quranm◉

Surah Sad transliteration

◉ ሱራ · ∞

38:1

صٓۚ وَٱلۡقُرۡءَانِ ذِي ٱلذِّكۡرِ ﴿1﴾

Transliteration: Sad waalqurani thee alththikri

Translation: 1. ሷድ፤ የግሳፄ ባለቤት በሆነው ቁርኣን እምላለሁ።

38:2

بَلِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فِي عِزَّةٖ وَشِقَاقٖ ﴿2﴾

Transliteration: Bali allatheena kafaroo fee AAizzatin washiqaqin

Translation: 2. ይልቁንም እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች በከባድ ትዕቢትና በአጓጉል ክርክር ውስጥ ናቸው።

38:3

كَمۡ أَهۡلَكۡنَا مِن قَبۡلِهِم مِّن قَرۡنٖ فَنَادَواْ وَّلَاتَ حِينَ مَنَاصٖ ﴿3﴾

Transliteration: Kam ahlakna min qablihim min qarnin fanadaw walata heena manasin

Translation: 3. ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች ብዙን አጥፍተናል:: ጊዜው የመሸሻና የማምለጫ ጊዜ ሳይሆንም (ለእርዳታ) ተጣሩ::

38:4

وَعَجِبُوٓاْ أَن جَآءَهُم مُّنذِرٞ مِّنۡهُمۡۖ وَقَالَ ٱلۡكَٰفِرُونَ هَٰذَا سَٰحِرٞ كَذَّابٌ ﴿4﴾

Transliteration: WaAAajiboo an jaahum munthirun minhum waqala alkafiroona hatha sahirun kaththabun

Translation: 4. ከእነርሱ መካከል የሆነ አስፈራሪ ስለመጣላቸውም ተደነቁ:: ከሓዲያንም አሉ: «ይህ ድግምተኛ ጠንቋይ ውሸታም ነው።

38:5

أَجَعَلَ ٱلۡأٓلِهَةَ إِلَٰهٗا وَٰحِدًاۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَيۡءٌ عُجَابٞ ﴿5﴾

Transliteration: AjaAAala alalihata ilahan wahidan inna hatha lashayon AAujabun

Translation: 5. «አማልዕክቶችን አንድ አምላክ አደረጋቸውን? ይህ አስደናቂ ነገር ነው።» አሉ።

38:6

وَٱنطَلَقَ ٱلۡمَلَأُ مِنۡهُمۡ أَنِ ٱمۡشُواْ وَٱصۡبِرُواْ عَلَىٰٓ ءَالِهَتِكُمۡۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَيۡءٞ يُرَادُ ﴿6﴾

Transliteration: Waintalaqa almalao minhum ani imshoo waisbiroo AAala alihatikum inna hatha lashayon yuradu

Translation: 6. ከእነርሱም መካከል ባላባቶቹ (እንዲህ) እያሉ አዘገሙ: «ሂዱ በአማልክቶቻችሁም መገዛት ላይ ጽኑ:: ይህ ከእኛ የሚፈለግ ነገር ነውና

38:7

مَا سَمِعۡنَا بِهَٰذَا فِي ٱلۡمِلَّةِ ٱلۡأٓخِرَةِ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا ٱخۡتِلَٰقٌ ﴿7﴾

Transliteration: Ma samiAAna bihatha fee almillati alakhirati in hatha illa ikhtilaqun

Translation: 7. «ይህንንም አስተምህሮት ከኋለኛይቱ (ከመጨረሻይቱ) ሃይማኖት አልሰማንም:: ይህ ውሸትን መፍጠር እንጂ ሌላ አይደለም።

38:8

أَءُنزِلَ عَلَيۡهِ ٱلذِّكۡرُ مِنۢ بَيۡنِنَاۚ بَلۡ هُمۡ فِي شَكّٖ مِّن ذِكۡرِيۚ بَل لَّمَّا يَذُوقُواْ عَذَابِ ﴿8﴾

Transliteration: Aonzila AAalayhi alththikru min baynina bal hum fee shakkin min thikree bal lamma yathooqoo AAathabi

Translation: 8. «ከመካከላችን በእርሱ ላይ ብቻ ቁርኣን ተወረደን?» (እያሉ አዘገሙ።) ይልቁን እነርሱ ከግሳጼየ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው:: በእርግጥም ቅጣትን ገና አልቀመሱም::

38:9

أَمۡ عِندَهُمۡ خَزَآئِنُ رَحۡمَةِ رَبِّكَ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡوَهَّابِ ﴿9﴾

Transliteration: Am AAindahum khazainu rahmati rabbika alAAazeezi alwahhabi

Translation: 9. ወይስ የአሸናፊውና የለጋሹ ጌታህ የአላህ የችሮታው መካዚኖች እነርሱ ዘንድ ናቸውን?

38:10

أَمۡ لَهُم مُّلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَاۖ فَلۡيَرۡتَقُواْ فِي ٱلۡأَسۡبَٰبِ ﴿10﴾

Transliteration: Am lahum mulku alssamawati waalardi wama baynahuma falyartaqoo fee alasbabi

Translation: 10. ወይስ የሰማይ የምድር እና የመካከላቸዉም ንግስና የእነርሱ ነውን? (ነው ካሉ) እስቲ በመሰላሎች ወደ ላይ ይውጡ::

38:11

جُندٞ مَّا هُنَالِكَ مَهۡزُومٞ مِّنَ ٱلۡأَحۡزَابِ ﴿11﴾

Transliteration: Jundun ma hunalika mahzoomun mina alahzabi

Translation: 11. እነርሱም እዚያ ዘንድ ከአህዛብ ሁሉ ተሸናፊ የሆነ ሰራዊት ናቸው::

