quranm◉

Surah Al-Mu'minun transliteration

◉ ሱራ · ∞

23:1

قَدۡ أَفۡلَحَ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ ﴿1﴾

Transliteration: Qad aflaha almuminoona

Translation: 1.ምእምናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ተሳካላቸው)::

23:2

ٱلَّذِينَ هُمۡ فِي صَلَاتِهِمۡ خَٰشِعُونَ ﴿2﴾

Transliteration: Allatheena hum fee salatihim khashiAAoona

Translation: 2. እነዚያም በስግደታቸው ውስጥ አላህን ፈሪዎች የሆኑት፤

23:3

وَٱلَّذِينَ هُمۡ عَنِ ٱللَّغۡوِ مُعۡرِضُونَ ﴿3﴾

Transliteration: Waallatheena hum AAani allaghwi muAAridoona

Translation: 3. እነዚያም ከመጥፎ ነገር ሁሉ የራቁ::

23:4

وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِلزَّكَوٰةِ فَٰعِلُونَ ﴿4﴾

Transliteration: Waallatheena hum lilzzakati faAAiloona

Translation: 4. እነዚያም ዘካን በአግባቡ ሰጪዎች፤

23:5

وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِفُرُوجِهِمۡ حَٰفِظُونَ ﴿5﴾

Transliteration: Waallatheena hum lifuroojihim hafithoona

Translation: 5. እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት፤

23:6

إِلَّا عَلَىٰٓ أَزۡوَٰجِهِمۡ أَوۡ مَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُهُمۡ فَإِنَّهُمۡ غَيۡرُ مَلُومِينَ ﴿6﴾

Transliteration: Illa AAala azwajihim aw ma malakat aymanuhum fainnahum ghayru maloomeena

Translation: 6. በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዟቸው ሴት ባሪያዎች ላይ ካልሆነ በቀር (ብልቶቻቸውን ጠባቂ የሆኑት)፤ እነርሱ በነዚህ የማይወቀሱ ናቸውና።

23:7

فَمَنِ ٱبۡتَغَىٰ وَرَآءَ ذَٰلِكَ فَأُوْلَـٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡعَادُونَ ﴿7﴾

Transliteration: Famani ibtagha waraa thalika faolaika humu alAAadoona

Translation: 7. ከዚህ ሌላ በሆነ መንገድ (ስሜታቸዉን ሊያረኩ) የፈለጉ ሰዎች እነዚያ እነርሱ የአላህን ወሰን አላፊዎች ናቸው::

23:8

وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِأَمَٰنَٰتِهِمۡ وَعَهۡدِهِمۡ رَٰعُونَ ﴿8﴾

Transliteration: Waallatheena hum liamanatihim waAAahdihim raAAoona

Translation: 8. እነዚያም ለአደራዎቻቸውና ለቃል ኪዳናቸው ጠባቂዎች፤

23:9

وَٱلَّذِينَ هُمۡ عَلَىٰ صَلَوَٰتِهِمۡ يُحَافِظُونَ ﴿9﴾

Transliteration: Waallatheena hum AAala salawatihim yuhafithoona

Translation: 9. እነዚያም በስግደቶቻቸው ላይ (ሁለንተናዋን) የሚጠባበቁ የሆኑት

23:10

أُوْلَـٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡوَٰرِثُونَ ﴿10﴾

Transliteration: Olaika humu alwarithoona

Translation: 10. እነዚያ ወራሾቹ እነርሱ ናቸው::

23:11

ٱلَّذِينَ يَرِثُونَ ٱلۡفِرۡدَوۡسَ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ ﴿11﴾

Transliteration: Allatheena yarithoona alfirdawsa hum feeha khalidoona

Translation: 11. እነዚያ ፊርደውስን (ላዕላይ ገነትን) የሚወርሱ ናቸው:: እነርሱ በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች እነርሱ ብቻ ናቸው::

23:12

وَلَقَدۡ خَلَقۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ مِن سُلَٰلَةٖ مِّن طِينٖ ﴿12﴾

Transliteration: Walaqad khalaqna alinsana min sulalatin min teenin

Translation: 12. በእርግጥ ሰውን (አደምን) ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው::

23:13

ثُمَّ جَعَلۡنَٰهُ نُطۡفَةٗ فِي قَرَارٖ مَّكِينٖ ﴿13﴾

Transliteration: Thumma jaAAalnahu nutfatan fee qararin makeenin

Translation: 13. ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ የፍትወት ጠብታ አደረግነው::

23:14

ثُمَّ خَلَقۡنَا ٱلنُّطۡفَةَ عَلَقَةٗ فَخَلَقۡنَا ٱلۡعَلَقَةَ مُضۡغَةٗ فَخَلَقۡنَا ٱلۡمُضۡغَةَ عِظَٰمٗا فَكَسَوۡنَا ٱلۡعِظَٰمَ لَحۡمٗا ثُمَّ أَنشَأۡنَٰهُ خَلۡقًا ءَاخَرَۚ فَتَبَارَكَ ٱللَّهُ أَحۡسَنُ ٱلۡخَٰلِقِينَ ﴿14﴾

Transliteration: Thumma khalaqna alnnutfata AAalaqatan fakhalaqna alAAalaqata mudghatan fakhalaqna almudghata AAithaman fakasawna alAAithama lahman thumma anshanahu khalqan akhara fatabaraka Allahu ahsanu alkhaliqeena

Translation: 14. ከዚያም ጠብታዋን (በአርባ ቀን) የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን፤ የረጋውንም ደም ቁራጭ ስጋ አድርገን ፈጠርን፤ ቁራጭዋንም ስጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን:: አጥንቶችንም ስጋን አለበስናቸው። ከዚያም (በዉስጡ ነፍስን በመዝራት) ሌላ ፍጥረት አድርገን አስገኘነው:: ከቅርፅ ሰጪዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ከሁሉ ላቀ።

23:15

ثُمَّ إِنَّكُم بَعۡدَ ذَٰلِكَ لَمَيِّتُونَ ﴿15﴾

Transliteration: Thumma innakum baAAda thalika lamayyitoona

Translation: 15. (ሰዎች ሆይ!) ከዚያም እናንተ ከዚህ በኋላ በእርግጥ ሟቾች ናችሁ::

23:16

ثُمَّ إِنَّكُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ تُبۡعَثُونَ ﴿16﴾

Transliteration: Thumma innakum yawma alqiyamati tubAAathoona

Translation: 16. ከዚያም እናንተ በትንሳኤ ዕለት ትቀሰቀሳላችሁ::

23:17

وَلَقَدۡ خَلَقۡنَا فَوۡقَكُمۡ سَبۡعَ طَرَآئِقَ وَمَا كُنَّا عَنِ ٱلۡخَلۡقِ غَٰفِلِينَ ﴿17﴾

Transliteration: Walaqad khalaqna fawqakum sabAAa taraiqa wama kunna AAani alkhalqi ghafileena

Translation: 17. በእርግጥም ከበላያችሁ ሰባትን ሰማያት ፈጠርን:: ከፍጥረቶቹም ዘንጊዎች አይደለንም::

23:18

وَأَنزَلۡنَا مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءَۢ بِقَدَرٖ فَأَسۡكَنَّـٰهُ فِي ٱلۡأَرۡضِۖ وَإِنَّا عَلَىٰ ذَهَابِۭ بِهِۦ لَقَٰدِرُونَ ﴿18﴾

Transliteration: Waanzalna mina alssamai maan biqadarin faaskannahu fee alardi wainna AAala thahabin bihi laqadiroona

Translation: 18. ከሰማይም ውሃን በልክ አወረድን:: በምድርም ውስጥ አስቀመጥነው:: እኛም እርሱን በማስወገድ ላይ በእርግጥ ቻዮች ነን::

