quranm◉

Surah Saba transliteration

◉ ሱራ · ∞

34:1

ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِي لَهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَهُ ٱلۡحَمۡدُ فِي ٱلۡأٓخِرَةِۚ وَهُوَ ٱلۡحَكِيمُ ٱلۡخَبِيرُ ﴿1﴾

Transliteration: Alhamdu lillahi allathee lahu ma fee alssamawati wama fee alardi walahu alhamdu fee alakhirati wahuwa alhakeemu alkhabeeru

Translation: 1. ምስጋና ሁሉ ለዚያ በሰማያትም ያለው በምድርም ያለው ሁሉ የእርሱ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው:: በመጨረሻይቱም ዓለም ምስጋና ሁሉ ለእርሱ ብቻ ነው:: እርሱም ጥበበኛና ውስጠ አዋቂው ነው::

34:2

يَعۡلَمُ مَا يَلِجُ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا يَخۡرُجُ مِنۡهَا وَمَا يَنزِلُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ وَمَا يَعۡرُجُ فِيهَاۚ وَهُوَ ٱلرَّحِيمُ ٱلۡغَفُورُ ﴿2﴾

Transliteration: YaAAlamu ma yaliju fee alardi wama yakhruju minha wama yanzilu mina alssamai wama yaAAruju feeha wahuwa alrraheemu alghafooru

Translation: 2. አላህ በምድር ውስጥ የሚገባውን ሁሉ ከእርሷ የሚወጣውንም ከሰማይም የሚወርደውን በእርሷ ውስጥ የሚያርገውንም ሁሉ ያውቃል:: እርሱም አዛኝና መሃሪ ነው::

34:3

وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَا تَأۡتِينَا ٱلسَّاعَةُۖ قُلۡ بَلَىٰ وَرَبِّي لَتَأۡتِيَنَّكُمۡ عَٰلِمِ ٱلۡغَيۡبِۖ لَا يَعۡزُبُ عَنۡهُ مِثۡقَالُ ذَرَّةٖ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَلَا فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَآ أَصۡغَرُ مِن ذَٰلِكَ وَلَآ أَكۡبَرُ إِلَّا فِي كِتَٰبٖ مُّبِينٖ ﴿3﴾

Transliteration: Waqala allatheena kafaroo la tateena alssaAAatu qul bala warabbee latatiyannakum AAalimi alghaybi la yaAAzubu AAanhu mithqalu tharratin fee alssamawati wala fee alardi wala asgharu min thalika wala akbaru illa fee kitabin mubeenin

Translation: 3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህ የካዱትም ሰዎች «ሰዓቲቱ አትመጣብንም» አሉ፡ «ጉዳዩ እንዳሰባችሁት አይደለም። ሩቁን ሁሉ አዋቂ በሆነው ጌታዬ እምላለሁ:: በእርግጥ ትመጣባችኋለች:: የብናኝ ክብደት ያክል እንኳ በሰማያትና በምድር ውስጥ ከእሱ አይሰወርም አይርቅም:: ከዚህ ያነሰም ሆነ የበለጠ የለም በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ቢሆን እንጂ::» በላቸው

34:4

لِّيَجۡزِيَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّـٰلِحَٰتِۚ أُوْلَـٰٓئِكَ لَهُم مَّغۡفِرَةٞ وَرِزۡقٞ كَرِيمٞ ﴿4﴾

Transliteration: Liyajziya allatheena amanoo waAAamiloo alssalihati olaika lahum maghfiratun warizqun kareemun

Translation: 4. እነዚያን ያመኑትንና መልካም የሰሩትን ሊመነዳ ሰዓቲቱ ትመጣባችኋለች:: እነዚያ ለእነርሱ ምህረትና የከበረ ሲሳይ አለላቸው::

34:5

وَٱلَّذِينَ سَعَوۡ فِيٓ ءَايَٰتِنَا مُعَٰجِزِينَ أُوْلَـٰٓئِكَ لَهُمۡ عَذَابٞ مِّن رِّجۡزٍ أَلِيمٞ ﴿5﴾

Transliteration: Waallatheena saAAaw fee ayatina muAAajizeena olaika lahum AAathabun min rijzin aleemin

Translation: 5. እነዚያም የሚያመልጡ መስሏቸው አናቅጻችንን ለማፍረስ የጣሩ እነዚያ ለእነርሱ ከመጥፎ ቅጣት የሆነ አሳማሚ ስቃይ አለባቸው::

34:6

وَيَرَى ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡعِلۡمَ ٱلَّذِيٓ أُنزِلَ إِلَيۡكَ مِن رَّبِّكَ هُوَ ٱلۡحَقَّ وَيَهۡدِيٓ إِلَىٰ صِرَٰطِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡحَمِيدِ ﴿6﴾

Transliteration: Wayara allatheena ootoo alAAilma allathee onzila ilayka min rabbika huwa alhaqqa wayahdee ila sirati alAAazeezi alhameedi

Translation: 6. እነዚያም እውቀትን የተሰጡት ያንን ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን እውነትና አሸናፊ ምስጉን ወደ ሆነው የአላህ መንገድ የሚመራ መሆኑን ያውቃሉ::

34:7

وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ هَلۡ نَدُلُّكُمۡ عَلَىٰ رَجُلٖ يُنَبِّئُكُمۡ إِذَا مُزِّقۡتُمۡ كُلَّ مُمَزَّقٍ إِنَّكُمۡ لَفِي خَلۡقٖ جَدِيدٍ ﴿7﴾

Transliteration: Waqala allatheena kafaroo hal nadullukum AAala rajulin yunabbiokum itha muzziqtum kulla mumazzaqin innakum lafee khalqin jadeedin

Translation: 7. እነዚያም በአላህ የካዱት አሉ: «(ሙታችሁ) ሙሉ መበጣጠስን በተበጣጠሳችሁ ጊዜ በአዲስ መፈጠር ውስጥ ትሆናላችሁ ብሎ የሚነግራችሁን ሰው እናሳያችሁን?

