quranm◉

Surah Ya-Sin transliteration

◉ ሱራ · ∞

36:1

يسٓ ﴿1﴾

Transliteration: Yaseen

Translation: 1. ያሲን::

36:2

وَٱلۡقُرۡءَانِ ٱلۡحَكِيمِ ﴿2﴾

Transliteration: Waalqurani alhakeemi

Translation: 2-ጥበብ በተሞላበት ቁርኣን እምላለሁ::

36:3

إِنَّكَ لَمِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ ﴿3﴾

Transliteration: Innaka lamina almursaleena

Translation: 3.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞቹ መካከል አንዱ ነህ።

36:4

عَلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ ﴿4﴾

Transliteration: AAala siratin mustaqeemin

Translation: 4. አንተ በእርግጥ በቀጥታው መንገድ ላይ ነህ ::

36:5

تَنزِيلَ ٱلۡعَزِيزِ ٱلرَّحِيمِ ﴿5﴾

Transliteration: Tanzeela alAAazeezi alrraheemi

Translation: 5.ቁርኣን አሸናፊውና አዛኙ ከሆነው አምላክ ከአላህ ተወረደ::

36:6

لِتُنذِرَ قَوۡمٗا مَّآ أُنذِرَ ءَابَآؤُهُمۡ فَهُمۡ غَٰفِلُونَ ﴿6﴾

Transliteration: Litunthira qawman ma onthira abaohum fahum ghafiloona

Translation: 6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አባቶቻቸው ያልተስፈራሩትን ህዝቦች ልታስጠነቅቅበት ቁርኣን ተወረደ። እነርሱ ዘንጊዎች ናቸውና።

36:7

لَقَدۡ حَقَّ ٱلۡقَوۡلُ عَلَىٰٓ أَكۡثَرِهِمۡ فَهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ ﴿7﴾

Transliteration: Laqad haqqa alqawlu AAala aktharihim fahum la yuminoona

Translation: 7. በአብዛኞቻቸቸው ላይ ቃሉ በእውነት ተረጋገጠ:: ስለዚህ እነርሱ አያምኑም::

36:8

إِنَّا جَعَلۡنَا فِيٓ أَعۡنَٰقِهِمۡ أَغۡلَٰلٗا فَهِيَ إِلَى ٱلۡأَذۡقَانِ فَهُم مُّقۡمَحُونَ ﴿8﴾

Transliteration: Inna jaAAalna fee aAAnaqihim aghlalan fahiya ila alathqani fahum muqmahoona

Translation: 8. እኛ በአንገቶቻቸው ላይ እንዛዝላዎችን አደረግን። (እንዛዝላይቱም) ወደ አገጮቻቸው ደራሽ ናት። እናም ከዚያም እነርሱ ራሶቻቸውን ያንጋጠጡ ናቸው።

36:9

وَجَعَلۡنَا مِنۢ بَيۡنِ أَيۡدِيهِمۡ سَدّٗا وَمِنۡ خَلۡفِهِمۡ سَدّٗا فَأَغۡشَيۡنَٰهُمۡ فَهُمۡ لَا يُبۡصِرُونَ ﴿9﴾

Transliteration: WajaAAalna min bayni aydeehim saddan wamin khalfihim saddan faaghshaynahum fahum la yubsiroona

Translation: 9. ከበስተፊታቸዉም ግርዶን ከበስተኋላቸዉም ግርዶን አደረግንና ሸፈንናቸው:: ስለዚህ እነርሱ አያዩም::

36:10

وَسَوَآءٌ عَلَيۡهِمۡ ءَأَنذَرۡتَهُمۡ أَمۡ لَمۡ تُنذِرۡهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ ﴿10﴾

Transliteration: Wasawaon AAalayhim aanthartahum am lam tunthirhum la yuminoona

Translation: 10. ብታስጠነቅቃቸዉም ባታስጠነቅቃቸዉም ለእነርሱ ሁሉም እኩል ነው:: (ምንም ለውጥ አያመጣም) አያምኑምና::

36:11

إِنَّمَا تُنذِرُ مَنِ ٱتَّبَعَ ٱلذِّكۡرَ وَخَشِيَ ٱلرَّحۡمَٰنَ بِٱلۡغَيۡبِۖ فَبَشِّرۡهُ بِمَغۡفِرَةٖ وَأَجۡرٖ كَرِيمٍ ﴿11﴾

Transliteration: Innama tunthiru mani ittabaAAa alththikra wakhashiya alrrahmana bialghaybi fabashshirhu bimaghfiratin waajrin kareemin

Translation: 11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የምታስጠነቅቀው ግሳጼን የተከተለንና አር-ረህማንን በሩቅ የፈራን ሰው ብቻ ነው:: እናም በምህረትና በመልካም ምንዳ አብስረው::

36:12

إِنَّا نَحۡنُ نُحۡيِ ٱلۡمَوۡتَىٰ وَنَكۡتُبُ مَا قَدَّمُواْ وَءَاثَٰرَهُمۡۚ وَكُلَّ شَيۡءٍ أَحۡصَيۡنَٰهُ فِيٓ إِمَامٖ مُّبِينٖ ﴿12﴾

Transliteration: Inna nahnu nuhyee almawta wanaktubu ma qaddamoo waatharahum wakulla shayin ahsaynahu fee imamin mubeenin

Translation: 12. እኛ ሙታንን በእርግጥ ህያው እናደርጋለን:: ያስቀደሙትንም ስራ ፈለጎቻቸውንም እንጽፋለን:: ሁሉን ነገርም ገላጭና መሪ በሆነ መጽሐፍ ውስጥ አጠቃለልነው::