38:12

كَذَّبَتۡ قَبۡلَهُمۡ قَوۡمُ نُوحٖ وَعَادٞ وَفِرۡعَوۡنُ ذُو ٱلۡأَوۡتَادِ ﴿12﴾

Transliteration: Kaththabat qablahum qawmu noohin waAAadun wafirAAawnu thoo alawtadi

Translation: 12. ከእነርሱም በፊት የኑህ ህዝቦች፤ ዓድ እና የችካሎች ባለቤት የሆነው ፈርዖንም አስተባብለዋል።

38:13

وَثَمُودُ وَقَوۡمُ لُوطٖ وَأَصۡحَٰبُ لۡـَٔيۡكَةِۚ أُوْلَـٰٓئِكَ ٱلۡأَحۡزَابُ ﴿13﴾

Transliteration: Wathamoodu waqawmu lootin waashabu alaykati olaika alahzabu

Translation: 13. ሰሙድም፤ የሉጥ ሰዎችም፤ የአይካ ሰዎችም፤ አስተባበሉ:: እነዚህ አህዛቦቹ ናቸው::

38:14

إِن كُلٌّ إِلَّا كَذَّبَ ٱلرُّسُلَ فَحَقَّ عِقَابِ ﴿14﴾

Transliteration: In kullun illa kaththaba alrrusula fahaqqa AAiqabi

Translation: 14. ሁሉም መልዕክተኞችን ያስዋሹ እንጂ ሌላ አይደሉም:: ከዚያ ቅጣቴ ተረጋገጠባቸው::

38:15

وَمَا يَنظُرُ هَـٰٓؤُلَآءِ إِلَّا صَيۡحَةٗ وَٰحِدَةٗ مَّا لَهَا مِن فَوَاقٖ ﴿15﴾

Transliteration: Wama yanthuru haolai illa sayhatan wahidatan ma laha min fawaqin

Translation: 15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚህ ያችን ለእርሷ መመለስ የሌላትን አንዲት ጩኸት ብቻ እንጂ ሌላን አይጠባበቁም::

38:16

وَقَالُواْ رَبَّنَا عَجِّل لَّنَا قِطَّنَا قَبۡلَ يَوۡمِ ٱلۡحِسَابِ ﴿16﴾

Transliteration: Waqaloo rabbana AAajjil lana qittana qabla yawmi alhisabi

Translation: 16. (በመሳለቅም) «ጌታችን ሆይ! ከምርመራው ቀን በፊት ቅጣታችንን አጣድፍልን» አሉ።

38:17

ٱصۡبِرۡ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَٱذۡكُرۡ عَبۡدَنَا دَاوُۥدَ ذَا ٱلۡأَيۡدِۖ إِنَّهُۥٓ أَوَّابٌ ﴿17﴾

Transliteration: Isbir AAala ma yaqooloona waothkur AAabdana dawooda tha alaydi innahu awwabun

Translation: 17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሚሉት ነገር ላይ ታገስ:: የሃኃይል ባለቤት የሆነውን ባሪያችንንም ዳውድን አውሳው:: እርሱ በጣም መላሳ ነው::

38:18

إِنَّا سَخَّرۡنَا ٱلۡجِبَالَ مَعَهُۥ يُسَبِّحۡنَ بِٱلۡعَشِيِّ وَٱلۡإِشۡرَاقِ ﴿18﴾

Transliteration: Inna sakhkharna aljibala maAAahu yusabbihna bialAAashiyyi waalishraqi

Translation: 18. እኛ ተራራዎችን ከቀትር በኋላና በረፋዱም ከእርሱ ጋር የሚያወድሱ ሲሆን እንዲታዘዙት አገራንለት::

38:19

وَٱلطَّيۡرَ مَحۡشُورَةٗۖ كُلّٞ لَّهُۥٓ أَوَّابٞ ﴿19﴾

Transliteration: Waalttayra mahshooratan kullun lahu awwabun

Translation: 19. በራሪዎችንም (አእዋፍን) የሚሰበሰቡ ሆነው አገራንለት:: ሁሉም ለእርሱ ማወደስ የሚመላለስ ነው::

38:20

وَشَدَدۡنَا مُلۡكَهُۥ وَءَاتَيۡنَٰهُ ٱلۡحِكۡمَةَ وَفَصۡلَ ٱلۡخِطَابِ ﴿20﴾

Transliteration: Washadadna mulkahu waataynahu alhikmata wafasla alkhitabi

Translation: 20. ንግስናውንም አበረታንለት ጥበብንና ንግግርን መለየትንም ሰጠነው።

38:21

وَهَلۡ أَتَىٰكَ نَبَؤُاْ ٱلۡخَصۡمِ إِذۡ تَسَوَّرُواْ ٱلۡمِحۡرَابَ ﴿21﴾

Transliteration: Wahal ataka nabao alkhasmi ith tasawwaroo almihraba

Translation: 21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የተከራካሪዎቹ ወሬ መጥቶልሃልን? እልፍኙን (ምኩራቡን) በተንጠላጠሉ ጊዜ።

38:22

إِذۡ دَخَلُواْ عَلَىٰ دَاوُۥدَ فَفَزِعَ مِنۡهُمۡۖ قَالُواْ لَا تَخَفۡۖ خَصۡمَانِ بَغَىٰ بَعۡضُنَا عَلَىٰ بَعۡضٖ فَٱحۡكُم بَيۡنَنَا بِٱلۡحَقِّ وَلَا تُشۡطِطۡ وَٱهۡدِنَآ إِلَىٰ سَوَآءِ ٱلصِّرَٰطِ ﴿22﴾