23:19

فَأَنشَأۡنَا لَكُم بِهِۦ جَنَّـٰتٖ مِّن نَّخِيلٖ وَأَعۡنَٰبٖ لَّكُمۡ فِيهَا فَوَٰكِهُ كَثِيرَةٞ وَمِنۡهَا تَأۡكُلُونَ ﴿19﴾

Transliteration: Faanshana lakum bihi jannatin min nakheelin waaAAnabin lakum feeha fawakihu katheeratun waminha takuloona

Translation: 19. በእርሱም ከዘምባባዎችና ከወይኖች አትክልቶችን ለእናንተ አስገኘንላችሁ:: በውስጧ ለእናንተ ብዙ ፍራፍሬዎች አሏችሁ:: ከእርሷም ትበላላችሁ::

23:20

وَشَجَرَةٗ تَخۡرُجُ مِن طُورِ سَيۡنَآءَ تَنۢبُتُ بِٱلدُّهۡنِ وَصِبۡغٖ لِّلۡأٓكِلِينَ ﴿20﴾

Transliteration: Washajaratan takhruju min toori saynaa tanbutu bialdduhni wasibghin lilakileena

Translation: 20. ከሲና ተራራም የምትወጣ ዛፍ በቅባትና ለበይዎች መባያ በሚሆን ዘይት ተቀላቅላ የምትበቅልን አስገኘንላችሁ::

23:21

وَإِنَّ لَكُمۡ فِي ٱلۡأَنۡعَٰمِ لَعِبۡرَةٗۖ نُّسۡقِيكُم مِّمَّا فِي بُطُونِهَا وَلَكُمۡ فِيهَا مَنَٰفِعُ كَثِيرَةٞ وَمِنۡهَا تَأۡكُلُونَ ﴿21﴾

Transliteration: Wainna lakum fee alanAAami laAAibratan nusqeekum mimma fee butooniha walakum feeha manafiAAu katheeratun waminha takuloona

Translation: 21. (ሰዎች ሆይ!) እናንተም በግመል፤ በከብት በፍየልና በበግ መገምገሚያ አላችሁ:: በሆዶችዋ ውስጥ ካለው ወተት እናጠጣችኋለን:: ለእናንተም በእርሷ ብዙ ጥቅሞች አሏችሁ:: ከእርሷም ትበላላችሁ::

23:22

وَعَلَيۡهَا وَعَلَى ٱلۡفُلۡكِ تُحۡمَلُونَ ﴿22﴾

Transliteration: WaAAalayha waAAala alfulki tuhmaloona

Translation: 22. በእርሷም ላይና በመርከብም ላይ ትጫናላችሁ::

23:23

وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوۡمِهِۦ فَقَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥٓۚ أَفَلَا تَتَّقُونَ ﴿23﴾

Transliteration: Walaqad arsalna noohan ila qawmihi faqala ya qawmi oAAbudoo Allaha ma lakum min ilahin ghayruhu afala tattaqoona

Translation: 23. ኑሕን ወደ ህዝቦቹ በእርግጥ ላክነው። ወዲያዉም «ህዝቦቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም:: አትጠነቀቁምን?» አላቸው።

23:24

فَقَالَ ٱلۡمَلَؤُاْ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِن قَوۡمِهِۦ مَا هَٰذَآ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُكُمۡ يُرِيدُ أَن يَتَفَضَّلَ عَلَيۡكُمۡ وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ لَأَنزَلَ مَلَـٰٓئِكَةٗ مَّا سَمِعۡنَا بِهَٰذَا فِيٓ ءَابَآئِنَا ٱلۡأَوَّلِينَ ﴿24﴾

Transliteration: Faqala almalao allatheena kafaroo min qawmihi ma hatha illa basharun mithlukum yureedu an yatafaddala AAalaykum walaw shaa Allahu laanzala malaikatan ma samiAAna bihatha fee abaina alawwaleena

Translation: 24. ከህዝቦቹም እነዚያ ታላላቆቹ ሰዎች አሉ: «ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም። በእናንተ ላይ መብለጥን ይፈልጋል። አላህም ቢፈልግ ኖሮ መላእክትን ባወረደ ነበር። ይህንንም የሚለውን በመጀመሪያዎቹ አባቶቻችን አልሰማንም።

23:25

إِنۡ هُوَ إِلَّا رَجُلُۢ بِهِۦ جِنَّةٞ فَتَرَبَّصُواْ بِهِۦ حَتَّىٰ حِينٖ ﴿25﴾

Transliteration: In huwa illa rajulun bihi jinnatun fatarabbasoo bihi hatta heenin

Translation: 25. «እርሱ እብደት ያለበት ሰው እንጂ ሌላ አይደለም:: በእርሱም እስከ ጊዜው ድረስ ተጠባበቁ።» አሉ።

23:26

قَالَ رَبِّ ٱنصُرۡنِي بِمَا كَذَّبُونِ ﴿26﴾

Transliteration: Qala rabbi onsurnee bima kaththabooni

Translation: 26. ኑሕም «ጌታዬ ሆይ! ስለ አስተባበሉኝ እርዳኝ።» አለ።

23:27

فَأَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡهِ أَنِ ٱصۡنَعِ ٱلۡفُلۡكَ بِأَعۡيُنِنَا وَوَحۡيِنَا فَإِذَا جَآءَ أَمۡرُنَا وَفَارَ ٱلتَّنُّورُ فَٱسۡلُكۡ فِيهَا مِن كُلّٖ زَوۡجَيۡنِ ٱثۡنَيۡنِ وَأَهۡلَكَ إِلَّا مَن سَبَقَ عَلَيۡهِ ٱلۡقَوۡلُ مِنۡهُمۡۖ وَلَا تُخَٰطِبۡنِي فِي ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓاْ إِنَّهُم مُّغۡرَقُونَ ﴿27﴾

Transliteration: Faawhayna ilayhi ani isnaAAi alfulka biaAAyunina wawahyina faitha jaa amruna wafara alttannooru faosluk feeha min kullin zawjayni ithnayni waahlaka illa man sabaqa AAalayhi alqawlu minhum wala tukhatibnee fee allatheena thalamoo innahum mughraqoona

Translation: 27. ወደ እርሱ እንዲህ ስንል ላክን: «በተመልካችነታችንና በትእዛዛችን ታንኳን ስራ። ከዚያ ትእዛዛችን በመጣና ምድጃው (እቶኑ) በፈለቀ ጊዜ በውስጧ ከሁሉም ነገር ሁለት ሁለት ዓይነቶችንና ቤተሰቦችህን ከእነርሱ መካከል ጠፊ በመሆኑ ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር አስገባ። በእነዚያ ራሳቸውን በአላህ በመካድ በበደሉት ሰዎች ጉዳይ አታነጋግረኝ። እነርሱ በውኃ ተሰማጪዎች ናቸውና።

23:28

فَإِذَا ٱسۡتَوَيۡتَ أَنتَ وَمَن مَّعَكَ عَلَى ٱلۡفُلۡكِ فَقُلِ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِي نَجَّىٰنَا مِنَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلظَّـٰلِمِينَ ﴿28﴾

Transliteration: Faitha istawayta anta waman maAAaka AAala alfulki faquli alhamdu lillahi allathee najjana mina alqawmi alththalimeena

Translation: 28. አንተም አብረውህ ካሉት ፍጡሮች ጋር በታንኳይቱ ላይ በተደላደልክ ጊዜ በል: «ምስጋና ሁሉ ለዚያ ከበደለኛ ህዝቦች ላዳነን አላህ ይገባው።

23:29

وَقُل رَّبِّ أَنزِلۡنِي مُنزَلٗا مُّبَارَكٗا وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلۡمُنزِلِينَ ﴿29﴾