36:13

وَٱضۡرِبۡ لَهُم مَّثَلًا أَصۡحَٰبَ ٱلۡقَرۡيَةِ إِذۡ جَآءَهَا ٱلۡمُرۡسَلُونَ ﴿13﴾

Transliteration: Waidrib lahum mathalan ashaba alqaryati ith jaaha almursaloona

Translation: 13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነርሱም የከተማይቱን (የአንጾኪያን) ሰዎች ምሳሌ መልዕክተኞች በመጧት ጊዜ የሆነውን ግለጽላቸው።

36:14

إِذۡ أَرۡسَلۡنَآ إِلَيۡهِمُ ٱثۡنَيۡنِ فَكَذَّبُوهُمَا فَعَزَّزۡنَا بِثَالِثٖ فَقَالُوٓاْ إِنَّآ إِلَيۡكُم مُّرۡسَلُونَ ﴿14﴾

Transliteration: Ith arsalna ilayhimu ithnayni fakaththaboohuma faAAazzazna bithalithin faqaloo inna ilaykum mursaloona

Translation: 14. ወደ እነርሱ ሁለትን ሰዎች በላክንና ባስተባበሉዋቸውም ጊዜ፤ በሶስተኛም ባበረታናቸውና «እኛ ወደ እናንተ መልክተኞች ነን» ባሏቸው ጊዜ የሆነውን ምሳሌ ግለጽላቸው።

36:15

قَالُواْ مَآ أَنتُمۡ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُنَا وَمَآ أَنزَلَ ٱلرَّحۡمَٰنُ مِن شَيۡءٍ إِنۡ أَنتُمۡ إِلَّا تَكۡذِبُونَ ﴿15﴾

Transliteration: Qaloo ma antum illa basharun mithluna wama anzala alrrahmanu min shayin in antum illa takthiboona

Translation: 15. «እናንተ መሰላችን ሰዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም:: አር-ረህማንም ምንንም ነገር አላወረደም:: እናንተ የምትዋሹ እንጂ ሌላ አይደላችሁም» አሏቸው።

36:16

قَالُواْ رَبُّنَا يَعۡلَمُ إِنَّآ إِلَيۡكُمۡ لَمُرۡسَلُونَ ﴿16﴾

Transliteration: Qaloo rabbuna yaAAlamu inna ilaykum lamursaloona

Translation: 16. መልዕክተኞቹም አሉ: «ጌታችን ያውቃል። እኛ ወደ እናንተ በእርግጥ መልክተኞች ነን።

36:17

وَمَا عَلَيۡنَآ إِلَّا ٱلۡبَلَٰغُ ٱلۡمُبِينُ ﴿17﴾

Transliteration: Wama AAalayna illa albalaghu almubeenu

Translation: 17. «በእኛ ላይም ግልጽ የሆነ ማድረስ እንጂ ሌላ የለብንም።» አሉ።

36:18

قَالُوٓاْ إِنَّا تَطَيَّرۡنَا بِكُمۡۖ لَئِن لَّمۡ تَنتَهُواْ لَنَرۡجُمَنَّكُمۡ وَلَيَمَسَّنَّكُم مِّنَّا عَذَابٌ أَلِيمٞ ﴿18﴾

Transliteration: Qaloo inna tatayyarna bikum lain lam tantahoo lanarjumannakum walayamassannakum minna AAathabun aleemun

Translation: 18. ህዝቦቹም «እኛ በእናንተ ገደ ቢሶች ሆንን። ከዚህ ጥሪያችሁ ባትከለክሉም በእርግጥ እንወግራችኋለን:: ከእኛም አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ያገኛችኋል» አሉ።

36:19

قَالُواْ طَـٰٓئِرُكُم مَّعَكُمۡ أَئِن ذُكِّرۡتُمۚ بَلۡ أَنتُمۡ قَوۡمٞ مُّسۡرِفُونَ ﴿19﴾

Transliteration: Qaloo tairukum maAAakum ain thukkirtum bal antum qawmun musrifoona

Translation: 19. «ገደ ቢስነታችሁ ከናንተው ጋር ነው:: ብትገሰጹ (ትዝታላችሁን?) በእውነቱ እናንተ ወሰን አላፊ ህዝቦች ናችሁ» አሏቸው።

36:20

وَجَآءَ مِنۡ أَقۡصَا ٱلۡمَدِينَةِ رَجُلٞ يَسۡعَىٰ قَالَ يَٰقَوۡمِ ٱتَّبِعُواْ ٱلۡمُرۡسَلِينَ ﴿20﴾

Transliteration: Wajaa min aqsa almadeenati rajulun yasAAa qala ya qawmi ittabiAAoo almursaleena

Translation: 20. ከከተማይቱም ሩቅ ዳርቻ የሚሮጥ ሰው መጣና (እንዲህ) አለ: «ወገኖቼ ሆይ! መልዕክተኞቹን ተከተሉ።

36:21

ٱتَّبِعُواْ مَن لَّا يَسۡـَٔلُكُمۡ أَجۡرٗا وَهُم مُّهۡتَدُونَ ﴿21﴾

Transliteration: IttabiAAoo man la yasalukum ajran wahum muhtadoona

Translation: 21. «እነርሱም ቅኑን መንገድ የተመሩ ሲሆኑ ክፍያን የማይጠይቋችሁን ሰዎች ተከተሉ።

36:22

وَمَالِيَ لَآ أَعۡبُدُ ٱلَّذِي فَطَرَنِي وَإِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ ﴿22﴾

Transliteration: Wama liya la aAAbudu allathee fataranee wailayhi turjaAAoona

Translation: 22. «ያንንም የፈጠረኝንና ወደ እርሱም የምትመለሱበትን ጌታ የማልገዛበት ምን ምክንያት አለኝ?