Transliteration: Ith dakhaloo AAala dawooda fafaziAAa minhum qaloo la takhaf khasmani bagha baAAduna AAala baAAdin faohkum baynana bialhaqqi wala tushtit waihdina ila sawai alssirati

Translation: 22. በዳውድ ላይም በገቡ ጊዜ ከእነርሱም ሁኔታ በደነገጠ ጊዜ (እንዲህ) አሉት: «አትፍራ። እኛ ከፊላችን በከፊሉ ላይ ወሰን ያለፈ ሁለት ተከራካሪዎች ነን። በመካከላችንም በእውነት ፍረድ። አታዳላም። ወደ ትክክለኛው መንገድም ምራን።

38:23

إِنَّ هَٰذَآ أَخِي لَهُۥ تِسۡعٞ وَتِسۡعُونَ نَعۡجَةٗ وَلِيَ نَعۡجَةٞ وَٰحِدَةٞ فَقَالَ أَكۡفِلۡنِيهَا وَعَزَّنِي فِي ٱلۡخِطَابِ ﴿23﴾

Transliteration: Inna hatha akhee lahu tisAAun watisAAoona naAAjatan waliya naAAjatun wahidatun faqala akfilneeha waAAazzanee fee alkhitabi

Translation: 23. «ይህ ወንድሜ ነው:: ለእርሱ ዘጠና ዘጠኝ ሴት በጎች አሉት ለእኔም አንዲት ሴት በግ አለችኝ ‹እርሷንም ለእኔ አድርጋት› አለኝ:: በንግግርም አሸነፈኝ።» አለው::

38:24

قَالَ لَقَدۡ ظَلَمَكَ بِسُؤَالِ نَعۡجَتِكَ إِلَىٰ نِعَاجِهِۦۖ وَإِنَّ كَثِيرٗا مِّنَ ٱلۡخُلَطَآءِ لَيَبۡغِي بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٍ إِلَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّـٰلِحَٰتِ وَقَلِيلٞ مَّا هُمۡۗ وَظَنَّ دَاوُۥدُ أَنَّمَا فَتَنَّـٰهُ فَٱسۡتَغۡفَرَ رَبَّهُۥ وَخَرَّۤ رَاكِعٗاۤ وَأَنَابَ۩ ﴿24﴾

Transliteration: Qala laqad thalamaka bisuali naAAjatika ila niAAajihi wainna katheeran mina alkhulatai layabghee baAAduhum AAala baAAdin illa allatheena amanoo waAAamiloo alssalihati waqaleelun ma hum wathanna dawoodu annama fatannahu faistaghfara rabbahu wakharra rakiAAan waanaba

Translation: 24. «ሴት በግህን ወደ በጎቹ ለመቀላቀል በመጠየቁ በእርግጥ በደለህ። ከተጋሪዎች ብዙዎቹ ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ወሰን ያልፋሉ:: እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሰሩት ብቻ ሲቀሩ፤ እነርሱም በጣም ጥቂቶች ናቸው።» አለ:: ዳውድም የፈተንነው መሆኑን ወዲያዉኑ አወቀ:: ከጌታዉም ምህረትን ለመነና ሰጋጅ ሆኖም ወደቀ። በመጸጸትም ተመለሰ:: {1}

38:25

فَغَفَرۡنَا لَهُۥ ذَٰلِكَۖ وَإِنَّ لَهُۥ عِندَنَا لَزُلۡفَىٰ وَحُسۡنَ مَـَٔابٖ ﴿25﴾

Transliteration: Faghafarna lahu thalika wainna lahu AAindana lazulfa wahusna maabin

Translation: 25. ያንንም ማርነው። ለእርሱም እኛ ዘንድ የመቅረብ ክብር መልካም መመለሻም አለው።

38:26

يَٰدَاوُۥدُ إِنَّا جَعَلۡنَٰكَ خَلِيفَةٗ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَٱحۡكُم بَيۡنَ ٱلنَّاسِ بِٱلۡحَقِّ وَلَا تَتَّبِعِ ٱلۡهَوَىٰ فَيُضِلَّكَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَضِلُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ لَهُمۡ عَذَابٞ شَدِيدُۢ بِمَا نَسُواْ يَوۡمَ ٱلۡحِسَابِ ﴿26﴾

Transliteration: Ya dawoodu inna jaAAalnaka khaleefatan fee alardi faohkum bayna alnnasi bialhaqqi wala tattabiAAi alhawa fayudillaka AAan sabeeli Allahi inna allatheena yadilloona AAan sabeeli Allahi lahum AAathabun shadeedun bima nasoo yawma alhisabi

Translation: 26. (እኛም አልነው) «ዳውድ ሆይ! እኛ በምድር ላይ ምትክ አድርገንሀልና በሰዎች መካከል በእውነት ፍረድ:: የግል ዝንባሌህንም አትከተል:: ከአላህ መንገድ ያሳስተሃልና።» እነዚያ ከአላህ መንገድ የሚሳሳቱ ሁሉ የምርመራውን ቀን በመርሳታቸው ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አለባቸው::

38:27

وَمَا خَلَقۡنَا ٱلسَّمَآءَ وَٱلۡأَرۡضَ وَمَا بَيۡنَهُمَا بَٰطِلٗاۚ ذَٰلِكَ ظَنُّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْۚ فَوَيۡلٞ لِّلَّذِينَ كَفَرُواْ مِنَ ٱلنَّارِ ﴿27﴾

Transliteration: Wama khalaqna alssamaa waalarda wama baynahuma batilan thalika thannu allatheena kafaroo fawaylun lillatheena kafaroo mina alnnari

Translation: 27. ሰማይን ምድርና በመካከላቸዉም ያለውን ሁሉ ለከንቱ አልፈጠርንም:: ይህ የእነዚያ የካዱት ሰዎች ጥርጣሬ ነው:: ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ሁሉ ከእሳት ወዮላቸው።

