quranm◉

ገጽ 528

Range
from 53:45 to 54:6
Surahs covered
ትርጉም
24 ትርጉም

◉

53:45

وَأَنَّهُۥ خَلَقَ ٱلزَّوۡجَيۡنِ ٱلذَّكَرَ وَٱلۡأُنثَىٰ ﴿45﴾

45. እርሱ ያ ጥንድን፤ ወንድንና ሴትን የፈጠረ ነው::

53:46

مِن نُّطۡفَةٍ إِذَا تُمۡنَىٰ ﴿46﴾

46. ይኸዉም ከፍትወት ጠብታ በማሕጸን ውስጥ በምትፈሰስ ጊዜ ነው::

53:47

وَأَنَّ عَلَيۡهِ ٱلنَّشۡأَةَ ٱلۡأُخۡرَىٰ ﴿47﴾

47. ሌላውን ማስገኘትም በእርሱ ላይ ነው::

53:48

وَأَنَّهُۥ هُوَ أَغۡنَىٰ وَأَقۡنَىٰ ﴿48﴾

48. እርሱ ያ ሀብትን የሰጠና ያብቃቃ ነው::

53:49

وَأَنَّهُۥ هُوَ رَبُّ ٱلشِّعۡرَىٰ ﴿49﴾

49. እርሱ የሺዕራ ጌታ ነው::

53:50

وَأَنَّهُۥٓ أَهۡلَكَ عَادًا ٱلۡأُولَىٰ ﴿50﴾

50. እርሱ የቀድሞ ሰዎችን የአድ ሕዝቦችንም አጠፋ።

53:51

وَثَمُودَاْ فَمَآ أَبۡقَىٰ ﴿51﴾

51. ሰሙድንም አጠፋ:: አንድንም አላስቀረም::

53:52

وَقَوۡمَ نُوحٖ مِّن قَبۡلُۖ إِنَّهُمۡ كَانُواْ هُمۡ أَظۡلَمَ وَأَطۡغَىٰ ﴿52﴾

52. በፊትም የኑህን ህዝቦች አጥፍቷል:: እነርሱ እጅግ በዳዮችና በጣም አመጸኞች ነበሩና ነው::

53:53

وَٱلۡمُؤۡتَفِكَةَ أَهۡوَىٰ ﴿53﴾

53.የተገለበጡትንም ደፋ።

53:54

فَغَشَّىٰهَا مَا غَشَّىٰ ﴿54﴾

54. ባሸፈናት ሸፈናት::

53:55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكَ تَتَمَارَىٰ ﴿55﴾

55. (የሰው ልጅ ሆይ)፤ ከጌታህ ጸጋዎች በየትኛው ነው የምትጠራጠረው::

53:56

هَٰذَا نَذِيرٞ مِّنَ ٱلنُّذُرِ ٱلۡأُولَىٰٓ ﴿56﴾

56. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ከቀድሞዎቹ አስጠንቃቂዎች አንዱ ነው::

53:57

أَزِفَتِ ٱلۡأٓزِفَةُ ﴿57﴾

57. ቀራቢቱም ቀረበች::

53:58

لَيۡسَ لَهَا مِن دُونِ ٱللَّهِ كَاشِفَةٌ ﴿58﴾

58. ከአላህ በስተቀር ገላጭ የላትም::

53:59

أَفَمِنۡ هَٰذَا ٱلۡحَدِيثِ تَعۡجَبُونَ ﴿59﴾

59. በዚህ ዘገባ ትደነቃላችሁን?

53:60

وَتَضۡحَكُونَ وَلَا تَبۡكُونَ ﴿60﴾

60 ትስቃላችሁን? አታለቅሱምን?

53:61

وَأَنتُمۡ سَٰمِدُونَ ﴿61﴾

61. እናንተ ዘወትር ዘንጊዎች ናችሁን?

53:62

فَٱسۡجُدُواْۤ لِلَّهِۤ وَٱعۡبُدُواْ۩ ﴿62﴾

62. ለአላህ ስገዱ በብቸኝነትም አምልኩትም::

54:1

ٱقۡتَرَبَتِ ٱلسَّاعَةُ وَٱنشَقَّ ٱلۡقَمَرُ ﴿1﴾

1. የትንሳኤ ቀን ተቃረበ:: ጨረቃም ተገመሰ::

54:2

وَإِن يَرَوۡاْ ءَايَةٗ يُعۡرِضُواْ وَيَقُولُواْ سِحۡرٞ مُّسۡتَمِرّٞ ﴿2﴾

2. ከሓዲያን ተዐምርን ቢያዩም እንቢ ብለው ይዞራሉ:: «ይህ ዘውታሪ ድግምት ነው» ይላሉ::

54:3

وَكَذَّبُواْ وَٱتَّبَعُوٓاْ أَهۡوَآءَهُمۡۚ وَكُلُّ أَمۡرٖ مُّسۡتَقِرّٞ ﴿3﴾

3.አስተባበሉም :: ዝንባሌዎቻቸውንም ተከተሉ:: ነገርም ሁሉ (ወሰን አለው) ረጊ ነው።

54:4

وَلَقَدۡ جَآءَهُم مِّنَ ٱلۡأَنۢبَآءِ مَا فِيهِ مُزۡدَجَرٌ ﴿4﴾

4. ከዜናዎቹ በእርሱ ውስጥ መገሰጫ የሚሆን ነገር ያለበት በእርግጥ መጣላቸው::

54:5

حِكۡمَةُۢ بَٰلِغَةٞۖ فَمَا تُغۡنِ ٱلنُّذُرُ ﴿5﴾

5. ሙሉ ከሆነ ጥበብ (መጣላቸው):: ግን አስፈራሪዎች (ለማያምኑት) አይፈይዱም።

54:6

فَتَوَلَّ عَنۡهُمۡۘ يَوۡمَ يَدۡعُ ٱلدَّاعِ إِلَىٰ شَيۡءٖ نُّكُرٍ ﴿6﴾

6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ተውና ዙር። (ይልቁንስ) ጠሪው መልዓክ ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን አስታውስ።