36:23

ءَأَتَّخِذُ مِن دُونِهِۦٓ ءَالِهَةً إِن يُرِدۡنِ ٱلرَّحۡمَٰنُ بِضُرّٖ لَّا تُغۡنِ عَنِّي شَفَٰعَتُهُمۡ شَيۡـٔٗا وَلَا يُنقِذُونِ ﴿23﴾

Transliteration: Aattakhithu min doonihi alihatan in yuridni alrrahmanu bidurrin la tughni AAannee shafaAAatuhum shayan wala yunqithooni

Translation: 23. «ከእርሱ ሌላ አማልክትን እይዛለሁን? አልራህማን ሊጎዳኝ ቢፈልግ ምልጃቸው ከእኔ (ለመመለስ) ምንም አትጠቅመኝም አያድኑኝምም።

36:24

إِنِّيٓ إِذٗا لَّفِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٍ ﴿24﴾

Transliteration: Innee ithan lafee dalalin mubeenin

Translation: 24. «እኔ ያን ጊዜ በግልጽ ስህተት ውስጥ ነኝ።

36:25

إِنِّيٓ ءَامَنتُ بِرَبِّكُمۡ فَٱسۡمَعُونِ ﴿25﴾

Transliteration: Innee amantu birabbikum faismaAAooni

Translation: 25. «እኔ በጌታችሁ አመንኩ። ስሙኝም።» አለ።

36:26

قِيلَ ٱدۡخُلِ ٱلۡجَنَّةَۖ قَالَ يَٰلَيۡتَ قَوۡمِي يَعۡلَمُونَ ﴿26﴾

Transliteration: Qeela odkhuli aljannata qala ya layta qawmee yaAAlamoona

Translation: 26. {1} «ገነትን ግባ» ተባለም። እርሱም አለ: «ወገኖቼ ቢያውቁ እመኛለሁ።

36:27

بِمَا غَفَرَ لِي رَبِّي وَجَعَلَنِي مِنَ ٱلۡمُكۡرَمِينَ ﴿27﴾

Transliteration: Bima ghafara lee rabbee wajaAAalanee mina almukrameena

Translation: 27. «ጌታዬ ለእኔ ምህረት ያደረገልኝና ከተከበሩትም ያደረገኝ መሆኑን።» (ቢያውቁ ተመኘሁ)

36:28

وَمَآ أَنزَلۡنَا عَلَىٰ قَوۡمِهِۦ مِنۢ بَعۡدِهِۦ مِن جُندٖ مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَمَا كُنَّا مُنزِلِينَ ﴿28﴾

Transliteration: Wama anzalna AAala qawmihi min baAAdihi min jundin mina alssamai wama kunna munzileena

Translation: 28. ከእርሱም በኋላ በህዝቦቹ ላይ ልናጠፋቸው ሰራዊትን ከሰማይ አላወረድንም (በማንም) ላይ አውራጆችም አልነበርንም::

36:29

إِن كَانَتۡ إِلَّا صَيۡحَةٗ وَٰحِدَةٗ فَإِذَا هُمۡ خَٰمِدُونَ ﴿29﴾

Transliteration: In kanat illa sayhatan wahidatan faitha hum khamidoona

Translation: 29. ቅጣታቸው አንዲት ጩኸት እንጂ ሌላ አልነበረችም:: ወዲያውኑም እነርሱ ጠፊዎች ሆኑ::

36:30

يَٰحَسۡرَةً عَلَى ٱلۡعِبَادِۚ مَا يَأۡتِيهِم مِّن رَّسُولٍ إِلَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ ﴿30﴾

Transliteration: Ya hasratan AAala alAAibadi ma yateehim min rasoolin illa kanoo bihi yastahzioona

Translation: 30. በባሮች ላይ ዋ ቁጭት! ከመልዕክተኛ አንድም አልመጣላቸዉም በእርሱ ያፌዙበት ቢሆን እንጂ፤

36:31

أَلَمۡ يَرَوۡاْ كَمۡ أَهۡلَكۡنَا قَبۡلَهُم مِّنَ ٱلۡقُرُونِ أَنَّهُمۡ إِلَيۡهِمۡ لَا يَرۡجِعُونَ ﴿31﴾

Transliteration: Alam yaraw kam ahlakna qablahum mina alqurooni annahum ilayhim la yarjiAAoona

Translation: 31. ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች ብዙዎችን ማጥፋታችንንና እነርሱ የማይመለሱ መሆናቸውን አላወቁምን?