38:28

أَمۡ نَجۡعَلُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّـٰلِحَٰتِ كَٱلۡمُفۡسِدِينَ فِي ٱلۡأَرۡضِ أَمۡ نَجۡعَلُ ٱلۡمُتَّقِينَ كَٱلۡفُجَّارِ ﴿28﴾

Transliteration: Am najAAalu allatheena amanoo waAAamiloo alssalihati kaalmufsideena fee alardi am najAAalu almuttaqeena kaalfujjari

Translation: 28. በእውነቱ እነዚያ ያመኑትና መልካም ተግባሮችን የሰሩትን ልክ በምድር ውስጥ እንደሚያጠፉት እናደርጋለንን? ወይስ አላህን ፈሪዎችን ልክ እንደ ከሓዲያን እናደርጋለን?

38:29

كِتَٰبٌ أَنزَلۡنَٰهُ إِلَيۡكَ مُبَٰرَكٞ لِّيَدَّبَّرُوٓاْ ءَايَٰتِهِۦ وَلِيَتَذَكَّرَ أُوْلُواْ ٱلۡأَلۡبَٰبِ ﴿29﴾

Transliteration: Kitabun anzalnahu ilayka mubarakun liyaddabbaroo ayatihi waliyatathakkara oloo alalbabi

Translation: 29. ይህ መጽሀፍ ወደ አንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሀፍ ነው:: አናቅጽን እንዲያስተነትኑና የአእምሮ ባላቤቶችም እንዲገሰጹበት አወረድነው::

38:30

وَوَهَبۡنَا لِدَاوُۥدَ سُلَيۡمَٰنَۚ نِعۡمَ ٱلۡعَبۡدُ إِنَّهُۥٓ أَوَّابٌ ﴿30﴾

Transliteration: Wawahabna lidawooda sulaymana niAAma alAAabdu innahu awwabun

Translation: 30. ለዳውድም ሱለይማንን ሰጠነው:: ሱለይማን ምን ያምር ባሪያ ነው:: እርሱ ወደ ጌታው መላሳ ነውና::

38:31

إِذۡ عُرِضَ عَلَيۡهِ بِٱلۡعَشِيِّ ٱلصَّـٰفِنَٰتُ ٱلۡجِيَادُ ﴿31﴾

Transliteration: Ith AAurida AAalayhi bialAAashiyyi alssafinatu aljiyadu

Translation: 31. በእርሱ ላይ ከቀትር በኋላ በሶስት እግሮችና በአራተኛው እግር ኮቴ ጫፍ የሚቆሙ ጮሌ ፈረሶች በተቀረቡለት ጊዜ (የሆነዉን አስታውስ)::

38:32

فَقَالَ إِنِّيٓ أَحۡبَبۡتُ حُبَّ ٱلۡخَيۡرِ عَن ذِكۡرِ رَبِّي حَتَّىٰ تَوَارَتۡ بِٱلۡحِجَابِ ﴿32﴾

Transliteration: Faqala innee ahbabtu hubba alkhayri AAan thikri rabbee hatta tawarat bialhijabi

Translation: 32. (እንዲህም) አለ: «ጸሀይ በግርዶ እስከተደበቀች ድረስ ጌታየን ከማስታወስ ፈንታ ፈረስን መውደድን መረጥኩ!

38:33

رُدُّوهَا عَلَيَّۖ فَطَفِقَ مَسۡحَۢا بِٱلسُّوقِ وَٱلۡأَعۡنَاقِ ﴿33﴾

Transliteration: Ruddooha AAalayya fatafiqa mashan bialssooqi waalaAAnaqi

Translation: 33. «በሉ ፈረሶችን ወደ እኔ መልሷቸው።» (አለ)። ከዚያም እግሮቻቸዉንና አንገቶቻቸዉን መቁረጥ ያዘ::

38:34

وَلَقَدۡ فَتَنَّا سُلَيۡمَٰنَ وَأَلۡقَيۡنَا عَلَىٰ كُرۡسِيِّهِۦ جَسَدٗا ثُمَّ أَنَابَ ﴿34﴾

Transliteration: Walaqad fatanna sulaymana waalqayna AAala kursiyyihi jasadan thumma anaba

Translation: 34. ሱለይማንንም በእርግጥ ፈተንነው። በመንበሩም ላይ የሆነ አካልን ጣልን:: ከዚያም በመጸጸት ተመለሰ።

38:35

قَالَ رَبِّ ٱغۡفِرۡ لِي وَهَبۡ لِي مُلۡكٗا لَّا يَنۢبَغِي لِأَحَدٖ مِّنۢ بَعۡدِيٓۖ إِنَّكَ أَنتَ ٱلۡوَهَّابُ ﴿35﴾

Transliteration: Qala rabbi ighfir lee wahab lee mulkan la yanbaghee liahadin min baAAdee innaka anta alwahhabu

Translation: 35. «ጌታዬ ሆይ! ማረኝ ከእኔ በኋላ ለአንድም የማይገባን ንግስናንም ስጠኝ:: ለጋሹ አንተ ብቻ ነህና» አለ።

38:36

فَسَخَّرۡنَا لَهُ ٱلرِّيحَ تَجۡرِي بِأَمۡرِهِۦ رُخَآءً حَيۡثُ أَصَابَ ﴿36﴾

Transliteration: Fasakhkharna lahu alrreeha tajree biamrihi rukhaan haythu asaba

Translation: 36. ንፋስንም በትዕዛዙ ወደ ፈለገበት ስፍራ ልዝብ ሆና የምትነፍስ ስትሆን ገራንለት::

