quranm◉

Surah Al-Anbya transliteration

◉ ሱራ · ∞

21:1

ٱقۡتَرَبَ لِلنَّاسِ حِسَابُهُمۡ وَهُمۡ فِي غَفۡلَةٖ مُّعۡرِضُونَ ﴿1﴾

Transliteration: Iqtaraba lilnnasi hisabuhum wahum fee ghaflatin muAAridoona

Translation: 1. ለሰዎች እነርሱ በዝንጋታ ውስጥ መሰናዳትን የተዉ ሆነው ሳሉ ምርመራቸው ቀረበ::

21:2

مَا يَأۡتِيهِم مِّن ذِكۡرٖ مِّن رَّبِّهِم مُّحۡدَثٍ إِلَّا ٱسۡتَمَعُوهُ وَهُمۡ يَلۡعَبُونَ ﴿2﴾

Transliteration: Ma yateehim min thikrin min rabbihim muhdathin illa istamaAAoohu wahum yalAAaboona

Translation: 2. ከጌታቸው አዲስ የተወረደ ቁርኣን አይመጣላቸዉም:: እነርሱ የሚያላግጡበት ሆነው ፤ የሚያዳምጡት ቢሆኑ እንጂ::

21:3

لَاهِيَةٗ قُلُوبُهُمۡۗ وَأَسَرُّواْ ٱلنَّجۡوَى ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ هَلۡ هَٰذَآ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُكُمۡۖ أَفَتَأۡتُونَ ٱلسِّحۡرَ وَأَنتُمۡ تُبۡصِرُونَ ﴿3﴾

Transliteration: Lahiyatan quloobuhum waasarroo alnnajwa allatheena thalamoo hal hatha illa basharun mithlukum afatatoona alssihra waantum tubsiroona

Translation: 3.ልቦቻቸው ዝንጉዎች ሆነው። እነዚያም የበደሉት ሰዎች መንሾካሾክን ደበቁ:: «ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጂ ሌላ ነውን? እናንተም የምታዩ ስትሆኑ ድግምትን ለመቀበል ትመጣላችሁን?» አሉ።

21:4

قَالَ رَبِّي يَعۡلَمُ ٱلۡقَوۡلَ فِي ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ ﴿4﴾

Transliteration: Qala rabbee yaAAlamu alqawla fee alssamai waalardi wahuwa alssameeAAu alAAaleemu

Translation: 4. (ሙሐመድም) «ጌታዬ ቃልን ሁሉ በሰማይና በምድር ውስጥ ያለ ሲሆን ያውቃል:: እርሱም ሰሚና አዋቂ ነው።» አለ።

21:5

بَلۡ قَالُوٓاْ أَضۡغَٰثُ أَحۡلَٰمِۭ بَلِ ٱفۡتَرَىٰهُ بَلۡ هُوَ شَاعِرٞ فَلۡيَأۡتِنَا بِـَٔايَةٖ كَمَآ أُرۡسِلَ ٱلۡأَوَّلُونَ ﴿5﴾

Transliteration: Bal qaloo adghathu ahlamin bali iftarahu bal huwa shaAAirun falyatina biayatin kama orsila alawwaloona

Translation: 5. በእውነቱ «ቁርኣኑ የሕልሞች ቅዠቶች ነው። ይልቁንም ቀጠፈው፤ እንዲያዉም እርሱ ቅኔን ገጣሚ ነው:: የቀድሞዎቹም እንደ ተላኩ ሁሉ መልዕክተኛ ከሆነ በተዓምር ይምጣብን።» አሉ።

21:6

مَآ ءَامَنَتۡ قَبۡلَهُم مِّن قَرۡيَةٍ أَهۡلَكۡنَٰهَآۖ أَفَهُمۡ يُؤۡمِنُونَ ﴿6﴾

Transliteration: Ma amanat qablahum min qaryatin ahlaknaha afahum yuminoona

Translation: 6. ከእነርሱ በፊት ያጠፋናት ከተማ አላመነችም:: ታዲያ እነርሱ ያምናሉን?

21:7

وَمَآ أَرۡسَلۡنَا قَبۡلَكَ إِلَّا رِجَالٗا نُّوحِيٓ إِلَيۡهِمۡۖ فَسۡـَٔلُوٓاْ أَهۡلَ ٱلذِّكۡرِ إِن كُنتُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ ﴿7﴾

Transliteration: Wama arsalna qablaka illa rijalan noohee ilayhim faisaloo ahla alththikri in kuntum la taAAlamoona

Translation: 7.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከአንተም በፊት ወደእነሱ የምናወርድላቸው የኾነን ሰዎችን እንጂ ሌላን አላክንም፡፡ የማታውቁ ከሆናችሁ የመጽሐፉን ባለቤቶች ጠይቁ::

21:8

وَمَا جَعَلۡنَٰهُمۡ جَسَدٗا لَّا يَأۡكُلُونَ ٱلطَّعَامَ وَمَا كَانُواْ خَٰلِدِينَ ﴿8﴾

Transliteration: Wama jaAAalnahum jasadan la yakuloona alttaAAama wama kanoo khalideena

Translation: 8.ምግብን የማይበላ አካልም አላደረግናቸዉም:: ዘውታሪዎችም አልነበሩም::

21:9

ثُمَّ صَدَقۡنَٰهُمُ ٱلۡوَعۡدَ فَأَنجَيۡنَٰهُمۡ وَمَن نَّشَآءُ وَأَهۡلَكۡنَا ٱلۡمُسۡرِفِينَ ﴿9﴾

Transliteration: Thumma sadaqnahumu alwaAAda faanjaynahum waman nashao waahlakna almusrifeena

Translation: 9.ከዚያ ቀጠሮን ሞላንላቸውና እነርሱንና የምንሻውን ሰው አዳንናቸዉም:: ወሰን አላፊዎችንም አጠፋን::

21:10

لَقَدۡ أَنزَلۡنَآ إِلَيۡكُمۡ كِتَٰبٗا فِيهِ ذِكۡرُكُمۡۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ ﴿10﴾

Transliteration: Laqad anzalna ilaykum kitaban feehi thikrukum afala taAAqiloona

Translation: 10. (ሙስሊሞች ሆይ!) ክብራችሁ በውስጡ ያለበትን መጽሐፍ ወደእናንተ በእርግጥ አወረድን፡፡ አታውቁምን?

21:11

وَكَمۡ قَصَمۡنَا مِن قَرۡيَةٖ كَانَتۡ ظَالِمَةٗ وَأَنشَأۡنَا بَعۡدَهَا قَوۡمًا ءَاخَرِينَ ﴿11﴾

Transliteration: Wakam qasamna min qaryatin kanat thalimatan waanshana baAAdaha qawman akhareena

Translation: 11. በዳይም ከነበረች ከተማ ያጠፋናትና ከኋላዋም ሌሎችን ህዝቦች ያስገኘነው ብዙ ናት::

21:12

فَلَمَّآ أَحَسُّواْ بَأۡسَنَآ إِذَا هُم مِّنۡهَا يَرۡكُضُونَ ﴿12﴾

Transliteration: Falamma ahassoo basana itha hum minha yarkudoona

Translation: 12. ቅጣታችንም በተሰማቸው ጊዜ እነርሱ ወዲያውኑ ከርሷ ለመሸሽ ይገሰግሳሉ።

21:13

لَا تَرۡكُضُواْ وَٱرۡجِعُوٓاْ إِلَىٰ مَآ أُتۡرِفۡتُمۡ فِيهِ وَمَسَٰكِنِكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تُسۡـَٔلُونَ ﴿13﴾

Transliteration: La tarkudoo wairjiAAoo ila ma otriftum feehi wamasakinikum laAAallakum tusaloona

Translation: 13. «አትገስግሱ፤ ትጠየቁም ይሆናልና በእርሱ ወደ ተቀማጠላችሁበት ጸጋ ወደ መኖሪያዎቻችሁም ተመለሱ።» ይባላሉ።

21:14

قَالُواْ يَٰوَيۡلَنَآ إِنَّا كُنَّا ظَٰلِمِينَ ﴿14﴾

Transliteration: Qaloo ya waylana inna kunna thalimeena

Translation: 14. «ዋ ጥፋታችን! እኛ በእርግጥ በዳዮች ነበርን።» ይላሉ።

21:15

فَمَا زَالَت تِّلۡكَ دَعۡوَىٰهُمۡ حَتَّىٰ جَعَلۡنَٰهُمۡ حَصِيدًا خَٰمِدِينَ ﴿15﴾

Transliteration: Fama zalat tilka daAAwahum hatta jaAAalnahum haseedan khamideena