36:32

وَإِن كُلّٞ لَّمَّا جَمِيعٞ لَّدَيۡنَا مُحۡضَرُونَ ﴿32﴾

Transliteration: Wain kullun lamma jameeAAun ladayna muhdaroona

Translation: 32. ሁሉም እኛ ዘንድ (የሚሰበሰቡ) የሚቀረቡ እንጂ ሌላ አይደሉም::

36:33

وَءَايَةٞ لَّهُمُ ٱلۡأَرۡضُ ٱلۡمَيۡتَةُ أَحۡيَيۡنَٰهَا وَأَخۡرَجۡنَا مِنۡهَا حَبّٗا فَمِنۡهُ يَأۡكُلُونَ ﴿33﴾

Transliteration: Waayatun lahumu alardu almaytatu ahyaynaha waakhrajna minha habban faminhu yakuloona

Translation: 33. የሞተችዉም ምድር ለእነርሱ ምልክት ናት:: ህያው አደረግናት:: ከእርሷ ፍሬን አወጣን፤ ከእሱም ይበላሉ::

36:34

وَجَعَلۡنَا فِيهَا جَنَّـٰتٖ مِّن نَّخِيلٖ وَأَعۡنَٰبٖ وَفَجَّرۡنَا فِيهَا مِنَ ٱلۡعُيُونِ ﴿34﴾

Transliteration: WajaAAalna feeha jannatin min nakheelin waaAAnabin wafajjarna feeha mina alAAuyooni

Translation: 34. በእርሷ ውስጥ ከዘምባባዎችና ከወይኖች የሆነ አትክልቶችን አደረግን:: በእርሷም ውስጥ ምንጮችን አፈለቅን::

36:35

لِيَأۡكُلُواْ مِن ثَمَرِهِۦ وَمَا عَمِلَتۡهُ أَيۡدِيهِمۡۚ أَفَلَا يَشۡكُرُونَ ﴿35﴾

Transliteration: Liyakuloo min thamarihi wama AAamilathu aydeehim afala yashkuroona

Translation: 35. ከፍሬዉና እጆቻቸው ከሰሩትም ይበሉ ዘንድ ይህን አደረግን:: አያመሰግኑምን?

36:36

سُبۡحَٰنَ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلۡأَزۡوَٰجَ كُلَّهَا مِمَّا تُنۢبِتُ ٱلۡأَرۡضُ وَمِنۡ أَنفُسِهِمۡ وَمِمَّا لَا يَعۡلَمُونَ ﴿36﴾

Transliteration: Subhana allathee khalaqa alazwaja kullaha mimma tunbitu alardu wamin anfusihim wamimma la yaAAlamoona

Translation: 36. ያ! ምድር ከምታበቅለው፤ ወንዴንና ሴቴን ከነፍሶቻቸዉም ከማያውቁትም ነገር (ዓይነቶችን) ሁሏንም የፈጠረ (አምላክ) ጥራት ይገባው::

36:37

وَءَايَةٞ لَّهُمُ ٱلَّيۡلُ نَسۡلَخُ مِنۡهُ ٱلنَّهَارَ فَإِذَا هُم مُّظۡلِمُونَ ﴿37﴾

Transliteration: Waayatun lahumu allaylu naslakhu minhu alnnahara faitha hum muthlimoona

Translation: 37. ሌሊቱም ለእነርሱ ምልክት ነው:: ከእርሱ ላይ ቀንን አንገፋለን:: ወዲያውኑም እነርሱ በጨለማ ውስጥ ይገባሉ::

36:38

وَٱلشَّمۡسُ تَجۡرِي لِمُسۡتَقَرّٖ لَّهَاۚ ذَٰلِكَ تَقۡدِيرُ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡعَلِيمِ ﴿38﴾

Transliteration: Waalshshamsu tajree limustaqarrin laha thalika taqdeeru alAAazeezi alAAaleemi

Translation: 38. ጸሐይም ለእርሷ ወደ ሆነው መርጊያ ትሮጣለች:: ይህ የአሸናፊውና የአዋቂው አምላክ የአላህ ውሳኔ ነው::

36:39

وَٱلۡقَمَرَ قَدَّرۡنَٰهُ مَنَازِلَ حَتَّىٰ عَادَ كَٱلۡعُرۡجُونِ ٱلۡقَدِيمِ ﴿39﴾

Transliteration: Waalqamara qaddarnahu manazila hatta AAada kaalAAurjooni alqadeemi

Translation: 39. ጨረቃንም የመስፈሪያዎች ባለቤት ሲሆን እንደ አሮጌ ዘንባባ ቀንዘል እስኪሆን ድረስ መሄዱን ለካነው::

36:40

لَا ٱلشَّمۡسُ يَنۢبَغِي لَهَآ أَن تُدۡرِكَ ٱلۡقَمَرَ وَلَا ٱلَّيۡلُ سَابِقُ ٱلنَّهَارِۚ وَكُلّٞ فِي فَلَكٖ يَسۡبَحُونَ ﴿40﴾

Transliteration: La alshshamsu yanbaghee laha an tudrika alqamara wala allaylu sabiqu alnnahari wakullun fee falakin yasbahoona

Translation: 40. ጸሐይ ጨረቃን ልትደርስበት አይገባትም:: ሌሊትም ቀንን ያለ ጊዜው ቀዳሚ አይሆንም:: ሁሉም በየመዞሪያቸው (በፈለክ) ውስጥ ይዋኛሉ::

36:41

وَءَايَةٞ لَّهُمۡ أَنَّا حَمَلۡنَا ذُرِّيَّتَهُمۡ فِي ٱلۡفُلۡكِ ٱلۡمَشۡحُونِ ﴿41﴾

Transliteration: Waayatun lahum anna hamalna thurriyyatahum fee alfulki almashhooni

Translation: 41. እኛም የቀድሞ ትውልዳቸውን (አባቶቻቸውን) በተሞላች መርከብ ውስጥ የጫን መሆናችን ለእነርሱ ምልክት ነው::

