quranm◉

Surah Al-A'raf transliteration

◉ ሱራ · ∞

7:1

الٓمٓصٓ ﴿1﴾

Transliteration: Aliflammeemsad

Translation: 1. አሊፍ፤ ላም፤ ሚም፤ ሷድ::

7:2

كِتَٰبٌ أُنزِلَ إِلَيۡكَ فَلَا يَكُن فِي صَدۡرِكَ حَرَجٞ مِّنۡهُ لِتُنذِرَ بِهِۦ وَذِكۡرَىٰ لِلۡمُؤۡمِنِينَ ﴿2﴾

Transliteration: Kitabun onzila ilayka fala yakun fee sadrika harajun minhu litunthira bihi wathikra lilmumineena

Translation: 2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ልታስጠነቅቅበትና ለምእመናንም መገሰጫ እንዲሆን ወደ አንተ የተወረደ ቁርኣን ነው:: ስለዚህ ልብህ ውስጥ ከእርሱ ጭንቀት አይኑር::

7:3

ٱتَّبِعُواْ مَآ أُنزِلَ إِلَيۡكُم مِّن رَّبِّكُمۡ وَلَا تَتَّبِعُواْ مِن دُونِهِۦٓ أَوۡلِيَآءَۗ قَلِيلٗا مَّا تَذَكَّرُونَ ﴿3﴾

Transliteration: IttabiAAoo ma onzila ilaykum min rabbikum wala tattabiAAoo min doonihi awliyaa qaleelan ma tathakkaroona

Translation: 3. (ሰዎች ሆይ! ) ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደላችሁን መልዕክት ተከተሉ:: ከአላህ ሌላ ረዳቶችን አትከተሉ:: ጥቂትን ብቻ ትገሰፃላችሁ::

7:4

وَكَم مِّن قَرۡيَةٍ أَهۡلَكۡنَٰهَا فَجَآءَهَا بَأۡسُنَا بَيَٰتًا أَوۡ هُمۡ قَآئِلُونَ ﴿4﴾

Transliteration: Wakam min qaryatin ahlaknaha fajaaha basuna bayatan aw hum qailoona

Translation: 4. ከከተማ (ሰዎች) መካከል ልናጠፋቸው የፈለግነውንና ወዲያውኑ ብርቱ ቅጣታችን ሌሊት ወይም ቀን እነርሱ በቀትር አርፈው ሳሉ የመጣባቸው ብዙ ህዝቦች ናቸው::

7:5

فَمَا كَانَ دَعۡوَىٰهُمۡ إِذۡ جَآءَهُم بَأۡسُنَآ إِلَّآ أَن قَالُوٓاْ إِنَّا كُنَّا ظَٰلِمِينَ ﴿5﴾

Transliteration: Fama kana daAAwahum ith jaahum basuna illa an qaloo inna kunna thalimeena

Translation: 5. ቅጣታችንም በመጣባቸው ጊዜ ጸሎታቸው «እኛ በደለኞች ነበርን።» ከማለት በስተቀር ሌላ አልነበረም::

7:6

فَلَنَسۡـَٔلَنَّ ٱلَّذِينَ أُرۡسِلَ إِلَيۡهِمۡ وَلَنَسۡـَٔلَنَّ ٱلۡمُرۡسَلِينَ ﴿6﴾

Transliteration: Falanasalanna allatheena orsila ilayhim walanasalanna almursaleena

Translation: 6. ከዚያ ወደ እነርሱ የተላከባቸውን ህዝቦችና መልዕክተኞቹንም እንጠይቃቸዋለን::

7:7

فَلَنَقُصَّنَّ عَلَيۡهِم بِعِلۡمٖۖ وَمَا كُنَّا غَآئِبِينَ ﴿7﴾

Transliteration: Falanaqussanna AAalayhim biAAilmin wama kunna ghaibeena

Translation: 7. ከዚያም በእነርሱ ላይ የነበሩትን ሁሉ ከእውቀት ጋር እንተርክላቸዋለን:: ከእነርሱ የራቅን አልነበርንምና::

7:8

وَٱلۡوَزۡنُ يَوۡمَئِذٍ ٱلۡحَقُّۚ فَمَن ثَقُلَتۡ مَوَٰزِينُهُۥ فَأُوْلَـٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ ﴿8﴾

Transliteration: Waalwaznu yawmaithini alhaqqu faman thaqulat mawazeenuhu faolaika humu almuflihoona

Translation: 8. የዚያን ቀኑ ሚዛን ትክክለኛ ነው:: እናም እነዚያ ሚዛኖቻቸው የከበዱላቸውም እነዚያ እነርሱ የፈለጉትን ያገኙ እነርሱ ብቻ ናቸው::

7:9

وَمَنۡ خَفَّتۡ مَوَٰزِينُهُۥ فَأُوْلَـٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُم بِمَا كَانُواْ بِـَٔايَٰتِنَا يَظۡلِمُونَ ﴿9﴾

Transliteration: Waman khaffat mawazeenuhu faolaika allatheena khasiroo anfusahum bima kanoo biayatina yathlimoona

Translation: 9. እነዚያ ሚዛኖቻቸው የቀለሉባቸውም በአናቅጻችን ይክዱ በነበሩት ምክንያት ነፍሶቻቸውን ያከሰሩት ናቸው።

7:10

وَلَقَدۡ مَكَّنَّـٰكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَجَعَلۡنَا لَكُمۡ فِيهَا مَعَٰيِشَۗ قَلِيلٗا مَّا تَشۡكُرُونَ ﴿10﴾

Transliteration: Walaqad makkannakum fee alardi wajaAAalna lakum feeha maAAayisha qaleelan ma tashkuroona

Translation: 10. (ሰዎች ሆይ! ) በምድር ላይ በእርግጥም አስመቸናችሁ:: በእርሷም ላይ ለእናንተ መኖሪያዎችን አደረግንላችሁ። ጥቂትን ብቻ ታመሰግናላችሁ።

7:11

وَلَقَدۡ خَلَقۡنَٰكُمۡ ثُمَّ صَوَّرۡنَٰكُمۡ ثُمَّ قُلۡنَا لِلۡمَلَـٰٓئِكَةِ ٱسۡجُدُواْ لِأٓدَمَ فَسَجَدُوٓاْ إِلَّآ إِبۡلِيسَ لَمۡ يَكُن مِّنَ ٱلسَّـٰجِدِينَ ﴿11﴾

Transliteration: Walaqad khalaqnakum thumma sawwarnakum thumma qulna lilmalaikati osjudoo liadama fasajadoo illa ibleesa lam yakun mina alssajideena

Translation: 11. በእርግጥም ፈጠርናችሁ:: ከዚያም ቀረጽናችሁ:: ከዚያም ለመላዕክት « ለአደም ስገዱ።» አልን:: ወዲያዉም ሁሉም ሰገዱ:: ኢብሊስ ብቻ ሲቀር:: እሱማ ከሰጋጆቹ አልሆነም::

7:12

قَالَ مَا مَنَعَكَ أَلَّا تَسۡجُدَ إِذۡ أَمَرۡتُكَۖ قَالَ أَنَا۠ خَيۡرٞ مِّنۡهُ خَلَقۡتَنِي مِن نَّارٖ وَخَلَقۡتَهُۥ مِن طِينٖ ﴿12﴾

Transliteration: Qala ma manaAAaka alla tasjuda ith amartuka qala ana khayrun minhu khalaqtanee min narin wakhalaqtahu min teenin

Translation: 12. አላህም «ዲያብሎስ ሆይ! ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ?» አለው:: ዲያብሎስም «እኔ ከእርሱ የበለጥኩ ነኝ:: እኔን ከእሳት ፈጠርከኝ እርሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው።» አለ።

7:13

قَالَ فَٱهۡبِطۡ مِنۡهَا فَمَا يَكُونُ لَكَ أَن تَتَكَبَّرَ فِيهَا فَٱخۡرُجۡ إِنَّكَ مِنَ ٱلصَّـٰغِرِينَ ﴿13﴾

Transliteration: Qala faihbit minha fama yakoonu laka an tatakabbara feeha faokhruj innaka mina alssaghireena

Translation: 13. (አላህም) «ከእርሷ ውረድ:: በእርሷ ውስጥ ልትኮራ አይገባህምና:: ውጣም:: አንተ ከወራዶቹ ነህና።» አለው::

7:14

قَالَ أَنظِرۡنِيٓ إِلَىٰ يَوۡمِ يُبۡعَثُونَ ﴿14﴾

Transliteration: Qala anthirnee ila yawmi yubAAathoona

Translation: 14. (ኢብሊስም): «እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝ።» አለ::

7:15

قَالَ إِنَّكَ مِنَ ٱلۡمُنظَرِينَ ﴿15﴾

Transliteration: Qala innaka mina almunthareena

Translation: 15. አላህ «አንተ ከሚቆዩት ነህ።» አለው።

7:16

قَالَ فَبِمَآ أَغۡوَيۡتَنِي لَأَقۡعُدَنَّ لَهُمۡ صِرَٰطَكَ ٱلۡمُسۡتَقِيمَ ﴿16﴾

Transliteration: Qala fabima aghwaytanee laaqAAudanna lahum sirataka almustaqeema

Translation: 16. (ኢብሊስም) አለ: «ስላጠመምከኝም ለእነርሱ በቀጥተኛው መንገድ ላይ በእርግጥ እቀመጥባቸዋለሁ።

7:17

ثُمَّ لَأٓتِيَنَّهُم مِّنۢ بَيۡنِ أَيۡدِيهِمۡ وَمِنۡ خَلۡفِهِمۡ وَعَنۡ أَيۡمَٰنِهِمۡ وَعَن شَمَآئِلِهِمۡۖ وَلَا تَجِدُ أَكۡثَرَهُمۡ شَٰكِرِينَ ﴿17﴾

Transliteration: Thumma laatiyannahum min bayni aydeehim wamin khalfihim waAAan aymanihim waAAan shamailihim wala tajidu aktharahum shakireena

Translation: 17. «ከዚያም ከበስተፊቶቻቸው፤ ከየኋላቸዉም፤ ከየቀኞቻቸውና ከየግራዎቻቸዉም በእርግጥ እመጣባቸዋለሁ:: አብዛኞቻቸውንም አመስጋኞች ሆነው አታገኛቸዉም።» አለ።

7:18

قَالَ ٱخۡرُجۡ مِنۡهَا مَذۡءُومٗا مَّدۡحُورٗاۖ لَّمَن تَبِعَكَ مِنۡهُمۡ لَأَمۡلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنكُمۡ أَجۡمَعِينَ ﴿18﴾

Transliteration: Qala okhruj minha mathooman madhooran laman tabiAAaka minhum laamlaanna jahannama minkum ajmaAAeena

Translation: 18. «የተጠላህ ብራሪ ስትሆን ከእርሷ ውጣ:: ከእነርሱ መካከልም አንተን ከተከተሉህ እና አንተንም ሁላችሁንም ገሀነምን በእርግጥ በእናንተ እሞላታለሁ።» አለው።

7:19

وَيَـٰٓـَٔادَمُ ٱسۡكُنۡ أَنتَ وَزَوۡجُكَ ٱلۡجَنَّةَ فَكُلَا مِنۡ حَيۡثُ شِئۡتُمَا وَلَا تَقۡرَبَا هَٰذِهِ ٱلشَّجَرَةَ فَتَكُونَا مِنَ ٱلظَّـٰلِمِينَ ﴿19﴾

Transliteration: Waya adamu oskun anta wazawjuka aljannata fakula min haythu shituma wala taqraba hathihi alshshajarata fatakoona mina alththalimeena

Translation: 19. ‹‹አደም ሆይ! አንተና ሚስትህ በገነት ውስጥ ተቀመጡ:: በእርሷም ዉስጥ እንደፈለጋችሁ ተመገቡ:: ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ:: ራሳቸውን ከሚበድሉት ትሆናላችሁና።» አላቸው።

7:20

فَوَسۡوَسَ لَهُمَا ٱلشَّيۡطَٰنُ لِيُبۡدِيَ لَهُمَا مَا وُۥرِيَ عَنۡهُمَا مِن سَوۡءَٰتِهِمَا وَقَالَ مَا نَهَىٰكُمَا رَبُّكُمَا عَنۡ هَٰذِهِ ٱلشَّجَرَةِ إِلَّآ أَن تَكُونَا مَلَكَيۡنِ أَوۡ تَكُونَا مِنَ ٱلۡخَٰلِدِينَ ﴿20﴾

Transliteration: Fawaswasa lahuma alshshaytanu liyubdiya lahuma ma wooriya AAanhuma min sawatihima waqala ma nahakuma rabbukuma AAan hathihi alshshajarati illa an takoona malakayni aw takoona mina alkhalideena

Translation: 20. ሰይጣንም ከሀፍረተ ገላቸው የተሸሸገውን ሊገልጽባቸው በድብቅ ንግግር ጎተጎታቸው። «ጌታችሁ እኮ መልአኮች እንዳትሆኑ ወይም ከዘላለም ኗዋሪዎቹ እንዳትሆኑ እንጂ ከዚህች ዛፍ አልከለከላችሁም።» አላቸው።

7:21

وَقَاسَمَهُمَآ إِنِّي لَكُمَا لَمِنَ ٱلنَّـٰصِحِينَ ﴿21﴾

Transliteration: Waqasamahuma innee lakuma lamina alnnasiheena

Translation: 21. «እኔ ለእናንተ በእርግጥ ከሚመክሯችሁ ነኝ።» ሲልም ማለላቸው።

7:22

فَدَلَّىٰهُمَا بِغُرُورٖۚ فَلَمَّا ذَاقَا ٱلشَّجَرَةَ بَدَتۡ لَهُمَا سَوۡءَٰتُهُمَا وَطَفِقَا يَخۡصِفَانِ عَلَيۡهِمَا مِن وَرَقِ ٱلۡجَنَّةِۖ وَنَادَىٰهُمَا رَبُّهُمَآ أَلَمۡ أَنۡهَكُمَا عَن تِلۡكُمَا ٱلشَّجَرَةِ وَأَقُل لَّكُمَآ إِنَّ ٱلشَّيۡطَٰنَ لَكُمَا عَدُوّٞ مُّبِينٞ ﴿22﴾

Transliteration: Fadallahuma bighuroorin falamma thaqa alshshajarata badat lahuma sawatuhuma watafiqa yakhsifani AAalayhima min waraqi aljannati wanadahuma rabbuhuma alam anhakuma AAan tilkuma alshshajarati waaqul lakuma inna alshshaytana lakuma AAaduwwun mubeenun

Translation: 22. በማታለልም አዋረዳቸው:: ከዛፊቱም በቀመሱ ጊዜ ሀፍረተ ገላቸው የሁለቱም ተገለጠባቸው:: ከገነት ቅጠልም በላያቸው ላይ ይደርቱ (ይለጥፉ) ጀመር:: ጌታቸዉም «ይህችን ዛፍ አልከለከልኳችሁም ነበርን? ሰይጣንም ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነው አላልኳችሁም ነበርን?» ሲል ጠራቸው።

7:23

قَالَا رَبَّنَا ظَلَمۡنَآ أَنفُسَنَا وَإِن لَّمۡ تَغۡفِرۡ لَنَا وَتَرۡحَمۡنَا لَنَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ ﴿23﴾

Transliteration: Qala rabbana thalamna anfusana wain lam taghfir lana watarhamna lanakoonanna mina alkhasireena

Translation: 23. «ጌታችን ሆይ! ነፍሶቻችንን በደልን:: ባትምረንና ባታዝንልን በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንሆናለን።» አሉ።

7:24

قَالَ ٱهۡبِطُواْ بَعۡضُكُمۡ لِبَعۡضٍ عَدُوّٞۖ وَلَكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ مُسۡتَقَرّٞ وَمَتَٰعٌ إِلَىٰ حِينٖ ﴿24﴾

Transliteration: Qala ihbitoo baAAdukum libaAAdin AAaduwwun walakum fee alardi mustaqarrun wamataAAun ila heenin

Translation: 24. (አላህም) «ከፊላችሁ ለከፊሉ ጠላት ሲሆን ከዚህ ዉጡ ወደ ምድር ውረዱ:: ለእናንተም በምድር ላይ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ መርጊያና መጠቀሚያ አላችሁ።» አላቸው።

7:25

قَالَ فِيهَا تَحۡيَوۡنَ وَفِيهَا تَمُوتُونَ وَمِنۡهَا تُخۡرَجُونَ ﴿25﴾

Transliteration: Qala feeha tahyawna wafeeha tamootoona waminha tukhrajoona

Translation: 25. «በእርሷ ላይ ትኖራላችሁ:: በእርሷም ላይ ትሞታላችሁ:: ከእርሷም ውስጥ ትወጣላችሁ።» አላቸው።

7:26

يَٰبَنِيٓ ءَادَمَ قَدۡ أَنزَلۡنَا عَلَيۡكُمۡ لِبَاسٗا يُوَٰرِي سَوۡءَٰتِكُمۡ وَرِيشٗاۖ وَلِبَاسُ ٱلتَّقۡوَىٰ ذَٰلِكَ خَيۡرٞۚ ذَٰلِكَ مِنۡ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ لَعَلَّهُمۡ يَذَّكَّرُونَ ﴿26﴾

Transliteration: Ya banee adama qad anzalna AAalaykum libasan yuwaree sawatikum wareeshan walibasu alttaqwa thalika khayrun thalika min ayati Allahi laAAallahum yaththakkaroona

Translation: 26. የአደም ልጆች ሆይ! ሀፍረተ ገላችሁን የሚሸሽግን ልብስና ጌጥን በእርግጥ በእናንተ ላይ አወረድን:: አላህን የመፍራትም ልብስም እርሱ የተሻለ ነው:: ይህ ከአላህ ተዓምራት ነው:: ይገሰጹ ዘንድ አወረደላቸው::

7:27

يَٰبَنِيٓ ءَادَمَ لَا يَفۡتِنَنَّكُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ كَمَآ أَخۡرَجَ أَبَوَيۡكُم مِّنَ ٱلۡجَنَّةِ يَنزِعُ عَنۡهُمَا لِبَاسَهُمَا لِيُرِيَهُمَا سَوۡءَٰتِهِمَآۚ إِنَّهُۥ يَرَىٰكُمۡ هُوَ وَقَبِيلُهُۥ مِنۡ حَيۡثُ لَا تَرَوۡنَهُمۡۗ إِنَّا جَعَلۡنَا ٱلشَّيَٰطِينَ أَوۡلِيَآءَ لِلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ ﴿27﴾

Transliteration: Ya banee adama la yaftinannakumu alshshaytanu kama akhraja abawaykum mina aljannati yanziAAu AAanhuma libasahuma liyuriyahuma sawatihima innahu yarakum huwa waqabeeluhu min haythu la tarawnahum inna jaAAalna alshshayateena awliyaa lillatheena la yuminoona

Translation: 27. የአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣን አባታችሁንና እናታችሁን ሀፍረተ ገላቸውን ሊያሳያቸው ልብሶቻቸውን ከእነርሱ የገፈፋቸው ሲሆን ከገነት እንዳወጣቸው ሁሉ እናንተንም አይሞክራችሁ:: እነሆ እርሱ ከነሰራዊቱ ከማታዩዋቸው ስፍራ ሁነው ያያቹሀልና: እኛ ሰይጣናትን ለእነዚያ ለማያምኑት ወዳጆች አድርገናል::

7:28

وَإِذَا فَعَلُواْ فَٰحِشَةٗ قَالُواْ وَجَدۡنَا عَلَيۡهَآ ءَابَآءَنَا وَٱللَّهُ أَمَرَنَا بِهَاۗ قُلۡ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَأۡمُرُ بِٱلۡفَحۡشَآءِۖ أَتَقُولُونَ عَلَى ٱللَّهِ مَا لَا تَعۡلَمُونَ ﴿28﴾

Transliteration: Waitha faAAaloo fahishatan qaloo wajadna AAalayha abaana waAllahu amarana biha qul inna Allaha la yamuru bialfahshai ataqooloona AAala Allahi ma la taAAlamoona

Translation: 28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መጥፎንም ሥራ በሠሩ ጊዜ፡- «በእርሷ ላይ አባቶቻችንን አገኘን:: አላህም በእርሷ አዞናል።» ይላሉ። «አላህ በመጥፎ ነገር አያዝም፤ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን?» በላቸው።

7:29

قُلۡ أَمَرَ رَبِّي بِٱلۡقِسۡطِۖ وَأَقِيمُواْ وُجُوهَكُمۡ عِندَ كُلِّ مَسۡجِدٖ وَٱدۡعُوهُ مُخۡلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَۚ كَمَا بَدَأَكُمۡ تَعُودُونَ ﴿29﴾

Transliteration: Qul amara rabbee bialqisti waaqeemoo wujoohakum AAinda kulli masjidin waodAAoohu mukhliseena lahu alddeena kama badaakum taAAoodoona

Translation: 29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ በማስተካከል በፍትህ አዘዘ:: በየመስገጃ ቦታ ዘንድም ፊቶቻችሁን እርሱን ለመገዛት አስተካክሉ:: ሃይማኖትንም ለእርሱ ብቻ ፍጹም አድርጋችሁ አምልኩት:: መጀመሪያ እርሱ እንደፈጠራችሁ በመጨረሻም ወደ እርሱ ትመለሳላችሁና።» በላቸው።

7:30

فَرِيقًا هَدَىٰ وَفَرِيقًا حَقَّ عَلَيۡهِمُ ٱلضَّلَٰلَةُۚ إِنَّهُمُ ٱتَّخَذُواْ ٱلشَّيَٰطِينَ أَوۡلِيَآءَ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَيَحۡسَبُونَ أَنَّهُم مُّهۡتَدُونَ ﴿30﴾

Transliteration: Fareeqan hada wafareeqan haqqa AAalayhimu alddalalatu innahumu ittakhathoo alshshayateena awliyaa min dooni Allahi wayahsaboona annahum muhtadoona

Translation: 30. ከፊሉን ወደ ቅን መንገድ መራ:: ከፊሎቹ ደግሞ በእነርሱ ላይ ጥመት ተረጋግጦባቸዋል:: እነርሱ ሰይጣናትን ከአላህ ሌላ ረዳቶች አድርገው ይዘዋልና:: እነርሱም ቅኑን መንገድ የተመሩ እንደሆኑ ያስባሉ::

7:31

يَٰبَنِيٓ ءَادَمَ خُذُواْ زِينَتَكُمۡ عِندَ كُلِّ مَسۡجِدٖ وَكُلُواْ وَٱشۡرَبُواْ وَلَا تُسۡرِفُوٓاْۚ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلۡمُسۡرِفِينَ ﴿31﴾

Transliteration: Ya banee adama khuthoo zeenatakum AAinda kulli masjidin wakuloo waishraboo wala tusrifoo innahu la yuhibbu almusrifeena

