quranm◉

Surah Qaf transliteration

◉ ሱራ · ∞

50:1

قٓۚ وَٱلۡقُرۡءَانِ ٱلۡمَجِيدِ ﴿1﴾

Transliteration: Qaf waalqurani almajeedi

Translation: 1. ቃፍ ፤ በተከበረው ቁርኣን እምላለሁ::

50:2

بَلۡ عَجِبُوٓاْ أَن جَآءَهُم مُّنذِرٞ مِّنۡهُمۡ فَقَالَ ٱلۡكَٰفِرُونَ هَٰذَا شَيۡءٌ عَجِيبٌ ﴿2﴾

Transliteration: Bal AAajiboo an jaahum munthirun minhum faqala alkafiroona hatha shayon AAajeebun

Translation: 2. ይልቁንም ከእነርሱ መካከል የሆነ አስፈራሪ ስለ መጣላቸው ተደነቁ:: ከሓዲያንም አሉ: «ይህ አስደናቂ ነገር ነው።

50:3

أَءِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابٗاۖ ذَٰلِكَ رَجۡعُۢ بَعِيدٞ ﴿3﴾

Transliteration: Aitha mitna wakunna turaban thalika rajAAun baAAeedun

Translation: 3. «በሞትንና አፈር በሆንን ጊዜ እንመለሳለንን? ይህ ሩቅ የሆነ መመለስ ነው።» አሉ።

50:4

قَدۡ عَلِمۡنَا مَا تَنقُصُ ٱلۡأَرۡضُ مِنۡهُمۡۖ وَعِندَنَا كِتَٰبٌ حَفِيظُۢ ﴿4﴾

Transliteration: Qad AAalimna ma tanqusu alardu minhum waAAindana kitabun hafeethun

Translation: 4. ከእነርሱ አካል ምድር የምታጎድለውን በእርግጥ አውቀናል:: እኛም ዘንድ ጠባቂ መጽሐፍ አለ::

50:5

بَلۡ كَذَّبُواْ بِٱلۡحَقِّ لَمَّا جَآءَهُمۡ فَهُمۡ فِيٓ أَمۡرٖ مَّرِيجٍ ﴿5﴾

Transliteration: Bal kaththaboo bialhaqqi lamma jaahum fahum fee amrin mareejin

Translation: 5. ይልቁንም ቁርኣን በመጣላቸው ጊዜ አስተባበሉ። እነርሱም በተምታታ ነገር ውስጥ ናቸው።

50:6

أَفَلَمۡ يَنظُرُوٓاْ إِلَى ٱلسَّمَآءِ فَوۡقَهُمۡ كَيۡفَ بَنَيۡنَٰهَا وَزَيَّنَّـٰهَا وَمَا لَهَا مِن فُرُوجٖ ﴿6﴾

Transliteration: Afalam yanthuroo ila alssamai fawqahum kayfa banaynaha wazayyannaha wama laha min furoojin

Translation: 6. ወደ ሰማይም ከበላያቸው ስትሆን ለእርሷ ምንም ቀዳዳዎች የሌሏቸው ሆነው እንዴት እንደገነባናትና በከዋክብት እንዳጌጥናት አልተመለከቱምን?

50:7

وَٱلۡأَرۡضَ مَدَدۡنَٰهَا وَأَلۡقَيۡنَا فِيهَا رَوَٰسِيَ وَأَنۢبَتۡنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوۡجِۭ بَهِيجٖ ﴿7﴾

Transliteration: Waalarda madadnaha waalqayna feeha rawasiya waanbatna feeha min kulli zawjin baheejin

Translation: 7. ምድርም ዘረጋናት በእርሷም ውስጥ ጋራዎችን ጣልንባት :: በውስጧም ከሚያስደስት አይነት ሁሉ አበቀልን::