36:42

وَخَلَقۡنَا لَهُم مِّن مِّثۡلِهِۦ مَا يَرۡكَبُونَ ﴿42﴾

Transliteration: Wakhalaqna lahum min mithlihi ma yarkaboona

Translation: 42. ከመሰሉም በእርሱ የሚሳፈሩበትን ለእነርሱ ፈጠርንላቸው::

36:43

وَإِن نَّشَأۡ نُغۡرِقۡهُمۡ فَلَا صَرِيخَ لَهُمۡ وَلَا هُمۡ يُنقَذُونَ ﴿43﴾

Transliteration: Wain nasha nughriqhum fala sareekha lahum wala hum yunqathoona

Translation: 43. ስንፈልግ እናሰምጣቸዋለን:: ለእነርሱም ነፃ የሚያደርጋቸው ረዳት የላቸዉም:: እንዲድኑ የሚደረጉም አይደሉም።

36:44

إِلَّا رَحۡمَةٗ مِّنَّا وَمَتَٰعًا إِلَىٰ حِينٖ ﴿44﴾

Transliteration: Illa rahmatan minna wamataAAan ila heenin

Translation: 44. እኛ ግን በችሮታችንና እስከ ጊዜ ሞታቸው ለማጣቀም አዳንናቸው::

36:45

وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ٱتَّقُواْ مَا بَيۡنَ أَيۡدِيكُمۡ وَمَا خَلۡفَكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تُرۡحَمُونَ ﴿45﴾

Transliteration: Waitha qeela lahumu ittaqoo ma bayna aydeekum wama khalfakum laAAallakum turhamoona

Translation: 45. ለእነርሱም «በስተፊታችሁና በኋላችሁ ያለውን ነገር ተጠንቀቁ፤ ይታዘንላችኋልና» በተባለ ጊዜ ፊታቸውን ያዞራሉ።

36:46

وَمَا تَأۡتِيهِم مِّنۡ ءَايَةٖ مِّنۡ ءَايَٰتِ رَبِّهِمۡ إِلَّا كَانُواْ عَنۡهَا مُعۡرِضِينَ ﴿46﴾

Transliteration: Wama tateehim min ayatin min ayati rabbihim illa kanoo AAanha muAArideena

Translation: 46. ከጌታቸውም ተዓምራት አንዲትም ተዓምር አትመጣላቸዉም ከእርሷ የሚሸሹ ቢሆኑ እንጅ።

36:47

وَإِذَا قِيلَ لَهُمۡ أَنفِقُواْ مِمَّا رَزَقَكُمُ ٱللَّهُ قَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لِلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَنُطۡعِمُ مَن لَّوۡ يَشَآءُ ٱللَّهُ أَطۡعَمَهُۥٓ إِنۡ أَنتُمۡ إِلَّا فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ ﴿47﴾

Transliteration: Waitha qeela lahum anfiqoo mimma razaqakumu Allahu qala allatheena kafaroo lillatheena amanoo anutAAimu man law yashao Allahu atAAamahu in antum illa fee dalalin mubeenin

Translation: 47. ለእነርሱም «አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ ለግሱ» በተባሉ ጊዜ እነዚያ በአላህ የካዱት ለእነዚያ በአላህ ላመኑት «አላህ ቢሻ ኖሮ የሚያበላውን እናበላለን? እናንተ በግልጽ ስህተት ውስጥ እንጂ በሌላ ላይ አይደላችሁም።» ይላሉ።

36:48

وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلۡوَعۡدُ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ ﴿48﴾

Transliteration: Wayaqooloona mata hatha alwaAAdu in kuntum sadiqeena

Translation: 48. «እውነተኞችም እንደ ሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ።

36:49

مَا يَنظُرُونَ إِلَّا صَيۡحَةٗ وَٰحِدَةٗ تَأۡخُذُهُمۡ وَهُمۡ يَخِصِّمُونَ ﴿49﴾

Transliteration: Ma yanthuroona illa sayhatan wahidatan takhuthuhum wahum yakhissimoona

Translation: 49. እነርሱ የሚከራከሩ ሲሆኑ በድንገት የምትይዛቸው የሆነችን አንዲትን ጩኸት እንጂ ሌላን አይጠባበቁም::

36:50

فَلَا يَسۡتَطِيعُونَ تَوۡصِيَةٗ وَلَآ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِمۡ يَرۡجِعُونَ ﴿50﴾

Transliteration: Fala yastateeAAoona tawsiyatan wala ila ahlihim yarjiAAoona

Translation: 50. ያን ጊዜ መናዘዝን እንኳን አይችሉም:: ወደ ቤተሰቦቻቸዉም አይመለሱም::

36:51

وَنُفِخَ فِي ٱلصُّورِ فَإِذَا هُم مِّنَ ٱلۡأَجۡدَاثِ إِلَىٰ رَبِّهِمۡ يَنسِلُونَ ﴿51﴾

Transliteration: Wanufikha fee alssoori faitha hum mina alajdathi ila rabbihim yansiloona

Translation: 51. በቀንዱም ይነፋል:: ወዲያውኑም እነርሱ ከየመቃብሮቻቸው ወደ ጌታቸው በፍጥነት ይገሰግሳሉ::

36:52

قَالُواْ يَٰوَيۡلَنَا مَنۢ بَعَثَنَا مِن مَّرۡقَدِنَاۜۗ هَٰذَا مَا وَعَدَ ٱلرَّحۡمَٰنُ وَصَدَقَ ٱلۡمُرۡسَلُونَ ﴿52﴾

Transliteration: Qaloo ya waylana man baAAathana min marqadina hatha ma waAAada alrrahmanu wasadaqa almursaloona