Transliteration: Waqul rabbi anzilnee munzalan mubarakan waanta khayru almunzileena

Translation: 29. «ጌታዬ ሆይ! ብሩክ የሆነን ማውረድ አውርደኝ:: አንተም ከአደላዳዮች ሁሉ በላጭ ነህና።» በል።

23:30

إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ وَإِن كُنَّا لَمُبۡتَلِينَ ﴿30﴾

Transliteration: Inna fee thalika laayatin wain kunna lamubtaleena

Translation: 30. በዚህ ውስጥ ለሃያልነታችን አያሌ ተዓምራት አሉበት:: እነሆ እኛ (የኑሕን ሰዎች) ፈታኞች ነበርን::

23:31

ثُمَّ أَنشَأۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِمۡ قَرۡنًا ءَاخَرِينَ ﴿31﴾

Transliteration: Thumma anshana min baAAdihim qarnan akhareena

Translation: 31. ከዚያ ከኋላቸው ሌሎችን የክፍለ ዘመናት ህዝቦች አስገኘን::

23:32

فَأَرۡسَلۡنَا فِيهِمۡ رَسُولٗا مِّنۡهُمۡ أَنِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥٓۚ أَفَلَا تَتَّقُونَ ﴿32﴾

Transliteration: Faarsalna feehim rasoolan minhum ani oAAbudoo Allaha ma lakum min ilahin ghayruhu afala tattaqoona

Translation: 32. በውስጣቸዉም ከእነርሱ የሆኑን መልዕክተኛ አላህን ተገዙ ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የላችሁም:: አትጠነቀቁምን? በማለት ላክን።

23:33

وَقَالَ ٱلۡمَلَأُ مِن قَوۡمِهِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَكَذَّبُواْ بِلِقَآءِ ٱلۡأٓخِرَةِ وَأَتۡرَفۡنَٰهُمۡ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا مَا هَٰذَآ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُكُمۡ يَأۡكُلُ مِمَّا تَأۡكُلُونَ مِنۡهُ وَيَشۡرَبُ مِمَّا تَشۡرَبُونَ ﴿33﴾

Transliteration: Waqala almalao min qawmihi allatheena kafaroo wakaththaboo biliqai alakhirati waatrafnahum fee alhayati alddunya ma hatha illa basharun mithlukum yakulu mimma takuloona minhu wayashrabu mimma tashraboona

Translation: 33. ከህዝቦቹም እነዚያ የካዱት ሰዎች በመጨረሻይቱም ቀን መገናኘት ያስተባበሉት በቅርቢቱም ህይወት ያቀማጠልናቸው ታላላቅ ሰዎች አሉ: «ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም። ከምትበሉት ምግብ ይበላል፤ ከምትጠጡትም ውሃ ይጠጣል።

23:34

وَلَئِنۡ أَطَعۡتُم بَشَرٗا مِّثۡلَكُمۡ إِنَّكُمۡ إِذٗا لَّخَٰسِرُونَ ﴿34﴾

Transliteration: Walain ataAAtum basharan mithlakum innakum ithan lakhasiroona

Translation: 34. «የናንተው ብጤያችሁ የሆነን ሰው ብትታዘዙ በእርግጥ የተሞኛችሁ ናችሁ።

23:35

أَيَعِدُكُمۡ أَنَّكُمۡ إِذَا مِتُّمۡ وَكُنتُمۡ تُرَابٗا وَعِظَٰمًا أَنَّكُم مُّخۡرَجُونَ ﴿35﴾

Transliteration: AyaAAidukum annakum itha mittum wakuntum turaban waAAithaman annakum mukhrajoona

Translation: 35. «‹እናንተ ሞታችሁ አፈርና አጥንቶችም በሆናችሁ ጊዜ እናንተ ከመቃብር ትወጣላችሁ› በማለት ያስፈራራችኋልን?

23:36

هَيۡهَاتَ هَيۡهَاتَ لِمَا تُوعَدُونَ ﴿36﴾

Transliteration: Hayhata hayhata lima tooAAadoona

Translation: 36. «ያ የምትስፈራሩበት ነገር ከእውነት ራቀ፤ በጣም ራቀ

23:37

إِنۡ هِيَ إِلَّا حَيَاتُنَا ٱلدُّنۡيَا نَمُوتُ وَنَحۡيَا وَمَا نَحۡنُ بِمَبۡعُوثِينَ ﴿37﴾

Transliteration: In hiya illa hayatuna alddunya namootu wanahya wama nahnu bimabAAootheena

Translation: 37. «እርሷ (ህይወት) ማለት ቅርቢቱ ህይወታችን ብቻ እንጂ ሌላ አይደለችም:: እንሞታለን። ህያዉም እንሆናለን። እኛም ፈጽሞ ተቀስቃሾች አይደለንም" (አሉ)።

23:38

إِنۡ هُوَ إِلَّا رَجُلٌ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبٗا وَمَا نَحۡنُ لَهُۥ بِمُؤۡمِنِينَ ﴿38﴾

Transliteration: In huwa illa rajulun iftara AAala Allahi kathiban wama nahnu lahu bimumineena

Translation: 38. «እርሱ በአላህ ላይ ውሸትን የቀጠፈ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም:: እኛም በእርሱ አማኞች አይደለንም።» አሉ።

23:39

قَالَ رَبِّ ٱنصُرۡنِي بِمَا كَذَّبُونِ ﴿39﴾

Transliteration: Qala rabbi onsurnee bima kaththabooni

Translation: 39. መልዕክተኛዉም «ጌታዬ ሆይ! ስላስተባበሉኝ በእነርሱ ላይ እርዳኝ።» አለ።

23:40

قَالَ عَمَّا قَلِيلٖ لَّيُصۡبِحُنَّ نَٰدِمِينَ ﴿40﴾

Transliteration: Qala AAamma qaleelin layusbihunna nadimeena

Translation: 40. አላህም «ከጥቂት ጊዜ በኋላ በጥፋታቸው በእርግጥ ተጸጻቾች ይሆናሉ።» አለው።

23:41

فَأَخَذَتۡهُمُ ٱلصَّيۡحَةُ بِٱلۡحَقِّ فَجَعَلۡنَٰهُمۡ غُثَآءٗۚ فَبُعۡدٗا لِّلۡقَوۡمِ ٱلظَّـٰلِمِينَ ﴿41﴾

Transliteration: Faakhathathumu alssayhatu bialhaqqi fajaAAalnahum ghuthaan fabuAAdan lilqawmi alththalimeena

Translation: 41. ወዲያዉም (የጥፋት) ጩኸቲቱ በእውነት ያዘቻቸው፤ እንደ ጎርፍ ግብስባሽም አደረግናቸው:: ለበደለኞች ህዝቦችም ከእዝነት መራቅ ተገባቸው::

23:42

ثُمَّ أَنشَأۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِمۡ قُرُونًا ءَاخَرِينَ ﴿42﴾

Transliteration: Thumma anshana min baAAdihim quroonan akhareena

Translation: 42. ከዚያም ከእነርሱ በኋላ ሌሎችን የክፍለ ዘመናት ህዝቦች አስገኘን::

23:43

مَا تَسۡبِقُ مِنۡ أُمَّةٍ أَجَلَهَا وَمَا يَسۡتَـٔۡخِرُونَ ﴿43﴾

Transliteration: Ma tasbiqu min ommatin ajalaha wama yastakhiroona

Translation: 43. ማንኛይቱም ህዝብ ጊዜዋን አትቀድምም:: ከጊዜያቸዉም አይቆዩምም::