50:8

تَبۡصِرَةٗ وَذِكۡرَىٰ لِكُلِّ عَبۡدٖ مُّنِيبٖ ﴿8﴾

Transliteration: Tabsiratan wathikra likulli AAabdin muneebin

Translation: 8. ይህንን ያደረግነው ተመላሽ ለሆነ ባሪያ ሁሉ ለማሳየትና ለማስገንዘብ ነው::

50:9

وَنَزَّلۡنَا مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ مُّبَٰرَكٗا فَأَنۢبَتۡنَا بِهِۦ جَنَّـٰتٖ وَحَبَّ ٱلۡحَصِيدِ ﴿9﴾

Transliteration: Wanazzalna mina alssamai maan mubarakan faanbatna bihi jannatin wahabba alhaseedi

Translation: 9. ከሰማይም ብሩክን ውሃ አወረድን በእርሱም አትክልቶችንና የሚታጨድን አዝመራ ፍሬ አበቀልን::

50:10

وَٱلنَّخۡلَ بَاسِقَٰتٖ لَّهَا طَلۡعٞ نَّضِيدٞ ﴿10﴾

Transliteration: Waalnnakhla basiqatin laha talAAun nadeedun

Translation: 10. ዘንባባንም ረዣዥም ለእርሷ የተደራረበ እንቡጥ ያላት ስትሆን አበቀልን::

50:11

رِّزۡقٗا لِّلۡعِبَادِۖ وَأَحۡيَيۡنَا بِهِۦ بَلۡدَةٗ مَّيۡتٗاۚ كَذَٰلِكَ ٱلۡخُرُوجُ ﴿11﴾

Transliteration: Rizqan lilAAibadi waahyayna bihi baldatan maytan kathalika alkhurooju

Translation: 11. ለባሮቹ ሲሳይ ትሆን ዘንድ (አዘጋጀናት):: በእርሱም የሞተችን ሀገር ሕያው አደረግንበት:: ከመቃብር መውጣትም ልክ እንደዚሁ ነው::

50:12

كَذَّبَتۡ قَبۡلَهُمۡ قَوۡمُ نُوحٖ وَأَصۡحَٰبُ ٱلرَّسِّ وَثَمُودُ ﴿12﴾

Transliteration: Kaththabat qablahum qawmu noohin waashabu alrrassi wathamoodu

Translation: 12. ከእነርሱ በፊት የኑህ ህዝቦችና የረስስ ሰዎችም ሰሙድም አስተባበሉ::

50:13

وَعَادٞ وَفِرۡعَوۡنُ وَإِخۡوَٰنُ لُوطٖ ﴿13﴾

Transliteration: WaAAadun wafirAAawnu waikhwanu lootin

Translation: 13. ዓድም ፈርዖንም የሉጥ ወንድሞችም፤

50:14

وَأَصۡحَٰبُ ٱلۡأَيۡكَةِ وَقَوۡمُ تُبَّعٖۚ كُلّٞ كَذَّبَ ٱلرُّسُلَ فَحَقَّ وَعِيدِ ﴿14﴾

Transliteration: Waashabu alaykati waqawmu tubbaAAin kullun kaththaba alrrusula fahaqqa waAAeedi

Translation: 14. የጫካው ባለቤቶችም የቱብበዕ ህዝቦችም ሁሉ መልዕክተኞችን አስተባበሉ:: ዛቻየም ተረጋገጠባቸው።

50:15

أَفَعَيِينَا بِٱلۡخَلۡقِ ٱلۡأَوَّلِۚ بَلۡ هُمۡ فِي لَبۡسٖ مِّنۡ خَلۡقٖ جَدِيدٖ ﴿15﴾

Transliteration: AfaAAayeena bialkhalqi alawwali bal hum fee labsin min khalqin jadeedin

Translation: 15. በመጀመሪያው መፍጠር ደከምን? በእውነቱ እነርሱ ከአዲስ መፍጠር በመጠራጠር ውስጥ ናቸው::