34:8

أَفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَم بِهِۦ جِنَّةُۢۗ بَلِ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ فِي ٱلۡعَذَابِ وَٱلضَّلَٰلِ ٱلۡبَعِيدِ ﴿8﴾

Transliteration: Aftara AAala Allahi kathiban am bihi jinnatun bali allatheena la yuminoona bialakhirati fee alAAathabi waalddalali albaAAeedi

Translation: 8. «በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፈን? ወይስ በእርሱ እብደት አለበት?» አሉ:: እንዳሉት አይደለም። እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት በእርሷ በቅጣት ውስጥ የሚሆኑና አሁንም በራቀ ስህተት ውስጥ ናቸው::

34:9

أَفَلَمۡ يَرَوۡاْ إِلَىٰ مَا بَيۡنَ أَيۡدِيهِمۡ وَمَا خَلۡفَهُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِۚ إِن نَّشَأۡ نَخۡسِفۡ بِهِمُ ٱلۡأَرۡضَ أَوۡ نُسۡقِطۡ عَلَيۡهِمۡ كِسَفٗا مِّنَ ٱلسَّمَآءِۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗ لِّكُلِّ عَبۡدٖ مُّنِيبٖ ﴿9﴾

Transliteration: Afalam yaraw ila ma bayna aydeehim wama khalfahum mina alssamai waalardi in nasha nakhsif bihimu alarda aw nusqit AAalayhim kisafan mina alssamai inna fee thalika laayatan likulli AAabdin muneebin

Translation: 9. ከሰማይና ከምድር በፊታቸውና በኋላቸው ወደ አለው ሁሉ አይመለከቱምን? ብንሻ እኮ በእነርሱ ምድርን እንደረምስባቸዋለን :: ወይም በእነርሱ ላይ ከሰማይ ቁራጭን እንጥልባቸዋለን:: በዚህ ውስጥ ወደ ጌታው ተመላሽ ለሆነ ባሪያ ሁሉ ታላቅ ምልክት አለበት፡

34:10

وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا دَاوُۥدَ مِنَّا فَضۡلٗاۖ يَٰجِبَالُ أَوِّبِي مَعَهُۥ وَٱلطَّيۡرَۖ وَأَلَنَّا لَهُ ٱلۡحَدِيدَ ﴿10﴾

Transliteration: Walaqad atayna dawooda minna fadlan ya jibalu awwibee maAAahu waalttayra waalanna lahu alhadeeda

Translation: 10. ለዳውድም ከእኛ የሆነን ችሮታ በእርግጥ ሰጠነው:: (አልንም) ተራራዎች ሆይ! ከእሱ ጋር ውዳሴን መላልሱ:: በራሪዎችንም (ገራንለት)። ብረትንም ለእሱ አለዘብንለት::

34:11

أَنِ ٱعۡمَلۡ سَٰبِغَٰتٖ وَقَدِّرۡ فِي ٱلسَّرۡدِۖ وَٱعۡمَلُواْ صَٰلِحًاۖ إِنِّي بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٞ ﴿11﴾

Transliteration: Ani iAAmal sabighatin waqaddir fee alssardi waiAAmaloo salihan innee bima taAAmaloona baseerun

Translation: 11. ሰፋፊዎችን ጥሩሮዎች ስራ:: በአሰራርዋም መጥን:: መልካምንም ስራ ስሩ:: እኔ የምትሰሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነኝና (አልነው)::

34:12

وَلِسُلَيۡمَٰنَ ٱلرِّيحَ غُدُوُّهَا شَهۡرٞ وَرَوَاحُهَا شَهۡرٞۖ وَأَسَلۡنَا لَهُۥ عَيۡنَ ٱلۡقِطۡرِۖ وَمِنَ ٱلۡجِنِّ مَن يَعۡمَلُ بَيۡنَ يَدَيۡهِ بِإِذۡنِ رَبِّهِۦۖ وَمَن يَزِغۡ مِنۡهُمۡ عَنۡ أَمۡرِنَا نُذِقۡهُ مِنۡ عَذَابِ ٱلسَّعِيرِ ﴿12﴾

Transliteration: Walisulaymana alrreeha ghuduwwuha shahrun warawahuha shahrun waasalna lahu AAayna alqitri wamina aljinni man yaAAmalu bayna yadayhi biithni rabbihi waman yazigh minhum AAan amrina nuthiqhu min AAathabi alssaAAeeri

Translation: 12. ለሱለይማንም ንፋስን የቀትር በፊት ጉዞዋ የወር መንገድ፤ የቀትር በኋላ ጉዞዋም የወር መንገድ ሲሆን ገራንለት:: የነሀስንም ምንጭ ለእርሱ አፈሰስንለት:: ከአጋንንቶችም በጌታው ፈቃድ በፊቱ የሚሰሩትን (አደረግንለት):: ከእነርሱም ውስጥ ከትእዛዛችን ዝንፍ የሚል ከነዳጅ እሳት ቅጣት እናቀምሰዋለን::

34:13

يَعۡمَلُونَ لَهُۥ مَا يَشَآءُ مِن مَّحَٰرِيبَ وَتَمَٰثِيلَ وَجِفَانٖ كَٱلۡجَوَابِ وَقُدُورٖ رَّاسِيَٰتٍۚ ٱعۡمَلُوٓاْ ءَالَ دَاوُۥدَ شُكۡرٗاۚ وَقَلِيلٞ مِّنۡ عِبَادِيَ ٱلشَّكُورُ ﴿13﴾

Transliteration: YaAAmaloona lahu ma yashao min mahareeba watamatheela wajifanin kaaljawabi waqudoorin rasiyatin iAAmaloo ala dawooda shukran waqaleelun min AAibadiya alshshakooru