Translation: 52. «ወይ ጥፋታችን! ከመኝታችን ማን ቀሰቀሰን? ይህ ያ አዛኙ ጌታ በእርሱ የቀጠረን መልዕክተኞቹም እውነቱን የነገሩን ነው።» ይላሉ።

36:53

إِن كَانَتۡ إِلَّا صَيۡحَةٗ وَٰحِدَةٗ فَإِذَا هُمۡ جَمِيعٞ لَّدَيۡنَا مُحۡضَرُونَ ﴿53﴾

Transliteration: In kanat illa sayhatan wahidatan faitha hum jameeAAun ladayna muhdaroona

Translation: 53. እርሷ አንዲት ጩኸት እንጂ ሌላ አይደለችም:: ወዲያውኑም እነርሱ እኛ ዘንድ የሚሰበሰቡ የሚቀርቡ ናቸው::

36:54

فَٱلۡيَوۡمَ لَا تُظۡلَمُ نَفۡسٞ شَيۡـٔٗا وَلَا تُجۡزَوۡنَ إِلَّا مَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ ﴿54﴾

Transliteration: Faalyawma la tuthlamu nafsun shayan wala tujzawna illa ma kuntum taAAmaloona

Translation: 54. ዛሬም ማንኛይቱም ነፍስ ምንንም አትበደልም:: ትሰሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም (ይባላሉ።)

36:55

إِنَّ أَصۡحَٰبَ ٱلۡجَنَّةِ ٱلۡيَوۡمَ فِي شُغُلٖ فَٰكِهُونَ ﴿55﴾

Transliteration: Inna ashaba aljannati alyawma fee shughulin fakihoona

Translation: 55. የገነት ሰዎች ዛሬ በእርግጥ በስራዎች ውስጥ ተደሳቾች ናቸው::

36:56

هُمۡ وَأَزۡوَٰجُهُمۡ فِي ظِلَٰلٍ عَلَى ٱلۡأَرَآئِكِ مُتَّكِـُٔونَ ﴿56﴾

Transliteration: Hum waazwajuhum fee thilalin AAala alaraiki muttakioona

Translation: 56. እነርሱም ሆኑ ሚስቶቻቸው በጥላዎች ውስጥ ናቸው:: ባለ አጎበር አልጋዎች ላይም ተደጋፊዎች ናቸው::

36:57

لَهُمۡ فِيهَا فَٰكِهَةٞ وَلَهُم مَّا يَدَّعُونَ ﴿57﴾

Transliteration: Lahum feeha fakihatun walahum ma yaddaAAoona

Translation: 57. በውስጧ ለእነርሱ ፍራፍሬዎች አሏቸው:: ለእነርሱም የሚፈልጉት ሁሉ አለላቸው::

36:58

سَلَٰمٞ قَوۡلٗا مِّن رَّبّٖ رَّحِيمٖ ﴿58﴾

Transliteration: Salamun qawlan min rabbin raheemin

Translation: 58. ለእነርሱም አዛኝ ከሆነው ጌታ በቃል ሰላምታ አለላቸው።

36:59

وَٱمۡتَٰزُواْ ٱلۡيَوۡمَ أَيُّهَا ٱلۡمُجۡرِمُونَ ﴿59﴾

Transliteration: Waimtazoo alyawma ayyuha almujrimoona

Translation: 59. (አላህም ይላል): «እናንተ አመጸኞች ሆይ! ዛሬ ከትክክለኛ አማኞች ተለዩ።

36:60

أَلَمۡ أَعۡهَدۡ إِلَيۡكُمۡ يَٰبَنِيٓ ءَادَمَ أَن لَّا تَعۡبُدُواْ ٱلشَّيۡطَٰنَۖ إِنَّهُۥ لَكُمۡ عَدُوّٞ مُّبِينٞ ﴿60﴾

Transliteration: Alam aAAhad ilaykum ya banee adama an la taAAbudoo alshshaytana innahu lakum AAaduwwun mubeenun

Translation: 60. «የአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣንን አትገዙ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና በማለት ወደ እናንተ አላዘዝኩምን?

36:61

وَأَنِ ٱعۡبُدُونِيۚ هَٰذَا صِرَٰطٞ مُّسۡتَقِيمٞ ﴿61﴾

Transliteration: Waani oAAbudoonee hatha siratun mustaqeemun

Translation: 61. «ተገዙኝም ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው በማለትም::

36:62

وَلَقَدۡ أَضَلَّ مِنكُمۡ جِبِلّٗا كَثِيرًاۖ أَفَلَمۡ تَكُونُواْ تَعۡقِلُونَ ﴿62﴾

Transliteration: Walaqad adalla minkum jibillan katheeran afalam takoonoo taAAqiloona

Translation: 62. «ከናንተም ብዙን ፍጡር በእርግጥ አሳስቷል:: የምታውቁም አልነበራችሁምን?

