quranm◉

Surah Al-Kahf transliteration

◉ ሱራ · ∞

18:1

ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِيٓ أَنزَلَ عَلَىٰ عَبۡدِهِ ٱلۡكِتَٰبَ وَلَمۡ يَجۡعَل لَّهُۥ عِوَجَاۜ ﴿1﴾

Transliteration: Alhamdu lillahi allathee anzala AAala AAabdihi alkitaba walam yajAAal lahu AAiwajan

Translation: 1-ምስጋና ሁሉ ለዚያ መጽሐፉን በውስጡ ቅንጣት መጣመምን ሳያደርግ በባሪያው (በሙሐመድ) ላይ ላወረደው ለአላህ ብቻ ይገባው::

18:2

قَيِّمٗا لِّيُنذِرَ بَأۡسٗا شَدِيدٗا مِّن لَّدُنۡهُ وَيُبَشِّرَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ٱلَّذِينَ يَعۡمَلُونَ ٱلصَّـٰلِحَٰتِ أَنَّ لَهُمۡ أَجۡرًا حَسَنٗا ﴿2﴾

Transliteration: Qayyiman liyunthira basan shadeedan min ladunhu wayubashshira almumineena allatheena yaAAmaloona alssalihati anna lahum ajran hasanan

Translation: 2. ቀጥተኛ ሲሆን ከርሱ ዘንድ የሆነን ብርቱን ቅጣት ሊያስፈራራበት፤ እነዚያንም በጎ ሰሪዎችን ለእነርሱ መልካም ምንዳ ያላቸው መሆኑን ሊያበስርበት (አወረደው)።

18:3

مَّـٰكِثِينَ فِيهِ أَبَدٗا ﴿3﴾

Transliteration: Makitheena feehi abadan

Translation: 3. በውስጡም ዘለዓለም የሚቆዩ መሆናቸውን ሊያበስርበት አወረደው።

18:4

وَيُنذِرَ ٱلَّذِينَ قَالُواْ ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ وَلَدٗا ﴿4﴾

Transliteration: Wayunthira allatheena qaloo ittakhatha Allahu waladan

Translation: 4. እነዚያንም «አላህ ልጅን ይዟል።» ያሉትን ሊያስፈራራበት (ቁርኣንን አወረደው።)

18:5

مَّا لَهُم بِهِۦ مِنۡ عِلۡمٖ وَلَا لِأٓبَآئِهِمۡۚ كَبُرَتۡ كَلِمَةٗ تَخۡرُجُ مِنۡ أَفۡوَٰهِهِمۡۚ إِن يَقُولُونَ إِلَّا كَذِبٗا ﴿5﴾

Transliteration: Ma lahum bihi min AAilmin wala liabaihim kaburat kalimatan takhruju min afwahihim in yaqooloona illa kathiban

Translation: 5.ለእነርሱም ሆነ ለአባቶቻቸው ስለ አላህ ልጅ መኖር ምንም እውቀት የላቸዉም:: ከአፎቻቸው የሚወጣው ቃል ምን አከበደው! ውሸትን እንጂ ሌላን አይናገሩም::

18:6

فَلَعَلَّكَ بَٰخِعٞ نَّفۡسَكَ عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِمۡ إِن لَّمۡ يُؤۡمِنُواْ بِهَٰذَا ٱلۡحَدِيثِ أَسَفًا ﴿6﴾

Transliteration: FalaAAallaka bakhiAAun nafsaka AAala atharihim in lam yuminoo bihatha alhadeethi asafan

Translation: 6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዚህም ንግግር በቁርኣን ካላመኑ በፈለጎቻቸው ላይ በቁጭት ነፍስህን አጥፊ ልትሆን ይፈራልሀል::

18:7

إِنَّا جَعَلۡنَا مَا عَلَى ٱلۡأَرۡضِ زِينَةٗ لَّهَا لِنَبۡلُوَهُمۡ أَيُّهُمۡ أَحۡسَنُ عَمَلٗا ﴿7﴾

Transliteration: Inna jaAAalna ma AAala alardi zeenatan laha linabluwahum ayyuhum ahsanu AAamalan

Translation: 7.እኛ ማንኛቸው ሥራው ያማረ መሆኑን ልንፈትናቸው በምድር ላይ ያለን ሁሉ የእርሷ ጌጥ አደረግን::

18:8

وَإِنَّا لَجَٰعِلُونَ مَا عَلَيۡهَا صَعِيدٗا جُرُزًا ﴿8﴾

Transliteration: Wainna lajaAAiloona ma AAalayha saAAeedan juruzan

Translation: 8. እኛ በእርሷ ላይ ያለውን ሁሉ በመጨረሻ ቡቃያ የሌለበት ምልጥ አፈር አድራጊዎች ነን::

18:9

أَمۡ حَسِبۡتَ أَنَّ أَصۡحَٰبَ ٱلۡكَهۡفِ وَٱلرَّقِيمِ كَانُواْ مِنۡ ءَايَٰتِنَا عَجَبًا ﴿9﴾

Transliteration: Am hasibta anna ashaba alkahfi waalrraqeemi kanoo min ayatina AAajaban

Translation: 9-(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዋሻውና የሰሌዳው ባለቤቶች ከተዓምራታችን ሲሆኑ ግሩም መሆናቸውን አሰብክን?

18:10

إِذۡ أَوَى ٱلۡفِتۡيَةُ إِلَى ٱلۡكَهۡفِ فَقَالُواْ رَبَّنَآ ءَاتِنَا مِن لَّدُنكَ رَحۡمَةٗ وَهَيِّئۡ لَنَا مِنۡ أَمۡرِنَا رَشَدٗا ﴿10﴾

Transliteration: Ith awa alfityatu ila alkahfi faqaloo rabbana atina min ladunka rahmatan wahayyi lana min amrina rashadan

Translation: 10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወጣቶቹ ወደ ዋሻው በተጠጉና: «ጌታችን ሆይ! ካንተ ዘንድ እዝነትን ስጠን:: ለእኛም ከነገራችን ቅንን ነገር አዘጋጅልን።» ባሉ ጊዜ (የሆነውን ታሪክ አስታውስ።)

18:11

فَضَرَبۡنَا عَلَىٰٓ ءَاذَانِهِمۡ فِي ٱلۡكَهۡفِ سِنِينَ عَدَدٗا ﴿11﴾

Transliteration: Fadarabna AAala athanihim fee alkahfi sineena AAadadan

Translation: 11. በዋሻዉም ውስጥ የተቆጠሩን ዓመታት በጆሮዎቻቸው ላይ መታንባቸው (አስተኛናቸው)::

18:12

ثُمَّ بَعَثۡنَٰهُمۡ لِنَعۡلَمَ أَيُّ ٱلۡحِزۡبَيۡنِ أَحۡصَىٰ لِمَا لَبِثُوٓاْ أَمَدٗا ﴿12﴾

Transliteration: Thumma baAAathnahum linaAAlama ayyu alhizbayni ahsa lima labithoo amadan

Translation: 12.ከዚያም ከሁለቱ ክፍሎች ለቆዩት ጊዜ ልክ ያረጋገጠው ማንኛው መሆኑን ልናውቅ ከተኙበት አስነሳናቸው::

18:13

نَّحۡنُ نَقُصُّ عَلَيۡكَ نَبَأَهُم بِٱلۡحَقِّۚ إِنَّهُمۡ فِتۡيَةٌ ءَامَنُواْ بِرَبِّهِمۡ وَزِدۡنَٰهُمۡ هُدٗى ﴿13﴾

Transliteration: Nahnu naqussu AAalayka nabaahum bialhaqqi innahum fityatun amanoo birabbihim wazidnahum hudan

Translation: 13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ ወሬያቸውን ባንተ ላይ በእውነት እንተርክልሃለን:: እነርሱ በጌታቸው በትክክል ያመኑ ወጣቶች ናቸው:: ወደ ቀናው መንገድ መመራትንም ጨመርንላቸው::

18:14

وَرَبَطۡنَا عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ إِذۡ قَامُواْ فَقَالُواْ رَبُّنَا رَبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ لَن نَّدۡعُوَاْ مِن دُونِهِۦٓ إِلَٰهٗاۖ لَّقَدۡ قُلۡنَآ إِذٗا شَطَطًا ﴿14﴾

Transliteration: Warabatna AAala quloobihim ith qamoo faqaloo rabbuna rabbu alssamawati waalardi lan nadAAuwa min doonihi ilahan laqad qulna ithan shatatan

Translation: 14. በንጉሳቸው ፊት በቆሙና እንዲህም ባሉ ጊዜ ልቦቻቸውን በእምነት አጠነከርን: «ጌታችን የሰማያትና የምድር ጌታ ነው:: ከእርሱ ሌላ አምላክን አንገዛም:: ከእሱ ሌላን ብናመልክማ ወሰን ያለፈን ንግግር በእርግጥ ተናገርን።

18:15

هَـٰٓؤُلَآءِ قَوۡمُنَا ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِهِۦٓ ءَالِهَةٗۖ لَّوۡلَا يَأۡتُونَ عَلَيۡهِم بِسُلۡطَٰنِۭ بَيِّنٖۖ فَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّنِ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبٗا ﴿15﴾

Transliteration: Haolai qawmuna ittakhathoo min doonihi alihatan lawla yatoona AAalayhim bisultanin bayyinin faman athlamu mimmani iftara AAala Allahi kathiban

Translation: 15. «እነዚህ ህዝቦቻችን ከእርሱ ሌላ አማልክትን ያዙ:: እውነተኞች ከሆኑ በእነርሱ ላይ ግልጽ ማስረጃን ለምን አያመጡም? በአላህ ላይ ውሸትን ከሚቀጣጥፍ ይበልጥ በዳይ ማን ነው?» አሉ።

18:16

وَإِذِ ٱعۡتَزَلۡتُمُوهُمۡ وَمَا يَعۡبُدُونَ إِلَّا ٱللَّهَ فَأۡوُۥٓاْ إِلَى ٱلۡكَهۡفِ يَنشُرۡ لَكُمۡ رَبُّكُم مِّن رَّحۡمَتِهِۦ وَيُهَيِّئۡ لَكُم مِّنۡ أَمۡرِكُم مِّرۡفَقٗا ﴿16﴾

Transliteration: Waithi iAAtazaltumoohum wama yaAAbudoona illa Allaha fawoo ila alkahfi yanshur lakum rabbukum min rahmatihi wayuhayyi lakum min amrikum mirfaqan

Translation: 16. «እነርሱንና ያንን ከአላህ ሌላ የሚገዙትን በተለያችሁ ጊዜ ወደ ዋሻው ተጠጉ። ጌታችሁ ለእናንተ ከችሮታው ይዘረጋላችኋልና፤ ከነገራችሁም ለእናንተ መጠቃቀሚያ ያዘጋጅላችኋልና።» (ተባባሉ)።