38:37

وَٱلشَّيَٰطِينَ كُلَّ بَنَّآءٖ وَغَوَّاصٖ ﴿37﴾

Transliteration: Waalshshayateena kulla bannain waghawwasin

Translation: 37. ሰይጣናትንም ገንቢዎችንና ሰማጮችን ሁሉ ገራንለት::

38:38

وَءَاخَرِينَ مُقَرَّنِينَ فِي ٱلۡأَصۡفَادِ ﴿38﴾

Transliteration: Waakhareena muqarraneena fee alasfadi

Translation: 38. ሌሎችንም በሰንሰለቶች ተቆራኞችን ገራንለት::

38:39

هَٰذَا عَطَآؤُنَا فَٱمۡنُنۡ أَوۡ أَمۡسِكۡ بِغَيۡرِ حِسَابٖ ﴿39﴾

Transliteration: Hatha AAataona faomnun aw amsik bighayri hisabin

Translation: 39. ይህ ስጦታችን ነው ያለ ግምት ለግስ:: ወይም ጨብጥ (አልነው)።

38:40

وَإِنَّ لَهُۥ عِندَنَا لَزُلۡفَىٰ وَحُسۡنَ مَـَٔابٖ ﴿40﴾

Transliteration: Wainna lahu AAindana lazulfa wahusna maabin

Translation: 40. ለእርሱም እኛ ዘንድ መቅረብ መልካም መመለሻም በእርግጥ አለው::

38:41

وَٱذۡكُرۡ عَبۡدَنَآ أَيُّوبَ إِذۡ نَادَىٰ رَبَّهُۥٓ أَنِّي مَسَّنِيَ ٱلشَّيۡطَٰنُ بِنُصۡبٖ وَعَذَابٍ ﴿41﴾

Transliteration: Waothkur AAabdana ayyooba ith nada rabbahu annee massaniya alshshaytanu binusbin waAAathabin

Translation: 41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ባሪያችን አዩብንም: «እኔ ሰይጣን በጉዳትና በስቃይ ነካኝ» ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ።የሆነውን አስታውስ

38:42

ٱرۡكُضۡ بِرِجۡلِكَۖ هَٰذَا مُغۡتَسَلُۢ بَارِدٞ وَشَرَابٞ ﴿42﴾

Transliteration: Orkud birijlika hatha mughtasalun baridun washarabun

Translation: 42. በእግርህ ምድርን ምታ:: ይህ ቀዝቃዛ መታጠቢያ መጠጥም ነው (ተባለ)::

38:43

وَوَهَبۡنَا لَهُۥٓ أَهۡلَهُۥ وَمِثۡلَهُم مَّعَهُمۡ رَحۡمَةٗ مِّنَّا وَذِكۡرَىٰ لِأُوْلِي ٱلۡأَلۡبَٰبِ ﴿43﴾

Transliteration: Wawahabna lahu ahlahu wamithlahum maAAahum rahmatan minna wathikra liolee alalbabi

Translation: 43. ለእርሱ ከእኛ ዘንድ በሆነ ችሮታ ባለ አእምሮዎችንም ለመገሰጽ ቤተሰቦቹንም ከእነርሱ ጋር መሰላቸውን ሰጠነው።

38:44

وَخُذۡ بِيَدِكَ ضِغۡثٗا فَٱضۡرِب بِّهِۦ وَلَا تَحۡنَثۡۗ إِنَّا وَجَدۡنَٰهُ صَابِرٗاۚ نِّعۡمَ ٱلۡعَبۡدُ إِنَّهُۥٓ أَوَّابٞ ﴿44﴾

Transliteration: Wakhuth biyadika dighthan faidrib bihi wala tahnath inna wajadnahu sabiran niAAma alAAabdu innahu awwabun

Translation: 44. «በእጅህ ጭብጥ አርጩሜን ያዝ በእርሱም (ሚስትህን) ምታ። ማላህንም አታፍርስ።» (አልነው) እነሆ ታጋሽ ሆኖ አገኘነው:: ምን ያምር ባሪያ ነው:: እርሱም በጣም መላሳ ነው።

38:45

وَٱذۡكُرۡ عِبَٰدَنَآ إِبۡرَٰهِيمَ وَإِسۡحَٰقَ وَيَعۡقُوبَ أُوْلِي ٱلۡأَيۡدِي وَٱلۡأَبۡصَٰرِ ﴿45﴾

Transliteration: Waothkur AAibadana ibraheema waishaqa wayaAAqooba olee alaydee waalabsari

Translation: 45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንዚያን የኅይልና የማስተዋል ባለቤቶች የሆኑትን ባሮቻችንም ኢብራሂምን ኢስሐቅንና ያዕቆብንም ለህዝቦችህ አውሳላቸው።

38:46

إِنَّآ أَخۡلَصۡنَٰهُم بِخَالِصَةٖ ذِكۡرَى ٱلدَّارِ ﴿46﴾

Transliteration: Inna akhlasnahum bikhalisatin thikra alddari

Translation: 46. እኛ ጥሩ በሆነች ጠባይ መረጥናቸው፤ እርሷም የመጨረሻይቱን አገር ማስታወስ ናት::

38:47

وَإِنَّهُمۡ عِندَنَا لَمِنَ ٱلۡمُصۡطَفَيۡنَ ٱلۡأَخۡيَارِ ﴿47﴾

Transliteration: Wainnahum AAindana lamina almustafayna alakhyari

Translation: 47. እነርሱም እኛ ዘንድ ከመልካሞቹ ምርጦች ናቸው::

38:48

وَٱذۡكُرۡ إِسۡمَٰعِيلَ وَٱلۡيَسَعَ وَذَا ٱلۡكِفۡلِۖ وَكُلّٞ مِّنَ ٱلۡأَخۡيَارِ ﴿48﴾

