quranm◉

Surah Al-Jumu'ah transliteration

◉ ሱራ · ∞

62:1

يُسَبِّحُ لِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ ٱلۡمَلِكِ ٱلۡقُدُّوسِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡحَكِيمِ ﴿1﴾

Transliteration: Yusabbihu lillahi ma fee alssamawati wama fee alardi almaliki alquddoosi alAAazeezi alhakeemi

Translation: 1. በሰማይና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ ንጉስ፤ ፍፁም (ከጉድለት ንጹህ)፤ አሸናፊና ጥበበኛ የሆነውን አላህን ያሞግሳል::

62:2

هُوَ ٱلَّذِي بَعَثَ فِي ٱلۡأُمِّيِّـۧنَ رَسُولٗا مِّنۡهُمۡ يَتۡلُواْ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتِهِۦ وَيُزَكِّيهِمۡ وَيُعَلِّمُهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡحِكۡمَةَ وَإِن كَانُواْ مِن قَبۡلُ لَفِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ ﴿2﴾

Transliteration: Huwa allathee baAAatha fee alommiyyeena rasoolan minhum yatloo AAalayhim ayatihi wayuzakkeehim wayuAAallimuhumu alkitaba waalhikmata wain kanoo min qablu lafee dalalin mubeenin

Translation: 2. እርሱ ያ ለመሃይማን ዐረቦች የቁርአን አናቅጽን በእነርሱ ላይ የሚያነብላቸው፤ የሚያጠራቸዉም፤ መጽሐፍንና ጥበብን የሚያስተምራቸዉም የሆነን መልዕክተኛ ሙሐመድን ከእነርሱ መካከል የላከ ነው:: እነርሱም ከእርሱ በፊት በግልጽ ስህተት ውስጥ ነበሩ::

62:3

وَءَاخَرِينَ مِنۡهُمۡ لَمَّا يَلۡحَقُواْ بِهِمۡۚ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ ﴿3﴾

Transliteration: Waakhareena minhum lamma yalhaqoo bihim wahuwa alAAazeezu alhakeemu

Translation: 3.ከነሱም ሌሎችም ገና ያልተከተሏቸው በሆኑት ላይ የላከው ነው:: እርሱም አሸናፊና ጥበበኛ ነው::

62:4

ذَٰلِكَ فَضۡلُ ٱللَّهِ يُؤۡتِيهِ مَن يَشَآءُۚ وَٱللَّهُ ذُو ٱلۡفَضۡلِ ٱلۡعَظِيمِ ﴿4﴾

Transliteration: Thalika fadlu Allahi yuteehi man yashao waAllahu thoo alfadli alAAatheemi

Translation: 4. ይህ የአላህ ችሮታ ነው:: ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል:: አላህ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው::

62:5

مَثَلُ ٱلَّذِينَ حُمِّلُواْ ٱلتَّوۡرَىٰةَ ثُمَّ لَمۡ يَحۡمِلُوهَا كَمَثَلِ ٱلۡحِمَارِ يَحۡمِلُ أَسۡفَارَۢاۚ بِئۡسَ مَثَلُ ٱلۡقَوۡمِ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِۚ وَٱللَّهُ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلظَّـٰلِمِينَ ﴿5﴾

Transliteration: Mathalu allatheena hummiloo alttawrata thumma lam yahmilooha kamathali alhimari yahmilu asfaran bisa mathalu alqawmi allatheena kaththaboo biayati Allahi waAllahu la yahdee alqawma alththalimeena

Translation: 5. የእነዚያ ተውራትን የተጫኑትና ከዚያ ያልተሸከሟት (ያልሰሩባት) ሰዎች ምሳሌ ልክ መጽሐፎችን እንደሚሸከም አህያ ብጤ ነው:: የእነዚያ በአላህ አናቅጽ ያስተባበሉት ህዝቦች ምሳሌ ከፋ:: አላህም በዳዮችን ህዝቦች አይመራም::

62:6

قُلۡ يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ هَادُوٓاْ إِن زَعَمۡتُمۡ أَنَّكُمۡ أَوۡلِيَآءُ لِلَّهِ مِن دُونِ ٱلنَّاسِ فَتَمَنَّوُاْ ٱلۡمَوۡتَ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ ﴿6﴾

Transliteration: Qul ya ayyuha allatheena hadoo in zaAAamtum annakum awliyao lillahi min dooni alnnasi fatamannawoo almawta in kuntum sadiqeena

Translation: 6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ አይሁዳውያን ሆይ! ከሰው ሁሉ በተለየ እናንተ ብቻ ለአላህ ወዳጆች ነን ብትሉና በዚያ አባባላችሁ እውነተኞች እንደሆናችሁ እስቲ ሞትን ተመኙ» በላቸው::