18:17

وَتَرَى ٱلشَّمۡسَ إِذَا طَلَعَت تَّزَٰوَرُ عَن كَهۡفِهِمۡ ذَاتَ ٱلۡيَمِينِ وَإِذَا غَرَبَت تَّقۡرِضُهُمۡ ذَاتَ ٱلشِّمَالِ وَهُمۡ فِي فَجۡوَةٖ مِّنۡهُۚ ذَٰلِكَ مِنۡ ءَايَٰتِ ٱللَّهِۗ مَن يَهۡدِ ٱللَّهُ فَهُوَ ٱلۡمُهۡتَدِۖ وَمَن يُضۡلِلۡ فَلَن تَجِدَ لَهُۥ وَلِيّٗا مُّرۡشِدٗا ﴿17﴾

Transliteration: Watara alshshamsa itha talaAAat tazawaru AAan kahfihim thata alyameeni waitha gharabat taqriduhum thata alshshimali wahum fee fajwatin minhu thalika min ayati Allahi man yahdi Allahu fahuwa almuhtadi waman yudlil falan tajida lahu waliyyan murshidan

Translation: 17.ጸሐይዋ በወጣች ጊዜ ከዋሻቸው ወደ ቀኝ ጎን ስታዘነብል ታያታለህ:: በገባችም ጊዜ ከሰፊው ዋሻ ውስጥ እያሉ በግራ በኩል ትተዋቸዋለች:: ይህ ከአላህ ተዓምራት አንዱ ነው:: አላህ ያቀናው በእርግጥም የተቀናው እርሱ ብቻ ነው:: እርሱ ያጠመመውን ደግሞ ቅኑን መንገድ የሚመራው ረዳት ማንንም አታገኝለትም::

18:18

وَتَحۡسَبُهُمۡ أَيۡقَاظٗا وَهُمۡ رُقُودٞۚ وَنُقَلِّبُهُمۡ ذَاتَ ٱلۡيَمِينِ وَذَاتَ ٱلشِّمَالِۖ وَكَلۡبُهُم بَٰسِطٞ ذِرَاعَيۡهِ بِٱلۡوَصِيدِۚ لَوِ ٱطَّلَعۡتَ عَلَيۡهِمۡ لَوَلَّيۡتَ مِنۡهُمۡ فِرَارٗا وَلَمُلِئۡتَ مِنۡهُمۡ رُعۡبٗا ﴿18﴾

Transliteration: Watahsabuhum ayqathan wahum ruqoodun wanuqallibuhum thata alyameeni wathata alshshimali wakalbuhum basitun thiraAAayhi bialwaseedi lawi ittalaAAta AAalayhim lawallayta minhum firaran walamulita minhum ruAAban

Translation: 18. እነርሱ በጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ እያሉ የነቁ ይመስሉሃል:: ወደቀኝና ወደ ግራ ጎናቸው እናገላብጣቸዋለን:: ውሻቸዉም በዋሻቸው በር ላይ የፊት እግሩን ዘርግቷል:: ብታያቸው ኖሮ ከእነርሱ በእርግጥ የምትሸሽ ኾነህ በዞርክ ነበር:: በፍርሀትም በተሞላህ ነበር::

18:19

وَكَذَٰلِكَ بَعَثۡنَٰهُمۡ لِيَتَسَآءَلُواْ بَيۡنَهُمۡۚ قَالَ قَآئِلٞ مِّنۡهُمۡ كَمۡ لَبِثۡتُمۡۖ قَالُواْ لَبِثۡنَا يَوۡمًا أَوۡ بَعۡضَ يَوۡمٖۚ قَالُواْ رَبُّكُمۡ أَعۡلَمُ بِمَا لَبِثۡتُمۡ فَٱبۡعَثُوٓاْ أَحَدَكُم بِوَرِقِكُمۡ هَٰذِهِۦٓ إِلَى ٱلۡمَدِينَةِ فَلۡيَنظُرۡ أَيُّهَآ أَزۡكَىٰ طَعَامٗا فَلۡيَأۡتِكُم بِرِزۡقٖ مِّنۡهُ وَلۡيَتَلَطَّفۡ وَلَا يُشۡعِرَنَّ بِكُمۡ أَحَدًا ﴿19﴾

Transliteration: Wakathalika baAAathnahum liyatasaaloo baynahum qala qailun minhum kam labithtum qaloo labithna yawman aw baAAda yawmin qaloo rabbukum aAAlamu bima labithtum faibAAathoo ahadakum biwariqikum hathihi ila almadeenati falyanthur ayyuha azka taAAaman falyatikum birizqin minhu walyatalattaf wala yushAAiranna bikum ahadan

Translation: 19. ልክ እንዳስተኛናቸውም ሁሉ በመካከላቸው እንዲጠያየቁም ቀሰቀስናቸው:: ከእነርሱ አንድ ተናጋሪ «ምን ያህል ቆያችሁ አለ?» ሌሎቹም «አንድን ቀን ወይም የቀንን ከፊል ቆየን።» አሉ። ተባባሉም: «ጌታችሁ የቆያችሁትን ጊዜ ልክ አዋቂ ነው:: ከዚህም ገንዘባችሁ ጋር አንዳችሁን ወደ ከተማይቱ ላኩ:: ከምግብ የትኛዋ ንጹህ መሆኗንም ይመልከት:: (ከንጹሑ) ምግብን ያምጣላችሁ:: ቀስም ይበል:: በእናንተም አንድንም ሰው አያሳውቅ።

18:20

إِنَّهُمۡ إِن يَظۡهَرُواْ عَلَيۡكُمۡ يَرۡجُمُوكُمۡ أَوۡ يُعِيدُوكُمۡ فِي مِلَّتِهِمۡ وَلَن تُفۡلِحُوٓاْ إِذًا أَبَدٗا ﴿20﴾

Transliteration: Innahum in yathharoo AAalaykum yarjumookum aw yuAAeedookum fee millatihim walan tuflihoo ithan abadan

Translation: 20. «እነርሱ በእናንተ ላይ ቢዘልቁ ይቀጠቅጧችኋል:: ወይም ወደ ሃይማኖታቸው ይመልሷችኋል፤ ያን ጊዜም በፍጹም ፍላጎታችሁን አታገኙም።» ተባባሉ።

18:21

وَكَذَٰلِكَ أَعۡثَرۡنَا عَلَيۡهِمۡ لِيَعۡلَمُوٓاْ أَنَّ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقّٞ وَأَنَّ ٱلسَّاعَةَ لَا رَيۡبَ فِيهَآ إِذۡ يَتَنَٰزَعُونَ بَيۡنَهُمۡ أَمۡرَهُمۡۖ فَقَالُواْ ٱبۡنُواْ عَلَيۡهِم بُنۡيَٰنٗاۖ رَّبُّهُمۡ أَعۡلَمُ بِهِمۡۚ قَالَ ٱلَّذِينَ غَلَبُواْ عَلَىٰٓ أَمۡرِهِمۡ لَنَتَّخِذَنَّ عَلَيۡهِم مَّسۡجِدٗا ﴿21﴾

Transliteration: Wakathalika aAAtharna AAalayhim liyaAAlamoo anna waAAda Allahi haqqun waanna alsaAAata la rayba feeha ith yatanazaAAoona baynahum amrahum faqaloo ibnoo AAalayhim bunyanan rabbuhum aAAlamu bihim qala allatheena ghalaboo AAala amrihim lanattakhithanna AAalayhim masjidan

Translation: 21. ልክ እንደዚሁም የአላህ ቀጠሮ እርግጠኛ መሆኑን ሰዓቲቱም በእርሷ ጥርጣሬ የሌለ መሆኑን ያውቁ ዘንድ በእነርሱ ላይ ሰዎችን አሳወቅን:: አማኞቹና ከሓዲያን ነገራቸውን በመካከላቸው ሲከራከሩ የሆነውን አስታውስ:: ከሓዲያን «በእነርሱ ላይ ግንብን ገንቡ።» አሉ:: ጌታቸው ለእነርሱ ይበልጥ አዋቂ ነው:: እነዚያ በነገራቸው ላይ ያሸነፉት ግን «በእነርሱ ላይ በእርግጥ መስጊድን እንሰራለን።» አሉ።

18:22

سَيَقُولُونَ ثَلَٰثَةٞ رَّابِعُهُمۡ كَلۡبُهُمۡ وَيَقُولُونَ خَمۡسَةٞ سَادِسُهُمۡ كَلۡبُهُمۡ رَجۡمَۢا بِٱلۡغَيۡبِۖ وَيَقُولُونَ سَبۡعَةٞ وَثَامِنُهُمۡ كَلۡبُهُمۡۚ قُل رَّبِّيٓ أَعۡلَمُ بِعِدَّتِهِم مَّا يَعۡلَمُهُمۡ إِلَّا قَلِيلٞۗ فَلَا تُمَارِ فِيهِمۡ إِلَّا مِرَآءٗ ظَٰهِرٗا وَلَا تَسۡتَفۡتِ فِيهِم مِّنۡهُمۡ أَحَدٗا ﴿22﴾

Transliteration: Sayaqooloona thalathatun rabiAAuhum kalbuhum wayaqooloona khamsatun sadisuhum kalbuhum rajman bialghaybi wayaqooloona sabAAatun wathaminuhum kalbuhum qul rabbee aAAlamu biAAiddatihim ma yaAAlamuhum illa qaleelun fala tumari feehim illa miraan thahiran wala tastafti feehim minhum ahadan

Translation: 22. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (ስለ እነርሱ የተወሰኑ ቡድኖች በጥርጣሬ) «ሶስት ናቸው አራተኛው ውሻቸው ነው።» ይላሉ:: (ሌሎች ቡድኖች) «አምስት ናቸው ስድስተኛው ውሻቸው ነው።» ይላሉ። በሩቅ ወርዋሪዎች ሆነው (ባላወቁት አለም) ሲገምቱ። (ሶስተኛው ቡድን ደግሞ) «ሰባት ናቸው ስምንተኛቸው ውሻቸው ነዉ።» ይላሉ:: «ጌታዬ ብቻ ቁጥራቸውን አዋቂ ነው:: ጥቂት ሰው እንጂ አያውቃቸዉም።» በላቸው:: እናም በእነርሱ ነገር ግልጽን ክርክር እንጂ ጠልቀህ አትከራከር:: በእነርሱም ጉዳይ ከመጽሐፉ ሰዎች አንድንም አትጠይቅ::

18:23

وَلَا تَقُولَنَّ لِشَاْيۡءٍ إِنِّي فَاعِلٞ ذَٰلِكَ غَدًا ﴿23﴾

Transliteration: Wala taqoolanna lishayin innee faAAilun thalika ghadan

Translation: 23 ለማንኛዉም ነገር «እኔ ይህንን ነገ ሠሪ ነኝ።» አትበል።

18:24

إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُۚ وَٱذۡكُر رَّبَّكَ إِذَا نَسِيتَ وَقُلۡ عَسَىٰٓ أَن يَهۡدِيَنِ رَبِّي لِأَقۡرَبَ مِنۡ هَٰذَا رَشَدٗا ﴿24﴾