50:16

وَلَقَدۡ خَلَقۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ وَنَعۡلَمُ مَا تُوَسۡوِسُ بِهِۦ نَفۡسُهُۥۖ وَنَحۡنُ أَقۡرَبُ إِلَيۡهِ مِنۡ حَبۡلِ ٱلۡوَرِيدِ ﴿16﴾

Transliteration: Walaqad khalaqna alinsana wanaAAlamu ma tuwaswisu bihi nafsuhu wanahnu aqrabu ilayhi min habli alwareedi

Translation: 16. ሰውንም ነፍሱ በሀሳቡ የምታጫውተውን የምናውቅ ስንሆን ፈጠርነው:: እኛም ከደም ጋኑ ጅማት ይበልጥ ወደ እርሱ ቅርብ ነን::

50:17

إِذۡ يَتَلَقَّى ٱلۡمُتَلَقِّيَانِ عَنِ ٱلۡيَمِينِ وَعَنِ ٱلشِّمَالِ قَعِيدٞ ﴿17﴾

Transliteration: Ith yatalaqqa almutalaqqiyani AAani alyameeni waAAani alshshimali qaAAeedun

Translation: 17-ሁለት ቃል ተቀባዮች መላዕክት ከቀኝና ከግራ ተቀማጮች ሆነው በሚቀበሉ ጊዜ አስታውስ::

50:18

مَّا يَلۡفِظُ مِن قَوۡلٍ إِلَّا لَدَيۡهِ رَقِيبٌ عَتِيدٞ ﴿18﴾

Transliteration: Ma yalfithu min qawlin illa ladayhi raqeebun AAateedun

Translation: 18. ከቃል ምንም አይናገርም ከአጠገቡ ተጠባባቂ እና ዝግጁ የሆኑ መላዕክት ያሉበት ቢሆን እንጂ::

50:19

وَجَآءَتۡ سَكۡرَةُ ٱلۡمَوۡتِ بِٱلۡحَقِّۖ ذَٰلِكَ مَا كُنتَ مِنۡهُ تَحِيدُ ﴿19﴾

Transliteration: Wajaat sakratu almawti bialhaqqi thalika ma kunta minhu taheedu

Translation: 19. የሞትም መከራ እውነቱን ነገር ታመጣለች። «(ሰው ሆይ!) ይህ ያ ከእርሱ ትሸሸው የነበርከው ነው» ይባላል።

50:20

وَنُفِخَ فِي ٱلصُّورِۚ ذَٰلِكَ يَوۡمُ ٱلۡوَعِيدِ ﴿20﴾

Transliteration: Wanufikha fee alssoori thalika yawmu alwaAAeedi

Translation: 20. በቀንዱም ውስጥ ይነፋል። ያ ቀን የዛቻው መፈጸሚያ ቀን ነው::

50:21

وَجَآءَتۡ كُلُّ نَفۡسٖ مَّعَهَا سَآئِقٞ وَشَهِيدٞ ﴿21﴾

Transliteration: Wajaat kullu nafsin maAAaha saiqun washaheedun

Translation: 21. ነፍስም ሁሉ ከእርሷ ጋር ነጅና መስካሪ ያለባት ሆና ትመጣለች::

50:22

لَّقَدۡ كُنتَ فِي غَفۡلَةٖ مِّنۡ هَٰذَا فَكَشَفۡنَا عَنكَ غِطَآءَكَ فَبَصَرُكَ ٱلۡيَوۡمَ حَدِيدٞ ﴿22﴾

Transliteration: Laqad kunta fee ghaflatin min hatha fakashafna AAanka ghitaaka fabasaruka alyawma hadeedun

Translation: 22. «ከዚህ ነገር በእርግጥ የዘነጋህ ነበርክ። ሽፋንህንም ካንተ ላይ ገለጥንልህ:: ስለዚህ ዛሬ ዓይንህ ስለታም ነው» (ይባላል)::