Translation: 15.የታጨዱ ሬሳዎችም እስካደረግናቸው ድረስ ይህቺ ጥሪያቸው ከመሆን አልተወገደችም::

21:16

وَمَا خَلَقۡنَا ٱلسَّمَآءَ وَٱلۡأَرۡضَ وَمَا بَيۡنَهُمَا لَٰعِبِينَ ﴿16﴾

Transliteration: Wama khalaqna alssamaa waalarda wama baynahuma laAAibeena

Translation: 16. ሰማይንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ሆነን አልፈጠርንም::

21:17

لَوۡ أَرَدۡنَآ أَن نَّتَّخِذَ لَهۡوٗا لَّٱتَّخَذۡنَٰهُ مِن لَّدُنَّآ إِن كُنَّا فَٰعِلِينَ ﴿17﴾

Transliteration: Law aradna an nattakhitha lahwan laittakhathnahu min ladunna in kunna faAAileena

Translation: 17.መጫዎቻን (ሚስትንና ልጅን) ልንይዝ በሻን ኖሮ ከኛ ዘንድ በያዝነው ነበር፤ ግን ሰሪዎች አይደለንም።

21:18

بَلۡ نَقۡذِفُ بِٱلۡحَقِّ عَلَى ٱلۡبَٰطِلِ فَيَدۡمَغُهُۥ فَإِذَا هُوَ زَاهِقٞۚ وَلَكُمُ ٱلۡوَيۡلُ مِمَّا تَصِفُونَ ﴿18﴾

Transliteration: Bal naqthifu bialhaqqi AAala albatili fayadmaghuhu faitha huwa zahiqun walakumu alwaylu mimma tasifoona

Translation: 18. በእርግጥ እውነትን በውሸት ላይ እንጥላለን:: አንጎሉን ያፈርሰዋልም:: ወዲያዉም እርሱ ጠፊ ነው:: ለእናንተም ከዚያ (ሚስትና ልጅ) አለው በማለት ከምትመጥኑት ነገር ብርቱ ቅጣት አላችሁ:: (ወዮላችሁ)።

21:19

وَلَهُۥ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَمَنۡ عِندَهُۥ لَا يَسۡتَكۡبِرُونَ عَنۡ عِبَادَتِهِۦ وَلَا يَسۡتَحۡسِرُونَ ﴿19﴾

Transliteration: Walahu man fee alssamawati waalardi waman AAindahu la yastakbiroona AAan AAibadatihi wala yastahsiroona

Translation: 19. በሰማያትና በምድር ዉስጥ ያለው ሁሉም የእርሱ ብቻ ነው:: እርሱ ዘንድ ያሉትም መላእክት እርሱን ከመገዛት አይኮሩም:: አይሰለቹምም።

21:20

يُسَبِّحُونَ ٱلَّيۡلَ وَٱلنَّهَارَ لَا يَفۡتُرُونَ ﴿20﴾

Transliteration: Yusabbihoona allayla waalnnahara la yafturoona

Translation: 20. በበሌሊትና በቀንም ያጠሩታል:: አይታክቱም።

21:21

أَمِ ٱتَّخَذُوٓاْ ءَالِهَةٗ مِّنَ ٱلۡأَرۡضِ هُمۡ يُنشِرُونَ ﴿21﴾

Transliteration: Ami ittakhathoo alihatan mina alardi hum yunshiroona

Translation: 21. ይልቁንም ከምድር የሆኑን ሙታንን የሚያስነሱ አማልክትን ያዙን? የለም።

21:22

لَوۡ كَانَ فِيهِمَآ ءَالِهَةٌ إِلَّا ٱللَّهُ لَفَسَدَتَاۚ فَسُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ رَبِّ ٱلۡعَرۡشِ عَمَّا يَصِفُونَ ﴿22﴾

Transliteration: Law kana feehima alihatun illa Allahu lafasadata fasubhana Allahi rabbi alAAarshi AAamma yasifoona

Translation: 22.በሰማያትና በምድር ውስጥ ከአላህ ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ ሁለቱም በተበላሹ ነበር:: የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ::

21:23

لَا يُسۡـَٔلُ عَمَّا يَفۡعَلُ وَهُمۡ يُسۡـَٔلُونَ ﴿23﴾

Transliteration: La yusalu AAamma yafAAalu wahum yusaloona

Translation: 23. አላህ ከሚሰራው ሁሉ አይጠየቅም:: እነርሱ (ፍጥረቶቹ) ግን ይጠየቃሉ::

21:24

أَمِ ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِهِۦٓ ءَالِهَةٗۖ قُلۡ هَاتُواْ بُرۡهَٰنَكُمۡۖ هَٰذَا ذِكۡرُ مَن مَّعِيَ وَذِكۡرُ مَن قَبۡلِيۚ بَلۡ أَكۡثَرُهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ ٱلۡحَقَّۖ فَهُم مُّعۡرِضُونَ ﴿24﴾

Transliteration: Ami ittakhathoo min doonihi alihatan qul hatoo burhanakum hatha thikru man maAAiya wathikru man qablee bal aktharuhum la yaAAlamoona alhaqqa fahum muAAridoona

Translation: 24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁንም ከርሱ ሌላ አማልክትን ያዙን? «አስረጃችሁን አምጡ:: ይህ ቁርኣን እኔ ዘንድ ያለው ህዝብ መገሰጫ፤ ከኔ በፊትም የነበሩት ህዝቦች መገሠጫ ነው።» በላቸው:: እንዲያዉም አብዛኞቻቸው እውነቱን አያውቁም:: ስለዚህ እነርሱ እንቢተኞች ናቸው::

21:25

وَمَآ أَرۡسَلۡنَا مِن قَبۡلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِيٓ إِلَيۡهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعۡبُدُونِ ﴿25﴾

Transliteration: Wama arsalna min qablika min rasoolin illa noohee ilayhi annahu la ilaha illa ana faoAAbudooni

Translation: 25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢሆን እንጂ ከመልዕክተኛ አንድንም አላክንም::

21:26

وَقَالُواْ ٱتَّخَذَ ٱلرَّحۡمَٰنُ وَلَدٗاۗ سُبۡحَٰنَهُۥۚ بَلۡ عِبَادٞ مُّكۡرَمُونَ ﴿26﴾

Transliteration: Waqaloo ittakhatha alrrahmanu waladan subhanahu bal AAibadun mukramoona

Translation: 26. «አር-ረሕማንም ከመላእክት መካከል ልጅን ያዘ።» አሉ። ጥራት ተገባው። አይደለም መላእክት የተከበሩ ባሮች ብቻ ናቸው።

21:27

لَا يَسۡبِقُونَهُۥ بِٱلۡقَوۡلِ وَهُم بِأَمۡرِهِۦ يَعۡمَلُونَ ﴿27﴾

Transliteration: La yasbiqoonahu bialqawli wahum biamrihi yaAAmaloona

Translation: 27. በንግግር አይቀድሙትም፤ ያዘዘውንም ይፈጽማሉ።

21:28

يَعۡلَمُ مَا بَيۡنَ أَيۡدِيهِمۡ وَمَا خَلۡفَهُمۡ وَلَا يَشۡفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ٱرۡتَضَىٰ وَهُم مِّنۡ خَشۡيَتِهِۦ مُشۡفِقُونَ ﴿28﴾

Transliteration: YaAAlamu ma bayna aydeehim wama khalfahum wala yashfaAAoona illa limani irtada wahum min khashyatihi mushfiqoona

Translation: 28.በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል:: ለወደደውም እንጂ ለሌላው አያማልዱም:: እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው::

21:29

وَمَن يَقُلۡ مِنۡهُمۡ إِنِّيٓ إِلَٰهٞ مِّن دُونِهِۦ فَذَٰلِكَ نَجۡزِيهِ جَهَنَّمَۚ كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلظَّـٰلِمِينَ ﴿29﴾

Transliteration: Waman yaqul minhum innee ilahun min doonihi fathalika najzeehi jahannama kathalika najzee alththalimeena

Translation: 29. ከእነርሱም «እኔ ከእርሱ ሌላ አምላክ ነኝ።» የሚል ያንን ገሀነምን እንመነዳዋለን፤ በዳዮችን እንደዚሁ እንመነዳለን።

21:30

أَوَلَمۡ يَرَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ أَنَّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ كَانَتَا رَتۡقٗا فَفَتَقۡنَٰهُمَاۖ وَجَعَلۡنَا مِنَ ٱلۡمَآءِ كُلَّ شَيۡءٍ حَيٍّۚ أَفَلَا يُؤۡمِنُونَ ﴿30﴾

Transliteration: Awalam yara allatheena kafaroo anna alssamawati waalarda kanata ratqan fafataqnahuma wajaAAalna mina almai kulla shayin hayyin afala yuminoona

Translation: 30. እነዚያም በአላህ የካዱ ሰዎች ሰማያትና ምድር የተጣበቁ የነበሩና የለያየናቸው መሆናችንን አያውቁምን? ህያው የሆነንም ነገር ሁሉ ከውሃ ፈጠርን። አያምኑምን?