36:63

هَٰذِهِۦ جَهَنَّمُ ٱلَّتِي كُنتُمۡ تُوعَدُونَ ﴿63﴾

Transliteration: Hathihi jahannamu allatee kuntum tooAAadoona

Translation: 63. «ይህቺ ያቺ ትቀጠሯት የነበረችው ገሀነም ናት።

36:64

ٱصۡلَوۡهَا ٱلۡيَوۡمَ بِمَا كُنتُمۡ تَكۡفُرُونَ ﴿64﴾

Transliteration: Islawha alyawma bima kuntum takfuroona

Translation: 64. «ትክዱ በነበራችሁት ምክንያት ዛሬዉኑ ግቧት።» (ይባላሉ።)

36:65

ٱلۡيَوۡمَ نَخۡتِمُ عَلَىٰٓ أَفۡوَٰهِهِمۡ وَتُكَلِّمُنَآ أَيۡدِيهِمۡ وَتَشۡهَدُ أَرۡجُلُهُم بِمَا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ ﴿65﴾

Transliteration: Alyawma nakhtimu AAala afwahihim watukallimuna aydeehim watashhadu arjuluhum bima kanoo yaksiboona

Translation: 65. ዛሬ በአፎቻቸው ላይ እናትምና እጆቻቸው ያነጋግሩናል:: እግሮቻቸዉም ይሰሩት በነበሩት ሁሉ ይመሰክራሉ::

36:66

وَلَوۡ نَشَآءُ لَطَمَسۡنَا عَلَىٰٓ أَعۡيُنِهِمۡ فَٱسۡتَبَقُواْ ٱلصِّرَٰطَ فَأَنَّىٰ يُبۡصِرُونَ ﴿66﴾

Transliteration: Walaw nashao latamasna AAala aAAyunihim faistabaqoo alssirata faanna yubsiroona

Translation: 66. ብንፈልግ ኖሮ በዓይኖቻቸው ላይ በአበስን ነበር:: መንገድንም እንደ ልማዳቸው በተሸቀዳደሙ ነበር:: እንዴትስ ያያሉ?

36:67

وَلَوۡ نَشَآءُ لَمَسَخۡنَٰهُمۡ عَلَىٰ مَكَانَتِهِمۡ فَمَا ٱسۡتَطَٰعُواْ مُضِيّٗا وَلَا يَرۡجِعُونَ ﴿67﴾

Transliteration: Walaw nashao lamasakhnahum AAala makanatihim fama istataAAoo mudiyyan wala yarjiAAoona

Translation: 67. ብንፈልግ ኖሮ በስፍራቸው ላይ እንዳሉ ወደ ሌላ ፍጥረት በለወጥናቸው ነበር:: ከዚያም መሄድንም ሆነ መመለስን ባልቻሉም ነበር::

36:68

وَمَن نُّعَمِّرۡهُ نُنَكِّسۡهُ فِي ٱلۡخَلۡقِۚ أَفَلَا يَعۡقِلُونَ ﴿68﴾

Transliteration: Waman nuAAammirhu nunakkishu fee alkhalqi afala yaAAqiloona

Translation: 68. እድሜውንም የምናረዝመውን በፍጥረቱ ወደ ደካማነት እንመልሰዋለን:: አያውቁምን?

36:69

وَمَا عَلَّمۡنَٰهُ ٱلشِّعۡرَ وَمَا يَنۢبَغِي لَهُۥٓۚ إِنۡ هُوَ إِلَّا ذِكۡرٞ وَقُرۡءَانٞ مُّبِينٞ ﴿69﴾

Transliteration: Wama AAallamnahu alshshiAAra wama yanbaghee lahu in huwa illa thikrun waquranun mubeenun

Translation: 69. (ሙሐመድን) ቅኔንም አላስተማርነዉም:: ለእርሱም አይገባዉም:: እርሱ (መጽሐፉ) መገሰጫና ገላጭ ቁርኣን አንጅ (ቅኔ አይደለም)::

36:70

لِّيُنذِرَ مَن كَانَ حَيّٗا وَيَحِقَّ ٱلۡقَوۡلُ عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ ﴿70﴾

Transliteration: Liyunthira man kana hayyan wayahiqqa alqawlu AAala alkafireena

Translation: 70. ግሳጼነቱም ልቡ ህያው የሆነን ሰው ሊያስፈራራበትና ቃሉም በከሓዲያን ላይ ይፈጸም ዘንድ ነው::

36:71

أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ أَنَّا خَلَقۡنَا لَهُم مِّمَّا عَمِلَتۡ أَيۡدِينَآ أَنۡعَٰمٗا فَهُمۡ لَهَا مَٰلِكُونَ ﴿71﴾

Transliteration: Awalam yaraw anna khalaqna lahum mimma AAamilat aydeena anAAaman fahum laha malikoona

Translation: 71. እኛ እጆቻችን ከሰሩት ለእነርሱ እንሰሳዎችን መፍጠራችንን አያውቁምን? እነርሱም ለእርሷ ባለ መብቶች ናቸው::

36:72

وَذَلَّلۡنَٰهَا لَهُمۡ فَمِنۡهَا رَكُوبُهُمۡ وَمِنۡهَا يَأۡكُلُونَ ﴿72﴾

Transliteration: Wathallalnaha lahum faminha rakoobuhum waminha yakuloona

Translation: 72. ለእነርሱም ገራናት:: ስለዚህ ከእርሷ ውስጥ የሚጋልቡት አለ:: ከእርሷም ይመገባሉ::

36:73

وَلَهُمۡ فِيهَا مَنَٰفِعُ وَمَشَارِبُۚ أَفَلَا يَشۡكُرُونَ ﴿73﴾

Transliteration: Walahum feeha manafiAAu wamasharibu afala yashkuroona

Translation: 73. ለእነርሱም በእርሷ ውስጥ ሌሎች ጥቅሞችና መጠጦችም አሏቸው። ታዲያ አያመሰግኑምን?