50:23

وَقَالَ قَرِينُهُۥ هَٰذَا مَا لَدَيَّ عَتِيدٌ ﴿23﴾

Transliteration: Waqala qareenuhu hatha ma ladayya AAateedun

Translation: 23. ቁራኛዉም (መልዓክ) «ይህ ያ እኔ ዘንድ ያለው ቀራቢ ነው።» ይላል።

50:24

أَلۡقِيَا فِي جَهَنَّمَ كُلَّ كَفَّارٍ عَنِيدٖ ﴿24﴾

Transliteration: Alqiya fee jahannama kulla kaffarin AAaneedin

Translation: 24. (አላህም ይላል): «ሞገደኛ ከሓዲን ሁሉ በገሀነም ውስጥ ጣሉ።

50:25

مَّنَّاعٖ لِّلۡخَيۡرِ مُعۡتَدٖ مُّرِيبٍ ﴿25﴾

Transliteration: MannaAAin lilkhayri muAAtadin mureebin

Translation: 25. «ለበጎ ስራ ከልካይ በዳይ ተጠራጣሪ የሆነን ሁሉ ጣሉ።

50:26

ٱلَّذِي جَعَلَ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَأَلۡقِيَاهُ فِي ٱلۡعَذَابِ ٱلشَّدِيدِ ﴿26﴾

Transliteration: Allathee jaAAala maAAa Allahi ilahan akhara faalqiyahu fee alAAathabi alshshadeedi

Translation: 26. «ያንን ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ ያደረገውን በብርቱ ቅጣት ውስጥ ጣሉት» ይባላል።

50:27

قَالَ قَرِينُهُۥ رَبَّنَا مَآ أَطۡغَيۡتُهُۥ وَلَٰكِن كَانَ فِي ضَلَٰلِۭ بَعِيدٖ ﴿27﴾

Transliteration: Qala qareenuhu rabbana ma atghaytuhu walakin kana fee dalalin baAAeedin

Translation: 27. «ቁራኛው (ሰይጣን) ጌታችን ሆይ! እኔ አላሳሳትኩትም ግን ራሱ በሩቅ ስህተት ውስጥ ነበር» ይላል።

50:28

قَالَ لَا تَخۡتَصِمُواْ لَدَيَّ وَقَدۡ قَدَّمۡتُ إِلَيۡكُم بِٱلۡوَعِيدِ ﴿28﴾

Transliteration: Qala la takhtasimoo ladayya waqad qaddamtu ilaykum bialwaAAeedi

Translation: 28. (አላህም) ይላል: «ወደ እናተ ዛቻን በእርግጥ ያስቀደምኩ ስሆን እኔ ዘንድ አትጨቃጨቁ።

50:29

مَا يُبَدَّلُ ٱلۡقَوۡلُ لَدَيَّ وَمَآ أَنَا۠ بِظَلَّـٰمٖ لِّلۡعَبِيدِ ﴿29﴾

Transliteration: Ma yubaddalu alqawlu ladayya wama ana bithallamin lilAAabeedi

Translation: 29. «ቃሉ እኔ ዘንድ አይለወጥም እኔም ለባሮቼ ፈጽሞ በዳይ አይደለሁም» (ይላቸዋል)።

50:30

يَوۡمَ نَقُولُ لِجَهَنَّمَ هَلِ ٱمۡتَلَأۡتِ وَتَقُولُ هَلۡ مِن مَّزِيدٖ ﴿30﴾

Transliteration: Yawma naqoolu lijahannama hali imtalati wataqoolu hal min mazeedin

Translation: 30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለገሀነም «ሞላሽን?» የምንልበትንና (ገሀነምም) «ጭማሪ አለን?» የምትልበትን ቀን አስጠንቅቃቸው::