21:31

وَجَعَلۡنَا فِي ٱلۡأَرۡضِ رَوَٰسِيَ أَن تَمِيدَ بِهِمۡ وَجَعَلۡنَا فِيهَا فِجَاجٗا سُبُلٗا لَّعَلَّهُمۡ يَهۡتَدُونَ ﴿31﴾

Transliteration: WajaAAalna fee alardi rawasiya an tameeda bihim wajaAAalna feeha fijajan subulan laAAallahum yahtadoona

Translation: 31. በምድርም ውስጥ በእነርሱ እንዳታረገርግ ጋራዎችን አደረግን። ይመሩም ዘንድ በእርሷ ውስጥ ሰፋፊ መንገዶችን አደረግን።

21:32

وَجَعَلۡنَا ٱلسَّمَآءَ سَقۡفٗا مَّحۡفُوظٗاۖ وَهُمۡ عَنۡ ءَايَٰتِهَا مُعۡرِضُونَ ﴿32﴾

Transliteration: WajaAAalna alssamaa saqfan mahfoothan wahum AAan ayatiha muAAridoona

Translation: 32. ሰማይንም ከመውደቅ የተጠበቀ ጣራ አደረግን:: እነርሱ ግን ከተዓምራቱ ዘንጊዎች ናቸው::

21:33

وَهُوَ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلَّيۡلَ وَٱلنَّهَارَ وَٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَۖ كُلّٞ فِي فَلَكٖ يَسۡبَحُونَ ﴿33﴾

Transliteration: Wahuwa allathee khalaqa allayla waalnnahara waalshshamsa waalqamara kullun fee falakin yasbahoona

Translation: 33.እርሱም ሌሊትንና ቀንን ጸሐይንና ጨረቃንም የፈጠረ ነው:: ሁሉም በየ ምህዋራቸው (ፈለካቸው) ውስጥ ይዋኛሉ::

21:34

وَمَا جَعَلۡنَا لِبَشَرٖ مِّن قَبۡلِكَ ٱلۡخُلۡدَۖ أَفَإِيْن مِّتَّ فَهُمُ ٱلۡخَٰلِدُونَ ﴿34﴾

Transliteration: Wama jaAAalna libasharin min qablika alkhulda afain mitta fahumu alkhalidoona

Translation: 34. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ለማንም ሰው ዘለዓለም መኖርን አላደረግንም:: ታዲያ ብትሞት እነርሱ ዘውታሪዎች ናቸውን?

21:35

كُلُّ نَفۡسٖ ذَآئِقَةُ ٱلۡمَوۡتِۗ وَنَبۡلُوكُم بِٱلشَّرِّ وَٱلۡخَيۡرِ فِتۡنَةٗۖ وَإِلَيۡنَا تُرۡجَعُونَ ﴿35﴾

Transliteration: Kullu nafsin thaiqatu almawti wanablookum bialshsharri waalkhayri fitnatan wailayna turjaAAoona

Translation: 35.(ሰዎች ሆይ!) ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት:: ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንሞክራችኋለን:: ወደ እኛም ትመለሳላችሁ::

21:36

وَإِذَا رَءَاكَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِن يَتَّخِذُونَكَ إِلَّا هُزُوًا أَهَٰذَا ٱلَّذِي يَذۡكُرُ ءَالِهَتَكُمۡ وَهُم بِذِكۡرِ ٱلرَّحۡمَٰنِ هُمۡ كَٰفِرُونَ ﴿36﴾

Transliteration: Waitha raaka allatheena kafaroo in yattakhithoonaka illa huzuwan ahatha allathee yathkuru alihatakum wahum bithikri alrrahmani hum kafiroona

Translation: 36. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በአላህ የካዱት ሰዎች ባዩህ ጊዜ መሳለቂያ አድርገው እንጂ አይዙህም። እነርሱ በአር-ረህማን መወሳት እነርሱ ከሓዲያን ሲሆኑ: «ያ አማልክቶቻችሁን በክፉ የሚያነሳቸው ይህ ነውን?» ይላሉ።

21:37

خُلِقَ ٱلۡإِنسَٰنُ مِنۡ عَجَلٖۚ سَأُوْرِيكُمۡ ءَايَٰتِي فَلَا تَسۡتَعۡجِلُونِ ﴿37﴾

Transliteration: Khuliqa alinsanu min AAajalin saoreekum ayatee fala tastaAAjiloona

Translation: 37. ሰው ቸኳይ ሆኖ ተፈጠረ:: ታዓምራቶቼን በእርግጥ አሳያችኋለሁና አታቻኩሉኝ::

21:38

وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلۡوَعۡدُ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ ﴿38﴾

Transliteration: Wayaqooloona mata hatha alwaAAdu in kuntum sadiqeena

Translation: 38. «እውነተኞች ከሆናቸሁ ይህ ቀጠሮም መቼ ነው?» ይላሉ።

21:39

لَوۡ يَعۡلَمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ حِينَ لَا يَكُفُّونَ عَن وُجُوهِهِمُ ٱلنَّارَ وَلَا عَن ظُهُورِهِمۡ وَلَا هُمۡ يُنصَرُونَ ﴿39﴾

Transliteration: Law yaAAlamu allatheena kafaroo heena la yakuffoona AAan wujoohihimu alnnara wala AAan thuhoorihim wala hum yunsaroona

Translation: 39.እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች ከፊቶቻቸውና ከጀርቦቻቸው ላይ እሳትን የማይከለክሉበትን እነርሱም የማይረዳዱበትን ጊዜ ቢያውቁ ኖሮ ይህንን አይሉም ነበር::

21:40

بَلۡ تَأۡتِيهِم بَغۡتَةٗ فَتَبۡهَتُهُمۡ فَلَا يَسۡتَطِيعُونَ رَدَّهَا وَلَا هُمۡ يُنظَرُونَ ﴿40﴾

Transliteration: Bal tateehim baghtatan fatabhatuhum fala yastateeAAoona raddaha wala hum yuntharoona

Translation: 40. ይልቁንም ሰዓቲቱ በድንገት ትመጣቸዋለች:: ታስደነግጣቸዋለችም:: መመለሷንም አይችሉም:: እነርሱም የሚቆይላቸው አይደሉም።

21:41

وَلَقَدِ ٱسۡتُهۡزِئَ بِرُسُلٖ مِّن قَبۡلِكَ فَحَاقَ بِٱلَّذِينَ سَخِرُواْ مِنۡهُم مَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ ﴿41﴾

Transliteration: Walaqadi istuhzia birusulin min qablika fahaqa biallatheena sakhiroo minhum ma kanoo bihi yastahzioona

Translation: 41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊትም የነበሩት መልዕክተኞች በእርግጥ ተቀለደባቸው፤ በእነዚያ ከእነርሱ ይቀልዱ በነበሩት ይሳለቁበት የነበሩት ቅጣት ሰፈረባቸው።

21:42

قُلۡ مَن يَكۡلَؤُكُم بِٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِ مِنَ ٱلرَّحۡمَٰنِۚ بَلۡ هُمۡ عَن ذِكۡرِ رَبِّهِم مُّعۡرِضُونَ ﴿42﴾

Transliteration: Qul man yaklaokum biallayli waalnnahari mina alrrahmani bal hum AAan thikri rabbihim muAAridoona

Translation: 42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከአር-ረህማን ቅጣት በሌሊትና በቀን የሚጠብቃችሁ ማነው?» በላቸው:: በእውነቱ እነርሱ ከጌታቸው ግሠጼ ከቁርኣን ዘንጊዎች ናቸው::

21:43

أَمۡ لَهُمۡ ءَالِهَةٞ تَمۡنَعُهُم مِّن دُونِنَاۚ لَا يَسۡتَطِيعُونَ نَصۡرَ أَنفُسِهِمۡ وَلَا هُم مِّنَّا يُصۡحَبُونَ ﴿43﴾

Transliteration: Am lahum alihatun tamnaAAuhum min doonina la yastateeAAoona nasra anfusihim wala hum minna yushaboona