Translation: 31. የአደም ልጆች ሆይ! ሀፍረተ ገላችሁን የሚሸፍኑትን ጌጦቻችሁን በየመስገጃው ሁሉ ዘንድ ያዙ:: ብሉም ጠጡም:: ግን አታባክኑ:: እርሱ (አላህ) አባካኞችን አይወድምና::

7:32

قُلۡ مَنۡ حَرَّمَ زِينَةَ ٱللَّهِ ٱلَّتِيٓ أَخۡرَجَ لِعِبَادِهِۦ وَٱلطَّيِّبَٰتِ مِنَ ٱلرِّزۡقِۚ قُلۡ هِيَ لِلَّذِينَ ءَامَنُواْ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا خَالِصَةٗ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۗ كَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ ٱلۡأٓيَٰتِ لِقَوۡمٖ يَعۡلَمُونَ ﴿32﴾

Transliteration: Qul man harrama zeenata Allahi allatee akhraja liAAibadihi waalttayyibati mina alrrizqi qul hiya lillatheena amanoo fee alhayati alddunya khalisatan yawma alqiyamati kathalika nufassilu alayati liqawmin yaAAlamoona

Translation: 32. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያችን ለባሮች የፈጠራትን የአላህን ጌጥ ከሲሳይ ጥሩዎቹን እርም ያደረገ ማን ነው?» በላቸው። «እርሷ በትንሳኤ ቀን ለነዚያ በትክክል ላመኑት ብቻ ስትሆን በቅርቢቱ ህይወትም ተገቢያቸው ናት።» በላቸው:: ልክ እንደዚሁ ለሚያውቁ ህዝቦች ሁሉ አናቅጽን እናብራራለን::

7:33

قُلۡ إِنَّمَا حَرَّمَ رَبِّيَ ٱلۡفَوَٰحِشَ مَا ظَهَرَ مِنۡهَا وَمَا بَطَنَ وَٱلۡإِثۡمَ وَٱلۡبَغۡيَ بِغَيۡرِ ٱلۡحَقِّ وَأَن تُشۡرِكُواْ بِٱللَّهِ مَا لَمۡ يُنَزِّلۡ بِهِۦ سُلۡطَٰنٗا وَأَن تَقُولُواْ عَلَى ٱللَّهِ مَا لَا تَعۡلَمُونَ ﴿33﴾

Transliteration: Qul innama harrama rabbiya alfawahisha ma thahara minha wama batana waalithma waalbaghya bighayri alhaqqi waan tushrikoo biAllahi ma lam yunazzil bihi sultanan waan taqooloo AAala Allahi ma la taAAlamoona

Translation: 33. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ እርም ያደረገው የተገለጸም ሆነ የተደበቀን መጥፎ ስራን፣ ኃጢአትን፤ ያለ አግባብ መበደልንም፣ በእርሱም ማስረጃ ያላወረደበትን ጣኦት በአላህ ማጋራታችሁንና በአላህም ላይ የማታውቁትን መናገራችሁን ብቻ ነው።» በላቸው።

7:34

وَلِكُلِّ أُمَّةٍ أَجَلٞۖ فَإِذَا جَآءَ أَجَلُهُمۡ لَا يَسۡتَأۡخِرُونَ سَاعَةٗ وَلَا يَسۡتَقۡدِمُونَ ﴿34﴾

Transliteration: Walikulli ommatin ajalun faitha jaa ajaluhum la yastakhiroona saAAatan wala yastaqdimoona

Translation: 34. ለህዝቦች ሁሉ የተወሰነ ጊዜ አላቸው። እናም ጊዜያቸው በደረሰ ወቅት አንዲትንም ሰዓት አይዘገዩም። ከጊዜያቱም አይቀድሙም::

7:35

يَٰبَنِيٓ ءَادَمَ إِمَّا يَأۡتِيَنَّكُمۡ رُسُلٞ مِّنكُمۡ يَقُصُّونَ عَلَيۡكُمۡ ءَايَٰتِي فَمَنِ ٱتَّقَىٰ وَأَصۡلَحَ فَلَا خَوۡفٌ عَلَيۡهِمۡ وَلَا هُمۡ يَحۡزَنُونَ ﴿35﴾

Transliteration: Ya banee adama imma yatiyannakum rusulun minkum yaqussoona AAalaykum ayatee famani ittaqa waaslaha fala khawfun AAalayhim wala hum yahzanoona

Translation: 35. (የአደም ልጆች ሆይ!) ከናንተ መካከል አንቀፆቼን የሚያነቡላችሁ መልዕክተኞች ቢመጡላችሁ ከናንተ ክህደትን የተጠነቀቁና በጎንም ተግባር የሠሩ ሁሉ ምንም ፍርሀት የለባቸዉም:: ምንም አያዝኑምም::

7:36

وَٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَٱسۡتَكۡبَرُواْ عَنۡهَآ أُوْلَـٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ ﴿36﴾

Transliteration: Waallatheena kaththaboo biayatina waistakbaroo AAanha olaika ashabu alnnari hum feeha khalidoona

Translation: 36. እነዚያ በአናቅጻችን ያስተባበሉና ከእርሷ የኮሩ ሁሉ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው:: እነርሱም በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::

7:37

فَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّنِ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَوۡ كَذَّبَ بِـَٔايَٰتِهِۦٓۚ أُوْلَـٰٓئِكَ يَنَالُهُمۡ نَصِيبُهُم مِّنَ ٱلۡكِتَٰبِۖ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَتۡهُمۡ رُسُلُنَا يَتَوَفَّوۡنَهُمۡ قَالُوٓاْ أَيۡنَ مَا كُنتُمۡ تَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِۖ قَالُواْ ضَلُّواْ عَنَّا وَشَهِدُواْ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمۡ أَنَّهُمۡ كَانُواْ كَٰفِرِينَ ﴿37﴾

Transliteration: Faman athlamu mimmani iftara AAala Allahi kathiban aw kaththaba biayatihi olaika yanaluhum naseebuhum mina alkitabi hatta itha jaathum rusuluna yatawaffawnahum qaloo ayna ma kuntum tadAAoona min dooni Allahi qaloo dalloo AAanna washahidoo AAala anfusihim annahum kanoo kafireena

Translation: 37. በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጠፈ ወይም በአናቅጹ ካስተባበለ ይበልጥ በዳይ ማን ነው? እነዚያ ከተጻፈላቸው ከመጽሐፉ ውስጥ ሲሆን ድርሻቸው ያገኛቸዋል:: የሞት መልዕክተኞቻችንም የሚገድሏቸው ሆነው በመጡባቸው ጊዜ «ከአላህ ሌላ ትገዟቸው የነበራችሁት የት አሉ?» ይሏቸዋል:: «ከእኛ ተሰወሩብን» ይላሉ:: እነርሱም ከሓዲያን እንደነበሩ በነፍሶቻቸው ላይ ይመሰክራሉ::

7:38

قَالَ ٱدۡخُلُواْ فِيٓ أُمَمٖ قَدۡ خَلَتۡ مِن قَبۡلِكُم مِّنَ ٱلۡجِنِّ وَٱلۡإِنسِ فِي ٱلنَّارِۖ كُلَّمَا دَخَلَتۡ أُمَّةٞ لَّعَنَتۡ أُخۡتَهَاۖ حَتَّىٰٓ إِذَا ٱدَّارَكُواْ فِيهَا جَمِيعٗا قَالَتۡ أُخۡرَىٰهُمۡ لِأُولَىٰهُمۡ رَبَّنَا هَـٰٓؤُلَآءِ أَضَلُّونَا فَـَٔاتِهِمۡ عَذَابٗا ضِعۡفٗا مِّنَ ٱلنَّارِۖ قَالَ لِكُلّٖ ضِعۡفٞ وَلَٰكِن لَّا تَعۡلَمُونَ ﴿38﴾

Transliteration: Qala odkhuloo fee omamin qad khalat min qablikum mina aljinni waalinsi fee alnnari kullama dakhalat ommatun laAAanat okhtaha hatta itha iddarakoo feeha jameeAAan qalat okhrahum lioolahum rabbana haolai adalloona faatihim AAathaban diAAfan mina alnnari qala likullin diAAfun walakin la taAAlamoona

Translation: 38. «ከጋኔንና ከሰዉም ከናንተ በፊት በእርግጥ ካለፉት ህዝቦች ጋር ሆናችሁ እሳት ውስጥ ግቡ።» ይላቸዋል:: አንዲቱ ቡድን ህዝብ ወደ እሳት በገባች ቁጥር ያሳሳተቻትን ብጤዋን ቡድን ትረግማለች:: መላዉም በውስጧ ተሰብስበው በተገናኙ ጊዜ የኋለኛይቱ (ተከታዮች) ቡድን ለመጀመሪያይቱ (ለአስከታዮች) ቡድን፡- «ጌታችን ሆይ! እነዚህ አሳሳቱን ከእሳትም ስቃይ እጥፍን ስጣቸው።» ትላለች:: አላህም፡- «ለሁሉም እጥፍ አለው ግን አታውቁም።» ይላቸዋል።

7:39

وَقَالَتۡ أُولَىٰهُمۡ لِأُخۡرَىٰهُمۡ فَمَا كَانَ لَكُمۡ عَلَيۡنَا مِن فَضۡلٖ فَذُوقُواْ ٱلۡعَذَابَ بِمَا كُنتُمۡ تَكۡسِبُونَ ﴿39﴾

Transliteration: Waqalat oolahum liokhrahum fama kana lakum AAalayna min fadlin fathooqoo alAAathaba bima kuntum taksiboona

Translation: 39. መጀመሪያይቱ ቡድንም ለኋለኛይቱ ቡድን «ለእናንተ በእኛ ላይ ምንም ብልጫ አልነበራችሁም ትላለች:: ትሠሩትም በነበራችሁት ቅጣቱን ቅመሱ።» ይሏቸዋል።

7:40

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَٱسۡتَكۡبَرُواْ عَنۡهَا لَا تُفَتَّحُ لَهُمۡ أَبۡوَٰبُ ٱلسَّمَآءِ وَلَا يَدۡخُلُونَ ٱلۡجَنَّةَ حَتَّىٰ يَلِجَ ٱلۡجَمَلُ فِي سَمِّ ٱلۡخِيَاطِۚ وَكَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُجۡرِمِينَ ﴿40﴾

Transliteration: Inna allatheena kaththaboo biayatina waistakbaroo AAanha la tufattahu lahum abwabu alssamai wala yadkhuloona aljannata hatta yalija aljamalu fee sammi alkhiyati wakathalika najzee almujrimeena

Translation: 40. እነዚያ አናቅጻችንን ያስተባበሉና ከእርሷም የኮሩ ሁሉ ለእነርሱ የሰማይ ደጃፎች አይከፈቱላቸዉም:: ግመል በመርፌ ቀዳዳ እስከሚገባ ድረስም ወደ ገነት አይገቡም:: ልክ እንደዚሁ አመጸኞችን እንቀጣለን::

7:41

لَهُم مِّن جَهَنَّمَ مِهَادٞ وَمِن فَوۡقِهِمۡ غَوَاشٖۚ وَكَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلظَّـٰلِمِينَ ﴿41﴾

Transliteration: Lahum min jahannama mihadun wamin fawqihim ghawashin wakathalika najzee alththalimeena

Translation: 41. ለእነርሱም በሥራቸው ምክንያት ከገሀነም እሳት ምንጣፍ ከበላያቸዉም የእሳት መሸፈኛዎች አሉባቸው:: ልክ እንደዚሁ በደለኞችን እንቀጣለን::

7:42

وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّـٰلِحَٰتِ لَا نُكَلِّفُ نَفۡسًا إِلَّا وُسۡعَهَآ أُوْلَـٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡجَنَّةِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ ﴿42﴾

Transliteration: Waallatheena amanoo waAAamiloo alssalihati la nukallifu nafsan illa wusAAaha olaika ashabu aljannati hum feeha khalidoona

Translation: 42. እነዚያ በአላህ ያመኑና መልካሞችን የሰሩ ማንኛውንም ነፍስ የችሎታዋን እንጂ አናስገድድም:: እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው:: እነርሱም በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::

7:43

وَنَزَعۡنَا مَا فِي صُدُورِهِم مِّنۡ غِلّٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهِمُ ٱلۡأَنۡهَٰرُۖ وَقَالُواْ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِي هَدَىٰنَا لِهَٰذَا وَمَا كُنَّا لِنَهۡتَدِيَ لَوۡلَآ أَنۡ هَدَىٰنَا ٱللَّهُۖ لَقَدۡ جَآءَتۡ رُسُلُ رَبِّنَا بِٱلۡحَقِّۖ وَنُودُوٓاْ أَن تِلۡكُمُ ٱلۡجَنَّةُ أُورِثۡتُمُوهَا بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ ﴿43﴾

Transliteration: WanazaAAna ma fee sudoorihim min ghillin tajree min tahtihimu alanharu waqaloo alhamdu lillahi allathee hadana lihatha wama kunna linahtadiya lawla an hadana Allahu laqad jaat rusulu rabbina bialhaqqi wanoodoo an tilkumu aljannatu oorithtumooha bima kuntum taAAmaloona

Translation: 43. በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ጥላቻም እናስወግዳለን:: ወንዞች በሥሮቻቸው ይፈሳሉ:: «ለዚያም ወደዚህ ላደረሰን ሥራ ለመራን ለአላህ ብቻ ምስጋና ይገባው:: አላህ ባልመራን ኖሮ ወደዚህ አንመራም ነበር:: የጌታችን መልዕክተኞች በእውነት ላይ ሲሆኑ መጥተውልናል።» ይላሉ:: «ይህ ገነት ትሠሩት በነበራችሁት እንድትወርሱት የተደረጋችሁት ነው።» በማለት ይጠራሉ::

7:44

وَنَادَىٰٓ أَصۡحَٰبُ ٱلۡجَنَّةِ أَصۡحَٰبَ ٱلنَّارِ أَن قَدۡ وَجَدۡنَا مَا وَعَدَنَا رَبُّنَا حَقّٗا فَهَلۡ وَجَدتُّم مَّا وَعَدَ رَبُّكُمۡ حَقّٗاۖ قَالُواْ نَعَمۡۚ فَأَذَّنَ مُؤَذِّنُۢ بَيۡنَهُمۡ أَن لَّعۡنَةُ ٱللَّهِ عَلَى ٱلظَّـٰلِمِينَ ﴿44﴾

Transliteration: Wanada ashabu aljannati ashaba alnnari an qad wajadna ma waAAadana rabbuna haqqan fahal wajadtum ma waAAada rabbukum haqqan qaloo naAAam faaththana muaththinun baynahum an laAAnatu Allahi AAala alththalimeena

Translation: 44. የገነት ሰዎች የእሳት ሰዎችን «ጌታችን ቃል የገባልንን እውነት ሆኖ አገኘን እናንተስ ጌታችሁ የዛተባችሁን እውነት ሆኖ አገኛችሁትን?» ሲሉ ይጣራሉ:: የእሳት ሰዎችም «አዎን አገኘን» ይላሉ:: በመካከላቸዉም «የአላህ እርግማን በበደለኞች ላይ ይሁን» ሲል አዋጅ ነጋሪ ያውጃል::

7:45

ٱلَّذِينَ يَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ وَيَبۡغُونَهَا عِوَجٗا وَهُم بِٱلۡأٓخِرَةِ كَٰفِرُونَ ﴿45﴾

Transliteration: Allatheena yasuddoona AAan sabeeli Allahi wayabghoonaha AAiwajan wahum bialakhirati kafiroona

Translation: 45. በደለኞች ማለት እነዚያ ከአላህ መንገድ ሌሎችን ክፍሎች የሚከለክሉና የአላህ መንገድ እንድትጣመም የሚፈልጉ በመጨረሻዋ ዓለም ከሓዲያን የሆኑ ሰዎች ብቻ ናቸው::

7:46

وَبَيۡنَهُمَا حِجَابٞۚ وَعَلَى ٱلۡأَعۡرَافِ رِجَالٞ يَعۡرِفُونَ كُلَّۢا بِسِيمَىٰهُمۡۚ وَنَادَوۡاْ أَصۡحَٰبَ ٱلۡجَنَّةِ أَن سَلَٰمٌ عَلَيۡكُمۡۚ لَمۡ يَدۡخُلُوهَا وَهُمۡ يَطۡمَعُونَ ﴿46﴾

Transliteration: Wabaynahuma hijabun waAAala alaAArafi rijalun yaAArifoona kullan biseemahum wanadaw ashaba aljannati an salamun AAalaykum lam yadkhulooha wahum yatmaAAoona

Translation: 46. በገነት ሰዎችና በገሀነም ሰዎች መካከል አዕራፍ የሚባል ከባድ መጋረጃ አለ:: በአዕራፍ ላይ ሁሉንም በምልክታቸው የሚያውቁ ሰዎች አሉ:: የገነትን ሰዎችን «ሰላም ለእናንተ ይሁን» በማለት ይጣራሉ:: የአዕራፍ ሰዎች ገነት መግባትን የሚከጅሉ ሲሆኑ ገና እንዲገቡ አልተደረጉም::

7:47

وَإِذَا صُرِفَتۡ أَبۡصَٰرُهُمۡ تِلۡقَآءَ أَصۡحَٰبِ ٱلنَّارِ قَالُواْ رَبَّنَا لَا تَجۡعَلۡنَا مَعَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلظَّـٰلِمِينَ ﴿47﴾

Transliteration: Waitha surifat absaruhum tilqaa ashabi alnnari qaloo rabbana la tajAAalna maAAa alqawmi alththalimeena

Translation: 47. ዓይኖቻቸው ወደ እሳት ሰዎች አቅጣጫ በተዞሩ ጊዜም፡- «ጌታችን ሆይ! እባክህ ከበደለኞች ጋር አታድርገን።» ይላሉ::

7:48

وَنَادَىٰٓ أَصۡحَٰبُ ٱلۡأَعۡرَافِ رِجَالٗا يَعۡرِفُونَهُم بِسِيمَىٰهُمۡ قَالُواْ مَآ أَغۡنَىٰ عَنكُمۡ جَمۡعُكُمۡ وَمَا كُنتُمۡ تَسۡتَكۡبِرُونَ ﴿48﴾

Transliteration: Wanada ashabu alaAArafi rijalan yaAArifoonahum biseemahum qaloo ma aghna AAankum jamAAukum wama kuntum tastakbiroona

Translation: 48. የአዕራፍ ሰዎች በምልክታቸው የሚያውቋቸውን ታላላቅ ሰዎች ይጠራሉ:: «ክምችታችሁና (ብዛታችሁና) ኩራታችሁ ምን ጠቀማችሁ?» ይሏቸዋል::

7:49

أَهَـٰٓؤُلَآءِ ٱلَّذِينَ أَقۡسَمۡتُمۡ لَا يَنَالُهُمُ ٱللَّهُ بِرَحۡمَةٍۚ ٱدۡخُلُواْ ٱلۡجَنَّةَ لَا خَوۡفٌ عَلَيۡكُمۡ وَلَآ أَنتُمۡ تَحۡزَنُونَ ﴿49﴾

Transliteration: Ahaolai allatheena aqsamtum la yanaluhumu Allahu birahmatin odkhuloo aljannata la khawfun AAalaykum wala antum tahzanoona

Translation: 49. «እነዚያ የአላህ ችሮታው አይደርሳቸዉም ብላችሁ የማላችሁት ወገኖች ናቸውን? ገነትን ግቡ:: (አሁን ግን) ፍርሃት የለባችሁም:: እናንተም አታዝኑም።» (ተባሉ ይሏቸዋል::)

7:50

وَنَادَىٰٓ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِ أَصۡحَٰبَ ٱلۡجَنَّةِ أَنۡ أَفِيضُواْ عَلَيۡنَا مِنَ ٱلۡمَآءِ أَوۡ مِمَّا رَزَقَكُمُ ٱللَّهُۚ قَالُوٓاْ إِنَّ ٱللَّهَ حَرَّمَهُمَا عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ ﴿50﴾

Transliteration: Wanada ashabu alnari ashaba aljannati an afeedoo AAalayna mina almai aw mimma razaqakumu Allahu qaloo inna Allaha harramahuma AAala alkafireena

Translation: 50. የእሳት ሰዎች የገነት ሰዎችን «በእኛ ላይ ውሃ ወይም አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ እባካችሁ ጣሉልን (አፍስሱልን)።» ብለው ይጠሯቸዋል:: የገነት ሰዎችም «እነዚህ ሲሳዮች እኮ አላህ በከሓዲያን ላይ እርም አድርጓቸዋል።» ይሏቸዋል።

7:51

ٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ دِينَهُمۡ لَهۡوٗا وَلَعِبٗا وَغَرَّتۡهُمُ ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَاۚ فَٱلۡيَوۡمَ نَنسَىٰهُمۡ كَمَا نَسُواْ لِقَآءَ يَوۡمِهِمۡ هَٰذَا وَمَا كَانُواْ بِـَٔايَٰتِنَا يَجۡحَدُونَ ﴿51﴾

Transliteration: Allatheena ittakhathoo deenahum lahwan walaAAiban wagharrathumu alhayatu alddunya faalyawma nansahum kama nasoo liqaa yawmihim hatha wama kanoo biayatina yajhadoona

Translation: 51. ለእነዚያ ሃይማኖታቸውን መሳለቂያና መጫወቻ አድርገው የያዙና የቅርቢቱ ህይወት ያታለለቻቸው የዚህን ቀን መገናኘታቸውን እንደ ረሱና በተአምራታችን ይክዱ እንደ ነበሩ ሁሉ ዛሬ እኛም እንረሳቸዋለን (እንተዋቸዋለን)::

7:52

وَلَقَدۡ جِئۡنَٰهُم بِكِتَٰبٖ فَصَّلۡنَٰهُ عَلَىٰ عِلۡمٍ هُدٗى وَرَحۡمَةٗ لِّقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ ﴿52﴾

Transliteration: Walaqad jinahum bikitabin fassalnahu AAala AAilmin hudan warahmatan liqawmin yuminoona

Translation: 52. ከእውቀት ጋር የዘረዘርነው የሆነን መጽሐፍ ለሚያምኑ ህዝቦች መመሪያና እዝነት ሲሆን አመጣንላቸው።

7:53

هَلۡ يَنظُرُونَ إِلَّا تَأۡوِيلَهُۥۚ يَوۡمَ يَأۡتِي تَأۡوِيلُهُۥ يَقُولُ ٱلَّذِينَ نَسُوهُ مِن قَبۡلُ قَدۡ جَآءَتۡ رُسُلُ رَبِّنَا بِٱلۡحَقِّ فَهَل لَّنَا مِن شُفَعَآءَ فَيَشۡفَعُواْ لَنَآ أَوۡ نُرَدُّ فَنَعۡمَلَ غَيۡرَ ٱلَّذِي كُنَّا نَعۡمَلُۚ قَدۡ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ وَضَلَّ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ ﴿53﴾

