِجَانِبِهِۦ وَإِذَا مَسَّهُ ٱلشَّرُّ كَانَ يَـُٔوسٗا ﴿83﴾

Transliteration: Waitha anAAamna AAala alinsani aAArada wanaa bijanibihi waitha massahu alshsharru kana yaoosan

Translation: 83. በሰዉም ላይ ጸጋችንን በለገስን ጊዜ ከምስጋና ይዞራል ጎኑንም ከእውነት ያርቃል:: ችግርም በነካው ጊዜ ተስፋ ቆራጭ ይሆናል::

17:84

قُلۡ كُلّٞ يَعۡمَلُ عَلَىٰ شَاكِلَتِهِۦ فَرَبُّكُمۡ أَعۡلَمُ بِمَنۡ هُوَ أَهۡدَىٰ سَبِيلٗا ﴿84﴾

Transliteration: Qul kullun yaAAmalu AAala shakilatihi farabbukum aAAlamu biman huwa ahda sabeelan

Translation: 84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሁሉም በሚመስለው መንገድ ላይ ይሠራል:: ጌታችሁም እርሱ መንገዱ ቀጥተኛ የሆነውን አዋቂ ነው።» በላቸው።

17:85

وَيَسۡـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلرُّوحِۖ قُلِ ٱلرُّوحُ مِنۡ أَمۡرِ رَبِّي وَمَآ أُوتِيتُم مِّنَ ٱلۡعِلۡمِ إِلَّا قَلِيلٗا ﴿85﴾

Transliteration: Wayasaloonaka AAani alrroohi quli alrroohu min amri rabbee wama ooteetum mina alAAilmi illa qaleelan

Translation: 85. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያን ከሩህ ይጠይቁሃል። «ሩህ ከጌታዬ ነገር ነው:: ከእውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም።» በላቸው::

17:86

وَلَئِن شِئۡنَا لَنَذۡهَبَنَّ بِٱلَّذِيٓ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ ثُمَّ لَا تَجِدُ لَكَ بِهِۦ عَلَيۡنَا وَكِيلًا ﴿86﴾

Transliteration: Walain shina lanathhabanna biallathee awhayna ilayka thumma la tajidu laka bihi AAalayna wakeelan

Translation: 86. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ብንሻ ያንን ወደ አንተ ያወረድነውን በእርግጥ እንወስድብሃለን:: ከዚያም ላንተ በእኛ ላይ በእርሱ ለማስመለስ ተያዢን አታገኝም::

17:87

إِلَّا رَحۡمَةٗ مِّن رَّبِّكَۚ إِنَّ فَضۡلَهُۥ كَانَ عَلَيۡكَ كَبِيرٗا ﴿87﴾

Transliteration: Illa rahmatan min rabbika inna fadlahu kana AAalayka kabeeran

Translation: 87. ግን ከጌታህ በሆነው እዝነት ጠበቅነው:: ችሮታው ባንተ ላይ ታላቅ ነውና::

17:88

قُل لَّئِنِ ٱجۡتَمَعَتِ ٱلۡإِنسُ وَٱلۡجِنُّ عَلَىٰٓ أَن يَأۡتُواْ بِمِثۡلِ هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانِ لَا يَأۡتُونَ بِمِثۡلِهِۦ وَلَوۡ كَانَ بَعۡضُهُمۡ لِبَعۡضٖ ظَهِيرٗا ﴿88﴾

Transliteration: Qul laini ijtamaAAati alinsu waaljinnu AAala an yatoo bimithli hatha alqurani la yatoona bimithlihi walaw kana baAAduhum libaAAdin thaheeran

Translation: 88. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎችና ጋኔኖች የዚህን ቁርኣን ቢጤ በማምጣት ላይ ቢሰበሰቡና ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳት ቢሆኑም እንኳ ብጤውን አያመጡም።» በላቸው።

17:89

وَلَقَدۡ صَرَّفۡنَا لِلنَّاسِ فِي هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانِ مِن كُلِّ مَثَلٖ فَأَبَىٰٓ أَكۡثَرُ ٱلنَّاسِ إِلَّا كُفُورٗا ﴿89﴾

Transliteration: Walaqad sarrafna lilnnasi fee hatha alqurani min kulli mathalin faaba aktharu alnnasi illa kufooran

Translation: 89. በዚህም ቁርኣን ውስጥ ከምሳሌው ሁሉ ለሰዎች በእርግጥ መላልሰን አብራራን:: አብዛኞቹም ሰዎች ክህደትን እንጂ ሌላን እምቢ አሉ::