Transliteration: Illa an yashaa Allahu waothkur rabbaka itha naseeta waqul AAasa an yahdiyani rabbee liaqraba min hatha rashadan

Translation: 24. «አላህ ቢሻ እሠራዋለሁ።» ብትል እንጂ። በረሳህ ጊዜም ጌታህን አውሳ። «ጌታዬም ከዚህ ይበልጥ ለቀጥታ የቀረበን ሊመራኝ ይከጀላል» በላቸው።

18:25

وَلَبِثُواْ فِي كَهۡفِهِمۡ ثَلَٰثَ مِاْئَةٖ سِنِينَ وَٱزۡدَادُواْ تِسۡعٗا ﴿25﴾

Transliteration: Walabithoo fee kahfihim thalatha miatin sineena waizdadoo tisAAan

Translation: 25. በዋሻቸዉም ውስጥ ሶስት መቶ ዓመታትን ቆዩ:: ዘጠኝ አመታትንም ጨመሩ::

18:26

قُلِ ٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِمَا لَبِثُواْۖ لَهُۥ غَيۡبُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ أَبۡصِرۡ بِهِۦ وَأَسۡمِعۡۚ مَا لَهُم مِّن دُونِهِۦ مِن وَلِيّٖ وَلَا يُشۡرِكُ فِي حُكۡمِهِۦٓ أَحَدٗا ﴿26﴾

Transliteration: Quli Allahu aAAlamu bima labithoo lahu ghaybu alssamawati waalardi absir bihi waasmiAA ma lahum min doonihi min waliyyin wala yushriku fee hukmihi ahadan

Translation: 26.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ብቻ የቆዩትን ልክ በትክክል አዋቂ ነው። የሰማያትና የምድር ሚስጢር የእሱ ብቻ ነዉ። እርሱ (አላህ) ሁሉን ተመልካች ሁሉን ሰሚ መሆኑ ይግረምህ። ለእነርሱ ከእርሱ በስተቀር ምንም ወዳጅ የላቸዉም:: በፍርዱም አንድንም አያጋራም።» በላቸው።

18:27

وَٱتۡلُ مَآ أُوحِيَ إِلَيۡكَ مِن كِتَابِ رَبِّكَۖ لَا مُبَدِّلَ لِكَلِمَٰتِهِۦ وَلَن تَجِدَ مِن دُونِهِۦ مُلۡتَحَدٗا ﴿27﴾

Transliteration: Waotlu ma oohiya ilayka min kitabi rabbika la mubaddila likalimatihi walan tajida min doonihi multahadan

Translation: 27.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ መጽሀፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ:: ለቃሎቹ ለዋጭ የላቸዉም:: ከርሱም በስተቀር መጠጊያን በፍጹም አታገኝም።

18:28

وَٱصۡبِرۡ نَفۡسَكَ مَعَ ٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ رَبَّهُم بِٱلۡغَدَوٰةِ وَٱلۡعَشِيِّ يُرِيدُونَ وَجۡهَهُۥۖ وَلَا تَعۡدُ عَيۡنَاكَ عَنۡهُمۡ تُرِيدُ زِينَةَ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۖ وَلَا تُطِعۡ مَنۡ أَغۡفَلۡنَا قَلۡبَهُۥ عَن ذِكۡرِنَا وَٱتَّبَعَ هَوَىٰهُ وَكَانَ أَمۡرُهُۥ فُرُطٗا ﴿28﴾

Transliteration: Waisbir nafsaka maAAa allatheena yadAAoona rabbahum bialghadati waalAAashiyyi yureedoona wajhahu wala taAAdu AAaynaka AAanhum tureedu zeenata alhayati alddunya wala tutiAA man aghfalna qalbahu AAan thikrina waittabaAAa hawahu wakana amruhu furutan

Translation: 28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነፍስህንም ከእነዚያ ጌታቸውን ፊቱን የሚሹ ሆነው በጥዋትና በማታ ከሚገዙት ጋር አስታግስ:: የቅርቢቱንም ህይወት ሽልማት የምትሻ ሆነህ አይኖችህ ከእነርሱ ወደ ሌላ አይለፉ:: ያ ልቡን እኛን ከማስታወስ ያዘነጋነውንና የግል ፍላጎቱን የተከተለውን ነገሩ ሁሉ ወሰን ማለፍ የሆነውን ሰው አትታዘዝ።

18:29

وَقُلِ ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّكُمۡۖ فَمَن شَآءَ فَلۡيُؤۡمِن وَمَن شَآءَ فَلۡيَكۡفُرۡۚ إِنَّآ أَعۡتَدۡنَا لِلظَّـٰلِمِينَ نَارًا أَحَاطَ بِهِمۡ سُرَادِقُهَاۚ وَإِن يَسۡتَغِيثُواْ يُغَاثُواْ بِمَآءٖ كَٱلۡمُهۡلِ يَشۡوِي ٱلۡوُجُوهَۚ بِئۡسَ ٱلشَّرَابُ وَسَآءَتۡ مُرۡتَفَقًا ﴿29﴾

Transliteration: Waquli alhaqqu min rabbikum faman shaa falyumin waman shaa falyakfur inna aAAtadna lilththalimeena naran ahata bihim suradiquha wain yastagheethoo yughathoo bimain kaalmuhli yashwee alwujooha bisa alshsharabu wasaat murtafaqan

Translation: 29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎች ሆይ! እውነቱ ሁሉ ከጌታችሁ ነው:: ስለዚህ የፈለገም ሰው በእውነቱ ይመን:: የፈለገም ሰው ይካድ።» በላቸው:: እኛ ለበደለኛ ከሓዲያን አጥሯ በእነርሱ ላይ የከበበ የሆነችውን እሳት አዘጋጅተናል:: ከጥም ለመዳን እርዳታን ቢፈልጉ እንደ ዘይት ዝቃጭ ባለ ፊቶችን በሚጠብስ ውሃ ይረዳሉ:: መጠጡም ከፋ፤ መደገፊያይቱም ምንኛ አስከፋች!

18:30

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّـٰلِحَٰتِ إِنَّا لَا نُضِيعُ أَجۡرَ مَنۡ أَحۡسَنَ عَمَلًا ﴿30﴾

Transliteration: Inna allatheena amanoo waAAamiloo alssalihati inna la nudeeAAu ajra man ahsana AAamalan

Translation: 30. እነዚያ በአላህ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ እኛ ሥራ ያሳመረን ምንዳ አናጠፋም።

18:31

أُوْلَـٰٓئِكَ لَهُمۡ جَنَّـٰتُ عَدۡنٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهِمُ ٱلۡأَنۡهَٰرُ يُحَلَّوۡنَ فِيهَا مِنۡ أَسَاوِرَ مِن ذَهَبٖ وَيَلۡبَسُونَ ثِيَابًا خُضۡرٗا مِّن سُندُسٖ وَإِسۡتَبۡرَقٖ مُّتَّكِـِٔينَ فِيهَا عَلَى ٱلۡأَرَآئِكِۚ نِعۡمَ ٱلثَّوَابُ وَحَسُنَتۡ مُرۡتَفَقٗا ﴿31﴾

Transliteration: Olaika lahum jannatu AAadnin tajree min tahtihimu alanharu yuhallawna feeha min asawira min thahabin wayalbasoona thiyaban khudran min sundusin waistabraqin muttakieena feeha AAala alaraiki niAAma alththawabu wahasunat murtafaqan

Translation: 31.እነዚያ ለእነርሱ የመኖሪያ ገነቶች ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው አሏቸው:: በእርሷ ውስጥ ከወርቅ የሆኑን አምባሮች ይሸለማሉ:: ከቀጭን ሀርና ከወፍራም ሀርም አረንጓዴ ልብሶችን ይለብሳሉ:: በውስጧ በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ የተደገፉ ሆነው ይቀመጣሉ:: እነዚህ ሰዎች ምንዳቸው ምን ያምር! መኖሪያቸው ገነትም ምንኛ አማረች!

18:32

وَٱضۡرِبۡ لَهُم مَّثَلٗا رَّجُلَيۡنِ جَعَلۡنَا لِأَحَدِهِمَا جَنَّتَيۡنِ مِنۡ أَعۡنَٰبٖ وَحَفَفۡنَٰهُمَا بِنَخۡلٖ وَجَعَلۡنَا بَيۡنَهُمَا زَرۡعٗا ﴿32﴾

Transliteration: Waidrib lahum mathalan rajulayni jaAAalna liahadihima jannatayni min aAAnabin wahafafnahuma binakhlin wajaAAalna baynahuma zarAAan

Translation: 32. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለከሓዲያን የሁለትን ሰዎችን ምሳሌ ግለጽላቸው:: ለአንደኛው ከሓዲ ሁለት የወይን አትክልቶች አደረግንለት። በዘንባባም ከበብናቸው። በመካከላቸውም አዝመራን አደረግን።

18:33

كِلۡتَا ٱلۡجَنَّتَيۡنِ ءَاتَتۡ أُكُلَهَا وَلَمۡ تَظۡلِم مِّنۡهُ شَيۡـٔٗاۚ وَفَجَّرۡنَا خِلَٰلَهُمَا نَهَرٗا ﴿33﴾

Transliteration: Kilta aljannatayni atat okulaha walam tathlim minhu shayan wafajjarna khilalahuma naharan

Translation: 33. ሁለቱም አትክልቶች ሰብላቸውን ሰጡ፤ ከርሱም ምንም አላጎደሉም። በመካከላቸዉም ወንዝን አፈሰስን።

18:34

وَكَانَ لَهُۥ ثَمَرٞ فَقَالَ لِصَٰحِبِهِۦ وَهُوَ يُحَاوِرُهُۥٓ أَنَا۠ أَكۡثَرُ مِنكَ مَالٗا وَأَعَزُّ نَفَرٗا ﴿34﴾

Transliteration: Wakana lahu thamarun faqala lisahibihi wahuwa yuhawiruhu ana aktharu minka malan waaAAazzu nafaran

Translation: 34.ለእርሱ ከአትክልቶቹ ሌላ ፍሬያማ ሀብት ነበረው:: ለአማኙ ጓደኛዉም የሚወዳደረው ሲሆን «እኔ ካንተ በገንዘብ ይበልጥ የበዛሁ በወገንም ይበልጥ የበረታሁ ነኝ።» አለው።

18:35

وَدَخَلَ جَنَّتَهُۥ وَهُوَ ظَالِمٞ لِّنَفۡسِهِۦ قَالَ مَآ أَظُنُّ أَن تَبِيدَ هَٰذِهِۦٓ أَبَدٗا ﴿35﴾

Transliteration: Wadakhala jannatahu wahuwa thalimun linafsihi qala ma athunnu an tabeeda hathihi abadan

Translation: 35. እርሱም ነፍሱንም በዳይ ሆኖ ወደ አትክልቱ ገባ። (እንዲህም) አለ: «ይህች አትክልት መቸም ትጠፋለች ብዬ አልጠረጥርም።

18:36

وَمَآ أَظُنُّ ٱلسَّاعَةَ قَآئِمَةٗ وَلَئِن رُّدِدتُّ إِلَىٰ رَبِّي لَأَجِدَنَّ خَيۡرٗا مِّنۡهَا مُنقَلَبٗا ﴿36﴾

Transliteration: Wama athunnu alssaAAata qaimatan walain rudidtu ila rabbee laajidanna khayran minha munqalaban

Translation: 36. «ሰዓቲቱንም ትከሰታለች ብዬ አልጠረጥርም፤ እንደምትለው ወደ ጌታዬም ብመለስ ከእርሷ የበለጠን መመለሻ በእርግጥ አገኛለሁ።» አለው።

18:37

قَالَ لَهُۥ صَاحِبُهُۥ وَهُوَ يُحَاوِرُهُۥٓ أَكَفَرۡتَ بِٱلَّذِي خَلَقَكَ مِن تُرَابٖ ثُمَّ مِن نُّطۡفَةٖ ثُمَّ سَوَّىٰكَ رَجُلٗا ﴿37﴾

Transliteration: Qala lahu sahibuhu wahuwa yuhawiruhu akafarta biallathee khalaqaka min turabin thumma min nutfatin thumma sawwaka rajulan

Translation: 37. አማኙ ጓደኛውም ለእርሱ የሚመላለሰው ሲሆን (እንዲህ) አለው: «በዚያ ከአፈር ከዚያም ከፍትወት ጠብታ በፈጠረህ ከዚያም ሰው ባደረገህ ሃያል አምላክ ካድክን?