Transliteration: Hal yanthuroona illa taweelahu yawma yatee taweeluhu yaqoolu allatheena nasoohu min qablu qad jaat rusulu rabbina bialhaqqi fahal lana min shufaAAaa fayashfaAAoo lana aw nuraddu fanaAAmala ghayra allathee kunna naAAmalu qad khasiroo anfusahum wadalla AAanhum ma kanoo yaftaroona

Translation: 53. የዛቻውን ፍጻሜዉን እንጂ ሌላ ይጠባበቃሉን? (አይጠባበቁም):: ፍጻሜው በሚመጣበት ቀን ግን እነዚያ ከመምጣቱ በፊት የረሱት ሰዎች «የጌታችን መልዕክተኞች በእውነት መጥተዋል። ለእኛስ ያማልዱን ዘንድ አማላጆች አሉን? ወይስ ከዚያ እንሠራው ከነበርነው የተለየ ስራ እንድንሰራ ዘንድ ዕድሉ ይሰጠናልን?» ይላሉ:: በእርግጥም ራሳቸውን ይከስራሉ:: ይቀጥፉት የነበረው ሁሉ ከንቱ ሆኖ ያገኙታል::

7:54

إِنَّ رَبَّكُمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٖ ثُمَّ ٱسۡتَوَىٰ عَلَى ٱلۡعَرۡشِۖ يُغۡشِي ٱلَّيۡلَ ٱلنَّهَارَ يَطۡلُبُهُۥ حَثِيثٗا وَٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَ وَٱلنُّجُومَ مُسَخَّرَٰتِۭ بِأَمۡرِهِۦٓۗ أَلَا لَهُ ٱلۡخَلۡقُ وَٱلۡأَمۡرُۗ تَبَارَكَ ٱللَّهُ رَبُّ ٱلۡعَٰلَمِينَ ﴿54﴾

Transliteration: Inna rabbakumu Allahu allathee khalaqa alssamawati waalarda fee sittati ayyamin thumma istawa AAala alAAarshi yughshee allayla alnnahara yatlubuhu hatheethan waalshshamsa waalqamara waalnnujooma musakhkharatin biamrihi ala lahu alkhalqu waalamru tabaraka Allahu rabbu alAAalameena

Translation: 54. (ሰዎች ሆይ) ጌታችሁ አላህ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረና ከዚያም በዐርሹ ላይ ከፍ ያለ ነው። ቀኑንም በሌሊቱ ይሸፍነዋል:: ሁለቱም እርስ በእርስ በፍጥነት ይፈላለጋሉ:: ጸሐይ ጨረቃና ከዋክብት በትዕዛዙ የተገሩ ናቸው። አስተውሉ! መፍጠርም ማዘዝም የእርሱ (የአላህ) ነው:: የዓለማት ጌታ የሆነው አላህ ክብሩ ላቀ::

7:55

ٱدۡعُواْ رَبَّكُمۡ تَضَرُّعٗا وَخُفۡيَةًۚ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلۡمُعۡتَدِينَ ﴿55﴾

Transliteration: OdAAoo rabbakum tadarruAAan wakhufyatan innahu la yuhibbu almuAAtadeena

Translation: 55. ጌታችሁን ተናንሳችሁና ተዋርዳችሁ በድብቅ ለምኑት:: እርሱ ወሰን አላፊዎችን አይወድምና::

7:56

وَلَا تُفۡسِدُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ بَعۡدَ إِصۡلَٰحِهَا وَٱدۡعُوهُ خَوۡفٗا وَطَمَعًاۚ إِنَّ رَحۡمَتَ ٱللَّهِ قَرِيبٞ مِّنَ ٱلۡمُحۡسِنِينَ ﴿56﴾

Transliteration: Wala tufsidoo fee alardi baAAda islahiha waodAAoohu khawfan watamaAAan inna rahmata Allahi qareebun mina almuhsineena

Translation: 56. ምድር ከተበጀች በኋላ አታበላሿት:: አላህን ፈርታችሁና ከጅላችሁ ተገዙት:: የአላህ እዝነት ለበጎ አድራጊዎች ሁሉ ቅርብ ነውና::

7:57

وَهُوَ ٱلَّذِي يُرۡسِلُ ٱلرِّيَٰحَ بُشۡرَۢا بَيۡنَ يَدَيۡ رَحۡمَتِهِۦۖ حَتَّىٰٓ إِذَآ أَقَلَّتۡ سَحَابٗا ثِقَالٗا سُقۡنَٰهُ لِبَلَدٖ مَّيِّتٖ فَأَنزَلۡنَا بِهِ ٱلۡمَآءَ فَأَخۡرَجۡنَا بِهِۦ مِن كُلِّ ٱلثَّمَرَٰتِۚ كَذَٰلِكَ نُخۡرِجُ ٱلۡمَوۡتَىٰ لَعَلَّكُمۡ تَذَكَّرُونَ ﴿57﴾

Transliteration: Wahuwa allathee yursilu alrriyaha bushran bayna yaday rahmatihi hatta itha aqallat sahaban thiqalan suqnahu libaladin mayyitin faanzalna bihi almaa faakhrajna bihi min kulli alththamarati kathalika nukhriju almawta laAAallakum tathakkaroona

Translation: 57. አላህ ያ ንፋሶችን ከዝናብ በፊት አብሳሪዎች አድርጎ የሚልክ ነው:: ከባዶችንም ደመናዎች በተሸከሙ ጊዜ ሙት ወደ ሆነ አገር እንነዳዋለን:: በእነርሱም ውሃን እናወርዳለን:: እናም ከፍሬዎች ሁሉ በእነርሱ እናወጣለን:: ልክ እንደዚሁ ሙታንን ከመቃብር እናስወጣለን:: ይህን የምንለው ትገነዘቡ ዘንድ ነው::

7:58

وَٱلۡبَلَدُ ٱلطَّيِّبُ يَخۡرُجُ نَبَاتُهُۥ بِإِذۡنِ رَبِّهِۦۖ وَٱلَّذِي خَبُثَ لَا يَخۡرُجُ إِلَّا نَكِدٗاۚ كَذَٰلِكَ نُصَرِّفُ ٱلۡأٓيَٰتِ لِقَوۡمٖ يَشۡكُرُونَ ﴿58﴾

Transliteration: Waalbaladu alttayyibu yakhruju nabatuhu biithni rabbihi waallathee khabutha la yakhruju illa nakidan kathalika nusarrifu alayati liqawmin yashkuroona

Translation: 58. መልካሙ አገር በጌታው ፈቃድ በቃዩ ያማረ ሆኖ ይወጣል። ያ መጥፎ የሆነው አገር ደግሞ በቃዩ ደካማ ሆኖ እንጂ አይወጣም:: ልክ እንደዚሁ ለሚያመሰግኑ ህዝቦች ተዓምራትን እናብራራለን።

7:59

لَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوۡمِهِۦ فَقَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥٓ إِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُمۡ عَذَابَ يَوۡمٍ عَظِيمٖ ﴿59﴾

Transliteration: Laqad arsalna noohan ila qawmihi faqala ya qawmi oAAbudoo Allaha ma lakum min ilahin ghayruhu innee akhafu AAalaykum AAathaba yawmin AAatheemin

Translation: 59. ኑሕን ወደ ወገኖቹ ላክነው፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ለእናንተ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም:: እኔ በእናንተ ላይ የከባድ ቀንን ቅጣት እፈራላችኋለሁ።» አላቸው።

7:60

قَالَ ٱلۡمَلَأُ مِن قَوۡمِهِۦٓ إِنَّا لَنَرَىٰكَ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ ﴿60﴾

Transliteration: Qala almalao min qawmihi inna lanaraka fee dalalin mubeenin

Translation: 60. ከህዝቦቹ መካከል መሪዎቹ «እኛ በግልጽ ስህተት ውስጥ ሆነህ እናይሀለን።» አሉት።

7:61

قَالَ يَٰقَوۡمِ لَيۡسَ بِي ضَلَٰلَةٞ وَلَٰكِنِّي رَسُولٞ مِّن رَّبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ ﴿61﴾

Transliteration: Qala ya qawmi laysa bee dalalatun walakinnee rasoolun min rabbi alAAalameena

Translation: 61. ኑሕም አለ: «ወገኖቼ ሆይ! ምንም መሳሳት የለብኝም። ግን እኔ ከዓለማት ጌታ መልዕክተኛ ነኝ።

7:62

أُبَلِّغُكُمۡ رِسَٰلَٰتِ رَبِّي وَأَنصَحُ لَكُمۡ وَأَعۡلَمُ مِنَ ٱللَّهِ مَا لَا تَعۡلَمُونَ ﴿62﴾

Transliteration: Oballighukum risalati rabbee waansahu lakum waaAAlamu mina Allahi ma la taAAlamoona

Translation: 62. «የጌታዬን መልዕክቶች አደርስላችኋለሁ:: ለናንተም እመክራችኋለሁ:: ከአላህ በኩልም የማታውቁትን አውቃለሁ::

7:63

أَوَعَجِبۡتُمۡ أَن جَآءَكُمۡ ذِكۡرٞ مِّن رَّبِّكُمۡ عَلَىٰ رَجُلٖ مِّنكُمۡ لِيُنذِرَكُمۡ وَلِتَتَّقُواْ وَلَعَلَّكُمۡ تُرۡحَمُونَ ﴿63﴾

Transliteration: AwaAAajibtum an jaakum thikrun min rabbikum AAala rajulin minkum liyunthirakum walitattaqoo walaAAallakum turhamoona

Translation: 63. «አላህን ልትፈሩና ይታዘንላችሁም ዘንድ ከናንተው ጎሳ መካከል በሆነ ሰው ላይ እንዲያስጠነቅቃችሁ ከጌታችሁ ግሳጼ ስለመጣላችሁ ትደነቃላችሁን?» አላቸው።

7:64

فَكَذَّبُوهُ فَأَنجَيۡنَٰهُ وَٱلَّذِينَ مَعَهُۥ فِي ٱلۡفُلۡكِ وَأَغۡرَقۡنَا ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَآۚ إِنَّهُمۡ كَانُواْ قَوۡمًا عَمِينَ ﴿64﴾

Transliteration: Fakaththaboohu faanjaynahu waallatheena maAAahu fee alfulki waaghraqna allatheena kaththaboo biayatina innahum kanoo qawman AAameena

Translation: 64. ወዲያዉም አስተባበሉት:: እርሱንና እነዚያን ከእርሱ ጋር ያሉትንም በታንኳዋ ውስጥ አዳንናቸው:: እነዚያን በአናቅጻችን ያስተባበሉትን ግን በባህር አሰመጥናቸው:: እነርሱ ልበ እውራን ህዝቦች ነበሩና::

7:65

وَإِلَىٰ عَادٍ أَخَاهُمۡ هُودٗاۚ قَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥٓۚ أَفَلَا تَتَّقُونَ ﴿65﴾

Transliteration: Waila AAadin akhahum hoodan qala ya qawmi oAAbudoo Allaha ma lakum min ilahin ghayruhu afala tattaqoona

Translation: 65. ወደ ዓድ ህዝቦችም ወንድማቸውን ሁድን ላክን። «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም:: የአላህን ቅጣት አትፈሩምን?» አላቸው።

7:66

قَالَ ٱلۡمَلَأُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِن قَوۡمِهِۦٓ إِنَّا لَنَرَىٰكَ فِي سَفَاهَةٖ وَإِنَّا لَنَظُنُّكَ مِنَ ٱلۡكَٰذِبِينَ ﴿66﴾

Transliteration: Qala almalao allatheena kafaroo min qawmihi inna lanaraka fee safahatin wainna lanathunnuka mina alkathibeena

Translation: 66. ከህዝቦቹ መካከል መሪዎቹም «እኛ በሞኝነት ላይ ሆነህ እናይሀለን:: እኛ ከውሸተኞቹ ነህ ብለንም እንጠረጥርሀለን።» አሉት።

7:67

قَالَ يَٰقَوۡمِ لَيۡسَ بِي سَفَاهَةٞ وَلَٰكِنِّي رَسُولٞ مِّن رَّبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ ﴿67﴾

Transliteration: Qala ya qawmi laysa bee safahatun walakinnee rasoolun min rabbi alAAalameena

Translation: 67. እርሱም አላቸው፡- «ወገኖቼ ሆይ! እኔ ሞኝነት የለብኝም:: ግን እኔ ከአለማት ጌታ የተላኩ ነኝ።

7:68

أُبَلِّغُكُمۡ رِسَٰلَٰتِ رَبِّي وَأَنَا۠ لَكُمۡ نَاصِحٌ أَمِينٌ ﴿68﴾

Transliteration: Oballighukum risalati rabbee waana lakum nasihun ameenun

Translation: 68. «የጌታዬን መልዕክቶች አደርስላችኋለሁ። እኔም ለእናንተ ታማኝና መካሪ ነኝና።

7:69

أَوَعَجِبۡتُمۡ أَن جَآءَكُمۡ ذِكۡرٞ مِّن رَّبِّكُمۡ عَلَىٰ رَجُلٖ مِّنكُمۡ لِيُنذِرَكُمۡۚ وَٱذۡكُرُوٓاْ إِذۡ جَعَلَكُمۡ خُلَفَآءَ مِنۢ بَعۡدِ قَوۡمِ نُوحٖ وَزَادَكُمۡ فِي ٱلۡخَلۡقِ بَصۜۡطَةٗۖ فَٱذۡكُرُوٓاْ ءَالَآءَ ٱللَّهِ لَعَلَّكُمۡ تُفۡلِحُونَ ﴿69﴾

Transliteration: AwaAAajibtum an jaakum thikrun min rabbikum AAala rajulin minkum liyunthirakum waothkuroo ith jaAAalakum khulafaa min baAAdi qawmi noohin wazadakum fee alkhalqi bastatan faothkuroo alaa Allahi laAAallakum tuflihoona

Translation: 69. ያስጠነቅቃችሁ ዘንድ ከናንተው መካከል በሆነ ሰው ከጌታችሁ የሆነ ግሳጼ ስለመጣባችሁ ትደነቃላችሁን? ከኑህ ህዝቦች በኋላ ምትኮች ባደረጋችሁና በፍጥረትም ግዙፍነትን በጨመረላችሁ ጊዜ የሆነውን አስታውሱ:: የሻችሁትን ታገኙ ዘንድ የአላህን ጸጋዎች አስታውሱ::

7:70

قَالُوٓاْ أَجِئۡتَنَا لِنَعۡبُدَ ٱللَّهَ وَحۡدَهُۥ وَنَذَرَ مَا كَانَ يَعۡبُدُ ءَابَآؤُنَا فَأۡتِنَا بِمَا تَعِدُنَآ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّـٰدِقِينَ ﴿70﴾

Transliteration: Qaloo ajitana linaAAbuda Allaha wahdahu wanathara ma kana yaAAbudu abaona fatina bima taAAiduna in kunta mina alssadiqeena

Translation: 70. «አላህን አንድ አድርገን ብቻውን እንድንገዛውና አባቶቻችን ይገዟቸው የነበሩትን አማልክት እንድንተው መጣህብን? እውነተኛ ከሆንክ የምታስፈራራብንን ቅጣት እስቲ አምጣብን።» አሉ።

7:71

قَالَ قَدۡ وَقَعَ عَلَيۡكُم مِّن رَّبِّكُمۡ رِجۡسٞ وَغَضَبٌۖ أَتُجَٰدِلُونَنِي فِيٓ أَسۡمَآءٖ سَمَّيۡتُمُوهَآ أَنتُمۡ وَءَابَآؤُكُم مَّا نَزَّلَ ٱللَّهُ بِهَا مِن سُلۡطَٰنٖۚ فَٱنتَظِرُوٓاْ إِنِّي مَعَكُم مِّنَ ٱلۡمُنتَظِرِينَ ﴿71﴾

Transliteration: Qala qad waqaAAa AAalaykum min rabbikum rijsun waghadabun atujadiloonanee fee asmain sammaytumooha antum waabaokum ma nazzala Allahu biha min sultanin faintathiroo innee maAAakum mina almuntathireena

Translation: 71. «ከጌታችሁ የሆነ ቅጣትና ቁጣ በእናንተ ላይ በእውነት ተረጋገጠ:: እናንተና አባቶቻችሁ አማልክት ብላችሁ በጠራችኋቸው ስሞች አላህ በእነርሱ ምንም ማስረጃ ላላወረደባቸው ትከራከሩኛላችሁን? ተጠባበቁ እኔም ከናንተ ጋር ከተጠባባቂዎቹ ነኝና።» አለ::

7:72

فَأَنجَيۡنَٰهُ وَٱلَّذِينَ مَعَهُۥ بِرَحۡمَةٖ مِّنَّا وَقَطَعۡنَا دَابِرَ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَاۖ وَمَا كَانُواْ مُؤۡمِنِينَ ﴿72﴾

Transliteration: Faanjaynahu waallatheena maAAahu birahmatin minna waqataAAna dabira allatheena kaththaboo biayatina wama kanoo mumineena

Translation: 72. እርሱንና እነዚያን አብረውት የነበሩትን በችሮታችን ከቅጣት አዳናቸው::የእነዚያንም በተአምራታችን ያስተባበሉትንና አማኞች ያልነበሩትን መሠረት ቆረጥን፡፡

7:73

وَإِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمۡ صَٰلِحٗاۚ قَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥۖ قَدۡ جَآءَتۡكُم بَيِّنَةٞ مِّن رَّبِّكُمۡۖ هَٰذِهِۦ نَاقَةُ ٱللَّهِ لَكُمۡ ءَايَةٗۖ فَذَرُوهَا تَأۡكُلۡ فِيٓ أَرۡضِ ٱللَّهِۖ وَلَا تَمَسُّوهَا بِسُوٓءٖ فَيَأۡخُذَكُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ ﴿73﴾

Transliteration: Waila thamooda akhahum salihan qala ya qawmi oAAbudoo Allaha ma lakum min ilahin ghayruhu qad jaatkum bayyinatun min rabbikum hathihi naqatu Allahi lakum ayatan fatharooha takul fee ardi Allahi wala tamassooha bisooin fayakhuthakum AAathabun aleemun

Translation: 73. ወደ ሰሙድ ህዝቦችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን:: «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ምንም አምላክ የላችሁም:: እውነተኛ ለመሆኔ ከጌታችሁ የሆነች ምልክት በእርግጥ መጥታላችኋለች:: ይህች ለእናንተ ተዓምር ስትሆን የአላህ ግመል ናትና ተዋት:: በአላህ ምድር ውስጥ እንደፈለገች ትብላ፤ ትጠጣም:: በክፉ አትንኳትም:: አሳማሚ ቅጣት ይይዛችኋልና።» አለ።

7:74

وَٱذۡكُرُوٓاْ إِذۡ جَعَلَكُمۡ خُلَفَآءَ مِنۢ بَعۡدِ عَادٖ وَبَوَّأَكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ تَتَّخِذُونَ مِن سُهُولِهَا قُصُورٗا وَتَنۡحِتُونَ ٱلۡجِبَالَ بُيُوتٗاۖ فَٱذۡكُرُوٓاْ ءَالَآءَ ٱللَّهِ وَلَا تَعۡثَوۡاْ فِي ٱلۡأَرۡضِ مُفۡسِدِينَ ﴿74﴾

Transliteration: Waothkuroo ith jaAAalakum khulafaa min baAAdi AAadin wabawwaakum fee alardi tattakhithoona min suhooliha qusooran watanhitoona aljibala buyootan faothkuroo alaa Allahi wala taAAthaw fee alardi mufsideena

Translation: 74. ከዓድ ህዝቦችም በኋላ ምትኮች ባደረጋችሁና በምድሪቱም ላይ ባስቀመጣችሁ ጊዜ የሆነውን አስታውሱ:: ከሜዳዎቿ ሸክላ ሕንጻዎችን ትገነባላችሁ:: ከተራራዎቿም ቤቶችን ትጠርባላችሁ:: ስለዚህ የአላህን ጸጋዎች አስታውሱ:: በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ::

7:75

قَالَ ٱلۡمَلَأُ ٱلَّذِينَ ٱسۡتَكۡبَرُواْ مِن قَوۡمِهِۦ لِلَّذِينَ ٱسۡتُضۡعِفُواْ لِمَنۡ ءَامَنَ مِنۡهُمۡ أَتَعۡلَمُونَ أَنَّ صَٰلِحٗا مُّرۡسَلٞ مِّن رَّبِّهِۦۚ قَالُوٓاْ إِنَّا بِمَآ أُرۡسِلَ بِهِۦ مُؤۡمِنُونَ ﴿75﴾

Transliteration: Qala almalao allatheena istakbaroo min qawmihi lillatheena istudAAifoo liman amana minhum ataAAlamoona anna salihan mursalun min rabbihi qaloo inna bima orsila bihi muminoona

Translation: 75. ከወገኖቹ መካከል እነዚያ የኮሩት መሪዎች ለእነዚያ ለተሸነፉት በተለይም ከእነርሱ ላመኑት ክፍሎች: «ሷሊህ ከጌታው መላኩን ታውቃላችሁን?» አሏቸው:: እነርሱም «አዎን እናውቃለን:: እኛ እርሱ በተላከበት ነገር ሁሉ ትክክለኛ አማኞች ነን» አሉ።

7:76

قَالَ ٱلَّذِينَ ٱسۡتَكۡبَرُوٓاْ إِنَّا بِٱلَّذِيٓ ءَامَنتُم بِهِۦ كَٰفِرُونَ ﴿76﴾

Transliteration: Qala allatheena istakbaroo inna biallathee amantum bihi kafiroona

Translation: 76. እነዚያ የኮሩት እኛ ግን «በዚያ ባመናችሁበት ነገር ከሓዲያን ነን።» አሉ።

7:77

فَعَقَرُواْ ٱلنَّاقَةَ وَعَتَوۡاْ عَنۡ أَمۡرِ رَبِّهِمۡ وَقَالُواْ يَٰصَٰلِحُ ٱئۡتِنَا بِمَا تَعِدُنَآ إِن كُنتَ مِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ ﴿77﴾

Transliteration: FaAAaqaroo alnnaqata waAAataw AAan amri rabbihim waqaloo ya salihu itina bima taAAiduna in kunta mina almursaleena

Translation: 77. እናም ወዲያው ግመሊቱን ወጓትና ከጌታቸው ትዕዛዝ ወጡ:: «ሷሊህ ሆይ! ከመልዕክተኞቹ እንደሆንክ የምታስፈራራብንን ቅጣት እስቲ አምጣብን።» አሉ።

7:78

فَأَخَذَتۡهُمُ ٱلرَّجۡفَةُ فَأَصۡبَحُواْ فِي دَارِهِمۡ جَٰثِمِينَ ﴿78﴾

Transliteration: Faakhathathumu alrrajfatu faasbahoo fee darihim jathimeena

Translation: 78. ወዲያዉም የምድር መንቀጥቀጥ ያዘቻቸው:: በየቤቶቻቸዉም ውስጥ ተደፍተው አደሩ::

7:79

فَتَوَلَّىٰ عَنۡهُمۡ وَقَالَ يَٰقَوۡمِ لَقَدۡ أَبۡلَغۡتُكُمۡ رِسَالَةَ رَبِّي وَنَصَحۡتُ لَكُمۡ وَلَٰكِن لَّا تُحِبُّونَ ٱلنَّـٰصِحِينَ ﴿79﴾

Transliteration: Fatawalla AAanhum waqala ya qawmi laqad ablaghtukum risalata rabbee wanasahtu lakum walakin la tuhibboona alnnasiheena

Translation: 79. ሷሊህም ከእነርሱ ዞረና «ወገኖቼ ሆይ! የጌታዬን መልዕክት በእርግጥ አደረስኩላችሁ:: ለእናንተም መከርኳችሁ:: ግን እናንተ መካሪዎችን አትወዱም።» አለ።

7:80

وَلُوطًا إِذۡ قَالَ لِقَوۡمِهِۦٓ أَتَأۡتُونَ ٱلۡفَٰحِشَةَ مَا سَبَقَكُم بِهَا مِنۡ أَحَدٖ مِّنَ ٱلۡعَٰلَمِينَ ﴿80﴾

Transliteration: Walootan ith qala liqawmihi atatoona alfahishata ma sabaqakum biha min ahadin mina alAAalameena

Translation: 80. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሉጥም ለሕዝቦቹ (እንዲህ) ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ: «ከዓለማት ከናንተ በፊት አንድም ህዝብ ያልፈጸመውን አስቀያሚ ሥራ ትሠራላችሁን?