Transliteration: Waothkur ismaAAeela wailyasaAAa watha alkifli wakullun mina alakhyari

Translation: 48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢስማኢልንም፤ ኢልያስንም፤ ዙልኪፍልንም አውሳ፤ ሁሉም ከበላጮቹ ናቸው::

38:49

هَٰذَا ذِكۡرٞۚ وَإِنَّ لِلۡمُتَّقِينَ لَحُسۡنَ مَـَٔابٖ ﴿49﴾

Transliteration: Hatha thikrun wainna lilmuttaqeena lahusna maabin

Translation: 49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ መልካም ዝና ነው:: አላህን ለሚፈሩም በእርግጥ ውብ የሆነ መመለሻ አላቸው።

38:50

جَنَّـٰتِ عَدۡنٖ مُّفَتَّحَةٗ لَّهُمُ ٱلۡأَبۡوَٰبُ ﴿50﴾

Transliteration: Jannati AAadnin mufattahatan lahumu alabwabu

Translation: 50. በሮቻቸው ለእነርሱ የተከፈቱ ሲሆኑ የመኖሪያ ገነቶች አሏቸው::

38:51

مُتَّكِـِٔينَ فِيهَا يَدۡعُونَ فِيهَا بِفَٰكِهَةٖ كَثِيرَةٖ وَشَرَابٖ ﴿51﴾

Transliteration: Muttakieena feeha yadAAoona feeha bifakihatin katheeratin washarabin

Translation: 51. በእርሷ ውስጥ የተደገፉ ሆነው በውስጧ በብዙ እሸቶችና በመጠጥም ያዝዛሉ::

38:52

وَعِندَهُمۡ قَٰصِرَٰتُ ٱلطَّرۡفِ أَتۡرَابٌ ﴿52﴾

Transliteration: WaAAindahum qasiratu alttarfi atrabun

Translation: 52. እነርሱ ዘንድም ዓይኖቻቸውን በባሎቻቸው ላይ አሳጣሪዎች እኩያዎች ሴቶች አሉ::

38:53

هَٰذَا مَا تُوعَدُونَ لِيَوۡمِ ٱلۡحِسَابِ ﴿53﴾

Transliteration: Hatha ma tooAAadoona liyawmi alhisabi

Translation: 53. ይህ ለምርመራው ቀን የምትቀጠሩት ተስፋ ነው::

38:54

إِنَّ هَٰذَا لَرِزۡقُنَا مَا لَهُۥ مِن نَّفَادٍ ﴿54﴾

Transliteration: Inna hatha larizquna ma lahu min nafadin

Translation: 54. ይህ ሲሳያችን ነው:: ለእርሱ ምንም ማለቅ የለዉም::

38:55

هَٰذَاۚ وَإِنَّ لِلطَّـٰغِينَ لَشَرَّ مَـَٔابٖ ﴿55﴾

Transliteration: Hatha wainna lilttagheena lasharra maabin

Translation: 55. ይህ (ለትክክለኛ አማኞች ሲሆን።) ለጠማሞችም በጣም የከፋ መመለሻ አላቸው::

38:56

جَهَنَّمَ يَصۡلَوۡنَهَا فَبِئۡسَ ٱلۡمِهَادُ ﴿56﴾

Transliteration: Jahannama yaslawnaha fabisa almihadu

Translation: 56. የሚገቧት ስትሆን ገሀነም አለቻቸው:: ምንጣፊቱም ምንኛ ከፋች::

38:57

هَٰذَا فَلۡيَذُوقُوهُ حَمِيمٞ وَغَسَّاقٞ ﴿57﴾

Transliteration: Hatha falyathooqoohu hameemun waghassaqun

Translation: 57. ይህ ለከሓዲያን ነው:: ይቅመሱትም የፈላ ውሃና እዥ ነው::

38:58

وَءَاخَرُ مِن شَكۡلِهِۦٓ أَزۡوَٰجٌ ﴿58﴾

Transliteration: Waakharu min shaklihi azwajun

Translation: 58. ሌላም እነርሱን ከመሰሉ ብዙ አይነቶች አሉ::

38:59

هَٰذَا فَوۡجٞ مُّقۡتَحِمٞ مَّعَكُمۡ لَا مَرۡحَبَۢا بِهِمۡۚ إِنَّهُمۡ صَالُواْ ٱلنَّارِ ﴿59﴾

Transliteration: Hatha fawjun muqtahimun maAAakum la marhaban bihim innahum saloo alnnari

Translation: 59. ይህ ከናንተ ጋር በመጋፈጥ ገቢ ቡድን ነው (ይባላሉ):: ለእነርሱ አይስፋቸዉም:: እነርሱ እሳትን ገቢዎች ናቸውና (ይላሉ)::

38:60

قَالُواْ بَلۡ أَنتُمۡ لَا مَرۡحَبَۢا بِكُمۡۖ أَنتُمۡ قَدَّمۡتُمُوهُ لَنَاۖ فَبِئۡسَ ٱلۡقَرَارُ ﴿60﴾

Transliteration: Qaloo bal antum la marhaban bikum antum qaddamtumoohu lana fabisa alqararu

Translation: 60. ተከታዮቹም ይላሉ፡- «ይልቁን እናንተ አይስፋችሁ። እናንተ ክህደቱን ለእኛ አቀረባችሁት መርጊያይቱም ገሀነም ከፋች።»

38:61

قَالُواْ رَبَّنَا مَن قَدَّمَ لَنَا هَٰذَا فَزِدۡهُ عَذَابٗا ضِعۡفٗا فِي ٱلنَّارِ ﴿61﴾

Transliteration: Qaloo rabbana man qaddama lana hatha fazidhu AAathaban diAAfan fee alnnari