Translation: 13. ከምኩራቦች፤ ከምስሎችም እንደ ገንዳ ከሆነ ገበታዎችም፤ ከተደላደለ ታላላቅ ድስቶችም የሚሻውን ሁሉ ይሰሩለታል፣ (አልናቸዉም:) «የዳውድ ቤተሰቦች ሆይ! በጣም አመስጋኞች ሆናችሁ ለጌታችሁ ስሩ::» ከባሮቼ ውስጥ አመስጋኞቹ ጥቂቶች ናቸው::

34:14

فَلَمَّا قَضَيۡنَا عَلَيۡهِ ٱلۡمَوۡتَ مَا دَلَّهُمۡ عَلَىٰ مَوۡتِهِۦٓ إِلَّا دَآبَّةُ ٱلۡأَرۡضِ تَأۡكُلُ مِنسَأَتَهُۥۖ فَلَمَّا خَرَّ تَبَيَّنَتِ ٱلۡجِنُّ أَن لَّوۡ كَانُواْ يَعۡلَمُونَ ٱلۡغَيۡبَ مَا لَبِثُواْ فِي ٱلۡعَذَابِ ٱلۡمُهِينِ ﴿14﴾

Transliteration: Falamma qadayna AAalayhi almawta ma dallahum AAala mawtihi illa dabbatu alardi takulu minsaatahu falamma kharra tabayyanati aljinnu an law kanoo yaAAlamoona alghayba ma labithoo fee alAAathabi almuheeni

Translation: 14. በእርሱም ላይ ሞትን በፈጸምንበት ጊዜ መሞቱን ብትሩን የምትበላ ተንቀሳቃሽ ምስጥ እንጂ ሌላ አላመለከታቸዉም:: በወደቀ ጊዜም አጋንንቶች ሩቅን ሚስጥር የሚያውቁ በሆነ ኖሮ በአዋራጅ ስቃይ ውስጥ የማይቆዩ እንደነበሩ ተረዱ::

34:15

لَقَدۡ كَانَ لِسَبَإٖ فِي مَسۡكَنِهِمۡ ءَايَةٞۖ جَنَّتَانِ عَن يَمِينٖ وَشِمَالٖۖ كُلُواْ مِن رِّزۡقِ رَبِّكُمۡ وَٱشۡكُرُواْ لَهُۥۚ بَلۡدَةٞ طَيِّبَةٞ وَرَبٌّ غَفُورٞ ﴿15﴾

Transliteration: Laqad kana lisabain fee maskanihim ayatun jannatani AAan yameenin washimalin kuloo min rizqi rabbikum waoshkuroo lahu baldatun tayyibatun warabbun ghafoorun

Translation: 15. ለሰበእ ነገዶች በመኖሪያቸው በእውነት አስደናቂ ምልክት ነበራቸው:: ከግራና ከቀኝ ሁለት አትክልቶች ነበሯቸው:: «ከጌታችሁ ሲሳይ ብሉ ለእሱም አመስግኑ:: አገራችሁ ውብ አገር ናት:: ጌታችሁም መሃሪ ጌታ ነው» ተባሉ::

34:16

فَأَعۡرَضُواْ فَأَرۡسَلۡنَا عَلَيۡهِمۡ سَيۡلَ ٱلۡعَرِمِ وَبَدَّلۡنَٰهُم بِجَنَّتَيۡهِمۡ جَنَّتَيۡنِ ذَوَاتَيۡ أُكُلٍ خَمۡطٖ وَأَثۡلٖ وَشَيۡءٖ مِّن سِدۡرٖ قَلِيلٖ ﴿16﴾

Transliteration: FaaAAradoo faarsalna AAalayhim sayla alAAarimi wabaddalnahum bijannatayhim jannatayni thawatay okulin khamtin waathlin washayin min sidrin qaleelin

Translation: 16. አላህን ከማመስገን ዞሩም:: በእነርሱም ላይ የግድቡን ጎርፍ ለቀቅንባቸው:: በሁለቱ አትክልቶቻቸዉም ሌሎች ሁለትን አትክልቶች ባለ መርጋጋ ፍሬዎችን ባለ ጠደቻና ከቁርቁራም ባለ ጥቂት ዛፎችን ለወጥናቸው::

34:17

ذَٰلِكَ جَزَيۡنَٰهُم بِمَا كَفَرُواْۖ وَهَلۡ نُجَٰزِيٓ إِلَّا ٱلۡكَفُورَ ﴿17﴾

Transliteration: Thalika jazaynahum bima kafaroo wahal nujazee illa alkafoora

Translation: 17. በመካዳቸው ምክንያት ይህንን መነዳናቸው:: (እንደዚህ ያለውን ቅጣት) በጣም ከሓዲ ለሆነ ሰው ብቻ እንጂ ለሌላው እንሰጣለን?

34:18

وَجَعَلۡنَا بَيۡنَهُمۡ وَبَيۡنَ ٱلۡقُرَى ٱلَّتِي بَٰرَكۡنَا فِيهَا قُرٗى ظَٰهِرَةٗ وَقَدَّرۡنَا فِيهَا ٱلسَّيۡرَۖ سِيرُواْ فِيهَا لَيَالِيَ وَأَيَّامًا ءَامِنِينَ ﴿18﴾

Transliteration: WajaAAalna baynahum wabayna alqura allatee barakna feeha quran thahiratan waqaddarna feeha alssayra seeroo feeha layaliya waayyaman amineena

Translation: 18. በእነርሱና በዚያች በውስጧ በረከትን ባደረግንባት አገር (በሻም) መካከልም ተከታታይ መንደሮችን (ቅጥልጥል ከተሞች) አደረግን:: በእርሷም ጉዞን ወሰንን። «በሌሊቶችም ሆነ በቀኖች ዉስጥ ጸጥተኞች ሆናችሁ ተጓዙ» (አልን)::