18:38

لَّـٰكِنَّا۠ هُوَ ٱللَّهُ رَبِّي وَلَآ أُشۡرِكُ بِرَبِّيٓ أَحَدٗا ﴿38﴾

Transliteration: Lakinna huwa Allahu rabbee wala oshriku birabbee ahadan

Translation: 38. «እኔ ግን አላህ ጌታዬ ነው እላለሁ። በጌታዬም አንድንም አላጋራም።

18:39

وَلَوۡلَآ إِذۡ دَخَلۡتَ جَنَّتَكَ قُلۡتَ مَا شَآءَ ٱللَّهُ لَا قُوَّةَ إِلَّا بِٱللَّهِۚ إِن تَرَنِ أَنَا۠ أَقَلَّ مِنكَ مَالٗا وَوَلَدٗا ﴿39﴾

Transliteration: Walawla ith dakhalta jannataka qulta ma shaa Allahu la quwwata illa biAllahi in tarani ana aqalla minka malan wawaladan

Translation: 39. «እኔን በገንዘብም ሆነ በልጅ ካንተ በጣም ያነስኩ ሆኜ ብታየኝም ወደ አትክልትህ በገባህ ጊዜ ‹አላህ የሻው ሆኗል። በአላህ ቢሆን እንጂ ብልሃትም የለም› አትልም ኖሯልን?

18:40

فَعَسَىٰ رَبِّيٓ أَن يُؤۡتِيَنِ خَيۡرٗا مِّن جَنَّتِكَ وَيُرۡسِلَ عَلَيۡهَا حُسۡبَانٗا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ فَتُصۡبِحَ صَعِيدٗا زَلَقًا ﴿40﴾

Transliteration: FaAAasa rabbee an yutiyani khayran min jannatika wayursila AAalayha husbanan mina alssamai fatusbiha saAAeedan zalaqan

Translation: 40. «ጌታዬ ከአትክልትህ የበለጠን ሊሰጠኝ በአትክልትህ ላይ ደግሞ በሰማይ መብረቆችን ሊልክባትና የምታንዳልጥ ምልጥ ምድር ልትሆንም ይቻላል።

18:41

أَوۡ يُصۡبِحَ مَآؤُهَا غَوۡرٗا فَلَن تَسۡتَطِيعَ لَهُۥ طَلَبٗا ﴿41﴾

Transliteration: Aw yusbiha maoha ghawran falan tastateeAAa lahu talaban

Translation: 41. «ወይም ውሀው ሰራጊ ሊሆንብህ ይችላል። ያን ጊዜ እርሱን መፈለጉን ፈጽሞ አትችልም።» አለው።

18:42

وَأُحِيطَ بِثَمَرِهِۦ فَأَصۡبَحَ يُقَلِّبُ كَفَّيۡهِ عَلَىٰ مَآ أَنفَقَ فِيهَا وَهِيَ خَاوِيَةٌ عَلَىٰ عُرُوشِهَا وَيَقُولُ يَٰلَيۡتَنِي لَمۡ أُشۡرِكۡ بِرَبِّيٓ أَحَدٗا ﴿42﴾

Transliteration: Waoheeta bithamarihi faasbaha yuqallibu kaffayhi AAala ma anfaqa feeha wahiya khawiyatun AAala AAurooshiha wayaqoolu ya laytanee lam oshrik birabbee ahadan

Translation: 42. ሀብቱም ተጠፋ:: እርሷ በዳሶችዋ ላይ የወደቀች ሆና በእርሷ ባወጣው ገንዘብ ላይ የተጸጸተ መዳፎቹን የሚያገላብጥና «ወይ ጸጸቴ! በጌታዬ አንድንም ባላጋራሁ።» የሚል ሆነ።

18:43

وَلَمۡ تَكُن لَّهُۥ فِئَةٞ يَنصُرُونَهُۥ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَمَا كَانَ مُنتَصِرًا ﴿43﴾

Transliteration: Walam takun lahu fiatun yansuroonahu min dooni Allahi wama kana muntasiran

Translation: 43.እርሱም ከአላህ ሌላ የሚረዱት ቡድኖች አልነበሩትም:: ተረጂም አልነበረም::

18:44

هُنَالِكَ ٱلۡوَلَٰيَةُ لِلَّهِ ٱلۡحَقِّۚ هُوَ خَيۡرٞ ثَوَابٗا وَخَيۡرٌ عُقۡبٗا ﴿44﴾

Transliteration: Hunalika alwalayatu lillahi alhaqqi huwa khayrun thawaban wakhayrun AAuqban

Translation: 44.እዚያ ዘንድ በትንሳኤ ቀን ስልጣኑ እውነተኛ ለሆነው ለአላህ ብቻ ነው:: እርሱ በመመንዳት የበለጠ ፍጻሜንም በማሳመር የበለጠ ነው::

18:45

وَٱضۡرِبۡ لَهُم مَّثَلَ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا كَمَآءٍ أَنزَلۡنَٰهُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ فَٱخۡتَلَطَ بِهِۦ نَبَاتُ ٱلۡأَرۡضِ فَأَصۡبَحَ هَشِيمٗا تَذۡرُوهُ ٱلرِّيَٰحُۗ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ مُّقۡتَدِرًا ﴿45﴾

Transliteration: Waidrib lahum mathala alhayati alddunya kamain anzalnahu mina alssamai faikhtalata bihi nabatu alardi faasbaha hasheeman tathroohu alrriyahu wakana Allahu AAala kulli shayin muqtadiran

Translation: 45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነርሱም የቅርቢቱን ህይወት ምሳሌ አውሳላቸው:: እርሷ ከሰማይ እንዳወረድነው ውሃ በእርሱም የምድር ቡቃያ እንደተቀላቀለበት፤ ከተዋበ በኋላም ደርቆ ንፋሶች የሚያበኑት ደቃቅ እንደሆነ ብጤ ናት:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው::

18:46

ٱلۡمَالُ وَٱلۡبَنُونَ زِينَةُ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۖ وَٱلۡبَٰقِيَٰتُ ٱلصَّـٰلِحَٰتُ خَيۡرٌ عِندَ رَبِّكَ ثَوَابٗا وَخَيۡرٌ أَمَلٗا ﴿46﴾

Transliteration: Almalu waalbanoona zeenatu alhayati alddunya waalbaqiyatu alssalihatu khayrun AAinda rabbika thawaban wakhayrun amalan

Translation: 46. ገንዘብና ልጆች የቅርቢቱ ህይወት ጌጦች ብቻ ናቸው:: መልካም ቀሪ ሥራዎች ግን በጌታህ ዘንድ በምንዳ በላጭ ናቸው:: በተስፋም በላጭ ናቸው::

18:47

وَيَوۡمَ نُسَيِّرُ ٱلۡجِبَالَ وَتَرَى ٱلۡأَرۡضَ بَارِزَةٗ وَحَشَرۡنَٰهُمۡ فَلَمۡ نُغَادِرۡ مِنۡهُمۡ أَحَدٗا ﴿47﴾

Transliteration: Wayawma nusayyiru aljibala watara alarda barizatan wahasharnahum falam nughadir minhum ahadan

Translation: 47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተራራዎችን የምናስኬድበትን ቀን አስታውስ:: ምድርንም ግልጽ ሆና ታያታለህ:: እንሰበስባቸዋለንም:: ከእነርሱ አንድንም አንተዉም::

18:48

وَعُرِضُواْ عَلَىٰ رَبِّكَ صَفّٗا لَّقَدۡ جِئۡتُمُونَا كَمَا خَلَقۡنَٰكُمۡ أَوَّلَ مَرَّةِۭۚ بَلۡ زَعَمۡتُمۡ أَلَّن نَّجۡعَلَ لَكُم مَّوۡعِدٗا ﴿48﴾

Transliteration: WaAAuridoo AAala rabbika saffan laqad jitumoona kama khalaqnakum awwala marratin bal zaAAamtum allan najAAala lakum mawAAidan

Translation: 48. የተሰለፉ ሆነው በጌታህ ላይ ይቀርባሉ:: ይባላሉም «በመጀመሪያ ጊዜ እንደፈጠርናችሁ በእርግጥ ወደ እኛ መጣችሁ:: በእውነቱ ለእናንተ የመቀስቀሻ ጊዜን አናደርግም መስሏችሁ ነበር።»

18:49

وَوُضِعَ ٱلۡكِتَٰبُ فَتَرَى ٱلۡمُجۡرِمِينَ مُشۡفِقِينَ مِمَّا فِيهِ وَيَقُولُونَ يَٰوَيۡلَتَنَا مَالِ هَٰذَا ٱلۡكِتَٰبِ لَا يُغَادِرُ صَغِيرَةٗ وَلَا كَبِيرَةً إِلَّآ أَحۡصَىٰهَاۚ وَوَجَدُواْ مَا عَمِلُواْ حَاضِرٗاۗ وَلَا يَظۡلِمُ رَبُّكَ أَحَدٗا ﴿49﴾

Transliteration: WawudiAAa alkitabu fatara almujrimeena mushfiqeena mimma feehi wayaqooloona ya waylatana ma lihatha alkitabi la yughadiru sagheeratan wala kabeeratan illa ahsaha wawajadoo ma AAamiloo hadiran wala yathlimu rabbuka ahadan

Translation: 49 ለሰው ሁሉ መጽሐፉ ይቀርባል:: ወዲያዉም ከሓዲያንን በውስጡ ካለው ነገር ፈሪዎች ሆነው ታያቸዋለህ። «ዋ ጥፋታችን! ይህ መጽሐፍ ከሥራ ትንሽንም ትልቅንም የቆጠራት ቢሆን እንጂ የማይተወው ምን አለው?» ይላሉ:: የሠሩትንም ነገር ሁሉ ቅርብ ሆኖ ያገኙታል:: ጌታህም አንድንም አይበድልም::