Translation: 61. «ጌታችን ሆይ! ይህንን ያቀረበልንን ሰው በእሳት ውስጥ ድርብ ቅጣትን ጨምርለት» ይላሉ።

38:62

وَقَالُواْ مَا لَنَا لَا نَرَىٰ رِجَالٗا كُنَّا نَعُدُّهُم مِّنَ ٱلۡأَشۡرَارِ ﴿62﴾

Transliteration: Waqaloo ma lana la nara rijalan kunna naAAudduhum mina alashrari

Translation: 62. ይላሉም «ለእኛ ምን አለን? ከመጥፎዎች እንቆጥራቸው የነበሩትን ሰዎች እዚህ አናይምሳ።

38:63

أَتَّخَذۡنَٰهُمۡ سِخۡرِيًّا أَمۡ زَاغَتۡ عَنۡهُمُ ٱلۡأَبۡصَٰرُ ﴿63﴾

Transliteration: Attakhathnahum sikhriyyan am zaghat AAanhumu alabsaru

Translation: 63. «(ሳይገባቸው) መቀለጃ አድርገን ይዘናቸው ነውን? ወይስ ዓይኖቻችን ከእነርሱ ዋለሉ?»

38:64

إِنَّ ذَٰلِكَ لَحَقّٞ تَخَاصُمُ أَهۡلِ ٱلنَّارِ ﴿64﴾

Transliteration: Inna thalika lahaqqun takhasumu ahli alnnari

Translation: 64. ይህ በእርግጥ እውነት ነው:: እርሱም የእሳት ሰዎች የእርስ በርስ የመካሰስ ወሬ ነው::

38:65

قُلۡ إِنَّمَآ أَنَا۠ مُنذِرٞۖ وَمَا مِنۡ إِلَٰهٍ إِلَّا ٱللَّهُ ٱلۡوَٰحِدُ ٱلۡقَهَّارُ ﴿65﴾

Transliteration: Qul innama ana munthirun wama min ilahin illa Allahu alwahidu alqahharu

Translation: 65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በል: «እኔ አስፈራሪ ብቻ ነኝ። ኃያልና አንድ ከሆነ አላህ በስተቀር ምንም አምላክ የለም።

38:66

رَبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَا ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡغَفَّـٰرُ ﴿66﴾

Transliteration: Rabbu alssamawati waalardi wama baynahuma alAAazeezu alghaffaru

Translation: 66. «የሰማያትና የምድር በመካከላቸዉም ያለው ሁሉ ጌታ አሸናፊና መሐሪ ነው።»

38:67

قُلۡ هُوَ نَبَؤٌاْ عَظِيمٌ ﴿67﴾

Transliteration: Qul huwa nabaon AAatheemun

Translation: 67. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በል: «እርሱ (ቁርኣን) ታላቅ ዜና ነው።

38:68

أَنتُمۡ عَنۡهُ مُعۡرِضُونَ ﴿68﴾

Transliteration: Antum AAanhu muAAridoona

Translation: 68. «እናንተ ከእርሱ ዘንጊዎች ናችሁ።

38:69

مَا كَانَ لِيَ مِنۡ عِلۡمِۭ بِٱلۡمَلَإِ ٱلۡأَعۡلَىٰٓ إِذۡ يَخۡتَصِمُونَ ﴿69﴾

Transliteration: Ma kana liya min AAilmin bialmalai alaAAla ith yakhtasimoona

Translation: 69. «በሚከራከሩ ጊዜ በላይኛዋ ሰራዊት ለእኔ ምንም እውቀት አልነበረኝም።

38:70

إِن يُوحَىٰٓ إِلَيَّ إِلَّآ أَنَّمَآ أَنَا۠ نَذِيرٞ مُّبِينٌ ﴿70﴾

Transliteration: In yooha ilayya illa annama ana natheerun mubeenun

Translation: 70. «ወደ እኔም አስፈራሪ ገላጭ በመሆኔ እንጂ በሌላ አይወርድልኝም።» በል::

38:71

إِذۡ قَالَ رَبُّكَ لِلۡمَلَـٰٓئِكَةِ إِنِّي خَٰلِقُۢ بَشَرٗا مِّن طِينٖ ﴿71﴾

Transliteration: Ith qala rabbuka lilmalaikati innee khaliqun basharan min teenin

Translation: 71. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታህ ለመላዕክት እኔ ሰውን ከጭቃ ፈጣሪ ነኝ ባለ ጊዜ (የነበረዉን አስታውስ)::

38:72

فَإِذَا سَوَّيۡتُهُۥ وَنَفَخۡتُ فِيهِ مِن رُّوحِي فَقَعُواْ لَهُۥ سَٰجِدِينَ ﴿72﴾

Transliteration: Faitha sawwaytuhu wanafakhtu feehi min roohee faqaAAoo lahu sajideena

Translation: 72. «ፍጥረቱንም ባስተካከልኩና ከመንፈሴ በነፋሁበትም ጊዜ ሁላችሁም ለእርሱ ሰጋጆች ሆናችሁ ውደቁ።» (አልኩ።)

38:73

فَسَجَدَ ٱلۡمَلَـٰٓئِكَةُ كُلُّهُمۡ أَجۡمَعُونَ ﴿73﴾

Transliteration: Fasajada almalaikatu kulluhum ajmaAAoona

Translation: 73. መላው መላዕክትም በአንድነት ሰገዱ።

38:74

إِلَّآ إِبۡلِيسَ ٱسۡتَكۡبَرَ وَكَانَ مِنَ ٱلۡكَٰفِرِينَ ﴿74﴾

Transliteration: Illa ibleesa istakbara wakana mina alkafireena

Translation: 74. ዲያብሎስ ብቻ ሲቀር። ኮራም። ከከሓዲያንም ሆነ።

38:75

قَالَ يَـٰٓإِبۡلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسۡجُدَ لِمَا خَلَقۡتُ بِيَدَيَّۖ أَسۡتَكۡبَرۡتَ أَمۡ كُنتَ مِنَ ٱلۡعَالِينَ ﴿75﴾