7:81

إِنَّكُمۡ لَتَأۡتُونَ ٱلرِّجَالَ شَهۡوَةٗ مِّن دُونِ ٱلنِّسَآءِۚ بَلۡ أَنتُمۡ قَوۡمٞ مُّسۡرِفُونَ ﴿81﴾

Transliteration: Innakum latatoona alrrijala shahwatan min dooni alnnisai bal antum qawmun musrifoona

Translation: 81. «እናንተ ከሴቶች ሌላ ወንዶችን በመከጀል ትመጡባቸዋላችሁ። ይልቁንም እናንተ ወሰንን አላፊ ሕዝቦች ናችሁ።»

7:82

وَمَا كَانَ جَوَابَ قَوۡمِهِۦٓ إِلَّآ أَن قَالُوٓاْ أَخۡرِجُوهُم مِّن قَرۡيَتِكُمۡۖ إِنَّهُمۡ أُنَاسٞ يَتَطَهَّرُونَ ﴿82﴾

Transliteration: Wama kana jawaba qawmihi illa an qaloo akhrijoohum min qaryatikum innahum onasun yatatahharoona

Translation: 82. የሕዝቦቹም መልስ «ሉጥንና ተከታዮቹን ከከተማችሁ አውጧቸው:: እነርሱ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸው።» ከማለት ውጭ ሌላ አልነበረም::

7:83

فَأَنجَيۡنَٰهُ وَأَهۡلَهُۥٓ إِلَّا ٱمۡرَأَتَهُۥ كَانَتۡ مِنَ ٱلۡغَٰبِرِينَ ﴿83﴾

Transliteration: Faanjaynahu waahlahu illa imraatahu kanat mina alghabireena

Translation: 83. ከዚያም እርሱንና ቤተሰቦቹን አዳንናቸው ሚስቱ ብቻ ስትቀር:: እርሷማ ለጥፋት ከቀሩት ሰዎች ሆነች::

7:84

وَأَمۡطَرۡنَا عَلَيۡهِم مَّطَرٗاۖ فَٱنظُرۡ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُجۡرِمِينَ ﴿84﴾

Transliteration: Waamtarna AAalayhim mataran faonthur kayfa kana AAaqibatu almujrimeena

Translation: 84. በእነርሱ ላይ የእሳት ዝናብን አዘነብንባቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የኃጢአተኞች መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከት::

7:85

وَإِلَىٰ مَدۡيَنَ أَخَاهُمۡ شُعَيۡبٗاۚ قَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥۖ قَدۡ جَآءَتۡكُم بَيِّنَةٞ مِّن رَّبِّكُمۡۖ فَأَوۡفُواْ ٱلۡكَيۡلَ وَٱلۡمِيزَانَ وَلَا تَبۡخَسُواْ ٱلنَّاسَ أَشۡيَآءَهُمۡ وَلَا تُفۡسِدُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ بَعۡدَ إِصۡلَٰحِهَاۚ ذَٰلِكُمۡ خَيۡرٞ لَّكُمۡ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ ﴿85﴾

Transliteration: Waila madyana akhahum shuAAayban qala ya qawmi oAAbudoo Allaha ma lakum min ilahin ghayruhu qad jaatkum bayyinatun min rabbikum faawfoo alkayla waalmeezana wala tabkhasoo alnnasa ashyaahum wala tufsidoo fee alardi baAAda islahiha thalikum khayrun lakum in kuntum mumineena

Translation: 85. ወደ መድየን ሕዝብም ወንድማቸውን ሹዐይብን ላክን። አላቸዉም: «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ በስተቀር ምንም አምላክ የላችሁም:: ከጌታችሁ ዘንድ ግልጽ ማስረጃ መጥቶላችኋል:: ስፍርንና ሚዛንን በትክክል ሙሉ:: የሰዎችንም ገንዘቦቻቸውን አታጉድሉባቸው:: ምድርንም ከተበጀች በኋላ አታበላሹ። አማኞች ከሆናችሁ ይህ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነው::

7:86

وَلَا تَقۡعُدُواْ بِكُلِّ صِرَٰطٖ تُوعِدُونَ وَتَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ مَنۡ ءَامَنَ بِهِۦ وَتَبۡغُونَهَا عِوَجٗاۚ وَٱذۡكُرُوٓاْ إِذۡ كُنتُمۡ قَلِيلٗا فَكَثَّرَكُمۡۖ وَٱنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُفۡسِدِينَ ﴿86﴾

Transliteration: Wala taqAAudoo bikulli siratin tooAAidoona watasuddoona AAan sabeeli Allahi man amana bihi watabghoonaha AAiwajan waothkuroo ith kuntum qaleelan fakaththarakum waonthuroo kayfa kana AAaqibatu almufsideena

Translation: 86. «ሰዎችን የምታስፈራሩ፤ ከአላህም መንገድ በእርሱ ያመኑትን የምታግዱና የአላህን መንገድ መጥመሟንም የምትፈልጉ ሆናችሁ በየመንገዱ አትቀመጡ:: ጥቂቶች በነበራችሁና ባበዛችሁ ጊዜ የሆነውን አስታውሱ:: የአጥፊ ህዝቦች መጨረሻ እንዴት እንደነበረም ተመልከቱ::

7:87

وَإِن كَانَ طَآئِفَةٞ مِّنكُمۡ ءَامَنُواْ بِٱلَّذِيٓ أُرۡسِلۡتُ بِهِۦ وَطَآئِفَةٞ لَّمۡ يُؤۡمِنُواْ فَٱصۡبِرُواْ حَتَّىٰ يَحۡكُمَ ٱللَّهُ بَيۡنَنَاۚ وَهُوَ خَيۡرُ ٱلۡحَٰكِمِينَ ﴿87﴾

Transliteration: Wain kana taifatun minkum amanoo biallathee orsiltu bihi wataifatun lam yuminoo faisbiroo hatta yahkuma Allahu baynana wahuwa khayru alhakimeena

Translation: 87. «ከናንተም መካከል እኔ በተላኩበት ያመኑ ቡድኖችና ያላመኑ ቡድኖች ቢኖሩ በመካከላችን አላህ እስከሚፈርድ ታገሡ:: እርሱ ከፈራጆች ሁሉ እጅግ በላጭ ነው።»

7:88

قَالَ ٱلۡمَلَأُ ٱلَّذِينَ ٱسۡتَكۡبَرُواْ مِن قَوۡمِهِۦ لَنُخۡرِجَنَّكَ يَٰشُعَيۡبُ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَعَكَ مِن قَرۡيَتِنَآ أَوۡ لَتَعُودُنَّ فِي مِلَّتِنَاۚ قَالَ أَوَلَوۡ كُنَّا كَٰرِهِينَ ﴿88﴾

Transliteration: Qala almalao allatheena istakbaroo min qawmihi lanukhrijannaka ya shuAAaybu waallatheena amanoo maAAaka min qaryatina aw lataAAoodunna fee millatina qala awalaw kunna kariheena

Translation: 88. ከህዝቦቹ መካከል እነዚያ የኮሩት መሪዎችም፡- «ሹዐይብ ሆይ! አንተንና እነዚያን ካንተ ጋር ያመኑትን ከከተማችን እናወጣችኋለን ወይም ወደ ሃይማኖታችን መመለስ አለባችሁ።» አሉ:: እርሱም አላቸው: «የጠላንም ብንሆን?

7:89

قَدِ ٱفۡتَرَيۡنَا عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا إِنۡ عُدۡنَا فِي مِلَّتِكُم بَعۡدَ إِذۡ نَجَّىٰنَا ٱللَّهُ مِنۡهَاۚ وَمَا يَكُونُ لَنَآ أَن نَّعُودَ فِيهَآ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُ رَبُّنَاۚ وَسِعَ رَبُّنَا كُلَّ شَيۡءٍ عِلۡمًاۚ عَلَى ٱللَّهِ تَوَكَّلۡنَاۚ رَبَّنَا ٱفۡتَحۡ بَيۡنَنَا وَبَيۡنَ قَوۡمِنَا بِٱلۡحَقِّ وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلۡفَٰتِحِينَ ﴿89﴾

Transliteration: Qadi iftarayna AAala Allahi kathiban in AAudna fee millatikum baAAda ith najjana Allahu minha wama yakoonu lana an naAAooda feeha illa an yashaa Allahu rabbuna wasiAAa rabbuna kulla shayin AAilman AAala Allahi tawakkalna rabbana iftah baynana wabayna qawmina bialhaqqi waanta khayru alfatiheena

Translation: 89. «አላህ ከእርሷ ከአዳንን በኋላ ወደ ሃይማኖታችሁ ብንመለስ በአላህ ላይ ውሸትን ቀጠፍን:: አላህ ጌታችን ካልሻም በስተቀር ወደ እርሷ ልንመለስ አይገባንም:: የጌታችን እውቀቱ ከሁሉ ሰፋ:: በአላህ ላይ ብቻ ተመካን:: ጌታችን ሆይ! በእኛና በወገኖቻችን መካከል ፍረድ:: አንተም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነህና።» አለ።

7:90

وَقَالَ ٱلۡمَلَأُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِن قَوۡمِهِۦ لَئِنِ ٱتَّبَعۡتُمۡ شُعَيۡبًا إِنَّكُمۡ إِذٗا لَّخَٰسِرُونَ ﴿90﴾

Transliteration: Waqala almalao allatheena kafaroo min qawmihi laini ittabaAAtum shuAAayban innakum ithan lakhasiroona

Translation: 90. ከወገኖቹም መካከል እነዚያ በአላህ የካዱት መሪዎች ለሕዝቡ «ሹዐይብን ብትከተሉ እናንተ ያኔ ከሳሪዎች ናችሁ።» አሉ።

7:91

فَأَخَذَتۡهُمُ ٱلرَّجۡفَةُ فَأَصۡبَحُواْ فِي دَارِهِمۡ جَٰثِمِينَ ﴿91﴾

Transliteration: Faakhathathumu alrrajfatu faasbahoo fee darihim jathimeena

Translation: 91. ወዲያውኑ የምድር መንቀጥቀጥ ያዘቻቸው:: በየቤታቸው ውስጥ ተደፍተው አደሩ::

7:92

ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ شُعَيۡبٗا كَأَن لَّمۡ يَغۡنَوۡاْ فِيهَاۚ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ شُعَيۡبٗا كَانُواْ هُمُ ٱلۡخَٰسِرِينَ ﴿92﴾

Transliteration: Allatheena kaththaboo shuAAayban kaan lam yaghnaw feeha allatheena kaththaboo shuAAayban kanoo humu alkhasireena

Translation: 92. እነዚያ ሹዓይብን ያስተባበሉት ሰዎች በእርሷ እንዳልነበሩባት ሆኑ:: እነዚያ ሹዓይብን ያስተባበሉት ከሳሪዎቹ እነርሱው ሆኑ::

7:93

فَتَوَلَّىٰ عَنۡهُمۡ وَقَالَ يَٰقَوۡمِ لَقَدۡ أَبۡلَغۡتُكُمۡ رِسَٰلَٰتِ رَبِّي وَنَصَحۡتُ لَكُمۡۖ فَكَيۡفَ ءَاسَىٰ عَلَىٰ قَوۡمٖ كَٰفِرِينَ ﴿93﴾

Transliteration: Fatawalla AAanhum waqala ya qawmi laqad ablaghtukum risalati rabbee wanasahtu lakum fakayfa asa AAala qawmin kafireena

Translation: 93. ሹዐይብም ትቷቸው ከእነርሱ ዞረና «ወገኖቼ ሆይ! የጌታዬን መልእክቶች በእርግጥ አደረስኩላችሁ። ለእናንተም መከርኩ:: ታዲያ በከሃዲ ሰዎች ላይ እንዴት አዝናለሁ?» አለ::

7:94

وَمَآ أَرۡسَلۡنَا فِي قَرۡيَةٖ مِّن نَّبِيٍّ إِلَّآ أَخَذۡنَآ أَهۡلَهَا بِٱلۡبَأۡسَآءِ وَٱلضَّرَّآءِ لَعَلَّهُمۡ يَضَّرَّعُونَ ﴿94﴾

Transliteration: Wama arsalna fee qaryatin min nabiyyin illa akhathna ahlaha bialbasai waalddarrai laAAallahum yaddarraAAoona

Translation: 94. በየትኛዉም ከተማ ለአላህ ይተናነሱ ዘንድ በድህነትና በችግር የያዝናቸው ብንሆን እንጂ አንድንም ነብይ አልላክንም::

7:95

ثُمَّ بَدَّلۡنَا مَكَانَ ٱلسَّيِّئَةِ ٱلۡحَسَنَةَ حَتَّىٰ عَفَواْ وَّقَالُواْ قَدۡ مَسَّ ءَابَآءَنَا ٱلضَّرَّآءُ وَٱلسَّرَّآءُ فَأَخَذۡنَٰهُم بَغۡتَةٗ وَهُمۡ لَا يَشۡعُرُونَ ﴿95﴾

Transliteration: Thumma baddalna makana alssayyiati alhasanata hatta AAafaw waqaloo qad massa abaana alddarrao waalssarrao faakhathnahum baghtatan wahum la yashAAuroona

Translation: 95.ከዚያም እስከበዙና «አባቶቻችንን ድህነትና በሺታ በእርግጥ ነክቷቸዋል፡፡ (ይኽም የጊዜ ልማድ ነው)» እስካሉ ድረስ በመጥፎው ስፍራ በጎውን ለወጥን፡፡ ወዲያውም እነርሱ የማያውቁ ኾነው በድንገት ያዝናቸው፡፡

7:96

وَلَوۡ أَنَّ أَهۡلَ ٱلۡقُرَىٰٓ ءَامَنُواْ وَٱتَّقَوۡاْ لَفَتَحۡنَا عَلَيۡهِم بَرَكَٰتٖ مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِ وَلَٰكِن كَذَّبُواْ فَأَخَذۡنَٰهُم بِمَا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ ﴿96﴾

Transliteration: Walaw anna ahla alqura amanoo waittaqaw lafatahna AAalayhim barakatin mina alssamai waalardi walakin kaththaboo faakhathnahum bima kanoo yaksiboona

Translation: 96. የከተሞቹ (ሰዎችም) በትክክል ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ በእነርሱ ላይ ከሰማይና ከምድር በረከቶችን በከፈትንላቸው ነበር:: ግን አስተባበሉ:: ይሠሩት በነበሩትም ኃጢአት ምክኒያት ቀጣናቸው::

7:97

أَفَأَمِنَ أَهۡلُ ٱلۡقُرَىٰٓ أَن يَأۡتِيَهُم بَأۡسُنَا بَيَٰتٗا وَهُمۡ نَآئِمُونَ ﴿97﴾

Transliteration: Afaamina ahlu alqura an yatiyahum basuna bayatan wahum naimoona

Translation: 97. የከተሞቹ (ሰዎች) የተኙ ሆነው ቅጣታችን ሌሊት ሊመጣባቸው አይፈሩምን?

7:98

أَوَأَمِنَ أَهۡلُ ٱلۡقُرَىٰٓ أَن يَأۡتِيَهُم بَأۡسُنَا ضُحٗى وَهُمۡ يَلۡعَبُونَ ﴿98﴾

Transliteration: Awa amina ahlu alqura an yatiyahum basuna duhan wahum yalAAaboona

Translation: 98. የከተሞቹ ሰዎችም የሚጫወቱ ሆነው ሳሉ ቅጣታችን ቀን በረፋዱ ሊመጣባቸው አይፈሩምን?

7:99

أَفَأَمِنُواْ مَكۡرَ ٱللَّهِۚ فَلَا يَأۡمَنُ مَكۡرَ ٱللَّهِ إِلَّا ٱلۡقَوۡمُ ٱلۡخَٰسِرُونَ ﴿99﴾

Transliteration: Afaaminoo makra Allahi fala yamanu makra Allahi illa alqawmu alkhasiroona

Translation: 99. የአላህን ማዘናጋት አይፈሩምን? ተማመኑን? የአላህን ማዘናጋት ከከሳሪዎች ሕዝቦች በስተቀር ማንም የሚተማመን የለም::

7:100

أَوَلَمۡ يَهۡدِ لِلَّذِينَ يَرِثُونَ ٱلۡأَرۡضَ مِنۢ بَعۡدِ أَهۡلِهَآ أَن لَّوۡ نَشَآءُ أَصَبۡنَٰهُم بِذُنُوبِهِمۡۚ وَنَطۡبَعُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ فَهُمۡ لَا يَسۡمَعُونَ ﴿100﴾

Transliteration: Awalam yahdi lillatheena yarithoona alarda min baAAdi ahliha an law nashao asabnahum bithunoobihim wanatbaAAu AAala quloobihim fahum la yasmaAAoona

Translation: 100. ለእነዚያ ምድርን ከባለቤቶቿ ጥፋት በኋላ ለሚወርሱት ብንሻ ኖሮ በኃጢአቶቻቸው ምክኒያት የምንቀጣቸው መሆናችን አልተገለጸላቸዉምን? በልቦቻቸውም ላይ እናትማለን:: ስለዚህም እነርሱ አይሰሙም::

7:101

تِلۡكَ ٱلۡقُرَىٰ نَقُصُّ عَلَيۡكَ مِنۡ أَنۢبَآئِهَاۚ وَلَقَدۡ جَآءَتۡهُمۡ رُسُلُهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ فَمَا كَانُواْ لِيُؤۡمِنُواْ بِمَا كَذَّبُواْ مِن قَبۡلُۚ كَذَٰلِكَ يَطۡبَعُ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِ ٱلۡكَٰفِرِينَ ﴿101﴾

Transliteration: Tilka alqura naqussu AAalayka min anbaiha walaqad jaathum rusuluhum bialbayyinati fama kanoo liyuminoo bima kaththaboo min qablu kathalika yatbaAAu Allahu AAala quloobi alkafireena

Translation: 101. እነዚህ ከተሞች ከወሬዎቻቸው ባንተ ላይ እንተርካለን:: መልዕክተኞቻቸዉም በግልጽ ተዓምራት መጥተውላቸዋል:: ከመምጣታቸው በፊት ባስተባበሉትም ነገር የሚያምኑ አልሆነም:: ልክ እንደዚሁ አላህ በከሓዲያን ልቦች ላይ ያትማል::

7:102

وَمَا وَجَدۡنَا لِأَكۡثَرِهِم مِّنۡ عَهۡدٖۖ وَإِن وَجَدۡنَآ أَكۡثَرَهُمۡ لَفَٰسِقِينَ ﴿102﴾

Transliteration: Wama wajadna liaktharihim min AAahdin wain wajadna aktharahum lafasiqeena

Translation: 102. ለብዙዎቻቸው በቃል ኪዳናቸው መሙላትን አላገኘንም:: ይልቁንም አብዛኞቻቸውን አመጸኞች ሆነው አገኘናቸው::

7:103

ثُمَّ بَعَثۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِم مُّوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَآ إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ وَمَلَإِيْهِۦ فَظَلَمُواْ بِهَاۖ فَٱنظُرۡ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُفۡسِدِينَ ﴿103﴾

Transliteration: Thumma baAAathna min baAAdihim moosa biayatina ila firAAawna wamalaihi fathalamoo biha faonuthur kayfa kana AAaqibatu almufsideena

Translation: 103. ከዚያም ከበኋላቸው ነብዩ ሙሳን ወደ ፈርዖንና ወደ መማክርቶቹ ተዓምራታችንን አስይዘን ላክነው:: በእርሷም ካዱ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የአጥፊዎች መጨረሻ እንዴት እንደነበረ እስቲ ተመልከት::

7:104

وَقَالَ مُوسَىٰ يَٰفِرۡعَوۡنُ إِنِّي رَسُولٞ مِّن رَّبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ ﴿104﴾

Transliteration: Waqala moosa ya firAAawnu innee rasoolun min rabbi alAAalameena

Translation: 104. ሙሳም አለ፡- «ፈርዖን! ሆይ እኔ ከዓለማት ጌታ የተላኩ መልክተኛ ነኝ?