23:44

ثُمَّ أَرۡسَلۡنَا رُسُلَنَا تَتۡرَاۖ كُلَّ مَا جَآءَ أُمَّةٗ رَّسُولُهَا كَذَّبُوهُۖ فَأَتۡبَعۡنَا بَعۡضَهُم بَعۡضٗا وَجَعَلۡنَٰهُمۡ أَحَادِيثَۚ فَبُعۡدٗا لِّقَوۡمٖ لَّا يُؤۡمِنُونَ ﴿44﴾

Transliteration: Thumma arsalna rusulana tatra kulla ma jaa ommatan rasooluha kaththaboohu faatbaAAna baAAdahum baAAdan wajaAAalnahum ahadeetha fabuAAdan liqawmin la yuminoona

Translation: 44. ከዚያም መልዕክተኞቻችንን በተከታታይ ላክን፤ ማንኛይቱንም ህዝብ መልእክተኛዋ በመጣላት ቁጥር አስተባበሉት። ከፊላቸውንም በከፊሉ በጥፋት አስከታተልን፤ ወሬዎችም አደረግናቸው፤ ለማያምኑም ህዝቦች ከእዝነታችን መራቅ ተገባቸው።

23:45

ثُمَّ أَرۡسَلۡنَا مُوسَىٰ وَأَخَاهُ هَٰرُونَ بِـَٔايَٰتِنَا وَسُلۡطَٰنٖ مُّبِينٍ ﴿45﴾

Transliteration: Thumma arsalna moosa waakhahu haroona biayatina wasultanin mubeenin

Translation: 45. ከዚያ ሙሳንና ወንድሙን ሃሩንን በተአምራታችንና በግልጽ ማስረጃ ላክናቸው::

23:46

إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ وَمَلَإِيْهِۦ فَٱسۡتَكۡبَرُواْ وَكَانُواْ قَوۡمًا عَالِينَ ﴿46﴾

Transliteration: Ila firAAawna wamalaihi faistakbaroo wakanoo qawman AAaleena

Translation: 46. ወደ ፈርዖንና ወደ ጭፍሮቹ ላክናቸው። ድሮውም የኮሩና የተንበጣረሩ ህዝቦችም ነበሩ።

23:47

فَقَالُوٓاْ أَنُؤۡمِنُ لِبَشَرَيۡنِ مِثۡلِنَا وَقَوۡمُهُمَا لَنَا عَٰبِدُونَ ﴿47﴾

Transliteration: Faqaloo anuminu libasharayni mithlina waqawmuhuma lana AAabidoona

Translation: 47. «ህዝቦቻቸው ለኛ ተገዢዎች ሆነው ሳሉ ብጤያችን ለሆኑ ሰዎች እናምናለን?» አሉ።

23:48

فَكَذَّبُوهُمَا فَكَانُواْ مِنَ ٱلۡمُهۡلَكِينَ ﴿48﴾

Transliteration: Fakaththaboohuma fakanoo mina almuhlakeena

Translation: 48. አስተባበሏቸዉም፤ ከጠፊዎችም ሆኑ::

23:49

وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ لَعَلَّهُمۡ يَهۡتَدُونَ ﴿49﴾

Transliteration: Walaqad atayna moosa alkitaba laAAallahum yahtadoona

Translation: 49. ሙሳንም ነገዶቹ ይመሩ ዘንድ መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው::

23:50

وَجَعَلۡنَا ٱبۡنَ مَرۡيَمَ وَأُمَّهُۥٓ ءَايَةٗ وَءَاوَيۡنَٰهُمَآ إِلَىٰ رَبۡوَةٖ ذَاتِ قَرَارٖ وَمَعِينٖ ﴿50﴾

Transliteration: WajaAAalna ibna maryama waommahu ayatan waawaynahuma ila rabwatin thati qararin wamaAAeenin

Translation: 50. የመርየምን ልጅ ዒሳንና እናቱንም ተዓምር አደረግናቸው:: የመደላደልና የምንጭ ባለቤት ወደ ሆነች ከፍተኛ ስፍራም አስጠጋናቸው::

23:51

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلرُّسُلُ كُلُواْ مِنَ ٱلطَّيِّبَٰتِ وَٱعۡمَلُواْ صَٰلِحًاۖ إِنِّي بِمَا تَعۡمَلُونَ عَلِيمٞ ﴿51﴾

Transliteration: Ya ayyuha alrrusulu kuloo mina alttayyibati waiAAmaloo salihan innee bima taAAmaloona AAaleemun

Translation: 51. እናንተ መልእክተኞች ሆይ! ከተፈቀዱት ምግቦች ሁሉ ብሉ:: በጎ ስራንም ስሩ:: እኔ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነኝና::

23:52

وَإِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمۡ أُمَّةٗ وَٰحِدَةٗ وَأَنَا۠ رَبُّكُمۡ فَٱتَّقُونِ ﴿52﴾

Transliteration: Wainna hathihi ommatukum ommatan wahidatan waana rabbukum faittaqooni

Translation: 52. ይህችም በአንድ አምላክ የማመን ህግጋት አንድ መንገድ ስትሆን ሃይማኖታችሁ ናት:: እኔም ጌታችሁ ነኝና ፍሩኝ::

23:53

فَتَقَطَّعُوٓاْ أَمۡرَهُم بَيۡنَهُمۡ زُبُرٗاۖ كُلُّ حِزۡبِۭ بِمَا لَدَيۡهِمۡ فَرِحُونَ ﴿53﴾

Transliteration: FataqattaAAoo amrahum baynahum zuburan kullu hizbin bima ladayhim farihoona

Translation: 53. ከዚያም ተከታዮቻቸው ሃይማኖታቸውን በመካከላቸው ክፍልፍሎች አድርገው ቆራረጡ፤ ህዝቦች ሁሉ እነርሱ ዘንድ ባለው ሃይማኖት ተደሳቾች ናቸው::

23:54

فَذَرۡهُمۡ فِي غَمۡرَتِهِمۡ حَتَّىٰ حِينٍ ﴿54﴾

Transliteration: Fatharhum fee ghamratihim hatta heenin

Translation: 54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እስከ ጊዜያቸዉም ድረስ በጥመታቸው ውስጥ ተዋቸው::

23:55

أَيَحۡسَبُونَ أَنَّمَا نُمِدُّهُم بِهِۦ مِن مَّالٖ وَبَنِينَ ﴿55﴾

Transliteration: Ayahsaboona annama numidduhum bihi min malin wabaneena

Translation: 55. ከገንዘብና ከልጆች በእርሱ የምንጨምርላቸውን ያስባሉን?

23:56

نُسَارِعُ لَهُمۡ فِي ٱلۡخَيۡرَٰتِۚ بَل لَّا يَشۡعُرُونَ ﴿56﴾

Transliteration: NusariAAu lahum fee alkhayrati bal la yashAAuroona

Translation: 56. በበጎ ነገሮች የምንቻኮልላቸው እንደሆነ ያስባሉን? አይደለም፤ ይህ ሁሉ እነርሱን ለማዘናጋት መሆኑን አያውቁም።

23:57

إِنَّ ٱلَّذِينَ هُم مِّنۡ خَشۡيَةِ رَبِّهِم مُّشۡفِقُونَ ﴿57﴾

Transliteration: Inna allatheena hum min khashyati rabbihim mushfiqoona

Translation: 57. እነዚያ እነርሱ ጌታቸውን ከመፍራት የተነሳ ተጨናቂዎች የሆኑት፤

23:58

وَٱلَّذِينَ هُم بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمۡ يُؤۡمِنُونَ ﴿58﴾