Translation: 43.ለእነርሱ ከእኛ ሌላ የምትከላከልላቸው አማልዕክት አለቻቸውን? ነፍሶቻቸውን መርዳትን አይችሉም:: እነርሱም (ከሓዲያኑ) ከእኛ አይጠብቁም።

21:44

بَلۡ مَتَّعۡنَا هَـٰٓؤُلَآءِ وَءَابَآءَهُمۡ حَتَّىٰ طَالَ عَلَيۡهِمُ ٱلۡعُمُرُۗ أَفَلَا يَرَوۡنَ أَنَّا نَأۡتِي ٱلۡأَرۡضَ نَنقُصُهَا مِنۡ أَطۡرَافِهَآۚ أَفَهُمُ ٱلۡغَٰلِبُونَ ﴿44﴾

Transliteration: Bal mattaAAna haolai waabaahum hatta tala AAalayhimu alAAumuru afala yarawna anna natee alarda nanqusuha min atrafiha afahumu alghaliboona

Translation: 44.በእውነትም እነዚህንና አባቶቻቸውን በእነርሱ ላይ ዕድሜ እስከ ረዘመባቸው ድረስ አጣቀምናቸው:: ተታለሉም። እኛ ምድርን ከጫፎቿ የምናጎድላት ሆነን ስንመጣባት አያዩምን? እነርሱ አሸናፊዎች ናቸውን?

21:45

قُلۡ إِنَّمَآ أُنذِرُكُم بِٱلۡوَحۡيِۚ وَلَا يَسۡمَعُ ٱلصُّمُّ ٱلدُّعَآءَ إِذَا مَا يُنذَرُونَ ﴿45﴾

Transliteration: Qul innama onthirukum bialwahyi wala yasmaAAu alssummu aldduAAaa itha ma yuntharoona

Translation: 45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የማስፈራራችሁ በተወረድልኝ ብቻ ነው። ግን ደንቆሮዎች በሚስፈራሩበት ጊዜ ጥሪን አይሰሙም።» በላቸው።

21:46

وَلَئِن مَّسَّتۡهُمۡ نَفۡحَةٞ مِّنۡ عَذَابِ رَبِّكَ لَيَقُولُنَّ يَٰوَيۡلَنَآ إِنَّا كُنَّا ظَٰلِمِينَ ﴿46﴾

Transliteration: Walain massathum nafhatun min AAathabi rabbika layaqoolunna ya waylana inna kunna thalimeena

Translation: 46. ከጌታህ ቅጣትም ወላፈን ብትነካቸው «ዋ ጥፋታችን! እኛ በዳዮች ነበርን።» ይላሉ።

21:47

وَنَضَعُ ٱلۡمَوَٰزِينَ ٱلۡقِسۡطَ لِيَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ فَلَا تُظۡلَمُ نَفۡسٞ شَيۡـٔٗاۖ وَإِن كَانَ مِثۡقَالَ حَبَّةٖ مِّنۡ خَرۡدَلٍ أَتَيۡنَا بِهَاۗ وَكَفَىٰ بِنَا حَٰسِبِينَ ﴿47﴾

Transliteration: WanadaAAu almawazeena alqista liyawmi alqiyamati fala tuthlamu nafsun shayan wain kana mithqala habbatin min khardalin atayna biha wakafa bina hasibeena

Translation: 47.በትንሳኤ ቀን ትክክለኛ ሚዛኖችን እናቆማለን:: ማንኛይቱም ነፍስ ምንንም አትበደልም:: ስራው የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ቢሆንም እርሷን እናመጣታለን:: ተቆጣጣሪነትም በእኛ በቃ::

21:48

وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ ٱلۡفُرۡقَانَ وَضِيَآءٗ وَذِكۡرٗا لِّلۡمُتَّقِينَ ﴿48﴾

Transliteration: Walaqad atayna moosa waharoona alfurqana wadiyaan wathikran lilmuttaqeena

Translation: 48. ለሙሳና ለሃሩንም እውነትንና ውሸትን የሚለይን ብርሃንን ለጥንቁቆችም መገሰጫን በእርግጥ ሰጠናቸው::

21:49

ٱلَّذِينَ يَخۡشَوۡنَ رَبَّهُم بِٱلۡغَيۡبِ وَهُم مِّنَ ٱلسَّاعَةِ مُشۡفِقُونَ ﴿49﴾

Transliteration: Allatheena yakhshawna rabbahum bialghaybi wahum mina alssaAAati mushfiqoona

Translation: 49. ለእነዚያ ጌታቸውን በሩቅ ለሚፈሩት እነርሱም ከሰዓቲቱ ተጨናቂዎች ለሆኑት መገሰጫን ሰጠን::

21:50

وَهَٰذَا ذِكۡرٞ مُّبَارَكٌ أَنزَلۡنَٰهُۚ أَفَأَنتُمۡ لَهُۥ مُنكِرُونَ ﴿50﴾

Transliteration: Wahatha thikrun mubarakun anzalnahu afaantum lahu munkiroona

Translation: 50.ይህም (ቁርኣን) ያወረድነው የኾነ ብሩክ መገሰጫ ነው፡ ታዲያ እናንተ ለእርሱ ከሓዲያን ናችሁን?

21:51

وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَآ إِبۡرَٰهِيمَ رُشۡدَهُۥ مِن قَبۡلُ وَكُنَّا بِهِۦ عَٰلِمِينَ ﴿51﴾

Transliteration: Walaqad atayna ibraheema rushdahu min qablu wakunna bihi AAalimeena

Translation: 51. ለኢብራሂምም ከዚያ በፊት ቅን መንገዱን በእርግጥ ሰጠነው:: እኛም በእርሱ ተገቢነት አዋቂዎች ነበርን::

21:52

إِذۡ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوۡمِهِۦ مَا هَٰذِهِ ٱلتَّمَاثِيلُ ٱلَّتِيٓ أَنتُمۡ لَهَا عَٰكِفُونَ ﴿52﴾

Transliteration: Ith qala liabeehi waqawmihi ma hathihi alttamatheelu allatee antum laha AAakifoona

Translation: 52. ለአባቱና ለህዝቦቹ፡- «ይህቺ ቅርጻ ቅርጽ ያቺ እናንተ ለእርሷ ተገዢዎች የሆናችኃት ምንድን ናት?» ባለ ጊዜ መራነው።

21:53

قَالُواْ وَجَدۡنَآ ءَابَآءَنَا لَهَا عَٰبِدِينَ ﴿53﴾

Transliteration: Qaloo wajadna abaana laha AAabideena

Translation: 53. «አባቶቻችንን ለእርሷ ተገዢዎች ሆነው አገኘን።» አሉት።

21:54

قَالَ لَقَدۡ كُنتُمۡ أَنتُمۡ وَءَابَآؤُكُمۡ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ ﴿54﴾

Transliteration: Qala laqad kuntum antum waabaokum fee dalalin mubeenin

Translation: 54. «እናንተም አባቶቻችሁም በእርግጥ በግልጽ ስህተት ውስጥ ነበራችሁ።» አላቸው።

21:55

قَالُوٓاْ أَجِئۡتَنَا بِٱلۡحَقِّ أَمۡ أَنتَ مِنَ ٱللَّـٰعِبِينَ ﴿55﴾

Transliteration: Qaloo ajitana bialhaqqi am anta mina allaAAibeena

Translation: 55. «በምሩ መጣህልን? ወይንስ አንተ ከሚቀልዱት ነህ?» አሉት።

21:56

قَالَ بَل رَّبُّكُمۡ رَبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ ٱلَّذِي فَطَرَهُنَّ وَأَنَا۠ عَلَىٰ ذَٰلِكُم مِّنَ ٱلشَّـٰهِدِينَ ﴿56﴾

Transliteration: Qala bal rabbukum rabbu alssamawati waalardi allathee fatarahunna waana AAala thalikum mina alshshahideena

Translation: 56. (እርሱም) አለ: «አይደለም። ጌታችሁ የሰማያትና የምድር ጌታ ያ የፈጠራቸው ነው:: እኔም በይሃችሁ ላይ ከመስካሪዎች ነኝ።

21:57

وَتَٱللَّهِ لَأَكِيدَنَّ أَصۡنَٰمَكُم بَعۡدَ أَن تُوَلُّواْ مُدۡبِرِينَ ﴿57﴾

Transliteration: WataAllahi laakeedanna asnamakum baAAda an tuwalloo mudbireena

Translation: 57. «በአላህ እምላለሁ ዟሪዎች ሆናችሁ ከሄዳችሁ በኋላ ጣዖቶቻችሁን ተንኮል እሰራባቸዋለሁ።» አለ።

21:58

فَجَعَلَهُمۡ جُذَٰذًا إِلَّا كَبِيرٗا لَّهُمۡ لَعَلَّهُمۡ إِلَيۡهِ يَرۡجِعُونَ ﴿58﴾