17:90

وَقَالُواْ لَن نُّؤۡمِنَ لَكَ حَتَّىٰ تَفۡجُرَ لَنَا مِنَ ٱلۡأَرۡضِ يَنۢبُوعًا ﴿90﴾

Transliteration: Waqaloo lan numina laka hatta tafjura lana mina alardi yanbooAAan

Translation: 90. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አሉም: «ለእኛ ከምድር ምንጭን እስከምታፈልቅልን ድረስ ላንተ አናምንም።

17:91

أَوۡ تَكُونَ لَكَ جَنَّةٞ مِّن نَّخِيلٖ وَعِنَبٖ فَتُفَجِّرَ ٱلۡأَنۡهَٰرَ خِلَٰلَهَا تَفۡجِيرًا ﴿91﴾

Transliteration: Aw takoona laka jannatun min nakheelin waAAinabin fatufajjira alanhara khilalaha tafjeeran

Translation: 91. «ወይም ከዘንባባዎችና ከወይን የሆነች አትክልት ላንተ እስከምትኖርህና በመካከሏም ጅረቶችን በብዛት እስከምታንቧቧ ድረስ

17:92

أَوۡ تُسۡقِطَ ٱلسَّمَآءَ كَمَا زَعَمۡتَ عَلَيۡنَا كِسَفًا أَوۡ تَأۡتِيَ بِٱللَّهِ وَٱلۡمَلَـٰٓئِكَةِ قَبِيلًا ﴿92﴾

Transliteration: Aw tusqita alssamaa kama zaAAamta AAalayna kisafan aw tatiya biAllahi waalmalaikati qabeelan

Translation: 92. «ወይም እንደምትለው ከሰማይ ቁራጮችን በእኛ ላይ እስከምታወርድ ወይም አላህንና መላዕክትን በግልጽ እስከምታመጣ ድረስ

17:93

أَوۡ يَكُونَ لَكَ بَيۡتٞ مِّن زُخۡرُفٍ أَوۡ تَرۡقَىٰ فِي ٱلسَّمَآءِ وَلَن نُّؤۡمِنَ لِرُقِيِّكَ حَتَّىٰ تُنَزِّلَ عَلَيۡنَا كِتَٰبٗا نَّقۡرَؤُهُۥۗ قُلۡ سُبۡحَانَ رَبِّي هَلۡ كُنتُ إِلَّا بَشَرٗا رَّسُولٗا ﴿93﴾

Transliteration: Aw yakoona laka baytun min zukhrufin aw tarqa fee alssamai walan numina liruqiyyika hatta tunazzila AAalayna kitaban naqraohu qul subhana rabbee hal kuntu illa basharan rasoolan

Translation: 93 «ወይም ከወርቅ የሆነ ቤት ላንተ እስከሚኖርህ ወይም በሰማይ እስከምትወጣ፤ ለመውጣትህም በእኛ ላይ የምናነበው የሆነን መጽሐፍ እስከምታወርድልን ድረስ ፈጽሞ አናምንልህም።» አሉ:: «ጌታዬ ጥራት ይገባው:: እኔ መልዕክተኛ (የሆንኩ) ሰው እንጂ ሌላ ነገር ነኝ እንዴ?!» በላቸው::

17:94

وَمَا مَنَعَ ٱلنَّاسَ أَن يُؤۡمِنُوٓاْ إِذۡ جَآءَهُمُ ٱلۡهُدَىٰٓ إِلَّآ أَن قَالُوٓاْ أَبَعَثَ ٱللَّهُ بَشَرٗا رَّسُولٗا ﴿94﴾

Transliteration: Wama manaAAa alnnasa an yuminoo ith jaahumu alhuda illa an qaloo abaAAatha Allahu basharan rasoolan

Translation: 94. ሰዎችን መሪ ቁርኣን በመጣላቸው ጊዜ በሱ ከማመን «አላህ ሰውን መልዕክተኛ አድርጎ ላከን?» ማለታቸው ብቻ እንጂ ሌላ አልከለከላቸዉም።

17:95

قُل لَّوۡ كَانَ فِي ٱلۡأَرۡضِ مَلَـٰٓئِكَةٞ يَمۡشُونَ مُطۡمَئِنِّينَ لَنَزَّلۡنَا عَلَيۡهِم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ مَلَكٗا رَّسُولٗا ﴿95﴾

Transliteration: Qul law kana fee alardi malaikatun yamshoona mutmainneena lanazzalna AAalayhim mina alssamai malakan rasoolan