7:105

حَقِيقٌ عَلَىٰٓ أَن لَّآ أَقُولَ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلۡحَقَّۚ قَدۡ جِئۡتُكُم بِبَيِّنَةٖ مِّن رَّبِّكُمۡ فَأَرۡسِلۡ مَعِيَ بَنِيٓ إِسۡرَـٰٓءِيلَ ﴿105﴾

Transliteration: Haqeequn AAala an la aqoola AAala Allahi illa alhaqqa qad jitukum bibayyinatin min rabbikum faarsil maAAiya banee israeela

Translation: 105. «በአላህ ላይ ከእውነት በስተቀር አለመናገር ተገቢዬ ነው:: ከጌታችሁ ተዓምር ይዤ መጥቻለሁና የኢስራኢል ልጆችን ከእኔ ጋር ልቀቅ።» አለ።

7:106

قَالَ إِن كُنتَ جِئۡتَ بِـَٔايَةٖ فَأۡتِ بِهَآ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّـٰدِقِينَ ﴿106﴾

Transliteration: Qala in kunta jita biayatin fati biha in kunta mina alssadiqeena

Translation: 106. ፈርዖንም፡ «በተዓምር የመጣህ ከሆንክና ከእውነተኞቹ ከሆንክ እስቲ አምጣት።» አለው።

7:107

فَأَلۡقَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِيَ ثُعۡبَانٞ مُّبِينٞ ﴿107﴾

Transliteration: Faalqa AAasahu faitha hiya thuAAbanun mubeenun

Translation: 107. ሙሳም ዘንጉን ምድር ላይ ጣለ:: እርሷም ወዲያውኑ ግልጽ እባብ ሆነች::

7:108

وَنَزَعَ يَدَهُۥ فَإِذَا هِيَ بَيۡضَآءُ لِلنَّـٰظِرِينَ ﴿108﴾

Transliteration: WanazaAAa yadahu faitha hiya baydao lilnnathireena

Translation: 108. እጁንም አወጣ:: እርሷም ወዲያውኑ ለተመልካቾች ነጭ ሆነች::

7:109

قَالَ ٱلۡمَلَأُ مِن قَوۡمِ فِرۡعَوۡنَ إِنَّ هَٰذَا لَسَٰحِرٌ عَلِيمٞ ﴿109﴾

Transliteration: Qala almalao min qawmi firAAawna inna hatha lasahirun AAaleemun

Translation: 109. ከፈርዖን ሰዎች መማክርቶቹም አሉ፡ «ይህ በእርግጥ አዋቂ ድግምተኛ ነው።

7:110

يُرِيدُ أَن يُخۡرِجَكُم مِّنۡ أَرۡضِكُمۡۖ فَمَاذَا تَأۡمُرُونَ ﴿110﴾

Transliteration: Yureedu an yukhrijakum min ardikum famatha tamuroona

Translation: 110. «ከምድራችሁ ሊያወጣችሁ ይሻል።» አሉ። (ፊርዓውንም) «ታዲያ ምን? ታዛላችሁ?» አለ።

7:111

قَالُوٓاْ أَرۡجِهۡ وَأَخَاهُ وَأَرۡسِلۡ فِي ٱلۡمَدَآئِنِ حَٰشِرِينَ ﴿111﴾

Transliteration: Qaloo arjih waakhahu waarsil fee almadaini hashireena

Translation: 111. እነርሱም አሉ: «እርሱንና ወንድሙን አቆያቸው:: ወደ ከተሞቹ ሁሉ ሰብሳቢዎችን ላክ::

7:112

يَأۡتُوكَ بِكُلِّ سَٰحِرٍ عَلِيمٖ ﴿112﴾

Transliteration: Yatooka bikulli sahirin AAaleemin

Translation: 112. «አዋቂ ድግምተኞችን ሁሉ ያመጡልሃልና።» አሉ።

7:113

وَجَآءَ ٱلسَّحَرَةُ فِرۡعَوۡنَ قَالُوٓاْ إِنَّ لَنَا لَأَجۡرًا إِن كُنَّا نَحۡنُ ٱلۡغَٰلِبِينَ ﴿113﴾

Transliteration: Wajaa alssaharatu firAAawna qaloo inna lana laajran in kunna nahnu alghalibeena

Translation: 113. ድግምተኞቹም ወደ ፈርዖን መጡና «እኛ አሸናፊዎች ብንሆን ለኛ ክፍያ አለን?» አሉ።

7:114

قَالَ نَعَمۡ وَإِنَّكُمۡ لَمِنَ ٱلۡمُقَرَّبِينَ ﴿114﴾

Transliteration: Qala naAAam wainnakum lamina almuqarrabeena

Translation: 114. ፈርዖንም: «አዎን። እናንተ እኔ ዘንድ ከባለሟሎቹ ትሆናላችሁ።» አላቸው።

7:115

قَالُواْ يَٰمُوسَىٰٓ إِمَّآ أَن تُلۡقِيَ وَإِمَّآ أَن نَّكُونَ نَحۡنُ ٱلۡمُلۡقِينَ ﴿115﴾

Transliteration: Qaloo ya moosa imma an tulqiya waimma an nakoona nahnu almulqeena

Translation: 115. እነርሱም «ሙሳ ሆይ! ዘንግህን በፊት ትጥላለህ ወይስ ፊት ጣዮቹ እኛ እንሁን?» አሉት።

7:116

قَالَ أَلۡقُواْۖ فَلَمَّآ أَلۡقَوۡاْ سَحَرُوٓاْ أَعۡيُنَ ٱلنَّاسِ وَٱسۡتَرۡهَبُوهُمۡ وَجَآءُو بِسِحۡرٍ عَظِيمٖ ﴿116﴾

Transliteration: Qala alqoo falamma alqaw saharoo aAAyuna alnnasi waistarhaboohum wajaoo bisihrin AAatheemin

Translation: 116. ሙሳም «በፊት እናንተ ጣሉ።» አላቸው:: ከዚያም ገመዶቻቸውን በጣሉ ጊዜ የሰዎቹን ዓይኖች ደገሙባቸውና አስፈራሯቸው:: ትልቅ ድግምትንም አመጡ::

7:117

وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ أَنۡ أَلۡقِ عَصَاكَۖ فَإِذَا هِيَ تَلۡقَفُ مَا يَأۡفِكُونَ ﴿117﴾

Transliteration: Waawhayna ila moosa an alqi AAasaka faitha hiya talqafu ma yafikoona

Translation: 117. ወደ ሙሳም «ዘንግህን ጣል» ስንል ላክንበት (ጣላትም) ወዲውኑም የሚቀጣጥፉትን ማታለያ ሁሉ መዋጥ ጀመረች::

7:118

فَوَقَعَ ٱلۡحَقُّ وَبَطَلَ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ ﴿118﴾

Transliteration: FawaqaAAa alhaqqu wabatala ma kanoo yaAAmaloona

Translation: 118. እውነቱም ተገለጸ:: ይሠሩት የነበሩት ድግምትም ተበላሸ::

7:119

فَغُلِبُواْ هُنَالِكَ وَٱنقَلَبُواْ صَٰغِرِينَ ﴿119﴾

Transliteration: Faghuliboo hunalika wainqalaboo saghireena

Translation: 119. እዚያ ላይ ተሸነፉና ወራዶች ሆነው ተመለሱ::

7:120

وَأُلۡقِيَ ٱلسَّحَرَةُ سَٰجِدِينَ ﴿120﴾

Transliteration: Waolqiya alssaharatu sajideena

Translation: 120. ድግምተኞቹም ሰጋጆች ሆነው ሱጁድ ወረዱ::

7:121

قَالُوٓاْ ءَامَنَّا بِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ ﴿121﴾

Transliteration: Qaloo amanna birabbi alAAalameena

Translation: 121. አሉም: «በዓለማት ጌታ አመንን።

7:122

رَبِّ مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ ﴿122﴾

Transliteration: Rabbi moosa waharoona

Translation: 122. «በሙሳና በሃሩን ጌታ።»

7:123

قَالَ فِرۡعَوۡنُ ءَامَنتُم بِهِۦ قَبۡلَ أَنۡ ءَاذَنَ لَكُمۡۖ إِنَّ هَٰذَا لَمَكۡرٞ مَّكَرۡتُمُوهُ فِي ٱلۡمَدِينَةِ لِتُخۡرِجُواْ مِنۡهَآ أَهۡلَهَاۖ فَسَوۡفَ تَعۡلَمُونَ ﴿123﴾

Transliteration: Qala firAAawnu amantum bihi qabla an athana lakum inna hatha lamakrun makartumoohu fee almadeenati litukhrijoo minha ahlaha fasawfa taAAlamoona

Translation: 123. (ፊርዓውንም) አለ፡ «እኔ ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት በእርሱ አመናችሁን? ይህ በከተማይቱ ውስጥ ሰውን ከእርሷ ለማውጣት የተስማማችሁበት ተንኮል ነው:: ወደፊት የሚደርሰባችሁን ታውቃላችሁ።

7:124

لَأُقَطِّعَنَّ أَيۡدِيَكُمۡ وَأَرۡجُلَكُم مِّنۡ خِلَٰفٖ ثُمَّ لَأُصَلِّبَنَّكُمۡ أَجۡمَعِينَ ﴿124﴾

Transliteration: LaoqatiAAanna aydiyakum waarjulakum min khilafin thumma laosallibannakum ajmaAAeena

Translation: 124. «እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን በማፈራረቅ በእርግጥ እቆራርጣለሁ:: ከዚያም ሁላችሁንም በእንጨት ላይ እስቅላችኋለሁ።» አለ።

7:125

قَالُوٓاْ إِنَّآ إِلَىٰ رَبِّنَا مُنقَلِبُونَ ﴿125﴾

Transliteration: Qaloo inna ila rabbina munqaliboona

Translation: 125. እነርሱም አሉ: «እኛ ወደ ጌታችን ተመላሾች ነን።

7:126

وَمَا تَنقِمُ مِنَّآ إِلَّآ أَنۡ ءَامَنَّا بِـَٔايَٰتِ رَبِّنَا لَمَّا جَآءَتۡنَاۚ رَبَّنَآ أَفۡرِغۡ عَلَيۡنَا صَبۡرٗا وَتَوَفَّنَا مُسۡلِمِينَ ﴿126﴾

Transliteration: Wama tanqimu minna illa an amanna biayati rabbina lamma jaatna rabbana afrigh AAalayna sabran watawaffana muslimeena

Translation: 126. «የጌታችን ተዓምራት በመጡልን ጊዜ ከማመናችን በስተቀር ከእኛ አትጠላም:: ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አፍስስ:: ሙስሊሞችም ሆነን ግደለን።» አሉ።

7:127

وَقَالَ ٱلۡمَلَأُ مِن قَوۡمِ فِرۡعَوۡنَ أَتَذَرُ مُوسَىٰ وَقَوۡمَهُۥ لِيُفۡسِدُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَيَذَرَكَ وَءَالِهَتَكَۚ قَالَ سَنُقَتِّلُ أَبۡنَآءَهُمۡ وَنَسۡتَحۡيِۦ نِسَآءَهُمۡ وَإِنَّا فَوۡقَهُمۡ قَٰهِرُونَ ﴿127﴾

Transliteration: Waqala almalao min qawmi firAAawna atatharu moosa waqawmahu liyufsidoo fee alardi wayatharaka waalihataka qala sanuqattilu abnaahum wanastahyee nisaahum wainna fawqahum qahiroona

Translation: 127. ከፈርዖን ሰዎች ቅምጥሎቹ ለፈርዖን: «ሙሳንና ሰዎችን በምድር ላይ እንዲያበላሹና ሙሳም አንተንና አምልኮትህን እንዲተው ትተዋቸዋለህን?» አሉ:: እሱም «ወንዶች ልጆቻቸውን እንገድላለን:: ሴቶቻቸውንም እናስቀራለን:: እኛም ከበላያቸው ነን አሸናፊዎች ነን» አለ።

7:128

قَالَ مُوسَىٰ لِقَوۡمِهِ ٱسۡتَعِينُواْ بِٱللَّهِ وَٱصۡبِرُوٓاْۖ إِنَّ ٱلۡأَرۡضَ لِلَّهِ يُورِثُهَا مَن يَشَآءُ مِنۡ عِبَادِهِۦۖ وَٱلۡعَٰقِبَةُ لِلۡمُتَّقِينَ ﴿128﴾

Transliteration: Qala moosa liqawmihi istaAAeenoo biAllahi waisbiroo inna alarda lillahi yoorithuha man yashao min AAibadihi waalAAaqibatu lilmuttaqeena

Translation: 128. ሙሳም ለሰዎቹ፡- «በአላህ ታገዙ፤ ታገሱም። ምድር ለአላህ ናትና ከባሮቹ መካከል ለሚሻው ያወርሳታል:: ምስጉኗም ፍጻሜ ለጥንቁቆቹ ናት።» አላቸው።

7:129

قَالُوٓاْ أُوذِينَا مِن قَبۡلِ أَن تَأۡتِيَنَا وَمِنۢ بَعۡدِ مَا جِئۡتَنَاۚ قَالَ عَسَىٰ رَبُّكُمۡ أَن يُهۡلِكَ عَدُوَّكُمۡ وَيَسۡتَخۡلِفَكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَيَنظُرَ كَيۡفَ تَعۡمَلُونَ ﴿129﴾

Transliteration: Qaloo ootheena min qabli an tatiyana wamin baAAdi ma jitana qala AAasa rabbukum an yuhlika AAaduwwakum wayastakhlifakum fee alardi fayanthura kayfa taAAmaloona

Translation: 129. ህዝቦቹም «አንተ ከመምጣትህ በፊትም ሆነ ከመጣህልን በኋላ ተሰቃየን።» አሉት:: ሙሳም «ጌታችሁ ጠላቶቻችሁን ሊያጠፋና እንዴት እንደምትሰሩ ይመለከት ዘንድ በምድር ላይ ሊተካችሁ ይከጀላል።» አላቸው።

7:130

وَلَقَدۡ أَخَذۡنَآ ءَالَ فِرۡعَوۡنَ بِٱلسِّنِينَ وَنَقۡصٖ مِّنَ ٱلثَّمَرَٰتِ لَعَلَّهُمۡ يَذَّكَّرُونَ ﴿130﴾

Transliteration: Walaqad akhathna ala firAAawna bialssineena wanaqsin mina alththamarati laAAallahum yaththakkaroona

Translation: 130. የፈርዖንንም ቤተሰቦች እንዲገሰጹ በድርቅና የፍራፍሬ ምርታቸውን በመቀነስ በእርግጥ ቀጣናቸው::

7:131

فَإِذَا جَآءَتۡهُمُ ٱلۡحَسَنَةُ قَالُواْ لَنَا هَٰذِهِۦۖ وَإِن تُصِبۡهُمۡ سَيِّئَةٞ يَطَّيَّرُواْ بِمُوسَىٰ وَمَن مَّعَهُۥٓۗ أَلَآ إِنَّمَا طَـٰٓئِرُهُمۡ عِندَ ٱللَّهِ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ ﴿131﴾

Transliteration: Faitha jaathumu alhasanatu qaloo lana hathihi wain tusibhum sayyiatun yattayyaroo bimoosa waman maAAahu ala innama tairuhum AAinda Allahi walakinna aktharahum la yaAAlamoona

Translation: 131. ምቾት በመጣችላቸው ጊዜ «ይህች ለእኛ ተገቢ ናት።» ይላሉ። ክፋት ባገኛቸው ጊዜ ግን ሙሳና አብረውት ያሉት ክፉ ገዶቻቸው እንደሆኑ ያስባሉ። አስተውሉ! ክፉ እድላቸው (ገደቢስነታቸው) ከአላህ ዘንድ ነው:: አብዛኞቻቸው ግን ይህን አያውቁም::

7:132

وَقَالُواْ مَهۡمَا تَأۡتِنَا بِهِۦ مِنۡ ءَايَةٖ لِّتَسۡحَرَنَا بِهَا فَمَا نَحۡنُ لَكَ بِمُؤۡمِنِينَ ﴿132﴾

Transliteration: Waqaloo mahma tatina bihi min ayatin litasharana biha fama nahnu laka bimumineena

Translation: 132. «በማንኛይቱም ተዓምር ልትደግምብን ብታመጣም የምናምንልህ አይደለንም።» አሉ።

7:133

فَأَرۡسَلۡنَا عَلَيۡهِمُ ٱلطُّوفَانَ وَٱلۡجَرَادَ وَٱلۡقُمَّلَ وَٱلضَّفَادِعَ وَٱلدَّمَ ءَايَٰتٖ مُّفَصَّلَٰتٖ فَٱسۡتَكۡبَرُواْ وَكَانُواْ قَوۡمٗا مُّجۡرِمِينَ ﴿133﴾

Transliteration: Faarsalna AAalayhimu alttoofana waaljarada waalqummala waalddafadiAAa waalddama ayatin mufassalatin faistakbaroo wakanoo qawman mujrimeena

Translation: 133. ወዲያዉም የውሃን ማጥለቅለቅ፤ አንበጣን፤ ቅማልን፤ እንቁራሪቶችን፤ ደምን፤ የተለያዩ ተዓምራት ሲሆኑ በእነርሱ ላይ ላክን:: እነርሱ ግን ኮሩም:: ተንኮለኞችም ህዝቦች ነበሩ::

7:134

وَلَمَّا وَقَعَ عَلَيۡهِمُ ٱلرِّجۡزُ قَالُواْ يَٰمُوسَى ٱدۡعُ لَنَا رَبَّكَ بِمَا عَهِدَ عِندَكَۖ لَئِن كَشَفۡتَ عَنَّا ٱلرِّجۡزَ لَنُؤۡمِنَنَّ لَكَ وَلَنُرۡسِلَنَّ مَعَكَ بَنِيٓ إِسۡرَـٰٓءِيلَ ﴿134﴾

Transliteration: Walamma waqaAAa AAalayhimu alrrijzu qaloo ya moosa odAAu lana rabbaka bima AAahida AAindaka lain kashafta AAanna alrrijza lanuminanna laka walanursilanna maAAaka banee israeela

Translation: 134. በእነርሱ ላይ ቅጣቱ በወደቀባቸውም ጊዜ «ሙሳ ሆይ! ጌታህን ላንተ ቃል ኪዳን በገባልህ መሠረት ለምንልንና ከእኛ ቅጣቱን ብታነሳልን ላንተ እናምንልሀለን:: የኢስራኢልን ልጆችም ካንተ ጋር እንለቃለን።» አሉ።

7:135

فَلَمَّا كَشَفۡنَا عَنۡهُمُ ٱلرِّجۡزَ إِلَىٰٓ أَجَلٍ هُم بَٰلِغُوهُ إِذَا هُمۡ يَنكُثُونَ ﴿135﴾

Transliteration: Falamma kashafna AAanhumu alrrijza ila ajalin hum balighoohu itha hum yankuthoona

Translation: 135. ለሚደርሱበት የተወሰነ ጊዜ ድረስ ቅጣትን ከእነርሱ ላይ ባነሳን ጊዜ ወዲያውኑ እነርሱ ቃላቸውን አፈረሱ::

7:136

فَٱنتَقَمۡنَا مِنۡهُمۡ فَأَغۡرَقۡنَٰهُمۡ فِي ٱلۡيَمِّ بِأَنَّهُمۡ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَكَانُواْ عَنۡهَا غَٰفِلِينَ ﴿136﴾

Transliteration: Faintaqamna minhum faaghraqnahum fee alyammi biannahum kaththaboo biayatina wakanoo AAanha ghafileena

Translation: 136. እነርሱም በተዓምራታችን ስላስተባበሉና ከእርሷ ዘንጊዎች ስለሆኑ ተበቀልናቸው:: በባህር ውስጥም አሰመጥናቸው::

7:137

وَأَوۡرَثۡنَا ٱلۡقَوۡمَ ٱلَّذِينَ كَانُواْ يُسۡتَضۡعَفُونَ مَشَٰرِقَ ٱلۡأَرۡضِ وَمَغَٰرِبَهَا ٱلَّتِي بَٰرَكۡنَا فِيهَاۖ وَتَمَّتۡ كَلِمَتُ رَبِّكَ ٱلۡحُسۡنَىٰ عَلَىٰ بَنِيٓ إِسۡرَـٰٓءِيلَ بِمَا صَبَرُواْۖ وَدَمَّرۡنَا مَا كَانَ يَصۡنَعُ فِرۡعَوۡنُ وَقَوۡمُهُۥ وَمَا كَانُواْ يَعۡرِشُونَ ﴿137﴾

Transliteration: Waawrathna alqawma allatheena kanoo yustadAAafoona mashariqa alardi wamagharibaha allatee barakna feeha watammat kalimatu rabbika alhusna AAala banee israeela bima sabaroo wadammarna ma kana yasnaAAu firAAawnu waqawmuhu wama kanoo yaAArishoona

Translation: 137. እነዚያንም ደካሞች የነበሩትን ህዝቦች ያቺን በውስጧ በረከት ያደረግንባትን ምድር ምስራቋንም ምዕራቧንም አወረስናቸው:: መልዕክተኛችን ሆይ! የጌታህ መልካሚቱ ቃል በኢስራኢል ልጆች ላይ በመታገሳቸው ተፈጸመች:: ፈርዖንና ሰዎቹ ይሰሩት የነበረውን ህንጻና ዳስ ያደርጉት የነበረውንም አፈረስን::

7:138

وَجَٰوَزۡنَا بِبَنِيٓ إِسۡرَـٰٓءِيلَ ٱلۡبَحۡرَ فَأَتَوۡاْ عَلَىٰ قَوۡمٖ يَعۡكُفُونَ عَلَىٰٓ أَصۡنَامٖ لَّهُمۡۚ قَالُواْ يَٰمُوسَى ٱجۡعَل لَّنَآ إِلَٰهٗا كَمَا لَهُمۡ ءَالِهَةٞۚ قَالَ إِنَّكُمۡ قَوۡمٞ تَجۡهَلُونَ ﴿138﴾

Transliteration: Wajawazna bibanee israeela albahra faataw AAala qawmin yaAAkufoona AAala asnamin lahum qaloo ya moosa ijAAal lana ilahan kama lahum alihatun qala innakum qawmun tajhaloona

Translation: 138. የኢስራኢል ልጆችን ባህሩን አሻገርናቸው:: ለእነርሱ በሆኑ ጣኦታት መገዛት ላይ በሚዘወትሩ ህዝቦች አጠገብ አለፉም:: «ሙሳ ሆይ! ለእነርሱ ለሰዎቹ አማልክት እንዳሏቸው ሁሉ ለኛም አምላክን አድርግልን።» አሉት:: «እናንተ የምትሳሳቱ ህዝቦች ናችሁ።» አላቸው።

7:139

إِنَّ هَـٰٓؤُلَآءِ مُتَبَّرٞ مَّا هُمۡ فِيهِ وَبَٰطِلٞ مَّا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ ﴿139﴾

Transliteration: Inna haolai mutabbarun ma hum feehi wabatilun ma kanoo yaAAmaloona

Translation: 139. «እነዚህ እነርሱ በውስጡ ያሉበት ነገር ጠፊ ነው:: ይሰሩት የነበሩትም ብልሹ ነው።» አላቸው።

7:140

قَالَ أَغَيۡرَ ٱللَّهِ أَبۡغِيكُمۡ إِلَٰهٗا وَهُوَ فَضَّلَكُمۡ عَلَى ٱلۡعَٰلَمِينَ ﴿140﴾