Transliteration: Waallatheena hum biayati rabbihim yuminoona

Translation: 58. እነዚያም እነርሱ በጌታቸው ተዓምራት የሚያምኑት፤

23:59

وَٱلَّذِينَ هُم بِرَبِّهِمۡ لَا يُشۡرِكُونَ ﴿59﴾

Transliteration: Waallatheena hum birabbihim la yushrikoona

Translation: 59. እነዚያም በጌታቸው የማያጋሩት፤

23:60

وَٱلَّذِينَ يُؤۡتُونَ مَآ ءَاتَواْ وَّقُلُوبُهُمۡ وَجِلَةٌ أَنَّهُمۡ إِلَىٰ رَبِّهِمۡ رَٰجِعُونَ ﴿60﴾

Transliteration: Waallatheena yutoona ma ataw waquloobuhum wajilatun annahum ila rabbihim rajiAAoona

Translation: 60. እነዚያም የሚሰጡትን ነገር ሁሉ እነርሱ ወደ ጌታቸው ተመላሾች መሆናቸውን ልቦቻቸው የሚፈሩ ሆነው የሚሰጡ ናቸው::

23:61

أُوْلَـٰٓئِكَ يُسَٰرِعُونَ فِي ٱلۡخَيۡرَٰتِ وَهُمۡ لَهَا سَٰبِقُونَ ﴿61﴾

Transliteration: Olaika yusariAAoona fee alkhayrati wahum laha sabiqoona

Translation: 61. እነዚያ በመልካም ስራዎች ይጣደፋሉ:: እነርሱም ለርሷ ቀዳሚዎች ናቸው::

23:62

وَلَا نُكَلِّفُ نَفۡسًا إِلَّا وُسۡعَهَاۚ وَلَدَيۡنَا كِتَٰبٞ يَنطِقُ بِٱلۡحَقِّ وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ ﴿62﴾

Transliteration: Wala nukallifu nafsan illa wusAAaha waladayna kitabun yantiqu bialhaqqi wahum la yuthlamoona

Translation: 62. ማንኛይቱንም ነፍስ የችሎታዋን ያህል እንጂ አናስገድዳትም:: እኛም ዘንድ በእውነት የሚናገር መጽሐፍ አለ:: እነርሱም አይበደሉም::

23:63

بَلۡ قُلُوبُهُمۡ فِي غَمۡرَةٖ مِّنۡ هَٰذَا وَلَهُمۡ أَعۡمَٰلٞ مِّن دُونِ ذَٰلِكَ هُمۡ لَهَا عَٰمِلُونَ ﴿63﴾

Transliteration: Bal quloobuhum fee ghamratin min hatha walahum aAAmalun min dooni thalika hum laha AAamiloona

Translation: 63. በእውነቱ ከሓዲያን ልቦቻቸው ከዚህ መጽሐፍ በዝንጋታ ውስጥ ናቸው:: ለእነርሱም ከዚህ ሌላ እነርሱ ለእርሷ ሰሪዎችዋ የሆኑ መጥፎ ስራዎች አሏቸው::

23:64

حَتَّىٰٓ إِذَآ أَخَذۡنَا مُتۡرَفِيهِم بِٱلۡعَذَابِ إِذَا هُمۡ يَجۡـَٔرُونَ ﴿64﴾

Transliteration: Hatta itha akhathna mutrafeehim bialAAathabi itha hum yajaroona

Translation: 64. ቅምጥሎቻቸውንም በቅጣት በያዝናቸው ጊዜ ወዲያውኑ እነርሱ ይወተውታሉ::

23:65

لَا تَجۡـَٔرُواْ ٱلۡيَوۡمَۖ إِنَّكُم مِّنَّا لَا تُنصَرُونَ ﴿65﴾

Transliteration: La tajaroo alyawma innakum minna la tunsaroona

Translation: 65. (ይባላሉም) «ዛሬ አትወትውቱ፤ እናንተ ከእኛ ዘንድ አትረዱምና።

23:66

قَدۡ كَانَتۡ ءَايَٰتِي تُتۡلَىٰ عَلَيۡكُمۡ فَكُنتُمۡ عَلَىٰٓ أَعۡقَٰبِكُمۡ تَنكِصُونَ ﴿66﴾

Transliteration: Qad kanat ayatee tutla AAalaykum fakuntum AAala aAAqabikum tankisoona

Translation: 66. «አንቀፆቼ በእናንተ ላይ በእርግጥ ይነበቡላችሁ ነበር። እናንተ ግን በተረከዞቻችሁ ላይ ወደ ኋላችሁ ትመለሱ ነበር።

23:67

مُسۡتَكۡبِرِينَ بِهِۦ سَٰمِرٗا تَهۡجُرُونَ ﴿67﴾

Transliteration: Mustakbireena bihi samiran tahjuroona

Translation: 67. «በእርሱ (በክልሉ ቤት) ኩሩዎች ሌሊት ተጫዋቾች (ቁርኣንንም) የምትተው ሆናችሁ (ትመለሱ ነበር)።» ይባላሉ።

23:68

أَفَلَمۡ يَدَّبَّرُواْ ٱلۡقَوۡلَ أَمۡ جَآءَهُم مَّا لَمۡ يَأۡتِ ءَابَآءَهُمُ ٱلۡأَوَّلِينَ ﴿68﴾

Transliteration: Afalam yaddabbaroo alqawla am jaahum ma lam yati abaahumu alawwaleena

Translation: 68. የቁርኣንን ንግግርን አያስተነትኑምን? ወይስ ለመጀመሪያዎቹ አባቶቻቸው ያልመጣ ነገር መጣባቸውን?

23:69

أَمۡ لَمۡ يَعۡرِفُواْ رَسُولَهُمۡ فَهُمۡ لَهُۥ مُنكِرُونَ ﴿69﴾

Transliteration: Am lam yaAArifoo rasoolahum fahum lahu munkiroona

Translation: 69. ወይስ መልዕክተኛቸውን አላወቁምን? ስለዚህ እነርሱ በእርሱ ከሓዲያን ናቸውን?

23:70

أَمۡ يَقُولُونَ بِهِۦ جِنَّةُۢۚ بَلۡ جَآءَهُم بِٱلۡحَقِّ وَأَكۡثَرُهُمۡ لِلۡحَقِّ كَٰرِهُونَ ﴿70﴾

Transliteration: Am yaqooloona bihi jinnatun bal jaahum bialhaqqi waaktharuhum lilhaqqi karihoona

Translation: 70. ወይስ «በእርሱ ዕብደት አለበት» ይላሉን? እብድ አይደለም። እውነትን ይዞ መጣላቸው:: አብዛኞቻቸዉም ግን እውነትን ጠይዎች ናቸው።

23:71

وَلَوِ ٱتَّبَعَ ٱلۡحَقُّ أَهۡوَآءَهُمۡ لَفَسَدَتِ ٱلسَّمَٰوَٰتُ وَٱلۡأَرۡضُ وَمَن فِيهِنَّۚ بَلۡ أَتَيۡنَٰهُم بِذِكۡرِهِمۡ فَهُمۡ عَن ذِكۡرِهِم مُّعۡرِضُونَ ﴿71﴾

Transliteration: Walawi ittabaAAa alhaqqu ahwaahum lafasadati alssamawatu waalardu waman feehinna bal ataynahum bithikrihim fahum AAan thikrihim muAAridoona

Translation: 71. እውነታው (አላህ) ዝንባሌዎቻቸውን በተከተለ ኖሮ ሰማያትና ምድር በውስጣቸዉም ያለው ሁሉ በእርግጥ በተበላሸ ነበር:: ይልቁንም ክብራቸው ያለበትን ቁርኣን አመጣንላቸው:: እነርሱም ክብራቸውን ዘንጊዎች ናቸው::

23:72

أَمۡ تَسۡـَٔلُهُمۡ خَرۡجٗا فَخَرَاجُ رَبِّكَ خَيۡرٞۖ وَهُوَ خَيۡرُ ٱلرَّـٰزِقِينَ ﴿72﴾