Transliteration: FajaAAalahum juthathan illa kabeeran lahum laAAallahum ilayhi yarjiAAoona

Translation: 58. ዘወር ሲሉም ስብርብሮች አደረጋቸው:: ለእነርሱ የሆነ አንድ ትልቅ ጣዖት ብቻ ሲቀር :: ወደ እርሱ ይመለሱ ዘንድ እርሱን ብቻ ተወው።

21:59

قَالُواْ مَن فَعَلَ هَٰذَا بِـَٔالِهَتِنَآ إِنَّهُۥ لَمِنَ ٱلظَّـٰلِمِينَ ﴿59﴾

Transliteration: Qaloo man faAAala hatha bialihatina innahu lamina alththalimeena

Translation: 59. «በአማልክቶቻችን ይህንን የሰራ ማነው? እርሱ በእርግጥ ከበደለኞች ነው።» አሉ።

21:60

قَالُواْ سَمِعۡنَا فَتٗى يَذۡكُرُهُمۡ يُقَالُ لَهُۥٓ إِبۡرَٰهِيمُ ﴿60﴾

Transliteration: Qaloo samiAAna fatan yathkuruhum yuqalu lahu ibraheemu

Translation: 60. «ኢብራሂም የሚባል ጎበዝ (ወጣት) በመጥፎ ሲያነሳቸው ሰምተናል።» ተባባሉ።

21:61

قَالُواْ فَأۡتُواْ بِهِۦ عَلَىٰٓ أَعۡيُنِ ٱلنَّاسِ لَعَلَّهُمۡ يَشۡهَدُونَ ﴿61﴾

Transliteration: Qaloo fatoo bihi AAala aAAyuni alnnasi laAAallahum yashhadoona

Translation: 61. «ይመሰክሩበት ዘንድ በሰዎች ዓይን ፊት ላይ አምጡት።» አሉ።

21:62

قَالُوٓاْ ءَأَنتَ فَعَلۡتَ هَٰذَا بِـَٔالِهَتِنَا يَـٰٓإِبۡرَٰهِيمُ ﴿62﴾

Transliteration: Qaloo aanta faAAalta hatha bialihatina ya ibraheemu

Translation: 62. «ኢብራሂም ሆይ! በአማልክቶቻችን ይህንን የሰራህ አንተ ነህን?» አሉት።

21:63

قَالَ بَلۡ فَعَلَهُۥ كَبِيرُهُمۡ هَٰذَا فَسۡـَٔلُوهُمۡ إِن كَانُواْ يَنطِقُونَ ﴿63﴾

Transliteration: Qala bal faAAalahu kabeeruhum hatha faisaloohum in kanoo yantiqoona

Translation: 63. «አይደለም:: ይህ ትልቃቸው ሰራው፤ ይናገሩም እንደ ሆነ ጠይቋቸው።» አለ።

21:64

فَرَجَعُوٓاْ إِلَىٰٓ أَنفُسِهِمۡ فَقَالُوٓاْ إِنَّكُمۡ أَنتُمُ ٱلظَّـٰلِمُونَ ﴿64﴾

Transliteration: FarajaAAoo ila anfusihim faqaloo innakum antumu alththalimoona

Translation: 64. ወደ ነፍሶቻቸዉም ተመለሱ: «እናንተ በመጠየቃችሁ በዳዮቹ እናንተው ናችሁ።» ተባባሉም።

21:65

ثُمَّ نُكِسُواْ عَلَىٰ رُءُوسِهِمۡ لَقَدۡ عَلِمۡتَ مَا هَـٰٓؤُلَآءِ يَنطِقُونَ ﴿65﴾

Transliteration: Thumma nukisoo AAala ruoosihim laqad AAalimta ma haolai yantiqoona

Translation: 65. ከዚያም በራሶቻቸው ላይ ተገለበጡና «እነዚህ የሚናገሩ አለመሆናቸውን በእርግጥ አውቀሃል።» አሉ።

21:66

قَالَ أَفَتَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَنفَعُكُمۡ شَيۡـٔٗا وَلَا يَضُرُّكُمۡ ﴿66﴾

Transliteration: Qala afataAAbudoona min dooni Allahi ma la yanfaAAukum shayan wala yadurrukum

Translation: 66.ኢብራሂምም አላቸው: «ታዲያ ለእናንተ ብታመልኳቸው ምንም የማይጠቅማችሁንና ባታመልኳቸዉም በምንም ነገር የማይጎዳችሁን ጣዖታትን ከአላህ ሌላ ትገዛላችሁን?

21:67

أُفّٖ لَّكُمۡ وَلِمَا تَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ ﴿67﴾

Transliteration: Offin lakum walima taAAbudoona min dooni Allahi afala taAAqiloona

Translation: 67. «ኡፍ! ለእናንተም ሆነ ከአላህ ሌላ ለምትገዙት ጣዖታት። አታስተውሉምን?» አለ።

21:68

قَالُواْ حَرِّقُوهُ وَٱنصُرُوٓاْ ءَالِهَتَكُمۡ إِن كُنتُمۡ فَٰعِلِينَ ﴿68﴾

Transliteration: Qaloo harriqoohu waonsuroo alihatakum in kuntum faAAileena

Translation: 68. «ሰሪዎች (ተቆርቋሪዎች) እንደ ሆናችሁ ኢብራሂምን በእሳት አቃጥሉት አማልክቶቻችሁንም እርዱ።» አሉ:: (በእሳት ላይ ጣሉትም።)

21:69

قُلۡنَا يَٰنَارُ كُونِي بَرۡدٗا وَسَلَٰمًا عَلَىٰٓ إِبۡرَٰهِيمَ ﴿69﴾

Transliteration: Qulna ya naru koonee bardan wasalaman AAala ibraheema

Translation: 69. «እሳት ሆይ! በኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛና ሰላም ሁኚ።» አልን።

21:70

وَأَرَادُواْ بِهِۦ كَيۡدٗا فَجَعَلۡنَٰهُمُ ٱلۡأَخۡسَرِينَ ﴿70﴾

Transliteration: Waaradoo bihi kaydan fajaAAalnahumu alakhsareena

Translation: 70. በእርሱም ተንኮልን አሰቡ። በጣም ከሳሪዎች አደረግናቸው።

21:71

وَنَجَّيۡنَٰهُ وَلُوطًا إِلَى ٱلۡأَرۡضِ ٱلَّتِي بَٰرَكۡنَا فِيهَا لِلۡعَٰلَمِينَ ﴿71﴾

Transliteration: Wanajjaynahu walootan ila alardi allatee barakna feeha lilAAalameena

Translation: 71. እርሱንና ሉጥንም ወደዚያች በውስጡ ለዓለማት በረከትን ወደ አደረግንባት ምድር በመውሰድ አዳንናቸው::

21:72

وَوَهَبۡنَا لَهُۥٓ إِسۡحَٰقَ وَيَعۡقُوبَ نَافِلَةٗۖ وَكُلّٗا جَعَلۡنَا صَٰلِحِينَ ﴿72﴾

Transliteration: Wawahabna lahu ishaqa wayaAAqooba nafilatan wakullan jaAAalna saliheena

Translation: 72.ለእርሱም ኢስሐቅን ያዕቆብንም ተጨማሪ አድርገን ሰጠነው:: ሁሉንም መልካሞች አደረግን::

21:73

وَجَعَلۡنَٰهُمۡ أَئِمَّةٗ يَهۡدُونَ بِأَمۡرِنَا وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡهِمۡ فِعۡلَ ٱلۡخَيۡرَٰتِ وَإِقَامَ ٱلصَّلَوٰةِ وَإِيتَآءَ ٱلزَّكَوٰةِۖ وَكَانُواْ لَنَا عَٰبِدِينَ ﴿73﴾

Transliteration: WajaAAalnahum aimmatan yahdoona biamrina waawhayna ilayhim fiAAla alkhayrati waiqama alssalati waeetaa alzzakati wakanoo lana AAabideena

Translation: 73. በትእዛዛችንም ወደ በጎ ስራ የሚመሩ መሪዎች አደረግናቸው:: ወደነሱም መልካም ስራዎችን መስራትን፤ ሶላትንም መስገድን ዘካንም መስጠትን አወረድን:: ለእኛም ተገዢዎች ነበሩ::