Transliteration: Qala aghayra Allahi abgheekum ilahan wahuwa faddalakum AAala alAAalameena

Translation: 140. «እርሱ ከዓለማት ያበለጣችሁ ሲሆን ከአላህ ሌላ የምትገዙትን አምላክ እፈልግላችኋለሁን?» አለ::

7:141

وَإِذۡ أَنجَيۡنَٰكُم مِّنۡ ءَالِ فِرۡعَوۡنَ يَسُومُونَكُمۡ سُوٓءَ ٱلۡعَذَابِ يُقَتِّلُونَ أَبۡنَآءَكُمۡ وَيَسۡتَحۡيُونَ نِسَآءَكُمۡۚ وَفِي ذَٰلِكُم بَلَآءٞ مِّن رَّبِّكُمۡ عَظِيمٞ ﴿141﴾

Transliteration: Waith anjaynakum min ali firAAawna yasoomoonakum sooa alAAathabi yuqattiloona abnaakum wayastahyoona nisaakum wafee thalikum balaon min rabbikum AAatheemun

Translation: 141. የኢስራኢል ልጆች ሆይ! ከፈርዖንም ቤተሰቦች ብርቱን ቅጣት የሚያቀምሷችሁ ወንዶች ልጆቻችሁንም የሚገድሉ ሴቶቻችሁንም የሚተው ሲሆኑ ባዳንናችሁ ጊዜ (የሆነዉን አስታውሱ):: በዚህ ውስጥ ከጌታችሁ የሆነ ከባድ ፈተና አለበት::

7:142

وَوَٰعَدۡنَا مُوسَىٰ ثَلَٰثِينَ لَيۡلَةٗ وَأَتۡمَمۡنَٰهَا بِعَشۡرٖ فَتَمَّ مِيقَٰتُ رَبِّهِۦٓ أَرۡبَعِينَ لَيۡلَةٗۚ وَقَالَ مُوسَىٰ لِأَخِيهِ هَٰرُونَ ٱخۡلُفۡنِي فِي قَوۡمِي وَأَصۡلِحۡ وَلَا تَتَّبِعۡ سَبِيلَ ٱلۡمُفۡسِدِينَ ﴿142﴾

Transliteration: WawaAAadna moosa thalatheena laylatan waatmamnaha biAAashrin fatamma meeqatu rabbihi arbaAAeena laylatan waqala moosa liakheehi haroona okhlufnee fee qawmee waaslih wala tattabiAA sabeela almufsideena

Translation: 142. ነብዩ ሙሳን ሰላሳን ሌሊት (ሊፆምና ልናነጋግረው) ቀጠርነው:: በአስርም (ሌሊት) ሞላናት:: የጌታዉም ቀጠሮ አርባ ሌሊት ሲሆን ተፈጸመ:: ሙሳም ለወንድሙ ለሀሩን «በህዝቦቼ ላይ ተተካኝና አሳምር:: የአጥፊዎችን መንገድ አትከተል።» አለው::

7:143

وَلَمَّا جَآءَ مُوسَىٰ لِمِيقَٰتِنَا وَكَلَّمَهُۥ رَبُّهُۥ قَالَ رَبِّ أَرِنِيٓ أَنظُرۡ إِلَيۡكَۚ قَالَ لَن تَرَىٰنِي وَلَٰكِنِ ٱنظُرۡ إِلَى ٱلۡجَبَلِ فَإِنِ ٱسۡتَقَرَّ مَكَانَهُۥ فَسَوۡفَ تَرَىٰنِيۚ فَلَمَّا تَجَلَّىٰ رَبُّهُۥ لِلۡجَبَلِ جَعَلَهُۥ دَكّٗا وَخَرَّ مُوسَىٰ صَعِقٗاۚ فَلَمَّآ أَفَاقَ قَالَ سُبۡحَٰنَكَ تُبۡتُ إِلَيۡكَ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ﴿143﴾

Transliteration: Walamma jaa moosa limeeqatina wakallamahu rabbuhu qala rabbi arinee anthur ilayka qala lan taranee walakini onthur ila aljabali faini istaqarra makanahu fasawfa taranee falamma tajalla rabbuhu liljabali jaAAalahu dakkan wakharra moosa saAAiqan falamma afaqa qala subhanaka tubtu ilayka waana awwalu almumineena

Translation: 143. ሙሳ ለቀጠሮው በመጣና ጌታዉም ባነጋገረው ጊዜ፡ «ጌታዬ ሆይ! በእርግጥ ራስህን አሳየኝ ወደ አንተ እመለከታለሁና።» አለ። (አላህም)፡- «እኔን በፍጹም አታየኝም:: ግን ወደ ተራራው ተመልከትና በስፍራው ከረጋ አንተም ታየኛለህ።» አለው:: ጌታዉም ለተራራው በተገለጸ ጊዜ እንኩትኩት አደረገው:: ሙሳም ጮኸና ወደቀ:: በአንሰራራም ጊዜ «ጌታዬ ጥራት ይገባህ ወደ አንተ ተመለስኩ:: እኔም በጊዜያቴ የአማኞች መጀመሪያ ነኝ።» አለ።

7:144

قَالَ يَٰمُوسَىٰٓ إِنِّي ٱصۡطَفَيۡتُكَ عَلَى ٱلنَّاسِ بِرِسَٰلَٰتِي وَبِكَلَٰمِي فَخُذۡ مَآ ءَاتَيۡتُكَ وَكُن مِّنَ ٱلشَّـٰكِرِينَ ﴿144﴾

Transliteration: Qala ya moosa innee istafaytuka AAala alnnasi birisalatee wabikalamee fakhuth ma ataytuka wakun mina alshshakireena

Translation: 144. አላህም አለ፡- «ሙሳ ሆይ! እኔ በመልዕክቶቼና በማናገሬ በሰዎች ላይ መረጥኩህ:: የሰጠሁህንም ያዝ። ከአመስጋኞችም ሁን።» አለው።

7:145

وَكَتَبۡنَا لَهُۥ فِي ٱلۡأَلۡوَاحِ مِن كُلِّ شَيۡءٖ مَّوۡعِظَةٗ وَتَفۡصِيلٗا لِّكُلِّ شَيۡءٖ فَخُذۡهَا بِقُوَّةٖ وَأۡمُرۡ قَوۡمَكَ يَأۡخُذُواْ بِأَحۡسَنِهَاۚ سَأُوْرِيكُمۡ دَارَ ٱلۡفَٰسِقِينَ ﴿145﴾

Transliteration: Wakatabna lahu fee alalwahi min kulli shayin mawAAithatan watafseelan likulli shayin fakhuthha biquwwatin wamur qawmaka yakhuthoo biahsaniha saoreekum dara alfasiqeena

Translation: 145. ለእርሱም በሰሌዳዎቹ ላይ ከሁሉ ነገር ግሳጼንና ለሁሉ ነገር ማብራራትን ጻፍንለትና አልንም: «በብርታትም ያዛት። ሕዝቦችህንም በመልካሟ እንዲይዙ እዘዛቸው። የአመጸኞቹን አገር በእርግጥ አሳያችኋለሁ።»

7:146

سَأَصۡرِفُ عَنۡ ءَايَٰتِيَ ٱلَّذِينَ يَتَكَبَّرُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ بِغَيۡرِ ٱلۡحَقِّ وَإِن يَرَوۡاْ كُلَّ ءَايَةٖ لَّا يُؤۡمِنُواْ بِهَا وَإِن يَرَوۡاْ سَبِيلَ ٱلرُّشۡدِ لَا يَتَّخِذُوهُ سَبِيلٗا وَإِن يَرَوۡاْ سَبِيلَ ٱلۡغَيِّ يَتَّخِذُوهُ سَبِيلٗاۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَكَانُواْ عَنۡهَا غَٰفِلِينَ ﴿146﴾

Transliteration: Saasrifu AAan ayatiya allatheena yatakabbaroona fee alardi bighayri alhaqqi wain yaraw kulla ayatin la yuminoo biha wain yaraw sabeela alrrushdi la yattakhithoohu sabeelan wain yaraw sabeela alghayyi yattakhithoohu sabeelan thalika biannahum kaththaboo biayatina wakanoo AAanha ghafileena

Translation: 146. እነዚያን ያለ አግባብ በምድር ላይ የሚኮሩትን ከአንቀፆቼ በእርግጥ አዞራቸዋለሁ:: ተዓምርንም ሁሉ ቢያዩ እንኳን አያምኑም:: ቅንንም መንገድ ቢያዩ መንገድ አድርገው አይዙትም:: ግን የጥመትን መንገድ ቢያዩ መንገድ አድርገው ይይዙታል:: ይህ እነርሱ በአንቀፆቻችን ስለ አስተባበሉና ከእርሷም ዘንጊዎች ስለሆኑ ነው::

7:147

وَٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَلِقَآءِ ٱلۡأٓخِرَةِ حَبِطَتۡ أَعۡمَٰلُهُمۡۚ هَلۡ يُجۡزَوۡنَ إِلَّا مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ ﴿147﴾

Transliteration: Waallatheena kaththaboo biayatina waliqai alakhirati habitat aAAmaluhum hal yujzawna illa ma kanoo yaAAmaloona

Translation: 147. እነዚያም በአናቅጻችንና መጨረሻይቱን ዓለም በመገናኘት ያስተባበሉት ሥራዎቻቸው ተበላሹ:: ይሰሩት የነበረውን እንጂ ይመነዳሉን?

7:148

وَٱتَّخَذَ قَوۡمُ مُوسَىٰ مِنۢ بَعۡدِهِۦ مِنۡ حُلِيِّهِمۡ عِجۡلٗا جَسَدٗا لَّهُۥ خُوَارٌۚ أَلَمۡ يَرَوۡاْ أَنَّهُۥ لَا يُكَلِّمُهُمۡ وَلَا يَهۡدِيهِمۡ سَبِيلًاۘ ٱتَّخَذُوهُ وَكَانُواْ ظَٰلِمِينَ ﴿148﴾

Transliteration: Waittakhatha qawmu moosa min baAAdihi min huliyyihim AAijlan jasadan lahu khuwarun alam yaraw annahu la yukallimuhum wala yahdeehim sabeelan ittakhathoohu wakanoo thalimeena

Translation: 148. የሙሳም ህዝቦች ከእርሱ መሄድ በኋላ ከጌጦቻቸው በወይፈን ቅርጽ የተቀረጸውን እና የራሱ የሆነ ድምጽ የነበረውን አካል አምላክ አድርገው ያዙት:: እርሱ የማያናግራቸው መንገድን የማይመራቸው መሆኑን አይመለከቱምን? አምላክ አደረጉት:: በዳዮችም ሆኑ::

7:149

وَلَمَّا سُقِطَ فِيٓ أَيۡدِيهِمۡ وَرَأَوۡاْ أَنَّهُمۡ قَدۡ ضَلُّواْ قَالُواْ لَئِن لَّمۡ يَرۡحَمۡنَا رَبُّنَا وَيَغۡفِرۡ لَنَا لَنَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ ﴿149﴾

Transliteration: Walamma suqita fee aydeehim waraaw annahum qad dalloo qaloo lain lam yarhamna rabbuna wayaghfir lana lanakoonanna mina alkhasireena

Translation: 149. በተጸጸቱና እነርሱም በእርግጥ የተሳሳቱ መሆናቸውን ባዩ ጊዜ «ጌታችን ካላዘነልንና ካልማረን በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንሆናለን።» አሉ::

7:150

وَلَمَّا رَجَعَ مُوسَىٰٓ إِلَىٰ قَوۡمِهِۦ غَضۡبَٰنَ أَسِفٗا قَالَ بِئۡسَمَا خَلَفۡتُمُونِي مِنۢ بَعۡدِيٓۖ أَعَجِلۡتُمۡ أَمۡرَ رَبِّكُمۡۖ وَأَلۡقَى ٱلۡأَلۡوَاحَ وَأَخَذَ بِرَأۡسِ أَخِيهِ يَجُرُّهُۥٓ إِلَيۡهِۚ قَالَ ٱبۡنَ أُمَّ إِنَّ ٱلۡقَوۡمَ ٱسۡتَضۡعَفُونِي وَكَادُواْ يَقۡتُلُونَنِي فَلَا تُشۡمِتۡ بِيَ ٱلۡأَعۡدَآءَ وَلَا تَجۡعَلۡنِي مَعَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلظَّـٰلِمِينَ ﴿150﴾

Transliteration: Walamma rajaAAa moosa ila qawmihi ghadbana asifan qala bisama khalaftumoonee min baAAdee aAAajiltum amra rabbikum waalqa alalwaha waakhatha birasi akheehi yajurruhu ilayhi qala ibna omma inna alqawma istadAAafoonee wakadoo yaqtuloonanee fala tushmit biya alaAAdaa wala tajAAalnee maAAa alqawmi alththalimeena

Translation: 150. ሙሳ እየተቆጣና እያዘነ ወደ ህዝቦቹ በተመለሰ ጊዜ «በእኔ ቦታ የተካችሁት ነገር ምንኛ ከፋ! የጌታችሁን ትዕዛዝ ተቻኮላችሁን?» አላቸውና ሰሌዳዎቹንም ጣላቸው። የወንድሙን የራስ ጸጉር ወደ እርሱ እየጎተተው ያዘ:: ወንድሙም፡- «የእናቴ ልጅ ሆይ! ህዝቦቹ ናቁኝ ሊገድሉኝም ተቃረቡ:: ስለዚህ በእኔ ጠላቶችን አታስደስትብኝ። ከአመጸኞች ህዝቦችም ጋር አታድርገኝ።» አለው።

7:151

قَالَ رَبِّ ٱغۡفِرۡ لِي وَلِأَخِي وَأَدۡخِلۡنَا فِي رَحۡمَتِكَۖ وَأَنتَ أَرۡحَمُ ٱلرَّـٰحِمِينَ ﴿151﴾

Transliteration: Qala rabbi ighfir lee waliakhee waadkhilna fee rahmatika waanta arhamu alrrahimeena

Translation: 151. ሙሳም፡- «ጌታዬ ሆይ! ለኔም ለወንድሜም ማረን:: በእዝነትህ ውስጥም አስገባን። አንተም ከአዛኞቹ ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህና።» አለ::

7:152

إِنَّ ٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ ٱلۡعِجۡلَ سَيَنَالُهُمۡ غَضَبٞ مِّن رَّبِّهِمۡ وَذِلَّةٞ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۚ وَكَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُفۡتَرِينَ ﴿152﴾

Transliteration: Inna allatheena ittakhathoo alAAijla sayanaluhum ghadabun min rabbihim wathillatun fee alhayati alddunya wakathalika najzee almuftareena

Translation: 152. እነዚያ ወይፈኑን አምላክ ያደረጉት ሰዎች ከጌታቸው ዘንድ ቁጣ በቅርቢቱም ህይወት ውርደት ያገኛቸዋል:: ቀጣፊዎችን ልክ እንዲዚሁ እንቀጣለን::

7:153

وَٱلَّذِينَ عَمِلُواْ ٱلسَّيِّـَٔاتِ ثُمَّ تَابُواْ مِنۢ بَعۡدِهَا وَءَامَنُوٓاْ إِنَّ رَبَّكَ مِنۢ بَعۡدِهَا لَغَفُورٞ رَّحِيمٞ ﴿153﴾

Transliteration: Waallatheena AAamiloo alssayyiati thumma taboo min baAAdiha waamanoo inna rabbaka min baAAdiha laghafoorun raheemun

Translation: 153. እነዚያም ኃጢአቶችን የሠሩ ከዚያም በኋላ የተጸጸቱና በአላህ ያመኑ ጌታህ ከእርሷ በኋላ መሀሪና አዛኝ ነው:: (ጸጸታቸውን ይቀበላቸዋል)::

7:154

وَلَمَّا سَكَتَ عَن مُّوسَى ٱلۡغَضَبُ أَخَذَ ٱلۡأَلۡوَاحَۖ وَفِي نُسۡخَتِهَا هُدٗى وَرَحۡمَةٞ لِّلَّذِينَ هُمۡ لِرَبِّهِمۡ يَرۡهَبُونَ ﴿154﴾

Transliteration: Walamma sakata AAan moosa alghadabu akhatha alalwaha wafee nuskhatiha hudan warahmatun lillatheena hum lirabbihim yarhaboona

Translation: 154. ሙሳም ቁጣው በበረደ ጊዜ ሰሌዳዎቹን አነሳቸው:: በግልባጫቸውም ውስጥ ለእነዚያ እነርሱ ጌታቸውን ለሚፈሩት ሰዎች ሁሉ መምሪያና እዝነት አለባቸው::

7:155

وَٱخۡتَارَ مُوسَىٰ قَوۡمَهُۥ سَبۡعِينَ رَجُلٗا لِّمِيقَٰتِنَاۖ فَلَمَّآ أَخَذَتۡهُمُ ٱلرَّجۡفَةُ قَالَ رَبِّ لَوۡ شِئۡتَ أَهۡلَكۡتَهُم مِّن قَبۡلُ وَإِيَّـٰيَۖ أَتُهۡلِكُنَا بِمَا فَعَلَ ٱلسُّفَهَآءُ مِنَّآۖ إِنۡ هِيَ إِلَّا فِتۡنَتُكَ تُضِلُّ بِهَا مَن تَشَآءُ وَتَهۡدِي مَن تَشَآءُۖ أَنتَ وَلِيُّنَا فَٱغۡفِرۡ لَنَا وَٱرۡحَمۡنَاۖ وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلۡغَٰفِرِينَ ﴿155﴾

Transliteration: Waikhtara moosa qawmahu sabAAeena rajulan limeeqatina falamma akhathathumu alrrajfatu qala rabbi law shita ahlaktahum min qablu waiyyaya atuhlikuna bima faAAala alssufahao minna in hiya illa fitnatuka tudillu biha man tashao watahdee man tashao anta waliyyuna faighfir lana wairhamna waanta khayru alghafireena

Translation: 155. ሙሳም ከህዝቦቹ መካከል ለቀጠሯችን ሰባ ሰዎችን መረጠ:: ከዚያ ብርቱ የምድር እንቅጥቃጤ በደረሰባቸው ጊዜ ሙሳ አለ፡- «ጌታዬ ሆይ! ብትፈልግ ኖሮ ከአሁን በፊት ባጠፋሀቸው ነበር:: እኔንም ባጠፋኸኝ ነበር:: ከእኛ መሀከል ቂሎቹ በሠሩት ጥፋት ታጠፋናለህን? ፈተናይቱ የአንተ ፈተና እንጂ ሌላ አይደለችም:: በእርሷ የምትሻውን ታሳስታለህ። የምትሻውንም ታቀናለህ:: አንተ ረዳታችን ነህና:: ለእኛ ምህረት አድርግልን። እዘንልንም:: አንተ ከመሀሪዎች ሁሉ በላጭ ነህና::

7:156

وَٱكۡتُبۡ لَنَا فِي هَٰذِهِ ٱلدُّنۡيَا حَسَنَةٗ وَفِي ٱلۡأٓخِرَةِ إِنَّا هُدۡنَآ إِلَيۡكَۚ قَالَ عَذَابِيٓ أُصِيبُ بِهِۦ مَنۡ أَشَآءُۖ وَرَحۡمَتِي وَسِعَتۡ كُلَّ شَيۡءٖۚ فَسَأَكۡتُبُهَا لِلَّذِينَ يَتَّقُونَ وَيُؤۡتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَٱلَّذِينَ هُم بِـَٔايَٰتِنَا يُؤۡمِنُونَ ﴿156﴾

Transliteration: Waoktub lana fee hathihi alddunya hasanatan wafee alakhirati inna hudna ilayka qala AAathabee oseebu bihi man ashao warahmatee wasiAAat kulla shayin fasaaktubuha lillatheena yattaqoona wayutoona alzzakata waallatheena hum biayatina yuminoona

Translation: 156. «ጌታችን ሆይ! ለእኛ በዚች በቅርቢቱ ዓለም መልካሟን በመጨረሻይቱም ዓለም መልካሟን ጻፍልን:: እኛ ወደ አንተ ተመልሰናል።» (ሲል ሙሳ ጌታውን ለመነ):: አላህም አለ: «ቅጣቴ በእርሱ ልቀጣው የምፈልገውን ሰው እቀጣበታለሁ:: ችሮታዬ ከሁሉም ነገር የሰፋ ነው:: ለእነዚያ ለሚጠነቀቁ ዘካንም ለሚሰጡ ለእነዚያም በአናቅጻችን ለሚያምኑ ሁሉ በእርግጥ እጽፈዋለሁ::»

7:157

ٱلَّذِينَ يَتَّبِعُونَ ٱلرَّسُولَ ٱلنَّبِيَّ ٱلۡأُمِّيَّ ٱلَّذِي يَجِدُونَهُۥ مَكۡتُوبًا عِندَهُمۡ فِي ٱلتَّوۡرَىٰةِ وَٱلۡإِنجِيلِ يَأۡمُرُهُم بِٱلۡمَعۡرُوفِ وَيَنۡهَىٰهُمۡ عَنِ ٱلۡمُنكَرِ وَيُحِلُّ لَهُمُ ٱلطَّيِّبَٰتِ وَيُحَرِّمُ عَلَيۡهِمُ ٱلۡخَبَـٰٓئِثَ وَيَضَعُ عَنۡهُمۡ إِصۡرَهُمۡ وَٱلۡأَغۡلَٰلَ ٱلَّتِي كَانَتۡ عَلَيۡهِمۡۚ فَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ بِهِۦ وَعَزَّرُوهُ وَنَصَرُوهُ وَٱتَّبَعُواْ ٱلنُّورَ ٱلَّذِيٓ أُنزِلَ مَعَهُۥٓ أُوْلَـٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ ﴿157﴾

Transliteration: Allatheena yattabiAAoona alrrasoola alnnabiyya alommiyya allathee yajidoonahu maktooban AAindahum fee alttawrati waalinjeeli yamuruhum bialmaAAroofi wayanhahum AAani almunkari wayuhillu lahumu alttayyibati wayuharrimu AAalayhimu alkhabaitha wayadaAAu AAanhum israhum waalaghlala allatee kanat AAalayhim faallatheena amanoo bihi waAAazzaroohu wanasaroohu waittabaAAoo alnnoora allathee onzila maAAahu olaika humu almuflihoona