Transliteration: Am tasaluhum kharjan fakharaju rabbika khayrun wahuwa khayru alrraziqeena

Translation: 72. ወይስ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ግብርን ትጠይቃቸዋለህን? የጌታህም ችሮታ ከሁሉም በላጭ ነው:: እርሱም ከሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው::

23:73

وَإِنَّكَ لَتَدۡعُوهُمۡ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ ﴿73﴾

Transliteration: Wainnaka latadAAoohum ila siratin mustaqeemin

Translation: 73.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትጠራቸዋለህ::

23:74

وَإِنَّ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ عَنِ ٱلصِّرَٰطِ لَنَٰكِبُونَ ﴿74﴾

Transliteration: Wainna allatheena la yuminoona bialakhirati AAani alssirati lanakiboona

Translation: 74. እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ሰዎች ግን ከትክክለኛው መንገድ ተዘንባዮች ናቸው።

23:75

وَلَوۡ رَحِمۡنَٰهُمۡ وَكَشَفۡنَا مَا بِهِم مِّن ضُرّٖ لَّلَجُّواْ فِي طُغۡيَٰنِهِمۡ يَعۡمَهُونَ ﴿75﴾

Transliteration: Walaw rahimnahum wakashafna ma bihim min durrin lalajjoo fee tughyanihim yaAAmahoona

Translation: 75. ባዘንላቸውና በእነርሱ ያለውን ጉዳትም ባነሳንላቸው ኖሮ በጥመታቸው ውስጥ የሚዋዥቁ ሆነው ይዘወትሩ ነበር::

23:76

وَلَقَدۡ أَخَذۡنَٰهُم بِٱلۡعَذَابِ فَمَا ٱسۡتَكَانُواْ لِرَبِّهِمۡ وَمَا يَتَضَرَّعُونَ ﴿76﴾

Transliteration: Walaqad akhathnahum bialAAathabi fama istakanoo lirabbihim wama yatadarraAAoona

Translation: 76. በእርግጥም በቅጣት ያዝናቸው:: ታዲያ ለጌታቸው አልተናነሱም:: የሚዋደቁም አይደሉም።

23:77

حَتَّىٰٓ إِذَا فَتَحۡنَا عَلَيۡهِم بَابٗا ذَا عَذَابٖ شَدِيدٍ إِذَا هُمۡ فِيهِ مُبۡلِسُونَ ﴿77﴾

Transliteration: Hatta itha fatahna AAalayhim baban tha AAathabin shadeedin itha hum feehi mublisoona

Translation: 77. በእነርሱም ላይ የብርቱ ቅጣት ባለቤት የሆነ ደጃፍን በከፈትንባቸው ጊዜ እነርሱ ያን ጊዜ በእርሱ ተስፋ ቆራጮች ናቸው::

23:78

وَهُوَ ٱلَّذِيٓ أَنشَأَ لَكُمُ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡأَبۡصَٰرَ وَٱلۡأَفۡـِٔدَةَۚ قَلِيلٗا مَّا تَشۡكُرُونَ ﴿78﴾

Transliteration: Wahuwa allathee anshaa lakumu alssamAAa waalabsara waalafidata qaleelan ma tashkuroona

Translation: 78. እርሱም ያ መስሚያዎችን፤ ማያዎችንና ልቦችን ለእናንተ የፈጠረላችሁ ነው:: ጥቂትን እንጂ አታመሰግኑም::

23:79

وَهُوَ ٱلَّذِي ذَرَأَكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَإِلَيۡهِ تُحۡشَرُونَ ﴿79﴾

Transliteration: Wahuwa allathee tharaakum fee alardi wailayhi tuhsharoona

Translation: 79. እርሱም ያ በምድር ውስጥ የበተናችሁ ነው:: በመጨረሻም ጊዜ ወደ እርሱም ትሰበሰባላችሁ::

23:80

وَهُوَ ٱلَّذِي يُحۡيِۦ وَيُمِيتُ وَلَهُ ٱخۡتِلَٰفُ ٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ ﴿80﴾

Transliteration: Wahuwa allathee yuhyee wayumeetu walahu ikhtilafu allayli waalnnahari afala taAAqiloona

Translation: 80. እርሱም ያ ህያው የሚያደርግ የሚገድልም ነው:: የሌሊትና የቀን መተካካትም የእርሱ ነው :: አታውቁምን?

23:81

بَلۡ قَالُواْ مِثۡلَ مَا قَالَ ٱلۡأَوَّلُونَ ﴿81﴾

Transliteration: Bal qaloo mithla ma qala alawwaloona

Translation: 81. ይልቁንም የመካ ከሓዲያን ልክ የፊተኞቹ ህዝቦች እንዳሉት ብጤ አሉ::

23:82

قَالُوٓاْ أَءِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابٗا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ ﴿82﴾

Transliteration: Qaloo aitha mitna wakunna turaban waAAithaman ainna lamabAAoothoona

Translation: 82. አሉም: «በሞትንና አፈርና አጥንቶች በሆንን ጊዜ እኛ እንደገና ተቀስቃሾች ነን?

23:83

لَقَدۡ وُعِدۡنَا نَحۡنُ وَءَابَآؤُنَا هَٰذَا مِن قَبۡلُ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّآ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ ﴿83﴾

Transliteration: Laqad wuAAidna nahnu waabaona hatha min qablu in hatha illa asateeru alawwaleena

Translation: 83. «ይህንን ሁኔታ እኛም ሆነ ከእኛ በፊት የነበሩት አባቶቻችን በእርግጥ ተቀጥረናል፤ ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ።

23:84

قُل لِّمَنِ ٱلۡأَرۡضُ وَمَن فِيهَآ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ ﴿84﴾

Transliteration: Qul limani alardu waman feeha in kuntum taAAlamoona

Translation: 84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ምድርና በውስጧ ያለው ሁሉ የማን ነው? የምታውቁ ከሆናችሁ እስቲ ንገሩኝ።» በላቸው።

23:85

سَيَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ ﴿85﴾

Transliteration: Sayaqooloona lillahi qul afala tathakkaroona

Translation: 85. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርግጥ የአላህ ነው።» ይሉሃል። «ታዲያ አትገሠጹምን?» በላቸው።

23:86

قُلۡ مَن رَّبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ ٱلسَّبۡعِ وَرَبُّ ٱلۡعَرۡشِ ٱلۡعَظِيمِ ﴿86﴾

Transliteration: Qul man rabbu alssamawati alssabAAi warabbu alAAarshi alAAatheemi

Translation: 86. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የሰባቱ ሰማያት ጌታ የታላቁም ዐርሽ ጌታ ማን ነው?» በላቸው።

23:87

سَيَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ أَفَلَا تَتَّقُونَ ﴿87﴾

Transliteration: Sayaqooloona lillahi qul afala tattaqoona

Translation: 87. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርግጥ አላህ ነው።» ይሉሃል፤ «እንግዲያ አትፈሩትምን?» በላቸው።

23:88

قُلۡ مَنۢ بِيَدِهِۦ مَلَكُوتُ كُلِّ شَيۡءٖ وَهُوَ يُجِيرُ وَلَا يُجَارُ عَلَيۡهِ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ ﴿88﴾

Transliteration: Qul man biyadihi malakootu kulli shayin wahuwa yujeeru wala yujaru AAalayhi in kuntum taAAlamoona

Translation: 88. «የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የሆነ፤ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው? የምታውቁ ከሆናችሁ (እስቲ መልሱልኝ)» በላቸው።

23:89

سَيَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ فَأَنَّىٰ تُسۡحَرُونَ ﴿89﴾