62:7

وَلَا يَتَمَنَّوۡنَهُۥٓ أَبَدَۢا بِمَا قَدَّمَتۡ أَيۡدِيهِمۡۚ وَٱللَّهُ عَلِيمُۢ بِٱلظَّـٰلِمِينَ ﴿7﴾

Transliteration: Wala yatamannawnahu abadan bima qaddamat aydeehim waAllahu AAaleemun bialththalimeena

Translation: 7. እጆቻቸው ባስቀደሙት ኃጢአት ምክንያት በፍጹም አይመኙትም:: አላህ በዳዮችን አዋቂ ነው::

62:8

قُلۡ إِنَّ ٱلۡمَوۡتَ ٱلَّذِي تَفِرُّونَ مِنۡهُ فَإِنَّهُۥ مُلَٰقِيكُمۡۖ ثُمَّ تُرَدُّونَ إِلَىٰ عَٰلِمِ ٱلۡغَيۡبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ ﴿8﴾

Transliteration: Qul inna almawta allathee tafirroona minhu fainnahu mulaqeekum thumma turaddoona ila AAalimi alghaybi waalshshahadati fayunabbiokum bima kuntum taAAmaloona

Translation: 8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያ ከእርሱ የምትሸሹት ሞት እርሱ በእርግጥ አግኛችሁ ነው:: ከዚያም ሩቁንና ቅርቡን አዋቂ ወደ ሆነው ጌታ በቂያማ ዕለት ተመላሾች ናችሁ:: ትሰሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል» በላቸው::

62:9

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِذَا نُودِيَ لِلصَّلَوٰةِ مِن يَوۡمِ ٱلۡجُمُعَةِ فَٱسۡعَوۡاْ إِلَىٰ ذِكۡرِ ٱللَّهِ وَذَرُواْ ٱلۡبَيۡعَۚ ذَٰلِكُمۡ خَيۡرٞ لَّكُمۡ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ ﴿9﴾

Transliteration: Ya ayyuha allatheena amanoo itha noodiya lilssalati min yawmi aljumuAAati faisAAaw ila thikri Allahi watharoo albayAAa thalikum khayrun lakum in kuntum taAAlamoona

Translation: 9. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአርብ (በጁሙዓ) ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት (ኹጥባ፣ ሶላት) ተጣደፉ:: መሸጥንም ተው:: የምታውቁ ብትሆኑ ይህ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነው::

62:10

فَإِذَا قُضِيَتِ ٱلصَّلَوٰةُ فَٱنتَشِرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَٱبۡتَغُواْ مِن فَضۡلِ ٱللَّهِ وَٱذۡكُرُواْ ٱللَّهَ كَثِيرٗا لَّعَلَّكُمۡ تُفۡلِحُونَ ﴿10﴾

Transliteration: Faitha qudiyati alssalatu faintashiroo fee alardi waibtaghoo min fadli Allahi waothkuroo Allaha katheeran laAAallakum tuflihoona

Translation: 10. ሶላቷ በተፈጸመችም ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑና የአላህን ችሮታ ፈልጉ:: ልትድኑ ይከጀላልና አላህንም በብዙው አውሱ::

62:11

وَإِذَا رَأَوۡاْ تِجَٰرَةً أَوۡ لَهۡوًا ٱنفَضُّوٓاْ إِلَيۡهَا وَتَرَكُوكَ قَآئِمٗاۚ قُلۡ مَا عِندَ ٱللَّهِ خَيۡرٞ مِّنَ ٱللَّهۡوِ وَمِنَ ٱلتِّجَٰرَةِۚ وَٱللَّهُ خَيۡرُ ٱلرَّـٰزِقِينَ ﴿11﴾

Transliteration: Waitha raaw tijaratan aw lahwan infaddoo ilayha watarakooka qaiman qul ma AAinda Allahi khayrun mina allahwi wamina alttijarati waAllahu khayru alrraziqeena

Translation: 11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ንግድን ወይም ዛዛታን ባዩ ጊዜም ቆመህ የተውህ ሲሆኑ ወደ እርሷ ይበተናሉ:: «አላህ ዘንድ ያለው ከዛዛታም ከንግድም በላጭ ነው:: አላህም ከሰጭዎች ሁሉ ይበልጥ ሲሳይን ሰጪ ነው» በላቸው::

Transliteration source: English Transliteration by Tanzil. Used under Tanzil's non-commercial terms; see the source and latest updates at Tanzil. Tanzil translation download