36:74

وَٱتَّخَذُواْ مِن دُونِ ٱللَّهِ ءَالِهَةٗ لَّعَلَّهُمۡ يُنصَرُونَ ﴿74﴾

Transliteration: Waittakhathoo min dooni Allahi alihatan laAAallahum yunsaroona

Translation: 74. መረዳትንም በመከጀል ከአላህ ሌላ አመለኩ።

36:75

لَا يَسۡتَطِيعُونَ نَصۡرَهُمۡ وَهُمۡ لَهُمۡ جُندٞ مُّحۡضَرُونَ ﴿75﴾

Transliteration: La yastateeAAoona nasrahum wahum lahum jundun muhdaroona

Translation: 75. ሊረዷቸውም አይችሉም። እነርሱም ለእርሳቸው ወደ እሳት የተቀረቡ ሰራዊት ናቸው::

36:76

فَلَا يَحۡزُنكَ قَوۡلُهُمۡۘ إِنَّا نَعۡلَمُ مَا يُسِرُّونَ وَمَا يُعۡلِنُونَ ﴿76﴾

Transliteration: Fala yahzunka qawluhum inna naAAlamu ma yusirroona wama yuAAlinoona

Translation: 76. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ንግግራቸዉም አያሳዝንህ:: እኛ የሚደብቁትንም የሚገልፁትንም እናውቃለንና::

36:77

أَوَلَمۡ يَرَ ٱلۡإِنسَٰنُ أَنَّا خَلَقۡنَٰهُ مِن نُّطۡفَةٖ فَإِذَا هُوَ خَصِيمٞ مُّبِينٞ ﴿77﴾

Transliteration: Awalam yara alinsanu anna khalaqnahu min nutfatin faitha huwa khaseemun mubeenun

Translation: 77. ሰው እኛ ከፍትወት ጠብታ የፈጠርነው መሆናችንን አላወቀምን? ወዲያዉም እርሱ ትንሳኤን በመካድ ግልጽ ተከራካሪ ይሆናልን?

36:78

وَضَرَبَ لَنَا مَثَلٗا وَنَسِيَ خَلۡقَهُۥۖ قَالَ مَن يُحۡيِ ٱلۡعِظَٰمَ وَهِيَ رَمِيمٞ ﴿78﴾

Transliteration: Wadaraba lana mathalan wanasiya khalqahu qala man yuhyee alAAithama wahiya rameemun

Translation: 78. ለእኛም ምሳሌን አደረገልን:: መፈጠሩንም ረሳ:: «አጥንቶችን እነርሱ የበሰበሱ ሲሆኑ ህያው የሚያደርጋቸው ማነው?» አለ::

36:79

قُلۡ يُحۡيِيهَا ٱلَّذِيٓ أَنشَأَهَآ أَوَّلَ مَرَّةٖۖ وَهُوَ بِكُلِّ خَلۡقٍ عَلِيمٌ ﴿79﴾

Transliteration: Qul yuhyeeha allathee anshaaha awwala marratin wahuwa bikulli khalqin AAaleemun

Translation: 79. «ያ! በመጀመሪያ ጊዜ (ከኢምንት) ያስገኛት ጌታ እንደገና ህያው ያደረጋታል:: እርሱም በፍጡሩ ሁሉ ሁኔታ አዋቂ ነው።» በለው።

36:80

ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُم مِّنَ ٱلشَّجَرِ ٱلۡأَخۡضَرِ نَارٗا فَإِذَآ أَنتُم مِّنۡهُ تُوقِدُونَ ﴿80﴾

Transliteration: Allathee jaAAala lakum mina alshshajari alakhdari naran faitha antum minhu tooqidoona

Translation: 80. ያ! ለእናንተ ከእርጥብ ዛፍ እሳትን የፈጠረላችሁ ነው:: ወዲያውኑም እናንተ ከእርሱ ታቀጣጥላላችሁ::

36:81

أَوَلَيۡسَ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ بِقَٰدِرٍ عَلَىٰٓ أَن يَخۡلُقَ مِثۡلَهُمۚ بَلَىٰ وَهُوَ ٱلۡخَلَّـٰقُ ٱلۡعَلِيمُ ﴿81﴾

Transliteration: Awalaysa allathee khalaqa alssamawati waalarda biqadirin AAala an yakhluqa mithlahum bala wahuwa alkhallaqu alAAaleemu

Translation: 81. ያ! ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ብጤያቸውን በመፍጠር ላይ ቻይ አይደለምን? እንዴታ ቻይ ነው እንጂ:: እርሱም በብዙ ፈጣሪውና እጅግ አዋቂው ነው።

36:82

إِنَّمَآ أَمۡرُهُۥٓ إِذَآ أَرَادَ شَيۡـًٔا أَن يَقُولَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ ﴿82﴾

Transliteration: Innama amruhu itha arada shayan an yaqoola lahu kun fayakoonu

Translation: 82. ነገሩ አንድን ነገር በሻ ጊዜ ሁን ማለት ብቻ ነው:: ከዚያ ወዲያው ይሆናልም::

36:83

فَسُبۡحَٰنَ ٱلَّذِي بِيَدِهِۦ مَلَكُوتُ كُلِّ شَيۡءٖ وَإِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ ﴿83﴾

Transliteration: Fasubhana allathee biyadihi malakootu kulli shayin wailayhi turjaAAoona

Translation: 83. እናም ያ የነገሩ ሁሉ ስልጣን በእጁ የሆነው ጌታ ጥራት ይገባው:: ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ::

Transliteration source: English Transliteration by Tanzil. Used under Tanzil's non-commercial terms; see the source and latest updates at Tanzil. Tanzil translation download