34:19

فَقَالُواْ رَبَّنَا بَٰعِدۡ بَيۡنَ أَسۡفَارِنَا وَظَلَمُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ فَجَعَلۡنَٰهُمۡ أَحَادِيثَ وَمَزَّقۡنَٰهُمۡ كُلَّ مُمَزَّقٍۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّكُلِّ صَبَّارٖ شَكُورٖ ﴿19﴾

Transliteration: Faqaloo rabbana baAAid bayna asfarina wathalamoo anfusahum fajaAAalnahum ahadeetha wamazzaqnahum kulla mumazzaqin inna fee thalika laayatin likulli sabbarin shakoorin

Translation: 19. «ጌታችን ሆይ! በጉዞዎቻችን መካከል አራርቅልን» አሉም:: ነፍሶቻቸውንም በደሉ:: መገረሚያ ወሬዎችም አደረግናቸው:: መበታተንንም ሁሉ በታተንናቸው:: በዚህ ውስጥ በጣም ታጋሽና አመስጋኝ ለሆነ ሁሉ ብዙ መገለጫዎች አሉበት::

34:20

وَلَقَدۡ صَدَّقَ عَلَيۡهِمۡ إِبۡلِيسُ ظَنَّهُۥ فَٱتَّبَعُوهُ إِلَّا فَرِيقٗا مِّنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ﴿20﴾

Transliteration: Walaqad saddaqa AAalayhim ibleesu thannahu faittabaAAoohu illa fareeqan mina almumineena

Translation: 20. ዲያብሎስም በእነርሱ ላይ ምኞቱን በእርግጥ ፈጸመ:: እናም ከአመኑት የሆኑት ቡድኖች በስተቀር ተከተሉት::

34:21

وَمَا كَانَ لَهُۥ عَلَيۡهِم مِّن سُلۡطَٰنٍ إِلَّا لِنَعۡلَمَ مَن يُؤۡمِنُ بِٱلۡأٓخِرَةِ مِمَّنۡ هُوَ مِنۡهَا فِي شَكّٖۗ وَرَبُّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٍ حَفِيظٞ ﴿21﴾

Transliteration: Wama kana lahu AAalayhim min sultanin illa linaAAlama man yuminu bialakhirati mimman huwa minha fee shakkin warabbuka AAala kulli shayin hafeethun

Translation: 21. በመጨረሻይቱም ዓለም የሚያምነውን ከዚያ እርሱ ከእርሷ በመጠራጠር ውስጥ ከሆነው ሰው ለይተን እንድናውቅ እንጂ በእነርሱ ላይ ለእርሱ ምንም ስልጣን አልነበረዉም:: ጌታህም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው::

34:22

قُلِ ٱدۡعُواْ ٱلَّذِينَ زَعَمۡتُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ لَا يَمۡلِكُونَ مِثۡقَالَ ذَرَّةٖ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَلَا فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا لَهُمۡ فِيهِمَا مِن شِرۡكٖ وَمَا لَهُۥ مِنۡهُم مِّن ظَهِيرٖ ﴿22﴾

Transliteration: Quli odAAoo allatheena zaAAamtum min dooni Allahi la yamlikoona mithqala tharratin fee alssamawati wala fee alardi wama lahum feehima min shirkin wama lahu minhum min thaheerin

Translation: 22. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያን ከአላህ ሌላ አማልክት ብላችሁ የምታስቧቸውን ጥሩ:: በሰማያትም ሆነ በምድር ውስጥ የብናኝ ክብደት ያህል እንኳ ምንም አይችሉም:: ለእነርሱም በሁለቱም ውስጥ ምንም ሽርክና የላቸዉም:: ከእነርሱም ለእርሱ ምንም አጋዥ የለዉም።» በላቸው::

34:23

وَلَا تَنفَعُ ٱلشَّفَٰعَةُ عِندَهُۥٓ إِلَّا لِمَنۡ أَذِنَ لَهُۥۚ حَتَّىٰٓ إِذَا فُزِّعَ عَن قُلُوبِهِمۡ قَالُواْ مَاذَا قَالَ رَبُّكُمۡۖ قَالُواْ ٱلۡحَقَّۖ وَهُوَ ٱلۡعَلِيُّ ٱلۡكَبِيرُ ﴿23﴾

Transliteration: Wala tanfaAAu alshshafaAAatu AAindahu illa liman athina lahu hatta itha fuzziAAa AAan quloobihim qaloo matha qala rabbukum qaloo alhaqqa wahuwa alAAaliyyu alkabeeru

Translation: 23. ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም:: ከልቦቻቸው ላይ ድንጋጤው በተገለጠ ጊዜ ተማላጆቹ «ጌታችሁ ምን አለ?» ይላሉ:: አማላጆቹም: «እውነትን አለ። እርሱም ከፍተኛውና ታላቁ ጌታ ነው።» ይላሉ::

34:24

قُلۡ مَن يَرۡزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ قُلِ ٱللَّهُۖ وَإِنَّآ أَوۡ إِيَّاكُمۡ لَعَلَىٰ هُدًى أَوۡ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ ﴿24﴾

Transliteration: Qul man yarzuqukum mina alssamawati waalardi quli Allahu wainna aw iyyakum laAAala hudan aw fee dalalin mubeenin

Translation: 24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ)፤ «ከሰማያትና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማነው?» በላቸው። «አላህ ነው እኛ ወይም እናንተ በትክክለኛው መንገድ ላይ ወይም በግልጽ መሳሳት ውስጥ ነን።» በላቸው።

34:25

قُل لَّا تُسۡـَٔلُونَ عَمَّآ أَجۡرَمۡنَا وَلَا نُسۡـَٔلُ عَمَّا تَعۡمَلُونَ ﴿25﴾

Transliteration: Qul la tusaloona AAamma ajramna wala nusalu AAamma taAAmaloona

Translation: 25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ !)«ካጠፋነው ጥፋት አትጠየቁም:: ከምትሰሩትም ስራ አንጠየቅም።» በላቸው::