Translation: 95. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በምድር ላይ ተረጋግተው የሚጓዙ መላእክት ቢኖሩ ኑሮ ከሰማይ የመልአክ መልዕክተኛ እናወርድላቸው እንደነበር ንገራቸው።

17:96

قُلۡ كَفَىٰ بِٱللَّهِ شَهِيدَۢا بَيۡنِي وَبَيۡنَكُمۡۚ إِنَّهُۥ كَانَ بِعِبَادِهِۦ خَبِيرَۢا بَصِيرٗا ﴿96﴾

Transliteration: Qul kafa biAllahi shaheedan baynee wabaynakum innahu kana biAAibadihi khabeeran baseeran

Translation: 96. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእኔና በእናንተ መካከል ላለን ልዩነት መስካሪ በአላህ በቃ:: ምክኒያቱም እርሱ ባሮቹን ጠንቅቆ አዋቂና ተመልካች ነውና።» በላቸው።

17:97

وَمَن يَهۡدِ ٱللَّهُ فَهُوَ ٱلۡمُهۡتَدِۖ وَمَن يُضۡلِلۡ فَلَن تَجِدَ لَهُمۡ أَوۡلِيَآءَ مِن دُونِهِۦۖ وَنَحۡشُرُهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ عَلَىٰ وُجُوهِهِمۡ عُمۡيٗا وَبُكۡمٗا وَصُمّٗاۖ مَّأۡوَىٰهُمۡ جَهَنَّمُۖ كُلَّمَا خَبَتۡ زِدۡنَٰهُمۡ سَعِيرٗا ﴿97﴾

Transliteration: Waman yahdi Allahu fahuwa almuhtadi waman yudlil falan tajida lahum awliyaa min doonihi wanahshuruhum yawma alqiyamati AAala wujoohihim AAumyan wabukman wasumman mawahum jahannamu kullama khabat zidnahum saAAeeran

Translation: 97. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ያቀናው በእርግጥም የተቀና ማለት እርሱው ነው:: እርሱ ያጠመማቸውን ግን ከቅጣቱ የሚያድናቸው ማንም ወዳጅ አታገኝላቸዉም:: የትንሳኤ ቀንም እውር፤ ዲዳና፤ ደንቆሮ አድርገን በፊቶቻቸው እየተጎተቱ እንሰበስባቸዋለን:: መኖሪያቸዉም ገሀነም ናት:: ሀይሏ በደከመ ጊዜም ግለትን እንጨምርላቸዋለን::

17:98

ذَٰلِكَ جَزَآؤُهُم بِأَنَّهُمۡ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَقَالُوٓاْ أَءِذَا كُنَّا عِظَٰمٗا وَرُفَٰتًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ خَلۡقٗا جَدِيدًا ﴿98﴾

Transliteration: Thalika jazaohum biannahum kafaroo biayatina waqaloo aitha kunna AAithaman warufatan ainna lamabAAoothoona khalqan jadeedan

Translation: 98. ይህ ቅጣት የሚጠብቃቸው ቅጣታቸው ነው:: ምክንያቱም በመልዕክተኞቻችን ክደው «የበሰበሰ አጥንት ከሆንና (ወደ አቧራነት) ከተቀየርን በኋላ እንደ አዲስ እንቀሰቀሳለን?» በማለታቸውም ነው።

17:99

أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ أَنَّ ٱللَّهَ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ قَادِرٌ عَلَىٰٓ أَن يَخۡلُقَ مِثۡلَهُمۡ وَجَعَلَ لَهُمۡ أَجَلٗا لَّا رَيۡبَ فِيهِ فَأَبَى ٱلظَّـٰلِمُونَ إِلَّا كُفُورٗا ﴿99﴾

Transliteration: Awalam yaraw anna Allaha allathee khalaqa alssamawati waalarda qadirun AAala an yakhluqa mithlahum wajaAAala lahum ajalan la rayba feehi faaba alththalimoona illa kufooran

Translation: 99. ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ አላህ ብጤያቸውን በመፍጠር ላይ ቻይ መሆኑን በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበትንም ጊዜ ለሞትም ለትንሳኤም ለእነርሱ የወሰነ መሆኑን አላወቁምን? በደለኞችም ከክህደት በስተቀር እምቢ አሉ::

17:100

قُل لَّوۡ أَنتُمۡ تَمۡلِكُونَ خَزَآئِنَ رَحۡمَةِ رَبِّيٓ إِذٗا لَّأَمۡسَكۡتُمۡ خَشۡيَةَ ٱلۡإِنفَاقِۚ وَكَانَ ٱلۡإِنسَٰنُ قَتُورٗا ﴿100﴾

