وَبِٱلۡحَقِّ أَنزَلۡنَٰهُ وَبِٱلۡحَقِّ نَزَلَۗ وَمَآ أَرۡسَلۡنَٰكَ إِلَّا مُبَشِّرٗا وَنَذِيرٗا ﴿105﴾وَبِٱلۡحَقِّ أَنزَلۡنَٰهُ وَبِٱلۡحَقِّ نَزَلَۗ وَمَآ أَرۡسَلۡنَٰكَ إِلَّا مُبَشِّرٗا وَنَذِيرٗا
105. ቁርኣንን በእውነትም አወረድነው:: በእውነትም ወረደ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተንም አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን እንጂ አልላክንህም::
وَقُرۡءَانٗا فَرَقۡنَٰهُ لِتَقۡرَأَهُۥ عَلَى ٱلنَّاسِ عَلَىٰ مُكۡثٖ وَنَزَّلۡنَٰهُ تَنزِيلٗا ﴿106﴾وَقُرۡءَانٗا فَرَقۡنَٰهُ لِتَقۡرَأَهُۥ عَلَى ٱلنَّاسِ عَلَىٰ مُكۡثٖ وَنَزَّلۡنَٰهُ تَنزِيلٗا
106. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቁርኣንንም በሰዎች ላይ ሁነህ በዝግታ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው:: ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው::
قُلۡ ءَامِنُواْ بِهِۦٓ أَوۡ لَا تُؤۡمِنُوٓاْۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡعِلۡمَ مِن قَبۡلِهِۦٓ إِذَا يُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ يَخِرُّونَۤ لِلۡأَذۡقَانِۤ سُجَّدٗاۤ ﴿107﴾قُلۡ ءَامِنُواْ بِهِۦٓ أَوۡ لَا تُؤۡمِنُوٓاْۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡعِلۡمَ مِن قَبۡلِهِۦٓ إِذَا يُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ يَخِرُّونَۤ لِلۡأَذۡقَانِۤ سُجَّدٗاۤ
107. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርሱ እመኑ ወይም አትመኑ።» በላቸው:: እነዚያ ከእርሱ በፊት እውቀትን የተሰጡት በእነርሱ ላይ በተነበበ ጊዜ ሰጋጆች ሆነው በሸንጎበቶቻቸው ላይ ይወድቃሉ::
وَيَقُولُونَ سُبۡحَٰنَ رَبِّنَآ إِن كَانَ وَعۡدُ رَبِّنَا لَمَفۡعُولٗا ﴿108﴾وَيَقُولُونَ سُبۡحَٰنَ رَبِّنَآ إِن كَانَ وَعۡدُ رَبِّنَا لَمَفۡعُولٗا
108. ይላሉም: «ጌታችን ጥራት ይገባው። እነሆ የጌታችን ተስፋ ተፈጻሚ ነው።» ይላሉ።
وَيَخِرُّونَ لِلۡأَذۡقَانِ يَبۡكُونَ وَيَزِيدُهُمۡ خُشُوعٗا۩ ﴿109﴾وَيَخِرُّونَ لِلۡأَذۡقَانِ يَبۡكُونَ وَيَزِيدُهُمۡ خُشُوعٗا۩
109. እያለቀሱም በአሸንጎበቶቻቸው (በአገጮቻቸው) ላይ ይወድቃሉ:: አላህም ፍርሃትን ይጨምርላቸዋል::{1}
قُلِ ٱدۡعُواْ ٱللَّهَ أَوِ ٱدۡعُواْ ٱلرَّحۡمَٰنَۖ أَيّٗا مَّا تَدۡعُواْ فَلَهُ ٱلۡأَسۡمَآءُ ٱلۡحُسۡنَىٰۚ وَلَا تَجۡهَرۡ بِصَلَاتِكَ وَلَا تُخَافِتۡ بِهَا وَٱبۡتَغِ بَيۡنَ ذَٰلِكَ سَبِيلٗا ﴿110﴾قُلِ ٱدۡعُواْ ٱللَّهَ أَوِ ٱدۡعُواْ ٱلرَّحۡمَٰنَۖ أَيّٗا مَّا تَدۡعُواْ فَلَهُ ٱلۡأَسۡمَآءُ ٱلۡحُسۡنَىٰۚ وَلَا تَجۡهَرۡ بِصَلَاتِكَ وَلَا تُخَافِتۡ بِهَا وَٱبۡتَغِ بَيۡنَ ذَٰلِكَ سَبِيلٗا
110. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህን ጥሩ ወይም አር-ረህማንን ጥሩ:: ማንኛውንም ስም ብትጠሩ መልካም ነው:: ለእርሱ ብዙ መልካም ስሞች አሉትና።» በላቸው። በስግደትህም ስታነብ በጣም ድምጽህን አትጩህ:: በእርሷም በጣም ድምጽህን ዝቅ አታድርግ:: በሁለቱ መካከል የሆነ መንገድን ፈልግ::
وَقُلِ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِي لَمۡ يَتَّخِذۡ وَلَدٗا وَلَمۡ يَكُن لَّهُۥ شَرِيكٞ فِي ٱلۡمُلۡكِ وَلَمۡ يَكُن لَّهُۥ وَلِيّٞ مِّنَ ٱلذُّلِّۖ وَكَبِّرۡهُ تَكۡبِيرَۢا ﴿111﴾وَقُلِ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِي لَمۡ يَتَّخِذۡ وَلَدٗا وَلَمۡ يَكُن لَّهُۥ شَرِيكٞ فِي ٱلۡمُلۡكِ وَلَمۡ يَكُن لَّهُۥ وَلِيّٞ مِّنَ ٱلذُّلِّۖ وَكَبِّرۡهُ تَكۡبِيرَۢا
111. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ምስጋና ሁሉ ለዚያ ልጅን ላልያዘው ለእርሱም በንግስናው ተጋሪ ለሌለው ለእርሱም ከውርደት የሚያድነው ወዳጅ ለሌለው ለአላህ ብቻ ይገባው።» በል። እርሱን ማክበርንም አክብረው።
ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِيٓ أَنزَلَ عَلَىٰ عَبۡدِهِ ٱلۡكِتَٰبَ وَلَمۡ يَجۡعَل لَّهُۥ عِوَجَاۜ ﴿1﴾ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِيٓ أَنزَلَ عَلَىٰ عَبۡدِهِ ٱلۡكِتَٰبَ وَلَمۡ يَجۡعَل لَّهُۥ عِوَجَاۜ
1-ምስጋና ሁሉ ለዚያ መጽሐፉን በውስጡ ቅንጣት መጣመምን ሳያደርግ በባሪያው (በሙሐመድ) ላይ ላወረደው ለአላህ ብቻ ይገባው::
قَيِّمٗا لِّيُنذِرَ بَأۡسٗا شَدِيدٗا مِّن لَّدُنۡهُ وَيُبَشِّرَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ٱلَّذِينَ يَعۡمَلُونَ ٱلصَّـٰلِحَٰتِ أَنَّ لَهُمۡ أَجۡرًا حَسَنٗا ﴿2﴾قَيِّمٗا لِّيُنذِرَ بَأۡسٗا شَدِيدٗا مِّن لَّدُنۡهُ وَيُبَشِّرَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ٱلَّذِينَ يَعۡمَلُونَ ٱلصَّـٰلِحَٰتِ أَنَّ لَهُمۡ أَجۡرًا حَسَنٗا
2. ቀጥተኛ ሲሆን ከርሱ ዘንድ የሆነን ብርቱን ቅጣት ሊያስፈራራበት፤ እነዚያንም በጎ ሰሪዎችን ለእነርሱ መልካም ምንዳ ያላቸው መሆኑን ሊያበስርበት (አወረደው)።
مَّـٰكِثِينَ فِيهِ أَبَدٗا ﴿3﴾مَّـٰكِثِينَ فِيهِ أَبَدٗا
3. በውስጡም ዘለዓለም የሚቆዩ መሆናቸውን ሊያበስርበት አወረደው።
وَيُنذِرَ ٱلَّذِينَ قَالُواْ ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ وَلَدٗا ﴿4﴾وَيُنذِرَ ٱلَّذِينَ قَالُواْ ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ وَلَدٗا
4. እነዚያንም «አላህ ልጅን ይዟል።» ያሉትን ሊያስፈራራበት (ቁርኣንን አወረደው።)