Translation: 157. ለእነዚያ ያንን እነርሱ ዘንድ በተውራትና በኢንጂል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብን መልዕክተኛ የሚከተሉ ለሆኑ (ሁሉ በእርግጥ እጽፋታለሁ):: በበጎ ሥራ ያዛቸዋል:: ከክፉም ነገር ይከለክላቸዋል:: መልካም ነገሮችንም ለእነርሱ ይፈቅድላቸዋል:: መጥፎ ነገሮችንም በነሱ ላይ እርም ያደርግባቸዋል:: ከእነርሱም ላይ ሸክማቸውንና እነዚያንም በእነርሱ ላይ የነበሩትን እንደ እንዛዝላ ይከብዱ የነበሩ ከባድ ህግጋትን ያነሳላቸዋል:: እነዚያ በእርሱ ያመኑ፤ ያከበሩት፤ የረዱትና ያንን ከርሱ ጋር የተወረደውን ብርሃን የተከተሉ ሁሉ እነዚያ እነርሱ ከቅጣት የሚድኑ ናቸው::

7:158

قُلۡ يَـٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنِّي رَسُولُ ٱللَّهِ إِلَيۡكُمۡ جَمِيعًا ٱلَّذِي لَهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ يُحۡيِۦ وَيُمِيتُۖ فَـَٔامِنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِ ٱلنَّبِيِّ ٱلۡأُمِّيِّ ٱلَّذِي يُؤۡمِنُ بِٱللَّهِ وَكَلِمَٰتِهِۦ وَٱتَّبِعُوهُ لَعَلَّكُمۡ تَهۡتَدُونَ ﴿158﴾

Transliteration: Qul ya ayyuha alnnasu innee rasoolu Allahi ilaykum jameeAAan allathee lahu mulku alssamawati waalardi la ilaha illa huwa yuhyee wayumeetu faaminoo biAllahi warasoolihi alnnabiyyi alommiyyi allathee yuminu biAllahi wakalimatihi waittabiAAoohu laAAallakum tahtadoona

Translation: 158. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎች ሆይ! እኔ ወደ እናንተ ወደ ሁላችሁም የአላህ መልዕክተኛ ነኝ:: እርሱም ያ የሰማያትና የምድር ንግስና ለእርሱ ብቻ የሆነ ነው:: እርሱ እንጂ ሌላ አምላክ የለም:: ህያው ያደርጋል:: ይገድላልም:: በአላህ በዚያም በአላህና በቃላቶቹ በሚያምነው የማይጽፍ የማያነብ በሆነው መልዕክተኛውም እመኑ:: ወደ ቅኑ መንገድ ትመሩ ዘንድም ተከተሉት።» በላቸው::

7:159

وَمِن قَوۡمِ مُوسَىٰٓ أُمَّةٞ يَهۡدُونَ بِٱلۡحَقِّ وَبِهِۦ يَعۡدِلُونَ ﴿159﴾

Transliteration: Wamin qawmi moosa ommatun yahdoona bialhaqqi wabihi yaAAdiloona

Translation: 159. ከሙሳ ህዝቦች መካከል በእውነት የሚመሩና በእውነት ፍርድን የሚያስተካከሉ ቡድኖችም አሉ::

7:160

وَقَطَّعۡنَٰهُمُ ٱثۡنَتَيۡ عَشۡرَةَ أَسۡبَاطًا أُمَمٗاۚ وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ إِذِ ٱسۡتَسۡقَىٰهُ قَوۡمُهُۥٓ أَنِ ٱضۡرِب بِّعَصَاكَ ٱلۡحَجَرَۖ فَٱنۢبَجَسَتۡ مِنۡهُ ٱثۡنَتَا عَشۡرَةَ عَيۡنٗاۖ قَدۡ عَلِمَ كُلُّ أُنَاسٖ مَّشۡرَبَهُمۡۚ وَظَلَّلۡنَا عَلَيۡهِمُ ٱلۡغَمَٰمَ وَأَنزَلۡنَا عَلَيۡهِمُ ٱلۡمَنَّ وَٱلسَّلۡوَىٰۖ كُلُواْ مِن طَيِّبَٰتِ مَا رَزَقۡنَٰكُمۡۚ وَمَا ظَلَمُونَا وَلَٰكِن كَانُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ ﴿160﴾

Transliteration: WaqattaAAnahumu ithnatay AAashrata asbatan omaman waawhayna ila moosa ithi istasqahu qawmuhu ani idrib biAAasaka alhajara fainbajasat minhu ithnata AAashrata AAaynan qad AAalima kullu onasin mashrabahum wathallalna AAalayhimu alghamama waanzalna AAalayhimu almanna waalssalwa kuloo min tayyibati ma razaqnakum wama thalamoona walakin kanoo anfusahum yathlimoona

Translation: 160. የሙሳን ህዝቦች አስራ ሁለት ነገዶች አድርገን ከፋፈልናቸው:: ወደ ሙሳም ወገኖቹ ውሃን በፈለጉበት ጊዜ ድንጋዩን በበትርህ ምታው ስንል ላክን:: (መታዉም) አስራ ሁለት ምንጮች ፈለቁ:: ሰዎቹ ሁሉ መጠጫቸውን በእርግጥ አወቁ:: በእነርሱም ላይ ዳመናን አጠለልን:: በእነርሱም ላይ "መንን" እና ድርጭትን አወረድን:: «ከሰጠናችሁም መልካም ሲሳይ ብሉ።» አልን:: ጸጋዎቻችንን በመካዳቸው አልበደሉንም:: ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ህዝቦች ነበሩ::

7:161

وَإِذۡ قِيلَ لَهُمُ ٱسۡكُنُواْ هَٰذِهِ ٱلۡقَرۡيَةَ وَكُلُواْ مِنۡهَا حَيۡثُ شِئۡتُمۡ وَقُولُواْ حِطَّةٞ وَٱدۡخُلُواْ ٱلۡبَابَ سُجَّدٗا نَّغۡفِرۡ لَكُمۡ خَطِيٓـَٰٔتِكُمۡۚ سَنَزِيدُ ٱلۡمُحۡسِنِينَ ﴿161﴾

Transliteration: Waith qeela lahumu oskunoo hathihi alqaryata wakuloo minha haythu shitum waqooloo hittatun waodkhuloo albaba sujjadan naghfir lakum khateeatikum sanazeedu almuhsineena

Translation: 161. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለነርሱም «በዚች ከተማ ተቀመጡ:: ከእርሷም በፈለጋችሁት ስፍራ ብሉ:: ‹የምንፈልገው የኃጢታችንን መርገፍ ብቻ ነው።› በሉም:: የከተማይቱን በር አጎንብሳችሁ ግቡ ኃጢአቶቻችሁን ለእናንተ እንምራለንና:: በጎ ለሠሩት ሰዎች በእርግጥ እንጨምራለን።» ባልን ጊዜ የሆነውን አስታውስ።

7:162

فَبَدَّلَ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ مِنۡهُمۡ قَوۡلًا غَيۡرَ ٱلَّذِي قِيلَ لَهُمۡ فَأَرۡسَلۡنَا عَلَيۡهِمۡ رِجۡزٗا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ بِمَا كَانُواْ يَظۡلِمُونَ ﴿162﴾

Transliteration: Fabaddala allatheena thalamoo minhum qawlan ghayra allathee qeela lahum faarsalna AAalayhim rijzan mina alssamai bima kanoo yathlimoona

Translation: 162. ከእነርሱም ውስጥ እነዚያ ራሳቸውን የበደሉ ሰዎች ከዚያ ለእነርሱ ከተባለው ሌላ የሆነን ቃል ለወጡ:: በእነርሱም ላይ ይበድሉ በነበሩት በደል ምክንያት መአትን ከሰማይ ላክንባቸው::

7:163

وَسۡـَٔلۡهُمۡ عَنِ ٱلۡقَرۡيَةِ ٱلَّتِي كَانَتۡ حَاضِرَةَ ٱلۡبَحۡرِ إِذۡ يَعۡدُونَ فِي ٱلسَّبۡتِ إِذۡ تَأۡتِيهِمۡ حِيتَانُهُمۡ يَوۡمَ سَبۡتِهِمۡ شُرَّعٗا وَيَوۡمَ لَا يَسۡبِتُونَ لَا تَأۡتِيهِمۡۚ كَذَٰلِكَ نَبۡلُوهُم بِمَا كَانُواْ يَفۡسُقُونَ ﴿163﴾

Transliteration: Waisalhum AAani alqaryati allatee kanat hadirata albahri ith yaAAdoona fee alssabti ith tateehim heetanuhum yawma sabtihim shurraAAan wayawma la yasbitoona la tateehim kathalika nabloohum bima kanoo yafsuqoona

Translation: 163. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚያም በባህሩ ዳርቻ ከነበረችው ከተማ በቅዳሜ ቀን ወሰን ባለፉ ጊዜ በሰንበታቸው ቀን አሳዎቻቸው የተከማቹ ሆነው በሚመጡላቸው ጊዜ የሆነውን ጠይቃቸው:: ሰንበትንም በማያከብሩበት (በሌላው) ቀን አይመጡላቸዉም:: ልክ እንደዚሁ በአመፃቸው ምክንያት እንሞክራቸዋለን::

7:164

وَإِذۡ قَالَتۡ أُمَّةٞ مِّنۡهُمۡ لِمَ تَعِظُونَ قَوۡمًا ٱللَّهُ مُهۡلِكُهُمۡ أَوۡ مُعَذِّبُهُمۡ عَذَابٗا شَدِيدٗاۖ قَالُواْ مَعۡذِرَةً إِلَىٰ رَبِّكُمۡ وَلَعَلَّهُمۡ يَتَّقُونَ ﴿164﴾

Transliteration: Waith qalat ommatun minhum lima taAAithoona qawman Allahu muhlikuhum aw muAAaththibuhum AAathaban shadeedan qaloo maAAthiratan ila rabbikum walaAAallahum yattaqoona

Translation: 164. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ከፊሎቹ ህዝቦች «አላህ አጥፊያቸው ወይም በብርቱ ቅጣት ቀጫቸው የሆኑትን ህዝቦች ለምን ትገስጻላችሁ?» ባሉ ጊዜ ገሳጮቹም «በጌታችሁ ዘንድ በቂ ምክንያት እንዲሆንና እነርሱም ቢከለከሉ ብለን ነው።» ባሉበት ጊዜ የሆነውን አስታውስ::

7:165

فَلَمَّا نَسُواْ مَا ذُكِّرُواْ بِهِۦٓ أَنجَيۡنَا ٱلَّذِينَ يَنۡهَوۡنَ عَنِ ٱلسُّوٓءِ وَأَخَذۡنَا ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ بِعَذَابِۭ بَـِٔيسِۭ بِمَا كَانُواْ يَفۡسُقُونَ ﴿165﴾

Transliteration: Falamma nasoo ma thukkiroo bihi anjayna allatheena yanhawna AAani alssooi waakhathna allatheena thalamoo biAAathabin baeesin bima kanoo yafsuqoona

Translation: 165. የተገሰጹበትንም ነገር በተው ጊዜ እነዚያን ከክፉ የሚከለክሉትን ክፍሎች አዳንን:: እነዚያንም የበደሉትን ሰዎች ያምጹ በነበሩበት ምክንያት በብርቱ ቅጣት ቀጣናቸው::

7:166

فَلَمَّا عَتَوۡاْ عَن مَّا نُهُواْ عَنۡهُ قُلۡنَا لَهُمۡ كُونُواْ قِرَدَةً خَٰسِـِٔينَ ﴿166﴾

Transliteration: Falamma AAataw AAan ma nuhoo AAanhu qulna lahum koonoo qiradatan khasieena

Translation: 166. ከእርሱም ከተከለከሉት ነገር በኮሩ ጊዜ ለእነርሱ «ወራዶች ዝንጀሮዎች ሁኑ።» አልን:: (ሆኑም)::

7:167

وَإِذۡ تَأَذَّنَ رَبُّكَ لَيَبۡعَثَنَّ عَلَيۡهِمۡ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ مَن يَسُومُهُمۡ سُوٓءَ ٱلۡعَذَابِۗ إِنَّ رَبَّكَ لَسَرِيعُ ٱلۡعِقَابِ وَإِنَّهُۥ لَغَفُورٞ رَّحِيمٞ ﴿167﴾

Transliteration: Waith taaththana rabbuka layabAAathanna AAalayhim ila yawmi alqiyamati man yasoomuhum sooa alAAathabi inna rabbaka lasareeAAu alAAiqabi wainnahu laghafoorun raheemun

Translation: 167. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም እስከ ትንሳኤ ቀን ክፉ ቅጣትን የሚያቀምሳቸውን ወገን በነሱ ላይ በእርግጥ የሚልክ መሆኑን ባስታወቀ ጊዜ (የሆነውን አስታውሳቸው):: ጌታህ በእርግጥ ቅጣተ ፈጣን ነው:: እርሱም በእርግጥ እጅግ መሀሪና አዛኝ ነውና::

7:168

وَقَطَّعۡنَٰهُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ أُمَمٗاۖ مِّنۡهُمُ ٱلصَّـٰلِحُونَ وَمِنۡهُمۡ دُونَ ذَٰلِكَۖ وَبَلَوۡنَٰهُم بِٱلۡحَسَنَٰتِ وَٱلسَّيِّـَٔاتِ لَعَلَّهُمۡ يَرۡجِعُونَ ﴿168﴾

Transliteration: WaqattaAAnahum fee alardi omaman minhumu alssalihoona waminhum doona thalika wabalawnahum bialhasanati waalssayyiati laAAallahum yarjiAAoona

Translation: 168. (የኢስራኢልን ልጆችን) በምድር ላይ የተለያዩ ህዝቦች አድርገንም ከፋፈልናቸው:: ከእነርሱ መልካሞች አሉ:: ከእነርሱም ከዚያ ሌላ የሆኑ አሉ:: ይመለሱ ዘንድም በተድላዎችና በመከራዎቻች ሞከርናቸው::

7:169

فَخَلَفَ مِنۢ بَعۡدِهِمۡ خَلۡفٞ وَرِثُواْ ٱلۡكِتَٰبَ يَأۡخُذُونَ عَرَضَ هَٰذَا ٱلۡأَدۡنَىٰ وَيَقُولُونَ سَيُغۡفَرُ لَنَا وَإِن يَأۡتِهِمۡ عَرَضٞ مِّثۡلُهُۥ يَأۡخُذُوهُۚ أَلَمۡ يُؤۡخَذۡ عَلَيۡهِم مِّيثَٰقُ ٱلۡكِتَٰبِ أَن لَّا يَقُولُواْ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلۡحَقَّ وَدَرَسُواْ مَا فِيهِۗ وَٱلدَّارُ ٱلۡأٓخِرَةُ خَيۡرٞ لِّلَّذِينَ يَتَّقُونَۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ ﴿169﴾

Transliteration: Fakhalafa min baAAdihim khalfun warithoo alkitaba yakhuthoona AAarada hatha aladna wayaqooloona sayughfaru lana wain yatihim AAaradun mithluhu yakhuthoohu alam yukhath AAalayhim meethaqu alkitabi an la yaqooloo AAala Allahi illa alhaqqa wadarasoo ma feehi waalddaru alakhiratu khayrun lillatheena yattaqoona afala taAAqiloona

Translation: 169. ከኋላቸዉም መጽሐፉን የወረሱ መጥፎ ምትኮች በእነርሱ ቦታ ተተኩ:: የዚህም የቅርቡን ጠፊ ጥቅም ይይዛሉ:: ብጤዉም ጥቅም ቢመጣላቸው የሚይዙት ሲሆኑ «በሠራነው ለእኛ ምህረት ይደርግልናል።» ይላሉ:: በአላህ ላይ በእውነት በስተቀር እንዳይናገሩ በእነርሱ ላይ የመጽሐፉ ቃል ኪዳን አልተያዘባቸዉምን? በእርሱ ውስጥ ያለውንም አላነበቡምን? የመጨረሻይቱን አገር ለእነዚያ ጌታቸውን ለሚፈሩት ሰዎች ሁሉ በላጭ ናት:: አታውቁምን?

7:170

وَٱلَّذِينَ يُمَسِّكُونَ بِٱلۡكِتَٰبِ وَأَقَامُواْ ٱلصَّلَوٰةَ إِنَّا لَا نُضِيعُ أَجۡرَ ٱلۡمُصۡلِحِينَ ﴿170﴾

Transliteration: Waallatheena yumassikoona bialkitabi waaqamoo alssalata inna la nudeeAAu ajra almusliheena

Translation: 170. እነዚያም መጽሐፉን ጠብቀው የሚይዙ፤ ሶላትንም በደንቡ የሰገዱ ሁሉ (ምንዳቸውን እንከፍላቸዋለን):: እኛ የመልካም ሠሪዎችን ምንዳ አናጠፋምና::

7:171

وَإِذۡ نَتَقۡنَا ٱلۡجَبَلَ فَوۡقَهُمۡ كَأَنَّهُۥ ظُلَّةٞ وَظَنُّوٓاْ أَنَّهُۥ وَاقِعُۢ بِهِمۡ خُذُواْ مَآ ءَاتَيۡنَٰكُم بِقُوَّةٖ وَٱذۡكُرُواْ مَا فِيهِ لَعَلَّكُمۡ تَتَّقُونَ ﴿171﴾

Transliteration: Waith nataqna aljabala fawqahum kaannahu thullatun wathannoo annahu waqiAAun bihim khuthoo ma ataynakum biquwwatin waothkuroo ma feehi laAAallakum tattaqoona

Translation: 171. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጡርን ተራራ ነቅለን ከበላያቸው እንደ ጥላ ሆኖ ባነሳነውና እርሱም በእነርሱ ላይ ወዳቂ መሆኑን ባረጋገጡ ጊዜ የሆነውን( አስታውስ):: «የሰጠናችሁን በብርታት ያዙ:: ትጠነቀቁም ዘንድ በዉስጡ ያለውን ተገንዘቡ።» አልን::

7:172

وَإِذۡ أَخَذَ رَبُّكَ مِنۢ بَنِيٓ ءَادَمَ مِن ظُهُورِهِمۡ ذُرِّيَّتَهُمۡ وَأَشۡهَدَهُمۡ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمۡ أَلَسۡتُ بِرَبِّكُمۡۖ قَالُواْ بَلَىٰ شَهِدۡنَآۚ أَن تَقُولُواْ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ إِنَّا كُنَّا عَنۡ هَٰذَا غَٰفِلِينَ ﴿172﴾

Transliteration: Waith akhatha rabbuka min banee adama min thuhoorihim thurriyyatahum waashhadahum AAala anfusihim alastu birabbikum qaloo bala shahidna an taqooloo yawma alqiyamati inna kunna AAan hatha ghafileena

Translation: 172. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም ከአደም ልጆች ከጀርቦቻቸው ዘሮቻቸውን ባወጣና «ጌታችሁ አይደለሁምን?» ሲል በነፍሶቻቸው ላይ ባስመሰከራቸው ጊዜ (የሆነውን አስታውስ):: «ጌታችን ነህ መሰከርን» አሉ። በትንሳኤ ቀን «ከዚህ ቃል ኪዳን ዘንጊዎች ነበርን» እንዳትሉ።

7:173

أَوۡ تَقُولُوٓاْ إِنَّمَآ أَشۡرَكَ ءَابَآؤُنَا مِن قَبۡلُ وَكُنَّا ذُرِّيَّةٗ مِّنۢ بَعۡدِهِمۡۖ أَفَتُهۡلِكُنَا بِمَا فَعَلَ ٱلۡمُبۡطِلُونَ ﴿173﴾

Transliteration: Aw taqooloo innama ashraka abaona min qablu wakunna thurriyyatan min baAAdihim afatuhlikuna bima faAAala almubtiloona

Translation: 173. ወይም «ጣኦታትን ያጋሩት ከኛ በፊት የነበሩት አባቶቻችን ብቻ ናቸው:: እኛም ከእነርሱ በኋላ የሆንን ዘሮች ነበርን አጥፊዎቹ በሠሩት ጥፋት እኛን ታጠፋናለህን?» እንዳትሉ አስመሰከርናችሁ::

7:174

وَكَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ ٱلۡأٓيَٰتِ وَلَعَلَّهُمۡ يَرۡجِعُونَ ﴿174﴾

Transliteration: Wakathalika nufassilu alayati walaAAallahum yarjiAAoona

Translation: 174. ልክ እንደዚሁም (እንዲያስቡ) እንዲመለሱም አናቅጽን እናብራራለን::

7:175

وَٱتۡلُ عَلَيۡهِمۡ نَبَأَ ٱلَّذِيٓ ءَاتَيۡنَٰهُ ءَايَٰتِنَا فَٱنسَلَخَ مِنۡهَا فَأَتۡبَعَهُ ٱلشَّيۡطَٰنُ فَكَانَ مِنَ ٱلۡغَاوِينَ ﴿175﴾

Transliteration: Waotlu AAalayhim nabaa allathee ataynahu ayatina fainsalakha minha faatbaAAahu alshshaytanu fakana mina alghaweena

Translation: 175. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዚያን ተዓምራታችንን የሰጠነውንና ከዚያ እርሱም ከእርሷ የወጣውን ሰይጣንም ያስከተለውን በዚህም ምክንያት ከጠማሞቹ የሆነውን ሰው ወሬ በእነርሱ ላይ አንብብላቸው::

7:176

وَلَوۡ شِئۡنَا لَرَفَعۡنَٰهُ بِهَا وَلَٰكِنَّهُۥٓ أَخۡلَدَ إِلَى ٱلۡأَرۡضِ وَٱتَّبَعَ هَوَىٰهُۚ فَمَثَلُهُۥ كَمَثَلِ ٱلۡكَلۡبِ إِن تَحۡمِلۡ عَلَيۡهِ يَلۡهَثۡ أَوۡ تَتۡرُكۡهُ يَلۡهَثۚ ذَّـٰلِكَ مَثَلُ ٱلۡقَوۡمِ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَاۚ فَٱقۡصُصِ ٱلۡقَصَصَ لَعَلَّهُمۡ يَتَفَكَّرُونَ ﴿176﴾

Transliteration: Walaw shina larafaAAnahu biha walakinnahu akhlada ila alardi waittabaAAa hawahu famathaluhu kamathali alkalbi in tahmil AAalayhi yalhath aw tatrukhu yalhath thalika mathalu alqawmi allatheena kaththaboo biayatina faoqsusi alqasasa laAAallahum yatafakkaroona

Translation: 176. ብንፈልግ ኖሮ በእርሷ ከፍ ባደረግነው ነበር:: እርሱ ግን ወደ ምድር ተዘነበለ:: ፍላጎቱንም ተከተለ:: ብጤዉም ብታባርረዉም ባታባርረዉም ምላሱን አውጥቶ እንደሚያለከልክ ውሻ ነው:: ይህ የእነዚያ በአናቅጻችን ያስተባበሉት ህዝቦች ምሳሌ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያስተነትኑም ዘንድ ታሪኮችን ተርክላቸው::

7:177

سَآءَ مَثَلًا ٱلۡقَوۡمُ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَأَنفُسَهُمۡ كَانُواْ يَظۡلِمُونَ ﴿177﴾

Transliteration: Saa mathalan alqawmu allatheena kaththaboo biayatina waanfusahum kanoo yathlimoona