34:26

قُلۡ يَجۡمَعُ بَيۡنَنَا رَبُّنَا ثُمَّ يَفۡتَحُ بَيۡنَنَا بِٱلۡحَقِّ وَهُوَ ٱلۡفَتَّاحُ ٱلۡعَلِيمُ ﴿26﴾

Transliteration: Qul yajmaAAu baynana rabbuna thumma yaftahu baynana bialhaqqi wahuwa alfattahu alAAaleemu

Translation: 26.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል። ከዚያም በመካከላችን በእውነት ይፈርዳል:: እርሱም በትክክል ፈራጁና አዋቂው ነው።» በላቸው።

34:27

قُلۡ أَرُونِيَ ٱلَّذِينَ أَلۡحَقۡتُم بِهِۦ شُرَكَآءَۖ كَلَّاۚ بَلۡ هُوَ ٱللَّهُ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ ﴿27﴾

Transliteration: Qul arooniya allatheena alhaqtum bihi shurakaa kalla bal huwa Allahu alAAazeezu alhakeemu

Translation: 27.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያን ተጋሪዎች አድርጋችሁ በእሱ ያስጠጋችኋቸውን ጣዖታት እስቲ አሳዩኝ:: ተው አታጋሩ:: በእውነት እርሱ አሸናፊዉና ጥበበኛው አላህ ነው።» በላቸው::

34:28

وَمَآ أَرۡسَلۡنَٰكَ إِلَّا كَآفَّةٗ لِّلنَّاسِ بَشِيرٗا وَنَذِيرٗا وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ ﴿28﴾

Transliteration: Wama arsalnaka illa kaffatan lilnnasi basheeran wanatheeran walakinna akthara alnnasi la yaAAlamoona

Translation: 28. አንተንም ለሰዎች ሁሉ በመላ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ቢሆን እንጂ አልላክንህም:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም::

34:29

وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلۡوَعۡدُ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ ﴿29﴾

Transliteration: Wayaqooloona mata hatha alwaAAdu in kuntum sadiqeena

Translation: 29. «እውነተኞችም እንደ ሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ::

34:30

قُل لَّكُم مِّيعَادُ يَوۡمٖ لَّا تَسۡتَـٔۡخِرُونَ عَنۡهُ سَاعَةٗ وَلَا تَسۡتَقۡدِمُونَ ﴿30﴾

Transliteration: Qul lakum meeAAadu yawmin la tastakhiroona AAanhu saAAatan wala tastaqdimoona

Translation: 30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ለእናንተ ከእርሱ አንዳችንም ሰዓት የማትዘገዩበት የማትቀድሙበትም የቀጠሮ ቀን አላችሁ።» በላቸው::

34:31

وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَن نُّؤۡمِنَ بِهَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانِ وَلَا بِٱلَّذِي بَيۡنَ يَدَيۡهِۗ وَلَوۡ تَرَىٰٓ إِذِ ٱلظَّـٰلِمُونَ مَوۡقُوفُونَ عِندَ رَبِّهِمۡ يَرۡجِعُ بَعۡضُهُمۡ إِلَىٰ بَعۡضٍ ٱلۡقَوۡلَ يَقُولُ ٱلَّذِينَ ٱسۡتُضۡعِفُواْ لِلَّذِينَ ٱسۡتَكۡبَرُواْ لَوۡلَآ أَنتُمۡ لَكُنَّا مُؤۡمِنِينَ ﴿31﴾

Transliteration: Waqala allatheena kafaroo lan numina bihatha alqurani wala biallathee bayna yadayhi walaw tara ithi alththalimoona mawqoofoona AAinda rabbihim yarjiAAu baAAduhum ila baAAdin alqawla yaqoolu allatheena istudAAifoo lillatheena istakbaroo lawla antum lakunna mumineena

Translation: 31. እነዚያም የካዱት «በዚህ ቁርኣንና በዚያ ከበፊቱ ባለዉም መጽሐፍ በጭራሽ አናምንም።» አሉ:: በዳዮችም ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ንግግርን የሚመላላሱ ሆነው በጌታቸው ዘንድ በሚቆሙ ጊዜ ብታይ ኖሮ አስደናቂን ነገር ታይ ነበር:: እነዚያ የተዋረዱት ለእነዚያ ለኮሩት «እናንተ ባልነበራችሁ ኖሮ ትክክለኛ አማኞች በሆንን ነበር።» ይላሉ::

34:32

قَالَ ٱلَّذِينَ ٱسۡتَكۡبَرُواْ لِلَّذِينَ ٱسۡتُضۡعِفُوٓاْ أَنَحۡنُ صَدَدۡنَٰكُمۡ عَنِ ٱلۡهُدَىٰ بَعۡدَ إِذۡ جَآءَكُمۖ بَلۡ كُنتُم مُّجۡرِمِينَ ﴿32﴾

Transliteration: Qala allatheena istakbaroo lillatheena istudAAifoo anahnu sadadnakum AAani alhuda baAAda ith jaakum bal kuntum mujrimeena

Translation: 32. እነዚያ የኮሩት ለእነዚያ ለተዋረዱት «ትክክለኛው እምነት ከመጣላችሁ በኋላ እኛ ከለከልናችሁን? አይደለም:: እናንተው ከሓዲያን ነበራችሁ።» ይሏቸዋል።

34:33

وَقَالَ ٱلَّذِينَ ٱسۡتُضۡعِفُواْ لِلَّذِينَ ٱسۡتَكۡبَرُواْ بَلۡ مَكۡرُ ٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِ إِذۡ تَأۡمُرُونَنَآ أَن نَّكۡفُرَ بِٱللَّهِ وَنَجۡعَلَ لَهُۥٓ أَندَادٗاۚ وَأَسَرُّواْ ٱلنَّدَامَةَ لَمَّا رَأَوُاْ ٱلۡعَذَابَۚ وَجَعَلۡنَا ٱلۡأَغۡلَٰلَ فِيٓ أَعۡنَاقِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْۖ هَلۡ يُجۡزَوۡنَ إِلَّا مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ ﴿33﴾