18:50

وَإِذۡ قُلۡنَا لِلۡمَلَـٰٓئِكَةِ ٱسۡجُدُواْ لِأٓدَمَ فَسَجَدُوٓاْ إِلَّآ إِبۡلِيسَ كَانَ مِنَ ٱلۡجِنِّ فَفَسَقَ عَنۡ أَمۡرِ رَبِّهِۦٓۗ أَفَتَتَّخِذُونَهُۥ وَذُرِّيَّتَهُۥٓ أَوۡلِيَآءَ مِن دُونِي وَهُمۡ لَكُمۡ عَدُوُّۢۚ بِئۡسَ لِلظَّـٰلِمِينَ بَدَلٗا ﴿50﴾

Transliteration: Waith qulna lilmalaikati osjudoo liadama fasajadoo illa ibleesa kana mina aljinni fafasaqa AAan amri rabbihi afatattakhithoonahu wathurriyyatahu awliyaa min doonee wahum lakum AAaduwwun bisa lilththalimeena badalan

Translation: 50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለመላዕክት «ለአደም ስገዱ።» ባልናቸው ጊዜ (የሆነውን አስታውስ):: ወዲያዉም ዲያብሎስ ብቻ ሲቀር ሁሉም ሰገዱ:: ከአጋንንት ጎሳ ነበርና:: ከጌታዉም ትዕዛዝ ወጣ:: እርሱንና ዘሮቹን እነርሱም ለእናንተ ጠላቶች ሲሆኑ ከኔ ሌላ ረዳቶች ታደርጋላችሁን? ለበዳዮች ልዋጭነቱ ከፋ::

18:51

مَّآ أَشۡهَدتُّهُمۡ خَلۡقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَلَا خَلۡقَ أَنفُسِهِمۡ وَمَا كُنتُ مُتَّخِذَ ٱلۡمُضِلِّينَ عَضُدٗا ﴿51﴾

Transliteration: Ma ashhadtuhum khalqa alssamawati waalardi wala khalqa anfusihim wama kuntu muttakhitha almudilleena AAadudan

Translation: 51.የሰማያትና የምድርም አፈጣጠር አላሰየኋቸዉም:: የነፍሶቻቸውንም አፈጣጠር እንደዚሁ አሳሳቾችንም ረዳቶች አድርጌ የምይዝ አይደለሁም::

18:52

وَيَوۡمَ يَقُولُ نَادُواْ شُرَكَآءِيَ ٱلَّذِينَ زَعَمۡتُمۡ فَدَعَوۡهُمۡ فَلَمۡ يَسۡتَجِيبُواْ لَهُمۡ وَجَعَلۡنَا بَيۡنَهُم مَّوۡبِقٗا ﴿52﴾

Transliteration: Wayawma yaqoolu nadoo shurakaiya allatheena zaAAamtum fadaAAawhum falam yastajeeboo lahum wajaAAalna baynahum mawbiqan

Translation: 52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያንም አምላክ የምትሏቸውን ተጋሪዎቼን ጥሩ።» የሚልበትን ቀን አስታውስ:: ይጠሯቸዋልም። ግን አይመልሱላቸዉም:: በመካከላቸዉም መጥፊያን ስፍራ ገሀነምንም አደረግን።

18:53

وَرَءَا ٱلۡمُجۡرِمُونَ ٱلنَّارَ فَظَنُّوٓاْ أَنَّهُم مُّوَاقِعُوهَا وَلَمۡ يَجِدُواْ عَنۡهَا مَصۡرِفٗا ﴿53﴾

Transliteration: Waraa almujrimoona alnnara fathannoo annahum muwaqiAAooha walam yajidoo AAanha masrifan

Translation: 53. ከሓዲያንም እሳትን ያያሉ፤ እነርሱም በውስጧ ወዳቂዎች መሆናቸውን ያረጋግጣሉ:: ከእርሷም መሸሻን አያገኙም።

18:54

وَلَقَدۡ صَرَّفۡنَا فِي هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانِ لِلنَّاسِ مِن كُلِّ مَثَلٖۚ وَكَانَ ٱلۡإِنسَٰنُ أَكۡثَرَ شَيۡءٖ جَدَلٗا ﴿54﴾

Transliteration: Walaqad sarrafna fee hatha alqurani lilnnasi min kulli mathalin wakana alinsanu akthara shayin jadalan

Translation: 54. በዚህም ቁርኣን ውስጥ ከየምሳሌው ሁሉ ለሰዎች መላልሰን ገለጽን፤ ሰዉም ከነገሩ ሁሉ ይበልጥ ክርክረ ብዙ ነው::

18:55

وَمَا مَنَعَ ٱلنَّاسَ أَن يُؤۡمِنُوٓاْ إِذۡ جَآءَهُمُ ٱلۡهُدَىٰ وَيَسۡتَغۡفِرُواْ رَبَّهُمۡ إِلَّآ أَن تَأۡتِيَهُمۡ سُنَّةُ ٱلۡأَوَّلِينَ أَوۡ يَأۡتِيَهُمُ ٱلۡعَذَابُ قُبُلٗا ﴿55﴾

Transliteration: Wama manaAAa alnnasa an yuminoo ith jaahumu alhuda wayastaghfiroo rabbahum illa an tatiyahum sunnatu alawwaleena aw yatiyahumu alAAathabu qubulan

Translation: 55.ሰዎችንም መመሪያ በመጣላችሁ ጊዜ ከማመንና ጌታቸውንም ምህረትን ከመለመን የከለከላቸው የመጀመሪያዎቹ ህዝቦች ልማድ መጥፋት ልትመጣባቸው ወይም ቅጣቱ በየዓይነቱ ሊመጣባቸው መጠባበቅ ብቻ እንጂ ሌላ አይደለም::

18:56

وَمَا نُرۡسِلُ ٱلۡمُرۡسَلِينَ إِلَّا مُبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَۚ وَيُجَٰدِلُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِٱلۡبَٰطِلِ لِيُدۡحِضُواْ بِهِ ٱلۡحَقَّۖ وَٱتَّخَذُوٓاْ ءَايَٰتِي وَمَآ أُنذِرُواْ هُزُوٗا ﴿56﴾

Transliteration: Wama nursilu almursaleena illa mubashshireena wamunthireena wayujadilu allatheena kafaroo bialbatili liyudhidoo bihi alhaqqa waittakhathoo ayatee wama onthiroo huzuwan

Translation: 56. መልዕክተኞችንም አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች ሆነው እንጂ አንልክም:: እነዚያ የካዱትም በውሸት እውነቱን በእሱ ሊያበላሹ ይከራከራሉ:: አንቀፆቼንና በእርሱ የተስፈራሩበትንም ነገር ማላገጫ አድርገው ያዙ::

18:57

وَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّن ذُكِّرَ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِۦ فَأَعۡرَضَ عَنۡهَا وَنَسِيَ مَا قَدَّمَتۡ يَدَاهُۚ إِنَّا جَعَلۡنَا عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ أَكِنَّةً أَن يَفۡقَهُوهُ وَفِيٓ ءَاذَانِهِمۡ وَقۡرٗاۖ وَإِن تَدۡعُهُمۡ إِلَى ٱلۡهُدَىٰ فَلَن يَهۡتَدُوٓاْ إِذًا أَبَدٗا ﴿57﴾

Transliteration: Waman athlamu mimman thukkira biayati rabbihi faaAArada AAanha wanasiya ma qaddamat yadahu inna jaAAalna AAala quloobihim akinnatan an yafqahoohu wafee athanihim waqran wain tadAAuhum ila alhuda falan yahtadoo ithan abadan

Translation: 57.በጌታዉም አናቅጽ ከተገሰጸና ከእርሷም ከዞረ፤ ሁለት እጆቹም ያስቀደሙትን ነገር ከረሳቸዉም ይበልጥ በዳይ ማን ነው? እኛ በልቦቻቸው ላይ እንዳያውቁት ሽፋኖችን፤ በጆሮዎቻቸዉም ውስጥ ድንቁርናን አደረግን። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ መመራትም ብትጠራቸው ያን ጊዜ ፈጽሞ አይመሩም::

18:58

وَرَبُّكَ ٱلۡغَفُورُ ذُو ٱلرَّحۡمَةِۖ لَوۡ يُؤَاخِذُهُم بِمَا كَسَبُواْ لَعَجَّلَ لَهُمُ ٱلۡعَذَابَۚ بَل لَّهُم مَّوۡعِدٞ لَّن يَجِدُواْ مِن دُونِهِۦ مَوۡئِلٗا ﴿58﴾

Transliteration: Warabbuka alghafooru thoo alrrahmati law yuakhithuhum bima kasaboo laAAajjala lahumu alAAathaba bal lahum mawAAidun lan yajidoo min doonihi mawilan

Translation: 58. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም በጣም መሀሪው የእዝነት ባለቤት ነው:: በሠሩት ሥራ ቢይዛቸው ኖሮ ቅጣቱን ለእነርሱ ባስቸኮለባቸው ነበር:: ግን ለእነርሱ ከእርሱ ሌላ መጠጊያን ፈጽሞ የማያገኙበት ቀጠሮ አላቸው::

18:59

وَتِلۡكَ ٱلۡقُرَىٰٓ أَهۡلَكۡنَٰهُمۡ لَمَّا ظَلَمُواْ وَجَعَلۡنَا لِمَهۡلِكِهِم مَّوۡعِدٗا ﴿59﴾

Transliteration: Watilka alqura ahlaknahum lamma thalamoo wajaAAalna limahlikihim mawAAidan

Translation: 59.እነዚህ ከተሞችም በበደሉ ጊዜ አጠፋናቸው፤ ለመጥፊያቸዉም የተወሰነ ጊዜ አደረግን::

18:60

وَإِذۡ قَالَ مُوسَىٰ لِفَتَىٰهُ لَآ أَبۡرَحُ حَتَّىٰٓ أَبۡلُغَ مَجۡمَعَ ٱلۡبَحۡرَيۡنِ أَوۡ أَمۡضِيَ حُقُبٗا ﴿60﴾

Transliteration: Waith qala moosa lifatahu la abrahu hatta ablugha majmaAAa albahrayni aw amdiya huquban

Translation: 60. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳ ለወጣቱ «የሁለቱን ባህሮች መገናኛ እስከምደርስ ወይም ብዙን ጊዜ እስከምሄድ ድረስ ከመጓዝ አልወገድም።» ያለውን (አስታውስ)።

18:61

فَلَمَّا بَلَغَا مَجۡمَعَ بَيۡنِهِمَا نَسِيَا حُوتَهُمَا فَٱتَّخَذَ سَبِيلَهُۥ فِي ٱلۡبَحۡرِ سَرَبٗا ﴿61﴾