Transliteration: Qul law antum tamlikoona khazaina rahmati rabbee ithan laamsaktum khashyata alinfaqi wakana alinsanu qatooran

Translation: 100. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ የጌታዬን የችሮታ መካዚኖች ብትይዙ ኖሮ ያን ጊዜ በማውጣታችሁ ማለቋን በመፍራት በጨበጣችሁ ነበር:: ሰው በጣም ንፉግ ነውና።» በላቸው።

17:101

وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَىٰ تِسۡعَ ءَايَٰتِۭ بَيِّنَٰتٖۖ فَسۡـَٔلۡ بَنِيٓ إِسۡرَـٰٓءِيلَ إِذۡ جَآءَهُمۡ فَقَالَ لَهُۥ فِرۡعَوۡنُ إِنِّي لَأَظُنُّكَ يَٰمُوسَىٰ مَسۡحُورٗا ﴿101﴾

Transliteration: Walaqad atayna moosa tisAAa ayatin bayyinatin faisal banee israeela ith jaahum faqala lahu firAAawnu innee laathunnuka ya moosa mashooran

Translation: 101. ለሙሳ ግልጽ የሆኑን ዘጠኝ ተዓምራት በእርግጥ ሰጠነው:: በመጣቸዉም ጊዜ የኢስራኢልን ልጆች ከፈርዖን እንዲለቀቁ ጠይቅ አልነው:: ፈርዖንም፡- «ሙሳ ሆይ! እኔ የተደገመብህ መሆንህን በእርግጥ እጠረጥርሃለሁ።» አለው።

17:102

قَالَ لَقَدۡ عَلِمۡتَ مَآ أَنزَلَ هَـٰٓؤُلَآءِ إِلَّا رَبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ بَصَآئِرَ وَإِنِّي لَأَظُنُّكَ يَٰفِرۡعَوۡنُ مَثۡبُورٗا ﴿102﴾

Transliteration: Qala laqad AAalimta ma anzala haolai illa rabbu alssamawati waalardi basaira wainnee laathunnuka ya firAAawnu mathbooran

Translation: 102. ሙሳም፡- «እነዚህን ተዓምራት መግሰጫዎች ሲሆኑ የሰማያትና የምድር ጌታ እንጂ ሌላ እንዳላወረዳቸው በእርግጥ አውቀሀል:: እኔም ፈርዖን ሆይ! የምትጠፋ መሆንህን በእርግጥ እጠረጥርሃለሁ።» አለው።

17:103

فَأَرَادَ أَن يَسۡتَفِزَّهُم مِّنَ ٱلۡأَرۡضِ فَأَغۡرَقۡنَٰهُ وَمَن مَّعَهُۥ جَمِيعٗا ﴿103﴾

Transliteration: Faarada an yastafizzahum mina alardi faaghraqnahu waman maAAahu jameeAAan

Translation: 103. ከምድርም ሊያባርራቸው አሰበ:: እርሱንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ሁሉንም አሰመጥናቸው::

17:104

وَقُلۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِۦ لِبَنِيٓ إِسۡرَـٰٓءِيلَ ٱسۡكُنُواْ ٱلۡأَرۡضَ فَإِذَا جَآءَ وَعۡدُ ٱلۡأٓخِرَةِ جِئۡنَا بِكُمۡ لَفِيفٗا ﴿104﴾

Transliteration: Waqulna min baAAdihi libanee israeela oskunoo alarda faitha jaa waAAdu alakhirati jina bikum lafeefan

Translation: 104. ከእርሱም በኋላ ለኢስራኢል ልጆች «ምድሪቱን ተቀመጡባት:: የኋለኛይቱም ሰዓት ቀጠሮ በመጣ ጊዜ እናንተን የተከማቻችሁ ስትሆኑ እናመጣችኋለን።» አልናቸው።

17:105

وَبِٱلۡحَقِّ أَنزَلۡنَٰهُ وَبِٱلۡحَقِّ نَزَلَۗ وَمَآ أَرۡسَلۡنَٰكَ إِلَّا مُبَشِّرٗا وَنَذِيرٗا ﴿105﴾

Transliteration: Wabialhaqqi anzalnahu wabialhaqqi nazala wama arsalnaka illa mubashshiran wanatheeran

Translation: 105. ቁርኣንን በእውነትም አወረድነው:: በእውነትም ወረደ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተንም አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን እንጂ አልላክንህም::

17:106

وَقُرۡءَانٗا فَرَقۡنَٰهُ لِتَقۡرَأَهُۥ عَلَى ٱلنَّاسِ عَلَىٰ مُكۡثٖ وَنَزَّلۡنَٰهُ تَنزِيلٗا ﴿106﴾