Transliteration: Sayaqooloona lillahi qul faanna tusharoona

Translation: 89. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርግጥ አላህ ነው።» ይሉሃል፤ «ታዲያ እንዴት ትታለላላችሁ?» በላቸው።

23:90

بَلۡ أَتَيۡنَٰهُم بِٱلۡحَقِّ وَإِنَّهُمۡ لَكَٰذِبُونَ ﴿90﴾

Transliteration: Bal ataynahum bialhaqqi wainnahum lakathiboona

Translation: 90. ይልቁንም እውነትን አመጣንላቸው እነርሱም በመካዳቸው ውሸታሞች ናቸው::

23:91

مَا ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ مِن وَلَدٖ وَمَا كَانَ مَعَهُۥ مِنۡ إِلَٰهٍۚ إِذٗا لَّذَهَبَ كُلُّ إِلَٰهِۭ بِمَا خَلَقَ وَلَعَلَا بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖۚ سُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ ﴿91﴾

Transliteration: Ma ittakhatha Allahu min waladin wama kana maAAahu min ilahin ithan lathahaba kullu ilahin bima khalaqa walaAAala baAAduhum AAala baAAdin subhana Allahi AAamma yasifoona

Translation: 91. አላህ ምንም ልጅን አልያዘም አልወለደም:: ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም:: ሌላ አምላክ በነበረማ አምላኩ ሁሉ የፈጠረውን ነገር በማስተዳደር ከሌላው በተለየ ነበር:: ከፊላቸዉም በከፊሉ ላይ በነገሰ ነበር:: አላህ ከሓዲያን እሱን ከሚመጥኑበት መግለጫ ሁሉ ጠራ::

23:92

عَٰلِمِ ٱلۡغَيۡبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ فَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشۡرِكُونَ ﴿92﴾

Transliteration: AAalimi alghaybi waalshshahadati fataAAala AAamma yushrikoona

Translation: 92. ሩቁንና ቅርቡን ሁሉ አዋቂ ነው:: በእርሱ ከሚያጋሩትም ሁሉ ከፍ አለ::

23:93

قُل رَّبِّ إِمَّا تُرِيَنِّي مَا يُوعَدُونَ ﴿93﴾

Transliteration: Qul rabbi imma turiyannee ma yooAAadoona

Translation: 93. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በል: «ጌታዬ ሆይ! የሚስፈራሩበትን ቅጣት ብታሳየኝ፤

23:94

رَبِّ فَلَا تَجۡعَلۡنِي فِي ٱلۡقَوۡمِ ٱلظَّـٰلِمِينَ ﴿94﴾

Transliteration: Rabbi fala tajAAalnee fee alqawmi alththalimeena

Translation: 94. «ጌታዬ ሆይ! በበደለኞች ህዝቦች ውስጥ አታድርገኝ።» በል።

23:95

وَإِنَّا عَلَىٰٓ أَن نُّرِيَكَ مَا نَعِدُهُمۡ لَقَٰدِرُونَ ﴿95﴾

Transliteration: Wainna AAala an nuriyaka ma naAAiduhum laqadiroona

Translation: 95. እኛ የምናስፈራራቸውን ነገር ልናሳይህ በእርግጥ ቻዮች ነን::

23:96

ٱدۡفَعۡ بِٱلَّتِي هِيَ أَحۡسَنُ ٱلسَّيِّئَةَۚ نَحۡنُ أَعۡلَمُ بِمَا يَصِفُونَ ﴿96﴾

Transliteration: IdfaAA biallatee hiya ahsanu alssayyiata nahnu aAAlamu bima yasifoona

Translation: 96. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዚያች እርሷ መልካም በሆነችው ጠባይ መጥፎይቱን ነገር መልስ:: እኛ ከሓዲያን የሚሉትን ሁሉ አዋቂዎች ነንና::

23:97

وَقُل رَّبِّ أَعُوذُ بِكَ مِنۡ هَمَزَٰتِ ٱلشَّيَٰطِينِ ﴿97﴾

Transliteration: Waqul rabbi aAAoothu bika min hamazati alshshayateeni

Translation: 97. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (እንዲህ) በል: «ጌታዬ ሆይ ከሰይጣናት ጉትጎታዎች ባንተ እጠበቃለሁ።

23:98

وَأَعُوذُ بِكَ رَبِّ أَن يَحۡضُرُونِ ﴿98﴾

Transliteration: WaaAAoothu bika rabbi an yahdurooni

Translation: 98. «ጌታዬ ሆይ! ወደ እኔ ከመጣዳቸው ከመቅረባቸውም ባንተው እጠበቃለሁ።» በል።

23:99

حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَ أَحَدَهُمُ ٱلۡمَوۡتُ قَالَ رَبِّ ٱرۡجِعُونِ ﴿99﴾

Transliteration: Hatta itha jaa ahadahumu almawtu qala rabbi irjiAAooni

Translation: 99. አንዳቸውን ሞት በመጣበት ጊዜ ይላል: «ጌታዬ ሆይ! ወደ ምድረ ዓለም መልሱኝ።

23:100

لَعَلِّيٓ أَعۡمَلُ صَٰلِحٗا فِيمَا تَرَكۡتُۚ كَلَّآۚ إِنَّهَا كَلِمَةٌ هُوَ قَآئِلُهَاۖ وَمِن وَرَآئِهِم بَرۡزَخٌ إِلَىٰ يَوۡمِ يُبۡعَثُونَ ﴿100﴾

Transliteration: LaAAallee aAAmalu salihan feema taraktu kalla innaha kalimatun huwa qailuha wamin waraihim barzakhun ila yawmi yubAAathoona

Translation: 100. «ችላ ብዬ የተውኩትን በጎ ስራ ልሰራ እከጅላለሁና።» (ይላል)። (ይህን ከማለት ይከልከል):: እርስዋ እርሱ ተናጋሪዋ የሆነች ቃል (ብቻ) ናት:: ከበስተፊታቸዉም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ ግርዶ አለ::

23:101

فَإِذَا نُفِخَ فِي ٱلصُّورِ فَلَآ أَنسَابَ بَيۡنَهُمۡ يَوۡمَئِذٖ وَلَا يَتَسَآءَلُونَ ﴿101﴾

Transliteration: Faitha nufikha fee alssoori fala ansaba baynahum yawmaithin wala yatasaaloona

Translation: 101. በቀንዱም በተነፋ ጊዜ በዚያ ቀን በመካከላቸው ዝምድና የለም። አይጠያየቁምም::

23:102

فَمَن ثَقُلَتۡ مَوَٰزِينُهُۥ فَأُوْلَـٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ ﴿102﴾

Transliteration: Faman thaqulat mawazeenuhu faolaika humu almuflihoona

Translation: 102.ሚዛኖቻቸው የከበዱላቸው ሰዎች እነዚያ እነርሱ ፍላጎታቸውን ያገኙ ናቸው::

23:103

وَمَنۡ خَفَّتۡ مَوَٰزِينُهُۥ فَأُوْلَـٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ فِي جَهَنَّمَ خَٰلِدُونَ ﴿103﴾

Transliteration: Waman khaffat mawazeenuhu faolaika allatheena khasiroo anfusahum fee jahannama khalidoona

Translation: 103. እነዚያ ሚዛኖቻቸዉም የቀለሉባቸው ሰዎች እነዚያ እነርሱ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ናቸው፤ በገሀነም ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::

23:104

تَلۡفَحُ وُجُوهَهُمُ ٱلنَّارُ وَهُمۡ فِيهَا كَٰلِحُونَ ﴿104﴾

Transliteration: Talfahu wujoohahumu alnnaru wahum feeha kalihoona

Translation: 104. ፊቶቻቸውን እሳት ትገርፋቸዋለች:: እነርሱም በእርሷ ውስጥ ከንፈሮቻቸው የተኮማተሩ ናቸው::