Transliteration: Waqala allatheena istudAAifoo lillatheena istakbaroo bal makru allayli waalnnahari ith tamuroonana an nakfura biAllahi wanajAAala lahu andadan waasarroo alnnadamata lamma raawoo alAAathaba wajaAAalna alaghlala fee aAAnaqi allatheena kafaroo hal yujzawna illa ma kanoo yaAAmaloona

Translation: 33. እነዚያም የተዋረዱት ለእነዚያ ለኮሩት «አይደለም። በአላህ እንድንክድና ለእርሱ ባላንጣዎችን እንድናደርግ ስታዙን (የከለከለን) የሌሊትና የቀን ዱለታችሁ ነው።» ይላሉ:: ቅጣትንም ባዩ ጊዜ ጸጸትን ይደብቃሉ:: በእነዚያም በካዱት አንገቶች ላይ እንዛዝሎችን እናደርጋለን:: ይሰሩት የነበሩትን እንጂ ሌላን ይመነዳሉን?

34:34

وَمَآ أَرۡسَلۡنَا فِي قَرۡيَةٖ مِّن نَّذِيرٍ إِلَّا قَالَ مُتۡرَفُوهَآ إِنَّا بِمَآ أُرۡسِلۡتُم بِهِۦ كَٰفِرُونَ ﴿34﴾

Transliteration: Wama arsalna fee qaryatin min natheerin illa qala mutrafooha inna bima orsiltum bihi kafiroona

Translation: 34. በየትኛዋም ከተማ አስፈራሪን አላክንም ነዋሪዎችዋ «እኛ በተላካችሁት ከሓዲያን ነን።» ያሉ ቢሆኑ እንጂ::

34:35

وَقَالُواْ نَحۡنُ أَكۡثَرُ أَمۡوَٰلٗا وَأَوۡلَٰدٗا وَمَا نَحۡنُ بِمُعَذَّبِينَ ﴿35﴾

Transliteration: Waqaloo nahnu aktharu amwalan waawladan wama nahnu bimuAAaththabeena

Translation: 35. «እኛም በገንዘቦችና በልጆች ይበልጥ የበዛን ነን:: እኛም የምንቀጣ አይደለንም» አሉ::

34:36

قُلۡ إِنَّ رَبِّي يَبۡسُطُ ٱلرِّزۡقَ لِمَن يَشَآءُ وَيَقۡدِرُ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ ﴿36﴾

Transliteration: Qul inna rabbee yabsutu alrrizqa liman yashao wayaqdiru walakinna akthara alnnasi la yaAAlamoona

Translation: 36. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ ሲሳይን ለሚሻው ሰው ሁሉ ያሰፋል:: ለሚሻው ሰዉም ሁሉ ያጠባል:: ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች ይህን አያውቁም።» በላቸው።

34:37

وَمَآ أَمۡوَٰلُكُمۡ وَلَآ أَوۡلَٰدُكُم بِٱلَّتِي تُقَرِّبُكُمۡ عِندَنَا زُلۡفَىٰٓ إِلَّا مَنۡ ءَامَنَ وَعَمِلَ صَٰلِحٗا فَأُوْلَـٰٓئِكَ لَهُمۡ جَزَآءُ ٱلضِّعۡفِ بِمَا عَمِلُواْ وَهُمۡ فِي ٱلۡغُرُفَٰتِ ءَامِنُونَ ﴿37﴾

Transliteration: Wama amwalukum wala awladukum biallatee tuqarribukum AAindana zulfa illa man amana waAAamila salihan faolaika lahum jazao alddiAAfi bima AAamiloo wahum fee alghurufati aminoona

Translation: 37. ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁም ያች እኛ ዘንድ መቅረብን የምታቀርባችሁ አይደለችም:: ያ በትክክል ያመነና መልካምን የሰራ ብቻ ሲቀር:: እነዚያ ለእነርሱ በሰሩት መልካም ስራ እጥፍ ምንዳ አለላቸው:: እነርሱም በገነት ሰገነቶች ውስጥ ጸጥተኞች ናቸው።

34:38

وَٱلَّذِينَ يَسۡعَوۡنَ فِيٓ ءَايَٰتِنَا مُعَٰجِزِينَ أُوْلَـٰٓئِكَ فِي ٱلۡعَذَابِ مُحۡضَرُونَ ﴿38﴾

Transliteration: Waallatheena yasAAawna fee ayatina muAAajizeena olaika fee alAAathabi muhdaroona

Translation: 38. እነዚያም የሚያቅቱ መስሏቸው አናቅጻችንን ለማበላሸት የሚጥሩ ሁሉ እነዚያ በቅጣት ውስጥ የሚጣዱ ናቸው::

34:39

قُلۡ إِنَّ رَبِّي يَبۡسُطُ ٱلرِّزۡقَ لِمَن يَشَآءُ مِنۡ عِبَادِهِۦ وَيَقۡدِرُ لَهُۥۚ وَمَآ أَنفَقۡتُم مِّن شَيۡءٖ فَهُوَ يُخۡلِفُهُۥۖ وَهُوَ خَيۡرُ ٱلرَّـٰزِقِينَ ﴿39﴾

Transliteration: Qul inna rabbee yabsutu alrrizqa liman yashao min AAibadihi wayaqdiru lahu wama anfaqtum min shayin fahuwa yukhlifuhu wahuwa khayru alrraziqeena

Translation: 39. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ ሲሳይን ከባሮቹ ለሚሻው ሰው ያሰፋል:: ለእርሱም ያጠባል:: ከማንኛዉም ነገር የምትለግሱትን እርሱ ይተካዋል:: እርሱም ከሲሳይ ሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው።» በላቸው።