21:74

وَلُوطًا ءَاتَيۡنَٰهُ حُكۡمٗا وَعِلۡمٗا وَنَجَّيۡنَٰهُ مِنَ ٱلۡقَرۡيَةِ ٱلَّتِي كَانَت تَّعۡمَلُ ٱلۡخَبَـٰٓئِثَۚ إِنَّهُمۡ كَانُواْ قَوۡمَ سَوۡءٖ فَٰسِقِينَ ﴿74﴾

Transliteration: Walootan ataynahu hukman waAAilman wanajjaynahu mina alqaryati allatee kanat taAAmalu alkhabaitha innahum kanoo qawma sawin fasiqeena

Translation: 74. ሉጥንም ፍርድንና ዕውቀትን ሰጠነው:: ከዚያችም መጥፎ ስራዎችን ትሰራ ከነበረችው ከተማ አዳንነው:: እነርሱ ክፉ ሰዎች አመጸኞች ነበሩና::

21:75

وَأَدۡخَلۡنَٰهُ فِي رَحۡمَتِنَآۖ إِنَّهُۥ مِنَ ٱلصَّـٰلِحِينَ ﴿75﴾

Transliteration: Waadkhalnahu fee rahmatina innahu mina alssaliheena

Translation: 75. በችሮታችንም ውስጥ አስገባነው:: እርሱ ከመልካሞች አንዱ ነውና::

21:76

وَنُوحًا إِذۡ نَادَىٰ مِن قَبۡلُ فَٱسۡتَجَبۡنَا لَهُۥ فَنَجَّيۡنَٰهُ وَأَهۡلَهُۥ مِنَ ٱلۡكَرۡبِ ٱلۡعَظِيمِ ﴿76﴾

Transliteration: Wanoohan ith nada min qablu faistajabna lahu fanajjaynahu waahlahu mina alkarbi alAAatheemi

Translation: 76.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኑሕንም ከዚያ በፊት ጌታውን በጠራ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፤ እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳን::

21:77

وَنَصَرۡنَٰهُ مِنَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَآۚ إِنَّهُمۡ كَانُواْ قَوۡمَ سَوۡءٖ فَأَغۡرَقۡنَٰهُمۡ أَجۡمَعِينَ ﴿77﴾

Transliteration: Wanasarnahu mina alqawmi allatheena kaththaboo biayatina innahum kanoo qawma sawin faaghraqnahum ajmaAAeena

Translation: 77.ከእነዚያም በታዓምራቶቻችን ከአስተባበሉት ህዝቦች ተንኮል ጠበቅነው:: እነርሱ ክፉ ህዝቦች አመጸኞች ነበሩና ሁሉንም አሰመጥናቸዉም::

21:78

وَدَاوُۥدَ وَسُلَيۡمَٰنَ إِذۡ يَحۡكُمَانِ فِي ٱلۡحَرۡثِ إِذۡ نَفَشَتۡ فِيهِ غَنَمُ ٱلۡقَوۡمِ وَكُنَّا لِحُكۡمِهِمۡ شَٰهِدِينَ ﴿78﴾

Transliteration: Wadawooda wasulaymana ith yahkumani fee alharthi ith nafashat feehi ghanamu alqawmi wakunna lihukmihim shahideena

Translation: 78.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ ! ) ዳውድንና ሱለይማንንም በአዝመራው ነገር በሚፈርዱ ጊዜ የህዝቦቸ ፍየሎች ሌሊት በእርሱ ውስጥ በተሰማሩ ጊዜ አስታውስ:: ፍርዳቸውንም አዋቂዎች ነበርን::

21:79

فَفَهَّمۡنَٰهَا سُلَيۡمَٰنَۚ وَكُلًّا ءَاتَيۡنَا حُكۡمٗا وَعِلۡمٗاۚ وَسَخَّرۡنَا مَعَ دَاوُۥدَ ٱلۡجِبَالَ يُسَبِّحۡنَ وَٱلطَّيۡرَۚ وَكُنَّا فَٰعِلِينَ ﴿79﴾

Transliteration: Fafahhamnaha sulaymana wakullan atayna hukman waAAilman wasakhkharna maAAa dawooda aljibala yusabbihna waalttayra wakunna faAAileena

Translation: 79. ለሱለይማንም ትክክለኛይቱን ፍርድ አሳወቅነው:: ለሁሉም ጥበብንና እውቀትን ሰጠን:: ተራራዎችን ከዳውድ ጋር የሚያወድሱ ሲሆን ገራን፤ አእዋፍንም እንደዚሁ ገራን ሰሪዎችም ነበርን።

21:80

وَعَلَّمۡنَٰهُ صَنۡعَةَ لَبُوسٖ لَّكُمۡ لِتُحۡصِنَكُم مِّنۢ بَأۡسِكُمۡۖ فَهَلۡ أَنتُمۡ شَٰكِرُونَ ﴿80﴾

Transliteration: WaAAallamnahu sanAAata laboosin lakum lituhsinakum min basikum fahal antum shakiroona

Translation: 80.የብረት ልብስንም ስራ ለእናንተ ከጦራችሁ ትጠብቃችሁ ዘንድ አስተማርነው:: እናንተ አመስጋኞች ናችሁን?

21:81

وَلِسُلَيۡمَٰنَ ٱلرِّيحَ عَاصِفَةٗ تَجۡرِي بِأَمۡرِهِۦٓ إِلَى ٱلۡأَرۡضِ ٱلَّتِي بَٰرَكۡنَا فِيهَاۚ وَكُنَّا بِكُلِّ شَيۡءٍ عَٰلِمِينَ ﴿81﴾

Transliteration: Walisulaymana alrreeha AAasifatan tajree biamrihi ila alardi allatee barakna feeha wakunna bikulli shayin AAalimeena

Translation: 81. ለሱለይማንም ነፋስን በኃይል የምትነፍስ በትእዛዙ ወደዚያች በእርሷ ውስጥ በረከትን ወደ አደረግንባት ምድር (ወደ ሻም) የምትነፍስ ስትሆን (ገራንለት) በነገሩ ሁሉም አዋቂዎች ነበርን::

21:82

وَمِنَ ٱلشَّيَٰطِينِ مَن يَغُوصُونَ لَهُۥ وَيَعۡمَلُونَ عَمَلٗا دُونَ ذَٰلِكَۖ وَكُنَّا لَهُمۡ حَٰفِظِينَ ﴿82﴾

Transliteration: Wamina alshshayateeni man yaghoosoona lahu wayaAAmaloona AAamalan doona thalika wakunna lahum hafitheena

Translation: 82.ከሰይጣናትም ለእርሱ (ሉልን ለማውጣት) የሚጠልሙንና ከዚያ ሌላ ያለን ስራ የሚሰሩን ገራንለት፤ ለእነርሱም ተጠባባቂዎች ነበርን::

21:83

وَأَيُّوبَ إِذۡ نَادَىٰ رَبَّهُۥٓ أَنِّي مَسَّنِيَ ٱلضُّرُّ وَأَنتَ أَرۡحَمُ ٱلرَّـٰحِمِينَ ﴿83﴾

Transliteration: Waayyooba ith nada rabbahu annee massaniya alddurru waanta arhamu alrrahimeena

Translation: 83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አዩብንም ጌታውን «እኔ መከራ አገኘኝ:: አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ።» ሲል በተጣራ ጊዜ የሆነውን አስታውስ።

21:84

فَٱسۡتَجَبۡنَا لَهُۥ فَكَشَفۡنَا مَا بِهِۦ مِن ضُرّٖۖ وَءَاتَيۡنَٰهُ أَهۡلَهُۥ وَمِثۡلَهُم مَّعَهُمۡ رَحۡمَةٗ مِّنۡ عِندِنَا وَذِكۡرَىٰ لِلۡعَٰبِدِينَ ﴿84﴾

Transliteration: Faistajabna lahu fakashafna ma bihi min durrin waataynahu ahlahu wamithlahum maAAahum rahmatan min AAindina wathikra lilAAabideena

Translation: 84. ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፤ ከጉዳትም በእርሱ ላይ የነበረውን ሁሉ አስወገድን:: ቤተሰቦቹንም ከእነርሱም ጋር መሰላቸውን ከእኛ ዘንድ ለችሮታና ለተገዢዎች ለማስገንዘብ ሰጠነው::