23:105

أَلَمۡ تَكُنۡ ءَايَٰتِي تُتۡلَىٰ عَلَيۡكُمۡ فَكُنتُم بِهَا تُكَذِّبُونَ ﴿105﴾

Transliteration: Alam takun ayatee tutla AAalaykum fakuntum biha tukaththiboona

Translation: 105. «አንቀፆቼ በእናንተ ላይ የሚነበቡላችሁና በእነርሱ የምታስተባብሉ አልነበራችሁምን?» ይባላሉ።

23:106

قَالُواْ رَبَّنَا غَلَبَتۡ عَلَيۡنَا شِقۡوَتُنَا وَكُنَّا قَوۡمٗا ضَآلِّينَ ﴿106﴾

Transliteration: Qaloo rabbana ghalabat AAalayna shiqwatuna wakunna qawman dalleena

Translation: 106. (እነርሱም) ይላሉ: «ታላቁ ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ መናጢነታችን አሸነፈችንና ጠማማ ህዝቦች ነበርን።

23:107

رَبَّنَآ أَخۡرِجۡنَا مِنۡهَا فَإِنۡ عُدۡنَا فَإِنَّا ظَٰلِمُونَ ﴿107﴾

Transliteration: Rabbana akhrijna minha fain AAudna fainna thalimoona

Translation: 107. «ጌታችን ሆይ! ከእርሷ አውጣንና ወደ ዱንያ መልሰን:: ከዚህ በኋላ ወደ ክህደት ብንመለስ እኛ በዳዮች ነን።» ይላሉ።

23:108

قَالَ ٱخۡسَـُٔواْ فِيهَا وَلَا تُكَلِّمُونِ ﴿108﴾

Transliteration: Qala ikhsaoo feeha wala tukallimooni

Translation: 108. አላህም ይላቸዋል: «ወራዶች ሆናችሁ በውስጧ አርፋችሁ ኑሩ እንጂ ፍጹም አታናግሩኝ።

23:109

إِنَّهُۥ كَانَ فَرِيقٞ مِّنۡ عِبَادِي يَقُولُونَ رَبَّنَآ ءَامَنَّا فَٱغۡفِرۡ لَنَا وَٱرۡحَمۡنَا وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلرَّـٰحِمِينَ ﴿109﴾

Transliteration: Innahu kana fareequn min AAibadee yaqooloona rabbana amanna faighfir lana wairhamna waanta khayru alrrahimeena

Translation: 109. «እነሆ ከባሮቼ መካከል ‹ጌታችን ሆይ! አምነናልና ማረን:: እዘንልንም:: አንተ ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ› የሚሉ ክፍሎች ነበሩ።

23:110

فَٱتَّخَذۡتُمُوهُمۡ سِخۡرِيًّا حَتَّىٰٓ أَنسَوۡكُمۡ ذِكۡرِي وَكُنتُم مِّنۡهُمۡ تَضۡحَكُونَ ﴿110﴾

Transliteration: Faittakhathtumoohum sikhriyyan hatta ansawkum thikree wakuntum minhum tadhakoona

Translation: 110. «እኔንም ማውሳትን እስካስረሷችሁ ድረስም ማላገጫ አድርጋችሁ ያዛችኋቸው:: በእነርሱም ላይ ትስቁባቸው ነበር።

23:111

إِنِّي جَزَيۡتُهُمُ ٱلۡيَوۡمَ بِمَا صَبَرُوٓاْ أَنَّهُمۡ هُمُ ٱلۡفَآئِزُونَ ﴿111﴾

Transliteration: Innee jazaytuhumu alyawma bima sabaroo annahum humu alfaizoona

Translation: 111. «እኔ ዛሬ በትዕግስታቸው ምክንያት ፍላጎታቸውን የሚያገኙት እነርሱን ብቻ በማድረግ መነዳኋቸው።» ይላቸዋል።

23:112

قَٰلَ كَمۡ لَبِثۡتُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ عَدَدَ سِنِينَ ﴿112﴾

Transliteration: Qala kam labithtum fee alardi AAadada sineena

Translation: 112. «በምድር ውስጥ ስንትን አመታትን ቆያችሁ?» ይላቸዋል።

23:113

قَالُواْ لَبِثۡنَا يَوۡمًا أَوۡ بَعۡضَ يَوۡمٖ فَسۡـَٔلِ ٱلۡعَآدِّينَ ﴿113﴾

Transliteration: Qaloo labithna yawman aw baAAda yawmin faisali alAAaddeena

Translation: 113. «አንድ ቀንን ወይም ከፊል ቀንን ቆየን:: ቆጣሪዎችንም ጠይቅ» ይላሉ።

23:114

قَٰلَ إِن لَّبِثۡتُمۡ إِلَّا قَلِيلٗاۖ لَّوۡ أَنَّكُمۡ كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ ﴿114﴾

Transliteration: Qala in labithtum illa qaleelan law annakum kuntum taAAlamoona

Translation: 114. ይላቸዋልም: «እናንተ የቆያችሁትን መጠን የምታውቁ ብትሆኑ ኖሮ (በእሳት ውስጥ ከምትቆዩት ጊዜ አንጻር) ጥቂትን ጊዜ እንጂ አልቆያችሁም።

23:115

أَفَحَسِبۡتُمۡ أَنَّمَا خَلَقۡنَٰكُمۡ عَبَثٗا وَأَنَّكُمۡ إِلَيۡنَا لَا تُرۡجَعُونَ ﴿115﴾

Transliteration: Afahasibtum annama khalaqnakum AAabathan waannakum ilayna la turjaAAoona

Translation: 115. «የፈጠርናችሁ ለከንቱ መሆኑን እናንተም ወደ እኛ የማትመለሱ መሆናችሁን ጠረጠራችሁን? (ለከንቱ የፈጠርናችሁ መሰላችሁን?)።» (ይባላሉ።)

23:116

فَتَعَٰلَى ٱللَّهُ ٱلۡمَلِكُ ٱلۡحَقُّۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ رَبُّ ٱلۡعَرۡشِ ٱلۡكَرِيمِ ﴿116﴾

Transliteration: FataAAala Allahu almaliku alhaqqu la ilaha illa huwa rabbu alAAarshi alkareemi

Translation: 116. የእውነቱ ንጉስ አላህ ከፍተኛነት ተገባው:: ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: የዚያ የሚያምረው ዐርሽ ጌታም እሱ ብቻ ነው::

23:117

وَمَن يَدۡعُ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ لَا بُرۡهَٰنَ لَهُۥ بِهِۦ فَإِنَّمَا حِسَابُهُۥ عِندَ رَبِّهِۦٓۚ إِنَّهُۥ لَا يُفۡلِحُ ٱلۡكَٰفِرُونَ ﴿117﴾

Transliteration: Waman yadAAu maAAa Allahi ilahan akhara la burhana lahu bihi fainnama hisabuhu AAinda rabbihi innahu la yuflihu alkafiroona

Translation: 117. ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ በእርሱ ማስረጃ የሌለውን የሚገዛ ሁሉ ምርመራው እጌታው ዘንድ ብቻ ነው:: እነሆ ከሓዲያን አይድኑም።

23:118

وَقُل رَّبِّ ٱغۡفِرۡ وَٱرۡحَمۡ وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلرَّـٰحِمِينَ ﴿118﴾

Transliteration: Waqul rabbi ighfir wairham waanta khayru alrrahimeena

Translation: 118. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ ሆይ! ማር:: እዘንም:: አንተም ከአዛኞች ሁሉ በላጭ ነህና።» በል፡:

Transliteration source: English Transliteration by Tanzil. Used under Tanzil's non-commercial terms; see the source and latest updates at Tanzil. Tanzil translation download