34:40

وَيَوۡمَ يَحۡشُرُهُمۡ جَمِيعٗا ثُمَّ يَقُولُ لِلۡمَلَـٰٓئِكَةِ أَهَـٰٓؤُلَآءِ إِيَّاكُمۡ كَانُواْ يَعۡبُدُونَ ﴿40﴾

Transliteration: Wayawma yahshuruhum jameeAAan thumma yaqoolu lilmalaikati ahaolai iyyakum kanoo yaAAbudoona

Translation: 40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሁሉንም በሚሰበስባቸውና ከዚያም ለመላእክቶቹ «እነዚህ እናንተን ይገዙ ነበሩን?» በሚላቸው ቀን የሚሆነውን አስታውስ::

34:41

قَالُواْ سُبۡحَٰنَكَ أَنتَ وَلِيُّنَا مِن دُونِهِمۖ بَلۡ كَانُواْ يَعۡبُدُونَ ٱلۡجِنَّۖ أَكۡثَرُهُم بِهِم مُّؤۡمِنُونَ ﴿41﴾

Transliteration: Qaloo subhanaka anta waliyyuna min doonihim bal kanoo yaAAbudoona aljinna aktharuhum bihim muminoona

Translation: 41. መላእክቶቹም «ጥራት ይገባህ ረዳታችን ከእነርሱ ሌላ የሆንከው አንተው ብቻ ነህ:: እንደሚሉት አይደለም:: ይልቁንም አጋንንትን ይገዙ ነበሩ:: አብዛኞቻቸው በእነርሱ አማኞች ናቸው።» ይላሉ።

34:42

فَٱلۡيَوۡمَ لَا يَمۡلِكُ بَعۡضُكُمۡ لِبَعۡضٖ نَّفۡعٗا وَلَا ضَرّٗا وَنَقُولُ لِلَّذِينَ ظَلَمُواْ ذُوقُواْ عَذَابَ ٱلنَّارِ ٱلَّتِي كُنتُم بِهَا تُكَذِّبُونَ ﴿42﴾

Transliteration: Faalyawma la yamliku baAAdukum libaAAdin nafAAan wala darran wanaqoolu lillatheena thalamoo thooqoo AAathaba alnnari allatee kuntum biha tukaththiboona

Translation: 42. ዛሬም ከፊላችሁ ለከፊሉ መጥቀምንም ሆነ መጉዳትን አይችሉም:: ለእነዚያም ለበደሉት ሰዎች «ያችን በእርሷ ታስተባብሉባት የነበራችሁትን የእሳት ቅጣት ቅመሱ» እንላቸዋለን::

34:43

وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتُنَا بَيِّنَٰتٖ قَالُواْ مَا هَٰذَآ إِلَّا رَجُلٞ يُرِيدُ أَن يَصُدَّكُمۡ عَمَّا كَانَ يَعۡبُدُ ءَابَآؤُكُمۡ وَقَالُواْ مَا هَٰذَآ إِلَّآ إِفۡكٞ مُّفۡتَرٗىۚ وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لِلۡحَقِّ لَمَّا جَآءَهُمۡ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٞ مُّبِينٞ ﴿43﴾

Transliteration: Waitha tutla AAalayhim ayatuna bayyinatin qaloo ma hatha illa rajulun yureedu an yasuddakum AAamma kana yaAAbudu abaokum waqaloo ma hatha illa ifkun muftaran waqala allatheena kafaroo lilhaqqi lamma jaahum in hatha illa sihrun mubeenun

Translation: 43. በእነርሱም ላይ አናቅጻችን ግልጽ ሆነው በተነበቡላቸው ጊዜ «ይህ አባቶቻችሁ ይገዙት ከነበሩት ነገር ሊከለክላችሁ የሚፈልግ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ:: «ይህም ቁርዓን የተቀጣጠፈ ውሸት ነው እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉም። እነዚያም በአላህ የካዱት እውነትን በመጣላቸው ጊዜ «ግልጥ ድግምት ነው እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ።

34:44

وَمَآ ءَاتَيۡنَٰهُم مِّن كُتُبٖ يَدۡرُسُونَهَاۖ وَمَآ أَرۡسَلۡنَآ إِلَيۡهِمۡ قَبۡلَكَ مِن نَّذِيرٖ ﴿44﴾

Transliteration: Wama ataynahum min kutubin yadrusoonaha wama arsalna ilayhim qablaka min natheerin

Translation: 44. የሚያጠኗቸው የሆኑ መጽሐፎችንም ምንም አልሰጠናቸዉም:: ካንተ በፊትም አስፈራሪ ነብይን ወደ እነርሱ አልላክንም::

34:45

وَكَذَّبَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ وَمَا بَلَغُواْ مِعۡشَارَ مَآ ءَاتَيۡنَٰهُمۡ فَكَذَّبُواْ رُسُلِيۖ فَكَيۡفَ كَانَ نَكِيرِ ﴿45﴾

Transliteration: Wakaththaba allatheena min qablihim wama balaghoo miAAshara ma ataynahum fakaththaboo rusulee fakayfa kana nakeeri

Translation: 45. እነዚያም ከእነርሱ በፊት የነበሩት አስተባብለዋል:: የሰጠናቸውንም ከአስር አንዱን እንኳን እነዚህ አልደረሱም:: እናም መልዕክተኞቼን አስተባበሉ:: ነቀፍኳቸዉም:: መንቀፌም እንዴት ነበር::

34:46

قُلۡ إِنَّمَآ أَعِظُكُم بِوَٰحِدَةٍۖ أَن تَقُومُواْ لِلَّهِ مَثۡنَىٰ وَفُرَٰدَىٰ ثُمَّ تَتَفَكَّرُواْۚ مَا بِصَاحِبِكُم مِّن جِنَّةٍۚ إِنۡ هُوَ إِلَّا نَذِيرٞ لَّكُم بَيۡنَ يَدَيۡ عَذَابٖ شَدِيدٖ ﴿46﴾