Transliteration: Qala ya ibleesu ma manaAAaka an tasjuda lima khalaqtu biyadayya astakbarta am kunta mina alAAaleena

Translation: 75. አላህ «ዲያብሎስ ሆይ! በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት ለአደም ከመስገድ ምን ከለከለህ? ኮርተህ ነው? ወይስ ፊቱኑ ከትዕቢተኞች ነበርክ?» አለው።

38:76

قَالَ أَنَا۠ خَيۡرٞ مِّنۡهُ خَلَقۡتَنِي مِن نَّارٖ وَخَلَقۡتَهُۥ مِن طِينٖ ﴿76﴾

Transliteration: Qala ana khayrun minhu khalaqtanee min narin wakhalaqtahu min teenin

Translation: 76. ዲያብሎስም «እኔ ከእርሱ የተሻልኩ ነኝ። እኔን ከእሳት የፈጠርከኝ ስትሆን እሱን ግን ከጭቃ ነው የፈጠርከው።» አለ።

38:77

قَالَ فَٱخۡرُجۡ مِنۡهَا فَإِنَّكَ رَجِيمٞ ﴿77﴾

Transliteration: Qala faokhruj minha fainnaka rajeemun

Translation: 77. (አላህም) አለ፡- «ከእርሷ ውጣ። አንተ የተባረርክ ነህና።

38:78

وَإِنَّ عَلَيۡكَ لَعۡنَتِيٓ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلدِّينِ ﴿78﴾

Transliteration: Wainna AAalayka laAAnatee ila yawmi alddeeni

Translation: 78. «እርግማኔም እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ ባንተ ላይ ይሁን።» አለው።

38:79

قَالَ رَبِّ فَأَنظِرۡنِيٓ إِلَىٰ يَوۡمِ يُبۡعَثُونَ ﴿79﴾

Transliteration: Qala rabbi faanthirnee ila yawmi yubAAathoona

Translation: 79. (ዲያብሎስም) «ጌታየ ሆይ! እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ እባክህ አቆየኝ።» አለ

38:80

قَالَ فَإِنَّكَ مِنَ ٱلۡمُنظَرِينَ ﴿80﴾

Transliteration: Qala fainnaka mina almunthareena

Translation: 80. (አላህም) አለ፡- «አንተ ከሚቆዩት ነህ።

38:81

إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡوَقۡتِ ٱلۡمَعۡلُومِ ﴿81﴾

Transliteration: Ila yawmi alwaqti almaAAloomi

Translation: 81. «እስከ ታወቀው ወቅት ቀን ድረስ።»

38:82

قَالَ فَبِعِزَّتِكَ لَأُغۡوِيَنَّهُمۡ أَجۡمَعِينَ ﴿82﴾

Transliteration: Qala fabiAAizzatika laoghwiyannahum ajmaAAeena

Translation: 82. (እርሱም) አለ: «በአሸናፊነትህ ይሁንብኝ ሁላቸዉንም አሳስታቸዋለሁ።

38:83

إِلَّا عِبَادَكَ مِنۡهُمُ ٱلۡمُخۡلَصِينَ ﴿83﴾

Transliteration: Illa AAibadaka minhumu almukhlaseena

Translation: 83. «ከእነርሱ መካከል ምርጥ ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ።»

38:84

قَالَ فَٱلۡحَقُّ وَٱلۡحَقَّ أَقُولُ ﴿84﴾

Transliteration: Qala faalhaqqu waalhaqqa aqoolu

Translation: 84. (አላህም) አለ: «እውነቱም ከእኔ ነው:: እውነትንም እላለሁ(እናገራለሁ)።

38:85

لَأَمۡلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنكَ وَمِمَّن تَبِعَكَ مِنۡهُمۡ أَجۡمَعِينَ ﴿85﴾

Transliteration: Laamlaanna jahannama minka wamimman tabiAAaka minhum ajmaAAeena

Translation: 85. «በአንተና ከእነርሱ መካከል በተከተሉህም ባንድ ላይ ገሀነምን በእርግጥ እሞላታለሁ» አለው።

38:86

قُلۡ مَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٖ وَمَآ أَنَا۠ مِنَ ٱلۡمُتَكَلِّفِينَ ﴿86﴾

Transliteration: Qul ma asalukum AAalayhi min ajrin wama ana mina almutakallifeena

Translation: 86.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በል: «በእርሱ ላይ ምንም ዋጋ አል ጠይቃችሁም:: እኔም ከተግደርዳሪዎቹ አይደለሁም።

38:87

إِنۡ هُوَ إِلَّا ذِكۡرٞ لِّلۡعَٰلَمِينَ ﴿87﴾

Transliteration: In huwa illa thikrun lilAAalameena

Translation: 87. «እርሱ (ቁርኣን) ለዓለማት መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም።

38:88

وَلَتَعۡلَمُنَّ نَبَأَهُۥ بَعۡدَ حِينِۭ ﴿88﴾

Transliteration: WalataAAlamunna nabaahu baAAda heenin

Translation: 88. «የትንቢቱን እውነትነት ከጊዜ በኋላም ቢሆን በእርግጥ ታውቁታላችሁ።» በላቸው።

Transliteration source: English Transliteration by Tanzil. Used under Tanzil's non-commercial terms; see the source and latest updates at Tanzil. Tanzil translation download