50:31

وَأُزۡلِفَتِ ٱلۡجَنَّةُ لِلۡمُتَّقِينَ غَيۡرَ بَعِيدٍ ﴿31﴾

Transliteration: Waozlifati aljannatu lilmuttaqeena ghayra baAAeedin

Translation: 31. ገነትም አላህን ለፈሩት ሁሉ ሩቅ ባልሆነ ስፍራ ትቀረባለች::

50:32

هَٰذَا مَا تُوعَدُونَ لِكُلِّ أَوَّابٍ حَفِيظٖ ﴿32﴾

Transliteration: Hatha ma tooAAadoona likulli awwabin hafeethin

Translation: 32. (ይባላሉም) «ይህ ወደ አላህ ተመላሽና ህግጋቱን ጠባቂ ለሆነ ሁሉ የተቀጠራችሁት ነው።

50:33

مَّنۡ خَشِيَ ٱلرَّحۡمَٰنَ بِٱلۡغَيۡبِ وَجَآءَ بِقَلۡبٖ مُّنِيبٍ ﴿33﴾

Transliteration: Man khashiya alrrahmana bialghaybi wajaa biqalbin muneebin

Translation: 33. «አር-ረህማንን በሩቅ ሆኖ ለፈራና በተመላሽ ልብ ለመጣ ትቅቀረባለች::

50:34

ٱدۡخُلُوهَا بِسَلَٰمٖۖ ذَٰلِكَ يَوۡمُ ٱلۡخُلُودِ ﴿34﴾

Transliteration: Odkhulooha bisalamin thalika yawmu alkhuloodi

Translation: 34. «በሰላም ግቧታ ይህ የመዘውተሪያ ቀን ነው» (ይባላሉ)።

50:35

لَهُم مَّا يَشَآءُونَ فِيهَا وَلَدَيۡنَا مَزِيدٞ ﴿35﴾

Transliteration: Lahum ma yashaoona feeha waladayna mazeedun

Translation: 35. ለእነርሱ በውስጧ ሲሆኑ የሚሹት ሁሉ አላቸው እኛም ዘንድ ጭማሪ አለ::

50:36

وَكَمۡ أَهۡلَكۡنَا قَبۡلَهُم مِّن قَرۡنٍ هُمۡ أَشَدُّ مِنۡهُم بَطۡشٗا فَنَقَّبُواْ فِي ٱلۡبِلَٰدِ هَلۡ مِن مَّحِيصٍ ﴿36﴾

Transliteration: Wakam ahlakna qablahum min qarnin hum ashaddu minhum batshan fanaqqaboo fee albiladi hal min maheesin

Translation: 36. ከእነርሱም (ከቁረይሾች) በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች በሀያልነት ከእነርሱ ይበልጥ የበረቱ ሆነው ማምለጫ ፍለጋ በየሀገሮቹ የመረመሩ ብዙዎችንም አጥፍተናል። ማምለጫ አለን?

50:37

إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَذِكۡرَىٰ لِمَن كَانَ لَهُۥ قَلۡبٌ أَوۡ أَلۡقَى ٱلسَّمۡعَ وَهُوَ شَهِيدٞ ﴿37﴾

Transliteration: Inna fee thalika lathikra liman kana lahu qalbun aw alqa alssamAAa wahuwa shaheedun

Translation: 37. በዚሁ ውስጥ ልብ ላለው ወይም እርሱ በህሊናው ጆሮውን የሰጠ ሆኖ ወደ ሚነበብለት ጆሮውን ለጣለ ሰው ሁሉ ግሳጼ አለበት::

50:38

وَلَقَدۡ خَلَقۡنَا ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ وَمَا بَيۡنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٖ وَمَا مَسَّنَا مِن لُّغُوبٖ ﴿38﴾

Transliteration: Walaqad khalaqna alssamawati waalarda wama baynahuma fee sittati ayyamin wama massana min lughoobin

Translation: 38. ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን። ድካምም ምንም አልነካንም::