Transliteration: Qul innama aAAithukum biwahidatin an taqoomoo lillahi mathna wafurada thumma tatafakkaroo ma bisahibikum min jinnatin in huwa illa natheerun lakum bayna yaday AAathabin shadeedin

Translation: 46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የምገስጻችሁ በአንዲት ነገር ብቻ ነው:: እርሷም ሁለት ሁለት፤ አንድ አንድም ሆናችሁ ለአላህ እንድትነሱና ከዚያም በጓደኛችሁ (በሙሐመድ) ምንም እብደት የሌለበት መሆኑን መርምራችሁ እንድትረዱ ነው:: እርሱ ለእናንተ ከብርቱ ቅጣት በስተፊት አስጠንቃቂ ነው እንጂ ሌላ አይደለም።» በላቸው።

34:47

قُلۡ مَا سَأَلۡتُكُم مِّنۡ أَجۡرٖ فَهُوَ لَكُمۡۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَى ٱللَّهِۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ شَهِيدٞ ﴿47﴾

Transliteration: Qul ma saaltukum min ajrin fahuwa lakum in ajriya illa AAala Allahi wahuwa AAala kulli shayin shaheedun

Translation: 47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከዋጋ ማንኛውንም የጠየቅኋችሁ ቢኖር እርሱ ለእናንተው ነው:: ዋጋዬ በአላህ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም:: እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ ነው።» በላቸው።

34:48

قُلۡ إِنَّ رَبِّي يَقۡذِفُ بِٱلۡحَقِّ عَلَّـٰمُ ٱلۡغُيُوبِ ﴿48﴾

Transliteration: Qul inna rabbee yaqthifu bialhaqqi AAallamu alghuyoobi

Translation: 48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ እውነትን ብቻ ያወርዳል:: ሩቅ የሆኑትን ምስጢሮች ሁሉ አዋቂ ነው።» በላቸው።

34:49

قُلۡ جَآءَ ٱلۡحَقُّ وَمَا يُبۡدِئُ ٱلۡبَٰطِلُ وَمَا يُعِيدُ ﴿49﴾

Transliteration: Qul jaa alhaqqu wama yubdio albatilu wama yuAAeedu

Translation: 49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እውነቱ መጣ ውሸት መነሻም መድረሻም የለዉምና ተወገደ።» በላቸው።

34:50

قُلۡ إِن ضَلَلۡتُ فَإِنَّمَآ أَضِلُّ عَلَىٰ نَفۡسِيۖ وَإِنِ ٱهۡتَدَيۡتُ فَبِمَا يُوحِيٓ إِلَيَّ رَبِّيٓۚ إِنَّهُۥ سَمِيعٞ قَرِيبٞ ﴿50﴾

Transliteration: Qul in dalaltu fainnama adillu AAala nafsee waini ihtadaytu fabima yoohee ilayya rabbee innahu sameeAAun qareebun

Translation: 50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ብሳሳትም የምሳሳተው በራሴ ላይ ብቻ ነው:: ብመራም ጌታዬ ወደ እኔ በሚያወርደው መመሪያ መሰረት ነው:: እርሱ ሁሉ ሰሚና ለሁሉም ቅርብ ነውና።» በላቸው::

34:51

وَلَوۡ تَرَىٰٓ إِذۡ فَزِعُواْ فَلَا فَوۡتَ وَأُخِذُواْ مِن مَّكَانٖ قَرِيبٖ ﴿51﴾

Transliteration: Walaw tara ith faziAAoo fala fawta waokhithoo min makanin qareebin

Translation: 51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በደነገጡና ማምለጫ በሌላቸው ጊዜ ከቅርብ ስፍራም በተያዙ ጊዜ ሁኔታቸውን ብታይ ኖሮ (አስደናቂን ነገር ባየህ ነበር)::

34:52

وَقَالُوٓاْ ءَامَنَّا بِهِۦ وَأَنَّىٰ لَهُمُ ٱلتَّنَاوُشُ مِن مَّكَانِۭ بَعِيدٖ ﴿52﴾

Transliteration: Waqaloo amanna bihi waanna lahumu alttanawushu min makanin baAAeedin

Translation: 52. «በእርሱም አሁን አመንን።» ይላሉ:: ለእነርሱም ከሩቅ ስፍራ እምነትን በቀላሉ ማግኘት ከየታቸው ይታደሉና?

34:53

وَقَدۡ كَفَرُواْ بِهِۦ مِن قَبۡلُۖ وَيَقۡذِفُونَ بِٱلۡغَيۡبِ مِن مَّكَانِۭ بَعِيدٖ ﴿53﴾

Transliteration: Waqad kafaroo bihi min qablu wayaqthifoona bialghaybi min makanin baAAeedin

Translation: 53. በፊትም በእርሱ በእርግጥ ክደዋል:: ከሩቅ ስፍራም በግምት ንግግርን ይጥላሉ::

34:54

وَحِيلَ بَيۡنَهُمۡ وَبَيۡنَ مَا يَشۡتَهُونَ كَمَا فُعِلَ بِأَشۡيَاعِهِم مِّن قَبۡلُۚ إِنَّهُمۡ كَانُواْ فِي شَكّٖ مُّرِيبِۭ ﴿54﴾

Transliteration: Waheela baynahum wabayna ma yashtahoona kama fuAAila biashyaAAihim min qablu innahum kanoo fee shakkin mureebin

Translation: 54. ከዚህ ቀደም በመሰሎቻቸው እንደተሰራዉም ብጤ በእነርሱና በሚፈልጉት መካከል ተጋረደ:: እነርሱ በእርግጥ በአወላዋይ ጥርጣሬ ውስጥ ነበሩና::

Transliteration source: English Transliteration by Tanzil. Used under Tanzil's non-commercial terms; see the source and latest updates at Tanzil. Tanzil translation download