Transliteration: Falamma balagha majmaAAa baynihima nasiya hootahuma faittakhatha sabeelahu fee albahri saraban

Translation: 61. የሁለቱን ባህር መገናኛ በደረሱም ጊዜ ዓሳቸውን ረሱ፤ ዓሳውም መንገዱን በባህር ውስጥ ቀዳዳ አድርጎ ያዘ።

18:62

فَلَمَّا جَاوَزَا قَالَ لِفَتَىٰهُ ءَاتِنَا غَدَآءَنَا لَقَدۡ لَقِينَا مِن سَفَرِنَا هَٰذَا نَصَبٗا ﴿62﴾

Transliteration: Falamma jawaza qala lifatahu atina ghadaana laqad laqeena min safarina hatha nasaban

Translation: 62. ባለፉም ጊዜ ለወጣቱ «ምሳችንን ስጠን ከዚህ ጉዟችን በእርግጥ ድካምን አግኝተናልና።» አለ።

18:63

قَالَ أَرَءَيۡتَ إِذۡ أَوَيۡنَآ إِلَى ٱلصَّخۡرَةِ فَإِنِّي نَسِيتُ ٱلۡحُوتَ وَمَآ أَنسَىٰنِيهُ إِلَّا ٱلشَّيۡطَٰنُ أَنۡ أَذۡكُرَهُۥۚ وَٱتَّخَذَ سَبِيلَهُۥ فِي ٱلۡبَحۡرِ عَجَبٗا ﴿63﴾

Transliteration: Qala araayta ith awayna ila alssakhrati fainnee naseetu alhoota wama ansaneehu illa alshshaytanu an athkurahu waittakhatha sabeelahu fee albahri AAajaban

Translation: 63. «አየህን? ወደ ቋጥኟ በተጠጋን ጊዜ እኔ ዐሳውን ረሳሁ፤ ሰይጣን እንጂ ሌላ አላስረሳኝም፤ በባህሩም ውስጥ መንገዱን አስደናቂ መንገድ አድርጎ ያዘ።» አለ።

18:64

قَالَ ذَٰلِكَ مَا كُنَّا نَبۡغِۚ فَٱرۡتَدَّا عَلَىٰٓ ءَاثَارِهِمَا قَصَصٗا ﴿64﴾

Transliteration: Qala thalika ma kunna nabghi fairtadda AAala atharihima qasasan

Translation: 64. ሙሳም «ይህ እኮ እንፈልገው የነበረው ነው።» አለው። ከዚያ በኮቴዎቻቸው (ዱካቸው) ላይ እየተከተሉ ተመለሱ።

18:65

فَوَجَدَا عَبۡدٗا مِّنۡ عِبَادِنَآ ءَاتَيۡنَٰهُ رَحۡمَةٗ مِّنۡ عِندِنَا وَعَلَّمۡنَٰهُ مِن لَّدُنَّا عِلۡمٗا ﴿65﴾

Transliteration: Fawajada AAabdan min AAibadina ataynahu rahmatan min AAindina waAAallamnahu min ladunna AAilman

Translation: 65.ከባሮቻችንም ከእኛ ዘንድ ችሮታን የሰጠነውን ከኛም ዘንድ እውቀትን ያስተማርነውን አንድን ባሪያችንን አገኙ::

18:66

قَالَ لَهُۥ مُوسَىٰ هَلۡ أَتَّبِعُكَ عَلَىٰٓ أَن تُعَلِّمَنِ مِمَّا عُلِّمۡتَ رُشۡدٗا ﴿66﴾

Transliteration: Qala lahu moosa hal attabiAAuka AAala an tuAAallimani mimma AAullimta rushdan

Translation: 66. ሙሳ «ለእርሱ ከተማርከው ነገር ቀጥተኛን እውቀት ታስተምረኝ ዘንድ ልከተልህ?» አለው።

18:67

قَالَ إِنَّكَ لَن تَسۡتَطِيعَ مَعِيَ صَبۡرٗا ﴿67﴾

Transliteration: Qala innaka lan tastateeAAa maAAiya sabran

Translation: 67. ባሪያዉም አለ: «አንተ ከእኔ ጋር መታገስን በጭራሽ አትችልም።

18:68

وَكَيۡفَ تَصۡبِرُ عَلَىٰ مَا لَمۡ تُحِطۡ بِهِۦ خُبۡرٗا ﴿68﴾

Transliteration: Wakayfa tasbiru AAala ma lam tuhit bihi khubran

Translation: 68. «በእውቀት ባልደረስክበት ነገር ላይስ እንዴት ትታገሳለህ?»

18:69

قَالَ سَتَجِدُنِيٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ صَابِرٗا وَلَآ أَعۡصِي لَكَ أَمۡرٗا ﴿69﴾

Transliteration: Qala satajidunee in shaa Allahu sabiran wala aAAsee laka amran

Translation: 69. ሙሳም «አላህ የፈለገ እንደሆነ ታጋሽና ላንተ ትዕዛዝን የማልጥስ ሆኜ ታገኘኛለህ።» አለው።

18:70

قَالَ فَإِنِ ٱتَّبَعۡتَنِي فَلَا تَسۡـَٔلۡنِي عَن شَيۡءٍ حَتَّىٰٓ أُحۡدِثَ لَكَ مِنۡهُ ذِكۡرٗا ﴿70﴾

Transliteration: Qala faini ittabaAAtanee fala tasalnee AAan shayin hatta ohditha laka minhu thikran

Translation: 70. «ብትከተለኝም ላንተ ከእርሱ ማውሳትን እስከምጀምርልህ ድረስ ከምንም ነገር እንዳትጠይቀኝ።» አለው።

18:71

فَٱنطَلَقَا حَتَّىٰٓ إِذَا رَكِبَا فِي ٱلسَّفِينَةِ خَرَقَهَاۖ قَالَ أَخَرَقۡتَهَا لِتُغۡرِقَ أَهۡلَهَا لَقَدۡ جِئۡتَ شَيۡـًٔا إِمۡرٗا ﴿71﴾

Transliteration: Faintalaqa hatta itha rakiba fee alssafeenati kharaqaha qala akharaqtaha litughriqa ahlaha laqad jita shayan imran

Translation: 71. ሄዱም:: በመርከቢቱም በተሳፈሩ ጊዜ መርከቢቱን ቀደዳት። «ባለቤቶችዋን ልታሰምጥ ቀደድካትን? ትልቅን ጥፋት በእርግጥ ሠራህ።» አለው።

18:72

قَالَ أَلَمۡ أَقُلۡ إِنَّكَ لَن تَسۡتَطِيعَ مَعِيَ صَبۡرٗا ﴿72﴾

Transliteration: Qala alam aqul innaka lan tastateeAAa maAAiya sabran

Translation: 72. «አንተ ከእኔ ጋር ትዕግስትን ፈጽሞ አትችልም አላልኩምን?» አለ።

18:73

قَالَ لَا تُؤَاخِذۡنِي بِمَا نَسِيتُ وَلَا تُرۡهِقۡنِي مِنۡ أَمۡرِي عُسۡرٗا ﴿73﴾

Transliteration: Qala la tuakhithnee bima naseetu wala turhiqnee min amree AAusran

Translation: 73. «በረሳሁት ነገር አትያዝብኝ:: ከነገሬም ችግርን አታሸክመኝ።» አለው።

18:74

فَٱنطَلَقَا حَتَّىٰٓ إِذَا لَقِيَا غُلَٰمٗا فَقَتَلَهُۥ قَالَ أَقَتَلۡتَ نَفۡسٗا زَكِيَّةَۢ بِغَيۡرِ نَفۡسٖ لَّقَدۡ جِئۡتَ شَيۡـٔٗا نُّكۡرٗا ﴿74﴾

Transliteration: Faintalaqa hatta itha laqiya ghulaman faqatalahu qala aqatalta nafsan zakiyyatan bighayri nafsin laqad jita shayan nukran

Translation: 74. ወርደው ተጓዙም ወጣቱንም ልጅ ባገኘውና በገደለው ጊዜ «ነፍስን ያልገደለችን ንጹህን ነፍስ ገደልክን? በእርግጥ መጥፎን ነገር ሰራህ።» አለው።

18:75

قَالَ أَلَمۡ أَقُل لَّكَ إِنَّكَ لَن تَسۡتَطِيعَ مَعِيَ صَبۡرٗا ﴿75﴾

Transliteration: Qala alam aqul laka innaka lan tastateeAAa maAAiya sabran

Translation: 75. «አንተ ከእኔ ጋር ትዕግስትን ፈጽሞ አትችልም አላልኩህምን?» አለ።

18:76

قَالَ إِن سَأَلۡتُكَ عَن شَيۡءِۭ بَعۡدَهَا فَلَا تُصَٰحِبۡنِيۖ قَدۡ بَلَغۡتَ مِن لَّدُنِّي عُذۡرٗا ﴿76﴾

Transliteration: Qala in saaltuka AAan shayin baAAdaha fala tusahibnee qad balaghta min ladunnee AAuthran

Translation: 76. «ከአሁኒቱ በኋላ ከምንም ነገር ብጠይቅህ አትጎዳኘኝ:: ከእኔ የይቅርታን መጨረሻ በእርግጥ ደርሰሃል።» አለው።

18:77

فَٱنطَلَقَا حَتَّىٰٓ إِذَآ أَتَيَآ أَهۡلَ قَرۡيَةٍ ٱسۡتَطۡعَمَآ أَهۡلَهَا فَأَبَوۡاْ أَن يُضَيِّفُوهُمَا فَوَجَدَا فِيهَا جِدَارٗا يُرِيدُ أَن يَنقَضَّ فَأَقَامَهُۥۖ قَالَ لَوۡ شِئۡتَ لَتَّخَذۡتَ عَلَيۡهِ أَجۡرٗا ﴿77﴾

Transliteration: Faintalaqa hatta itha ataya ahla qaryatin istatAAama ahlaha faabaw an yudayyifoohuma fawajada feeha jidaran yureedu an yanqadda faaqamahu qala law shita laittakhathta AAalayhi ajran

Translation: 77. ሄዱም። ወደ አንዲት ከተማ ሰዎች ዘንድ ደረሱ ከነዋሪዎች ምግብን ጠየቁ:: (እንደ እንግዳ) ማስተናገዳቸዉንም እምቢ አሉ:: በእርሷም ውስጥ ለመውደቅ የተቃረበን የቤት ግድግዳ አገኙ:: አቆመው:: ሙሳም «ብትፈልግ ኖሮ በእርሱ ላይ ዋጋን በተቀበልክ ነበር።» አለው።

18:78

قَالَ هَٰذَا فِرَاقُ بَيۡنِي وَبَيۡنِكَۚ سَأُنَبِّئُكَ بِتَأۡوِيلِ مَا لَمۡ تَسۡتَطِع عَّلَيۡهِ صَبۡرًا ﴿78﴾

Transliteration: Qala hatha firaqu baynee wabaynika saonabbioka bitaweeli ma lam tastatiAA AAalayhi sabran