50:39

فَٱصۡبِرۡ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَسَبِّحۡ بِحَمۡدِ رَبِّكَ قَبۡلَ طُلُوعِ ٱلشَّمۡسِ وَقَبۡلَ ٱلۡغُرُوبِ ﴿39﴾

Transliteration: Faisbir AAala ma yaqooloona wasabbih bihamdi rabbika qabla tulooAAi alshshamsi waqabla alghuroobi

Translation: 39. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሚሉትም ላይ ታገስ ጌታህንም ከማመስገን ጋር ጸሐይ ከመውጣቷ በፊትና ከመገባቷም በፊት አጥራው።

50:40

وَمِنَ ٱلَّيۡلِ فَسَبِّحۡهُ وَأَدۡبَٰرَ ٱلسُّجُودِ ﴿40﴾

Transliteration: Wamina allayli fasabbihhu waadbara alssujoodi

Translation: 40. ከሌሊትም አጥራው፤ ከስግደቶችም በኋላዎች አጥራው።

50:41

وَٱسۡتَمِعۡ يَوۡمَ يُنَادِ ٱلۡمُنَادِ مِن مَّكَانٖ قَرِيبٖ ﴿41﴾

Transliteration: WaistamiAA yawma yunadi almunadi min makanin qareebin

Translation: 41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (የሚነገርህን) አዳምጥም፤ ጠሪው ከቅርብ ስፍራ በሚጠራበት ቀን ከመቃብራቸው ይወጣሉ።

50:42

يَوۡمَ يَسۡمَعُونَ ٱلصَّيۡحَةَ بِٱلۡحَقِّۚ ذَٰلِكَ يَوۡمُ ٱلۡخُرُوجِ ﴿42﴾

Transliteration: Yawma yasmaAAoona alssayhata bialhaqqi thalika yawmu alkhurooji

Translation: 42. ጩኸቲቱን በእውነቱ የሚሰሙበት ቀን፤ ያ ከመቃብር የመውጫው ቀን ነው።

50:43

إِنَّا نَحۡنُ نُحۡيِۦ وَنُمِيتُ وَإِلَيۡنَا ٱلۡمَصِيرُ ﴿43﴾

Transliteration: Inna nahnu nuhyee wanumeetu wailayna almaseeru

Translation: 43. እኛው ሕያው እናደርጋለን:: እንገድላለንም:: በመጨረሻም ጊዜ መመለሻው ወደ እኛ ብቻ ነው::

50:44

يَوۡمَ تَشَقَّقُ ٱلۡأَرۡضُ عَنۡهُمۡ سِرَاعٗاۚ ذَٰلِكَ حَشۡرٌ عَلَيۡنَا يَسِيرٞ ﴿44﴾

Transliteration: Yawma tashaqqaqu alardu AAanhum siraAAan thalika hashrun AAalayna yaseerun

Translation: 44. የሚፈጥኑ ሆነው ምድር ከእነርሱ ላይ የምትሰነጣጠቅበት ቀን (የመውጫ ቀን ነው):: ይህ በእኛ ላይ ገር የሆነ መሰብሰብ ነው::

50:45

نَّحۡنُ أَعۡلَمُ بِمَا يَقُولُونَۖ وَمَآ أَنتَ عَلَيۡهِم بِجَبَّارٖۖ فَذَكِّرۡ بِٱلۡقُرۡءَانِ مَن يَخَافُ وَعِيدِ ﴿45﴾

Transliteration: Nahnu aAAlamu bima yaqooloona wama anta AAalayhim bijabbarin fathakkir bialqurani man yakhafu waAAeedi

Translation: 45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ የሚሉትን ሁሉ አዋቂ ነን:: አንተም በእነርሱ ላይ አሰገዳጅ አይደለህም:: ስለዚህ ዛቻየን የሚፈራን ሰው ሁሉ በቁርኣን አስታውስ::

Transliteration source: English Transliteration by Tanzil. Used under Tanzil's non-commercial terms; see the source and latest updates at Tanzil. Tanzil translation download