21:85

وَإِسۡمَٰعِيلَ وَإِدۡرِيسَ وَذَا ٱلۡكِفۡلِۖ كُلّٞ مِّنَ ٱلصَّـٰبِرِينَ ﴿85﴾

Transliteration: WaismaAAeela waidreesa watha alkifli kullun mina alssabireena

Translation: 85. ኢስማዒልንም፤ ኢድሪስንም፤ ዙልኪፍልንም፤ አስታውስ:: ሁሉም ከታጋሾች ናቸው::

21:86

وَأَدۡخَلۡنَٰهُمۡ فِي رَحۡمَتِنَآۖ إِنَّهُم مِّنَ ٱلصَّـٰلِحِينَ ﴿86﴾

Transliteration: Waadkhalnahum fee rahmatina innahum mina alssaliheena

Translation: 86. በችሮታችንም ውስጥ አስገባናቸው:: እነርሱ ከመልካሞቹ ናቸውና::

21:87

وَذَا ٱلنُّونِ إِذ ذَّهَبَ مُغَٰضِبٗا فَظَنَّ أَن لَّن نَّقۡدِرَ عَلَيۡهِ فَنَادَىٰ فِي ٱلظُّلُمَٰتِ أَن لَّآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنتَ سُبۡحَٰنَكَ إِنِّي كُنتُ مِنَ ٱلظَّـٰلِمِينَ ﴿87﴾

Transliteration: Watha alnnooni ith thahaba mughadiban fathanna an lan naqdira AAalayhi fanada fee alththulumati an la ilaha illa anta subhanaka innee kuntu mina alththalimeena

Translation: 87. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዓሳውንም ባለቤት ተቆጥቶ በሄደ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: በእርሱም ላይ ፈጽሞ የማንፈርድበት መሆናችንን ጠረጠረ:: ዓሳም ዋጠው:: በጨለማዎችም ውስጥ ሆኖ «ካንተ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም ጥራት ይገባህ:: እኔ በእርግጥ ከበዳዮች ነበርኩ።» በማለት ተጣራ።

21:88

فَٱسۡتَجَبۡنَا لَهُۥ وَنَجَّيۡنَٰهُ مِنَ ٱلۡغَمِّۚ وَكَذَٰلِكَ نُـۨجِي ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ﴿88﴾

Transliteration: Faistajabna lahu wanajjaynahu mina alghammi wakathalika nunjee almumineena

Translation: 88. ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው:: ከጭንቅም አዳነው:: ልክ እንደዚሁም ምዕምናንን እናድናለን::

21:89

وَزَكَرِيَّآ إِذۡ نَادَىٰ رَبَّهُۥ رَبِّ لَا تَذَرۡنِي فَرۡدٗا وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلۡوَٰرِثِينَ ﴿89﴾

Transliteration: Wazakariyya ith nada rabbahu rabbi la tatharnee fardan waanta khayru alwaritheena

Translation: 89. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ዘከሪያንም «ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ:: አንተም ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህ።» ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ አስታውስ።

21:90

فَٱسۡتَجَبۡنَا لَهُۥ وَوَهَبۡنَا لَهُۥ يَحۡيَىٰ وَأَصۡلَحۡنَا لَهُۥ زَوۡجَهُۥٓۚ إِنَّهُمۡ كَانُواْ يُسَٰرِعُونَ فِي ٱلۡخَيۡرَٰتِ وَيَدۡعُونَنَا رَغَبٗا وَرَهَبٗاۖ وَكَانُواْ لَنَا خَٰشِعِينَ ﴿90﴾

Transliteration: Faistajabna lahu wawahabna lahu yahya waaslahna lahu zawjahu innahum kanoo yusariAAoona fee alkhayrati wayadAAoonana raghaban warahaban wakanoo lana khashiAAeena

Translation: 90. ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው:: ለእርሱም የህያን ሰጠነው:: ለእርሱም ሚስቱን አበጀንለት:: እነርሱ በበጎ ስራዎች የሚቻኮሉ ከጃዮችና ፈሪዎች ሆነው የሚለምኑንም ነበሩ:: ለእኛ ተዋራጆችም ነበሩ::

21:91

وَٱلَّتِيٓ أَحۡصَنَتۡ فَرۡجَهَا فَنَفَخۡنَا فِيهَا مِن رُّوحِنَا وَجَعَلۡنَٰهَا وَٱبۡنَهَآ ءَايَةٗ لِّلۡعَٰلَمِينَ ﴿91﴾

Transliteration: Waallatee ahsanat farjaha fanafakhna feeha min roohina wajaAAalnaha waibnaha ayatan lilAAalameena

Translation: 91.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያችንም ብልቷን (ከዝሙት) የጠበቀችውንና በእርሷም ውስጥ ከመንፈሳችን የነፋንባትን እርሷንም ሆነ ልጇን ለዓለማት ተዓምር ያደረግናትን መርየምን አስታውስ::

21:92

إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمۡ أُمَّةٗ وَٰحِدَةٗ وَأَنَا۠ رَبُّكُمۡ فَٱعۡبُدُونِ ﴿92﴾

Transliteration: Inna hathihi ommatukum ommatan wahidatan waana rabbukum faoAAbudooni

Translation: 92. እነዚህ ህግጋት አንድ መንገድ ሲሆኑ በእርግጥ የሃይማኖታችሁ ህግጋት ናቸው:: እኔም ጌታችሁ ነኝና ተገዙኝ::

21:93

وَتَقَطَّعُوٓاْ أَمۡرَهُم بَيۡنَهُمۡۖ كُلٌّ إِلَيۡنَا رَٰجِعُونَ ﴿93﴾

Transliteration: WataqattaAAoo amrahum baynahum kullun ilayna rajiAAoona

Translation: 93.በሃይማኖታቸዉም ነገር በመካከላቸው ተለያዩ:: ሁሉም ወደ እኛ ተመላሾች ናቸው::

21:94

فَمَن يَعۡمَلۡ مِنَ ٱلصَّـٰلِحَٰتِ وَهُوَ مُؤۡمِنٞ فَلَا كُفۡرَانَ لِسَعۡيِهِۦ وَإِنَّا لَهُۥ كَٰتِبُونَ ﴿94﴾

Transliteration: Faman yaAAmal mina alssalihati wahuwa muminun fala kufrana lisaAAyihi wainna lahu katiboona

Translation: 94. እርሱ ያመነ ሆኖ ከበጎ ስራዎች ማንኛውንም የሚሰራም ምንዳውን አይነፍግም፤ እኛም ለእርሱ መዝጋቢዎች ነን::

21:95

وَحَرَٰمٌ عَلَىٰ قَرۡيَةٍ أَهۡلَكۡنَٰهَآ أَنَّهُمۡ لَا يَرۡجِعُونَ ﴿95﴾

Transliteration: Waharamun AAala qaryatin ahlaknaha annahum la yarjiAAoona

Translation: 95. ባጠፋናትም ከተማ ላይ ዘበት ነው፤ (ወደ ዱኒያ) አይመለሱምና።

21:96

حَتَّىٰٓ إِذَا فُتِحَتۡ يَأۡجُوجُ وَمَأۡجُوجُ وَهُم مِّن كُلِّ حَدَبٖ يَنسِلُونَ ﴿96﴾

Transliteration: Hatta itha futihat yajooju wamajooju wahum min kulli hadabin yansiloona

Translation: 96.የዕጁጅና መዕጁጅም እነርሱ ከየሸንተረሩ የሚንደረደሩ ሲሆኑ ግድባቸው በተከፈተች ጊዜ ፤

21:97

وَٱقۡتَرَبَ ٱلۡوَعۡدُ ٱلۡحَقُّ فَإِذَا هِيَ شَٰخِصَةٌ أَبۡصَٰرُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ يَٰوَيۡلَنَا قَدۡ كُنَّا فِي غَفۡلَةٖ مِّنۡ هَٰذَا بَلۡ كُنَّا ظَٰلِمِينَ ﴿97﴾

Transliteration: Waiqtaraba alwaAAdu alhaqqu faitha hiya shakhisatun absaru allatheena kafaroo ya waylana qad kunna fee ghaflatin min hatha bal kunna thalimeena

Translation: 97. እውነተኛዉም ቀጠሮ በቀረበ ጊዜ ያንን ጊዜ እነሆ የእነዚያ ከሀዲያን ዓይኖች ይፈጥጣሉ:: «ዋ ጥፍታችን! ከዚያ ቀን በእርግጥ በዝንጋቴ ላይ ነበርን:: በእውነትም በዳዮች ነበርን።» ይላሉ።

21:98

إِنَّكُمۡ وَمَا تَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ حَصَبُ جَهَنَّمَ أَنتُمۡ لَهَا وَٰرِدُونَ ﴿98﴾