Translation: 78. አለም: «ይህ በእኔና ባንተ መካከል መለያያችን ነው። በእርሱ ላይ መታገስን ያልቻለክበትን ፍቺ እነግርሃለሁ።

18:79

أَمَّا ٱلسَّفِينَةُ فَكَانَتۡ لِمَسَٰكِينَ يَعۡمَلُونَ فِي ٱلۡبَحۡرِ فَأَرَدتُّ أَنۡ أَعِيبَهَا وَكَانَ وَرَآءَهُم مَّلِكٞ يَأۡخُذُ كُلَّ سَفِينَةٍ غَصۡبٗا ﴿79﴾

Transliteration: Amma alssafeenatu fakanat limasakeena yaAAmaloona fee albahri faaradtu an aAAeebaha wakana waraahum malikun yakhuthu kulla safeenatin ghasban

Translation: 79. «መርከቢቱማ በባህር ውስጥ ለሚሠሩ ምስኪኖች ነበረች:: ከኋላቸው መርከብን ሁሉ በቅሚያ የሚወስድ ክፉ ንጉስ ነበረና እንዳይቀማቸው ላስነውራት ፈልጌ ነው።

18:80

وَأَمَّا ٱلۡغُلَٰمُ فَكَانَ أَبَوَاهُ مُؤۡمِنَيۡنِ فَخَشِينَآ أَن يُرۡهِقَهُمَا طُغۡيَٰنٗا وَكُفۡرٗا ﴿80﴾

Transliteration: Waamma alghulamu fakana abawahu muminayni fakhasheena an yurhiqahuma tughyanan wakufran

Translation: 80. «ያ ወጣቱም ልጅ ወላጆቹ አማኞች ነበሩ:: ቢያድግ በትዕቢትና በክህደት ወላጆቹን የሚያስገድዳቸው መሆኑን ፈራን።

18:81

فَأَرَدۡنَآ أَن يُبۡدِلَهُمَا رَبُّهُمَا خَيۡرٗا مِّنۡهُ زَكَوٰةٗ وَأَقۡرَبَ رُحۡمٗا ﴿81﴾

Transliteration: Faaradna an yubdilahuma rabbuhuma khayran minhu zakatan waaqraba ruhman

Translation: 81. «ጌታቸው በንጹሕነት ከእርሱ በላጭን፤ በእዝነትም ከእርሱ በጣም ቀራቢን ልጅ ሊለውጥላቸው ፈለግን።

18:82

وَأَمَّا ٱلۡجِدَارُ فَكَانَ لِغُلَٰمَيۡنِ يَتِيمَيۡنِ فِي ٱلۡمَدِينَةِ وَكَانَ تَحۡتَهُۥ كَنزٞ لَّهُمَا وَكَانَ أَبُوهُمَا صَٰلِحٗا فَأَرَادَ رَبُّكَ أَن يَبۡلُغَآ أَشُدَّهُمَا وَيَسۡتَخۡرِجَا كَنزَهُمَا رَحۡمَةٗ مِّن رَّبِّكَۚ وَمَا فَعَلۡتُهُۥ عَنۡ أَمۡرِيۚ ذَٰلِكَ تَأۡوِيلُ مَا لَمۡ تَسۡطِع عَّلَيۡهِ صَبۡرٗا ﴿82﴾

Transliteration: Waamma aljidaru fakana lighulamayni yateemayni fee almadeenati wakana tahtahu kanzun lahuma wakana aboohuma salihan faarada rabbuka an yablugha ashuddahuma wayastakhrija kanzahuma rahmatan min rabbika wama faAAaltuhu AAan amree thalika taweelu ma lam tastiAA AAalayhi sabran

Translation: 82. «ግድግዳዉም በከተማይቱ ውስጥ የነበሩ የሁለት የቲሞች ወጣቶች ነበር:: በስሩም ለእነርሱ የሆነ የተቀበረ ድልብ ነበረና አባታቸዉም መልካም ሰው ነበር:: ጌታህም ለአካለ መጠን እንዲደርሱና ከጌታህ ችሮታ ድልባቸውን እንዲያወጡ ፈቀደ:: በፈቃዴም አልሠራሁትም:: ይህ ያ በእርሱ ላይ መታገስን ያልቻልከው ነገር ፍቹ ነው።» አለው።

18:83

وَيَسۡـَٔلُونَكَ عَن ذِي ٱلۡقَرۡنَيۡنِۖ قُلۡ سَأَتۡلُواْ عَلَيۡكُم مِّنۡهُ ذِكۡرًا ﴿83﴾

Transliteration: Wayasaloonaka AAan thee alqarnayni qul saatloo AAalaykum minhu thikran

Translation: 83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ስለ ዙልቀርነይንም ይጠይቁሀል:: «በእናንተ ላይ ከእርሱ ወሬን (ማስታወሻን) አነባለሁ።» በላቸው።

18:84

إِنَّا مَكَّنَّا لَهُۥ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَءَاتَيۡنَٰهُ مِن كُلِّ شَيۡءٖ سَبَبٗا ﴿84﴾

Transliteration: Inna makkanna lahu fee alardi waataynahu min kulli shayin sababan

Translation: 84.እኛ እርሱን በምድር ላይ አስመቸነው:: በነገሩም ሁሉ መዳረሻ መንገድን ሰጠነው::

18:85

فَأَتۡبَعَ سَبَبًا ﴿85﴾

Transliteration: FaatbaAAa sababan

Translation: 85. መንገድንም (ወደ ምዕራብ) ተከተለ::

18:86

حَتَّىٰٓ إِذَا بَلَغَ مَغۡرِبَ ٱلشَّمۡسِ وَجَدَهَا تَغۡرُبُ فِي عَيۡنٍ حَمِئَةٖ وَوَجَدَ عِندَهَا قَوۡمٗاۖ قُلۡنَا يَٰذَا ٱلۡقَرۡنَيۡنِ إِمَّآ أَن تُعَذِّبَ وَإِمَّآ أَن تَتَّخِذَ فِيهِمۡ حُسۡنٗا ﴿86﴾

Transliteration: Hatta itha balagha maghriba alshshamsi wajadaha taghrubu fee AAaynin hamiatin wawajada AAindaha qawman qulna ya tha alqarnayni imma an tuAAaththiba waimma an tattakhitha feehim husnan

Translation: 86. ወደ ጸሐይ መግቢያም በደረሰ ጊዜ ጥቁር ጭቃማ ምንጭ ውስጥ ስትጠልቅ አገኛት:: በአጠገቧም ህዝቦችን አገኘ:: «ዙልቀርነይን ሆይ! ወይም በመግደል ትቀጣለህ፤ ወይም በእነርሱ መልካም ነገርን ትሠራለህ።» አልነው።

18:87

قَالَ أَمَّا مَن ظَلَمَ فَسَوۡفَ نُعَذِّبُهُۥ ثُمَّ يُرَدُّ إِلَىٰ رَبِّهِۦ فَيُعَذِّبُهُۥ عَذَابٗا نُّكۡرٗا ﴿87﴾

Transliteration: Qala amma man thalama fasawfa nuAAaththibuhu thumma yuraddu ila rabbihi fayuAAaththibuhu AAathaban nukran

Translation: 87. (እርሱም) አለ: «የበደለውንማ ወደፊት እንቀጣዋለን ከዚያ ወደ ጌታው ይመለሳል:: ብርቱንም ቅጣት ይቀጣዋል።

18:88

وَأَمَّا مَنۡ ءَامَنَ وَعَمِلَ صَٰلِحٗا فَلَهُۥ جَزَآءً ٱلۡحُسۡنَىٰۖ وَسَنَقُولُ لَهُۥ مِنۡ أَمۡرِنَا يُسۡرٗا ﴿88﴾

Transliteration: Waamma man amana waAAamila salihan falahu jazaan alhusna wasanaqoolu lahu min amrina yusran

Translation: 88. «ያመነና መልካምን ሥራ የሰራ ለእርሱ ከምንዳ በኩል መልካሚቱ ገነት አለችው:: ለእርሱም ከትዕዛዛችን ገርን ነገር እናዘዋለን።» አለ።

18:89

ثُمَّ أَتۡبَعَ سَبَبًا ﴿89﴾

Transliteration: Thumma atbaAAa sababan

Translation: 89-. ከዚያ መንገድን (ወደ ምስራቅ) ቀጠለ::

18:90

حَتَّىٰٓ إِذَا بَلَغَ مَطۡلِعَ ٱلشَّمۡسِ وَجَدَهَا تَطۡلُعُ عَلَىٰ قَوۡمٖ لَّمۡ نَجۡعَل لَّهُم مِّن دُونِهَا سِتۡرٗا ﴿90﴾

Transliteration: Hatta itha balagha matliAAa alshshamsi wajadaha tatluAAu AAala qawmin lam najAAal lahum min dooniha sitran

Translation: 90.ወደ ጸሐይ መውጫ በደረሰም ጊዜ ለእነርሱ ከበታቹ መከለያን ባላደረግንላቸው ህዝቦች ላይ ስትወጣ አገኛት::

18:91

كَذَٰلِكَۖ وَقَدۡ أَحَطۡنَا بِمَا لَدَيۡهِ خُبۡرٗا ﴿91﴾

Transliteration: Kathalika waqad ahatna bima ladayhi khubran

Translation: 91.ነገሩ ልክ እንደዚሁ ነው:: እርሱም ዘንድ ባለው ነገር ሁሉ በእርግጥ በእውቀት ከበብን::

18:92

ثُمَّ أَتۡبَعَ سَبَبًا ﴿92﴾

Transliteration: Thumma atbaAAa sababan

Translation: 92. ከዚያ (ወደ ሰሜን አቅጣጫ) መንገድን ቀጠለ::

18:93

حَتَّىٰٓ إِذَا بَلَغَ بَيۡنَ ٱلسَّدَّيۡنِ وَجَدَ مِن دُونِهِمَا قَوۡمٗا لَّا يَكَادُونَ يَفۡقَهُونَ قَوۡلٗا ﴿93﴾

Transliteration: Hatta itha balagha bayna alssaddayni wajada min doonihima qawman la yakadoona yafqahoona qawlan

Translation: 93.በሁለቱ ጋራዎችም መካከል በደረሰ ጊዜ በአቅራቢያቸው ንግግርን ለማወቅ የማይቃረቡ ህዝቦችን አገኘ::

18:94

قَالُواْ يَٰذَا ٱلۡقَرۡنَيۡنِ إِنَّ يَأۡجُوجَ وَمَأۡجُوجَ مُفۡسِدُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَهَلۡ نَجۡعَلُ لَكَ خَرۡجًا عَلَىٰٓ أَن تَجۡعَلَ بَيۡنَنَا وَبَيۡنَهُمۡ سَدّٗا ﴿94﴾

Transliteration: Qaloo ya tha alqarnayni inna yajooja wamajooja mufsidoona fee alardi fahal najAAalu laka kharjan AAala an tajAAala baynana wabaynahum saddan