Translation: 177. የእነዚያ በአናቅጻችን ያስተባበሉትና ነፍሶቻቸውን ይበድሉ የነበሩት ሰዎች ምሳሌ ከፋ::

7:178

مَن يَهۡدِ ٱللَّهُ فَهُوَ ٱلۡمُهۡتَدِيۖ وَمَن يُضۡلِلۡ فَأُوْلَـٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡخَٰسِرُونَ ﴿178﴾

Transliteration: Man yahdi Allahu fahuwa almuhtadee waman yudlil faolaika humu alkhasiroona

Translation: 178. አላህ የሚያቀናው ሰው ሁሉ ቅን ማለት እርሱው ነው:: የሚያጠማቸዉም ሰዎች እነዚያ ከሳሪዎቹ ማለት እነርሱው ናቸው::

7:179

وَلَقَدۡ ذَرَأۡنَا لِجَهَنَّمَ كَثِيرٗا مِّنَ ٱلۡجِنِّ وَٱلۡإِنسِۖ لَهُمۡ قُلُوبٞ لَّا يَفۡقَهُونَ بِهَا وَلَهُمۡ أَعۡيُنٞ لَّا يُبۡصِرُونَ بِهَا وَلَهُمۡ ءَاذَانٞ لَّا يَسۡمَعُونَ بِهَآۚ أُوْلَـٰٓئِكَ كَٱلۡأَنۡعَٰمِ بَلۡ هُمۡ أَضَلُّۚ أُوْلَـٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡغَٰفِلُونَ ﴿179﴾

Transliteration: Walaqad tharana lijahannama katheeran mina aljinni waalinsi lahum quloobun la yafqahoona biha walahum aAAyunun la yubsiroona biha walahum athanun la yasmaAAoona biha olaika kaalanAAami bal hum adallu olaika humu alghafiloona

Translation: 179. ከአጋንንትም ሆነ ከሰዎች መካከል ብዙዎችን ለገሀነም በእርግጥ ፈጠርን:: ለእነርሱ የማያውቁባቸው ልቦች አሏቸው:: ለእነርሱም የማያዩባቸው ዓይኖች አሏቸው:: ለእነርሱም የማይሰሙባቸው ጆሮዎች አሏቸው:: እነዚያ እንደ እንስሳዎች ናቸው:: ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ህዝቦች ናቸው:: እነዚያ ዘንጊዎቹ እነርሱው ናቸው::

7:180

وَلِلَّهِ ٱلۡأَسۡمَآءُ ٱلۡحُسۡنَىٰ فَٱدۡعُوهُ بِهَاۖ وَذَرُواْ ٱلَّذِينَ يُلۡحِدُونَ فِيٓ أَسۡمَـٰٓئِهِۦۚ سَيُجۡزَوۡنَ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ ﴿180﴾

Transliteration: Walillahi alasmao alhusna faodAAoohu biha watharoo allatheena yulhidoona fee asmaihi sayujzawna ma kanoo yaAAmaloona

Translation: 180. ለአላህ መልካም ስሞች አሉት:: (ዱዓ ስታደርጉ) በእርሷ ጥሩት:: እነዚያን ስሞቹን የሚያጣምሙትን ክፍሎች ተዋቸው:: ይሠሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይመነዳሉ::

7:181

وَمِمَّنۡ خَلَقۡنَآ أُمَّةٞ يَهۡدُونَ بِٱلۡحَقِّ وَبِهِۦ يَعۡدِلُونَ ﴿181﴾

Transliteration: Wamimman khalaqna ommatun yahdoona bialhaqqi wabihi yaAAdiloona

Translation: 181. ከፈጠርናቸዉም መካከል በእውነት የሚመሩና በእውነት ፍርድን የሚያስተካክሉ ህዝቦችም አሉ::

7:182

وَٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا سَنَسۡتَدۡرِجُهُم مِّنۡ حَيۡثُ لَا يَعۡلَمُونَ ﴿182﴾

Transliteration: Waallatheena kaththaboo biayatina sanastadrijuhum min haythu la yaAAlamoona

Translation: 182. እነዚያን በአናቅጻችን ያስተባበሉትን ሰዎች ከማያውቁት ስፍራ ቀስ በቀስ እናዘናጋቸዋለን::

7:183

وَأُمۡلِي لَهُمۡۚ إِنَّ كَيۡدِي مَتِينٌ ﴿183﴾

Transliteration: Waomlee lahum inna kaydee mateenun

Translation: 183. ለእነርሱም ጊዜ እሰጣቸዋለሁ:: ጥበቤ ብርቱ ነውና::

7:184

أَوَلَمۡ يَتَفَكَّرُواْۗ مَا بِصَاحِبِهِم مِّن جِنَّةٍۚ إِنۡ هُوَ إِلَّا نَذِيرٞ مُّبِينٌ ﴿184﴾

Transliteration: Awalam yatafakkaroo ma bisahibihim min jinnatin in huwa illa natheerun mubeenun

Translation: 184. በነብያቸው በሙሐመድ ምንም እብደት የሌለበት መሆኑን አያስተውሉምን? እርሱ ግልጽ አስፈራሪ እንጂ ሌላ አይደለም::

7:185

أَوَلَمۡ يَنظُرُواْ فِي مَلَكُوتِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا خَلَقَ ٱللَّهُ مِن شَيۡءٖ وَأَنۡ عَسَىٰٓ أَن يَكُونَ قَدِ ٱقۡتَرَبَ أَجَلُهُمۡۖ فَبِأَيِّ حَدِيثِۭ بَعۡدَهُۥ يُؤۡمِنُونَ ﴿185﴾

Transliteration: Awalam yanthuroo fee malakooti alssamawati waalardi wama khalaqa Allahu min shayin waan AAasa an yakoona qadi iqtaraba ajaluhum fabiayyi hadeethin baAAdahu yuminoona

Translation: 185. በሰማያትና በምድር ግዛት ውስጥ ከማንኛዉም ነገር አላህ በፈጠራቸው ሁሉ የሞት ጊዜያቸዉም በእርግጥ መቅረቡ የሚፈራ መሆኑን አያስተውሉምን? ለመሆኑ እነርሱ ከቁርኣን ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ::

7:186

مَن يُضۡلِلِ ٱللَّهُ فَلَا هَادِيَ لَهُۥۚ وَيَذَرُهُمۡ فِي طُغۡيَٰنِهِمۡ يَعۡمَهُونَ ﴿186﴾

Transliteration: Man yudlili Allahu fala hadiya lahu wayatharuhum fee tughyanihim yaAAmahoona

Translation: 186. አላህ የሚያጠመውን ለእርሱ ምንም አቅኝ የለዉም:: በጥመታቸዉም ውስጥ የሚዋልሉ ሲሆኑ ይተዋቸዋል::

7:187

يَسۡـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلسَّاعَةِ أَيَّانَ مُرۡسَىٰهَاۖ قُلۡ إِنَّمَا عِلۡمُهَا عِندَ رَبِّيۖ لَا يُجَلِّيهَا لِوَقۡتِهَآ إِلَّا هُوَۚ ثَقُلَتۡ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ لَا تَأۡتِيكُمۡ إِلَّا بَغۡتَةٗۗ يَسۡـَٔلُونَكَ كَأَنَّكَ حَفِيٌّ عَنۡهَاۖ قُلۡ إِنَّمَا عِلۡمُهَا عِندَ ٱللَّهِ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ ﴿187﴾

Transliteration: Yasaloonaka AAani alssaAAati ayyana mursaha qul innama AAilmuha AAinda rabbee la yujalleeha liwaqtiha illa huwa thaqulat fee alssamawati waalardi la tateekum illa baghtatan yasaloonaka kaannaka hafiyyun AAanha qul innama AAilmuha AAinda Allahi walakinna akthara alnnasi la yaAAlamoona

Translation: 187. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ትንሳኤ መቼ እንደምትመጣ ይጠይቁሃል:: «እውቀቷ በጌታዬ ዘንድ ብቻ ነው:: በመከሰቻዋ ጊዜም እርሱ እንጂ ሌላ አይገልጽላችሁም:: በሰማያትና በምድርም ከበደች:: በድንገት ቢሆን እንጂ አትመጣባችሁም።» በላቸው:: ስለ እርሷ በደንብ እንደተረዳ አድርገው ይጠይቁሃል:: «እውቀቷ ግን አላህ ዘንድ ብቻ ነው:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች ይህን ነገር ጠንቅቀው አያውቁም።» በላቸው።

7:188

قُل لَّآ أَمۡلِكُ لِنَفۡسِي نَفۡعٗا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُۚ وَلَوۡ كُنتُ أَعۡلَمُ ٱلۡغَيۡبَ لَٱسۡتَكۡثَرۡتُ مِنَ ٱلۡخَيۡرِ وَمَا مَسَّنِيَ ٱلسُّوٓءُۚ إِنۡ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٞ وَبَشِيرٞ لِّقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ ﴿188﴾

Transliteration: Qul la amliku linafsee nafAAan wala darran illa ma shaa Allahu walaw kuntu aAAlamu alghayba laistakthartu mina alkhayri wama massaniya alssooo in ana illa natheerun wabasheerun liqawmin yuminoona

Translation: 188. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ የፈለገዉን በስተቀር ለራሴ ጥቅምንም ሆነ ጉዳት ማምጣት አልችልም:: የሩቅን ሚስጥር የማውቅ በነበርኩ ኖሮ ከመልካም ነገር ሁሉ ባበዛሁና ክፉም ነገር ባልነካኝ ነበር:: እኔም ለሚያምኑ ህዝቦች ሁሉ አስፈራሪና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም።» በላቸው::

7:189

هُوَ ٱلَّذِي خَلَقَكُم مِّن نَّفۡسٖ وَٰحِدَةٖ وَجَعَلَ مِنۡهَا زَوۡجَهَا لِيَسۡكُنَ إِلَيۡهَاۖ فَلَمَّا تَغَشَّىٰهَا حَمَلَتۡ حَمۡلًا خَفِيفٗا فَمَرَّتۡ بِهِۦۖ فَلَمَّآ أَثۡقَلَت دَّعَوَا ٱللَّهَ رَبَّهُمَا لَئِنۡ ءَاتَيۡتَنَا صَٰلِحٗا لَّنَكُونَنَّ مِنَ ٱلشَّـٰكِرِينَ ﴿189﴾

Transliteration: Huwa allathee khalaqakum min nafsin wahidatin wajaAAala minha zawjaha liyaskuna ilayha falamma taghashshaha hamalat hamlan khafeefan famarrat bihi falamma athqalat daAAawa Allaha rabbahuma lain ataytana salihan lanakoonanna mina alshshakireena

Translation: 189. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ ያ ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁና ከእርሷም መቀናጆዋን ወደ እርሷ ይረካ ዘንድ የፈጠረ ነው:: በተገናኛትም ጊዜ ቀላልን እርግዝና አረገዘች:: ጽንሱን ይዛው ሄደች:: ባረገዘችም ጊዜ «ደግን ልጅ ብትሰጠን በእርግጥ ከአመስጋኞቹ እንሆናለን።» ሲሉ ጌታቸውን አላህን ለመኑ::

7:190

فَلَمَّآ ءَاتَىٰهُمَا صَٰلِحٗا جَعَلَا لَهُۥ شُرَكَآءَ فِيمَآ ءَاتَىٰهُمَاۚ فَتَعَٰلَى ٱللَّهُ عَمَّا يُشۡرِكُونَ ﴿190﴾

Transliteration: Falamma atahuma salihan jaAAala lahu shurakaa feema atahuma fataAAala Allahu AAamma yushrikoona

Translation: 190. መልካምን ልጅ በሰጣቸዉም ጊዜ በሰጣቸው ልጅ (ስም) ለእርሱ ተጋሪዎችን አደረጉለት:: አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ላቀ::

7:191

أَيُشۡرِكُونَ مَا لَا يَخۡلُقُ شَيۡـٔٗا وَهُمۡ يُخۡلَقُونَ ﴿191﴾

Transliteration: Ayushrikoona ma la yakhluqu shayan wahum yukhlaqoona

Translation: 191. ምንንም የማይፈጥሩትንና እነርሱ ራሳቸው የሚፈጠሩትን ፍጡሮች በአላህ ያጋራሉን?

7:192

وَلَا يَسۡتَطِيعُونَ لَهُمۡ نَصۡرٗا وَلَآ أَنفُسَهُمۡ يَنصُرُونَ ﴿192﴾

Transliteration: Wala yastateeAAoona lahum nasran wala anfusahum yansuroona

Translation: 192. ለነርሱም መርዳትንም የማይችሉትን፤ ነፍሶቻቸውንም እንኳን የማይረዱትን ያጋራሉን?

7:193

وَإِن تَدۡعُوهُمۡ إِلَى ٱلۡهُدَىٰ لَا يَتَّبِعُوكُمۡۚ سَوَآءٌ عَلَيۡكُمۡ أَدَعَوۡتُمُوهُمۡ أَمۡ أَنتُمۡ صَٰمِتُونَ ﴿193﴾

Transliteration: Wain tadAAoohum ila alhuda la yattabiAAookum sawaon AAalaykum adaAAawtumoohum am antum samitoona

Translation: 193. ወደ ቅን መንገድ ብትጠሯቸዉም አይከተሏችሁም:: ብትጠሯቸው ወይም ዝምተኞች ብትሆኑም በእናንተ ላይ እኩል ነው::

7:194

إِنَّ ٱلَّذِينَ تَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ عِبَادٌ أَمۡثَالُكُمۡۖ فَٱدۡعُوهُمۡ فَلۡيَسۡتَجِيبُواْ لَكُمۡ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ ﴿194﴾

Transliteration: Inna allatheena tadAAoona min dooni Allahi AAibadun amthalukum faodAAoohum falyastajeeboo lakum in kuntum sadiqeena

Translation: 194. (ከሀዲያን ሆይ!) እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ጣኦቶች ብጤዎቻችሁ የአላህ ባሮች ናቸው:: እውነተኞች ከሆናችሁ እስቲ ጥሯቸውና ለእናንተ ይመልሱላችሁ:: (መመለስ አይችሉም።)

7:195

أَلَهُمۡ أَرۡجُلٞ يَمۡشُونَ بِهَآۖ أَمۡ لَهُمۡ أَيۡدٖ يَبۡطِشُونَ بِهَآۖ أَمۡ لَهُمۡ أَعۡيُنٞ يُبۡصِرُونَ بِهَآۖ أَمۡ لَهُمۡ ءَاذَانٞ يَسۡمَعُونَ بِهَاۗ قُلِ ٱدۡعُواْ شُرَكَآءَكُمۡ ثُمَّ كِيدُونِ فَلَا تُنظِرُونِ ﴿195﴾

Transliteration: Alahum arjulun yamshoona biha am lahum aydin yabtishoona biha am lahum aAAyunun yubsiroona biha am lahum athanun yasmaAAoona biha quli odAAoo shurakaakum thumma keedooni fala tunthirooni

Translation: 195. ለእነርሱ የሚሄዱባቸው እግሮች አሏቸውን? ወይስ የሚጨብጡባቸው እጆች አሏቸውን? ወይንስ እነርሱ የሚያዩባቸው አይኖች አሏቸውን? ወይንስ እነርሱ የሚሰሙባቸው ጆሮዎች አሏቸዉን? (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያጋራችኃቸውን ጥሩና ከዚያም አሲሩብኝ:: ጊዜም አትስጡኝ።» በላቸው::

7:196

إِنَّ وَلِـِّۧيَ ٱللَّهُ ٱلَّذِي نَزَّلَ ٱلۡكِتَٰبَۖ وَهُوَ يَتَوَلَّى ٱلصَّـٰلِحِينَ ﴿196﴾

Transliteration: Inna waliyyiya Allahu allathee nazzala alkitaba wahuwa yatawalla alssaliheena

Translation: 196. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ በላቸው) «የእኔ ረዳቴ ያ ቁርኣንን ያወረደልኝ አላህ ብቻ ነው:: እርሱ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ ይረዳልና።

7:197

وَٱلَّذِينَ تَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا يَسۡتَطِيعُونَ نَصۡرَكُمۡ وَلَآ أَنفُسَهُمۡ يَنصُرُونَ ﴿197﴾

Transliteration: Waallatheena tadAAoona min doonihi la yastateeAAoona nasrakum wala anfusahum yansuroona

Translation: 197. (አጋሪዎች ሆይ! ) «እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ጣኦታት ሁሉ ሊረዷችሁ ፍጽሞ አይችሉም:: ነፍሶቻቸውንም እንኳን አይረዱም።»

7:198

وَإِن تَدۡعُوهُمۡ إِلَى ٱلۡهُدَىٰ لَا يَسۡمَعُواْۖ وَتَرَىٰهُمۡ يَنظُرُونَ إِلَيۡكَ وَهُمۡ لَا يُبۡصِرُونَ ﴿198﴾

Transliteration: Wain tadAAoohum ila alhuda la yasmaAAoo watarahum yanthuroona ilayka wahum la yubsiroona

Translation: 198. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ ቀናው መንገድ እንዲመሩ ብትጠሯቸው አይሰሙም። እነርሱንም የማያዩ ሲሆኑ ወደ አንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ::

7:199

خُذِ ٱلۡعَفۡوَ وَأۡمُرۡ بِٱلۡعُرۡفِ وَأَعۡرِضۡ عَنِ ٱلۡجَٰهِلِينَ ﴿199﴾

Transliteration: Khuthi alAAafwa wamur bialAAurfi waaAArid AAani aljahileena

Translation: 199. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይቅርባይነትን ያዝ:: በመልካምም እዘዝ:: ባለጌዎቹንም ተዋቸው::

7:200

وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ ٱلشَّيۡطَٰنِ نَزۡغٞ فَٱسۡتَعِذۡ بِٱللَّهِۚ إِنَّهُۥ سَمِيعٌ عَلِيمٌ ﴿200﴾

Transliteration: Waimma yanzaghannaka mina alshshaytani nazghun faistaAAith biAllahi innahu sameeAAun AAaleemun

Translation: 200. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሰይጣን የተንኮል ጉትጎታ ቢያጋጥምህ በአላህ ብቻ ተጠበቅ:: አላህ ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነው::

7:201

إِنَّ ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوۡاْ إِذَا مَسَّهُمۡ طَـٰٓئِفٞ مِّنَ ٱلشَّيۡطَٰنِ تَذَكَّرُواْ فَإِذَا هُم مُّبۡصِرُونَ ﴿201﴾

Transliteration: Inna allatheena ittaqaw itha massahum taifun mina alshshaytani tathakkaroo faitha hum mubsiroona

Translation: 201.እነዚያ የተጠነቀቁት ከሰይጣን የኾነ ዘዋሪ በነካቸው ጊዜ (ጌታቸውን) ይገነዘባሉ:: ወዲያዉም እነርሱ ተመልካቾች ይሆናሉ:

7:202

وَإِخۡوَٰنُهُمۡ يَمُدُّونَهُمۡ فِي ٱلۡغَيِّ ثُمَّ لَا يُقۡصِرُونَ ﴿202﴾

Transliteration: Waikhwanuhum yamuddoonahum fee alghayyi thumma la yuqsiroona

Translation: 202. ወንድሞቻቸዉም ጥመትን ይጨምሩላቸዋል:: ከዚያም እነርሱ አይገቱም::

7:203

وَإِذَا لَمۡ تَأۡتِهِم بِـَٔايَةٖ قَالُواْ لَوۡلَا ٱجۡتَبَيۡتَهَاۚ قُلۡ إِنَّمَآ أَتَّبِعُ مَا يُوحَىٰٓ إِلَيَّ مِن رَّبِّيۚ هَٰذَا بَصَآئِرُ مِن رَّبِّكُمۡ وَهُدٗى وَرَحۡمَةٞ لِّقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ ﴿203﴾

Transliteration: Waitha lam tatihim biayatin qaloo lawla ijtabaytaha qul innama attabiAAu ma yooha ilayya min rabbee hatha basairu min rabbikum wahudan warahmatun liqawmin yuminoona

Translation: 203. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተዓምርም ባላመጣህላቸው ጊዜ «በራስህ ለምን አትመርጣትም።» ይላሉ:: «ከጌታዬ ወደ እኔ የተወረደውን ብቻ ነው የምከተለው:: ይህ ቁርኣን ከጌታችሁ የተወረደ ሲሆን ለሚያምኑ ህዝቦች ሁሉ መረጃ፤ መመሪያና እዝነት ነው።» በላቸው::

7:204

وَإِذَا قُرِئَ ٱلۡقُرۡءَانُ فَٱسۡتَمِعُواْ لَهُۥ وَأَنصِتُواْ لَعَلَّكُمۡ تُرۡحَمُونَ ﴿204﴾

Transliteration: Waitha quria alquranu faistamiAAoo lahu waansitoo laAAallakum turhamoona

Translation: 204. (ሙስሊሞች ሆይ!) ቁርኣን በሚነበብበት ጊዜ እርሱን በጥሞና አድምጡ:: ጸጥም በሉ። ይታዘንላችኋልና።

7:205

وَٱذۡكُر رَّبَّكَ فِي نَفۡسِكَ تَضَرُّعٗا وَخِيفَةٗ وَدُونَ ٱلۡجَهۡرِ مِنَ ٱلۡقَوۡلِ بِٱلۡغُدُوِّ وَٱلۡأٓصَالِ وَلَا تَكُن مِّنَ ٱلۡغَٰفِلِينَ ﴿205﴾

Transliteration: Waothkur rabbaka fee nafsika tadarruAAan wakheefatan wadoona aljahri mina alqawli bialghuduwwi waalasali wala takun mina alghafileena

Translation: 205. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህን በሚስጥር ተናንሰህና ፈርተህ ከጩኸት በታች በሆነ ድምጽ በጥዋትና በማታ አውሳው:: ከዘንጊዎቹም አትሁን::

7:206

إِنَّ ٱلَّذِينَ عِندَ رَبِّكَ لَا يَسۡتَكۡبِرُونَ عَنۡ عِبَادَتِهِۦ وَيُسَبِّحُونَهُۥ وَلَهُۥ يَسۡجُدُونَۤ۩ ﴿206﴾

Transliteration: Inna allatheena AAinda rabbika la yastakbiroona AAan AAibadatihi wayusabbihoonahu walahu yasjudoona

Translation: 206. እነዚያ በጌታህ ዘንድ ያሉት መላዕክት እንኳን እርሱን ከመገዛት ፈጽሞ አይኮሩም:: ሁል ጊዜም ያወድሱታል:: ለእርሱም ብቻ ይሰግዳሉ::

Transliteration source: English Transliteration by Tanzil. Used under Tanzil's non-commercial terms; see the source and latest updates at Tanzil. Tanzil translation download