Transliteration: Innakum wama taAAbudoona min dooni Allahi hasabu jahannama antum laha waridoona

Translation: 98. (ከሓዲያን ሆይ!) እናንተና ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ጣዖታት የገሀነም ማገዶዎች ናችሁ:: እናንተ ለእርሷ ወራጆች ናችሁ::

21:99

لَوۡ كَانَ هَـٰٓؤُلَآءِ ءَالِهَةٗ مَّا وَرَدُوهَاۖ وَكُلّٞ فِيهَا خَٰلِدُونَ ﴿99﴾

Transliteration: Law kana haolai alihatan ma waradooha wakullun feeha khalidoona

Translation: 99.እነዚህ ጣዖታት አማልክት በነበሩ ኖሮ ገሀነምን አይገቧትም ነበር:: ግን ሁሉም በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::

21:100

لَهُمۡ فِيهَا زَفِيرٞ وَهُمۡ فِيهَا لَا يَسۡمَعُونَ ﴿100﴾

Transliteration: Lahum feeha zafeerun wahum feeha la yasmaAAoona

Translation: 100.እነርሱ በእርሷ ውስጥ ይንሰቀሰቃሉ:: እነርሱም በውስጧ ምንንም አይሰሙም::

21:101

إِنَّ ٱلَّذِينَ سَبَقَتۡ لَهُم مِّنَّا ٱلۡحُسۡنَىٰٓ أُوْلَـٰٓئِكَ عَنۡهَا مُبۡعَدُونَ ﴿101﴾

Transliteration: Inna allatheena sabaqat lahum minna alhusna olaika AAanha mubAAadoona

Translation: 101. እነዚያ ከእኛ መልካሟ ቃል ለእነርሱ ያለፈችላቸው እነዚያ ከእርሷ የተራቁ ናቸው::

21:102

لَا يَسۡمَعُونَ حَسِيسَهَاۖ وَهُمۡ فِي مَا ٱشۡتَهَتۡ أَنفُسُهُمۡ خَٰلِدُونَ ﴿102﴾

Transliteration: La yasmaAAoona haseesaha wahum fee ma ishtahat anfusuhum khalidoona

Translation: 102. ድምጿንም አይሰሙም:: እነርሱም ነፍሶቻቸው በሚሹት ነገር ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው::

21:103

لَا يَحۡزُنُهُمُ ٱلۡفَزَعُ ٱلۡأَكۡبَرُ وَتَتَلَقَّىٰهُمُ ٱلۡمَلَـٰٓئِكَةُ هَٰذَا يَوۡمُكُمُ ٱلَّذِي كُنتُمۡ تُوعَدُونَ ﴿103﴾

Transliteration: La yahzunuhumu alfazaAAu alakbaru watatalaqqahumu almalaikatu hatha yawmukumu allathee kuntum tooAAadoona

Translation: 103. ታላቁ ድንጋጤ አያስተክዛቸዉም:: መላእክትም «ይህ ያ ! ትቀጠሩት የነበራችሁት ቀናችሁ ነው።» እያሉ ይቀበሏቸዋል።

21:104

يَوۡمَ نَطۡوِي ٱلسَّمَآءَ كَطَيِّ ٱلسِّجِلِّ لِلۡكُتُبِۚ كَمَا بَدَأۡنَآ أَوَّلَ خَلۡقٖ نُّعِيدُهُۥۚ وَعۡدًا عَلَيۡنَآۚ إِنَّا كُنَّا فَٰعِلِينَ ﴿104﴾

Transliteration: Yawma natwee alssamaa katayyi alssijlli lilkutubi kama badana awwala khalqin nuAAeeduhu waAAdan AAalayna inna kunna faAAileena

Translation: 104. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለመጽሐፎች ገፆች እንደሚጠቀለሉ ሁሉ ሰማይን የምንጠቀልልበትን ቀን አስታውስ:: የመጀመሪያን ፍጥረት እንደ ጀመርን እንመልሰዋለን:: ይህን መፈጸሙ የማይቀር ቀጠሮን ቀጠርን:: እኛ የቀጠርነውን ሰሪዎች ነን::

21:105

وَلَقَدۡ كَتَبۡنَا فِي ٱلزَّبُورِ مِنۢ بَعۡدِ ٱلذِّكۡرِ أَنَّ ٱلۡأَرۡضَ يَرِثُهَا عِبَادِيَ ٱلصَّـٰلِحُونَ ﴿105﴾

Transliteration: Walaqad katabna fee alzzaboori min baAAdi alththikri anna alarda yarithuha AAibadiya alssalihoona

Translation: 105. ምድርንም መልካሞቹ ባሮቼ ይወርሷታል ማለትን ከመጽሐፉ (ከተጠበቀው ሰሌዳ) በኋላ በመጽሐፎች በእርግጥ ጽፈናል::

21:106

إِنَّ فِي هَٰذَا لَبَلَٰغٗا لِّقَوۡمٍ عَٰبِدِينَ ﴿106﴾

Transliteration: Inna fee hatha labalaghan liqawmin AAabideena

Translation: 106.በዚህ ቁርኣን ውስጥ ያሉት ህግጋት ለአላህ ተገዢ ህዝቦች ሁሉ በቂ ናቸው።

21:107

وَمَآ أَرۡسَلۡنَٰكَ إِلَّا رَحۡمَةٗ لِّلۡعَٰلَمِينَ ﴿107﴾

Transliteration: Wama arsalnaka illa rahmatan lilAAalameena

Translation: 107. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለዓለማት እዝነት አድርገን እንጂ አልላክንህም::

21:108

قُلۡ إِنَّمَا يُوحَىٰٓ إِلَيَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمۡ إِلَٰهٞ وَٰحِدٞۖ فَهَلۡ أَنتُم مُّسۡلِمُونَ ﴿108﴾

Transliteration: Qul innama yooha ilayya annama ilahukum ilahun wahidun fahal antum muslimoona

Translation: 108. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያ ወደ እኔ የሚወርደው መልዕክት ‹አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው።› የሚል ነው:: ታዲያ እናንተ ፍጹም ታዛዦች ናችሁን?» በላቸው።

21:109

فَإِن تَوَلَّوۡاْ فَقُلۡ ءَاذَنتُكُمۡ عَلَىٰ سَوَآءٖۖ وَإِنۡ أَدۡرِيٓ أَقَرِيبٌ أَم بَعِيدٞ مَّا تُوعَدُونَ ﴿109﴾

Transliteration: Fain tawallaw faqul athantukum AAala sawain wain adree aqareebun am baAAeedun ma tooAAadoona

Translation: 109. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እምቢ ቢሉም (እንዲህ) በላቸው: «የታዘዝኩትን በእኩልነት አሳውቂያችኋለሁ:: የምትስፈራሩበትም ነገር ቅርብ ወይም ሩቅ መሆኑን አላውቅም።

21:110

إِنَّهُۥ يَعۡلَمُ ٱلۡجَهۡرَ مِنَ ٱلۡقَوۡلِ وَيَعۡلَمُ مَا تَكۡتُمُونَ ﴿110﴾

Transliteration: Innahu yaAAlamu aljahra mina alqawli wayaAAlamu ma taktumoona

Translation: 110. «እርሱ ከንግግር ጩኸቱን ያውቃል:: የምትደብቁትንም ሁሉ ያውቃል::

21:111

وَإِنۡ أَدۡرِي لَعَلَّهُۥ فِتۡنَةٞ لَّكُمۡ وَمَتَٰعٌ إِلَىٰ حِينٖ ﴿111﴾

Transliteration: Wain adree laAAallahu fitnatun lakum wamataAAun ila heenin

Translation: 111. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እርሱም ቅጣትን ማቆየት ምናልባት ለእናንተ ፈተናና እስከ ጊዜው መጣቀሚያ እንደ ሆነም አላውቅም።» በላቸው::

21:112

قَٰلَ رَبِّ ٱحۡكُم بِٱلۡحَقِّۗ وَرَبُّنَا ٱلرَّحۡمَٰنُ ٱلۡمُسۡتَعَانُ عَلَىٰ مَا تَصِفُونَ ﴿112﴾

Transliteration: Qala rabbi ohkum bialhaqqi warabbuna alrrahmanu almustaAAanu AAala ma tasifoona

Translation: 112. «ጌታዬ ሆይ! በእውነት ፍረድ:: ጌታችንም እጅግ በጣም ሩህሩህን በምትሉት ነገር ላይ መታገዣ ነው።» አለ::

Transliteration source: English Transliteration by Tanzil. Used under Tanzil's non-commercial terms; see the source and latest updates at Tanzil. Tanzil translation download