Translation: 94. «ዙልቀርነይን ሆይ! የዕጁጅና መዕጁጅ በምድር ላይ አበላሾች ናቸው። ግብር እናድርግልህና በእኛና በእነርሱ መካከል ግድብን ታደርግልን?» አሉ።

18:95

قَالَ مَا مَكَّنِّي فِيهِ رَبِّي خَيۡرٞ فَأَعِينُونِي بِقُوَّةٍ أَجۡعَلۡ بَيۡنَكُمۡ وَبَيۡنَهُمۡ رَدۡمًا ﴿95﴾

Transliteration: Qala ma makkannee feehi rabbee khayrun faaAAeenoonee biquwwatin ajAAal baynakum wabaynahum radman

Translation: 95. (እርሱም) አለ: «ጌታዬ ያስመቸብኝ ሀብት ከናንተ ግብር በላጭ ነው:: እናም በጉልበት ብቻ እገዙኝ:: በእናንተና በእነርሱ መካከል ብርቱን ግድብ አደርጋለሁና።

18:96

ءَاتُونِي زُبَرَ ٱلۡحَدِيدِۖ حَتَّىٰٓ إِذَا سَاوَىٰ بَيۡنَ ٱلصَّدَفَيۡنِ قَالَ ٱنفُخُواْۖ حَتَّىٰٓ إِذَا جَعَلَهُۥ نَارٗا قَالَ ءَاتُونِيٓ أُفۡرِغۡ عَلَيۡهِ قِطۡرٗا ﴿96﴾

Transliteration: Atoonee zubara alhadeedi hatta itha sawa bayna alsadafayni qala onfukhoo hatta itha jaAAalahu naran qala atoonee ofrigh AAalayhi qitran

Translation: 96. «የብረትን ታላላቅ ቁራጮች ስጡኝ።» አላቸው:: በሁለቱ ኮረብታዎች ጫፍ መካከልም ባስተካከለ ጊዜ «አናፉ» አላቸው። ብረቱን እሳትም ባደረገው ጊዜም: «የቀለጠውን ነሀስ ስጡኝ በእርሱ ላይ አፈስበታለሁና።» አላቸው።

18:97

فَمَا ٱسۡطَٰعُوٓاْ أَن يَظۡهَرُوهُ وَمَا ٱسۡتَطَٰعُواْ لَهُۥ نَقۡبٗا ﴿97﴾

Transliteration: Fama istaAAoo an yathharoohu wama istataAAoo lahu naqban

Translation: 97. የእጁጅና መእጁጅ ይህን መከላከያ ሊወጡት አልቻሉም:: ለእርሱ መሸንቆሩንም እንኳን አልቻሉም።

18:98

قَالَ هَٰذَا رَحۡمَةٞ مِّن رَّبِّيۖ فَإِذَا جَآءَ وَعۡدُ رَبِّي جَعَلَهُۥ دَكَّآءَۖ وَكَانَ وَعۡدُ رَبِّي حَقّٗا ﴿98﴾

Transliteration: Qala hatha rahmatun min rabbee faitha jaa waAAdu rabbee jaAAalahu dakkaa wakana waAAdu rabbee haqqan

Translation: 98. «ይህ ግድብ ከጌታዬ ችሮታዎች ነው:: የጌታዬ ቀጠሮ በመጣ ጊዜ እንኩትኩት ያደርገዋል:: የጌታዬም ቀጠሮ የተረጋገጠ ነው።» አለ።

18:99

وَتَرَكۡنَا بَعۡضَهُمۡ يَوۡمَئِذٖ يَمُوجُ فِي بَعۡضٖۖ وَنُفِخَ فِي ٱلصُّورِ فَجَمَعۡنَٰهُمۡ جَمۡعٗا ﴿99﴾

Transliteration: Watarakna baAAdahum yawmaithin yamooju fee baAAdin wanufikha fee alssoori fajamaAAnahum jamAAan

Translation: 99. በዚያን ቀን ከፊላቸውን በከፊሉ የሚቀላቀሉ አድርገን እንተዋቸዋለን:: በቀንዱም ይነፋል:: መሰብሰብንም እንሰበስባቸዋለን::

18:100

وَعَرَضۡنَا جَهَنَّمَ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡكَٰفِرِينَ عَرۡضًا ﴿100﴾

Transliteration: WaAAaradna jahannama yawmaithin lilkafireena AAardan

Translation: 100. ገሀነምንም በዚያ ቀን ለከሓዲያን በጣም ማቅረብን እናቀርባታለን::

18:101

ٱلَّذِينَ كَانَتۡ أَعۡيُنُهُمۡ فِي غِطَآءٍ عَن ذِكۡرِي وَكَانُواْ لَا يَسۡتَطِيعُونَ سَمۡعًا ﴿101﴾

Transliteration: Allatheena kanat aAAyunuhum fee ghitain AAan thikree wakanoo la yastateeAAoona samAAan

Translation: 101.ለእነዚያ አይኖቻቸው ከግሳጼዬ በሽፋን ውስጥ ለነበሩትና መስማትንም የማይችሉ ለነበሩት እናቀርባታለን::

18:102

أَفَحَسِبَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ أَن يَتَّخِذُواْ عِبَادِي مِن دُونِيٓ أَوۡلِيَآءَۚ إِنَّآ أَعۡتَدۡنَا جَهَنَّمَ لِلۡكَٰفِرِينَ نُزُلٗا ﴿102﴾

Transliteration: Afahasiba allatheena kafaroo an yattakhithoo AAibadee min doonee awliyaa inna aAAtadna jahannama lilkafireena nuzulan

Translation: 102. እነዚያ በእኔ የካዱት ባሮቼን ከኔ ሌላ አማልክት አድርገው መያዛቸውን የማያስቆጣኝ አድርገው አሰቡን? እኛ ገሀነምን ለከሓዲያን መስተንግዶ አዘጋጅተናል::

18:103

قُلۡ هَلۡ نُنَبِّئُكُم بِٱلۡأَخۡسَرِينَ أَعۡمَٰلًا ﴿103﴾

Transliteration: Qul hal nunabbiokum bialakhsareena aAAmalan

Translation: 103. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (እንዲህ) በላቸው: «በሥራዎች በጣም ከሳሪዎቹን እንንገራችሁን?

18:104

ٱلَّذِينَ ضَلَّ سَعۡيُهُمۡ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَهُمۡ يَحۡسَبُونَ أَنَّهُمۡ يُحۡسِنُونَ صُنۡعًا ﴿104﴾

Transliteration: Allatheena dalla saAAyuhum fee alhayati alddunya wahum yahsaboona annahum yuhsinoona sunAAan

Translation: 104. «እነዚያ እነርሱ ሥራን የሚያሳምሩ የሚመስላቸው ሲሆኑ በቅርቢቱ ህይወት ሥራቸው የጠፋባቸው ናቸው።»

18:105

أُوْلَـٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمۡ وَلِقَآئِهِۦ فَحَبِطَتۡ أَعۡمَٰلُهُمۡ فَلَا نُقِيمُ لَهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ وَزۡنٗا ﴿105﴾

Transliteration: Olaika allatheena kafaroo biayati rabbihim waliqaihi fahabitat aAAmaluhum fala nuqeemu lahum yawma alqiyamati waznan

Translation: 105. እነዚያ እነርሱ በጌታቸው ተዓምራትና መገናኘት የካዱ ናቸው። ሥራዎቻቸዉም ተበላሸ:: ለእነርሱም በትንሳኤ ቀን ሚዛንን አናቆምላቸዉም::

18:106

ذَٰلِكَ جَزَآؤُهُمۡ جَهَنَّمُ بِمَا كَفَرُواْ وَٱتَّخَذُوٓاْ ءَايَٰتِي وَرُسُلِي هُزُوًا ﴿106﴾

Transliteration: Thalika jazaohum jahannamu bima kafaroo waittakhathoo ayatee warusulee huzuwan

Translation: 106. ነገሩ ይህ ነው:: በክህደታቸው፣ አንቀፆቼንና መልዕክተኞቼንም መሳለቂያ አድርገው በመያዛቸው ፍዳቸው ገሀነም ነው::

18:107

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّـٰلِحَٰتِ كَانَتۡ لَهُمۡ جَنَّـٰتُ ٱلۡفِرۡدَوۡسِ نُزُلًا ﴿107﴾

Transliteration: Inna allatheena amanoo waAAamiloo alssalihati kanat lahum jannatu alfirdawsi nuzulan

Translation: 107. እነዚያ በአላህ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ፊርደውስ የተባለው የገነት ክፍል ለእነርሱ መስፈሪያ ናቸው::

18:108

خَٰلِدِينَ فِيهَا لَا يَبۡغُونَ عَنۡهَا حِوَلٗا ﴿108﴾

Transliteration: Khalideena feeha la yabghoona AAanha hiwalan

Translation: 108. በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች፤ ከእርሷም መዛወርን የማይፈልጉ ሲሆኑ መስፈሪያቸው ነው።

18:109

قُل لَّوۡ كَانَ ٱلۡبَحۡرُ مِدَادٗا لِّكَلِمَٰتِ رَبِّي لَنَفِدَ ٱلۡبَحۡرُ قَبۡلَ أَن تَنفَدَ كَلِمَٰتُ رَبِّي وَلَوۡ جِئۡنَا بِمِثۡلِهِۦ مَدَدٗا ﴿109﴾

Transliteration: Qul law kana albahru midadan likalimati rabbee lanafida albahru qabla an tanfada kalimatu rabbee walaw jina bimithlihi madadan

Translation: 109. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ባህሩ ለጌታዬ ቃላት መጻፊያ ቀለሞችን ቢሆን ኖሮ ብጤውን ጭማሪ ብናመጣም እንኳ የጌታዬ ቃላት ከማለቋ በፊት ባህሩ ባለቀ ነበር።» በላቸው።

18:110

قُلۡ إِنَّمَآ أَنَا۠ بَشَرٞ مِّثۡلُكُمۡ يُوحَىٰٓ إِلَيَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمۡ إِلَٰهٞ وَٰحِدٞۖ فَمَن كَانَ يَرۡجُواْ لِقَآءَ رَبِّهِۦ فَلۡيَعۡمَلۡ عَمَلٗا صَٰلِحٗا وَلَا يُشۡرِكۡ بِعِبَادَةِ رَبِّهِۦٓ أَحَدَۢا ﴿110﴾

Transliteration: Qul innama ana basharun mithlukum yooha ilayya annama ilahukum ilahun wahidun faman kana yarjoo liqaa rabbihi falyaAAmal AAamalan salihan wala yushrik biAAibadati rabbihi ahadan

Translation: 110. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ መሰላችሁ ሰው ነኝ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው የሚል መልዕክት ወደ እኔ የሚወረድልኝ:: እናም ከጌታው ጋር መገናኘት የሚፈልግ ሰው ሁሉ መልካም ሥራን ይሥራ:: በጌታዉም መገዛት ላይ አንድንም አያጋራ።» በላቸው።

Transliteration source: English Transliteration by Tanzil. Used under Tanzil's non-commercial terms; see the source and latest updates at Tanzil. Tanzil translation download