Transliteration: Waquranan faraqnahu litaqraahu AAala alnnasi AAala mukthin wanazzalnahu tanzeelan

Translation: 106. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቁርኣንንም በሰዎች ላይ ሁነህ በዝግታ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው:: ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው::

17:107

قُلۡ ءَامِنُواْ بِهِۦٓ أَوۡ لَا تُؤۡمِنُوٓاْۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡعِلۡمَ مِن قَبۡلِهِۦٓ إِذَا يُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ يَخِرُّونَۤ لِلۡأَذۡقَانِۤ سُجَّدٗاۤ ﴿107﴾

Transliteration: Qul aminoo bihi aw la tuminoo inna allatheena ootoo alAAilma min qablihi itha yutla AAalayhim yakhirroona lilathqani sujjadan

Translation: 107. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርሱ እመኑ ወይም አትመኑ።» በላቸው:: እነዚያ ከእርሱ በፊት እውቀትን የተሰጡት በእነርሱ ላይ በተነበበ ጊዜ ሰጋጆች ሆነው በሸንጎበቶቻቸው ላይ ይወድቃሉ::

17:108

وَيَقُولُونَ سُبۡحَٰنَ رَبِّنَآ إِن كَانَ وَعۡدُ رَبِّنَا لَمَفۡعُولٗا ﴿108﴾

Transliteration: Wayaqooloona subhana rabbina in kana waAAdu rabbina lamafAAoolan

Translation: 108. ይላሉም: «ጌታችን ጥራት ይገባው። እነሆ የጌታችን ተስፋ ተፈጻሚ ነው።» ይላሉ።

17:109

وَيَخِرُّونَ لِلۡأَذۡقَانِ يَبۡكُونَ وَيَزِيدُهُمۡ خُشُوعٗا۩ ﴿109﴾

Transliteration: Wayakhirroona lilathqani yabkoona wayazeeduhum khushooAAan

Translation: 109. እያለቀሱም በአሸንጎበቶቻቸው (በአገጮቻቸው) ላይ ይወድቃሉ:: አላህም ፍርሃትን ይጨምርላቸዋል::{1}

17:110

قُلِ ٱدۡعُواْ ٱللَّهَ أَوِ ٱدۡعُواْ ٱلرَّحۡمَٰنَۖ أَيّٗا مَّا تَدۡعُواْ فَلَهُ ٱلۡأَسۡمَآءُ ٱلۡحُسۡنَىٰۚ وَلَا تَجۡهَرۡ بِصَلَاتِكَ وَلَا تُخَافِتۡ بِهَا وَٱبۡتَغِ بَيۡنَ ذَٰلِكَ سَبِيلٗا ﴿110﴾

Transliteration: Quli odAAoo Allaha awi odAAoo alrrahmana ayyan ma tadAAoo falahu alasmao alhusna wala tajhar bisalatika wala tukhafit biha waibtaghi bayna thalika sabeelan

Translation: 110. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህን ጥሩ ወይም አር-ረህማንን ጥሩ:: ማንኛውንም ስም ብትጠሩ መልካም ነው:: ለእርሱ ብዙ መልካም ስሞች አሉትና።» በላቸው። በስግደትህም ስታነብ በጣም ድምጽህን አትጩህ:: በእርሷም በጣም ድምጽህን ዝቅ አታድርግ:: በሁለቱ መካከል የሆነ መንገድን ፈልግ::

17:111

وَقُلِ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِي لَمۡ يَتَّخِذۡ وَلَدٗا وَلَمۡ يَكُن لَّهُۥ شَرِيكٞ فِي ٱلۡمُلۡكِ وَلَمۡ يَكُن لَّهُۥ وَلِيّٞ مِّنَ ٱلذُّلِّۖ وَكَبِّرۡهُ تَكۡبِيرَۢا ﴿111﴾

Transliteration: Waquli alhamdu lillahi allathee lam yattakhith waladan walam yakun lahu shareekun fee almulki walam yakun lahu waliyyun mina alththulli wakabbirhu takbeeran

Translation: 111. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ምስጋና ሁሉ ለዚያ ልጅን ላልያዘው ለእርሱም በንግስናው ተጋሪ ለሌለው ለእርሱም ከውርደት የሚያድነው ወዳጅ ለሌለው ለአላህ ብቻ ይገባው።» በል። እርሱን ማክበርንም አክብረው።

Transliteration source: English Transliteration by Tanzil. Used under Tanzil's non-commercial terms; see the source and latest updates at Tanzil. Tanzil translation download